Saturday, September 26, 2015

United Movement for the Salvation of Ethiopia through Democracy:



Launching an Effective Resistance against TPLF Tyranny – a tyranny which is the Real Driver of Instability and Civil Strife in Ethiopia

Ethiopia is one of the oldest nation-states in the world. Both written and oral history and recent archeological discoveries, despite regional rivalries, suggest the historical continuity of the nation. It was a Monarchy until 1974. From 1974 to 1991 the country was declared to be ‘Peoples Democratic Republic’ by the military junta, Derg, and went through a traumatic experience. Tigrai Peoples Liberation Front (TPLF), a guerrilla force from a minority ethnic group that led the rebellion against the military junta and captured the institutions of the State, has been in power for the past 24 years. The country is ruled as a one-party state under a façade of multi-party system since 1991.

The state is characterized by an intensifying political repression, rampant economic corruption, denial of basic human and political rights and repeated sham elections. The top brass of the army and security organs of the state, including key diplomatic positions, are effectively mono-ethnic despite the claim of the regime to stand for the equality of all ethnic groups. The people have completely lost confidence in the government after the regime shamelessly declared itself to have won 100% of the parliamentary seats in the 2015 election. Ethiopians, with no other choice available to them for democratic transition, have now risen up in arms. And this is a credible threat of force to the regime. History has time and again proven that no government that denies freedom, justice and democracy to its people will not survive their wrath.

Against this background, Ethiopian democratic forces, reflecting the broad diversity of the Ethiopian society, have recently formed the United Movement for the Salvation of Ethiopia through Democracy (UMSED) as an umbrella organization. UMSED is committed to coordinate the people’s struggle for effective resistance against TPLF’s tyranny and to ensure the transition to true democracy and stable political order in Ethiopia. No one relishes the idea of armed conflict; but, there are times when armed self-defense becomes the only choice to resist the unbearable violence by minority against majorities and to bring about an enduring peace and stability in a society.

Ethiopians have given up on elections as they have become meaningless rituals: There have been five national elections under the TPLF. The first election in 1995 resulted in 3 opposition members being elected to the parliament that has a total of 548 MPs. In the second election of 2000, the number for the opposition members rose to 27. In the 2005 general election, which was monitored by the Carter Center, European Union and other observers, Ethiopians turned out in record numbers and voted for the opposition, mainly CUD and UEDF. The results were rigged; and the election was blatantly stolen.

Tuesday, September 22, 2015

የተናገሩት ከሚጠፋ . . . (በኤፍሬም ማዴቦ)

                                                                   
ባለፈዉ መጣጥፌ “ቃል የእምነት ዕዳ ነዉ” ብዬ ጀምሬ “ቃላችን አይለወጥ” ብዬ ነበር የተለየኋችሁ። አለምክንያት አልነበረም እንዲህ ያልኳችሁ፤ በአንድ በኩለ ቃል መከበርም መከፈልም ያለበት ዕዳ ስለሆነ በሌላ በኩል ደግሞ ቀትር ላይ የገባዉን ቃል ሳይመሽ እንደ ጴጥሮስ ሦስቴ የሚክድ ብዙ ቃላ አባይ ሰላለ ነዉ። አገሬን ከወያኔ አጸዳለሁ ብሎ ቃል የሚገባ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዕዳ አለበት። ዕዳዉ ደግሞ ገንዘብ ወይም ንብረት አይደለም። ቃሉን መጠበቅ ወይም ቃሉን ማክበር ነዉ። ደግሞም አንድ ሰዉ የተናገርዉን ቃል ሰብሮ የእምነት ባለዕዳ ከሚሆን ዕድሜ ልኩን የገንዘብ ባለዕዳ ቢሆን ይሻለዋል። የገንዘብ ዕዳ ቆይቶም ቢሆን ይከፈላል ወይም አበዳሪዉ ሊምረን ይችላል፤ የዕምነት ዕዳ ግን የማይሽር ጠባሳዉ እየቆረቆረን አብሮን ይኖራል እንጂ አይጠፋም። ማንም ሰዉ ለአገሬ ህይወቴን እሰጣለሁ ብሎ ቃል ሲገባ መሃላዉ ከህዝብና ከአገር ጋር ብቻ አይደለም፤ እንዳዉም የሰዉ ልጅ ቃል የሚገባዉ መጀመሪያ ከራሱ ጋር ነዉ። ለራሱ የገባዉን ቃል የማያከብርና ቃሌ ቃል ነዉ ብሎ የገዛ ራሱን የእምነት ዕዳ ያልከፈለ ሰዉ ለህዝብና ለአገር ቃል መግባት አይችልም። ዛሬ ወያኔን እናጥፋ ብሎ ካራ ጨብጦ አብሮኝ የቆመ ሰዉ ነገ ከወያኔ ጋር ሆኖ ካራዉን እኔዉ ላይ አዙሮ ባየዉ እሱ ቀድሞዉንም ካራ የጨበጠዉ ወያኔን ለማጥፋት ሳይሆን ስጋ ሊቆርጥብት ነዉና ብዙ አይገርመኝም። እንዲህ አይነቱን ለቁም ነገር ሲፈልጉት አልሰማ ብሎ ሆዱ ሲሞላለት ግን ሳይጠሩት አቤት የሚል ስጋ ወዳድ ሆዳም ደግሞ ኢትዮጵያ በየዘመኑ አፍርታለችና ብዙ ሊገርመን አይገባም።  ከሰሞኑ ከምድረ ኤርትራ የነፈሰዉ ነፋስ ያስተማረን አንድ ትልቅ ቁም ነገር ቢኖር እንዲህ አይነቱን ሞላ ጎደለ የሚባል የካራና የስጋ ጨዋታ ነዉ። አዎ! የካራ ጨወታ – ወዲህ ማዶ ስጋ ሊቆርጡበት ወዲያ ማዶም ስጋ ሊቆርጡበት።

“የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” . . . ገዢዎቻችን በተለይ የዛሬዎቹ ቃል አባዮች እንደቆሻሻ ዕቃ መሬት ላይ ጣሉት እንጂ ቃል የዕምነት ዕዳ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ዘመን አይሽሬ የአገራችን አባባል ነዉ። አባቶቻችን የተናገሩትን ወይም ቃል ገብተዉ የተማማሉትን ነገር ከሚያጥፉ የወለዱትን ማጣት ይቀላቸዋል። እኛ ልጆቻቸዉ ግን ከዬት የመጣን ጉዶች አንደሆንን አላዉቅም ቃል አባይነታችን እኛን፤ ልጆቻቸንና አገራችንን ሲያጠፋ በአይናችን እያየን ቅር እንኳን አይለንም። “እመጣለሁ ብሎ ሰዉ እንዴት ይዋሻል፤ ማበል እንኳን አንቺን ምድር ያበላሻል” መሬት ላይ ጠብ የማይል ትክክለኛ አባባል ነዉ። አገራችን ኢትዮጵያ ትናንት እንሞትልሻለን ብለዉ ዛሬ በሚገድሏት ቃል አባይ ልጆቿ እየተበላሸች ነዉ። እነዚህ ቃልአባዮች የኢትዮጵያን የምድር ላይና የምድር ዉስጥ ኋብቷን አንጂ የገረጣዉን ፊቷን ማየት አይፈልጉም- አዎ ወያኔ የሚያየዉ ኃብትሽን፤ የሳዑዲዉ ሰዉ ወርቅሽን፤ ባዕድ ከበርቴዉ ለምለም መሬትሽን . . . ወይኔ ኢትዮጵያ ማን ይሆን የሚያየዉ የጠቆረዉ ፊትሽን፤ ማን ይሆን የሚያብሰዉ እምባሽን፤ እኮ ማን ይሆን የሚያቆመዉ መከራሺን . . .  ማን ይሆን?. . . ማን ይሆን?

የዛሬዋ ኢትዮጵያ አንድ ትዉልድ ዉሸት ብቻ እየሰማ ያደገባት የዉሸት መዲና ሆናለች። ጳጳሱ፤ ቄሱና ፓስተሩ “እኔ መንገድ፤ አዉነትና ህይወትና ነኝ” ያለዉን የሰማዩን አምላካቸዉን ረስተዉ ለምድር ዉሸታሞች አደሩ። ሂዱና ዋሹ ሲባሉ ሄደዉ ዋሹ፤ እዉነትን በዉሸት አስተባብሉ ሲባሉ አስተባበሉ፤ በሀሰት መስክሩ ሲባሉ አፋቸዉን ሞልተዉ በሀሰት መሰከሩ።  “ታላቁ መሪ” እየዋሸን ኖሮ እየዋሸን ሞተ። መታወቂያዉ ዉሸት ነዉና ሞቶም አልሞተም ተብሎ ተዋሸለት። ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር ምን ለምዳ ትመጣለች እንዲሉ ሌላ ሁሉ ቢቀር ዉሸትን ይፀየፋል ተብሎ የተነገረለት የዛሬዉ ጠ/ሚኒስቴር ጭራሽ “ታላቁን መሪ” እንደዋቢ እየጠቀሰ ስራዉ ሁሉ ዉሸት፤ ዉሸት፤ ዉሸት ብቻ ሆኖ ቀረ። የኢትዮጵያ ሬድዮ ሲከፈት ዉሸት ይናገራል፤ ሲዘጋ ደግሞ ነገ ስለሚዋሸዉ ዉሸት ያስባል። ጋዜጦች በስህተት አንኳን እዉነት አይጻፍባቸዉም። የኢቲቪ ዜና አንባቢ ተመስገን በየነ ግማሽ ሰዐት የዋሸዉን ዉሸት ለማካካስ ዜናዉን አንብቦ ሲጨርስ ለ15 ደቂቃ ጎንበስ ብሎ ይሰግዳል።

ለረጂም ግዜ ተማምነን ጀርባችንን የሰጠነዉ ሰዉ ለጠላት እጁን ሰጥቶ ጦርነት ሲያዉጅብን አንዳንዴ በትግሉ ዉስጥ ማንን አምነን ጀርባችንን እንደምንሰጠዉ ግራ ሊገባን ይችላል። ከሰሞኑ የሰማነዉ ዜና እንዲህ ግራ የሚያጋባ ዜና ነዉ። ሆኖም ሳንተማመን ትግል ብሎ ነገር የለምና የትግል ጓዶቻችንን ማመን ብርታት እንጂ ደካሞች እንደሚሉት ሞኝነት ወይም የዋህነት አይደለም። በጓዶቻችን ላይ ክህደት ፈጽመን ከምናሰቃያቸዉ እኛ ብንሰቃይ ይሻላል፤ ደግሞም ጓዶቻችንን ማመን አቅቶን በጥርጣሬ ተፋጥጠን ባለንበት ከምንረግጥ አንዳንዴ አዉቀንም ቢሆን ብንታለል ብዙ መንገድ መጓዝ እንችላለን። ትግል በተለይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ከሚያስተምረን ትምህርቶች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ሌሎች በኛ ላይ እምነት እንዲኖራቸዉ ከፈለግን እኛ አስቀድመን ልናምናቸዉ አንደሚገባን ነዉ። አለዚያ ሁለታችንም አንተማመንም። አለመተማመን ደግሞ ያጠፋፋናል እንጂ አንድ ቤት ዉስጥ አብሮ አያኖረንም። እንደኔ እንደኔ የወያኔን ስርዐት ደምስሰን ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር የምናደርጋት እያንዳንዳችን ለትግል ጓዶቻችን የገባነዉን ቃል ሰብረን ረጂም ህይወት ከመኖር ቃላችንን አክብረን ዛሬዉኑ መሞትን ስንመርጥ ብቻ ነዉ። ወያኔ አንደ እሳት የሚፈራዉና በፍጹም የማያሸንፈዉ አንዲህ አይነቱን ከብረት የጠነከረ ጽኑ አቋማችንን ብቻ ነዉ። ለዚህ ነዉ እንዲህ አይነት ጽናት የሌላቸዉን ደካማ ግለሰቦች ፈልጎ እያማለለ ጽናታችንን የሚፈታተነዉ። ከሰሞኑ ለህዝብ ከመታገል ህዝብን መታገል መርጦ ከለየላቸዉ የህዝብ ጠላቶች ጋር የተቀላቀለዉ ሞላ አስገዶም ለዚህ ዉሳኔ የበቃዉ ህዝባዊዉ ትግል የሚፈልገዉ የአለማ ጽናት የሌለዉ ደካማ ግለሰብ ስለሆነ ብቻ ነዉ። ዉድ ኢትዮጵያዉያን ክህደት ትናንት ነበር፤ ዛሬ አለ፤ ነገም ይኖራል። ስለዚህ ክህደት ሊያስተምረን እንጂ በፍጹም ሊያስበረግገንና አንገታችንን ሊያሰደፋን አይገባም። ክህደትና ከሀዲዎችን እያሰላሰልን የምንኖር ከሆነ የበለጠ እንዲጎዱን ተጨማሪ ዕድል እንሰጣቸዋለን እንጂ ሌላ ምንም የምንፈይደዉ ፋይዳ የለም።

የሀገር አድን ጥሪ ለወጣቱ!(ከአርበኞች ግንቦት7 ወጣቶች መምርያ)

እኛ የዘመኑ ወጣቶች በሃገራችን ላይ የተጫነብን የወያኔ የመርገምት አገዛዝ ያጎሳቆለን፤ በኑሮ የተበደልንና በሰላም ለመኖር ያልታደልን ፍጡሮች ብንሆንም ህዝባችን ነጻነቱን ሲቀማ፣ መብቱ ሲደፈር፣ ክብሩ ሲዋረድ ከዳር ቁመን የምንመለከትበት አንዳች ምክንያት ሊኖረን አይገባም። ወቅቱ ለነፃነታችንና ለመብታችን ባላንጣ የሆነውን አምባገነን የወያኔን ስርዓት ፊት ለፊት ተጋፍጠን፣ በትግላችን ደቁስን ማንነታችንን የምናስመስክርበት ወቅት እንጂ በፍርሃትና በዝምታ ተውጠን ወደኋላ የምንልበት ስዓት አይደለም። ደግሞም እኛ ወጣቶች ለመብት እና ነፃነታችን ተፈጥሮ የለገሰችንን እምቅ ኃይልና ጉልበት ተጠቅመን በቁርጠኝነት ተነስተን ካልታገልን የሥርዓቱን አምባገነናዊ የጭቆና አገዛዝ በፍርሃትና በዝምታ እንደተቀበልን ተደርጎ መወስዱ የማይቀር ነው።
 ከምንግዜውም በላይ እኛ ወጣቶችን ዛሬ ሁለት አበይት ጉዳዮች በጉልህ ያሳስቡናል፤ ሊያሳስቡንም ይገባል። እነዚህም ሃገራችን ያለችበት አሳሳቢ ሁኔታና የኛ የተተኪው ትውልድ የወደፊት ተስፋ ምን ሊሆን ይችላል? የሚሉት ናችው። በቀደመው ጊዜ በሃገራችን የተፈራረቁት አምባገነን ገዥዎች ለወጣቱ ተስፋና የተሻለ ነገር ከመስጠት ይልቅ በጠላትነት ፈርጀው በሽብር እየገደሉና ጥቃት እየፈጸሙበት ሲያሳድዱት ኖረዋል። የወጣቱ ሰቆቃ አሁን በወያኔ ዘመን ደግሞ እጅግ በጣም በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል።
 የወያኔ መሪዎች ለኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ማዕከላዊን፡ ቃሊቲን፤ ሽዋሮቢትን፣ ዝዋይን እና የመሳስሉ የሰቆቃ እስር ቤቶችን ሲያሰፉ እንጂ የሥልጠናና የምርምር ተቋም ሲያድሱና ሲገነቡ ለማየት አልታደልንም። የሚገነቡ የትምህርት ተቋማትም ለሥርዓቱ የእድሜ ማራዘሚያ እንጂ የእውቀት ማስጨበጫ ተቋም እንዳልሆኑ ተግባራቸውንና ውጤታቸውን መመልከት ይቻላል። በአደባባይ ያለፍትህ የሚገደለው ወጣት ባንክ ሲዘርፍ ተገኘ፣ ወንጀል ሲሰራ ተያዘ የሚሉ የሀሰት ምክንያቶች እየተለጠፉበት ያለኃጢአቱ የሀሰት ስም በመቀባት ዳግም ይገሉታል።

የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ከሚፈራበት የትምህርት ተቋም ድረስ በመግባት የአማራ ህንጻ፣ የኦሮሞ ህንጻ፣ የትግሬ ህንጻ…ወዘተ እያሉ የትምህርት ሥርዓቱን ከጠባቡ የፓለቲካ ግባቸው ጋር በማያያዝ በነገ ተስፋችን ላይ ዘምተው የልዩነት ግድግዳ ባሳፋሪ መልክ እየገነቡ ቀጥለዋል። አላማው ደግሞ በጎስኝነት በሽታ ተውጠን ከእህቶቻችንና ከወንድሞቻችን ጋር እየተባላንና እየተገዳደልን የምንኖርበት ሲኦል ለመፍጠር መሆኑ አያጠያይቅም። በዚህም ሳቢያ ብሔራዊ ሰሜታችን እየደበዘዘ ሄዷል። ብሔራዊ ሰሜት ከሌለን ደግሞ አገር አለን ማለት ጨርሶ የሚታስብ እንደማይሆን ግልጽ ነው።

በነገራችን ላይ ዛሬም ድረስ ወያኔዎች ለእድገትና ለልማት መዘጋጀታችውን እየደሰኮሩ ህዝብን በማታለል የስልጣን ዘመናቸውን ለማርዘም መውተርተራቸውን አላቆሙም። በየጊዜው ኢትዮጵያ ተመነደገች፤ ልማቱ ተፋጥኗል እያሉ በሃሰት ህዝብን ለማወናበድ ይሞክራሉ።እውነታው ግን በእጅጉ ተቃራኒ መሆኑን የህዝቡን የኑሮ ሁኔታን በመመልከት መረዳት ይቻላል። ዛሬ የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ በፈጠረው የተወሳሰበ ችግር በሀገሪቱ የወጣት ሥራ ፈትና ተጧሪ ሞልቶና ተትረፍርፎ በሚታይበት፤ ሥራ የማግኘት እድል በፓለቲካ ታማኝነት ብቻ በሆነባት ሃገርና ወያኔ የፓለቲካ ሥልጣኑንና ወታደራዊ ኃይሉን ተጠቅሞ የሀገሪቷን ሀብት እያጋበስ በሚዘርፍበት ሁኔታ ላይ ቆመን ልማትና እድገት ማለት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ተራ ማጭበርበሪያና ዲስኩር ካልሆኑ በስተቀር ፈጽሞ ትርጉም የሚሰጥ አይደለም።

Sunday, September 20, 2015

አቶ ነአምን ዘለቀ በሚኒሶታው የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ ይገኛሉ!

አስመራ የገቡት አቶ ነአምን ዘለቀ በሚኒሶታው የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ!

ለአርበኞች ግንቦት 7 የሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀጠሉበት በዚህ ወቅት በሚኒሶታም የፊታችን ኦክቶበር 17, 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስተባባሪዎቹ ገለጹ:: በሚኒሶታ የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ አሰባሳቢ አስተባባሪ ኮሚቴ በመግለጫው እንዳስታወቀው አቶ ነአምን ዘለቀ ከአስመራ መልስ በሚኒሶታው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ:: ኦክቶበር 17 ቅዳሜ ከቀኑ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው በዚህ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ ከአቶ ነአምን በተጨማሪም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እንደሚኖሩ አስተባባሪው አስታውቋል:: አቶ ነአምን ዘለቀ የአስመራ ቆይታቸውን በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ እንደሚያካፍሉ በርካታ ሕዝብ ተስፋ እንዳለው ይጠበቃል:: ስብሰባው የሚደረግበት አድራሻን እና ቦታን ለማወቅ ለዝግጅቱ የተሰራውን ፖስተር ይመልከቱ:: 

The few, the proud, the Ethiopians

By Yilma Bekele

I was present at a festival of resurgence and determination a few days ago. The program was organized to show appreciation to Arbegnoche Ginbot7 Movement’s determination to liberate our country from the grip of TPLF/EPDRF dictatorship. It was a bright California day and it felt like Enkutatash. What was missing was a blanket of Meskel flower coving the East bay hills.Patriotic Ginbot 7 support California

Unlike other gatherings I went to this one was a little different. The people that organized the event and the folks that showed up to attend were there to celebrate our new style of practicing the ‘Art of Self Defense’ not to sit around a table and recite the evil doings of the shameless gangster regime. The atmosphere was that of a weeding not a wake (Lekso Bet). I was perfectly fine with that.

There are over twenty thousand Ethiopians in the greater bay Area where we live. Most of these people are here because the group that is in charge in Ethiopia is not really interested in making our home a safe and sound place to live and raise a family. Some choose to flee rather than die. This is the reason we have mastered the art of getting up and leaving with nothing but our shirts. It is common in our community for people to leave without notice. East Coast, West coast, the South or the Mid West it really do not matter, it is not like the real home. Sure after a while any place is home but there is no way of forgetting the highland on the horn.

No one I know left his country because they are curious about the outside world. We left because there is no future in our homeland. We got our education and stayed because our home is always on fire. We leave because knowing tomorrow would be better than today is an important human condition and that is absent in Ethiopia.

All politics is local. The young Ethiopians that set up this event decided to do what they could to help their people that have resolved to fight on their behalf. The truth of the matter is that many thousands have already sacrificed for the cause and the current attempt is building on that tradition of doing everything to save the motherland.

I said twenty thousand people of Ethiopian origin at the beginning, you really did not expect for all those to show up did you? That only happens in Woyane supervised elections or in North Korea. There are a million and one reason people are unable to be present in person. So the organizers were very accommodating. Tickets were sold ahead of time to those that choose to buy and also donate whatever they could. Those that showed up made up for those that had prior commitments or are just not interested. The few, the beautiful the patriotic Ethiopians made all of us proud.

The meeting Hotel was very charming Inn with beautiful hand carved entry and and large windows making the hall bright. It filled up in no time. The few proud Ethiopians poured their heart out. It is not due to the oratory of our speakers, the smart presentation of the organizers or the bright California sun that made our people respond in such a generous manner. It is all about the cause of freedom and Democracy for our people. They felt the need to help.

Monday, September 14, 2015

ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ 
(ሞላ አስገዶምን አስመልክቶ)

በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ ባጠቃላይና በተለይ ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠረባቸው ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ህወሓት/ኢህአዴግን እንቃወማለን በሚለው ወገን ገንነው የመጡ ሁለት አፍራሽና ኋላቀር የፖለቲካ አዝማሚያዎች (trends ) አሉ። ከነኝህ ውስጥ አንደኛው ራስን በፖለቲካ አመለካከት ዙሪያ ከማሰባሰብ ይልቅ በጎጥና በዘውግ ደረጃ የመመልከትና ሀገራዊ ፖለቲካን በደም ቆጠራ የመመንዘር አባዜ ነው። ሁለተኛውና ከዚሁ ያልተናነሰው ችግር የፖለቲካ ድርጅት በመሰረታዊ ያመለካከት መርሆች ዙሪያ ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ክፍልን የማሰባሰቢያ ድንኳን መሆኑ ቀርቶ፤ በስራ ሳይሆን ድንገተኛ አጋጣሚን በመጠበቅ ትርፍ ለማጋበስ በሚቋምጡ ሰነፍ “ነጋዴዎች“ የተቋቋሙ ሩቅ የማይሄዱ የንግድ ድርጅቶች ይመስልበ ተግባር ምንም የማይፈይዱ ”የፖለቲካ ድርጅቶች“ እንደ አሸን የመፍላታቸው ፈሊጥ ነው። እነኝህ ሁለቱም አዝማሚያዎች የህወሓት/ኢህአዴግን ህይወት ከማራዘም አልፈዉ ማህበረሰቡን ወደሚመኘው እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት አንድ ጋት እንኳን ፈቀቅ አላደረጉትም። ይልቁንም ዴሞክራሲን የሚናፍቁ ታጋዮች ተሰባስበውና ተጠናክረው ስርዓቱን ከመግፋት ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ወይንም በትናንሽ ቡድኖች በመሰባሰብ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በስርዓቱ በቀላሉ እየተመቱ ብዙ ታጋዮች ለሞት፤ ለስቃይና ለእስር ተዳርገዋል። አሁንም እየተዳረጉ ነው።

የዚህ አይነት የትግል አካሄድ ሩቅ እንደማያስኬድ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተገነዘበው ቆይቷል። ይህ አካሄድ እንዲቀየርና የፖለቲካ ሀይሎች ተሰባስበው ይህንን በስልጣን ላይ ከሚገባው በላይ የቆየና አገሪቱን ለውርደት የዳረገ የጥቂት ዘራፊዎች ቡድን ከጫንቃው ላይ እንዲያነሱለት ሲማጠን ቆይቷል።ምንም እንኳን በመሪዎች ድክመት የሚመኘውን ዳር መድረስ ባይችልም ባጭር ጊዜ ልምዱ በትንሹም ቢሆን የተባበረ ትግል ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም በመጠኑም ቢሆን አይቶታል።

ይህ የህዝብ ፍላጎት መኖር ግን በራሱ ይህንን የተባበረ ሰፊ ማህበራዊ እንቅስቃሴ መፍጠርን ቀላል ያደርገዋል ማለት አይደለም። በብዙ ስራ፤ በብዙ ድካምና ያላሰለሰ ጥረት የሚፈጠር እልህ አስጨራሽ ሂደት ነው። ባንድ በኩል እንዲህ አይነት ሰፊ የህዝብ እንቅስቃሴ በስልጣኑ ለመቆየት የሚፈጥርበትን ችግር የሚረዳው በስልጣን ላይ ያለው የዘራፊዎች ቡድን ይህን እንቅስቃሴ ከወዲሁ ለማምከን ያለ የሌለ የገንዘብ፤ የስለላና የተንኮል ሀይሉን ይጠቀማል። በተቃዋሚ ድርጅቶች ውስጥ ሰርጎ በመግባትና ደካማ ሀይሎችን በገንዘብ በመግዛት ወይንም በማስፈራራት እንዲህ አይነት ትብብሮች እንዳይፈጠሩ ከውስጥ ለመቦርቦር ተግቶ ይሰራል። በሌላ በኩል ደግሞ የትም የማያደርሳቸውን “የራሳቸውን ድርጅት” የሙጢኝ ብለው ለትልቅና አገራዊ አላማ እራሳቸውን ላለማስገዛት የቆረጡ ደካማ “የድርጅት መሪዎች” እንዲህ አይነቱን የጋራ እንቅስቃሴ በራሳቸው ግብዝነትና ስግብግብነት ምክንያት ብቻ ሊያሰናክሉት መሞከራቸው አይቀርም።

ይህ ግን ጊዜው ያለፈበት አዝማሚያ ነውና የሚሳካ ሙከራ አይሆንም። የተናጠል ትግል ሂደት ማብቂያው ጊዜ ተቃርቧል። የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚታገሉ ኃይሎች እንዲህ አይነቱን ፋይዳ ቢስ ሂደት የመቀበል ትዕግስታቸው ተሟጧል። በቅርብ ጊዜ የሞላ አስገዶምን መክዳት በማስመልከት የትህዴን አመራር ባወጣው መግለጫ“ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማድረግ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር አብሮ መስራት የድርጅታችን መሰረታዊ መርሆ ነው” እንዳለው ይህ መሰረታዊ መርሆ በሀገራችን የጸረ ህወሓት/ኢህአዴግ ትግል የበላይነት ይዞ እየመጣ ያለ እጅግ አስፈላጊና ለድሉም ወሳኝ የሆነ የጊዜው የፖለቲካ አዝማሚያ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ይህን መሰረታዊ መርሆ ከምር ወስዶ የሚንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ነው።

አቶ ሞላ አስግዶም አስመልክቶ የትህዴን መግለጫ!

ከትህዴን የወጣ አስቸኳይ መግለጫ!

ድርጅታችን ትህዴን በየካቲት 1993 ዓ/ም ብረት አንስቶ ትግል ሲጀምር አላማው ግልፅና የማያሻማ ነበር።

እሱም በሃገራችን የገነነው አፋኝ ስርዓት ህዝባችንን ከፋፍሎ ሰብኣዊ መብቱን ረግጦ ለመግዛት በሚያመቸው መንገድ ይጓዝ ስለነበር ድርጅታችን ትህዴን ችግሩን ለመፍታት ኩሁሉም በኢትዮጵያ አንድነት ከሚያምኑ ድርጅቶች በመተባበር ህዝባዊ ስርአት ለመትከልና አንድነቷ የተጠበቀ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መገንባት የሚል አላማ አንግቦ የህወሓት-ኢህ አዴግ ስርዓትን በመቃወም ነፍጥ አንስቶ በትጥቅ ትግል መፋለም ከጀመረ 14 ዓመታት ሆኖታል።

በነዚህ 14 ዓምታት የትግል ጉዞ ድርጅታችን ትህዴን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ወታደራዊ መስክ ከፍተኛ ድሎችን እያስመዝገበ መጥቷል። ትግል ሲባል ቀላል እንዳልሆነ ካሳለፍነው የትግል ታሪክ እየተማርን መጥተናል። ድርጅታችን ትህዴንም በዚህ አጭር እድሜው ክፍተኛ ድሎችን ሲጎናጸፍ የተለያዩ መስናክሎችን በመሻገር ነው።

በቅርብ ጊዜ የተወሰኑ በትግሉ የቆዩና ግላዊ ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለስቦች ትግሉን ባሻቸው መንገድ ሊጠመዝዙት ስላልቻሉና በአብዛኛው ታጋይ በመድረክ ተይዘው መፈናፈኛ ስላጡ ተስፋ ቆርጠው ከትግሉ ጎራ ሸሽተዋል።

የተከበርከው ሰፊው ህዝባችን እነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ለግል ጥቅማቸው ያደሩ እንጂ ትህዴንን የሚወክሉ አይደሉም። የእነዚህ ስዎች ከትግሉ መክዳት ደግሞ ድርጅታችን ትህዴን የቆሸሸውን በመጥረግ ጥንካሬውን ከመቸውም ጊዜ በላይ ያጎለብተዋል እንጂ ትግሉን ለሰክንድም ቢሆን አያደናቅፈውም።

ትህዴን ይዞት የተነሳ ዓላማ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ስለሆነ ሊቅበለውም ውይም ላይቅበለውም የሚችለው ህዝብ እንጂ ግለሰቦች አይደሉም። ትግላችን ደግሞ በሃገራችን ያለውን ፀረህዝብ ስርዓት ከስልጣኑ ተወግዶ ህዝባችን የጀመረውን የትጥቅ ትግል ግቡን ሳይመታ ለአፍታም ቢሆን አይቆምም።

ስለሆነም መላው የኢትዮጵያ ስፊ ህዝብ ይህንን ተረድተህ እንደበፊቱ ሁሉ በልጆችህ እይተካሄደ ባለው ህዝባዊ ትግል ጎን እንድትሰለፍ መላው የትህዴን ታጋይ ጥሪውን ያቀርባል።

ፍኖተ ትህዴን ፍኖተ ድል ነው!
ድል ለጭቁኖች!!

Thursday, September 10, 2015

የኢትዮጵያ አገር አድን በዲሞክራሲ የጋራ ንቅናቄን ምሥረታ በማስመልከት የወጣ ድርጅታዊ መግለጫ

…በጋራ አብሮ በመታገል የሚገኘው ዘርፈ ብዙ ጥቅም የገባቸውና ካለፈው ተደጋጋሚ የታሪክ ስህተት የተማሩ፣ በአገራችን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሰረት በምድር ላይ በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ አራት ድርጅቶች በጥምረት ተባብረው በጋራ ለመታገል ወስነዋል። እነዚህ አራት ድርጅቶች ለብዙ ዓመታት የአብሮ መታገል ፍላጎት እንቅፋት የሆነውን የገዢ መደቦች የከፋፍለህ ግዛው ሴራ በጣጥሰዋል። ይህ ዛሬ በጥምረት የተጀመረው ትብብር እያደገ ሄዶ በአጭር ግዜ ውስጥ ወደ ውህደት እንዲያድግ ይደረጋል። ከዚህም በተጨማሪ ንቅናቄው ከሌሎች ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት ከሚታገሉ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ ለመስራት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይገፋበታል።

በዚህም መሠረት፣

1ኛ) የአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ
2ኛ) የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ
3ኛ) የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ፣ እና
4ኛ) የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ

የኢትዮጵያ አገር አድን በዲሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ (በአጭሩ “የአገር አድን ንቅናቄ”) የሚባል ድርጅት ዛሬ በአዲስ ዓመት መባቻ ጳጉሜ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ፈጥረዋል። የንቅናቄውን ምክርቤት፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የተለያዩ መምሪያዎችን ከማቋቋሙም በላይ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ሊ/መንበር፣ አቶ ሞላ አስግዶምን ም/ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። [ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

Friday, September 4, 2015

ማስታወሻ፤ የእናት ሐገር ጥሪ!!

ቅዱስ ዮሃንስ

የነገ ቅዳሜና እሁድ አገርን የማዳንና የደጀንነት የድጋፍ ጥሪ ዝግጅቶች

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ በመላው ዓለም ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በነፃነት ትግሉ ዙሪያ እየመከረና ድጋፎችን እያሰባሰበ ቀጥሏል። እስካሁን በተደረጉት ሕዝባዊ ስብሰባዎች ንቅናቄው ከነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን ጋር ስኬታማ ውይይቶችን በማድረግ፤ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰውን አገርን የማዳን ትግል ከዳር ለማድረስ ከኢትዮጵያውያኑ የገንዘብና የሞራል ድጋፎችን ማሰባሰብ ችሏል። በየ ሕዝባዊ ስብሰባዎቹ ኢትዮጵያውያን በነቂስ በመውጣት የታደሙባቸው እንደነበርና ከንቅናቄ ጋር እስከ ትግሉ ፍፃሜ አብረው ለመጓዝ ቃል በመግባት ደጀንነታቸውን ያረጋገጡባቸው እንደነበር መዘገቡ አይዘነጋም።

ሕዝባዊ ስብሰባዎቹ ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ቀጥለው የሚውሉ ሲሆን ፕሮግራሞችን ለማስታወስ ያህል፤

ነገ ቅዳሜ Sept 5፡


  • በካልጋሪ ካናዳ ሰዓት ከ 3 PM ጀምሮ =====>> ቦታ፡ Whitehorn Community Hall
  • በስዊዘርላንድ ዙሪክ ሰዓት ከ 13 ሰዓት ጀምሮ 
  • በኖርዌይ ስታቫንገር ሰዓት ከ 16 ሰዓት ጀምሮ


እሁድ Sept 6፡


  • በኦክላንድ ሳንጆሴ ካሊፎርኒያ ሰዓት ክ 2 PM ጀምሮ ===>> ቦታ፡ Washington Inn
  • በቶሮንቶ ካናዳ ሰዓት ከ 4 PM ጀምሮ ====>> ቦታ፡ Estonian House

ስለዚህ በካልጋሪ ካናዳ፤ በስዊዘርላንድ ዙሪክ፤ በኖርዌይ ስታቫንገር፤ በኦክላንድ ሳንጆሴ ካሊፎርኒያ፤ በቶሮንቶ ካናዳ አገራት እንዲሁም አጎራባች ከተሞች የምትኖሩ ነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በሕዝባዊ ስብሰባዎቹ ላይ በመገኘት ለተጀመረው የነፃነት ትግል ደጀንነታችሁንና ድጋፋችሁን በተግባር ታረጋግጡ ዘንድ በክብር ተጠርታችኋል።

Thursday, September 3, 2015

The sun is shining over Ethiopia

By Yilma Bekele

Ethiopia has been in darkness. We had light before most but that is history. We can recite our ancient history; write beautiful poetry extolling our virtues and fill a library with our traditional lore unfortunately it is not something we can take to the bank. It is not all lost. Ethiopia and her wellness has been woven into our soul. Thus today where ever we go we survive and thrive. Don’t take the fact you walk with your head high for granted my friend, that pride in you is cultivated and nurtured.

The Ottoman Turks, the Egyptians, the British, the French, the Italians have all tried to force their ways on us. It just did not work. Outsiders have learnt their lesson and have stopped trying force to make us serve their interest. It is the homegrown variety that has become a challenge. It could be a (seyawkush yinkush ሲያውቁሽ ይንቁሽ) situation where naturally one disarms in the presence of family and friends. Sooner or later one member goes rogue. It never fails. Throughout our history we have encountered such situations where kings, warlords or madmen have fought for power and glory. TPLF is our child gone rogue.

TPLF is the worst internal enemy faced by our county. There isn’t any aspect of our culture and history they have not tried to contaminate with negativity and hate. For over thirty years they have systematically worked on destroying the unity and strength that has taken hundreds of years to build. It is due to the solid foundation that our dear country has been built on that they are unable to even cause a little crack let alone a fissure. We are grateful to all those that sacrificed and painstakingly built this formidable home we call Ethiopia.

The current struggle being waged by TPLF on one side and Democratic forces on the other is about the kind of Ethiopia we want to build on the foundations already laid by our ancestors. Instead of building on that and adding value we have been busy subtracting, dividing and undermining our precious asset.

On this side we have the current Ethiopian government led by Tigrai Peoples Liberation Front (TPLF) that has been in power for the last twenty two years uninterrupted. The TPLF Party with its clueless and unwritten guiding dogma it calls ‘Revolutionary Democracy is based on the following principles:
• The Ethiopian people are not ready for Democracy.
• The vanguard TPLF will oversee the development of Democracy.

Despite what the regime and its international supporters claim this arrangement has not worked well for the average Ethiopian. There is no need to try to convince an Ethiopian how bad the Tigrai People’s party has been to our country. All one has to do is look around one’s own family and ask ‘how are you doing?’ If you do not know of a family member in distress you my friend is an exceptional Ethiopian. We all salute you but that unfortunately is not the norm.

That is why there are many that have decided to sacrifice life and family and stood against the tyranny of the Tigrai Peoples Liberation Front. We Ethiopians are such a lucky people to have been able to produce such dynamic and selfless leaders that would rather suffer than accept injustice.

ረሀብን ለማጥፋት ህወሓትን ማስወገድ

ረሀብ በአገራችን ላይ እያንዣንበበ ነው። በአፋርና በሱማሌ ከከብቶች አልፎ ሕፃናት እየሞቱ ነው። የረሀቡ አደጋ ወደ ኦሮሚያና ሌሎች የደቡብ ገጠሮች እየተዛመተ ነው፤ ሰሜን ኢትዮጵያም ከአደጋ ውጭ አይደለም።

“ከአስር ዓመታት በላይ በተከታታይ በየዓመቱ ከአስር በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት አሳይተናል” የሚለው ዓይን ያወጣ ውሸት፤ “ድህነትን ተረት እናደርጋለን” የሚለው ጉረኛ መፈክር፤ “መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ተርታ እንደርሳለን” የሚለው ባዶ ተስፋ፤ የወያኔዎችና ጀሌዎቻቸው በፎቅና ቪላዎች መንበሽበሽ፤ የድግሶችና የስብሰባዎች መብዛት ለሕዝባችን ቁርስ፣ ምሳና እራት አልሆኑም።

አገዛዙ ጉራውና ባዶ ተስፋ መስጠቱ እንዳለ ሆኖ የረሀቡን ምክንያት በተፈጥሮ ላይ ማላከኩን ተያይዞታል። ለመሆኑ ተፈጥሮ ብቻውን እየተደጋገመ ለሚመጣ ችጋርና ቸነፈር በቂ ምክንያት ሆኖ ያውቃልን? አስከፊ የረሀብ ዜናዎች የሚሰማባቸው አገሮች በሙሉ ነፃነት የታፈነባቸው አገሮች መሆናቸው የአጋጣሚ ጉዳይ ነውን? ለምንድነው አንድ ዓይነት ችግር እየተደጋገመብን መላ መፈለግ ያቃተን? መልሱ አጭርና ቀጥተኛ ነው። “ችግር የመሳካት እናት” የምትሆነው በነፃነት ማሰብ የሚችል ጭንቅላት ሲኖር ነው። በባርነት ጨለማ ውስጥ ያለ ጭንቅላት ለችግሮች መፍትሄ የማፍለቅ አቅም የለውም። እንዲያውም እንዲህ ዓይነቱ ድኩም ጭንቅላት ችግሮችን ማሸነፍ ሳይሆን ተሸናፊነትን ተቀብሎ ከችግሮች ጋር ተስማምቶና ተወዳጅቶ መኖርን ይመርጣል። ነፃነት ያለው ሕዝብ ረሀብን እንደሚያሸነፍ ተደጋግሞ የታየ ጉዳይ ነው። ለዚህም ነው ረሀብን የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት ውጤት ብቻ አድርጎ ማቅረብ እውነትን መሸፈጥ የሚሆነው። ረሀብ የብልሹ አስተዳደር ውጤት ነው።

አገራችንን የረሀብ ቀጠና ካደረጉ የ24 ዓመታት የህወሓት “ድሃን ዘርፈህ ብላ” የኢኮኖሚ ፓሊሲ ውጤቶች መካከል አንዳንዱን ለአብነት ያህል መዘርዘር ይቻላል።

1. ገበሬና መሬት ተለያይተዋል። ለም መሬቶች በኢንቨስትመንት ስም በዘመኑ የህወሓት ጉልተኞች በመያዛቸውና እነሱ ደግሞ በተራቸው ለባዕዳን እየሸጡ በመሆኑ ባለሀገሩ ጭሰኝነት እንኳን አጥቶ ለቀን ሠራተኝነትና ልመና ተዳርጓል። አዳዲሶቹ ባለሃብቶች ለፈጣን ኪስ መሙላት እንጂ ለዘለቄታ የአፈር ልማት ፍላጎቱም እውቀቱም የላቸውም። በዚህም ምክንያት ገበሬው ትንሽ የዝናብ ዝንፈት እንኳን መቋቋም እስከማይችልበት ደረጃ ተዳክሟል።

2. በዘር ላይ በተመሰረተ ክልላዊ ድንበር ሳቢያ ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎች በአገራቸው ውስጥ ተዘዋውረው መሥራት አልቻሉም። ከሰሜን ወደ ደቡብ ከተሰደደ የአገራችን አርሶ አደር ይልቅ ለቻይና ገበሬ መሬት ማግኘት ይቀለዋል። እንዲያውም ኢትዮጵያዊው ድሀ ገበሬ በዱላ ሲባረር፤ ከውጭ አገር የመጣው ቱጃር ገበሬ ብድርና ማበረታቻዎች ይሰጠዋል።

3. ደኖቻችን ተጨፍጭፈው፣ ለም መሬታችን ተሸርሽሮ በማለቁ የግብርናችን ምርታማነት በእጅጉ ቀንሷል። በዘመነ ወያኔ የደን ጭፍጨፋና የመሬት መሸርሸር በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨምሯል። አገሪቷ በፍጥነት ወደ ምድረበዳነት እየተቀየረች ነው።

4. ፋይዳ ያለው የስነ ሕዝብ ፖሊሲ ባለመኖሩ የሕዝብ ብዛት አሻቅቧል። እንደ ኢኮኖሚው ሁሉ ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ብዛት ሊቆጣጠር የሚሞክረው ቢሮ ውስጥ ቁጭ ተብሎ በሚደረግ የቁጥር ጨዋታ ነው። የስታተስቲክሱ ባለሥልጣን ቁጥራችንን በትክክል ሊነግረን ባይፈልግም እንኳን ረሀብ መብዛታችንን እየነገረን ነው።

5. የህወሓት ባለሥልጣኖችና በየክልሉ ያደራጇቸው ምስለኔዎች ራሳቸውን ባለሚሊዮኖች አድርገዋል። እነዚህ በአንድ ጀምበር የበቀሉ ቱጃሮች ከገንዘብ በተጨማሪም የጄኔራልነት፣ የሚኒስቴርነት፣ የክልል ገዢነት፣ እጅግ ቢያንስ የቢሮ ኃላፊነት ሥልጣንን ኪሳቸው ውሰጥ ከተዋል፤ ልባቸው የተመኘውን ዲግሪ ሸምተዋል። የመንግሥት ሥልጣንና ሃብት ይኸን ያህል የተቆራኙበት ሥርዓት በኢትዮጵያ ኖሮ አያውቅም። የጥቂቶች ያለአገባብና ያለቅጥ መክበር በአንፃሩ ደግሞ የብሃኑን ሕዝብ መደህየት ድህነትን መዋቅራዊ አድርጎታል።