Thursday, October 31, 2013

በወያኔ ሎሌነት ከመማቀቅ አንድ ቀን ነፃ ሆኖ መኖር ይሻላል!!!

በወያኔ ግፈኛ ስርአት መከራቸውን ከሚያዩ ዜጎች ውስጥ ራሱ ሥርአቱ ለራሱ መገልገያ የሰበሰባቸውና ያሰማራቸው ዜጎች ይገኙበታል። ከእጅ ወደ አፍ እንኳን ለማትሆን ደመዎዝ በሰራዊቱ ውስጥ በተራ ወታደርነትና በበታች ሹማምንት የሲኦልና የጉስቅልና ኖሮ እንደሚኖሩ እናውቃለን።

በየዞኑና በየወረዳው በካድሬነት ወያኔ ለገላጋይነት ያሰማራቸው ሰራተኞችና የድርጅቱ አባሎች ከህዝቡ የጥላቻ ሰለባነት ባልተናነሰ በኑሮአቸው ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ሳያልፍላቸው እንደሚኖሩ እናውቃለን።

ይልቁንስ የወያኔው የአመራር ጉጅሌ ነገ የት እንደሚያደርሳቸው በማያውቁት ጨለማ ውስጥ ነው የሚዳክሩት ሚስጥርና የዳጎሰ ጥቅም ከነሱ ዘንድ አይደርስም። በቀድሞ ጊዜ የነበሩት የባላባት ሎሌዎች እንኳን ክብር አላቸው።

በዚህ ላይ ሁሉም አስተማማኝ ሎሌ መሆኑን ወያኔ ለማረጋገጫ የሚጠቀምበት ግምገማ አለ። የወያኔ ግምገማ የበታች አባላትና ደጋፊዎቹን በማስፈራራት ያላቋረጠ ድጋፍ እንዲሰጡት የሚያደርግበት በመሰረቱ ከውሻ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የማይለይ ተቋም ነው። የትምህርት እድል የስራ እድገትና የደመወዝ ጭማሪ የወያኔው ጉጅሌ የባርነት መደለያዎች ናቸው።

ግንቦት 7 ከጥቂት ከመንገዳቸው እያወጡ ህዝብ ከሚያሰቃዩት የወያኔ ታዛዥ ሎሌዎች በቀር የሀገርና የወገን ጠላት ናቸው ብሎ አያምንም። ትግላችን ለነሱም ነጻነት ነው። እነዚህ ወገኖቻችን ባገኙት አጋጣሚና እድል ሁሉ ትግሉን ያግዛሉ ብሎም ያምናል። የሚያግዙም አሉ። እርግጥ ነው ባሽከርነት ኑሮ የተንገፈገፉ የሰራዊቱ አባላትና ለህሊናቸው ክብር ያላቸው በርካታ የስርአቱ አገልጋዮች ትግላችንን እየተቀላቀሉ ነው።

ግንቦት 7 ንቅናቄ ዛሬም እንደሁሌው ለነዚህ ወገኖች ኑ ተቀላቀሉን የሚል ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ከነክብራችን ሆነን ሰዎችን ሳይሆን ውዲቱን ሀገራችንና ህዝባችንን በፈቃደኝነት በነጻነት የምናገለግልበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

አንድነት ፓርቲ ስለ ብሄርተኝነት ያለውን አቋም ያውቃሉ?

የፓርተው የአምስት አመት ዕቅድና የስትራቴጂ መፅሀፍ የምከተለውን ይላል፡-
----------------------
በብሄርተኝነት ዙርያ ያለ የተሳሳተ ግንዛቤና እንደምታዎቹ

ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች አገር እንደመሆንዋ የብሔር ብሔረሰቦች መብት መከበር በአገራችን ፖለቲካ ትልቅ ስፍራ እንደያዘ የሚኖር ጉዳይ ነው፡፡ የብሄር ብሄረ ሰብ መብት መከበር በቋንቋ የመናገር መብት ብቻ አይደለም' በፖለቲካ የመወከልና የመደመጥ፤ በኢኮኖሚና በማሕበራዊ ዘርፍ አድልዎን የማጥፋትና ፍትሕንና እኩልነትን የማንገስ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ስስ ጉዳይ በሚገባ ሊያዝ ይገባዋል፡፡

የብሄር ጉዳይ አያያዝን በሚመለከት በአገራችን ሁለት ጫፍ የረገጡ አዝማምያዎች ይታያሉ፡፡ አንዱ ጫፍ ለኢትዮጵያ አንድነት እንጨነቃለን ከሚሉ ግን የብሔር መብትን ለመቀበል ከሚቸገሩ ወገኖች የሚመጣ ሆኖ ጉዳዩን የማሳነስና የማጣጣል ብሎም የብሔር መብት ጥያቄ የሕዝብ መብት ጥያቄ መሆኑን የመካድ ዝንባሌን የሚያጠቃልል ነው፡፡ አንዳንድ ወገኖች የሕዝብና የአገራችን አንኳር ጉዳይ መሆኑን በመቀበል ፈንታ የየብሄሩ ልሂቃን የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት ብለው የፈጠሩት ችግር አድርገው ያነብቡታል፡፡ ልሂቃኑ አይለጥጡትም ማለት አይቻልም፡፡ ሆኖም ግን የጉዳዩን ክብደትና በአገራችን ፖለቲካ ውስጥ ያለውን ስፍራ ለማሳነስ ምክንያት ሊሆን አይገባም፡፡

ሁለተኛው ጽንፍ የረገጠው አመለካከት የብሔር ብሔረ ሰብ መብትን ለማስጠበቅ እንታገላለን ከሚሉ ወገኖች የሚመጣና የብሄር መብት መከበርን ከአገር አንድነትና አብሮነት ነጥሎ የሚመለከት ዝንባሌ ነው፡፡ ከእነዚህ ወገኖች ውስጥ ጉዳዩን በማክረር ውጤቱ መገንጠል እንዲሆን የሚፈልጉ አሉ፤ በግልጽ መገንጠልን እንደ ዓላማ ያነገቡም አሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች እኛ ያልነው ካልሆነ በማለት አንድነትን በመያዣነት ያግቱታል (ሆስቴጅ ያደርጉታል)፡፡ ሁሉም የየራሱን መብት እያጠበቀና እያከረረ ከሄደ እያንዳንዱ ብሄረሰብ ከአጠገቡ ካለው ሌላ ብሄረሰብ እየተናከሰ እንደሚኖርና ከአንድነቱ መፍረስ ጋራ ሰላምም እንደሚደፈርስ ያለመገንዘብ ችግር አለባቸው፡፡

Monday, October 28, 2013

ኢህአዴግ የዘራውን አጨደ፣ ተጠያቂው ማን ነው?

እሳት አስነሳችሁ በሚል እስሩ ቀጥሏል



በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ተቃውሞ ቢያቀርቡም የኢህአዴግን ጆሮ ማግኘት ያልቻሉ ተበዳዮች ርምጃ ወሰዱ። ሕዝብ ወዶና ፈቅዶ ያልተቀበለው ኢንቨስትመንት ከዘረፋ ተለይቶ እንደማይታይ የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል። ውድመት የደረሰበት የህንድ ኩባንያ በልማት ባንክ ላይ ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋት አለ። ለደረሰው ጉዳት “ተጠያቂው ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ተነስቷል። በጥርጣሬ የሚታሰሩ መበራከታቸው በክልሉ ባሉ ተመሳሳይ የእርሻ ኢንቨስትመንት ባለቤቶችን ስጋት ላይ ጥሏል።

ሻይ ቅጠል ለማልማት የተፈጥሮ ጥብቅ ደን እንዲያወድም የተፈቀደለት ቬርዳንታ ሀርቨስት የተባለ ኩባንያ በከፍተኛ ወጪ ያለማውና ለመለቀም በደረሰ ምርት ላይ ማንነታቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች እሳት ለቀውበታል። ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓም ደረሰ በተባለው ቃጠሎ ኩባንያው የደረሰበት ሊሳራ እስከ 80 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ አስታውቀዋል።

አንጋፋ እድሜ ጠገብና ረዣዥም የተፈጥሮ ደን በመጨፍጨፍ ጣውላ እያመረተ ሲቸበችብ የነበረው ኩባንያ ሙሉ ንብረቱና ከፍተኛ መጠን ያለው የጣውላ ምርት ከተለያዩ ማሽኖች ጋር ወድሞበታል። የአካባቢው የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኩባንያው ላይ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ለመሰብሰብ የደረሰውን የሻይ ቅጠል ማሳ አጋይቶታል።

በጋምቤላ ክልል በመዠንግር ዞን፣ በጎደሬ ወረዳ በጉማሬና በካቦ ቀበሌዎች የሚገኝ 5000 ሄክታር በደን የተሸፈነ መሬት በኢንቨስትመንት ስም እንዲሸጥ መወሰኑን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ አሰምተው ነበር። በወቅቱ ውሳኔውን “በባዕድ ወራሪ ሃይል እንኳን የማይፈጸም” በማለት የተቹና ቅሬታቸውን የገለጹ ነበሩ።

ሙሉ በሙሉ በደን የተሸፈነ 3012 ሄክታር ድንግል ለም መሬት በሄክታር111 ብር ሂሳብ ለ50 ዓመት የሊዝ ኮንትራት የተሸጠለት ይህ ኩባንያ ጥብቅ ደኑን ከማውደሙ በፊት ውሳኔው እንዲጤን የአካባቢው ህዝብ በወኪሎቹ አማካይነት ለፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ጥያቄ አቀርበው ነበር። በወቅቱ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድርጊቱን በመቃወም የሚከተለውን ጽሁፍ አትሞ ነበር። ሰሚ ባለመገኘቱ የተፈራው ደረሰ።

Sunday, October 27, 2013

የኢዴፓ ገበና ሲገለጥ (ሊነበብ የሚገባው ደባ)

የልደቱ አያሌው ኢዴፓ በየትኛው ሞራሉ ነው ተቃዋሚውንም ይሁን ገዢውን ፓርቲ የሚተቸው??

በምንሊክ ሳልሳዊ


  • የአቶ ልደቱ አያለውን መጽሃፍ የጻፈው በወያኔ ልዩ ትእዛዝ አቶ ገነነ አሰፋ ነው::
  • ዶክተር በየነ ጴጥሮስ እና ሻለቃ አድማሴ መላኩ በአቶ መለስ ትእዛዝ የወር ደምወዝ ነበራቸው::
  • ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢዴፓ ህልውና አያምንም::ዘላለም ህዝቡ ኢዴፓን በበጎ መንፈስ አያየውም::
  • በአሁን ሰአት ለተፈጠረው ኢሕኣዴጋዊ አክራሪነት እና የፖለቲካ ጽንፈኝነት ተጠያቂው ኢዴፓ እና አመራሩ ናቸው::


ኢዴፓ ብሎ ራሱን የሚጠራው በኢሕኣዴግ የጎለበተው ድርጅት ባካሄደው ስብሰባ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እና ገዢውን ፓርቲ እንደተቸ እየሰማን ነው:: ኢዴፓ የ97 ምርጫ የህዝብን ድምጽ አፈር የከተተ እና ከገዢው ፓርቲ ጋር መሰሪ ተግባራትን በማከናወን የቅንጅት አመራርን ለእስር ቅንጅትን ደግሞአላማውን በማኮላሸት ድባቅ እንዲመታ ያደረገ ታማኝ ቅጥረኛ በራሱ አጠራር ተቃዋሚ ፓርቲ ነው::ኢዴፓ ለዚህ ላደረገው አፍራሽ ተልእኮ አመራሮቹን ሳይታሰሩበት የፓርላማ ወንበር እና ጉርሻ በማግኘት ተለጥጦ እስከዛሬ ድረስ በገዢው ፓርቲ አመራሮች እና ካድሬዎች የአንበሳነት ቡራኬ እየተሰጠው ይገኛል::

ኢዴፓ በተለያዩ ከገዢው ፓርቲ በተመደቡ የደህንነት ሴረኞች እና ከመንግስት ስልጣን ወደ ፓርቲ ስልጣን በተለወጡ ሰዎች እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች በኢንቨስትመት ስራ ለይ የተሰማረን ነን የሚሉ ከባለስልታናት ጋር በሙስና የተጨማለቁ ሰዎች የሞሉበት በተቃዋሚነት ስም የሚያላዝን የገዢው ፓርቲ አጋር የፖለቲካ አራጋቢ ነው::የገዢውን ፓርቲ ሁኔታ ገመገምኩ የሚለው ኢዴፓ ገዢው ፓርቲ ከፕሮፓጋንዳ ባለፈ ለዴሞክራሲ ሥርዓት መጠናከር ምንም ዓይነት ተጨባጭ ዕርምጃ እየወሰደ እንዳልሆነና ይህም በአገሪቱ የጽንፈኝነት ፖለቲካና አክራሪነት የበለጠ እየተጠናከረ እንዲመጣ አድርጓል ማለቱ ምን ለማለት እና ማንን ለማጭበርበር ፈልጎ አሊያም በየትኛው ሞራሉ ነው ይህንን ሊል የሚችለው ... በሃገሪቱ በ1997 እና ከዛ በኋላ የተገኙ የተቃዋሚ ድሎች እንዲኮላሹ ከማድረጋቸውን በላይ የድርጅቱ አመራሮች ሕወሓት ከመደበላቸው ከአቶ ስብሃት ነጋ በሚወርድ ትእዛዝ የዲሞክራሲ ጭላንጭሉ ከናካቴው እንዲጠፋ እና አሁን ላለንበት የጭለማ አፋኝ ስርኣት እንድንዳረግ አስታውጾ አበርክቷል::በአሁን ሰአት ለተፈጠረው ኢሕኣዴጋዊ አክራሪነት እና የፖለቲካ ጽንፈኝነት ተጠያቂው ኢዴፓ እና አመራሩ ናቸው::

አቶ ልደት አያሌው ኢዴፓን ይመራ በነበረበት ጊዜ በየወሩ 5000 ብር ይከፈለው ነበር እንዲሁም ሙሼ ሰሙ ዶክተር ሶፊያ እና አቶ አብዱ .. እንዲሁ ደሞወዝ ነበራቸው:: አቶ ልደቱ የደህንነት ሚኒስትሩ የነበሩት አቶ ገብረመድህን እስከ 1993 ድረስ ደሞዙን በመቀበል የቆየ ሲሆን ከዛ በኋላ ደሞዛቸውን በበላይነት የሚያገኙት አሁን በሙስና እስር ላይ ከሆነው የደህንነቱ አማካሪ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ነበር::በ97 ላደረጉት ውለታ ከስድስት ሚሊዮን ብር ስጦታ አግኝተዋል::
ለኢዴፓ አመራሮች ያዘጋጁትን መጽሃፍ ; ንግግር ; ማንኛውንም አርቲክል የጻፈው የገነት ዘውዴ ውንድም አቶ ገነነ አሰፋ ነበር ለዚህም በአቶ መለስ ዜናዊ ትእዛዝ ትልቅ የገንዘብ ጉርሻ ተሰቶታል::ታሪካቸው የማያልቀው ተቃዋሚ ነን የሚሉት የፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ውስጥ ውስጡ እንዲያሽመደምዱ በወቅቱ የፓርላማ አባል የነበሩት ሻለቃ አድማሴ መላኩ እና ዶክተር በየነ ጴጥሮስ ከአቶ መለስ ዜናዊ በተሰጠ ልዩ ምስጢራዊ ትእዛዝ በየወሩ የደህንነቱ አማካሪ የአሁኑ እስረኛ ወልደስላሴ ደምወዝ ይከፍላቸው ነበር::

ኢዴፓ አሁንም በህዝብ ፊት ቆሞ የህዝብን ማንነት ለመካድ እና ራሱን እንደ ህዝብ ፓርቲ ለማሳየት የሚቧጥጠው ነገር እንደማይሳካለት ቢያውቅም ከወያኔ በሚወርድለት ትእዛዝ በሙስና የተዘፈቁ የኮሌጅ ባለቤት የሆኑ የአማራ ክልል ግለሰብ አምጥቶ ሾሟል::የጸረ ሽብር ህጉን እንደግፋለን የሚሉት ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ጋር በእከክልህ እከክልኝ ኢንቨስተር የሆኑት የኢዴፓ አዲስ ሊቀመንበር ሙሰኛው አቶ ጫኔ ከበደ በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች ጋዜጠኞች እና የሃይማኖት ሰዎች አሸባሪ ናቸው ብለው የሚያምኑ ሰው ናቸው::

እንደ ኢዴፓ/ኢሕኣዴግ እምነት ተቃዋሚዎች የኢዴፓን የተቃዋሚነት ሚናና ህልውና የካዱና፣ በሕዝቡ ዘንድ በበጎ መንፈስ እንዳይታይ ሆን ብለው ሴረኛ አሉባልታዊ ዘመቻ የሚያካሂዱ መሆናቸውን መገንዘቡን ገልጿል፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች የወቅቱ ትግል ተጠናክሮ ለድል እንዳይበቃ ዋነኛ እንቅፋት መሆናቸውን ገልጾ ሕዝቡ የእነዚህን ተቃዋሚ ኃይሎች ትክክለኛ ማንነት እንዲገነዘብ ጠይቋል፡፡...ኢዴፓ ለገዢው ፓርቲ ታማኝነቱን ያሳየበት ይህ አባባል አሁንም ቢሆን ኢዴፓ ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢዴፓ ህልውና አያምንም::ህዝቡ ኢዴፓን በበጎ መንፈስ አያየውም:: ኢዴፓ 200 አመት እንደ አዲስ እየተወለደ ቢሰራ ተቀባይነት አያገኝም::በሃገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ ትግሉን አፈር እያበሉት ያሉት እንደ ኢዴፓ ያሉ ቅጥረኞች መሆናቸውን በአደባባይ ያየነው ጉዳይ ነው::ማንኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ ከኢዴፓ ጋር በትብብር እንደማይሰራ የታወቀ ሲሆን ኢዴፓ ራሱ ራሱን መርምሮ ከቅጥረኝነት ወደ ተቃዋሚነት መሸጋገር የራሱ ድርሻ እንጂ ለሌሎች የሚሰጠው መመሪያ አይደለም:: ሌሎች ተቃዋሚ እንደሆኑ ራሳቸውን ያውቃሉ::

የስልጣን ጥመኝነት ያለበት የኢዴፓ አመራር በየትኛው ሞራሉ ህዝብ ፊት እንደሚቀርብ ባይታወቅም በፖለቲካ እፍረት የማይሰማው ቅጥረኛ ፓርቲ መሆኑን ግን በይፋ ያስመሰከረ እና የሆዳሞች እና የሙሰኞች ስብስብ እንደሆነ ማናችንም የምንመሰክረው ሃቅ ነው::

Thursday, October 24, 2013

ሕዝባዊ እምቢተኝነት በውጭ አገር፤ እንዴት?


ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሁለገብ ትግል ወያኔ ማስወገድ ይገባል ብሎ የሚያምና ለዚህም የሚታገል ድርጅት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል ሰላማዊም ሰላማዊ ያልሆኑም የትግል ስልቶችን መጠቀም ማለት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም የሚደረጉ ትግሎች ማለት ነው።


ከዚህ አንፃር በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሚና ምን ሊሆን ይገባል?

በግንቦት 7 እምነት በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በድጋፍ ሰጭነት ሳይወሰኑ የትግሉ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች መሆን ይኖርባቸዋል። በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በወያኔ ጥቅሞችና ተቋማት ላይ በማመጽ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አርዓያ መሆን ይኖርባቸዋል።

በዚህ ረገድ የተጀመሩ አበረታች ጥረቶች አሉ፤ ለምሳሌ:

1. ወያኔ ሙስሊሞችን ከክርስቲያኖች ለማጣላት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን “እንቢ አንጣላልህም” ያሉት መሆኑ የሚያኮራ ነው። ወያኔ ከጠበቀው በተቃራኒ የሁለቱም ሃይማኖቶች መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ መታየቱ ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ነው። አብሮነታችንን ማጎልበትና ይህንን በአደባባይ፣ በአዳራሾች፣ በቴሌቪዥን መስኮቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳየት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። ውጭ የተጀመረው አገር ቤት መዳረሱ የማይቀር ነው። ይህ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርብናል።

2. ወያኔ በአባይ ግድብ ስም በውጭ አገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በርከት ያለ ገንዘብ እንደሚያገኝ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን “ከአባይ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይገደብ” “ከአባይ በፊት ሙስና ይገደብ” እያሉ ወዋጮዎቹን እንቢ ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የታየው ጽናት በጣም አበረታች ነው። የወያኔ ሹማምንት በአባይ ጉዳይ እንኳንስ ገንዘብ ስብሰባም ሊሰበሰቡ አልቻሉም። ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

3. ኢትዮጵያዊያን በስፖርትና በኪነጥበባት መስኮች የሚያደርጓቸው መሰባሰቦች ለትግሉ ትልቅ እገዛ ይሰጣሉ። የኢትዮጵያ ስፓርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA) ከወያኔና ከወያኔ ሸሪክ ቱጃር ጋር ያደረገው ትንንቅ የሚያኮራ ነው። በርካታ ኢትዮጵያዊያን አገር፣ ነፃነት፣ ክብር ይበልጥብኛል ብለው የቀረቡላቸውን አጓጊ ማባበያዎችን “እንቢ” ብለዋል። ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

Wednesday, October 23, 2013

ስብሃት ነጋ በመርሳት ችግር (ዳመንሺያ) በሽታ ተጠቂ እንደሆኑ ተገለጸ !

(ዘ-ሐበሻ) አዛውንቱ የሕወሐት መስራች ስብሃት ነጋ በመርሳት በሽታ (ዳመንሺያ) በሽታ ተጠቂ እንደሆኑ ለአዛውንቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገለጹ። ምንጮች በተለያዩ ሁኔታዎች እንደገለጹት ስብሃት በየመድረኩ አንድ ጊዜ የተናገሩትን በሌላኛው ጊዜ የማይደግሙት፣ ወይዘሮ አዜብን ጨምሮ ከተለያዩ የኢሕአዴግ ሰዎች ጋር የሚላተሙት ወይም ጥያቄ ሲጠየቁ አላስታውስም የሚሉት የዳመንሺያ ተጠቂ በመሆናቸው መሆኑን የህክምና ባለሙያዎችን ጥናት ያሰባሰቡት እነዚህ ምንጮች ገልጸዋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የሚፈልጉት እነዚሁ ምንጮች አቶ መለስ በሞቱበት ወቅት 33 ጀነራሎች ከተሾሙ በኋላ መሾማቸውን በሰሞኑ ቃለምልልሳቸው ላይ አላውቅም/አላስታውስም/ ማለታቸውንና ሌሎችንም በመጥቀስ፤ እነዚሁ ምንጮች ከህክምና ባለሙያዎች እንዳገኙት ጥቆማ “የመርሳት ችግር (ዳመንሺያ) ምንድን ነው?” የሚለውን ሲያብራሩ፦

“ከባድ  የመርሳት    ችግር  ይህ   ነው   የሚባል   በሽታ     አይደለም።   ይልቁንም     አእምሮን  በሚያውኩ የተለያዩ እክሎች   ምክንያት     የሚፈጠሩ   የህመም   ምልክቶች አጠቃላይ  መገለጫ     ነው፡፡  የከባድ    የመርሳት  ችግር ተጠቂዎች    አእምሯዊ    አተገባበራቸው  እጅጉን    በመስተጓጎሉ  የእለት     ተለት     ተግባራቸውና    ከሰዎች ጋር    ያላቸውን    ግንኙነት  ይጎዳል፡፡    እንዲሁም ግልፍተኝነት፣   የቀን   ቅዠት እና     በሌለ  ነገር    ማመን የመሳሰሉት   ሁኔታዎች     ስለሚያጋጥሟቸው  ለከባድ    ባህሪያዊ   ችግሮች   ሊዳረጉና     ማንነታቸውን   ሊያጡ  ይችላሉ።  የማስታወስ   ችሎታ    መቀነስ     የዚህ   ህመም    የተለመደ  ምልክት ቢሆንም የማስታወስ ችሎታው የቀነሰ ሰው በሙሉ የከባድ የመርሳት ችግር ተጠቂ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡” ይላሉ።

እነዚህ ችግሮች በስብሃት ላይ በየጊዜው እንደሚስተዋልባቸው የሚጠቅሱት እነዚሁ የቅርብ ምንጮች ”በሽታውን የሚቀሰቅሱ ነገሮች ምንድን ናቸው?” የሚለውን ሲያብራሩም “ለከባድ የመርሳት ችግር የመጋለጥ እድልን ከፍ ሊያደርጉ  ከሚችሉ ሁኔታዎች ውስጥ ቀጥሎ የተጠቀሱት ይገኙበታል፡-

• ከዘር የመጣ ከሆነ

• በአንጎል ውስጥ የሚከሰቱ እክሎች ካሉ

• የደም ዝውውርንና ወደ አንጎል የሚያመራውን ጤነኛ የደም ዝውውርን የሚያውክ በሽታ ከተከሰተ

• የኤችአይቪ ቫይረስ በደም ውስጥ መኖር (በተለይ ኤችአይቪ በደሙ ያለበት ሰው የኤድስ ታማሚነት ደረጃ ከደረሰ)” በማለት ይጠቅሳሉ።

የህክምና ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ የሚገልጹት እነዚሁ ምንጮች “የከባድ መርሳት ችግር ምልክቶች ምንድን ናቸው?” የሚለውን ሲገልጹም “አብዛኛውን ጊዜ የማስታወስ ችሎታ መቀነስ ከባድ የመርሳት ችግር ቀዳሚና በጉልህ የሚታይ ምልክት ነው፡፡

የሚከተሉትም ሌሎች ምልክቶች ናቸው፡-

• የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ማስታወስ ማዳገት • በደንብ የሚያውቋቸውን ሰዎችና ቦታዎች መዘንጋት

• ሀሳብን ለመግለጽና ቁሶችን በስማቸው ለመጥራት ትክክለኛ ቃላትን ለማግኘት በእጅጉ መቸገር

• የሂሳብ ስሌቶችን መስራት ማዳገት

• እቅድ ለማውጣትና ስራን ለመፈጸም መቸገር

• ለመወሰን መቸገር፥ ለምሳሌ በአጣዳፊና አደገኛ ሁኔታ ወቅት ምን ማድረግ እንደሚገባ አለማወቅ

• የራስን ባህሪይና ስሜት ለመቆጣጠር መቸገር፤ለምሳሌ ግልፍተኛ ወይም ቁጡ መሆን

• አዘውትሮ መደበት

• ራስን አለመንከባከብ፤ ለምሳሌ የግል ንጽህንናን አለመጠበቅ” ናቸው ይላሉ።

Ethiopians in Norway vowed to stand beside Ginbot 7 popular force

On 28th of September 2013, successful fundraising was conducted for Ginbot 7 Popular Force (G7pf), recently established and struggling against the woyane junta. The fundraising event, staged from 4:00 – 12:00 p.m. local time, was coordinated by a taskforce established by Democratic Change in Ethiopia Support Organization in Norway (DCESON). The event was able to attract many participants from all over Norway and other European countries. The event was one of the success stories in the history of fundraising in terms of both participation and raised amount of money.

The official announcement of the founding of the Ginbot 7 people`s force has been a positive development and was welcomed by most Ethiopians living in Norway. Ginbot 7 popular force has added a momentum to the struggle and elevated the moral and hope of many Ethiopians living in Norway. The formation of this force marks a new and decisive phase in the struggle against the racist and fascist rule of the Tigray People`s Liberation Front (TPLF) in Ethiopia. Hence, the enthusiasm, inspiration and increased degree of engagement that were witnessed during the event reflected the aspirations and commitments of the participants. Besides, it shows that the force has been able to garner an increasing and widespread support in Norway and inevitably in other parts of the Diaspora at the moment.

The DCESON has been supporting the struggle for democracy, freedom and justice in Ethiopia starting from the pre-kinijit time. The current fundraising event is purely the initiative of DCESON and it was conducted by forming a taskforce consisting of its committed members. DCESON took this mission as a national and timely one and undertook extensive planning and mobilization tasks. On the other hand, the agents of the TPLF and their supporters made futile attempts and campaigns to undermine and hamper this event. This shows that the formation of an armed Ethiopian resistance force has frightened and alarmed the TPLF camp and regime.

Ato Andargachew Tsege, the secretary of the Ginbot 7 Movement for Justice and Freedom and Democracy and Commander Assefa Maru, chief of Ginbot 7 Popular Force, were the guests of the event. The guests received a standing ovation in the event hall which was decorated with the Ethiopian flag and symbols of the popular force.

The event had a series of programs which went on as planned. After the program of the day was announced by Ato Abi Amare, leader of the PR group, opening remarks were given by preventative of the taskforce, Ato Worku Tadesse. A keynote address was given by the chairperson of the DCESON Ato Dawit Mekonnen. Representatives of the Ethiopian asylum seekers` association, w/t Sara Girma, DCESON women’s branch, w/o Guenet Worku, Chairperson of DCESON-Women’s section, W/t Lemlem Andarge, DCESON-Bergen branch, Ato Shume Werku gave speeches to the audience. In addition, W/t Kalkidan Kassahun from Steinskjer, Ato Sally Abraham from Vestness, also held speeches that focused on the significance of the event and the need for increased struggle against the TPLF rule in Ethiopia.  Moreover, the representative of the Tigray People Democratic Movement (TPDM) in Norway, Ato Haile Asmamaw, addressed the event and played the audiovisual message to all Ethiopians sent from the field.

The younger members of the DCESON in fatigues were a unique addition to the event.

Ato Andargachew outlined the tasks and current activities of the force and presented footage showing the training and preparations of the force out in the field. He also mentioned the cooperation with the Tigray People`s Democratic Movement (TPDM), hardships the members of the force undergo and the sacrifices they pay.

Commander Assefa Maru spoke on his part about the objectives, tasks and missions of the force. In his speech, he explained the importance of an armed force and resistance to remove the TPLF from power and pave the way for a democratic and an all-inclusive political system in Ethiopia. He underscored the commitment of the force to achieve its goal and necessity of offering help and support to the force.

The audience learnt from the two guests that Ginbot 7 Popular Force is established by freedom-loving Ethiopians, including youngsters and intellectuals and it is working to remove TPLF by force and to create a peaceful transition period enabling establishment of non-partisan and constitutional defense, police, security, judiciary, etc. which are crucial for a healthy playground for different political parties aspiring power in the country. Among the current G7PF members are many intellectuals who joined this force abandoning their relatively comfortable living, families and professional jobs. This is one of the peculiarities of the G7PF compared to traditional armed struggles in Ethiopia where mainly farmers and other non-intellectuals comprise the main components of the foot soldiers. Presence of skillful leadership on the ground is told to highly assist G7PF members equip not only with armament but also with political, social, cultural knowledge about Ethiopia which is important to build a force that understands why and whom they are fighting for and paying sacrifices.

Food and refreshments were served during the event. Ethiopian music and live performances were staged to make the event entertaining and enjoyable. A short drama showing the atrocities of the TPLF regime in Ethiopia, written by w/t Mihret Ashine, was also presented.

The latter parts of the event were devoted to auctions meant for raising money as planned. The inspiration and enthusiasm of auction hosts, Ato Million Abebe and Ato Amsal Kasie, was the driving force for the high sum of money raised during the auction. The financial contributions of the participants and others, including attendants of the Ethiopian Current Affairs Discussion Forum (ECADF) were high and laudable.

The successful staging of the event was made possible through the cooperation and
contributions of the participants as a whole. This event demonstrated what Ethiopians in the diaspora can achieve through cooperation and working together for a common goal.

The fundraising taskforce and DCESON extend their heartfelt thanks and appreciation to all the participants, contributors and huge thanks to all Ethiopians from all over Norway.

Ginbot 7 Popular Force fundraising taskforce in Norway

October 22, 2013

Tuesday, October 22, 2013

Ethiopia’s jailed journalists seek international support


“You may be really surprised by our nonsensical imprisonment,” Reeyot Alemu wrote in a letter recently smuggled out of a prison in Addis Ababa, “The international community should be aware of the objective reality that we are burdened to live a life which is inexplicable to contemplate, let alone easily engage with.”


In 2011, Ms. Reeyot, a schoolteacher, columnist and political activist, was convicted of conspiring to commit terrorist acts across Ethiopia and sentenced to 14 years in prison; her sentence was subsequently reduced to five years. At present she and at least six other journalists remain imprisoned, while at least 49 journalists have fled the country as a consequence of government intimidation according to the Committee for Protection of Journalists (CPJ).

Ms. Reeyot was awarded the UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize in 2013 and the International Women’s Media Foundation’s Courage in Journalism award last year, Woubshet Taye, sentenced to 14 years, was recently awarded the CNN Free Press Africa award this year, while Eskinder Nega, sentenced to 18 years on terror charges was awarded a PEN America press freedom award in 2012.

The Ethiopian government denies it is stifling free expression, and maintains that the three prisoners have not been targeted for their writings, but rather for associating with terrorists, and have condemned international campaigns demanding their release as an attack on Ethiopia’s sovereignty.

“No one convicted by a sovereign nation as a terrorist could be glorified and awarded with awards. That is an insult to the sovereignty of the nation,” said Communications Minister, Redwan Hussein in an interview, "They have not been accused for their writings...it is because they were guilty of working with terrorists."

The alleged attacks on Ethiopia’s press, and the government’s denials, are part of a broader struggle between the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF), that has ruled the country since 1991 and controls 99 per cent of the current parliament, and besieged opposition groups that have variously allied with the media, international rights groups and the diaspora.

Rights groups have criticized the 2009 anti-terrorism law, under which most journalists have been prosecuted, for its excessively expansive definitions of terrorism and support to terrorists.

Reeyot Alemu was born on June 21, 1980, the eldest of Alemu Gobebo Anjejo’s three children.  “She worked as columnist for Feteh newspaper and was editor of Change magazine,” Mr. Alemu said, “She wrote on gender equality, and wrote against the government and corruption.”

A retired lawyer and opposition politician, Mr. Alemu carries a folder familiar to those with imprisoned loved ones: charge-sheets, a short biography, and a well-thumbed copy of the Constitution with the section on freedom of expression marked by three asterisks.

Monday, October 21, 2013

ተገዥነታችን ለሕዝብና ለሕግ እንጅ ለአምባገነኖች ማስፈራሪያ አይደለም!!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)


ተገዥነታችን ለሕዝብና ለሕግ እንጅ ለአምባገነኖች ማስፈራሪያ አይደለም!!!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በሀገራችን ላይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲሰፍንና ፍትሃዊነት እንዲኖር በቁርጠኝነት እየታገለ ይገኛል፡፡ በትግሉ ውስጥም ፓርቲያችን የተጋረጡበትን ፈተናዎች እየተወጣና የሚከፈለውን ዋጋ እየከፈለ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ በመቀጠል ለህዝቡ ያለውን ታማኝነት እያረጋገጠም ነው፡፡

ፓርቲያችን በመላ ኢትዮጵያ ያለውን አደረጃጀት በመጠቀምና ሕዝቡን በማሳተፍ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በማካሄድ የመጀመሪያ ዙር የሆነውን ሰላማዊ ትግል ለማጠናቀቅ ችሏል፡፡ የሚልዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን ያነገበ ሲሆን እንደ ሁልጊዜውም ፓርቲው ሰላማዊነቱን በጠበቀ መልኩ በቁርጠኝነት ንቅናቄውን በታቀደለት መሰረት አካሂዷል፡፡ ወደፊትም ይህንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

ኢህአዴግና መሪዎቹ መንግስት እንደመሆናቸው መጠን በሰላማዊ መንገድ ለምንንቀሳቀስ ፓርቲዎች ድጋፍና ትብብር ማድረግ ሃላፊነታቸው ቢሆንም ከዚህ በተቃራኒ በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀስን ያለን ፓርቲዎችን ለማጥፋት ቀን ከሌሊት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ልክ ከዚህ በፊት ሲያደርጉት እንደነበረው ባልዋልንበት ዋሉ፣ ባልተገኘንበት ተገኙ… በማለት ህዝባዊ መሰረታችን ጥርጣሬ ላይ እንዲወድቅ ለማድረግ ያገኙትን አጋጣሚ ሁሉ ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህ አባባላችን ጥሩ ማስረጃ የሚሆነን ባለፈው ሳምንት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በመሪ ደረጃ በማይጠበቅ መልኩ ህጋዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴችንን እሳቸው ከፈለጉት አካል ጋር በማገናኘት ስም ለማጥፋት መሞከራቸው ነው፡፡

አቶ ኃይለማርያምም ሆኑ መንግስት የሆነው ፓርቲያቸው ለሚነሱ ሀገራዊ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠትና በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር በርን ከመክፈት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ ለጥያቄ አቅራቢዎች የተለየ መልክ ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት የምናውቀውና የነበረ አሮጌ መንገድ ነው፡፡

ፓርቲያችን ህዝባዊ ንቅናቄ ያደረገው ህጋዊ አግባቡን ጠብቆና የራሱን አጀንዳ ቀርፆ ነው፡፡ ጠ/ሚንስትሩ የራሳቸው አጀንዳ የላቸውም፤ የሻዕቢያ መልክት አድራሾች ናቸው ወዘተ ያሉበት ድፍረት የራሳችን አጀንዳ እንዳለን ጠፍቷቸው ሳይሆን ሆን ብለውና አቅደው ስም ለማጥፋት፣ ህዝቡ ውስጥ ጥርጣሬ ለመጫር በመፈለጋቸው ብቻ ነው፡፡ እኛ ተላላኪነታችን ለኢትዮጵያ ህዝብና ይጠቅማል ብለን ለቀረፅነው የፖለቲካ ፕሮግራም ብቻ ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱን ስም ማጉደፍም ፓርቲያችን በቸልታ አይመለከተውም፡፡ ስለዚህ አቶ ኃይለማርያም ከባለፈው ስህተታቸው በመማር ከአጉልና ማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አጥብቀን እንመክራለን፡፡

የሙስሊም ወገኖችን ጥያቄ በተመለከተ ፓርቲችን ያለው አቋም ግልፅ ሲሆን አሁንም ጥያቄያችው በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ መመለስ፤ ዜጎች የመብት ጥያቄ ሲያነሱ መፈረጁ ይቁም፤ ካላግባብ የሃማኖት ነፃነት ጥያቄ ስላነሱ ወደ እስር ቤት የተወረወሩ ዜጎች ባስቸኳይ ይፈቱ የሚል ነው፡፡ በተጨማሪም ስርዓቱ ካላግባብ ያሰራቸው ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች ባስቸኳይ ይፈቱ ብለን እንጠይቃለን፡፡ ወደፊትም ይህንን ጥቄያችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ እኛ እያልን ያለነው ከኢ-ፍትሃዊነት ጋር አንደራደርም፤ አንቀበለውም ነው፡፡ ስለዚህ ፓቲያችንን ከሙስሊም ወገኖች ጥያቄ ጋር በማያያዝ ትርፍ ፍለጋ መሯሯጥ ስህተት ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው፡፡

አቶ ኃይለማርያም በህገ መንግስቱ በግልጽ የተቀመጡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብትን በአደባባይ የጨፈለቀው ንግግራቸው ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ ነው፡፡ በቂ ጥበቃ የለንም በሚል ተልካሻ ሰበብ የዜጎችን መብት መንጠቅ አይቻልም፡፡ በቂ ጥበቃ ማድረግ ያልቻለ መንግስት ስልጣኑን ለህዝብ በማስረከብ ይቅርታ ጠይቆ መሄድ እንጅ ከአሁን በኋላ መብታችሁን አታገኟትም በማለት መዛት ትዝብት ውስጥ የሚጥል ድርጊት ነው፡፡

ስለዚህ ፓርቲያችን አንድነት አሁንም ተገዥነቱን ለህዝቡና ለህግ አድርጎ በአምባገነኖች ዛቻ ሳይበረግግ፤ ዘር፣ ፆታ፣ ሀይማኖት፣ ቀለም ሳይለይ ዜጎች የሚያነሱት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች እንዲመለሱ፤ የመንግስት በሐይማኖት ጣልቃ ገብነትም እንዲቆም ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያረጋግጣል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ፓርቲያችን የአፍሪካ መሪዎች ብዙ መፍትሄ ፈላጊ ችግሮች ባሉባት አፍሪካ ተሰብስበው እንግደል፣ እንሰር፣ እንጨፍጭፍ፣ ዘር እናጥፋ፣ ዜጎቻችንን እናሰቃይ ግን መታሰርም መከሰስም የለብንም በሚል የያዙት አቋም አሳፋሪና ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ ሕግ እየጣሱ በህግ አለመጠየቅ አይቻልም፡፡ ዘር እያጠፉ ያለመታሰር መብት አይኖርም፡፡ ማንም ሰው ከህግ በላይ የመሆን መብት የለውም፡፡

የአፍሪካ መሪዎች ተሰብስበው ማለት ያለባቸው አይሲሲ ሊከስሰን አይገባም ሳይሆን የዜጎቻቸውን እንባ ማበስ ነው፡፡ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጡ መጣር ነው፡፡ መሳሪያና ጉልበት የችግሮች መፍቻ መሆናቸው እንዲያበቃ የሰለጠነ መንገድ መከተል ነው፡፡ የሚያስከስሳቸውና የሚያሳስራቸው ስራቸው እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ስለዚህ ፓርቲያችን አሁንም ሆነ ወደፊት በዜጎቻቸው ላይ ግፍና ሰቆቃ የሚፈፅሙ ሁሉ ሳይውል ሳያድር ወደ ፍርድ መቅረብ አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡ አንዳንድ የአፍሪካ መሪዎች አይሲሲን በተመለከተ የሚያራምዱት የአትክሰሱን አቋም ፓርቲያችን አይቀበለውም፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ነሐሴ 11 ቀን 2005 ዓ.ም

አዲስ አበባ

Sunday, October 20, 2013

ሰይጣን ለማስመሰል ከመጽሃፍ ቅዱስ ይጠቅሳል

የኢህአዴግ ስርዓት ገዥዎች ያጥቱን የህዝብ Aመኔታ ለማግኘት ሲሉ ሓቀኛ መስለው በመቅረብ የኢትዮጵያን ህዝብና የዓለም ማህበረሰብን በማምታታት የስልጣን እድሜን ማራዘም በሚል ፖሊሲ በያዝነው ሳምንት አዲስ የሚመስል የማደናገሪያ ስልት ይዘው ብቅ ብለዋል። መቸም እብሪተኞች ምን ግዜም ቢሆን ከራሳቸው ሌላ አዋቂ አለ ብለው አያስቡምና የኢህአዴግ አመራሮች በዚሁ አዲስ የሚመስል ስልታዊ ድራማ እራሳቸውን ንጹህ አድርገው በማቅረብና በመተወን የህዝቡን ቀልብ በመሳብ ህዝቡ ስለነሱ ንጽህና እንዲናገርላቸውና ስርዓቱ ሙስናን በቆራጥነት እየተዋጋ እንደሆነ በማስመሰል የኢትዮጵያንና የዓለምን ማህበረሰብን ለማደናገር የሚደረግ የተለመደ ተንኮል ይዘው መምጣታቸው የሚያስገርም አይደለም ። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ኢህአዴጎች እንደሚያሱቡት ሳይሆን የስርዓቱን ባህሪ በሚገባ የሚያውቅ ህዝብ በመሆኑ በእንዲህ አይነቱ ተንኮል ህዝቡን ማደናገር የሚቻል አይደለም። ምክንያቱ የኢህAዴግ አመራሮች በእንዲህ አይነቱ የማስመሰል ድራማ ብጹአን መስለው ለመታየት ቢሞኩሩም ስልጣናቸውን አለአግባብ በመጠቀም በማን አለብኝነት የሃገርንና የህዝብን ሃብት በመዝረፍ ያካበቱት የሃብት ዝርዝር ተደጋግሞ የተገለጸ ዓለም ያወቀው ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ስለሆነ እርቃናቸውን ያወጣቸዋል። ሙስና በሃገሪቱ ስር እንደሰደደና የስርዓቱ ባለስልጣናትም ምን ያህል በሙስና መጨማለቃቸውን ከታች ባለው የባለስጣንቱ ሃብት ዝርዝር መረዳት ይቻላል። 

1-መለስ ዜናዊ/ጠቅላይ ሚኒስቴር……………………….3 ቢልዮን ዶላር 
2-ወ/ሮ አዜብ መስፍን…………………………………..3 ቢልዮን ዶላር 
3-ስብሓት ነጋ …………………………………………..2.5 ቢልዮን ዶላር  
4-ብርሃነ ገ/ክርስቶስ………………………………………2 ቢልዮን ዶላር 
5-ሳሙኤል ታፈሰ………………………………………...1.5 ቢልዮን ዶላር 
6-ስዩም መስፍን…………………………………………..1 ቢልዮን ዶላር 
7-አባዲ ዘሞ……………………………………………….500 ሚልዮን ዶላር 
8-ግርማ ብሩ………………………………………………300 ሚልዮን ዶላር 
9-ታደሰ ሃይሉ……………………………………………..250 ሚልዮን ዶላር 
10- ቴዎድሮስ ሓጎስ(የህወሓት ጽ/ቤት ሃላፊ……………..200 ሚልዮን ዶላር 
11-አብደላሂ ባገርሽ(በጉና ትሬዲንግ የሚሰራ)……………150 ሚልዮን ዶላር 
12-ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል………………………………….100 ሚልዮን ዶላር 
13-በረከት ስምኦን…………………………………………..100 ሚልዮን ዶላር 

ይህ እንደ አብነት ለመቀስ ያህል የቀረበ እንጂ ሁሉም ከዝቅተኛው እስከ ከፍተኛው የስልጣን እርከን የሚገኙ የስርዓቱ ባለስልጣናት እንደየ ዓቅማቸው የህዝብንና የሃገርን ሃብት በመዝረፍ ሃብት ያላካበተ ባለስልጣን አለ ብሎ ማለት ያስቸግራል። ሁኔታው Aዲስና ከህዝብም የተሰወረ ሳይሆን በሁሉም የመንግስት ተቋማት ሲሰራበት የቆየ የተለመደ Aሰራር ነው ። ሃቁ ይህ እያለ “ ሰይጣን ለማስመሰል ከመጽሃፍ ቁድስ ይጠቅሳል” እንዲሉ የስርዓቱ አመራሮች ብጹአን መስለው ደግመው ደጋግመው ሊያደናግሩን ይሞክራሉ። 

ምንጭ፡ http://demhitonline.blogspot.com/

Saturday, October 19, 2013

መዐሕድ “የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች መፈናቀል” እንዲቆም ጠየቀ!!!

በ15 ቀን ውስጥ ከወልቃይት  ጠገዴ ሁለት ሺ ተማሪዎች ተፈናቅለዋል”

የመላው አማራ ህዝብ (መዐህድ) በአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው መፈናቀል በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ፡፡ መአህድ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የአማራ ተወላጆችን መፈናቀል በተመለከተ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ማሳወቁንና መፈናቀሉ እንዲቆም መጠየቁን ጠቁሞ፤ ጉዳዩ እስካሁን እልባት አለማግኘቱን ገልጿል፡፡

መፈናቀሉ ሊቆም ቀርቶ ተጠናክሮ መቀጠሉንና በቅርቡም ከጉራፈርዳ፣ ከቤኒሻንጉል እና ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች መፈናቀላቸውን የጠቆመው መዐህድ፤ ድርጊቱ በአገሪቱ ስርዓት አልበኝነት መንሰራፋቱን ያሳያል ብሏል፡፡
ከተማሪዎች በተጨማሪ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮችንም ለይቶ ማፈናቀሉ ለመሪር ሀዘን እንደዳረገው መአህድ ገልፆ፤ አንድን ብሄር ማዕከል ያደረገ ማፈናቀል እንዲቆም ጠይቋል፡፡

ባለፉት 15 ቀናት ብቻ “አካባቢያችሁ አይደለም” በሚል ከወልቃይት ጠገዴ ሁለት ሺህ ተማሪዎች መፈናቀላቸውን የገለፁት የመአህድ ፕሬዚዳንት አቶ ሸዋንግዛው ገብረስላሴ፤ ከጉራፈርዳም ተማሪዎች ተፈናቅለው ከትምህርት መስተጓጐላቸውንና ለጊዜው ቁጥራቸው በውል አለመታወቁን ፕሬዚዳንቱ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ “ከጉራፈረዳ ምን ያህል ተማሪዎች እንደተፈናቀሉና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ የሚያጣራ ቡድን ልከናል” ያሉት አቶ ሸዋንግዛው፤ አጣሪ ቡድኑ ሁኔታውን አጣርቶ ሲመለስ መዐህድ በድጋሚ የአቋም መግለጫ እንደሚያወጣም ተናግረዋል፡፡

“ተማሪዎች የወደፊት አገር ተረካቢ ሲሆኑ አርሶ አደሮችም የአገር ህልውና ምሰሶ ስለሆኑ በአገራቸው የትኛውም ቦታ የመማርና የመስራት መብታቸው ተከብሮ፤ ተማሪዎችም ወደ ትምህርት፣ አርሶ አደሮችም ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ እንጠይቃለን” ብለዋል፤ ፕሬዚዳንቱ፡፡

የአማራ ተወላጆችን ከተለያዩ አካባቢዎች ከማፈናቀል በተጨማሪ የአማራውን ክልል ለማጥበብ ወደ አጐራባች ክልሎች የሚደረገው የመሬት ሽንሸና ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም መዐህድ በመግለጫው የጠየቀ ሲሆን በአማራ ህልውና ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው ስልታዊ እንቅስቃሴ እና ትንኮሳ ሊገታ ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡ ሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪል ማህበራትም ይህንን ኢ-ሰብአዊ ድርጊትና መብት ረገጣ እንዲያወግዙ ጠይቋል፡፡

ምንጭ አዲስ አድማስ

ዜጎችን እያቀጨጨ የሚፈረጥም መንግስት… ብዙ አይራመድም ስንት እድሜ ይኖረዋል?


  • የውጭ ንግድ ፈቅ አላለም፤ ባለበት ደንዝዞ ቆሟል - የንግድ ሚኒስቴር መረጃ።
  • የግል ኢንቨስትመንት ተዳክሟል፤ ድርሻው በግማሽ ቀንሷል - የIMF መረጃ።
  • የአገሪቱ የባንክ ብድር፣ 90% ወደ መንግስት ይሄዳል - የአለም ባንክ ሪፖርት።



“ትልልቅ ፕሮጀክቶች በውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተቀየዱ የሚሄዱበት እድል ሰፊ ነው” … የኤክስፖርት ገቢ መዳከሙን በመግለፅ ይህን የተናገሩት የንግድ ሚኒስቴር ሃላፊዎች ናቸው። ያሳስባል፣ እውነታቸውን ነው። ነገር ግን፣ ትልቁና አሳሳቢው ነገር፣ የመንግስት ፕሮጀክቶች መስተጓጎላቸው አይደለም። የውጭ ንግድ መዳከም፣ ጠቅላላ በአገር ኢኮኖሚና በዜጎች ኑሮ ላይ ተጨማሪ ችግር እንደተደቀነ የሚጠቁም ምልክት ነው። ደግሞስ፣ የመንግስት ገናናነት እየገዘፈ፣ የግል ኢንቨስትመንት እየቀጨጨ፣ እንዴት ጥሩ ውጤት ይገኛል ብሎ መጠበቅ ይቻላል? 

አሳዛኙ ነገር፣ መንግስት ራሱን በራሱ ጠልፎ እየጣለ መሆኑን አለመገንዘቡ ነው። መንግስት “የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ” ውስጥ የዘረዘራቸውን ትልልቅ ፕሮጀክቶች ለማሳካት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስፈልገዋል። ግን ምን ዋጋ አለው? ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ የሆነው የግል ኢንቨስትመንት እየቀጨጨ የመጣው፣ “በእድገትና ትራንፎርሜሽን እቅድ” ሳቢያ ነው። ተግባራዊ የተደረጉ የመንግስት እቅዶች፣ የኤክስፖርት ገበያውንና የውጭ ምንዛሬ ምንጮችን እንዴት እየጎዱ እንደሆነ ለማሳየት እሞክራለሁ። 

በእርግጥ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ የሚስተጓጎል ፕሮጀክት የለም ብለዋል። የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በጭራሽ አይጓተትም ያሉት ጠ/ሚ ኃይለማሪያም፣ ሌሎቹ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ደግሞ በውጭ ብድር የሚካሄዱ በመሆናቸው የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደማያሳስብ ለመግለፅ ሞክረዋል። 

እንዲያም ሆኖ፣ ከኤክስፖርት የሚገኘው ገቢ የታሰበውን ያህል እንዳልተሳካ አልካዱም። ቢሆንም፣ ይህንን ጉድለት የሚሸፍን ነገር ተገኝቷል። ከተለያዩ ምንጮች ወደ ኢትዮጵያ የተላከው የውጭ ምንዛሬ ከተጠበቀው በላይ ሆኗልና። ለነገሩ፣ በየአገሩ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በየአመቱ የሚልኩት ገንዘብ ቀላል አይደለም። በአመት ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ እየላኩ ነው። ከኤክስፖርት ከሚገኘው ዶላር ይልቅ፣ ከዳያስፖራ የሚመጣው በልጧል። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለቤተሰብና ለዘመድ የሚልኩት ገንዘብ መጨመሩ ጥሩ ነው። ነገር ግን፣ የኤክስፖርትን ጉድለት ይሸፍናል በሚል የሚያፅናና አይደለም - በእጅጉ የሚያሳስብ እንጂ።

ከሳምንት በፊት ጠ/ሚ ኃይለማሪያም፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት የመንግስት ፕሮጀክቶች እንደማይስተጓጎሉ ቢገልፁም፤ ከምር ሳያሳስባቸው የቀረ አይመስለኝም። በዚያው ሳምንት የንግድ ሚኒስቴር ሃላፊዎች ከክልል መስተዳድር ተወካዮች ጋር ተሰብስበው የተነጋገሩበት ዋና ርዕሰ ጉዳይ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ነው። ወደ ውጭ የሚላኩ የእርሻና የፋብሪካ ምርቶች፣ በጥራትና በብዛት እየቀረቡ አይደለም በማለት የተናገሩት የንግድ ሚኒስቴር ሃላፊዎች፣ “ትልልቅ ፕሮጀክቶች በውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተቀየዱ የሚሄዱበት እድል ሰፊ ነው” በማለት አሳሳቢነቱን ገልፀዋል።

ከአመት አመት የኤክስፖርት እድገት እየተዳከመ መምጣቱን የሚክድ ይኖራል ብዬ አልገምትም። አሁን ደግሞ፣ ከነጭራሹ ቅንጣት እድገት አልታየም። እንዲያውም የኤክስፖርት ገቢ ቀንሷል። በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ ከተዘረዘሩት “ግቦች” ጋር ሲነፃፀርማ፣ በእጅጉ ወደኋላ ቀርቷል። የእቅዱ ግማሽ ያህል እንኳ አልተሳካም።

በእቅዱ የመጀመሪያ ዓመት በ2003 ዓ.ም፣ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የነበረውን የኤክስፖርት ገቢ በአንድ ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ (3 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ) ቢታሰብም፣ የእቅዱ 75 በመቶ ብቻ ነው የተሳካው። ቀላል እድገት ነው ማለቴ አይደለም። 2.75 ቢሊዮን ደርሷል። በቀጣዩ ዓመት ግን፣ እድገቱ ተዳክሟል። በ“ኦሪጅናሉ” እቅድ መሰረት፣ የኤክስፖርት ገቢ በ2004 ዓ.ም ወደ አራት ቢሊዮን ዶለር የሚጠጋ ይሆናል ተብሎ ነበር የታሰበው። በተግባር የተገኘው ገቢ ግን 3.15 ቢ. ዶላር ነው። ከመነሻው አመት ጋር ሲነፃፀር በሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ገቢ ለማግኘት ቢታቀድም፣ በተግባር የተገኘው እድገት 1.2 ዶላር ገደማ ነው። እናም እቅዱ 60 በመቶ ብቻ ነው የተሳካው ማለት ይቻላል። 

አሁንም ኦሪጅናሉን እቅድ ካስታወስን፣ በ2005 ዓ.ም ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ የኤክስፖርት ገቢ ለማግኘት ታስቦ እንደነበር እናያለን። በተግባር የተገኘው ውጤት ደግሞ 3.1 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው። የአመት አመት እድገቱ ተዳክሞ ከመቆሙም በላይ፣ የኋሊት መንሸራተት ጀምሯል። በ2002 ዓ.ም ከነበረው መነሻ አሃዝ ጋር ስናነፃፅረው፣ በሦስት ቢሊዮን ዶላር የላቀ እንዲሆን ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ 1.1 ቢሊዮን ዶላር ያህል ብቻ ነው የተሳካው። የእቅዱ 37% ብቻ ማለት ነው። ከአመት አመት የስኬቱ መጠን እየቀነሰ መሆኑን የምታስተውሉ ይመስለኛል።

አዲሰ አበባ ዉስጥ ቦምብ ፈንድቶ የሁለት ሰዎች ህይወት አጠፋ

አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ዉስጥ በተለምዶ ሩዋንዳ ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ባለፈዉ እሁድ ጥቅምት ሦስት ቀን 2006 ዓም ቦምብ ፈንድቶ ሁለት ሰዎች መሞታቸዉን ተገለጸ። ከፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል በተገኘዉ መረጃ መሰረት በቦምቡ ፍንዳታ ሕይወታቸው ያለፈው ሁለቱ ሰዎች በህገወጥ መንገድ ወደ አገር ዉስጥ የገቡ የሶማሌ ዜጎች ሲሆኑ እንደ ፌዴራል ፖሊስ አገላለጽ ፍንዳታዉ የደረሰዉ ሰዎቹ ቦምቡን በሰዉነታቸዉ ዉስጥ ደብቀዉ ወደ ዕላማቸዉ ለመሄድ ሲዘጋጁ ነዉ። ፌዴራል ፖሊስ የሰጠዉን መግለጫ አስመልክቶ ከገለልተኛ አካላት የተሰጠ ሌላ መግለጫ ባይኖርም የሁለቱ ሰዎች ዝግጅትና ለመመሳሰል ብለዉ የያዙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መለያ እንደሚያመለክተዉ የሁለቱ ሰዎች የጥቃት ተልዕኮ አዲስ አበባ ስቴድዮም ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል። ጥቅምት ሦስት ቀን የኢትዮጵያና ናይጀሪያ ቡድኖች ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ የተጫወቱበት ቀን ስለነበር አዲስ አበባ ስቴድዮምና አካባቢዉ በዕለቱ በብዙ ሺዎች በሚቀጠሩ የስፖርት አፍቃረዎች ተጨናንቆ እንደነበር የሚታወስ ነዉ።

የአልሽባብ ሽብርተኞች እንደሆኑ የሚነገረዉ ሁለቱ የሶማሌ ዜጎች እጃቸዉ ላይ ከፈነዳዉ ቦምብ በተጨማሪ መጠናቸው ያልተገለጸ ቦምቦችና አንድ ሽጉጥ ከሁለት ካርታ ጥይት ጋር ፣ የፈንጂ ማቆጣጠያና የአደጋ መከላከያ ጃኬቶች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማሊያና ቀበቶዎች መገኘታቸውም ተገልጿል፡፡ የአንድ ግለሰብ ሰርቪስ ቤት ተከራይተው ከነበሩት ሁለቱ የሶማሌ ዜጎች ዉስጥ አንደኛው ከ20 ቀናት በላይ የቆየ ሲሆን፣ ሌላኛው ፍንዳታው ከመድረሱ ከሁለት ሰዓታት በፊት የደረሰ መሆኑን ግብረ ኃይሉ ማረጋገጡን አስረድቷል፡፡ ከሶማሊያውያኑ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎችና የቤቱ አከራይ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄባቸው መሆኑንም ግብረ ኃይሉ አክሎ ገልጿል፡፡

የወያኔ አገዛዝ የሶማሊያን ግዛትዘልቆ አየገባ በሚፈጽመዉ ጥቃት የተነሳ ኢትዮጵያ ለአመታት ለአልሽባብና ሌሎችም አክራሪ ኃይልች የሽብር ጥቃት የተጋለጠች መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን በላፈዉ ወር ኬንያ ናይሮቢ ዉስጥ ለደረሰዉ የሽብር ጥቃት አልሽባብ ሀለፊነት ከወሰደ በኋላ ግን ኢትዮጵያ የሚቀጥለዉ የአልሽባብ ጥቃት ሰለባ ትሆናለች የሚል ከፍጠኛ ፍራቻ አንዳለ ብዙዎች ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቦሌ ዉስጥ እንደዚያ አይነት ከፍተኛ የቦምብ ፍንዳታ ደርሶ ፖሊስ አደጋዉ ወደ ደረሰበት ቦታ የመጣዉ ከ30 ደቂቃ ቆይታ በኋላ መሆኑን የገለጹት የአካባበዉ ነዋሪዎች ስጋታቸዉን ገልጸዋል። እንደ ነዋሪዎቹ አባባል አደጋዉ ደረሰዉ በተወሰነ ቦታ መሆኑና ተጠርጣሪዎቹም ወዲያዉ ስለሞቱ ነዉ አንጂ እንደ ኬንያው ዌስትጌት ጥቃት ቢሆን ኖሮ ፖሊስ የሚደርሰዉ ብዙ ሊተርፍ የሚችል ሰዉ ከሞተ በኋላ ነበር በማለት ብዙ የአካባቢዉ ነዋሪዎች በፖሊስ ላይ ያላቸዉን ስጋት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን አባቶች መንግስት ቤ/ክርስቲያኑቱን ለማፍረስ ተነስቷል ሲሉ ከሰሱ

ወያኔ በሐይማኖት ተቋማት ላይ የሚያደርሰዉ በደልና ጫና የሰለቻቸዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርሲቲያን አባቶች የወያኔ አገዛዝ ታሪካዊቷን ቤተክርቲያን ታሪክ አልባ ለማድረግና ለማፍረስ ቆርጦ ተነስቷል ብለዉ መናገራቸዉንና ንግግሩ የአገዛዙን ባለስልጣኖች እንዳስደነገጠ ከአዲስ አበባ የደረስን ዜና አስረዳ። አባቶቹ ይህንን በቤተክርስቲያኒቱ የሺ አመታት ታሪክ ዉስጥ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነዉን በስልጣን ላይ ያለ መንግስትን ፊት ለፊት የመቃወምና የማዉገዝ ንግግር ያሰሙት ሰሞኑን አዲስ አበባ አራት ኪሎ ዉስጥ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያርክ የስብሰባ አዳራሽ ዉስጥ በመካሄድ ላይ ባለው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነዉ። አንድ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባት ለዝግጅት ክፍላችን በስልክ አንደገለጹት በስብሰባው ላይ ይህ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ እንደተነሳ በተደጋጋሚ ተነግሯል። እኚሁ አባት ጨምረዉ አንደገለጹት በዕለቱ በተደረገዉ ስብሰባ የፌደራል ጉዳዮች የሀይማኖት ክፍል ሃላፊዎች ስለ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ገለጻ ለመስጠት የመጡ የአገዛዙ ካድሬዎች ተገኝተዉ አንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

በወያኔ ዘመን ኢትዮጵያ ዉስጥ በክርስቲያን ተቋሞችና በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰዉ ግፍና መከራ እየጨመረ መምጣቱን አባቶቹ ተራ በተራ የተናገሩ ሲሆን ፓትሪያሪኩም አባቶች የተናገሩትን በመደገፍ እውነት ነው ይህ ሁሉ መከራና ጫና አለብን በማለት በሊቀ ጳጳሳቱ የተነገረውን ሀሳብ ደግፈዋል። ከመላው አለም የተሰባሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀይማኖቱ መሪዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ የተገኙት የመንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን የሀይማኖት ታሪክ አሳንሰዉና አጣጥለዉ ሲያቅርቡ ያዳመጡት አባቶች በቁጣ በመነሳት ለወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናት ተገቢዉን ምላሽ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያን ህዝብ መሬት ነጥቃችሁ፣ ህዝቡንም መሬቱንም የመንግስት ያደረጋችሁት እናንተ ናችሁ፣ ኢትዮጵያዊው ሀብትና ንብረት እንዳይኖረው ያደረጋችሁትም እናንተዉ ናችሁ። የኢትዮጵያን ህዝብ ከዚህ ቀደም የነበሩት መንግስታት ካደረሱበት የበለጠ መከራና ስቃይ ያየዉ በዚህ መንግስት ግዜ ነዉ በማለት አባቶቹ የወያኔን ባለስልጣናት ግራ በጋባና ባስደነገጠ መልኩ ትችትና ወቀሳ አቅርበዋል። ከስብሰባዉ ተካፋዮች አንዱ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ “በአጼዎቹ ዘመን አገራችን ታሪኳ የተከበረ ነበር፤ እናንተም ይህችን አገር ስትረከቡ እስከ ታሪኩዋ ነው . . . ታሪኩዋን አላጠፋችሁም ወይ?” ብለዉ ሲጠይቁ አዳራሹ ዉስጥ የነበረዉ ሰዉ ሁሉ አድናቆቱን በጭብጨባ ገልጾላቸዋል። በዕለቱ ስብሰባ ላይ የተሳተፉት አብዛኛዎቹ የሀይማኖት አባቶች የቤተክስርቲያኗን ታሪክ አዛብታችሁዋል፣ ቤተክርስቲያኑዋንም ታሪኩዋን አጥፍታችሁዋል በማለት ባለስልጣናቱን ወጥረው መያዛቸው ታውቋል። በስብሰባዉ ላይ የሰሜን ወሎ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቄርሊዮስ፣ የምእራብ ወለጋ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ፣ የጋሞ ጎፋ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤሊያስ፣ የምስራቅ ጎጃም ሊቀ ጳጳስ ብጹ አቡነ ማርቆስና የደቡብ ጎንደር ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንድሪያስ ተገኝተዋል።

ኃ/ማሪያም ደሳለኝ “መንግስት ፈርቷል እያላችሁ ራሳችሁን አታሞኙ” ሲል ማሾፉ ተሰማ

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት አንዴ “ቀይ መስመር ረገጣችሁ” አንዴ ሰላማዊ ሰልፍ እከለክላለሁ፤ ሌላ ግዜ ደግሞ ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎች ጥያቄ መልስ ሰጥቷል እያለ የባጥ የቆጡን ሲቀባጥር የሰነበተዉ የወያኔዉ ሎሌ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በዚህ ሳምንት ደግሞ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝቶ ““መንግስት ፈርቷል እያላችሁ ራሳችሁን አታሞኙ” ብሎ በመደንፋት “ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም” የሚባለዉን የአገራችንን ተረት የሚያስታዉስ የፈሪ ንግግር አድርጓል። ጠ/ሚኒስቴር ተብዬዉ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ከዚያ እንቅልፋም ፓርላማ አባላት ለቀረቡለት ጥያቄዎች መልስ ሲሰጥ መንግስት የጎዳና ላይ ነውጥ ከሚያሰቡት ሀይሎች ጋር ለመነጋገር የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል። ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር እንኳን መነጋገር እነሱ ባለፉበት መንገድ ማለፍ የሚፈራዉ ኃ/ማሪያም የጎዳና ላይ ነውጥ ከሚያሰቡት ሀይሎች ጋር ካሁን በኋላ አንነጋገርም ማለቱ አንዳንዶችን ያስገረመ ቢሆንም ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች አባባሉን የተለመደ የወያኔ የቃላት ጨዋታ ነዉ ብለዉ የኃይለማሪያምን ንግግር አጣጥለዉታል።

በተቃዋሚዎች ፓርቲዎች በኩል የሚቀርበው ጥያቄ ሁሉ ቅጥ ያጣ ፍረጃና የጥላቻ ፖለቲካ ብቻ ነዉ ያለዉ ሎሌዉ ሀይለማርያም ደሳለኝ የጎዳና ላይ ነውጥ እናደርጋለን ብለዉ የሚያስቡ ሀይሎች ሀሳባቸውን እንዲያቆሙ ጠይቋል። በመቀጠልም የጎዳና ላይ ነውጥ ለማስነሳት ስለሚያስቡ ኃይሎች በቂ መረጃ አለን ስንል “መንግስት ፈርቶ ማስፈራራት ጀመረ” እንባላለን ሆኖም ይህ መንግስት አይፈራም፣ ታሪኩም ባህሪውም እንደዛ አይደለም በማለት የሚያዉቀዉን የኢትዮጵያዉያንን የጀግንነትና የአይበገሬነት ታሪክ ትቶ የማያዉቀዉን፤ የሌለዉንና በታሪክ ያልተመዘገበዉን የወያኔን አለመፍራት “ይህ መንግስት ፈርቷል እያላችሁ እራሳችሁን አታሞኙ፣ መንግስት አይፈራም የህዝብ መንግስት ነው” እያለ ያለ ሀፍረት ተናግሯል። ዘረናዉ የወያኔ አገዛዝ ወይ እሱ እራሱ አይጫወትበት ወይ ሌሎቹን አያጫዉት ብቻዉን ጨምድዶ የያዘዉን ኳስ የወያኔዉ ተላላኪ ኃ/ማሪያም ጌቶቹ ሄደህ ተናገር ያሉትን ትእዛዝ ለመፈጸም ብቻ ሲል ብቻ “ኳሱ እናንተ እጅ ላይ ነው” በማለት አባባሉን እንኳን በዉል ያልተረዳዉን ምሳሌ ተናግራል።

የሞኝ ዘፈን አሁንም አሁንም አበብዬ


ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች ከዚህ ቀደም በቁንጯቸዉ በመለስ ዜናዊ በኩል እንኮረኩማለን፤ ምላስ እንቆርጣልን ወይም እጅ እናስራለን እያሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስተላልፉ የነበረዉን የማስፈራሪያ ቃላት ጋጋታ ባለፈዉ ዐርብ መስከረም 26 ቀን ለዚሁ እኩይ ተግባራቸዉ በቀጠሩት ታማኝ ሎሌያቸዉ በኃ/ማሪያም ደሳለኝ በኩል ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል። እንዳሰለጠኑት ጌኛ ፈረስ ወያኔ ባሳየዉ አቅጣጫ ሽምጥ የሚጋልበዉና ከጭንቅላቱ ወጥቶ የሚነገር ምንም ነገር የሌለዉ ኃ/ማሪያም ደሳለኝም የአሜሪካዉን ፕሬዚዳንት የባራክ ኦባማን አባባል እንዳለ በግርድፉ ወስዶ “ከቀይ መስመር በላይ መሄድ የሚፈልግ ይቆነጠጣል” ሲል በዚያ ባልተቆነጠጠ አፉ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ደንፍቷል። የወያኔዉ ተላላኪ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አልገባዉም እንጂ ይህ ቀይ መስመር ታልፉና ወዮላችሁ የሚሉት ዛቻ አንኳን በአንድ ጀምበር ትርምስምሱ ሊወጣ በሚችል የጦር ኃይል ለሚተማመነዉ ወያኔን ለመሰለ ፀረ ህዝብ ኃይል ቀርቶ በህዝብ ሙሉ ፈቃድ የተመረጠዉና የአለማችንን አስፈሪና እጅግ ጠንካራ ጦር የሚመራዉ ባራክ ኦባም ከተናገረና ከዛተ በኋላ ዛቻዉ አላዋጣ ስላለዉ ሌሎች አማራጮችን ለመመልከት ተገድዷል።


ባለፈዉ ዐርብ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የተናገራቸዉን ተራ ንግግሮች ሁሉ እንመልከት ብንል እንደሱ ስራ ፈቶች አይደለንምና ግዜዉም ፍላጎቱም የለንም፤ ሆኖም አንዳንድ ንግግሮቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱና ለነጻነቱ የሚያደርገዉን ትግል በንቀት አይን የተመለከቱ ናቸዉና ግንቦት 7 የሚያካሄደዉ የነጻነት ትግል ኃ/ማሪያም ደሳለኝን ከወያኔ ባርነት ነጻ ማዉጣትንም ያጠቃልላልና ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ይህንን ምክር አዘል መልዕክታችንን እንዲያዳምጥ እንጋብዘዋለን። ደግሞም የግንቦት ሰባትን እንቅስቃሴ እከታተላለሁ ብሎ ሲናገር ከራሱ አንደበት ሰምተናልና ምክራችንን ይሰማል የሚል ሙሉ እምነት አለን።

ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አገር ዉስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያነሷቸዉን ጥያቄዎች አስመልክቶ ከጋዜጠኞች የቀረበለትን ጥያቄ ሲመልስ ኢትዮጰያ ዉስጥ ወደ ዘጠና የሚጠጉ ፓርቲዎች ስላሉ ዘጠና እሁዶችን መጠበቅ አለብን በማለት ከተጠየቀዉ ጥያቄ ጋር በፍጹም የማይገናኝና እንኳን ከአገር መሪ ከሦስተኛ ክፍል ተማሪም የማይጠበቅ ተራ መልስ መልሷል። ከዚህ በተጨማሪ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እሁድ እሁድ በሚያደርጓቸው ሰላማዊ ሠልፎች የሚያቀርቡት ጥያቄ ተመሳሳይ ስለሆነ መንግሥት ምን ምላሽ መስጠት እንዳለበት ሊገባው አልቻለም በማለት ኃ/ማሪያም የእሱን የራሱን ብቻ ሳይሆን እሱ የሚመራዉ መንግስትም ምን ያክል ጨቅላ መንግስት አንደሆነ በግልጽ ተናግሯል። የኃ/ማሪያምና የጌቶቹ ጨቅላነትና ባዶነት ደግሞ አገር ያወቀዉና ፀሐይ የሞቀዉ እዉነት ነዉና ብዙ መረጃ የሚያስፈልገዉ አይመሰለንም።ከሰሞኑ አማካሪ ተብለዉ ኃ/ማሪያምን የከበቡትን ሰዎች መመልከቱ ይበቃል። የጭንቅላቱ ዝገት ለይቶለት በመለስ ዜናዊ ግዜ ስኳር እንዲቅም መተኃራና ወንጂ የተላከዉ አባይ ፀሐዬ እሱ እራሱ ይመረመር እንደሆነ ነዉ እንጂ አባይ ፀሐዬ እንኳን ለፖሊሲ ምርምር የተመራማሪዎችን ዶሴ ለመሸከም የማይበቃ ሰዉ ነዉ . . . ችግሩ “ግም ለግም አብረህ አዝግም” ነዉና ከምሁርና ከአዋቂ ጋር የተጣሉት የወያኔ መሪዎች አንዱን ጅል የሌላዉ ጅል አማካሪ እያደረጉ የፈረደባትን አራት ኪሎን የጅሎች መንደር አደረጓት።

ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ባለፈዉ ዐርብ ከአንድ ሰዐት በላይ በፈጀዉ ጋዜጣዊ መግለጫዉ ወቅት የተናገረዉ አንድ ብቸኛ እዉነት ቢኖር “መንግስት ተቃዋሚዎች ለሚያቀርቡት ጥያቄ ምን አይነት ምላሽ መስጠት እንዳለበት ሊገባዉ አልቻለም ብሎ የተናገረዉ ንግግር ብቻ ነዉ። አዎ በተራ የመንገድ ላይ ፖለቲከኞችና ዘራፊዎች የሚመራዉ የወያኔ /ኢህአዴግ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ የሚቀርብለትን የመብትና የነጻነት ጥያቄ ቀርቶ በአገዛዙ በራሱ መሃል የሚነሱ ጥያቄዎችን በቅጡ ተረድቶ የመወያየት ብቃትም ችሎታም ያለዉ አገዛዝ አይደለም። ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በአንድ በኩል ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለህዝብ ማለት የፈለጉትን ብለዋል፤ ህዝብም በሚገባ ሰምቷቸዋል በማለት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎች ለጠየቁት ጥያቄ መንግስት ተገቢዉን ምላሽ ሰጥቷል አሁን እየጠየቁ ያሉት ተመሳሳይ ጥያቄ ነዉ በማለት እሱም ሆነ ፈላጭ ቆራጩ የወያኔ አገዛዝ እንመራለን የሚሉትን ህዝብ የፖለቲካ ምጥቀት በፍጹም የማይመጥኑና ቀድሟቸዉ የሄደዉን ህዝብ ከኋላ ሆነዉ የሚመሩ ኋላ ቀሮች መሆናቸዉን በግልጽ አሳይቷል። ኃ/ማሪያም በሰላማዊ ሰልፍና በህዝብ መካከል ያለዉ አንድነትና ልዩነት የገባዉ ሰዉ አይመስልም፤ ለዚህ ነዉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያቀረቡት ጥያቄ ለህዝቡ መስሎት ህዝብ ሰምቷቸዋል ብሎ የተናገረዉ፡፡

ስብሐት ነጋና አሜሪካ የሚኖረዉ አግአዚ ኢትዮጵያዊዉን ደብድበዉ ተሰወሩ

ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት አይኑ አይቶ ያልወደደዉን ሁሉ እንዳሰኘዉ ሲያስር፤ ሲደበድብና ሲገድል የኖረዉ ወንጀለኛዉ ሽማግሌ ስብሐት ነጋ ያንን የለመደዉን ወንጀል አሜሪካ ድረስ ይዞ በመምጣት እየተከተለዉ ቪድዮ ሲቀርጸዉ የነበረዉን አንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ ከአጃቢዉ ጋር ደብድቦ መሰወሩን አሜሪካ ግዛት ቨርጂኒያ ዉስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን በላኩልን ዜና ገለጹ። ከአሜሪካዋ መናገሻ ከዋሺንግተን ዲሲ በስተደቡብ አስራ አምስት ኪሎ ሜትር ወጣ ብላ በምትገኘዉ አሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ዉስጥ ነበር ስብሐት ነጋና እዚሁ ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ የሚኖረዉ ታምራት ገ/መድህን የተባለ የህወሃት ሰላይ መስፍን ወርቅነህ የተባለዉን ሰላማዊ ኢትዮጵያዊ ለምን ቪድዮ ትቀርጸናለህ ብለዉ ያለበት ቦታ ድረስ ሄደዉ የደበደቡት። ተደብዳቢዉ መስፍን ወርቅነህ የተባለዉ ወጣት ጉዳት ደርሶበት እዚያዉ አለክሳንደሪያ ዉስጥ ወደሚገኘዉ ሆስፒታል ተወስዶ የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ዕርዳታ የተደረገለት ሲሆን የድብደባዉን ዜና የሰማዉ የአሌክሳንደሪያ ከተማ ፖሊስ ወንጀሉ ወደተፈጸመበት ቦታ ደርሶ ተጠርጣሪዎቹን ቢፈልግም ወንጀሉን የፈጸሙት ስብሐት ነጋና አጃቢዉ ታምራት ገ/መድህን ለግዜዉ ከፖሊስ መሰወራቸዉ ታዉቋል። የድብደባዉን ዜና ከኢሳትና ከሌሎች የተለያዩ የአካባቢዉ የዜና ማሰራጫዎች የሰሙት ኢትዮጵያዉያን የህግ ባለሙያዎችና የሲቪክ ማህበረት መሪዎች በስብሐት ነጋና በአጃቢዉ ላይ ክስ መስርተዉ ጉዳዩ በፖሊስ በመጣራት ላይ ነዉ። ይህ በዚህ አንዳለ የአሌክንደሪያ ፖሊሶች የነስብሐት ነጋ ጥቃት ሰለባ የሆነዉን መስፍን ወርቅነህን ድብደባዉን አስመልክቶ አነጋግረዉ የምስክርነት ቃሉን ተቀብለዋል።

የስብሐት ነጋና የአጃቢዉ የታምራት ገ/መድህን ድፍረት ዲሲ፤ ቨርጂኒያና ሜሪላንድ ግዛቶች ዉስጥ የሚኖረዉን ኢትዮጵያዊ ያስቆጣ ሲሆን ኢትዮጵያዉዉያኑ ፖሊስና ፍርድ ቤት በሁለቱ ወንጀለኞች ላይ የሚወስዱትን እርምጃ ለማወቅ በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸዉ። የዚህ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ያናገራቸዉ አንድ በቅርቡ ከኢትዮጵያ የመጡ ታደለ ጉርሙ የተባሉ ግለሰብ “የእነሱን ድብደባና እርግጫ ላለማየት አገሬን ጥዬ መጣሁ እነዚህ አይነ ደረቆች እዚህም እያመጡ ሰዉ ይደበድባሉ እንዴ” ካሉ በኋላ ደግነቱ አገሩ አሜሪካ ነዉና ሌላ ቢቀር እኛን አገራችን ዉስጥ የነፈጉንን ፍትህ እነሱ እዚህ በአይናቸዉ ያያሉ ብለዋል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ በመካሄድ ላይ ያለዉ ህዝባዊ እንቅስቃሴ መጎልበት፤ የተቃዋሚ ኃይሎች ጡንቻ መፈርጠምና የቱባ ቱባ የህወሃት ባለስልጣኖች አገር ጥሎ መፈርጠጥ ያሳሰባቸዉ የወያኔ ሹማምንት በትዕቢተኛዉ መሪያቸዉ በስብሐት ነጋ መሪነት እዚህ አሜሪካ መጥተዉ ከአሜሪካ መንግስት ባለስልኖች፤ እግሬ አዉጭኝ ብለዉ ከፈረጠጡ አባላቶቻቸዉና ከጥቂት ሆዳም ደጋፊዎቻቸዉ ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸዉ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች መዘገቡ የሚታወስ ነዉ። ትላልቅ የአገዛዙን የደህንነት ባለስልጣኖች ጨምሮ ከፍተኛ የህወሃት መሪዎችን ይዞ አሜሪካ የገባዉ የወያኔ ቡድን አሜሪካ ደርሶ እንቅስቃሴዉን እስኪጀምር ድረስ ትግርኛ ተናጋሪ ከሆኑት የኤምባሰዉ ሰራተኞች ዉጭ ግርማ ብሩን ጨምሮ ሌሎቹ ከፍተኛ የኤምባሲዉ ባለስልጣኖች በፍጹም አለመስማታቸዉን ከዉስጥ አዋቂ ምንጮች የተገኘዉ መረጃ ያለመክታል። ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት አሜሪካ ሲመጡ አሜሪካ ዉስጥ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማዉቁ የሚያሳየዉ አስፈላጊ በሆኑ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ወያኔ ከትግርኛ ተናጋሪዎች ዉጭ ማንንም የማያምን ዘረኛ ድርጅት መሆኑን ነዉ ሲሉ ብዙዎች ትችት ይሰነዝራሉ።

Friday, October 18, 2013

የእፎይታ ጊዜው፣ የመንግሥት ምላሽ እና የሙስሊሙ ሰላማዊ ትግል …

በነስረዲን ኡስማን

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሃይማኖት ነፃነትና መብታችን ላይ የተፈፀሙ ጥሰቶች እና ተያያዥ በደሎችን በመቃወም በመስጂዶች ስናካሂድ የቆየነውን የተቃውሞ ትዕይንት፣ “ጥያቄዎቻችንን በሰከነ አዕምሮ ለማጤን ይችል ዘንድ ለመንግሥት ፋታ እንስጠው” በሚል ከአሚራችን ድምፃችን ይሰማ በተላለፈው ትዕዛዝ መሠረት ጋብ ማድረጋችን ይታወቃል፡፡ ይህ የአሚራችን ትዕዛዝ የተላለፈው በዒድ አል ፊጥር ዋዜማ ነበር፡፡ ትዕዛዙ ከተላለፈበት ጊዜ አንስቶ ህዝበ ሙስሊሙ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል አንድም መስጂዶችን ማዕከል ያደረገ የተቃውሞ ትዕይንት አላካሄደም፡፡ በዚህም፣ በየትኛውም የአገሪቱ ጫፍ ያለው ሙስሊም ማኅበረሰብ ምን ያህል ለአሚሩ ትዕዛዝ ታዛዥ እንደሆነና፣ ባነሳቸው ጥያቄዎችና በሰላማዊ ትግሉ ዙርያ ምን ያህል በጠንካራ የአንድነት ገመድ እንደተሳሰረ በገሃድ አሳይቷል፡፡ መንግሥት ቢገባው፣ ይህ በራሱ ትልቅ መልዕክት ነበር፡፡

በአንጻሩ መንግሥት በዒድ አል ፊጥር ዋዜማ ድምፃችን ይሰማ በይፋ የእፎይታ ጊዜ ማወጁን እያወቀ፣ በዕለተ ዒድ በተለይ በአዲስ አበባ እንኳንስ አገር የሚያሥተዳድር መንግሥት ይቅርና ተራ የጫካ ሽፍታ የማይፈጽመውን አስነዋሪ ድርጊት ፈፀመ፡፡ የዒድ ሰላቱን አጠናቆ የሚመለሰውን ሰላማዊ ህዝብ በተለያዩ አቅጣጫዎች በተሰማሩና በየቅያሱ አድፍጠው፣ እንዲሁም በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ቅጥረ ግቢ መሽገው በሚጠባበቁ የፌደራልና ‹የአዲስ አበባ› ፖሊሶች ከፊትና ከኋላ እያስቆረጠ ህፃን፣ አዋቂ፣ አዛውንት፣ ወንድ፣ ሴት ሳይል በጅምላ በፖሊስ ቆመጥና በዱላ አስቀጠቀጠ፡፡ ሐሙስ ነሐሤ 2 ቀን 2005 በዕለተ ዒድ በአዲስ አበባ ነዋሪ ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመው ጅምላ ቅጥቀጣ፣ ከጥቃት መፈፀሚያ መሣሪያው አኳያ ካልሆነ በስተቀር፣ በባህሪው የካቲት 12 ቀን 1929 የፋሺስት ኢጣሊያ ወታደሮች በአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ላይ፣ እንዲሁም ደርግ በሐውዜን እና በመርሳ ነዋሪዎች ላይ ከፈፀመው ጅምላ ጥቃት የተለየ አልነበረም፡፡ …

ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት በአዲስ አበባ ሙስሊሞች ላይ እንዲፈፀም ያደረገው ይህ አስነዋሪ የጅምላ ቅጥቀጣ በተጎጂዎችና በቤተሰቦቻቸው፣ በቤተ ዘመዶቻቸውና የተጎጂዎችን ጉዳት ዓይተው በመሰከሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዘንድ መቼም የሚረሳ አይደለም፡፡ … መንግሥት በህዝብ ላይ ጅምላ ቅጥቀጣ ማካሄድ በምንም መለኪያ ተቀባይነት ሊያገኝ የማይችል እጅግ አስነዋሪ ድርጊት መሆኑን ቢያውቅም፣ ድርጊቱን ለማስተባበልም ሆነ የጅምላ ጥቃቱ ተጎጂ የሆነውን ህዝበ ሙስሊም ይቅርታ ለመጠየቅ አልደፈረም፡፡ ኢህአዴግ ይህ መንግሥታዊ ውንብድና በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ዋጋ አያስከፍልም ብሎ የሚያስብ ከሆነ፣ እጅግ በጣም ተሳስቷል፡፡

ወያኔና አሸባሪነት ምንና ምን ናቸው

የወያኔ ጉጅሌ ሰሞኑን የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ በእጅጉ ሊያስቅ የሚችል ቧልት ላይ ተጠምዷል። የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ሳይቀር ህብረተሰቡን በየተቋሙና በየመኖሪያው እየሰበሰበ ስለሽብርተኝነት ማብራሪያና ገለፃ በመስጠት ዜማ ላይ ተጠምዷል።

የወያኔ የሽብረተኝነት ገለፃ ዘመቻ ሚስጥር ደግሞ ብዙ ምርምር የሚሻ አይደለም። የሀገራችን ሰዎች ዶሮ ጭራ ልታወጣው የምትችል የሚሉት አይነት ሚስጥር ነው። አላማው ነጻነት አማረኝ፣ እምቢ ዘረኝነት እና ቢያንስ መሰረታዊ ሰበአዊ መብቴ ይገባኛል በማለት መብቱን እየጠየቀ የመጣው ህዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ታይቶታል።

የማእበሉ የመጀመሪያ ንቅናቄዎች ከወዲያ ወዲህ መታየት ጀምረዋል። የገለፀው ሽርጉድ ዋና አላማ ይህ መብቱን የሚጠይቅና አጎንብሶ መኖር የሰለቸው ህዝብ ለመብቴ የማደርገውን ትግል ሽብርተኛ ያስብለኛል ብሎ እንዲፈራና ይበልጥ እንዲያጎነብስ መሆኑ ነው። ይህን ደግሞ ህዝቡ አውቆታል። ሰሞኑን በአለምያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለገለፃው ለመጡ ካድሬዎች የሰጧቸው አጸፋዊ ገለጻ ይህንኑ ያሳያል፡፡

ሽብርተኝነት አንድና በነጻነትና በዴሞክራሲ ለመኖር የሚመኝና የወሰነን ህዝብ ሰላም በመንሳት የፖለቲካ አላማዪን አሳካለሁ ብለው የሚያምኑ ቡድኖችና ድርጅቶች የፖለቲካ መሳሪያ ነው። የወያኔ መሪዎች የሽብርተኝነት ትርጉም አልገባቸው ከሆነ ሰብስብ ብለው መሰዋእት ፊት ቢቆሙ ሽብረተኝነትን አፍጥጦ ሊያዩት ይችላሉ፡፡ ሽብርተኛው ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው።

ህዝቡ ፊት በቆሙ ቁጥር ግን ህዝቡ ሽብርተኞችን ያያል። ሰለባውን ለማስተማር መሞከር ለእናት ምጥ የማስተማር ያህል ነው፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ሁሉንም የዲሞክራሲና የሰላም ጥያቄ ሁሉ በጉልበትና ባፈና የደፈጠጠ አሸባሪ ቁጥር አንድ ወያኔ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ከሽብር ጋር የመረረ ችግር ላለባቸው ሀገሮች ሎሌነት ገብቶ ሌሎች ሽብርተኞችን ወደሀገራችን የሚጎትተው ራሱ ወያኔ ነው።

ዛሬ በማንም የባእድ አሸባሪ በህዝባችን ላይ ለሚደርስ ጉዳት ዋናው ተጠያቂ ወያኔ የሚሆነውም ለዚህ ነው። ለምእራብያውያን ጸረ ሽብር አጋራችሁ ነኝ እያልኩ ራሴ በምገዛው ህዝብ ላይ የምፈጽመውን ሽብር እንዳለ ያዩልኛል፣ ፍርፋሬም አገኝበታለሁ በሚል ስሌት የተገባበት መሆኑንም የማያውቅ ኢትዮጵያዊ ቁጥሩ ትንሽ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡- ነጻነት የናፈቀህ፣ አጎንብሶና በገዛ ሀገርህ ተዋርዶ መኖር የሰለቸህ፣ በወያኔ ተሰደህ በባእድ ሀገር የምትሰቃይ፣ የምትሞት የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ወያኔዎች ከግፍ አልፈው ሊቀልዱብህ፣ በቁምህ ሊገሉህ፣ ሊከፋፍሉህ አይገባም። ወያኔ የፈሪ አብራሪ ነው። አሻፈረኝ ሲሉት እንጂ ቢሸሹለት በቃኝ ብሎ አይመለስም፡፡

ግንቦት 7 ንቅናቄ እንደሁልግዜው ዛሬም ወገን ሆይ፡- የሀገርህን ህልውና ለመታደግ ተነሳ፣ ተቀላቀለን፤ የመከራችንን ቀን አጭር እንደርገው ዘንድ ጸሃይ ሳትገባብን፣ ሳይመሽብን ኑ ተቀላቀሉን የሚለውን ጥሪ ዛሬም አጠናክሮ ያቀርብልሃል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Wednesday, October 16, 2013

ለአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ፍትሕ አይቀሬ ናት!!!

በፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ማስታወሻ ለአንባቢው: ባለፈው ሳምንት ሐተታዬ ‹‹የዘር አደን›› በሚል አሉባልታዊ ክስ  የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በተሰነዘረበት ክስ ደግፌው ተሟግቼለታለሁ፡፡ በዚህም ሳምንት ድጋፌን በመቀጠል እነዚህ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የፈጠሙትን ግፍና በደል ጭቆና በመዘርዘር ራሳቸውን ነጻ በማድረግ የአይ ሲ ሲን (የኣለም ወንጀለኛ ፍርድ ቤት) ስም በማብጠልጠልና የቆመለትን ዓላማ የሳተ በማስመሰል ገዢዎችና አስፈጻሚዎ ቡችሎቻቸው ያነሱዋቸውን ማስረጃ ቢስ ውንጀላዎች በተጨባጭ ማስረጃ ድርጊቶታቸውንና ሸፍጣቸውን ይፋ ለማድረግ ወስኛለሁ፡፡ የኦክቶበር 11-12, 2013 የአፍሪካ አንድነት ‹‹መሪዎች›› የጨረባ ስብሰባ የተጠራውም ቴአትራዊ የልብ ወለድ ሴራ ለማካሄድና ነጻ ለመምሰል የሚያስችላቸውን ቅጥፈት ለማናፈስ ነው፡፡

በኔ እምነት አይ ሲ ሲ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ሕግጋት ትክክለኛውና ጠንካራው ምልክት ነው፡፡ አይ ሲ ሲ ላለፉት ጥቂት ዓመታት ስራውን በማከናወን ላይ ነው፡፡እስካሁን ያስመዘገባቸው ውጤቶች ጥቂት ቢሆኑም ለወደፊቱ ግን ያሻቸውን በደልና ግፍ ፈጥመው ግድያና አስገድዶ መድፈርን ሰብአዊ መብት በደልን አዘው በማስፈጸም በሥልጣናቸውም አላግባብ ባልገውና ተጠቅመው፤ ሃገርን አራዉተው፤ ሕዝብን በበደልና ግፍ ጫና አጉብጠውና አንበርክከው፤ በነጻ ሲቀመጡና ሲንደላቀቁ የነበሩትን እያጋለጠ ለፍርድ ለማቅረብ የሚችል ጠንካራ ተቋም እንደሚሆን እምነቴ ነው፡፡  የአፍሪካ ጨቋኝና የግፍ በደል ባለቤት የሆኑት ገዢዎች በሕዝቡ ላይ ሊኩራሩና ሊደነፉ፤ የሕግ የበላይነትን በመጨፍለቅ ሊቀጥሉ ይጥሩ ይሆናል፤ አሁን ግን አይ ሲ ሲ ስለመጣባቸውና ለሕዝቡ ወግኖ ስለቆመ ስሙ በተጠራ ጊዜ እየተርበደበዱና መግቢያ እያጡ በመሄዳቸው የአይ ሲ ሲን ስም በማጉደፍ ነጻ ለመሆን ቢጥሩ መንገድ ሁሉ፤ በደላቸው ሁሉ፤ ግፋቸው ሁሉ አይ ሲ ሲን እየቀሰቀሰባቸው በመሆኑ ኦክቶበር 13 2013 የቁም ተዝካራቸው ማውጫ አድርገው ሊሰባሰቡ ነው፡፡

በኦክቶበር 11-12,  2013 አድመኞቹ የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› አስተጋቢው የእንግዳ መቀበያ የአፍሪካ አዳራሽ በመሰባሰብ አብዛኛዎቹ በሮም ከጸደቀው ደንብ (አለም ኣቀፍ ዉል) በመውጣት በደስታ ተሞልተው የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትን የሞት ውሳኔ ያስተላልፋሉ፡፡ ቀብሩንም ለማስፈጸም የኢትዮጵያ የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአፍሪካ  አንድነት ተዘዋዋሪ የ2013ቱ ሊቀመንበር ሃይለማርያም ደሳለኝ ነው፡፡ ስብሰባውንም ሲከፍት ‹‹ዛሬ በዚህ የምጽዋት አዳራሻችን የተሰባሰብነው አይ ሲ ሲን ለማወደስ ሳይሀሆን ልንቀብረው ነው….›› በማለት ይሆናል፡፡ የዚህ የቀብር ጥድፍም ሰበቡ የኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ በተካሄደው የ2007 ምርጫ ወቅት በፈጸመው የሰብአዊ መብት ግፍ ለመጠየቅ ኖቬምበር 12 2013 ለፍርድ ሊቀርብ በመሆኑ ነው፡፡ በተመሳሳይ ወንጀልም ምክትሉ ዊሊያም ሩቶ ፍርዱ በሄይግ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ መታየት ከጀመረ ሁለተኛ ወሩ ነው፡፡ የአፍሪካ አንድነት በኬንያታ እና በሩቶ ላይ የተመሰረተውን ክስ ዘዴ ፈልጎ ካላነሳ በስተቀር ‹‹የኑክሊየር ፈንጂ መቃወሚያውን›› በመጠቀም ከአይ ሲ ሲ አባልነት ለመውጣት እንደሚችልም በማስፈራራት ላይ ነው፡፡

ላለፉት ጥቂት ወራት ሃይለማርያም በአይ ሲ ሲ ላይ የቃል ጦርነት ሲያካሂድ ነበር፡፡ ባለፈው ግንቦት የጃጀዉና በቅዠት ዓለም ያለው ሮበርት ሙጋቤን በመደገፍ በአይ ሲ ሲ ላይ ውንጀላ አካሂዷል፡፡ ግልጽና ማስረጃው ከመጠን ያለፈውን ግፍ ለፈጸመ የአፍሪካ ገዢ ጥብቅና መቆምና ሕዝብን ለባሰ ግፍ ማብቃት የሃይለማርያም የአፍሪካ ወቅታዊ ሊቀመንበርነት ተግባር ሆኗል፡፡ ሃይለማርያም ቃላትን በማሰባሰብና ከጀርባ ባሉት ሽነቋጭ አለቆቹ በመመራት ግራ የገባውን አባባል በመጠቀም አይ ሲ ሲ ‹‹99 በመቶ›› የሆኑት በደለኛ ተከሳሾች አፍሪካውያን በመሆናቸው  የዘር አደን ላይ ነው የሚል መሰረተ ቢስ ወሬ እየነዛ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት በተካሄደው 68ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ባሰማው ወሬው፤ አይ ሲ ሲ የኬንያታንና የሩቶን ክስ በማንሳት ጉዳዩ በኬንያ ባለስልጣናት እንዲታይ ማድረግ አለበት በማለት የማይገባ  የድፍረት ጥያቄ አንስቷል፡፡ ሆኖም ኬንያታ ከተሰነዘረበት ወንጀል ነጻ ሳያደርገው፤ ማድረግ ያሰበው ግን ኬንያታ ራሱ በሚያዘውና መመርያ በሚሰጠው ችሎት ይዳኝ ለማለት ነው፡፡ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ይይላሉ ሲተርቱ፡፡ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያና ናይጄርያ  ለአይ ሲ ሲ ይጋባኝ ሰሚ የኬንያው ክስ እንዲነሳ ያቀረቡትን የጽሁፍ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡

ሃይለማርያም የዚህ ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ጉዳይ አፈጉባኤ ሆኖ የመገኘቱ ምጸታዊ መነሾ አስገራሚ ነው፡፡ 34 የአፍሪካ ሃገራት የሮምን ደንብ/ዉል የፈረሙበት ሲሆን (አይ ሲ ሲ ሰን በማቋቋም ወንጀሎችን በመመርመር ሰብአዊ መብት ጥሰትን የዘር ጭፍጨፋን ግፍ በማጥራት ለፍርድ እንዲያቀርብ ውክልናና ስልጣን ሰጥቶታል):: እስከሁንም ኢትዮጵያ የዚህ ሕግ አባል ለመሆን ፊርማዋን ነፍጋ ቆይታለች፡፡ የሃይለማርያም የሥላጣን አባት ይህን ሕገ ደምብ ላለመፈረም ወስኖ ያቆየው ምናልባትስ አይ ሲ ሲ እንደማይለቀውና ወንጀሉን አጥርቶ እንደሚፋረደው ተገንዝቦ ይሆን? ለፊርማውም ችግር የሆነበት ሰበብ ሕጉን ፈርሞ ከተቀበለው የፊርማው ቀለም ሳይደረቅ በሰራቸው ሕገ ወጥ ተግባራት በፈጃቸውና ባስፈጃቸው ንጹኃን ዜጎች ሳቢያ አይ ሲ ሲ በሩን እንደሚያንኳኳና ለሕግ እንደሚያቀርበው ጠንቅቆ በመረዳቱ ነው?  እነዚያስ 34 ሃገራት ሕጉን አጽድቀው አይ ሲ ሲን ሲያቋቁሙ አይ ሲ ሲ የአፍሪካ ጋሻ መከታ ሆኖ ወንጀለኞችን አላንዳች አድልዎ እያደነ ለፍርድ እንደሚያቀርባቸው አልተገነዘቡትም ነበር?

Tuesday, October 15, 2013

አብሮ ያደገ በሽታ ካልገደለ አይለቅም!


አብሮ አደግ በሽታ ዛሬ ባለንበት በ21ኛው ሴንቸሪ በሕክምና የማይወገድበት ምክንያት ሊኖር አይችልም። ዳሩ ምን ይባላል መሰላችሁ አበው « በሽታውን የሸሸገ መድኃኒት አይገኝለትም » ይላሉ ። አቶ ስብሃትም ሊድን የሚችለውን በሽታ ሸሽጎ አጠነከረው በደሙ ውስጥ ገብቶ ሥር ሰደደበት ፤ ሱስ እንዲሆነው አደረገው ሰው የመግደል ፤ የማሰቃየት ፤ የመዝረፍ ፤ የማንጓጠጥና አስንሶ የማየት አገርንና ዘርን የማጥፋት ተንኮል የመምከር ሱስ!! በዚህ ምክንያት ነው ርእሱን የመረጥኩት፦ ይህ በሽታ ስብሃትንም ካልሞተ አይለቀውም።

ከሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ እንዲሁም አንዳንድ ድሕረ-ገጾች የህወሃት አባላት ወደ አሜሪካ እንደሚመጡ በተደጋጋሚ የዜና ሽፋን ሲሰጡ መሰንበታቸው ይታወሳል። እንደተባለውም የተጠቀሱት የህወሃት አባላት ስደተኛውን ኢትዮጵያዊ በቁጥጥር ሥር ለማድረግ ይመስላል እዚህ መጥተው እመሃላችን ይገኛሉ።የመጡበት ሥራቸውንም እያከናወኑ ይገኛሉ። ከመጡት መካከልም  የንጹሃንን ደም በማፍሰስ የሚታወቀው የገዳዮች ፊታውራሪ ስብሃት ነጋ የገኝበታል ። ስብሃት ነጋ ፀረ-ኢትዮጵያ በተለይም ጸረ- አማራና ጸረ- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አቋም ካላቸውና ለ40 ዓመታት ያህል ይህ የማፍረስ በሽታ ባህሪያቸው ከሆኑት ዋናውና ቀንደኛው መሆኑ ግልጽ ነው። ስብሃት ነጋ  ከበርሃ ጀምሮ በሀገር ቤት ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ባለው የኢትዮጵያ ግዛት የሚገኙ ውድ ኢትዮጵያውያንን በተለይም በጦርነት ምርኮ የተያዙ ፤ እጃቸውን የሰጡ ትውልደ ዓማራ የደርግ ወታደሮችን ጭካኔ በተሞላበት አረመኔያዊ ግድያ የፈጸመ፤በዓላማ አብረውት የተሰለፉና የትግል አጋሮቹን ለምን ኢትዮጵያዊ የሆነ አጀንዳ አነሳችሁ በማለት በቀጥታ ትእዛዝና ግልጽ ባልሆነ መመሪያ በሽዎች የሚቀጠሩ የትግራይ ህዝብ ልጆችን እየበላ የመጣ ሲሆን ከዚያም በመቀጠል የመሀል አገሩን ሕዝብ በሃይምኖት ፤ በዘር እያናከሰ እሱ ካሳደገው ሥርዓት ጋር ለ22 ዓመታት ያህል ዘልቋል።ስብሃት በድርጅቱም ሆነ በህወሃት መንግሥት ከሥርዓቱ ማዕድ ተገለለ ቢባልም የጥፋት መርሁን ባርኮና ቀድሶ ተፈጻሚነት እንዲያገኝ በማድረግ ከፍተኛ ድርሻ የተወጣና አሁንም በዚህ መንገድ እየሄደ እዚህ መድረሱን የማይቀበል ቢኖር እኔ ከዚህ አይነት አመለካከት እለያለሁ ።ስብሃት ነጋ ከዚህ ከመጣ በኋላ እያደረጋቸው (እየፈጸማቸው) ያሉት ድርጊቶች ደግሞ እጅጉን የሚያሳፍሩና ጠብ አጫሪ መሆናቸው ሰውየው ፍጹም በሽተኛ መሆኑን የሚያመላክቱ ናቸው።የሚገርመው ግን ራሱ ስብሃትም ሆነ የሱ አጃቢዎች ምን ያህል እንሰሳዎች እንደሆኑ የሚያሳየው የቆሙበትን መሬት የት እንደሆነ ሳያውቁ የተለመደውን  የወንጀል ተግባር መፈጸማቸው ነው። ስብሃት ከዚህ በፊት ወደዚህ አገር በተደጋጋሚ እንደሚመጣ እሰማ ነበር። ሲመጣ ለምን እንደሚመጣና ምን አድርጎ እንደሚመለስ የያዝኩት መረጃ ባይኖረኝም ከሰውየው የግል ባህሪ ስነሳ አገር ጥሎ እንዲሰደድ ያደረገውን ፤በእስራት ያንገላታውን ፤ሀብቱን ዘርፎ ያደኸውን ፤አፈር ረጭቶ ውሃ ተራጭቶ ካደገበት መንደሩ ያፈናቀለውን ምስኪን ኢትዮጵያዊ ወገናችን ሰላሙን የሚነሳ መርዝ ረጭቶ ከመሄድ ያለፈ እንደማይሆን በግሌ አምንበታለሁ።

Monday, October 14, 2013

ስንቱን አጣን!

በመስፍን ወልደ ማርያም

መስከረም 2006

እንደኢትዮጵያ ባለ ኋላቀር አገር አገር ውስጥ መሠልጠን ብዙ ችግር አለበት፤ እኔ ራሴ በኮምፒዩተር መጻፍ ከጀመርሁ ሠላሳ ዓመት ሊሆነኝ ነው፤ ታዲያ መብራት ጠፋና የምሠራው ባጣ የቆዩ ወረቀቶችን ሳገላብጥ አንድ እአአ በዲሴምበር 26 1965 ከዱሮ ተማሪዬ የተጻፈልኝን ደብዳቤ አገኘሁ፤ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በነበረ ከአንድ በጣም ጎበዝ ወጣት የተላከልኝ ነበረ፤ ከተመረቀ በኋላ በአንድ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ለጥቂት ዓመታት ሠርቶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወደአሜሪካ ሄዶ በሎዝ አንጄለስ አካባቢ ከሚገኝ ትምህርት ቤት ገብቶ ነበር፤ ደብዳቤውን የጻፈልኝ ከዚያ ነው፤ ደብዳቤው ሰባት ገጾች አሉት፤ ከሰባቱ ገጾች አምስቱ ስለኢትዮጵያ ያለውን ስጋት የሚገልጽ ነው፤ በሎዝ አንጀለስ አካባቢ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ብዙዎቹ የሚያሳዩት የመንደረኛነት ስሜት እያበሳጨው የተማሩት ሰዎች በእንደዚህ ያለ ማኅበረሰባዊ ኋላቀርነት ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንዴት መራመድ ትችላለች? እያለ ይሰጋ ነበር።

ደብዳቤውን ላቋርጥና ስለሰውየው ትንሽ ልናገር፤ ተማሪ ሆኖ ክፍል ውስጥ ምንም ነገር የማያሳልፍ በጣም ተከራካሪ ተማሪ ስለነበረ አደንቀው ነበር፤ አንድ ጊዜ እንዲያውም የዘውድ መንግሥት ደጋፊ ነኝ አልሁና አንዴት በትከሻው ላይ ጭንቅላት ያለው ሰው ዓመቱን በሙሉ የዘውድ አገዛዝ የሚያደርስብንን በደልና ችግር ሲነግረን ቆይቶ አሁን ደግሞ ያንን ደጋፊ ነኝ ይላል ብሎ ወረፈኝ፤ ልጁን ስለማውቀው አነጋገሩ አሳቀኝ እንጂ አላስቆጣኝም፤ ጥያቄህ ይገባኛል፤ ግን እኔን ሳትወርፈኝ መጠየቅ ትችል ነበር በዬ ቢቀበለውም ባይቀበለውም ለጥያቄው መልሱን ሰጠሁት፤ በኋላም ጥሩ ጓደኛዬ ነበር።

ከአሜሪካ ትምህርቱን ጨርሶ እንደመጣ ተገናኘንና ወደቀድሞ ሥራው ወደወንጂ ተመልሶ እንደሆነ ስጠይቀው ‹‹እንዴት ብዬ! ዕድሜ ልኬን የፈረንጅ አሽከር ሆኜ መኖር አልፈልግም፤ አሁን ደግሞ ያስተማረኝን ሕዝብ ላገልግል እንጂ!›› ነበር ያለኝ፤ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና በወንጂ ባሉት ደመወዞች መሀከል ከፍተኛ ልዩነት ነበረ፤ ቁም-ነገረኛነቱን፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለውን ታማኝነት፣ የግል ጥቅሙን ቀንሶ ኢትዮጵያን ለመርዳት ባሳየው ተግባራዊ አርአያነት የማደንቀው የወታደር ልጅ ነው።

ይህ ሰው በደርግ ጊዜም አልሸሸም፤ በአንድ ኢንዱስትሪ ውስጥ በሥልጣን ቦታ ላይ ነበር፤ ወያኔ/ኢሕአዴግ ወንበሩን ሲይዝ እንደዚህ ያሉ ሰዎች የማይፈለጉ መሆናቸው ሲታወቅ አገሩን ጥሎ ተሰደደ፤ በትልቅ ዓለም-አቀፍ መሥሪያ ቤት ጥሩ ሥራ አግኝቶ ዕድሜው ለጡረታ እስቲደርስ ቆየ፤ ወደሚወዳት አገሩ ለመመለስ አልቻለም፤ ከአንድ የትምህርት ቤት ጓደኛው ጋር ግንኙነት እንዳለው አውቃለሁ፤ አንድ ቀን ስለዚሁ የጋራ ጓደኛችን ስናወራ ለምን ወደኢትዮጵያ እንደማይመለስ ጠየቅሁ።

የዚህ ወጣት አጎት በወታደርነት ኢትዮጵያን ለረጅም ጊዜ በክብር ያገላገለ ነው፤ ይህ ሰው ወያኔና ሻቢያ በተጣሉ ጊዜ ዜግነታቸው በጉልበት እየተገፈፈ ከአገራቸው እንዲወጡ ከተደረጉት ሰዎች አንዱ ነው፤ በዚያን ጊዜ በሌላ የኤርትራ ተወላጅ ላይ የተፈጸመውን ግፍ ራሱ ሰውዬው በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ሲናገር የሰማሁት የሚከተለውን ነው፤– ‹‹ለኢትዮጵያ በአለኝ ሁሉ አገልግያለሁ፤ ኢትዮጵያን ሳገለግል አንድ እግሬን አጥቻለሁ፤  አንድ ሰው ለአገሩ ከዚህ የበለጠ ምን ያደርጋል?›› ብሎ ሲናገር አስለቅሶኛል።

የኔ የቀድሞ ተማሪና ወዳጅም ለምን ወደኢትዮጵያ እንደማይመለስ ሲጠየቅ ‹‹ለጋሼ (ማለት ለአጎቱ) ያልሆነች ኢትዮጵያ ለእኔ አንዴት ትሆነኛለች?  በማለት በጥያቄ መለሰ አሉ፤ አባቱ ያገለገላትን፣ አጎቱ የለፋላትን፣ አያት ቅድመ-አያቶች የሞቱላትንና የደሙላትን አገር እንዲህ በቀላሉ ማጣት ነፍስን ያቆስላል፤ የነዚያን ሰዎች ሁሉ መስዋእት ያከሽፋል፤ ያረክሰዋል፤ ይህንን የተገነዘቡና ያዘኑ፣ ያለቀሱ ሰዎች ናቸው –

እናት ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፣

የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!

Saturday, October 12, 2013

መብቱን ለማስከበር ታስሮም እንደማያጎበድድ በእስር ላይ የሚገኘው አንዷለም አራጌ አረጋገጠ

ፋሽስት ወያኔ ባቀነባበረው የውሸት ክስ በሽብርተኝነት ተከሶና በወያኔ አሻንጉሊት ዳኞች እድሜ ልክ ተፈርዶበት ቃሊቲ ወህኒ ቤት የሚገኘው የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አንዳለም አራጌ ዛሬም በእስር ቤት ለመብቱ እየታገለ እንደሆነ ተገለጸ። በውጭ ያሉት የተቃውሞ ሃይሎች መሰባሰብና እየተጠናከሩ መምጣት ሰላም የነሳው ፋሽስት ወያኔ በሀገር ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ባለው የፓርቲዎች ሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ ላይ ዛቻ እንዲያሰማ እንዳደረገው ይታወሳል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ነው እንግዲህ ፋሽስት ወያኔ ለአቶ አንዷለም አራጌ ሰላም በማሰብ በሚል በእስር ቤት የሚጠይቁትን ሰዎች ቁጥር ለመወሰን የፈለገው።

ፋሽስት ወያኔ ከሌሎች የቆዩ እስረኛ ጓደኞቹ ጋር እንዳይገናኝ በማሰብ እስካሁን ድረስ አቶ አንዷለም አራጌን በጊዜያዊ ማቆያ ውስጥ ማሰሩ ሳያንስ ይህን የነጻነት ታጋይ የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር ለመገደብ በመወሰን እነማን እንዲጎበኙት እንደሚፈልግ ስም ዝርዝር እንዲያቀርብ ጥያቄ ማቅረቡ አንዷለምን አበሳጭቷል ተብሏል። በማንኛውም ጊዜና ቦታ ለመብቱ እንደቆመ አስረግጦ በማሳየት ላይ ያለው አንዷለም ግን “መጎብኘት ሕገመንግስታዊ መብቴ ነው ። የስም ዝርዝርም አልሰጥም” በማለቱ የተነሳ ከመስከረም 29 2006 ዓ/ም ጀምሮ ማንም ሰው እንዳይጎበኘው ክልከላ መጣሉን ፓርቲው አንድነት አሳውቋል።

ፖለቲከኛና ሚስማር ሲመታ ይጠብቃል የሚሉ ወገኖች የነጻነት ታጋዩ የሞራል ፅናትና ጥንካሬ ከመቼውም በላይ መድረሱን አድንቀው፤ ፋሽስት ወያኔ የደረሰበት የወረደና የዘቀጠ የፍርሃት ደረጃ ግን በእስር ቤት አጉሮ እያሰቃያቸው ያሉትን የነፃነት ታጋዮች እስካለማመን አድርሶታል ያላሉ። እውነት አስፈሪ ናት የሚሉት እነዚሁ ወገኖች ሕገመንግስታችን የሚሉትን ተረት ተረት እንኳ ሳይቀር ከፋሽስት ወያኔ በተሻለ ሁኔታ የነጻነት ታጋዩ አንዷለም አራጌ አሳምሮ እንደሚያውቀውና እያከበረው መሆኑን የሚያውቀው ሕሊናቸው ጫፍ ከሌለው ፍርሃት ውስጥ እንደከተታቸውም ጨምረው ጠቁመዋል።

በወያኔው ብአዴን ውጥረት የነገሰበት ግምገማ ከ 170 በላይ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ እንዳስገቡ ተጠቆመ


ሁልጊዜም በያመቱ የአባላት ግምገማ (በሂሳብ ሰዎች አጠራር የሰዎች ኢንቬንተሪ) የሚያካሂደው ፋሽስት ወያኔ፤ የታመመ፣ የደከመ፣ ተነሳሽነት የጎደለው እንዲሁም ሌላል ሌላም በሚል ሰበብ፤ የፖለቲካ አቋም መስመራቸውን ያላስተካከሉ የሚላቸውን እንደሚቀጣ ይታወቃል። በዚህ መሰረትም ብአዴን የሚባለው የወያኔው አንዱ አንጃ ኪራይ ሰብሳቢነት በሚል አጀንዳ የጀመረው ግምገማ ከፍተኛ ውዝግብና መተረማመስ ከመፍጠሩም በላይ በስብሰባው የተገኙ አባላት በብአዴንና በወያኔው አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማት ላይ መሆናቸው ታውቋል።


“ባይናችን እያየነውና እየሰማነው ካለው በአገዛዙ ሹመኞች የሚከወን ንቅዘት አንጻር እኛን እስክርቢቶ ወሰዳችሁ እያሉ መገምገም ፌዝ ነው” ያሉት የግምገማው ተሳታፊዎች “በሚሊዮን ዶላር በሚቆጠር መጠን ወደ ውጭ ሀገራት ባንኮች የሚወጣውን ሃብት መቆጣጠር የተሻለ ነበር” ሲሉ በምሬት ተናግረዋል። አክለውም “ልጆቻችንን በቅጡ ለመመገብና ለማሳደግ ካቃተን አባላት ላይ የአባልነት ክፍያ እያለችሁ ትሰበስባላችሁ ሌላው ግን አገዛዙ የቸረውን የአገዛዝ ቦታ ተጠቅሞ ከሕዝብ በዘረፈው ሃብት ሶስትና አራት ሕንጻዎችን ሲገነባ የሚናገረው የለም፤ እኛም መረረን መኖር አቃተን በዚሁ ሳቢያም አባላት መልቀቂያ እያስገቡ ነው ብለዋል።”

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አክራሪነትና ሽብረተኝነት ላይ ስልጠና እንዲወስዱ እያስገደደ ነዉ


እሱ እራሱ ሽብርተኛ የሆነዉ የወያኔ አገዛዝ ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉ የትምህርት ተቋማት ስለ አክራሪነት፤ ሽብርተኝነትና ጸረ ሰላም እያለ ስለሚጠራቸዉ ኃይሎች መስጠት የጀመረዉን ስልጠና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ለመስጠት ማቀዱ ተሰማ። የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር ዘረኝነት፤ ሙሰኝነትና የሰብዓዊ መብቶች መደፍጠጥ መሆኑን በዉል ለሚረዳና የእነዚህ ሁሉ ችግሮች ምንጭ ደግሞ ወያኔ መሆኑን ለተገነዘበ ህዝብ ወያኔ አክራሪነትና ሽብርተኝነት በሚል ስልጠና መስጠት መጀመሩ ህዝቡ ልቡ እንዲሸፍት ከማድረግ ዉጭ ምንም ዉጤት የማይኖረዉ ከንቱ ድካም መሆኑን አንዳንድ የወያኔ አባላትን ጨምሮ ብዙዎች ይስማሙበታል። በተለይ እንዲህ አይነት ስልጠና ለህጻናት ጭምር መሰጠቱ ብዙዎችን አስቆጥቷል። ለምሳሌ ከሁለት ሳምንት በፊት በክልል ለሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞችና መምህራን ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት፣ በርካታ ተሳታፊዎች እድሜያቸው ከ15 አመታት በታች የሆኑ ተማሪዎች ስልጠናውን እንዳይወስዱ ጠይቀው ነበር።


የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ተማሪዎች ባለፈው አርብ እና ቅዳሜ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ለመመዝገብ ወደ ግቢ በገቡበት ሰአት፣ ምዝገባ ቆሞ ተማሪዎች ስድስት ኪሎ ወደሚገኘው የስብሰባ ማእከል እንዲያቀኑ ከታዘዙ በኋላ በአዉቶቡሶች እየተጫኑ ወደ ስልጠና ቦታ ተወስደዉ ያለፍላጎታቸዉ ቀኑን ሙሉ ስልጠናዉን ሲከታተሉ ዉለዋል። በስልጠናዉ ወቅት የወያኔ ካድሬዎች ለአገዛዙ አደጋ ይፈጥራሉ ብለዉ ያመኑባቸዉን እንደ ግንቦት7፣ ኦነግና ኦብነግ የመሳሰሉትን ድርጅቶች በጸረ ሰላምነትና በአሸባሪነት እንደምሳሌ ተጠቅመዉባቸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ ለሚሰጠው ስልጠና የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ለ10 ቀናት ተዘግተዋል። በከፍተኛ የአመራር ደረጃ የሚገኙ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለ10 ቀናት በአዳማ ከተማ በአክራሪነት እና ሽብርተኝነት ዙሪያ ስልጠና ሲሰጣቸው ከቆየ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ስልጠናው ወደ ታች አመራር አባላት በመውረዱ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች ለ10 ቀናት ያክል ጽህፈት ቤቶቻቸውን ዘግተው ስልጠናውን እየወሰዱ ነው።

አገልግሎት ፈላጊዉ ህዝብ ጉዳዩን ለማስፈጽም ወደ ተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲሄድ ባለስልጣናቱ ስልጠና ላይ ናቸው የሚል መልስ እየተሰጠ ነው። መንግስት በዚህ ስልጠና ምን ለማግኘት እንዳሰበ በግልጽ ባይታወቀም ስልጠናው ወደ ወረዳዎች ሁሉ ይዘልቃል ተብሎአል። እስካሁን ድረስ በስብብሰባው ላይ የሚቀርቡት አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት አብዛኛው ተሰብሳቢ በኢትዮጵያ ውስጥ አክራሪነት አለ ብሎ አያስብም። ይህ ደግሞ ወያኔን ክፉኛ እንዳስደነገጠዉ ለማወቅ ተችላል።

ወያኔ በእሳት የተቃጠሉ አብያተ ቤተክርስቲያናት ለፖለቲካ ፍጆታ አየተጠቀመ ነዉ

ምስራቅ ጎጃም ዉስጥ አዋበልና አነደድ በሚባሉ ወረዳዎች የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ ባለው የአምስት ወር ጊዜ ዉስጥ በእሳት ተቃጥለው መዉደማቸዉንና በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳትና መጽሐፍትም የእሳቱ ሰላባ መሆናቸዉን ምስራቅ ጎጃም ዉስጥ የሚገኙ የዜና ወኪሎቻችን በላኩልን ዜና ገለጹ። በቃጠሎዉ እጅግ ያዘኑት የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል የቃጠሎዉ ምክንያት ባስቸኳይ ተመርምሮ በወንጀለኞቹ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ሰሚ ጆሮ እንዳላገኙ ዘጋቢዎቻችን አክለዉ የላኩልን ዜና ያስረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጉዳዩን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው በክልሉ ቴሌቪዥን በዜና መልክ እንዲገለፅ ያደረጉት ጥረትም አለመሳካቱ ታዉቋል፡፡

በአንድ አካባቢ ብቻ በተለያየ ጊዜ አብያተ ክርስትያናት በተደጋጋሚ ሲቃጠሉና ንብረት ሲወድም በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኋን አንድም ቀን አለመዘገቡ ወንጀሉ የመንግስት እጅ እንዳለበት በግልጽ ያሳያል ሲሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ሰዎች በመናገር ላይ ናቸዉ። ይህንን ጉዳይ በሚመለከት ዘጋቢያችን ያናገራቸዉ አንድ የምስራቅ ጎጃም የባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት ሰራተኛ አብያተ ቤተክርስቲያናቱ መቃጠላቸውን አረጋግጠዉ በቃጠሎው የተነሳ በህዝብና በመንግስት በኩል እንዲሁም በህዝቡና በቱሪዝም ኮሚሽን በኩል ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱን ተናግረዋል። መንግስት ድርጊቱን የፈጸሙት የሙስሊም አክራሪዎች ወይም የማህበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው ሲል፣ ህዝቡ ደግሞ አክራሪዎች አይደሉም በማለት እየተከራከረ መሆኑን ሰራተኛው ጨምሮ ገልጿል። የባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤትም የችግሩ መነሻ በውል ባይታወቅም በአክራሪዎች ምክንያት እንዳልሆ በውል እንደሚያምን አክለው ገልጸዋል።

የሞኝ ዘፈን አሁንም አሁንም አበብዬ


ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች ከዚህ ቀደም በቁንጯቸዉ በመለስ ዜናዊ በኩል እንኮረኩማለን፤ ምላስ እንቆርጣልን ወይም እጅ እናስራለን እያሉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስተላልፉ የነበረዉን የማስፈራሪያ ቃላት ጋጋታ ባለፈዉ ዐርብ መስከረም 26 ቀን ለዚሁ እኩይ ተግባራቸዉ በቀጠሩት ታማኝ ሎሌያቸዉ በኃ/ማሪያም ደሳለኝ በኩል ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል። እንዳሰለጠኑት ጌኛ ፈረስ ወያኔ ባሳየዉ አቅጣጫ ሽምጥ የሚጋልበዉና ከጭንቅላቱ ወጥቶ የሚነገር ምንም ነገር የሌለዉ ኃ/ማሪያም ደሳለኝም የአሜሪካዉን ፕሬዚዳንት የባራክ ኦባማን አባባል እንዳለ በግርድፉ ወስዶ “ከቀይ መስመር በላይ መሄድ የሚፈልግ ይቆነጠጣል” ሲል በዚያ ባልተቆነጠጠ አፉ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ደንፍቷል። የወያኔዉ ተላላኪ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አልገባዉም እንጂ ይህ ቀይ መስመር ታልፉና ወዮላችሁ የሚሉት ዛቻ አንኳን በአንድ ጀምበር ትርምስምሱ ሊወጣ በሚችል የጦር ኃይል ለሚተማመነዉ ወያኔን ለመሰለ ፀረ ህዝብ ኃይል ቀርቶ በህዝብ ሙሉ ፈቃድ የተመረጠዉና የአለማችንን አስፈሪና እጅግ ጠንካራ ጦር የሚመራዉ ባራክ ኦባም ከተናገረና ከዛተ በኋላ ዛቻዉ አላዋጣ ስላለዉ ሌሎች አማራጮችን ለመመልከት ተገድዷል።


ባለፈዉ ዐርብ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ የተናገራቸዉን ተራ ንግግሮች ሁሉ እንመልከት ብንል እንደሱ ስራ ፈቶች አይደለንምና ግዜዉም ፍላጎቱም የለንም፤ ሆኖም አንዳንድ ንግግሮቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱና ለነጻነቱ የሚያደርገዉን ትግል በንቀት አይን የተመለከቱ ናቸዉና ግንቦት 7 የሚያካሄደዉ የነጻነት ትግል ኃ/ማሪያም ደሳለኝን ከወያኔ ባርነት ነጻ ማዉጣትንም ያጠቃልላልና ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ይህንን ምክር አዘል መልዕክታችንን እንዲያዳምጥ እንጋብዘዋለን። ደግሞም የግንቦት ሰባትን እንቅስቃሴ እከታተላለሁ ብሎ ሲናገር ከራሱ አንደበት ሰምተናልና ምክራችንን ይሰማል የሚል ሙሉ እምነት አለን።

ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አገር ዉስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያነሷቸዉን ጥያቄዎች አስመልክቶ ከጋዜጠኞች የቀረበለትን ጥያቄ ሲመልስ ኢትዮጰያ ዉስጥ ወደ ዘጠና የሚጠጉ ፓርቲዎች ስላሉ ዘጠና እሁዶችን መጠበቅ አለብን በማለት ከተጠየቀዉ ጥያቄ ጋር በፍጹም የማይገናኝና እንኳን ከአገር መሪ ከሦስተኛ ክፍል ተማሪም የማይጠበቅ ተራ መልስ መልሷል። ከዚህ በተጨማሪ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እሁድ እሁድ በሚያደርጓቸው ሰላማዊ ሠልፎች የሚያቀርቡት ጥያቄ ተመሳሳይ ስለሆነ መንግሥት ምን ምላሽ መስጠት እንዳለበት ሊገባው አልቻለም በማለት ኃ/ማሪያም የእሱን የራሱን ብቻ ሳይሆን እሱ የሚመራዉ መንግስትም ምን ያክል ጨቅላ መንግስት አንደሆነ በግልጽ ተናግሯል። የኃ/ማሪያምና የጌቶቹ ጨቅላነትና ባዶነት ደግሞ አገር ያወቀዉና ፀሐይ የሞቀዉ እዉነት ነዉና ብዙ መረጃ የሚያስፈልገዉ አይመሰለንም።ከሰሞኑ አማካሪ ተብለዉ ኃ/ማሪያምን የከበቡትን ሰዎች መመልከቱ ይበቃል። የጭንቅላቱ ዝገት ለይቶለት በመለስ ዜናዊ ግዜ ስኳር እንዲቅም መተኃራና ወንጂ የተላከዉ አባይ ፀሐዬ እሱ እራሱ ይመረመር እንደሆነ ነዉ እንጂ አባይ ፀሐዬ እንኳን ለፖሊሲ ምርምር የተመራማሪዎችን ዶሴ ለመሸከም የማይበቃ ሰዉ ነዉ . . . ችግሩ “ግም ለግም አብረህ አዝግም” ነዉና ከምሁርና ከአዋቂ ጋር የተጣሉት የወያኔ መሪዎች አንዱን ጅል የሌላዉ ጅል አማካሪ እያደረጉ የፈረደባትን አራት ኪሎን የጅሎች መንደር አደረጓት።

ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ባለፈዉ ዐርብ ከአንድ ሰዐት በላይ በፈጀዉ ጋዜጣዊ መግለጫዉ ወቅት የተናገረዉ አንድ ብቸኛ እዉነት ቢኖር “መንግስት ተቃዋሚዎች ለሚያቀርቡት ጥያቄ ምን አይነት ምላሽ መስጠት እንዳለበት ሊገባዉ አልቻለም ብሎ የተናገረዉ ንግግር ብቻ ነዉ። አዎ በተራ የመንገድ ላይ ፖለቲከኞችና ዘራፊዎች የሚመራዉ የወያኔ /ኢህአዴግ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ የሚቀርብለትን የመብትና የነጻነት ጥያቄ ቀርቶ በአገዛዙ በራሱ መሃል የሚነሱ ጥያቄዎችን በቅጡ ተረድቶ የመወያየት ብቃትም ችሎታም ያለዉ አገዛዝ አይደለም። ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በአንድ በኩል ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለህዝብ ማለት የፈለጉትን ብለዋል፤ ህዝብም በሚገባ ሰምቷቸዋል በማለት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎች ለጠየቁት ጥያቄ መንግስት ተገቢዉን ምላሽ ሰጥቷል አሁን እየጠየቁ ያሉት ተመሳሳይ ጥያቄ ነዉ በማለት እሱም ሆነ ፈላጭ ቆራጩ የወያኔ አገዛዝ እንመራለን የሚሉትን ህዝብ የፖለቲካ ምጥቀት በፍጹም የማይመጥኑና ቀድሟቸዉ የሄደዉን ህዝብ ከኋላ ሆነዉ የሚመሩ ኋላ ቀሮች መሆናቸዉን በግልጽ አሳይቷል። ኃ/ማሪያም በሰላማዊ ሰልፍና በህዝብ መካከል ያለዉ አንድነትና ልዩነት የገባዉ ሰዉ አይመስልም፤ ለዚህ ነዉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያቀረቡት ጥያቄ ለህዝቡ መስሎት ህዝብ ሰምቷቸዋል ብሎ የተናገረዉ፡፡

ኃ/ማሪያም እንደሚለዉ መንግስት የህዝብን ጥያቄ መልሶ ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ከዘረኞች ተላቅቃ ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት አገር ትሆን ነበር፤ ወይም ኃ/ማሪያም እራሱ የሞተ ሰዉ ራዕይ መሸከሙን አቁሞ የራሱ ጭንቅላት ያመነጨዉንና በራሱ እይታ ያየዉን ራዕይ ያጋራን ነበር። ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ፍትህ፤ ነጻነት፤ እኩልነትና ዲሞክራሲ እያሉ የሚጮሁት እነዚህ ጥያቄዎች ካልተመለሱ በሚወክሉት ህዝብና በአገራቸዉ በኢትዮጵያ ላይ ሊደርስ የሚችለዉን መጠነ ሰፊ ችግር ከወዲሁ ስለሚታያቸዉ ነዉ። እርግጠኞች ነን፤ ኃ/ማሪያም ደሳለኝም እንደ ተቃዋሚዎች አገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ነዉና ዘረኞች ያጠለቁለትን ማስክ አዉልቆ በራሱ አይን ማየት ሲጀምር እሱም እንደ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከተቃዋሚዎች ጋር ተሰልፎ ለነጻነቱ መጮህ ይምራል ብለን እናምናለን።

Friday, October 11, 2013

ሳይወለድ ሞት የለም!!!

                                            
                          

                 ከሞረሽ ወገኔ ዓለም አቀፍ የሴቶች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የአገራችን ሕዝብ ታሪክ በአመዛኙ የጦርነት ታሪክ እንደሆነ ይታወቃል። ጦርነት ደግሞ አውዳሚ ነው። በመሆኑም በታሪካችን በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱት ጦርነቶች አያሌ ሕይዎት ጠፍቷል ፣ ከፍተኛ ቁሣዊ እና መንፈሳዊ ኃብት ወድሟል። የተካሄዱት ጦርነቶች ዋነኛ መንስኤ የ«ሥልጣን ለእኔ ይገባኛል» ግብግብ ስለነበር ያደረሱት ጥፋት በተለይ በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ አልነበረም። ስለዚህ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን የጥፋቱም ሆነ የሹመቱ ተጎጂ እና ተጠቃሚ ያደረጉ ነበሩ። ለጥፋቱ ግን ግንባር ቀደም ሠለባና ተጠቂ የሆኑት፥ ሕፃናት ፣ እናቶች እና አረጋውያን እንደሆኑ ይታወቃል።


በታሪካችን አንድ ዘር በብቸኛነት የፖለቲካ ሥልጣንን ጨብጦ ፣ የሌሎችንም ጎሣዎች ጭምር በዘር አደራጅቶ ፣ «ተቀናቃኜ ነው« የሚለውን የሌላውን ነገድ አባሎች ግን በአድማ እና በሤራ ከምድረ-ኢትዮጵያ ለማጥፋት የተንቀሳቀሰበት አጋጣሚ በተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም። በአፍሪቃ ፖለቲካ ፥ በተለይም በኢትዮጵያ ፥ መሆን ያለበት ሣይሆን መሆን የሌለበት ስለሚሆን ፣ አንዳንድ ጊዜ ሁኔታዎች የወለፌንድ ሆነው ይገኛሉ። በተለይም በእኛ ዘመን ከአገሪቱ ሕዝብ አምስት ከመቶ ከማይሞሉት የትግሬ ነገድ የፈለቁት ገዢዎች ፣ ዘጠና አምስት ከመቶ የሚሆነውን የአገሪቱን ዜጎች እጅ ከወርች ጠፍረው አሥረው ያሰቃዩታል። ከሁሉም በላይ የትግሬ-ወያኔ ቡድን የራሱን ነገድ ተወላጆች በጥብቅ የወታደራዊ አደረጃጀት አደራጅቶ ፣ ዐማራ የተሰኘውን ነገድ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት ሌት ተቀን ይባዝናል። ይህ ናዚያዊ ቡድን በዐማራው ሕዝብ ላይ በከፈተው መጠነ ሠፊ የሆነ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ፣ የሥነ-ልቦና ፣ የባህል ፣ የማኅበራዊ እና ወታደራዊ ዘመቻዎች አያሌ ዐማሮች ተገድለዋል ፣ ከሥራ ተባርረዋል ፣ በአሠቃቂ ሁኔታ ተገርፈዋል ፣ ከቀያቸው እና ከአገራቸው ተሰድደዋል ፣ በመረጡት አካባቢ የመኖር መብታቸውን ተገፍፈው ፣ ኃብት ንብረታቸውን ተነጥቀው ተባርረዋል ፣ አልያም በማንነታቸው ተዋራጅ ሆነው በበታችነት ሕይዎታቸውን እንዲገፉ ፈርዶባቸዋል። በሠቆቃው የችግሩ ቀዳሚ ገፈት ቀማሾች የዐማራ ሕፃናት እና እናቶች መሆናቸውን ስናይ ደግሞ ልባችን ይበልጥ ይደማል ፣ ኅሊናችን ይቆስላል። ይህ የታሪካችን እጅግ አሣፋሪው እና አሣዛኙ ምዕራፍ ነው። በመሆኑም የትግሬ-ወያኔዎችን ድርጊት በአንክሮ ላየው የጀርመን ናዚዎች በአይሁዶች ላይ ከፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚበልጥ እንጂ የሚያንስ አይደለም። ግፉ ያንሳል ከተባለ ግን የሚያንሰው እንደ አይሁዶቹ ዐማራው ተደራጅቶ በዘሩ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ለዓለም ኅብረተሰብ አለማሰማቱ ብቻ ነው።

የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም!!! ሃገሪቱ ካለፈው የባሰ አደጋ ተጋርጦባታል!!!

"አገሪቱ በልማት ጎዳና ላይ እየነጎደች ...." ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በትእዛዝ የካዱት

"የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ የለም::ሃገሪቱ ካለፈው የባሰ አደጋ ተጋርጦባታል::" ሪፖርተር ርእስ አንቀጽ  
የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የሕወሓት ሪፖርተር መግለጫ ግጭት #1 ምንሊክ ሳልሳዊ

ኖሚናል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የተባሉት እና በህገመንግስት የተሰጣቸውን ስልጣን በትእዛዝ ብቻ የሚሰሩበት ምንም አይነት አገራዊ ፋይዳ የማያደርጉት ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እና የሕወሓት ታማኝ የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ ያሰፈረው ርእስ አንቀጽ የሃገሪቷ ላይ የሰፈነው አብዮታዊ ዲሞክራሲ አምባገነንነት እያደረሰ ያለውን ችግር እና መጪውን አደጋ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃገሪቱ ምንም አይነት ችግር እንዳሌለ እና ሁሉም ነገር በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዳለ በዲሞክራሲ እና በልማት እየነጎድን ህዝባዊ ድሎችን እየተጎናጸፍን ..ምናምን...የሚሉ እና ሃሰትን የተሞሉ የማደናገሪያ እና የማስፈራሪያ ቃላት ፍርሃት በሚነበብበት ፊታቸው እያስገመገሙ ደስኩረዋል:: የእርሳቸው ንግግር እንደተጠበቀ የሕወሓት ሪፖርተር ጋዜጣ ደሞ እንዲህ ብሎናል::የኢሕኣዴግ ባለስልጣናት ፕሮፓጋንዳ እና የሚከተለውን የሪፖርተር ወቀሳ ይመዝኑት::ሪፖርተር እንደውስጥ አዋቂነቱ ያየውን እና የታዘበውን ሃይለማርያም ደሳለኝ ግን በትእዛዝ የካዱት እኛ ደሞ ያነበብነውን የተከፋፈልነው የታዘብነውን እንደራሳችን እይታ እንደሚከተው በዝርዝር ለማየት እንፈቅዳለን::

ሰብሰብ፣ ጠንከርና ነቃ ያለ የመንግሥት አመራር በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሌለ እና እንደሚያስፈልግ በግልጽ አስቀምቷል:: የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በሞት ሲለዩና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሰየሙ ምንም ችግርና ብጥብጥ እንዳልነበር ይህ ማለት መሪ አልተተካም ሳይሆን ሰብሰብ፣ ጠንከርና ነቃ ያለ መንግሥትና አመራር ስላሌለ አገራችን ያያስፈልጋል እያልን ዓለም የኢኮኖሚ ቀውስ እኛንም እየጐዳን ነው፡፡ ትላልቅና በርካታ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ሲደረጉ በደመነፍስ ባጀት ተመድቦ ከፍተኛ ፋይናንስ ሳይኖር ወደ ላማት ይገባል ፡፡ ከዚህ በፊት ያልነበረ የሃይማኖት ግጭትና ልዩነት እየታየ ነው፡፡ ችግሩ ካልተፈታ አስጊ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ዕድገት የማይሹና የማይመኙ ጠላቶች በእጅጉ እየተፈታተኑን ናቸው፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ጠንካራ መንግሥትና ጠንካራ አመራር የግድ ይላል፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ተንካራ መንግስት እና አመራር እንደሌለ በግልጽ ሪፖርተር አስቀምጧል::

ገዥው ፓርቲ እርስ በኤርሱ እየተዋከበ እና እየተፈረካከሰ በውስጡ መተማመት እንደጠፋ በገሃድ መካሪ መስሎ የመሰከረው ሪፖርተር ኢሕኣዴግ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር አለበት፡ሲል በአደረጃጀቱ ምክንያት አራት አባል ድርጅቶች ቢኖሩትም ሲሠራና ሲንቀሳቀስ እንደ አንድ መሆን አለበት፡፡ኢሓዴግ አራት ድርጅቶችን አክፎ በተለያዩ አሰራሮች በመጠመድ እርስ በራሱ እየተዋጋ እና እየተሸበር መሆኑን ሪፖርተር ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል::ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የጠላት ወሬ ሲሉ ክደዋል::በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከልመራራቅ እና መፈረካከስ እየታየ ነው የሚለው ይሄው ዘገባ እንኳን እየተራራቁ አንድ ተሁኖም ለመፍታት የሚያስቸግሩና የሚፈታተኑ ችግሮች እያጋጠሙ ናቸው፡፡ሲል ጠላቶችና አንዳንድ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ተጣሉና ተሰነጣጠቁ እንደሚባለው ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተገቢና የሚጠበቅ አንድነት፣ መቀራረብ፣ የዓላማ ፅናትና ለመስዋዕትነት ዝግጁነት እየታየ አይደለም፡፡በማለት መክሯል ሆኖም ያለው ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር በሚሉ ቃላቶች ተክቶ አቅርቦታል::

የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የሕወሓት ጋዜጣ ሪፖርተር ግጭት === #2 ምንሊክ ሳልሳዊ
  
-ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን የሚያሳብቁ ተተኪ ቃላቶች ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር
-ሙሰኞችን ማደን - ‘እንትና ይደናገጣል እከሌ ያኮርፋል’ ተብሎ የሚቆምና የሚቀዘቅዝ ትግል 
-የትም ሥፍራ፣ የትም መሥሪያ ቤት በማንኛውም ጊዜ መልካም አስተዳደር እየተጣሰ፣ ፍትሕ እየጠፋ፣ የሕዝብ ጩኸትና ጥሪ ተቀባይ አልባ ሆኗል፡፡

ገዥው ፓርቲ እርስ በእርሱ እየተዋከበ እና እየተፈረካከሰ በውስጡ መተማመት እንደጠፋ በገሃድ መካሪ መስሎ የመሰከረው ሪፖርተር ኢሕኣዴግ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር አለበት፡ሲል በአደረጃጀቱ ምክንያት አራት አባል ድርጅቶች ቢኖሩትም ሲሠራና ሲንቀሳቀስ እንደ አንድ መሆን አለበት፡፡ኢሕኣዴግ አራት ድርጅቶችን አቅፎ በተለያዩ አሰራሮች በመጠመድ እርስ በራሱ እየተዋጋ እና እየተሸበር መሆኑን ሪፖርተር ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን የጠላት ወሬ ሲሉ ክደዋል::በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከል መራራቅ እና መፈረካከስ እየታየ ነው የሚለው ይሄው ዘገባ እንኳን እየተራራቁ አንድ ተሁኖም ለመፍታት የሚያስቸግሩና የሚፈታተኑ ችግሮች እያጋጠሙ ናቸው፡፡ሲል ጠላቶችና አንዳንድ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ተጣሉና ተሰነጣጠቁ እንደሚባለው ሳይሆን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ተገቢና የሚጠበቅ አንድነት፣ መቀራረብ፣ የዓላማ ፅናትና ለመስዋዕትነት ዝግጁነት እየታየ አይደለም፡፡በማለት መክሯል ሆኖም ያለው ገዢ ፓርቲ እየሞተ እየተበታተነ እና እየተልፈሰፈሰ መሆኑን በሚያሳብቁ ተተኪ ቃላቶች ሰብሰብ ነቃ እና ጠንከር በሚሉ ተክቶ አቅርቦታል::

እስክንድር ነጋ በአራት ጎብኚዎች ብቻ እንዲጎበኝ ተደረገ!!!

ታዋቂው የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሚገኝበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረት የጎብኚዎቹ ቅጥር መወሰኑን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ለፍኖተ ነጻነት ገለጹ፡፡

የመስከረም 19/2006 ሰላማዊ ሰልፍ ብስጭት ከፈጠረባቸው አካላት መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብስጭቱን አደባባይ ያወጡበትን እርምጃዎች መውሰድ መጀመሩ እያነጋገረ ነው፡፡ለአንዷለም አራጌ የጎብኚዎቹን ስም እንዲሰጥ ካልሆነ ግን በማንም እንደማይጎበኝ የነገረው አስተዳደሩ የእስክንድርን ጠያቂዎች ቁጥር በአራት መወሰኑ ታውቋል፡፡

ህገ መንግስቱ በግልጽ እስረኞች በወዳጅ ዘመዶቻቸውና ሊጠይቋቸው በሚፈልጓቸው ሰዎች መጎብኘት እንደሚገባቸው ቢደነግግም የቃሊቲው መንግስት ግን ህገ መንግስታዊውን ድንጋጌ በመጣስ በማን አለብኝነት የእስክንድር ጠያቂዎችን በዝቅተኛ ቁጥር ገድቧል፡፡

የማረሚያ ቤቱ ምንጮች እስረኞች ጥፋት ሲፈጽሙ እንዲህ አይነት ህግ ለተወሰነ ግዜ እንደሚወጣባቸው በማስታወስ በእነ እስክንድር ላይ የተላለፈው ውሳኔ ግን ‹‹ጥፋት መፈጸማቸው ሳይነገራቸው ፣ፈጸሙት ለተባለው ጥፋትም ቀርበው መከራከሪያ ሳያቀርቡ መሆኑ ውሳኔውን ፖለቲካዊ ያደርገዋል››ብለዋል፡፡

ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ በተመሳሳይ መልኩ ከጥቂት ሰዎች ውጪ እንደማትጎበኝ እርሷን ለመጠየቅ የሚፈቀድላቸው ሰዎችም ለአስር ደቂቃ ብቻ እንደሚያገኟት ከዚህ ቀደም መዘገቡ አይዘነጋም፡፡

ንንጭ፡ #millionsvoiceforfreedom

አንዷለም አራጌ ለህገ ወጥ ድርጊት ባለመተባበሩ ጎብኚ እንዳይኖረው ተደረገ!!!


በሽብርተኝነት ተከስሶ ዕድሜ ልክ እስራት ተበይኖበት በቃሊቲ ቅጣት ቤት የሚገኘው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ አንዷለም አራጌ በጎብኚዎች እንዳይታይ መደረጉ አንድነት ፓርቲን አሳስቧል፡፡አንዷለም ፍርድ ከተላለፈበት በኋላ በማረሚያ ቤቱ የፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ከጨረሱ እስረኞች ጋር መቀላቀል ይገባው የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ሆን ተብሎ እርሱን ለመጉዳት ጊዜያዊ እስረኞች በሚገኙበት ‹‹ቅጣት ቤት ››ውስጥ እንዲታሰር መደረጉም ህገ ወጥ ድርጊት መሆኑን ፓርቲው አስታውቋል፡፡


አንድነት መስከረም 19/2006 ባደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ለተገኙ ሰዎች በደብዳቤ መልእክቱን በሰደደው አንዷለም የተበሳጩ የሚመስሉት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሃላፊዎች ‹‹አንዷለምን መጠየቅ የሚችሉት ቤተሰቦቹ ብቻ ናቸው በማለት ጠያቂዎችን ሲያጉላሉ ከቆዮ በኋላ ከትናንትና መስከረም 29/2006 ጀምሮ በይፋ ማንንም አናስገባም ማለት ጀምረዋል፡፡

ከማረሚያ ቤቱ ባገኘነው መረጃ መሰረት የእስር ቤቱ ሃላፊዎች አንዷለምን ወደ ቢሮ በመጥራት ‹‹እንዲጠይቁህ የምንፈቅደው ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ ነው፣ስለዚህ በጣም ቅርቤ የምትላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር በመጻፍ ስጠን›› ይሉታል፡፡ሰላማዊው ታጋይ በበኩሉ በጠያቂዎች መጎብኘት ህገ መንግስታዊ መብቱ መሆኑን በመጥቀስ የማንንም ስም ጽፎ እንደማይሰጣቸው በመንገር ወደ ማረፊያው ተመልሷል፡፡

የአንዷለምን ምላሽ የሰሙ ሃላፊዎችም ማንኛውም (የአንዷለም) ጠያቂ ከበር እንዲመለስ የሚያደርግ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ታውቋል፡፡በጉዳዮ ዙሪያ የፓርቲውን አቋም ያንጸባረቁት የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊው አቶ ዳንኤል ተፈራ ‹‹ድርጊቱ የመጀመሪያቸው አይደለም፣ የሆነ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር እንዲህ አይነት እርምጃዎችን ይወስዳሉ፣ሽብርተኛ በማለት ያሰሩት ሰው ምን ያህል ህገ መንግስታዊ መብቶቹን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑንም እግረ መንገዱን አሳይቷቸዋል፡፡የአንዷለም ቁርጠኝነትና መብቴን አላስነካም ማለቱ እንደሁልግዜው አርአያችን ሆኖ ይቀጥላል ››ብለዋል፡፡

የእስር ቤቱ አስተዳደር በበኩሉ እንዲህ አይነት ውሳኔ የተላለፈው ለእስረኞች ደህንነት ተብሎ ነው ብሏል፡፡አንዷለም አራጌ ከዚህ ቀደም በእስር ቤቱ ውስጥ ደረቅ ወንጀል በመፈጸም በታሰረ እስረኛ መደብደቡ አይዘነጋም፡፡

ምንጭ፡ #millionsvoiceforfreedom

Thursday, October 10, 2013

ለመሆኑ እኛ ዐማሮች ምን እስከምንሆን እየጠበቅን ይሆን? – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት!!!



ዘረኛው የትግሬ ወያኔ ቡድን በዐማራው ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማያውቅ በመሆኑ ማነፃፀሪያ ሊገኝለት የሚችል አልሆነም። በአስከፊነቱ ዓለም ያወገዘው የደቡብ አፍሪቃ የአፓርታይድ አገዛዝ እንኳን ጥቁሮችን «አገራችሁ አይደለምና ደቡብ አፍሪቃን ለቅቃችሁ ውጡ» አላለም። ሥርዓተ ትምህርቱንም ለነጮች-ጠቀም አድርጎ ይዘርጋ እንጂ፣ የጥቁሮችን የመማር ዕድል ፈጽሞ አልከለከለም ነበር። አገር የለሾቹ ፍልስጤሞች እንኳን በሚኖሩበት በየትኛውም የዓለም ክፍል የመማር ዕድል አልተነፈጋቸውም፤ በራሷ በእስራኤል ጭምር። ወያኔ በዐማራው ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍ ግን ጥቁሮች በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ አገዛዝ ፣ ፍልስጤሞች በእስራኤል መንግሥት ፣ አይሁዶች በናዚ ጀርመን ፣ ኢትዮጵያውያን በፋሽስት ኢጣሊያ ከተፈጸመባቸው ግፍ በመጠንም ሆነ በዓይነት እጅግ የከፋ እና የሚዘገንን ነው።  

ሙሉ ፅሁፉን የቀረበውን ሊንክ በመጫን ያንብቡ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/8188

አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ !!!


ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት ዉሸትን የማያዉቅ ጠንካራ ክርሰቲያን ነዉ ተብሎ ሲነገርለት ሰምተን ነበር፤ ታድያ ይህ ሰዉ መለስን ሲተካ ብዙዎች በጥርስ የለሽ አንበሳነቱ ቢስማሙም ዉሸት እንደ ንጉስ በነገሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ዉሸት የማያዉቅ መሪ መጣ መባሉ ብዙዎቻችንን ነጻነት የተገኘ ያክል አስደስቶን ነበር። ሆኖም ከወያኔ ጋር የዋለ ሰዉ እራሱን ሆኖ መክረም አይችልምና ኃይለማሪያምም ባስቀመጡት ቦታ የማይገኝ የሌላ መንደር ሰዉ ሆኖ ተገኘ። በዚህም የዜጎችን ተሰፋ አመከነ፤ ደስታቸውንም ወደ ኃዘንና ትካዜ ለወጠው።


ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በመገናኛ ብዙኋን ፊት ያየዉን አላየሁም፤ የሰማዉን አልሰማሁም፤ ያልሆነዉን ሆነ የሆነዉን ደግሞ አልሆነም እያለ ሽምጥጥ አደርጎ የካደዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፤ በእርግጥም ጎበዝ የመለስ ዜናዊ ተማሪ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ኃይለማሪያም ባለፈዉ ዓርብ አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። ይህ ግለሰብ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫዉ ኢትዮጵያን ያክል ትልቅ አገር ከሚመራ ሰዉ ቀርቶ ከአንድ ተራ የቢሮ ተላላኪ እንኳን የማይጠበቅ መልስ ሲመልስ ተስተዉሏል።

ኃይለማሪያም በጋዜጣዊ መግለጫዉ ወቅት ከቀረቡለት ብዙ ዲሪቶ ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ አገር ቤት ውስጥ እየተደረገ ያለው ሠላማዊ ሰልፍ ጉዳይ ነበር። ኃይለማሪያም አገር ቤት የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች “በራሳቸው የሚደረጉ ሳይሆኑ ከኋላ ባሉ ሌሎች ኃይሎች መሪነት የሚደረጉ” ናቸው ሲል ተናግሯል። ኃይለማሪያም ጌቶቹ ፊቱን በጨርቅ አስረዉት የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር፤ መከራና ስደት አልታይ ብሎት ነዉ አንጂ ወያኔን የመሰለ ነብሰ ገዳይ ባለበት አገር ዉስጥ የህዝብን ብሶት የሚያስጋቡ ጥያቄዎች በየቀኑ ይመነጫሉ አንጂ ከዉጭ አገርማ አይመጡም። በሌላ በኩል ደግሞ ይሄዉ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያፈራቸዉ ዋሾ ሰዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያደርጉት ሠላማዊ እንቅስቃሴ የአሸባሪዎች እጅ ያለበትና፤አማኞቹ ሃይማኖታቸውን የወደዱ መስሏቸው ሳያውቁ የገቡበት ስለሆነ እንዲታረሙ እንመክራቸዋለንም” ብሏል። እዚህ ላይ በግልጽ እንደምናየዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እመራዋለሁ የሚለዉን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ፈጽሞ ሊረዳ አልቸለም፤ ስለዚህ ምክር የሚያስፈልገዉ መብትና ነጻነት ምን እንደሆኑ ገብቶት የሚታገለዉ የአትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ኃይለማሪያም እራሱ ነዉ።

እኛ ግንቦት ሰባቶች ወያኔን የመሰለ ጨካኝ እና ምንም አይነት አገራዊ ኃላፊነት የማይሰማውን ዘራፊና ዘረኛ ቡድን በሠላማዊ መንገድ የሚጋፈጡ ወገኖቻችንን እናደንቃለን። እነዚህ ወገኖቻችን ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንደሚለው የማንንም አጀንዳ የተሸከሙ ሳይሆኑ የራሳቸው የሆነ አጀንዳ ያላቸውና ኃይለማሪያም በዉክልና ለሚያስረግጣቸዉ ወገኖቻችዉ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ጅግኖች ናቸዉ። አጀንዳቸውም የተደበቀ ወይም ከጀርባውም ሌላ ነገር ያለው አጀንዳ አይደለም።አጀንዳቸው ግልጽ እና የታወቀ የነፃነት፤ የእኩልነት፤የፍትህና የሠላም አጀንዳ ነው። ኃይለማሪያም ደሳለኝ የዜጎችን ጥያቄ አድምጦ መልስ መስጠት ሲገባው እነዚህን የኢትዮጵያን ህዝብ አጀንዳ ተሸክመው የሚታገሉ ወገኖች ደካሞች አድርጎ ለመሳል የሚያደርገዉ ሙከራ አንድም በተቃዋሚዎቹ ዙሪያ የተሰባሰበውን የሰው ኃይል ካለማወቅ፤ አለዚያም ደግሞ “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ይሏታል ጅግራ” እንደሚባለው ነገር ነው።

ሌላው ኃይለማሪያም የሚናገረዉ ቃል ጠፍቶት በተደጋጋሚ ሲንተባተብ የታየዉ በሽብርተኝነት አካባቢ የተጠየቀዉን ጥያቄ ሲመለስ ነዉ። በእኛ እይታ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዋነኛው አገር በቀል አሸባሪ ህወሃት እና ህውሃት ብቻ ነው። ህወሃት ስልጣን ላይ ያቆየኛል ብሎ ከገመተ የማይመሰርተው የክስ ዓይነት፤ የማያፈሰው የንጹህ ሰው ደም ፤የማያፈነዳው የቦንብ እና የፈንጂ ዓይነት እንደሌለ ከሃውዜን እስከ አዲስ አበባ ያሉ መንገዶች ቋሚ ምስክሮች ናቸው። ይህንን እኩይ ተግባሩን ዓለም ሁሉ እንደሚያውቀው በዊክ-ሊክ ላይ የወጣው መረጃም አሳይቷል።

የህውሃት ታማኝ ሎሌ የሆነዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሠላማዊ ትግሉን ለማፈን ከፈለገ በትግሉ ዙሪያ የተሰባሰቡትን ዜጎች ከሌላ ከማንም ጋር ማነካካት አያስፈልገውም። ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ሁሉ አንደ ኃይለማሪያም ሞቶ የተቀበረን ሰዉ ራዕይ የተሸከሙ የአመለካከት ደሃዎች ሳይሆኑ የራሳቸው አስተሳሰብና ህያዉ ራዕይ ያላቸው ዜጎች ናቸው። አነዚህን ሠላማዊ ታጋዮች ከማይገናኝ ሌላ ኃይል ጋር አቆራኝቶ ለመምታት መሞከር ለኃይለማሪያምም ሆነ ለጌቶቹ አይበጃቸዉም። ዛሬ በወያኔ ነብሰ ገዳይ ወታደሮች ተከብቦ እዩኝ እዩኝ የሚለዉ ኃይለማሪያም ደሳለኝም የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጣ የነደደ ቀን ደብቁኝ ማለት ይመጣልና ያ ቀን ከመምጣቱ በፊት የበደለዉን ህዝብ ይቅርታ ጠይቆ የነጻነት ኃይሎችን እንዲቀላቀል ወገናዊ ምክራችንን እንለግሳለን።

በመጨረሻም ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ስለ ግንቦት ሰባት ተጠይቆ ሲመልስ ግንቦት ሰባት “በህልም ውስጥ ያለ ድርጅት” ነው ብሏል። ታድያ ምነዉ ተኝቶ ህልም የሚያልም ድርጅት ኃ/ማሪያምንና ጌቶቹን እንዲህ ያቃዣቸዋል? ለምንስ ይሆን ወያኔና ታማኝ ሎሌዉ ኃ/ማሪያም ያገኙትን ሁሉ ግንቦት ሰባት እያሉ የሚያስሩት፤ የሚደበድቡትና የሚገድሉት? ያገኛችሁትን ሁሉ የግንቦት ሰባት አባል እያላችሁ ትከሳላችሁ? ለምንስ በግንቦት ሰባት ስም ታስራላችሁ? ትገርፋላችሁ? ትገድላላችሁ? ተኝቶ ለሚያንቀላፋ ድርጅት ለምን ትሸበራላችሁ፤ ለምንስ እንቅልፍ አጥታችሁ ትባዝናላችሁ? ግንቦት ሰባት እናንተ አልገባችሁም አንጂ መነሻውንና መድረሻውን አጥርቶ የሚያውቅ፤ ከደመናው ባሻገር ፍንትው ያለ የነፃነት ዉጋገን የሚታየው ባለ ታላቅ ራዕይ ድርጅት ነው። አስኪ ምናልባት ቢገባችሁ ተረት ቢጤ እንንገራችሁ፤

“አንዲት ሚዳቋ ነበርች አሉ። ሚዳቆ ከመሬት ገንዘብ ተበድራ ሲትኖር ከእለታት አንድ ቀን መሬት አፍ አውጥታ ብድሬን መልሽ አንጂ ብላ ትጠይቃታለች። ሚዳቆዋም ደንግጣ ከነበረችበት ቦታ ፈትለክ ብላ ወደ ተራራ ጫፍ ላይ ወጥታ እፎይ ያንን ድምጽ ከአሁን በኋላ አልሰማም አለች። መሬትም በይ ብሬን ክፈይኝ ስትል ዳግም ጠየቀቻት። እንዴ ይህች መሬት የሌለችበት ዬት አገር ሊሂድ ብላ ሚዳቆ ወደ ማይታወቅ ቦታ ተፈተለከች። ከዚያም እያለከለከች በቃ አሁንስ አታገኚኝም ስትል አሁንም መሬት ብቅ ብላ እየጠበኩሽ ነውኮ ብድሬን ክፈይ እንጂ ስትል ጠንከር አድርጋ ጠየቀቻት። ሚዳቆዋም መሬት የሌለችበት ልትደረስ ስትበር ስትበር ሳንባዋ ፈንድቶ ሞተች”ይባላል።

የፍትህ፤ የእኩልነት፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች እንደ መሬት ናቸው። የትም ሂዱ፤ የትም ግቡ ይከተሏችኋል። መስጊድ ዉስጥ አሉ፤ ቤተክርስትያናት ውስጥ አሉ። ቤተመንግሰት ዉስጥም አሉ። የሌሉበት ቦታ የለም። መፍትሄው እንደ ሚዳቆዋ መሸሽ አይደለም። መፍትሄው ዜጎች የሚያነሷቸውን የፍትህ፤ የእኩልነ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን አድምጦ ትክክለኛ መልስ መስጠትና ከዕዳ ነጻ መሆን ብቻ ነዉ ። ከዚህ ዉጭ ጥያቄን ላለመስማት ወይም ሰምቶ ለመደፍጠጥ የሚደረገው ከንቱ ሩጫ መጨረሻው እንደ ሚዳቆዋ መፈንዳት እንጂ ህይወት አይሆንላችሁም።

እኛ ግንቦት ሰባቶች ዘረኛዉንና አሸባሪውንና የወያኔ ስርዐት ለመደምሰስና ህዝብ በነፃነት ያለፍርሃት የሚኖርበትን አገር ለመፍጠር ቆርጠን ተነስተናል። ከእንግዲህ የሚያቆመን ምንም ነገር የለም። የምንታገለዉ ለህዝብ ጥያቄያችንም ህዝባዊ ጥያቄ ነዉና እኛም አንደጥያቄዉ በየመስጊዱ፤ በየቤተክርሲቲያኑና በየሰፈሩ ዉስጥ አለን።እኛ የሌለንበት ስፍራ የለም። በዚህ አጋጣሚ የዘመናት ትግላችን ፍሬዉ የሚታይበት ቀን እጅግ በጣም ቅርብ ነዉና የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም አገር ተረካቢ የሆነዉ ወጣቱ ትዉልድ እራሱን፤ ወገኖቹንና እናት አገሩን ለማዳን የሚደረገዉን የነጻነት ትግል እየመጣ እንዲቀላቀል ወገናዊ ጥሪያችንን አቅርበናል። ኑ እና ተቀላቀሉን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

በሃገራችን የአባታዊነት ወረርሽኝ በሽታ ይወገድ (ከአስገደ ገ/ስላሴ ከመቐለ)

አባታዊነትና ሎሌነት ለአገር እድገት እንቅፋት ናቸዉ።

ኢትዮጵያ አገራችን ቀደም ሲል የንጉሱ የዘውድ አገዛዝ እኔን ያላከበረ ያላመለከ እኛ ያልነዉ ያልታዘዘ በዚች ምድር አይኖራትም ይሉን ነበር።ከአባታዊነትም አልፎ ለንጉሱ የአምላክን ያህል እንዲያመልክ ይታዘዝ ነበር።የዘውዳዊ ስርአት ግን የተሻለ ነበር።

ኃላም የዘውዳዊ አባታዊ ስርአት በጭቁኖች ተቃውሞና ትግል ተፍረክርኮ ሲወድቅ በወቅቱ ይደረግ የነበረ ትግል ያልተደራጀና ሲቪላዊ የሆነ የተረዳጀ ፓርቲ ስላልነበረ የአባታዊ ዘውዳዊ ስርአት አገልጋይ የነበረ ወታደራዊ ደርግ በትረ ስልጣን ጨብጦ ከአባታዊነት በባሰ አንባገነናዊና ገዳይ ወታደራዊ ደርግ ተተካ።

§     ደርግ ገና አንድ አመት ሳይቆይ በወቅቱ 60ሚሊዮን አካባቢ ለነበረዉ ህዝባችን በመዳፉ ስር በማስገባት ሁሉንም አይነት ነፃነት በማፈን የመናገር፣ ሃሳብን በነፃ የመግለፅ ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ፍፁም አባታዊ በሆነ መንገድ በአዋጅ ዘጋዉ መላዉ ህዝባችን መፈናፈኛ አጥቶ ግማሹ ነፍጥ አንስቶ ወደ ትግል ሜዳ ሲወርደ ሌላዉ ለስደት ተዳረገ፣፣ የቀረዉ ህዝብ ለ17 አመት በአባታዊ ፋሽስት ደርግ ታፍኖ ኖረ።

§   በዛን ጊዜ የዘውዳዊ አገዛዝና የደርግ ፋሽስታዊ ስርአት አገዛዝ በመቃወም ደርግ ለመጣል በሰላማዊ መንገድ አይቻልም ብለዉ በወቅቱ የነበሩ ምሁራኖች ለወዛደሮች ጭቁን ገበሬዎች በማንቃትና በማደራጀት እንዲሁም ባልተደራጀ በተናጠል በሁሉም የሃገራችን ክልሎች ብሄር ብሄረሰቦች ተሰማርተዉ በፖለቲካ ፓርቲና በቡድን በመደራጀት አባታዊ ፋሽስታዊ ደርግን በትግል  ለመጣል ነፍጥ ይዘዉ ዘመቱ።

§  ወደ ትጥቅ ትግል የዘመቱ ወገኖችም ብዙም ጥናት ሳያደርጉ  በግብታዊነት አንዳንዶቹ የብሄር ጥያቄ ሌሎችም ምንም ታሪካዊ መነሻ የሌላቸዉ ከአማራ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት ለመገንጠል የሚል አስተሳሰብ በመያዝ በሌላ አቅጣጫ የአንድነት ጥያቄ ግምት ላይ ያላስገባ አቋም የያዙም ነበሩ።መስመር በመያዝ ነገር ግን የነበረዉ የብሄሮች ግጭትና መቃቃር  ግምት ውስት ሳያስገቡ የተነሱ ነበሩ፣፣

§  በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ ወገኖች በሃገራችን የሚደረግ ትግል በደርግ ስርአት ውስጥ ሆነህ አስተካክሎ በማረም ለውጥ ሊመጣ ይችላል ብለዉ ደርግ ከደርግ ጋር ሆነዉ ብዙ ድርጊት የተፈፀሙ ነበሩ።

§  ከላይ የተጠቀሱት ሃይሎች እምቢ ለፋሽስታዊ አባታዊ አገዛዝ ብለዉ በወኔ ለመታገል በመዝመት እጅጉን የሚያስመሰግናቸዉ ቢሆንም በየአቅጣጫዉ ወደ ትግል የዘመቱ ሃይሎች ተስማምተዉ በሚያገናኛቸዉ ሃሳብ  ካለ በውይይት ልዩነት በማጥበብ አብረዉ ለአንድ ጠላት እንደማጥቃት ፋንታ ከዘውዳዊ አገዛዝና ከፋሽስታዊ ደርግ በወረሱት የአባታዊነት ከኔ በላይ ላሳር በሚል ፈሊጥ የኔ መስመር (አላማ) ይበልጣል ከሚል አባታዊ የሆነ ትእቢት እርሰ በራሳቸዉ በነፍጥና በሌላ ውስጥ ለውስጥ ሴራ ተጫርሷል።

§  በዚህ የአባታዊነት ባህሪያቸዉና ስራቸዉ ዋናዎቹ ተጠቃሾች በወቅቱ የነበሩት ፓርቲዎች በሙሉ ተጠያቂዎች ቢሆኑም የሁሉም ባህሪያት በዚች አጭር ፅሁፌ የሁሉም ገመና ለማስቀመጥ ስለማይቻል  ህ.ዋ.ሓ.ት ከተፈጠረበት ዓ/ም እስከ አለንበት ዘመን አባታዊነት ተጠናውቶት የቆየውና ያለዉ ህ.ወ.ሓ.ት አመራር ቀደም ሲል በ17 አመቱ የትጥቅ ትግል ወቅት ረጂም ሳይጓዝ በጊዜዉ ከነበሩት ፀረ ደርግ ሃይሎች በነፍጥ የሚዋጉ ተስማምቶና ተቻችሎ ለአንድ ጠላት ተባብሮ ከመምታት ፈንታ ገና በጥዋቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ለነበሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከአያቱ ጃንሆይና ከአባቱ ደርግ የወረሰዉ  የአባታዊነት ባህሪ ህዝቦች ባሉበት አካባቢ ማንም ፓርቲ መንቀሳቀስ የለበትም በሚል በግንባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ (T..L.F)   ( ግገሓት ) በመጨፍለቅ የጀመረዉ ኃላም ለተጋድሎ ሓርነት ትግራይ ጠርናፊት ኮሚቴ፣ ለኢድዩ፣ ለኢህአፓ በየተራ አጠፋቸዉ።

§  በህ.ወ.ሓ.ት ፓርቲ ውስጥ በአባላቱ ለሚነሱት ሃገራዊና አህጉራዊ ጥያቄ ስለዲሞክራሲና ስለሰብኣዊ መብት ጥያቄዎች ሲነሱ ሰከን ብሎ አስቦ በዲሞክራሲያዊ መንገድ አሳርጎ ከመፍታት ፈንታ በማሰር በመቅጣት በማባረር ነበር የሚፈታዉ። በተጨማሪ በፓርቲዉ ስለፖለቲካዊ ዲፕሎማሲያዊ  ፋይናንሳዊ ጥያቄ በሚነሳበት ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለበት ፍትሃዊ መልስ እንደመስጠት  ፋንታ ለዚሁም ከኔ በላይ ላሳር በሚል አባታዊ  ፈሊጥ ነበር የሚያስተናግደዉ።

§  በአሁኑ ጊዜም ህ.ወ.ሓ.ት  ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከጥንት ጀምሮ  የነበረዉ የአባታዊነት ባህሪ ሳይከለስ በሃገራችን ህገ-መንግስት መሰረት አድርገዉ በተቃዋሚ ፖለቲካዊ ፓርቲ ተደራጅተዉ በሰላማዊ መንገድ ለሚታገሉ በትጥቅ ትግል ጊዜ እንደለመደዉ ህግ-መንግስትን በመጣስ እኔ ካልኳችሁ ግቡ ፤ውጡ በማለት አባታዊ ተግባራቱ በመፈፀም የሰላማዊ ትግሉን እያጨለመዉ ይገኛል።

§  በሌላ በኩል የህ.ወ.ሓ.ት መንግስት አባታዊ ባህሪውን በሰላማዊ  መንገድ ለሚታገሉ ፓርቲዎች  ብቻ አይደሉም  እየፈፀመ ያለዉ። መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ምሁሩ፣ ነጋዴዉ፣ ተማሪዉ፣ አርሶአደሩ፣ አርብቶቸደሩ፣ የመንግስት ሰራተኛ እኛ ባልንህ መንገድ ሂድ በማለት እንዳይናገር፣ እንዳይቃወም በስለላ  ወጥመድ በመያዝ እንዲሁም ትናንት መሬት የህዝብ  ነዉ ይል የነበረዉ አባታዊ ፓርቲ የገጠርም የከተማም መሬት የኔ ነዉ ብሎ ህዝቡ ዜግነቱ አጥቶ ሞራሉ እንዲነጠቅ አድርጓል።