Sunday, July 21, 2013

ብርቱ ሰው! (The Iron Man) – (ከተመስገን ደሳለኝ)

ሁላችንም እንደምናውቀው በሀያኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻ ዓስርታት በተለያዩ ክፍለ አህጉራት ውስጥ ባሉ ታዳጊ ሀገር ህዝቦች የተነሱ የፖለቲካ እና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች በቀዳሚነት በጠመንጃ ኃይል የተደገፉ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያም በተመሳሳይ የታሪክ ክስተት ማለፏን የሚመሰክረው ዛሬም ወታደራዊ ስርዓቱን ብቻ ሳይሆን፣ ይህንን መንገድ የመረጡትን ጥቂት የተቃዋሚ ድርጅቶችንም በጦር ኃይል ድል አድርጎ ስልጣን ላይ ያለው ኢህአዴግ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና የቀዝቃዛው ዓለም ጦርነት ማብቃትና የአሜሪካ ብቸኛ ልዕለ ሀያል ሀገር ሆኖ መውጣት በኃይል የሚደረጉ ‹‹ፀረ-አምባገነን›› ንቅናቄዎች ሰላማዊውን መንገድ ብቻ እንዲከተሉ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡



የለውጡም ዋነኛ መግፍኤ አሜሪካ ለሰላማዊ ትግል የምትሰጠው ከፍ ያለ ቦታ ብቻ ሳይሆን የምታደርገው እገዛም መሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡ በእርግጥ የአሜሪካ አስተዳደር በሰላማዊ ትግል ላይ ያለው አቋምና ለትግሉ የሚያደርገው ቀጥተኛ አበረታችነት የሀገሪቱ መስራች አባቶች ካነፁት የሞራል እና የፖለቲካ እሴት እንደሚነሳም አውቃለሁ፡፡

ዝርዝሩን ጽሁፍ ሊንኩን በመጫን ያንብቡ: http://www.ethiomedia.com/2013report/bertu_saw.pdf

No comments:

Post a Comment