Monday, March 31, 2014

ኢህአዴግ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት?


አሜሪካ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ለመውጣት ወስናለች

ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ብቸኛ ተዋናይና ፊት አውራሪ አድርጎ ራሱን የሾመው ኢህአዴግ ለቀጠናው ስጋት እንደሚሆን ተጠቆመ። አልሸባብንና አልቃይዳን ከምንጩ እናጠፋለን በሚል ስትራቴጂ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ሰምጣ የነበረችው አሜሪካ ከጉድጓዱ ለመውጣት ወስናለች። ኢትዮጵያዊያን የሚያምኑትና የሚቀበሉትን መሪ በድፍረት አደባባይ የማውጣት ሃላፊነቱ “አገር ወዳድ” በሚሉ ዜጎችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጫንቃ ላይ ነው።

ህወሃት ያቋቋማቸው ጥቃቅን መንግስታት ከህዝብ ይልቅ ለህወሃት የወደፊት እቅድ ታማኝ በመሆን መጓዛቸው ከቀን ወደቅን የፈጠረው ስሜት ኢህአዴግን እየበላው እንደሆነ የጠቆሙ የዜናው ምንጮች፣ ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪቃ የሰላም አባት ሊሆን ቀርቶ የራሱንም ችግር መፍታት ወደማይችልበት የቁርሾ ማሳ ውስጥ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

ህወሃት “በነጻ አውጪነት” ያሰላውና፣ ይህንኑ ዓላማውን በፈለገበት ቀን ተግባራዊ ለማድረግ ያመቸው ዘንድ በየክልሉ ለጣጥፎ ያቋቋማቸውን ፓርቲዎች ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ በድንገት ካለፉ በኋላ ኢህአዴግ ውስጣዊ ሰላሙ መናጋቱ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። ኢህአዴግ በበኩሉ “የጓድ መለስን ውርስና ራዕይ ያለማዛነፍ እናስቀጥላለን” እያለ አገሪቱን በደቦ እንድተመራ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

Thursday, March 27, 2014

ወያኔ፡ የጨለማው ‘’መንግስት’’!!!

 በቅዱስ ዮሃንስ

ኢትዮጵያ ሀገራችን ረጅም የህላዌ ዘመንና የመንግሥትነት ታሪክ ካላቸው ጥቂት አገሮች አንዷ በመሆን ትታወቃለች፡፡ በሌላ ወገን መንግሥታት ወይንም ገዢዎች በህዝብ ላይ አሠቃቂ የጭቆናና የአፈና ሥርዓት በመዘርጋት ሕዝቡ ሁለንተናዊ ክብሩን ተገፎ የሚኖርባት አገር በመሆንም ትታወቃለች፡፡ ጭቆናውን እጅግ የከፋ የሚያደርገው ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነቱ፣ የሀገሩ እና የመብቱ ባለቤት ለመሆን ካደረገው ረጅምና እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ከእለት ወደ እለት እየከፋ በሚሄድ የጭቆና ሥርዓት ውስጥ እየማቀቀ መገኘቱ ነው፡፡ በተለይም በአለንበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን የነፃነትና የእኩልነት ጉዳይ የሁሉም ሰብአዊ መብቶች፣ ልማት ሁሉን አቀፍ እሴቶች ማዕከላዊ አጀንዳ በሆኑበት ሁኔታ ኢትዮጵያ ግን አሁን በአለም ላይ ከሚገኙ ለሰብአዊ ክብር፣ ለሀገር ሉዓላዊነትና እድገት ቁብ ከማይሰጡ ጥቂት አምባገነን መንግሥታት በአንደኛው በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት)መዳፍ ውስጥ ትገኛለች፡፡

የአለፉት 23 አመታት መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በአንድ በኩል በደርግ አምባገነናዊ መንግሥት ከደረሰበት ሠፊ አፈና እፎይ ለማለት ከፍተኛ ጉጉት ያደረበት፣ በሌላ ወገን ደግሞ የህወሓት ወያኔ የማያባራ የማማለያ ፕሮፓጋንዳ እውነት ይሆናል ብሎ በመገመት የነፃነት ንጋት በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሲበራ ለማየትና የአለፉትን ክፉ ዓመታት ለመርሳት በዝግጅት ላይ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ የሆነው ከዚህ ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡ ያለፉት ክፉ የጭቆና ዓመታት በሌላ የከፋ ጭቆናና ክፉ ዓመታት ተተኩ፡፡ ዘመነ ወያኔ ከታሪካዊ ክፋት ሁሉ የከፋ የክፉ-ክፉ ዘመን ነው። የነጻነት ብርሀን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የደበዘዘበት ዘመን ነው። የአገሪቱ ሉዓላዊነት ከመቼውም በበለጠ አደጋ ላይ የወደቀበት ዘመን ነው። ሕዝባችን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የድኅነት አርንቋ ውስጥ የተዘፈቀበት፣ ከሥቃዩ ማምለጫ ጠፍቶት የሚዋዥቅበት፣ አበሳውን ያየበት፣ ተስፋ የቆረጠበት ዘመን ነው። ሕዝባችን በደዌ የተመረዘበት፣ ሕይወት የረከሰበት ዘመን ነው። ዘመኑ፣ ዘመነ አበሳ ነው። የወያኔ ዘመን “ዘመነ ጨለማ” ነው። ይኸንን ሃቅ ሆዱ ልቦናውን ያልደፈነበት፣ ጥቅም የህሊና ዓይኑን ያላሳወረበት ኢትዮጵያዊ ሁሉ በግልጽ እያየ በቁጭት ቆሽቱ ይደብናል። ግን ከዚህ ሁሉ በደል ጋር ተስማምቶ እንዴት መኖር ይቻላል? ወይንስ ስለ እውነት በደል ይለመዳልን?

ፋሽስቱ ወያኔ አዲስ አባባን ከተቆጣጠራት ጊዜ ጀምሮ ድኅነት ድባቡን በአገሪቱ ዘርግቶባታል። ሕዝባችን ከምን ጊዜውም የበለጠ ተርቧል፣ ተጠማቷል፣ ታረዟል፣ ደኽይቷል! እርስብርስ አናቁረውት አነካክሰውታል፣ አበጣብጠውታል። ሰላሙን ነስተውታል። ሕዝባችንን ከፋፍለውት እያፋጁት ነው። የአምልኮ ቦታዎች ሳይቀሩ፣ በዘረኞች የወያኔ ካድሬዎች ቁጥጥር ሥር ውለዋል። አገራችን ላይ የፋሽስቱ ወያኔ ዘረኞች ነገሡ። ከሀዲዎች ፈነጩባት። ብሔራዊ ውርደትን አከናነቧት። ወያኔዎች የአገራችንን ለም የእርሻ መሬቶች ሸንሽነው፣ ባለርስቶቹን ከቄያቸው መንግለው ለባዕድ ቱጃሮች ቸብችበዋል። ሕዝቡን በወረዳና በቀበሌ ከፋፍለው ከመቆጣጠር አልፈው፣ በጎጥ ታች ድረስ ወርደው አንድ ለአምስት የሚባል የመቆጣጠሪያ ሕዋስ ፈጥረዋል። በዚህ ክትትል መሠረት፣ ማንም ዜጋ፣ ለምሳሌ ገብሬ፣ ከተወሰነለት ሁኔታ የማፈንገጥ ምልክት ካሳየ፣ ለዘር ብድር ከባንክ አያገኝም፣ ማዳበሪያ በብድር አይሸጥለትም፣ ከውጭ በልመና የመጣውን የዕርዳታ እህል እንኳን አያገኝም። እናት ኢትዮጵያ ለጠላቶቿ ተመቻችታ፣ ደረቷን ለሞት እንደትገልጥ ተገዳለች! ምነው ታዲያ ይኸ ሁሉ ግፍ ሲፈጸምበት ጀግናውና ቆራጡ ሕዝባችን ግፍን ለመከላከል ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲህ ወኔ ራቀው?

እብሪተኞቹ ወያኔዎች፣ የአገራችንን ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ ዘርፈው ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ እንዲሁ የሕዝባችንን ሕልውና ተቆጣጥረውታል። ኑሮውን፣ ውሎውን አዳሩን ሙሉ በሙሉ አንቀው ይዘውታል። ድምጽ እንዳያሰማ ጎሮሮውን አንቀውታል። እንዳይሰማ ጆሮውን ድፍነውበታል። በአገር ቤት፣ ነጻ ሬዲዮ የለም ቢባል ይሻላል! ነጻ ቴሌቪዢንማ ከቶ ማን አስቦት! ነጻ ጋዜጣን ድራሹን አጥፍተውታል! የተመጣጠን ዕውነተኛ መረጃ ከውጭ ለሕዝባችን እንዳይደርሰው ብዙ ሚሊዮን ዶላሮችን እያፈሰሰ ተግቶ የሚሰራው ፋሽስቱ ወያኔ፣ ኢሳት ቴሌቪዥንን፣ ሳተላየት እንዴት ማፈን እንደሚቻል የአፋኝ ቴክኖሎጂ መለማመጃ አድርጎታል። ዛሬ ሕዝባችን መጮህ ቀርቶ ከውጭ የምንጮለትን እንኳን እንዳይሰማ ምንም ዓይነት መረጃ እንዳይደርሰው ቀፍድደው ይዘውታል። እንዳይዘዋውር፣ እግሮችን ጠፍረው አስረውታል። በአገሩ እንደድሮው ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ አርሶ አምርቶ፣ ነግዶ አትርፎ እንዳይበላ ከልክለውታል። ግን ግን ከዚህ ሁሉ በደል ጋር ተስማምቶ እንዴትስ ይኖራ?

Wednesday, March 26, 2014

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር – 5 ቁልፍ አገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን ይዛ እነሆ በPDF ያንብቧት

Click here for PDF

- መዝሙረ ኢህአዴግ! (በላይ ማናዬ)

- የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት በተደረገላቸው ግብዣ ወደ አሜሪካ ያመራሉ፡፡ በጉዞው ዓላማና በተለያዩ የአገራችን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

-  ኢትዮጵያና የዩክሬኑ ግጥምጥሞሽ

- ባለ ቀለሙን አብዮት ማን ይመራዋል? (በጌታቸው ሺፈራው)

- አዲስ ጠብመንጃ በምንሽር፤
አገዳደሉ ሆድ የሚያሽር፡፡
(በዝክረ ታሪክ አምድ፡- አቶ ታዲዎስ ታንቱ)

- “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ዘመቻ” (ግርማ ሞገስ)

- ኑሮ ሆነብን እሮሮ (ጋሻው መርሻ)

- የኢትዮጵያ ፖለቲካና የሴቶች ተሳትፎ (ኤልሳቤት ወሰኔ)

- ሰላማዊ ትግሉ መሪዎቹን ይሻል (ታምራት ታረቀኝ)

- ኢትዮጵያዊነት ለእኔ! (አፈወርቅ በደዊ)

- እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራሞች የሚተዋወቁበት ገጽ አለልዎት

Click here for PDF

Tuesday, March 25, 2014

Telecom and Internet Surveillance in Ethiopia – Human Rights Watch report

The 137 page report details the technologies the Ethiopian government has acquired from several countries and uses to facilitate surveillance of perceived political opponents inside the country and among the diaspora. The government’s surveillance practices violate the rights to freedom of expression, association, and access to information. The government’s monopoly over all mobile and Internet services through its sole, state-owned telecom operator, Ethio Telecom, facilitates abuse of surveillance powers.

Summary

One day they arrested me and they showed me everything. They showed me a list of all my phone calls and they played a conversation I had with my brother. They arrested me because we talked about politics on the phone. Itwas the first phone I ever owned, and I thought I could finally talk freely.

— Former member of an Oromo opposition party, now a refugee in Kenya, May 2013

Sunday, March 23, 2014

ሃያ ሦስት የስቃይ፤ የሰቆቃና የእልቂትና ዓመታት

የኢትዮጵያ ህዝብ በፋሽስቱ ህወሓት ብልሹ አስተዳደርና አምባገነናዊ አገዛዝ ስር ወድቆ በኑሮ ውድነትና በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ፣ ሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቱ ተነጥቆ ለአፈናና ለእስራት እየተዳረገ፣ ሉዓላዊ ክብሩ ተደፍሮ ለም መሬቱንና አንጡራ ሃብቱን እየተሸነሸነና እየተቦረቦረ ለባዕድ እየተሸጠ፣ በገዛ ሀገሩ ተፈናቃይና የውጭ እጅ ተመልካች ሆኖ ለስደትና ለእንግልት እየተዳረገ እነሆ ዛሬ ከ23 ዓመት በላይ የሰቆቃ፣ የእልቂትና የመከራ ዓመታት ተቆጠሩ።

ለአለፉት 23 ዓመታት የደፈረሰው ፖለቲካችን ወደ ጭቃነት እየተቀየረ ስለመሆኑም ምንም ምስክር አያሻውም።ፋሽስቱ ወያኔ ከሀገር ሉዓላዊነት እስከ ታሪካችን፣ ከባንዲራችን እስከ እንደ ሕዝብና እንደ ሀገር ያለን ደረጃ መቀመቅ አውርዶታል። አንዳንዶቻችን እንደዚህ ዘመን ትውልድ አባልነታችን ያለፈውን መለወጥ፣ ዛሬን የሰውነት ደረጀችን በጠበቀ ሁኔታ መኖርና ነገንም ላልተወለዱ ልጆቻችን መልክ አስይዞ ለማውረስ ከቁጥጥራችን እየወጣ መሆኑን በግልጽ እንመለከታለን። በሌላ ወገን ወያኔዎቹ የአለፉት 23 ዓመታት የአንድ ጀምበር ያህል አጥረውባቸው፤ ተጨማሪ 40 አመታትን ለመግዛት በማለም ሲንፈራገጡና በቀቢጸ ተስፋ ህዝብን ለማማለል ሲሞክሩ እያየንና እየሰማን ነው። ስንራብ መጥገባችንን ይነግሩናል። ስንታረዝ ደራርበን መጎናፀፋችን ይታያቸዋል። ሀገራችን ከአለም ሀገሮች ተርታ በሁሉም መስኮች ለማለት በሚያስደፍር ደረጃ በማይታመን ፍጥነት እየወጣች ወደ ግርጌ ስትወረወር፤ ወንበዴዎቹ ወያኔወች ግን ሀገራችን ተሞሸረች አማራች ይሉናል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲረግጡት የሚደቅን ቅጠል ያህል በመቁጠር ከህግና ከአመክንዮ ውጭ በማን አለብኝነት ሕዝባችንን በንግድ ድርጅቶቻቸው እየገፈፉ እርቃኑን አስቀርተውታል።

Saturday, March 22, 2014

የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ዶክመንተሪ ሊዘጋጅ ነው ተባለ

ዶክመንተሪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት አካል እንደኾነ ተጠቁሟል ‹‹ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› ለሚለው የማኅበሩ ጥያቄ ምላሽ አልተሰጠም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሲኖዶሱን ይኹንታ አግኝቶ በመላው አገሪቱ የሚንቀሳቀሰውን የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ነው የተባለ ዶክመንተሪ ፊልም ለማዘጋጀት መታቀዱ ተጠቆመ፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አንዳንድ ሓላፊዎች አቀብለውታል በተባለ መረጃ እንደሚታገዝና በመንግሥት አካል እንደሚሰናዳ የተገለጸው የዶክመንተሪ ዝግጅቱ በማኅበሩ ኻያ አመራሮች እና አባላት ላይ እንዳነጣጠረ ተገልጧል፡፡ መንግሥት በምርጫ – 97 ውጤትና በተከታይ ኹኔታዎቹ ላይ ባካሔደው ግምገማ፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው የሚባሉ ግለሰቦች በተለይ በገጠር ቀበሌዎች ለተቃዋሚዎች ተሰሚነት ማግኘት በምክንያትነት መጥቀሱ በዜና ጥቆማው የተመለከተ ሲኾን ‹‹የአክራሪነትና የጽንፈኛ ፖሊቲከኞች ምሽግ ነው›› በሚል የሚያቀርበው ክሥም ከዚኹ የሚነሣና ለመጪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅትም አካል እንደኾነ ተነግሯል፡፡ በቅድመ ዝግጅቱ የሚወሰዱ ርምጃዎች የማኅበሩን አቅሞችና እንቅስቃሴዎች በመቆጣጠር በተለይም የማኅበሩ መሠረቶች ናቸው የሚባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያትን ‹‹በሴኩላሪዝም መርሖዎች የመግባቢያ ሰነድ›› ጠርንፎ ‹የአገልግሎት ቅኝቱን የማስተካከል› ዓላማ እንዳላቸው የገለጸው የዜና ምንጩ፣ ይህም ካልተሳካ በተከታታይ አስተዳደራዊ ርምጃዎችና የተቃውሞ ቅስቀሳዎች ማኅበሩን በማወከብ ተቋሙን ለዘለቄታው የማፍረስ ውጤት ሊኖረውም እንደሚችል አመልክቷል፡፡ ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አብያተ ክርስቲያናት የተጠሩ ናቸው የተባሉ አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች የሚሳተፉበት እንደኾነ የተገለጸና ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በማኅበሩ አገልግሎት ላይ ቁጥጥሩን እንዲያጠብቅ የሚጠይቅ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በቤተ ክህነቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሔድ የተዘገበ ሲኾን ዓላማውም ‹‹በአክራሪዎችና ጽንፈኛ ፖሊቲከኞች ምሽግነት፣ የቤተ ክህነቱን አሠራር ባለማክበርና ከቤተ ክህነቱ በላይ ገዝፎ በመውጣት›› ማኅበሩ የሚከሰስባቸውን ኹኔታዎች በማጠናከር ለታቀዱት ርምጃዎች የሚያመቻች ነው ተብሏል፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ በማተኮር የተማረው ትውልድ ሃይማኖቱን የሚወድ፣ ግብረ ገብነት ያለው፣ ሀገሩንና ቤተ ክርስቲያኑን በዕውቀቱ፣ በሞያውና በገንዘቡ የሚያገለግል ብቁ ዜጋ ይኾን ዘንድ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት በመሥራት ላይ እንዳለ የሚገልጹ የማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎቹ፣ ማኅበሩ ለቀረቡበት ክሦች የሚመች አደረጃጀት ይኹን ባሕርይ እንደሌለው በመግለጽ ተጠሪ ከኾነለት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋራ በአሠራር ሒደት የሚፈጠር ክፍተትን በማጦዝ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ የተጠቀሱት ክሦች ላቀረቡት አካላት ‹‹የሚነገረውና የሚጻፈው እኛን የሚገልጸን ስላልኾነ ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› የሚል ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ለሠለጠነ ውይይት ፍላጎት እንደሌላቸው አባላቱ አስረድተዋል፤ በምትኩ ‹‹ርምጃ እንወስዳለን›› በማለት በተለያዩ መድረኮች ማኅበሩን ማሳጣትና መክሠሥ እንደሚመርጡም ለፋክት መጽሔት አስታውቀዋል፡፡ ታቅዷል የተባለው የዶኩመንተሪ ዝግጅት እውነት ከኾነም ማኅበሩን ብቻ ሳይኾን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማዳከም አጠቃላይ ዘመቻ አድርገው እንደሚቆጥሩትና በቀላሉ እንደማይመለከቱት አሳስበዋል፡፡

ምንጭ:(ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፰፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.)

ጎሠኛነትና ሽብርተኛነት

በፕሮፍ. መስፍን ወልደ ማርያም

የካቲት 2006

የጎሠኛነት አጭር ትርጉም ዓለምን በራሱ ጠባብ ኢምንትነት የሚለካ ሰው ነው፤ ለኪው መለኪያው ነው፤ መለኪያውም ለኪው ነው፤ ጎሠኛነት የዘረኛነት የባሕርይ ልጅ ነው፤ ዘረኛነትም ሆነ ጎሠኛነት መሠረታቸው ድንቁርና ነው፤ የድንቁርናው ዓይነተኛ መገለጫ ‹‹ንጹሕ›› የሚለው ቃል ነው፤ ለዚህ ዋና ምስክር አድርጌ የማቀርበው አዶልፍ ሂትለርን ነው፤ ስለ‹‹አርያን ዘር›› ማንነትና ‹‹ንጹሕነት›› የሂትለር Mien Kampf የሚለውን መጽሐፍ ነው፤

የሰው ልጆች ባህል የሚባለው ሁሉ፣ ዛሬ የምናየው የሥነ ጥበብ፣ የሳይንስና የሳይንስ ጥበብ (ቴክኖሎጂ) ውጤት ሁሉ የአርያን ዘር የፈጠራ  ውጤቶች  ናቸው፤ … ‹ሰው› የሚባለውም እሱ ብቻ ነው።

የሂትለር ዘረኛነት የሰውን ልጅ ሁሉ ጉድጓድ ውስጥ ከተተው፤ አርያኑን ከንጹሕ የሰው ዘርነት ወደብቸኛ የሰው ዘርነት አሸጋገረው፤ ይህ ንጹሕ ድንቁርና ነው፤ የጎሠኞችም መነሻና መድረሻ፣ መንገዱም ይኸው ነው፤ በቅርቡ በፌስቡክ ላይ የታየው የቋንቋ ንጽሕና ክርክር የዚሁ የዘረኛነትና የጎሠኛነት ድንቁርና ቅጥያ ነው፤ ስለቋንቋዎች ባሕርይ ምንም ዓይነት እውቀት ሳይኖረው ቋንቋውን በማንገሥ እሱ ራሱ የነገሠ እየመሰለው ይደሰታል፤ ዓባይን ያላየ ምንጭ ያመሰግናል እንደሚባለው፤ ሙት ቋንቋ ካልሆነ በቀር ቋንቋ እንደሰው ልጅ ይጋባል፤ ይዋለዳል፤ ይለወጣል፤ በ1944 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ አገር ለማየት ከአዲስ አበባ የወጣሁት በጣልያን ትሬንታ ኳትሮ (34) ከባድ የዕቃ መጫኛ መኪና ላይ ተጭኜ ነው፤ ደብረ ማርቆስ ስገባ የሚናገሩት አይገባኝም ነበር፤ እኔ ከለመድሁት የሸዋ አማርኛ ጋር በጣም የተራራቀ ነበር፤ ወሎም ሄጄ አንደዚያው ነበር፤ ዛሬ ከስድሳ ዓመታት በኋላ ሌላ ነው፤ ዘረኛነትም ሆነ ጎሠኛነት የእውቀት፣ የመሻሻልና የእድገት ጸር ነው፤ ቆሞ-ቀር ነው፤ የአእምሮው እይታ አጠገቡ ካለው ወንዝና ጉብታ አያልፍም፤ ራሱ በፈጠረው ግርዶሽ መተናፈሻውንና መንቀሳቀሻውን ያጠበበ ነው፤ ተንጋሎ የተፋ ለራሱ ከፋ!

“ውሃ፣ መብራት፣ ኔትዎርክ የለም ፤ ኑሮ ከበደን” ሰሚ ጆሮ ያጣ የሕዝብ እሮሮ

“ውሃ የለም፤ መብራት፤ ኔትዎርክ የለም፤ መብት የለም፤ ፍትህ የለም፤ ኑሮ ከበደን” እያሉ ስለኑሮዓቸው የተሰማቸውን በሀቅ የተናገሩ ልጃገረዶች በጋጠወጥ የህወሓት ካድሬዎችና ታጣቂዎች እጅ መከራና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በእነዚህ ለጋ ወጣቶች ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ በዝምታ ያልፋል ተብሎ አይታመንም።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮን ጨምሮ በወያኔና የጥቅም ተጋሪዎቹ ሥር የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን በየዕለቱ ያለማቋረጥ ከሚዘገቡት የልማትና የዕድገት ዘገባዎች ከፍተኛውን ስፍራ የሚይዘው በአገራችን ውስጥ እየተሠሩ ስላሉ ትላልቅ የሃይድሮ ኤለክትሪክ ማመንጫ ግንባታዎች፤ በየከተማው ስለተዘረጉ የውሃ መስመሮች፤ የስልክ አገልግሎት ለማዳረስ ስለተወሰዱ እርምጃዎች፤ ስለ ረጃጅም የባቡር መስመሮች ግንባታ እና ስለ አገር አቋራጭ የመንገድ ሥራዎች የሚቀርቡ የተጋነኑ ዘገባዎች ናቸው።

እነዚህ የልማት አውታሮች ግንባታ በአብዛኛው የሚካሄዱት ከምዕራባዊያን መንግሥታት በሚሰጡ የገንዘብ እርዳታና ዕዳው ለልጅ ልጆቻችን በሚተርፍ አለም አቀፍ የገንዘብ አበዳሪ ድርጅቶች ወለድ እያስከፈሉ በሚሰጡት የረጅም ጊዜ ክፍያ ብድር እንደሆነ ግልጽ ነው።

ወያኔ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 23 አመታት በድህነት ቅነሳና የልማት ማስፋፊያ ስም ከአለም አቀፍ ኅብረተሰብ የተቀበለው የገንዘብ መጠን ሲሰላ ኢትዮጵያ አገራችን እንደ አገር ከተመሰረተችበት ዘመን ጀምሮ በብድርም ሆነ በእርዳታ ስም ይህንን ያህል መጠን ገንዘብ አግኝታ እንደማታውቅ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ ። በዚህም መሠረት ገንዘቡ በአግባብ ሥራ ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አገራችን የትና የት በደርሰች ነበር እያሉ የሚቆጩ የአገሪቱ ልሂቃንና ቅን አሳቢ ዜጎች ቁጥር ቀላል አይደለም ።

Wednesday, March 19, 2014

በጋዜጠኞች ላይ ያለ ማስረጃ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎች ባስቸኳይ እንዲቆሙ እንጠይቃለን!


የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ)
ETHIOPIAN JOURNALISTS FORUM (EJF)


ማህበራችን ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዶ የምዝገባ ሰርተፊኬት ለማግኘት የጀመረው እንቅስቀሴ በቅርቡ ከመንግስት አወንታዊ ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ በማድረግ የተቋቋመለትን አላማ ለማሳካት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅና የመናገር ነፃነትን ከማበረታታት ባለፈም ከአህጉራችን አፍሪቃ ጋዜጠኞች ጋር በመተባበር የመላው አፍሪቃ ጋዜጠኞችን መብትና ጥቅም የሚያስጠብቅና የመናገር ነፃነትን የሚያበረታታ አህጉራዊ ተቋም ለመመስረት ተነሳሽነትን ወስዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ በቅርቡም የምስራቅ አፍሪቃ ጋዜጠኞችን በማስተባበር አህጉር አቀፍ እንቅስቃሴያችንን ለማስጀመር ዝግጅት እያደረግን ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተግባር ጋዜጠኛውን ሳይወክሉ የጋዜጠኛውን ስም የያዙት የኢጋማ፣ የኢነጋማና የኢብጋህ አመራሮች ነን የሚሉት ግለሰቦች በመቀናጀት በየሚዲያው እየቀረቡ ጋዜጠኞችንና የሚዲያ ተቋማትን ለማሸማቀቅ ያለመ ውንጀላና አሉባልታ የመንዛት ዘመቻ ጀምረዋል፡፡ ግለሰቦቹ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ቀርበው በጋዜጠኞች ላይ ከሽብር ፈጠራ እስከ ሀገር ማተራመስ የደረሰ የውንጀላ መዓት ቢደረድሩም አንዳችም ማስረጃ አላቀረቡም፡፡

Tuesday, March 18, 2014

ኢሳት በአሁኑ ሰዓት ብቸኛው አማራጭ ሚዲያ ነው!

በአርኣያ ጌታቸው

ኢሳት እንደ በርካታ የኢትዮጵያ ተቋሞች በበርካታ ችግሮችና ጉድለቶች ያሉበት መሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ አፍጥጦ እየወጣ ነው፡፡ የገንዘብ፣ የፕሮግራም ጥራት፣ የግልጽነት፣ የገለልተኝነት፣ …. በጣም በርካታ ችግሮች ይጠቀሳሉ በአብዛኛዎቹም እስማማለሁ፤ ይሄን እራሳቸው ኢሳቶችም የሚክዱት አይመስለኝም፡፡ ልዩነቱ ግን “እና ምን ይሁን?” የሚለው ላይ ነው? ኢሳት ችግሮች ስላሉበት ይጥፋ፤ ይዘጋ?

ምን ያህሎቻችንስ ለዚህ ሚዲያ ከመመስረት አንስቶ አሁን እስካለበት ሲደርስ ምን አስተዋጽኦ አድርገን ነው ለድክመቱ ብቻ እንደደመራ እንጨት ዙሪያውን ከበን ወደ ምስራቅ፤ ወደ ምዕራብ ሊወደቀ ነው እያልን የምንጠቋቆመው፡፡ አዎ ምንአልባት በዚህ ማህበራዊ ገጽ ዙሪያ የምንገናኝ ጥቂቶች ከኢሳት የተሻለ መረጃ እናገኝ ይሆናል፤ ከዚህም ሶሻል ሚዲያም ተጠቃሚዎች አብዛኛዎቹ በተለይ ፖለቲካ ነክ ሀሳቦችን የሚጦምሩ ከሀገር ውጭ የሚገኙ /ዲያስፖራ/ ናቸው ፡፡ የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን የእድሜ ፤ የአቅም እና የእውቀት ገደብ ሳያንበረክከው የሚከታተለው ሚዲያ ከነችግሩ ኢሳትን ነው፡፡ ኢሳትም ብቸኛ አማራጭ እየሆነ ያለውም ለዚህ ነው፡፡

የኢሳት መዳከምም ሆነ ውድቀት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ትልቅ አደጋ ይዞ ይመጣል፤ ፖለቲካውን አንድ እርምጃ ሳይሆን ሁለትና ሶስት እርምጃ ወደ ኋላ ይጎትተዋል ባይ ነኘ፤ ምንም አማራጭ ሚዲያ በሌለበት ብቸኛ የሆነውን ኢሳት ቆመን ውድቀቱን እና እድገቱን ከምንተነትን አቅም ያለው በገንዘቡ፤ እውቀት ያለው በእውቀቱ በመተባበር መለያችን ወደመሆን የተቃረበው የመክሸፍ እጣ ፈንታ በኢሳትም ላይ እንዳይደርስበት ሁላችንም ተረባርበን ኢሳትን ወደ ተሻለ ሚዲያ ልናሸጋግረው ይገባል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 4ን በ PDF

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 4ን በ PDF ያንብቡ

           

Letter to My Son – Eskinder Nega from Kaliti Prison

The mistakes of my life. Ah! I could go on and on and on about them.  (Warning, I am aiming for your sympathy.) There are the missed opportunities. (God is generous, I squandered them all, literally.) There are the wrong choices (Hey there is at least the adrenaline rush that comes with every wrong move.) There is the conceited self-absorption (Obviously more and more as I rush through middle age.) There is the lack of direction (Bitter to admit, but true.) There is the incapacitating self-doubt. (Question: are you teary-eyed or disgusted?)

But here is what my strategy is not: a crafty debasement of expectation at the outset, so that by the end the balance of sympathy could sway no way but in my favor. I simply hanker honesty.

Indeed, I too yearn to be a hero in my son’s eye. Somehow privy to the notion that a male child’s first hero is the father, I dream to play the role. That this phase of the child is posed to pass quickly matters not an iota to me. I insist on my 15 minutes of fame. But I am also interested in the most enduring kind of appraisal, that of respect. While the former, unexplored adoration, is innate in every child, the latter, empathy and regard of the person, is the result of a complex process. And it has to be earned. Whether I merit this honor should be clear by the end of this letter.

I have reluctantly become an absent father because I ache for what the French in the late 18th century expressed in three simple words: liberté, egalité, fraternité. Before the advent of my son in my life, I was a nonchalant prisoner of conscience on at least seven occasions. The blithe was hardly unnoticed by my incarcerators.

በነፃነት ቀን ነፃነት ማጣት! በይድነቃቸው ከበደ


ሰብአዊ መብቶች እያንዳንዳችን ሰው በመሆናችን ብቻ የሚገቡን ከሰብአዊነታችን ተለይተው ሊታዩ የማያችሉ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስታት እነዚህን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን ሰብአዊ መብቶች ለማክበር ለማስከበርና ለማሟላት በቀዳሚነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት ኃላፊነት ከፈረሙ ቀደምት አገራት መካከል ኢትዩጵያ ትገኝበታላች፡፡

ይሁን እንጂ የሴቶች ሰብአዊ መብቶች በሚፈለገው መልኩ ተግባራዊ ካለመሆኑ ባሻገር ኢ-ፍትሃዊነት እጅግ የበዛ ነው፡፡ ይህም በመሆኑም እ.ኤ.አ. በ1908 በአሜሪካ ኒወርክ ከተማ በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ይሰሩ የነበሩ ላብአደር ሴቶች ‹‹ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያና የተመቻቸ የሥራ ሰዓት ለሴቶች›› በሚል መፈክር የሥራ ማቆም አድማ በማካሄድ የሴቶች ድምፅ እንዲስተጋባ አድርገዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የዓለም ሴቶች በማህበር በመደራጀት ትግላቸውን በማጠናከራቸው የዓለም መንግስታትን አስተሳሰብ በመለወጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል አገሮች የሴቶች መብት ስምምነት/ኮንቪክሽን/ እንዲፈራረሙ እብይ ምክንያት ሆነዋል፡፡

Monday, March 17, 2014

ውዳሴ መስከረም ወጽዮን

በፕሮፍ. መስፍን ወልደ ማርያም

የካቲት 2006

በብዙ አገሮች እንዲሁም በኢትዮጵያ የሴቶችና የወንዶች ቁጥር ብዙም አይለያይም፤ እኩል ለእኩል ይሆናሉ፤ ነገር ግን ይህ የቁጥር እኩልነት በኑሮአችን ላይ አይታይም፤ በ1983 የወያኔ ሠራዊት በየመንገዱ ይታይ በነበረበት ጊዜ አንድ ቀን ወደሂልተን ሆቴል ስገባ አንዲት ልጅ ከቁመትዋ የሚረዝምና ከክብደትዋ የበለጠ ጠመንጃ ይዛ አየሁና ዕድሜዋን ብጠይቃት አሥራ አራት አንደሆነ ነገረችኝ፤ ይቺ ልጅ በዚህ ዕድሜዋ ስንት መከራ እንዳየች እግዚአብሔር ይወቀው፤ በዚያን ጊዜ እንደስዋ ያሉ ብዙ ሴቶች ወያኔዎች አይቻለሁ።

የመጀመሪያው ወያኔ/ኢሕአዴግ ያዘጋጀው ጉባኤ በተካሄደበት ጊዜ በጉባኤው ውስጥ አንዲት ሴት ብቻ ነበረች፤ እስዋም ከሠራተኞች ማኅበር የተወከለች ነበረች፤ እነዚያ ጠመንጃ እየተሸከሙ በእግራቸው አዲስ አበባ የገቡትና በየመንገዱና በየመሥሪያ ቤቱ በር ላይ ሲጠብቁ የነበሩ የወያኔ ሴቶች በጉባኤው ላይ በአንድም ሴት አልተወከሉም ነበር፤ ነገሩ በጣም ከንክኖኝ ለመለስ ዜናዊ ነገርሁት፤ ይህንን ጉድለት በማንሣቴ ደስ ባይለውም ስሕተት መሆኑን ተቀብሎ ወደፊት እንደሚታረም ነገረኝ፤ ከዚያም በኋላ ቢሆን ከነጻነት አስፋው ሌላ (የእስዋን አርበኛነት ባላውቅም) በመድረኩ ላይ የምትታይ ሴት አልነበረችም፤ ምናልባት እነዚያ ከጫካ የመጡት እንደነጻነት በአውሮፓና በአሜሪካ አልሠለጠኑም ይሆናል፤ እንዲያውም ትንንሾቹን ወያኔዎች ወደትምህርት ቤት ቶሎ ማስገባት ያስፈልጋል ብዬ በመናገሬ ነጻነት አስፋው አንተ ብሎ ለነሱ አሳቢ ብላ ቁጣዋን አውርዳብኛለች፤ ምናልባትም ተማሪዬ በነበረች ጊዜ የደረሰባትን ‹‹ግፍ›› ልትመልስ ይሆናል፤ ዋናው ነጥቤ ግን በወያኔ ዘመን ብዙው ሰው ሲያልፍለት እነዚያ ጠመንጃ ተሸክመው ያየኋቸው እንኳን ሊያልፍላቸው ለዓይንም የጠፉ ይመስላል፤ አሁን በቅርቡ አንዳንድ መደበኛ የትራፊክ ፖሊሶች ሆነው አይቻለሁ፤ በተቀረ ከላይ ተንሳፍፈው የምናያቸው የእንትና ሚስት ወይም የእንትና እኅት ናቸው ይባላል።

Sunday, March 16, 2014

መቃጠል መቃጠል መቃጠል

በፋሲል የኔአለም

ከአስራ ምናምን ዓመታት በፊት ፔሩቪያዊው ኢኮኖሚስት ሄርናንዶ ደ ሶቶ ስለ “ኢንፎርማል” ኢኮኖሚ በጻፈው መጽሃፍ ውስጥ ፣ በአለም ላይ በህጋዊ መንገድ ያልተዘመገበ ከ10 ትሪሊየን ዶላር በላይ ሃብት መኖሩን፣ ይህን ሃብት መዝግቦ የባለቤትነት ህጋዊ መብት በመስጠት ብዙ ዜጎችን ከድህነት ማውጣት እንደሚቻል ገልጾ ነበር። ደ ሶቶ እንደሚለው በደሃ አገራት ሁለት አይነት ኢኮኖሚ አለ። አንደኛው ጥቂቶች የሚያንቀሳቅሱትና በመንግስት እውቅና የተሰጠው ኢኮኖሚ ሲሆን ሌላው ደግሞ መንግስት የማያውቀው በአብዛኛው ህዝብ የሚንቀሳቀሰው ኢኮኖሚ ነው ፤ ይህ ኢኮኖሚ በመንግስት እውቅና ያልተሰጠው በመሆኑ በዚህ ስር የታቀፉ ዜጎች ከባንክ ተበድረው ቢዝነሳቸውን ለማስፋፋት አይችሉም፤ መንግስትም ከእነዚህ ሰዎች ተገቢውን ታክስ አያገኝም። በደሃ አገራት ውስጥ መንግስታት እውቅና ሳይሰጡት የሚንቀሳቀሰው ሃብት እውቅና ከተሰጠው ሃብት ይበልጣል። ደ ሶቶ እንደሚመክረው ህጋዊው የኢኮኖሚ ስርአት የማያውቃቸውን ሀብቶች በመመዝገብና ህጋዊነት በማላበስ ዜጎች ሃብትና ንብረት እንዲያፈሩና ድህነትን እንዲሻገሩ ማድረግ ይቻላል።

የ ደ ሶቶን ሃሳብ ለማየት በአዲስ አበባ የተገነቡ የጨረቃ ቤቶችን እንመልከት። ነዋሪዎቹ ቤቶችን ለመስራት ብዙ ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ አፍስሰዋል፣ ይሁን እንጅ የመንግስትን የባለቤትነት ማረጋገጫ ቁራጭ ወረቀት ለማግኘት ባለመቻላቸው የሰሩት ቤት ሃብት ሊሆን አልቻለም። ቤታቸውን መሸጥ፣ መለወጥ እንዲሁም በባንክ አስይዘው ገንዘብ መበደር አይችሉም። እነዚህ ሰዎች የባለቤትነት ካርታ እስካላገኙ ድረስ ቤታቸው ሃብታቸው ነው ማለት አይቻልም። ነገር ግን የይዞታ ማረጋገጫ ብጣሽ ወረቀት ባገኙ በሰከንድ ውስጥ ቤታቸው ሃብታቸው ይሆናል፣ መሸጥ መለወጥ፣ ቤታቸውን አስይዘው ከባንክ መበደር ይችላሉ። በአንድ ወረቀት የቤቶቹ ባለቤቶች ከድህነት ወደ ሃብት ባለቤትነት ተሸጋገሩ፣ በሌላ አነጋገር የድህነትን መጋረጃ ቀደዱ ማለት ነው። መንግስት ህጋዊ እውቅና ለሌላቸው ሌሎች ቢዝነሶችም ህጋዊ እውቅና ቢሰጥ ፣ ሰዎችን ባለሀብት ማድረግ ብቻ ሳይሆን መንግስትም ከእነዚህ ቢዝነሶች ብዙ ግብር መሰብሰብ ይችል ነበር። በኢትዮጵያ ያለው የገዢዎች ስብስብ ግን ንብረት በማውደም የሚደሰት ይመስላል። ቤት ማፍረስና ንብረት ማቃጠል ልዩ መልክቱ ሆኗል። ባለፉት 22 ዓመታት ስንትና ስንት ቤቶች ፈረሱ፣ ስንቶቹ ተቃጠሉ፣ ስንትና ስንት የአገር ሃብት አብሮ ወደመ፣ ስንቶቹ ደኸዩ፤ ወረቀት በማደል ህጋዊ ማድረግ ሲቻል ሳይቻል ቀረ።

Thursday, March 13, 2014

በዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ዝክር፤ በእህቶቻችን ኮርተናል!!!

ለዘንድሮው ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን መታሰቢያ በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገው የሩጫ ትዕይንት ላይ ወጣት ሴቶች ባሳዩት ልበ ሙሉነት ኮርተናል። የሩጫውን ትዕይንት አስታከው፣ በአብዛኛው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እንደሆኑ የተነገረላቸው ወጣት ሴቶች ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለህሊና እስረኞች መፈታት እና ለሀገር አንድነት ድምፃቸውን ከፍ አድረገው ጮኸዋል፤ ዘምረዋል። እነዚህ ወጣት ሴቶች በሥርዓቱ ምን ያህል እንደተማረሩ በቃላትም በአካል ንቅናቄም አሳይተዋል። ዘረኛውና ፋሽስቱ ወያኔ ግን “ለምን ተቃወማችሁኝ” ብሎ አስሯቸዋል፤ ከፊሎቹም የደረሱበት አይታወቅም። በእህቶቻችን ቆራጥነት ኮርተናል፤ በወያኔ የፈሪ ዱላ ደግሞ ተቆጥተናል። በ1997 እና 98 “የወላጆቻችን ድምጽ ይከበር” ያሉ ሕፃናትን የጨፈጨፈው ወያኔ በ2006 ወጣት ሴቶችን ከማሰቃየት ይመለሳል ብለን አናምንም። ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ የፈሪ ዱላው የማይቀር ነገር ነው።

የወንዶቹን ያህል የተዘገበ አይሁን እንጂ በክፉም በደጉም ሴቶች ያልተሳተፉበት የኢትዮጵያ ታሪክ የለም። የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን እንኳን ብናይ በፋሽስት ወረራ ወቅት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች በአርበኝነት ዘምተው አዋግተዋል፤ ተዋግተዋል። በተለያዩ ምክንያቶች መዝመት ያልቻሉት ደግሞ በውስጥ አርበኝነት ተሰልፈው የጠላት ምስጢሮች ለአርበኞች እንዲደርሱ በማድረግ ከፍተኛ ጀብዱዎችን ፈጽመዋል። ከፋሺስት ወረራ ወዲህ በነበሩ ዓመታት ውስጥም ለፍትህ እና ለነፃነት በተደረጉ ተጋድሎዎች ሴቶች ጉልህ ተሳትፎ ነበራቸው። በተማሪዎች ትግል ውስጥ ለምሳሌ፣ ወጣት ሴቶች በአመራር ደረጃ በመሳተፍ ትግሉን መርተዋል፤ የሕይወት መስዋዕትነት ጭምር ከፍለዋል። ከዚያ ወዲህም በነበሩት ዓመታት በኢሕአፓ እና ሌሎችም ድርጅቶች አመራርና አባልነት ተሳትፈው ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ነበሩን። በቅርቡም በምርጫ 97 እንቅስቃሴም የሴቶች በተለይም የወጣት ሴቶች ተሳትፎ ምን ያህል ጉልህ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነውና እናስታውሳለን። ለምርጫ ድምጽ መከበር ወጣት ሽብሬ ደሣለኝን ጨምሮ በርካታ ሴቶች ሕይወታቸውን ሰውተዋል፤ ከዚያ የበለጡት ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ዛሬም እንደ ርዕዮት ዓለሙ የመሳሰሉ ጀግኖች በወያኔ ወህኒ ቤቶች እየማቀቁ፤ በየእለቱ ሰቆቃ (ቶርቸር) እየተፈፀመባቸው መሆናቸው በሀዘንና በቁጭት እናስባቸዋለን።

Tuesday, March 11, 2014

ችግር ነው አስቀድሞ ማሰብ

ፕሮፍ. መስፍን ወልደ ማርያም

የካቲት 2006

ወያኔ/ኢሕአዴግ ጥሩምባ ነፍቶ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦች ነጻነት ብሎ ከአወጀና ሁሉንም ለሃያ ሁለት ዓመታት በተስፋ ከአስፈነደቀ በኋላ ችግር ተፈጠረበት፤ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች የሚባለው ነው፤ ችግሩ አፍ ከሚችለው በላይ ለመጉረስ ከራስ ጋር መተናነቅ ሆነ፤ ችግሩ የማሰብ ድርቀት ነው፤ ችግሩ ከአሜሪካና ከአውሮፓ መንግሥታት ጀምሮ እስከቀበሌ መዋቅር ያሉትን ሁሉ በአንድ ዘዴ እያባበሉና እያታለሉ ማደናበር ነው፤ ችግሩ በሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ ዘዴው ሻግቶ ዓላማው ደብዛው መጥፋቱ ነው፤ ቸግሩ የዘዴው መሻገትና የዓላማው መክሸፍ መጋለጡ ነው፤ ችግሩ ወያኔ የተቀመጠበት የሥልጣን ወንበር መቆርቆር መጀመሩ ነው።

የግለሰብ ነጻነት ታፍኖ የጎሣ ነጻነት መታወጁ ፋይዳ እንዳላመጣ ታየ፤ የግለሰብን ነጻነት ለመደፍጠጥ ሲባል የጎሣዎች ነጻነትም አብሮ ተደፍጥጦ ነበር፤ ይህንን አስቀድሞ ለማየት ለምን ሳይቻል ቀረ? የሚል ጠያቂ ከመጣ መልሱ ቀላል ነው፤ በሚልዮኖች ብር እየወጣ መንገድ ሲሠራና አስፋልት ሲለብስ ቆይቶ ከጥቂት ወራት በኋላ የባቡር ሀዲድ ለመዘርጋት ተብሎ የተሠራውን አስፋልት የለበሰ መንገድ ማፍረስ እንዳስፈለገ አይተናል፤ የባቡሩ ጉዳይ ለምን አስቀድሞ አልታየም? የጎሣን ነጻነት ለማጉላት ሲባል የግለሰብን ነጻነት መደፍጠጡ ዞሮ ዞሮ የጎሣውንም ነጻነት አንደሚደፈጥጠው ያልታየበት የተለየ ምክንያት የለውም፤ አሰቀድሞ አለማየት የባሕርይ ነው፤ በተጠቀሱት ምሳሌዎች ሁለቱም ዋጋ ያስከፍላሉ፤ ልዩነቱ የአንዱ ዋጋ የሚከፈለው በፖሊቲካ ኪሳራ ሲሆን፣ ሌላው የሚከፈለው በኢኮኖሚ (በሀብት) ኪሳራ ነው፤ ሆኖም የፖሊቲካውም ሆነ የሀብቱ ኪሳራ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሙሉ ያለምንም የጎሣ ልዩነት ሲጫንበትና ችጋር ሲያንዣብበት በሥልጣኑ ወንበር ላይና በዙሪያው የሚንሳፈፉት ፈጣሪዎቹ ናቸውና የችግሩ ሸክም ሲያልፍም አይነካቸው! እንኳን ለፖሊቲካና ለሀብት ኪሳራ ለሕይወት ኪሳራም ቢሆን የማይጠየቅ መሆኑን በምክር ቤት በሚባለው ውስጥ በድፍረት የተነገረበት አገዛዝ ነው።

Monday, March 10, 2014

በሴቶች የነጻነት ቀን በሴት አባላቶቻችን ላይ የተወሰደውን ህገ ወጥ እርምጃ እናወግዛለን ! ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

‹‹ማርች-8›› የሴቶችን ነጻነትና እኩልት እንዲሁም ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የሚከበር የሴቶች ቀን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህን በዓል አስመልክቶ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፈው ዕሁድ የካቲት 30/2006 ዓ.ም ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት የጎዳና ላይ ሩጫ ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ የሐገራችንም ሆነ የዓለም ሴቶች የነጻነት ቀናቸውን በሚያከብሩበት ዕለት እንደሌሎች ሴቶች ሁሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትም አላማውን ደግፈው በዕለቱ ቀኑን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

እንደሚታወቀው ታላቁ ሩጫ በተለያየ ጊዜ በሚካሄድበት ወቅት ተሳታፊዎች በሐገራቸው የሰፈነውን ጭቆና በመቃወም ሀሳብን የመግለጽ ህገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀም ድምጻቸውን የሚያሰሙበት በመሆኑ ‹‹የብሶት መግለጫ›› መድረክ እስከመባል ደርሷል፡፡ ልክ እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ በእሁዱ የጎዳና ሩጫም በርካታ የሩጫው ተሳታፊዎች ይህን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ የመጣውን ጭቆና በመቃወም ድምጻቸውን ሊያሰሙበት ችለዋል፡፡

በዚህ በሴቶች የነጻነት ቀን በስርዓቱ ላይ የሚነሱ ብሶቶችን ካሰሙት ተሳታፊዎች ውስጥ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሚገኙበት ሲሆን፣ በተለየ መልኩ በእነዚህ አባላቶቻችን ላይ ያነጣጠረ የአፈሳ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደዚህ አይነት ህዝባዊ መድረኮችን ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል በማጋለጥ ለህዝብ መብት እና ለአገራችን ብሄራዊ ጥቅም በመቆሙ በገዥው ፓርቲ ተደጋጋሚ ህገ ወጥ እርምጃ ሲወሰድበት ቆይቷል፡፡ በትናንትናው ዕለት የተደረገውም ከዚሁ ፓርቲው ለህዝብና ለአገር መቆሙን ተከትሎ እየደረሰበት ያለው የከፋ የጭቆና አካል ነው፡፡

Friday, March 7, 2014

እኔ «ይህ ትውልድ» ነኝ

እውነት ነው... እኔ «ያ ትውልድ» አይደለሁም፤ ይህ ትውልድ እንጂ፡፡ እኔ ያ በሌኒንና ማርክስ አስተምሮ ልቡ የሸፈተው ለውጥ የጠማው ትውልድ አባል አይደለሁም፡፡ በሌሎች አገራት ይደረግ የነበረው የለውጥ እንቅስቃሴ ትኩረቴን አልሳበውም፡፡ «መሬት ላ'ራሹ!» ብየ የንጉስ ዘውድ አልነቀነኩም፤ «ፋኖ ተሰማራ ፋኖ ተሰማራ...እንደ ሆችምኒ እንደ ቼጉቬራ»ን አልዘመርኩም፡፡ «ትምህርት ለድሃው ልጅ!» ብዬ ወገንተኝነቴን በአደባባይ አልገለጽኩም፡፡

እኔ ፊውዳሊዝምንና ኢምፔራሊዝምን ለመዋጋት እጃቸውን ከጨበጡት አይደለሁም፡፡ የመሳፍንታዊ ካባን አሽቀንጥሮ ለመጣል ድንጋይ አልወረወርኩም፤ መፈንቅለ-መንግስት አላደረኩም፤ አልሞከርኩምም፡፡ አውሮፕላንም አልጠለፍኩም፡፡ በራሪ ወረቀቶችን በድብቅና በህቡ አላዘጋጀሁም፤ አልበተንኩም፤ በበተኑት ላይም «እርምጃ» አልወሰድኩም፡፡

እኔ ጎፈሬየን ነቅሼ ትዊስት አልደነስኩም፤ ማሪጌና ቡጊ ቡጊ አልተጫወትኩም፡፡ ቅኔ ሞልቶ ተርፎኝ በውስጠ-ወይራ አገላለፅ ገዝዎቼን አልሸነቆጥኩም፡፡ እንደነ አሳምነው ገብረወልድ በሙያዬ የህዝብ ልሳን መሆን አልደፈርኩም፡፡ እንደ በዓሉ ግርማ የተባ ብዕሬን በድፍረትና በትክክለኛው ሰዓት ከወረቀት ጋር አላገናኜሁም፤ ፍህራቴን ገና አልፈራሁትም፡፡ ምክንያቱም እኔ «ያ ትውልድ» አይደለሁም፡፡

እኔ ያን የተማሪ አብዮት አልቀለበስኩም፡፡ የህዝብ አጀንዳ በጠብመንጃ አልነጠኩም፤ በፖለቲካና በሌሎች ምክንያቶች ጎራ ለይቼ አልተታኮስኩም፤ ነፍጥ አንግቼ ጫካና በረሃ አልወጣሁም፤ ቀይ ሽብር...ነጭ ሽብር አላካሄድኩም፡፡ አድሃሪ፣ ወንበዴ፣ ገንጣይ፣ አስገንጣይ አልተባባልኩም፡፡ «አብዮት ልጆን ትበላለች» አላልኩም፤ ግዳይ ጣልኩ ብዬ ለሬሳ የጥይት ዋጋ አላስከፈልኩም፡፡ «ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም!»ን አልፈከርኩም፤ የ«ኢትዮጵያ ትቅደም ጠላ… ይውደም!» ፈፃሚም አስፈፃሚም አልነበርኩም፤ አይደለሁምም፡፡

ወያኔ በግንቦት 7 ስም ሠላማዊ ዜጎችን ማሰቃየቱን ባስቸኳይ ማቆም አለበት

ባለፉት አራትና አምስት አመታት በግልጽ እንዳየነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነቱን፤ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚያደርገዉ ትግል ጫና በፈጠረበት ቁጥር ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የራሱን ህገመንግስት የሚደፈጥጡ ህጎች አርቅቆ አያጸደቀ ሠላማዊ ዜጎችን አስሯል፤ ገድሏል ከአገር እንዲሰደዱም አድርጓል። ለምሳሌ በ2003 ዓም የኢትዮጵያ ፓርላማ ከቤተመንግሰት የተላለፈለትን ትዕዛዝ አክብሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነፃነት መከበር የሚታገለዉን የግንቦት 7 ንቅናቄ ሽብርተኛ አድርጎ ፈርጇል። ይህ ፈር የለቀቀ ፍረጃ ደግሞ ወያኔ የሱን ዘረኛ ስርዐት የሚቃወሙ ግለሰቦችን፤ ሀሳባቸዉን በነፃነት የሚገልጹ ዜጎችን፤ ጋዜጠኞችን፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ከወያኔ ጋር አናብርም ያሉ ወጣት ኢትዮጵያዉያንን “ግንቦት ሰባቶች” ናችሁ እያለ በጅምላ እያሰረ እንዲያሰቃይ ህጋዊ ሽፋን ሰጥቶታል። ለምሳሌ ከፍትህና ከነጻነት ጥማት ዉጭ ከግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የሌለዉን የፖለቲካ ፓርቲ መሪዉን አንዱአለም አራጌን፤ ታዋቂዉን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና መምህርት ርኢዮት አለሙን የግንቦት 7 አባላት ናቸዉ የሚል ሰንካላና መሠረተ ቢስ ክስ መስርቶ ለረጂም ዘመን እስራት ዳርጓቸዋል።

ወያኔ እንደ ዛሬዉ ከተማ ዉስጥ ሆኖ ሥልጣን ሳይቆጣጠር ገና ጫካ ዉስጥ እያለ ጥርሱን ከነከሰባቸዉና ከተቻለ አጠፋቸዋለሁ ካለዚያም አሽመደምዳቸዋለሁ ብሎ አስራ ሰባት አመት ሙሉ ከተዘጋጀላቸዉ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ የአማራ ብሄረሰብ ነዉ። በለስ ቀንቶት ሥልጣን ከጨበጠ ማግስት ጀምሮም በወሎና በጎንደር በኩል ከትግራይ ጋር የሚያዋሰኑ ሰፊ የሆነ ለም መሬቱን ጠቅልሎ በመውሰድ ዘረኛ ሥርዓቱን ዕድሜ ሊያራዝሙልኛል ይችላሉ ብሎ የሚተማመንባቸውን የቀድሞ የትግል አጋሮቹንና ካድሬዎቹን አስፍሮበታል:: ይህ በደልና ግፍ አልበቃ ብሎትም ቀደምቶቹ የኢትዮጵያ ገዥዎች ለፈጸሙት ግፍና የአስተዳደር በደሎች ሁሉ አማራዉን በጅምላ ተጠያቂ የሚያደርግ ፕሮፖጋንዳ እነሆ እስከዛሬ በመርጨት ለዘመናት በሠላም ከኖረው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በጠላትነት እንዲተያይ አድርጎታል:: በወያኔ አጋፋሪነት በበደኖ ፡በአርሲ በአረካና ሌሎች አካባቢዎች አማራው ላይ በግፍ የተፈጸመው ጭፍጨፋና ከ2004 እስከ 2005 ዓም አማራዉን ከጉራፈርዳና ከቤንሻንጉል ለማፈናቀል የተወሰደው እርምጃ የዚህ የወያኔ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ውጤት መሆኑን የምስት የለም::

Wednesday, March 5, 2014

ነገረ ኢትዮጵያን 2ኛ ዕትም በ PDF




ስለ ወቅቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውህደትና ትብብር በስፋት አትታለች


አድዋን ዘክራለች!

ለሱዳን ተላልፎ ሊሰጥ በታሰበው መሬት ህጋዊና ፖለቲካዊ ትንታኔዎች ተሰጥቶባታል

ኢትዮጵያ ለምን ወደ ኋላ እንደቀረች ተተንትኖባታል

ስለ አገራችን የምርጫ ፖለቲካና ሌሎች አገራዊ ጉዳዮችም አካትታለች

Neger Ethiopia Issue 2 In PDF

Tuesday, March 4, 2014

አድዋ…. አድዋ…. አድዋ…. የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም

በቅዱስ ዬሃንስ

የካቲት ወር የአፍሪካውያን ወር ይባላል፡፡ ይህን ወር የአፍሪካውያን ወር ያሰኘው ብቸኛ ምክንያት የዓድዋ ድል ነው፡፡ ነጮች አፍሪካውያንን በግፍ በሚረግጡበት፣ በባርነት በሚገዙበት፣ ያሻቸውን ያለከልካይ በሚፈፅሙበት በዚያን ወቅት " እምቢኝ! ሀገሬን በቅኝ አላስገዛም " ብሎ በጀግንነት የተነሳ፣ ተነስቶም የቅኝ ገዢዎችን በትር በሀይል መስበር የተቻለበት ወር ይህ የካቲት ወር ነው፡፡  

የአውሮፓ ሀገራት አፍሪካን በተቀራመቱበት ዘመን ኢጣሊያም ኢትዮጲያን በቅኝ ግዛቷ ለማድረግ መንገድ የሚከፍትላትን የውጫሌ ውል ከአፄ ምኒልክ ጋር ውጫሌ ከተማ ላይ በተወካይዋ አንቶሌኒ መሰረት ተዋዋለች፡፡ ከተደረገው ውል አንቀፅ 17 ግን የአማርኛ እና የኢጣልያንኛ ትርጓሜው የተለያየ ነው፡፡ በአማርኛ የተፃፈው ‹‹ ግርማዊ የኢትዮጲያ ንጉሠ ነገሥት ከአውሮፓ መንግስታ ጋር ግንኙነት ለማድረግ ወይም ለመነጋገር ሲፈልጉ በግርማዊ የኢጣሊያ ንጉሥ አማካይነት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡›› የሚል ሲሆን የኢጣሊያንኛው ትርጉም ግን እንዲህ የሚል ነበር….‹‹ ግርማዊ የኢትዮጲያ ንጉሠ ነገሥት ከአውሮፓ መንግስታት ጋር ግንኙነት ለማድረግ ወይም ለመነጋር ሲፈልጉ በግርማዊ የኢጣሊያ ንጉሥ አማካይነት ያደርጋሉ፡፡›› የዚህ ፍቺው ኢትዮጲያ በኢጣሊያ ሞግዚት አስተዳደር ስር መሆኗን የሚገልፅ ነው፡፡ ይህንንም የኢጣሊያ መንግስት ለአውሮፓ መንግስታት በደብዳቤ አሳውቋል፡፡  
ይህም በታወቀ ግዜ አንቀፅ 17 ይቅር በሚል አፄ ምኒልክ ከባለሟሎቻቸው ጋር ወሰኑ በዚህም ሌላ ውል ተፈረመ፡፡ ኮንት አንቶሌኒ ‹ይቅር› የሚለውን ቃል የተረዳው እንዳለ ይቀመጥ አይለወጥ በሚል ነበርና አለመሆኑን ሲረዳ ምኒልክ እልፍኝ ገብቶ ደነፋ፡፡ የኢጣሊያ መንግስት ይህን እንደውርደት ይቆጥራል፡፡ ክብሩን ለማስጠበቅ ጦርነት ያደርጋል፡፡ ክብሩን በጉልበት ያስጠብቃል ብሎ ፎከረ፡፡  

እቴጌ ጣይቱ እንዲህ አሉት… ‹‹የዛሬ ሳምንት አድርገው፡፡ እኔ ሴት ነኝ፡፡ ጦርነት አልወድም፤ ነገር ግን ሀገሬን እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ! እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር አስጥቶ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ ለአፈሩ ክብር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ! ሂድ! የኢትዮጲያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው፡፡ ሂድ ባሻህ ግዜ ተመለስ ተሰናድተን እንጠብቅሃለን፡፡ ያንተን ወንድነትና የጣይቱን ሴትነትም ያን ግዜ እናየዋለን ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ፡፡››

Monday, March 3, 2014

የዋሽንግተንና የአዲስ አበባ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየተተቸ ነዉ


“በሙስና በእምነት ማጉደል በማታለልና በአመለካከት የሚለዩን ዝም በማሰኘት ሐይልን የያዛችሁ በተሳሳተ የታሪክ ገጽታ ላይ ነው ያላችሁት! ቡጢያቹን የምትፈቱ ከሆነ እጅ እንዘረጋላችሗለን” ያሉት ኦባማ አንባገነናዊ ቡጢያቸዉን ካልፈቱ...አንባገነናዉያን ጋር እጃቸዉን ዘርግተዉ ሲጨባበጡ መታየታቸዉ ትዝብት ላይ እየጣላቸዉ ነዉ!

ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 24/2006 (ቢቢኤን) ፦ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን ገደብየለሽ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማመላከት ያደረጋቸዉን ጥናቶች ዋቢ በማድረግ በየካቲት 20/2006 ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።መሰረቱን አርሊንግተን ቨርጂኒያ ያደረገዉ ፖለቲኮ የሚባለዉ ጋዜጣ/መጽሔት የኦባማ አስተዳደር የኢትዮጵያ መንግስትን ከመሰሉ ለነጻነት ምቹ ካልሆኑ አገራት ጋር ያለዉ ምጸታዊ የዲፕሎማሲ ቁርኝትንም ይተቻል።

ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ጀምሮ የዩናይትድ እስቴትስ መንግስታት ዜጎቻቸዉን ከሚጨቁኑ አገራት ጋር ግንኙነት ለመመስረት እምብዛም እንደማይጥሩ ፖለቲኮ እየገለጸ፤ለሚዛናዊነቱ ተስፋ የተጣለበት የኦባማ ካቢኔ ከሌሎቹ የዩናይትድ እስቴትስ ፕሬዝዳንቶች በባሰ መልኩ ለዜጎቻቸዉ ደህነነት ምቹ ካልሆኑ 25 አገራት ጋር ግንኙነት አለዉ ሲል የኦባማን የብሐራዊ ደህነነትና ጥበቃ አማካሪ የሆኑትን ሱዛን ራይስ ንግግርን በዋቢነት ያቀርባል። ራይስ “ግልፅ እንሁን አንዳንዴ እኛ አጥብቀን የምንይዛቸዉን ዉድ የሆኑ መብቶችን ከማያከብሩ መንግስታት ጋር የስራ ግንኙነት አለን” በማለት በባለፈዉ የነሐሴ ወር መናገራቸዉን ፖለቲኮ ይገልጻል።

ፖለቲኮ ለነጻነት የማይመቹ ብሎ ከጠራቸዉ 25 አገራት ዉስጥ ኢትዮጵያን በቁጥር 11 ላይ ያስቀመጠ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ይመሯታል የምትባለዋ ኢትዮጵያ የጸረ-ሽብር ህጓን ፖለቲከኞችን፣አክቲቪስቶችን፣መንግስትን ተጠያቂ የሚያደርጉ አካላትን ለማሰር እንደ ማህተም ትጠቀምበታለች ሲል ተጠያቂ ያደርጋል።ፖለቲኮ አክሎም የመለስ ዜናዊ አስተዳደር በ1999 ሶማሊያን በመዉረር እራሱን ለዩናይትድ እስቴትስ ግልጋሎት ማቅረቡንያስረዳል። ይህንንኑ አጋጣሚ በመጠቀም በአሜሪካ የሰለጠኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከብሔር ብሔረሰቦች የተነሱ አማጺያንን ለማስቆም የጦርነት ወንጀል መፈጸማቸዉ በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ክስ ቢቀርብበትም ዋሽንግተን አዲስ አበባን በዲፕሎማሲ “እቅፍ-እቅፍቅፍ” እያደረገች መቀጠሏን ገልጿል።

ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ለችግሮቻችን የመፍትሄው ቁልፍ

ገለታው ዘለቀ

የሃገራቸው ነገር ሲነሳ የሚከነክናቸው ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ላለባት ችግር መፍት ሄው ምንድነው? እያሉ ኣጥብቀው ሲጠይቁ ይደመጣል። መፍትሄውም ብቻ ሳይሆን ችግሩ ማለትም እውነተኛው ችግር የት ላይ ነው ያለው? ብለውም ኣጥብቀው ሲደመሙ ይታያል። በዛሬዋ ኣጭር ጽህፌ በነዚህ መራራ ጥያቄዎች ዙሪያ ቁንጥል ኣሳብ ለማቀበል ኣስቢያለሁ።

በርግጥም ሁላችን  ኢትዮጵያዊያን የሆንን ችግሩ ምንድነው? ብለን ከጠየቅን ኣንዳንዶች ሊገረሙብን ይችላሉ። የችግሩ ተካፋይ ሆነን ሳለ፣ እየተጉላላን ያለነው እኛው ሆነን ሳለ፣  እንደገና መልሰን  የሃገራችን ችግር የት ጋር ነው? ብለን ስንጠይቅ የምናወጋቸው ሰዎች ምናልባትም ግራ ሊጋቡ ቢችሉ ኣይደንቅም። ነገር ግን መጠየቃችን ትክክል ነው።

በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ትንቢተ ዳንዔል ላይ ኣንድ ናቡከደነጾር የተባለ ንጉስ ኣንድ ጊዜ ጠቢባንን  ጠርቶ የህልም ፍቺ ይጠይቃል። ጥበበኞቹም ህልሙን ንገረንና ፍቺውን እንነግርሃለን ሲሉት ህልሙ ጠፍቶብኛል ስለዚህ ህልሙንም ፍቺውንም ውለዱ ብሎ ጉድ እንዳፈላ እናነባለን።

እኛ ኢትዮጵያዊያን የዋናው ችግር ተጽእኖዎች የየእለት ኑሮኣችንን ሲያምሱት ብናይም ዋናውን የችግሩን ምንጭ መፈለጋችን ግን ኣሁንም ትክክል ነው።

የሃገራችንን ዋና ችግር የት ጋር ነው ብለን ኣጥብቀን ከጠየቅን በርግጥ የስርዓት ችግር ነው ወይ? ስርዓት በማጣታችን ነው ወይ የከፋ ችግር ላይ የወደቅነው? ብለን እንጠይቃለን።  በዚህ ኣገባብ ስርዓት ስንል የኣይዲዮሎጂውን ጉዳይ ሳይሆን ፍትህና ተጠያቂነት፣ ግልጽነትና የህዝብ የበላይነት የሚንሸራሸርበት ሲስተም ተዘርግቷል ወይ ብሎ የመጠየቅ ያህል ነው።  ስለ ስርዓት ስናነሳ ደግሞ በዋናነት የሚታየው ህገ- መንግስታዊ ስርዓቱ ነው። ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ምን ያህል ለዜጎች ይጨነቃል፣ ምን ያህል ለፍትህና ለነጻነት ለህዝቦች ጥቅም መንሸራሸሪያ ይህናል? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። በዚህ ረገድ በርግጥ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም በዋናነት ግን ችግራችን የስርዓት ችግር ሆኖ ኣናይም። ለኣብነት የ1955ቱን ህገ መንግስት ስናይ የፕሬስ ነጻነትን ይሰጣል፣ እኩል የህግ ከለላ ይሰጣል፣ የመሰብሰብ፣ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሁሉ ይሰጣል። የደርጉም ቢሆን ለዜጎች የሚጨነቅ ኣይነት ነው። “ኢትዮጵያዊያን በህግ ፊት እኩል ናቸው” ይላል። ከሁሉ በላይ ደግሞ የ1995ቱን ስናይ “ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው” ብሎ እጅግ ኣጠንክሮ ለዜጎች መብት መቆሙን ይደነግጋል።

የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮያ ዉስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳለ በዘንድሮዉ አመታዊ ሪፖርቱ ይፋ አደረገ

ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 20/2006 (ቢቢኤን) ፦ የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (State Department) ባወጣዉ የዘንድሮ የሰዓዊ መብት ሪፖርት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ያከናዉናቸዋል ያለዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመዘርዘር ሰፋ ባለ መልኩ አቅርቦታል።

ቀድም ሲል ኢትዮጵያ ዉስጥ በ2003 በተደረገዉ ምርጫ፤ በሟቹና በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ይመራ የነበርዉ ኢ.ህ.አዴ.ግ ከ547 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ 545 መቀመጫዎች አሸንፏል መባሉን ሪፖርቱ እያመላከተ የምርጫ ጣቢያዎች በመንግስት ሐይላት ቁጥጥር ስር እንደነበሩና አለምአቀፍ ታዛቢዎች ስራቸዉን በተገቢዉ መልኩ እንዳያከናዉኑ ገደብ እንደነበረባቸዉ ይገፃል።

በአገሪቱ ዉስጥ ባለዉ ከፍተኛ የመብት ረገጣ ሳቢያ ዜጎች የመሰብሰብ፣የመደራጀት፣የመናገር መብትን በገሃድ እንደሚነፈጉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ያስደረግቸዉን ጥናቶች ተመርኩዞ ያብራራል። እነዚህን የዲሞክራሲ እሴቶችን ለመተግበር የሚሞክሩም ይታሰራሉ፣ይንገላታሉ፣ይዋከባሉ፣ዛቻ ይደርስባቸዋል፣ ክብራቸዉ ተነክቶ እንዲሸማቀቁምይደረጋሉ በማለት ሪፖርቱ ያትታል።እርዳታን የሚያስተባብሩ፣ እርዳታን ለጋሽ የሆኑ ድርጅቶች፣ ማህበራዊና ትርፍ አልባ የሆኑ ተቋማት (NGO) የግብረ-ሰናይ ተልእኮ አቸዉን እንዳይፈጽሙ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚከለክል፤ በሰዎች ላይ ህገ ወጥ የሆነ ግድያ እንደሚፈጽም፣ዜጎች ግርፋት-ድብደባ እንደሚደርስባቸዉ፣ ወጥ የሆኑ የማሰቃያ ተግባራት በመንግስት ሐይላት እንደሚፈጽምና በአገሪቱ እስርቤት የሚገኙ ታሳሪዎችን ህይወት ለአደጋ የሚያጋልጹ አሳቃቂ ተግባራትም እንዳሉም በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።

ጥፋተኛ ጥፋቱን በይቅርታ እንጂ በዉሸትና በዕብሪት መሸፈን አይችልም

በቅርቡ አንድም የወያኔ ጌቶቹን ለማስደሰት ደግሞም ከህወሃት ካድሬዎች ስድብና ግልምጫ የማያድን ጎደሎ ስልጣን ለማግኘት ሲል ተወልዶ ያደገበትንና እመራዋለሁ የሚለዉን የአማራን ህዝብ ክብርና ታሪክ ያጎደፈዉና ያዋረደዉ የአለምነዉ መኮንን አስጸያፊ ንግግር በአለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያንን ያስቆጣና ያነሳሳ ጉዳይ ሆኖ መሰንበቱ ይታወሳል። ይህ የአማራን ህዝብ ማንነትና ይህ ጀግና ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ ያለዉን አኩሪ ቦታ ያላገናዘበና ባልተሞረደ አንደበት የተነገረ አስጸያፊ ንግግር ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተዉን የአማራን ህዝብ ብቻ ሳይሆን አገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚኖሩትን በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን አስቆጥቷል። አይናቸዉ ከገንዘብና ከሥልጣን ዉጭ ሌላ ምንም ነገር የማይመለከት ለሆዳቸዉ ብቻ ያደሩ ሰዎች የተከፈተ ሆዳቸዉንና ማለቂያ የሌለዉ የሥልጣን ጥማታቸዉን ለማርካት ሲሉ ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉ ወያኔ በሥልጣን ላይ የቆየባቸዉ ያለፉት ሃያ ሦስት አመታት በግልጽ አሳይተዉናል። ሆኖም ግን አይናቸዉ የታወረና ጭንቅላታቸዉ ባዶ የሆነ ሰዎች በነገሱበት በወያኔ ስርዐት ዉስጥም ቢሆን የሚጠሉትን፤ የሚንቁትንና የገዛ ወገኖቹን የገቡበት ቦታ ሁሉ እየተከተሉ ወደ አገራችሁ ግቡ እያሉ የሚያፈናቅሉ ዘረኞችን ለማስደስት ሲል ስቃይ የበዛበትን የራሱን ህዝብ ያዋረደ ከሀዲና ሂሊና ቢስ ሰዉ ያየነዉ አንድ አለምነዉ መኮንንን ብቻ ነዉ። አለምነዉ የተናገራቸዉን አጥንት የሚሰብሩ የንቀት ቃላት ይሀንን ከንቱ ሰዉ ባወገዝን ቁጥር እየደጋገምን ብንጠቅስ በአንድ በኩል የወያኔን ዘረኞች አላማ ያራምዳል ብለን ስለምናምን በሌላ በኩል ደግሞ እንደዚህ አይነቱን ጸያፍ ንግግር መደጋገም ሂሊናችን ስለማይፈቅድንና የጠፈፈ ቁስል መቆስቆስ ይሆናል ብለን ስለምንሰጋም ንግግሩን አንደግመዉም።

አሜሪካንን በመሳሰሉና በዕድገት ወደፊት በገፉ አገሮች ዉስጥ ዉሻ የሚታወቀዉ የሰዉ ልጅ ታማኝ ወዳጅ በመባል ነዉ። ዉሻ ባለቤቱን ለማስደስት ጭራዉን ከመቁላት ባሻገር የባለቤቱን እግር ይልሳል፤ ይንበረከካል፤ እግር ስር ይተኛል፤ ደግሞም አምጣ ብለዉ የወረወሩለትን ነገር እየሮጠ ሄዶ ያመጣል። የሚገርመዉ እንስሳዉ ዉሻ እንኳን እነዚህን ነገሮች ሁሉ የሚያደርገዉ ለባለቤቱና ለለመደዉ ወዳጁ እንጂ ለሌላ ለማንም ሰዉ አያደርግም። ዉሻ ባለቤቱንና ወዳጁን በተለይ ደግሞ የሱንና የባለቤቱን ጠላቶች ለይቶ ያዉቃል፤ ስለዚህም ዉሻን ባለቤትህን ንከስ ብለን ያንን የሚወደዉን ስጋ ያሻንን ያክል ብናሸክመዉ እኛዉ ላይ መልሶ ይጮህብን እንደሆነ ነዉ እንጁ ዉሻ ባለቤቱን በፍጹም አይነክሰም።

Saturday, March 1, 2014

ትግራዊ ማንነት ካለ ኢትዮጵያዊ ማንነትም አለ!


በኣብርሃ ደስታ

"ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊ ማንነት አለኝ" ብዬ ስል የራሴ (የግሌ) ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። የአከባቢ ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። የክልል (የብሄር) ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። ወይም እነዚህ የተለያየ ደረጃ ያላቸው ማንነቶቼ መጥፋት አለባቸው ማለት አይደለም። እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል የራሴን ማንነት አልቀበልም ማለት አይደለም። የራሴ ማንነት ስላለኝ ነው ኢትዮጵያዊ ማንነት ሊኖረኝ የቻለው። እኔ የግል ማንነት ባይኖረኝ ኑሮ ኢትዮጵያዊ አልሆንም ነበር። ምክንያቱም የግል ማንነት ከሌለኝ የሀገር ማንነት ሊኖረኝ አይችልም። እያንዳንዱ ሰው የግሉ የሆነ ማንነት አለው። የግሉ ማንነት ስላለው ነው ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው። ኢትዮጵያዊ ማንነት ራሱ የቻለ የሁላችን የጋራ ማንነት ነው።

የትግራይ ማንነት ካለን የኢትዮጵያ ማንነት ለምን አይኖረንም? "ትግራዮች አንድ ነን" ካልን "ኢትዮጵያውያን አንድ ነን" ብንል ችግሩ ምንድነው? ኢትዮጵያዊነትኮ ከብሄር (ከክልል) ሰፋ ያለ ሀገራዊ ማንነት ነው። ሀገራዊ ማንነታችንን ብንቀበል ችግሩ ምንድነው?

ኢትዮጵያውያን አንድ አይደለንም አትበሉኝ። ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን አንድ ካልሆንን ትግራዮችም አንድ አይደለንም፤ አማራዎችም አንድ አይደለንም፣ ኦሮሞዎችም አንድ አይደለንም። አንድ የሆነ አይኖርም።

"ኢትዮጵያውያን አንድ አይደለንም ምክንያቱም የተለያየ ታሪክና ባህል አለን" አትበሉኝ። ምክንያቱም እያንዳንዱ ግለሰብ፣ አውራጃ፣ ክልል (ብሄር) ወዘተ...ም የተለያየ ታሪክና ባህል ሊኖረው ይችላል። ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህልና ታሪክ ስላለን አንድ አይደለንም ካላችሁኝ ኦሮሞዎችም አንድ አይደሉም እላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም የወለጋ ኦሮሞዎች፣ የሸዋ ኦሮሞዎችና የአርሲ ኦሮሞዎች የተለያየ ታሪክና ባህል አላቸው።

ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህልና ታሪክ ስላለን አንድ አይደለንም ካላችሁኝ አማራዎችም አንድ አይደሉም እላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ወለየዎች፣ ጎጃሞችና ጎንደሬዎችም የተለያየ ታሪክና ባህል አላቸው።

“ምኒልክነትን የጠየቀው” የአድዋ ድል!


“ … ወታደር ባለመሆኔ የጦርነቱን ውሎ ማተት አያምርብኝም፡፡ ያም ሆኖ የአድዋ ድል ዛሬ ብርቅ በሆኑብን ሁለት እሴቶች ረድኤት የተገኘ ይመስለኛል፡፡ እኒህ ሁለት እሴቶች መተባበርና መደማመጥ ናቸው፡፡ ጣልያኖቹ በጊዜው ወደ ጦርነት ሲገቡ ተስፋቸውን የጣሉት በመድፍና በጠመንጃቸው ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ዝነኛ በነበሩበት የውስጥ መቆራቆስ ላይ ነው፡፡ የትግራይ ቅልጥም ሲመታ ሸዋ ያነክሳል ብለው አላሰቡም፡፡ በርግጥም በክፍለ ሀገሮች ውስጥ የተለያዩ ሽኩቻዎች ነበሩ፡፡ እኒህን ሽኩቻዎች አስረስቶ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ለአንድ አላማ ማሠለፍ ምኒልክነትን ይጠይቃል፡፡

“መደማመጥ ያልሁትን ላሳይ፡፡ አባ ዳኘው ከዛሬው የይስሙላ ፓርላማችን በተሻለ ሁኔታ ለልዩነቶች ቦታ የሚሰጥ ተንቀሳቃሽ ምክር ቤት በጦርነቱ ወቅት መፍጠር ችለዋል፡፡ ፀሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ በውጊያው ዋዜማ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ይገልፁታል

‘… አፄ ሚኒልክም በበነጋው ሰራዊቱን የቀኙን በቀኝ፣ የግራውን በግራ አሰልፈው ነጋሪትዋን እያስመቱ ወደሱ ተጓዙ፡፡ ኢጣሊያኖችም ዘበኛው ሲመጣ ባዩ ጊዜ ተመልሰው ወደ እርዳቸው ገብተው ተኙ፡፡

ከዚህ በኋላ ሰራዊቱም እንደ ኤሊ ስንመጣበት ከድንጋይ ይገባል፤ ስንመለስ ይወጣል፤ እንዲህ አርጐ ሊጫወትብን ነውን? ብሎ እጅግ አጥብቆ ተናደደ፡፡ መኳንንቶቹም ተሰብስበው ከዚህ ሰፍረን አድረን በማለዳ እዚያው ካሉበት ከርዱ ድረስ ሄደን እንዋጋለን ብለው መከሩ፡፡ ንጉሠ ነገሥቱም እሺ ብለው ድንኳኑን ለማስመጣት አዘዙ፡፡