.jpg)
በተያያዘም ስለ ነጋ ገ/እግዚያብሄርና ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ የጀርባ ታሪክ በተመለከተ ምንጮቹ ተከታዩን መረጃ አስቀምጠዋል፤ “ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ የአቶ ነጋ ስራ የመኪና ድለላና ኮረዶችን ከባለስልጣናት ጋር የማገናኘት የድለላ ተግባር ላይ ተሰማርቶ እንደነበረ ይገልፃሉ። በተለይ ሴቶችን እየመረጠ ለበርካታ የገዢው ሹማምንት ለወሲብ ከማቅረብ ጎን ለጎን የሕወሐት ቁልፍ ባለስልጣናትን በእጁ የማስገባት አጋጣሚ ፈጥሮለታል ፥ ይላሉ ምንጮቹ። ከባዶ ተነስቶ ሚሊየነር የሆነበት ምስጢሩ አዜብ መስፍን መሆናቸውን ያሰምሩበታል። ለዚህም «ነፃ ትሬዲንግ፣ ባሰፋና…» ሌሎች ከፍተኛ የቢዝነስ ተቋማቱና በሕገወጥ የዘረፋ ተግባር በድፍረት ተሰማርቶ መቆየቱን ከሞላ ጎደል ይጠቅሳሉ። በባለስልጣናቱ ተረማምዶ ከአዜብ ጋር በፈጠረው <ልዩ ቁርኝት> የተገኘ ሃብት እንደሆነ ይገልፃሉ። ከአዜብ ጋር በማሌዢያና ለንደን የፈፀሟቸው አስነዋሪ ተግባራት የሚያሳዩ የምስል ማስረጃዎች በደህንነት ሃላፊው እጅ እንደገቡ የጠቆሙት ምንጮቹ፣ የሁለቱን ግንኙነት በተመለከተ አብዛኛው የሕወሐት አመራር ጠንቅቆ እንደሚያውቀው አስታውቀዋል። አቶ ነጋ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ማመን ተስኗቸው ከማንገራገራቸው ባሻገር፥ «..ለአዜብ ስልክ እንድደውል ፍቀዱልኝ?» በማለት መማፀናቸውንና ደህንነቶቹ እንዳልተቀበሏቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። በሌላም በኩል ከአዜብ ጋር ተመሳሳይ <ግንኙነት> ያላቸው ሌሎች ሁለት ባለሃብቶች፥ አንዱ 40 ሚሊዮን የፈጀ ባለስድስት ፎቅ የቢዝነስ ተቋም (ቦሌ ከሜጋ አጠገብ) አዜብ በለገሱት ገንዘብ እንዲገነባ ሲደረግ፣ ከዚህ ግለሰብ ጋር በተደጋጋሚ በዱባይ በውቂያኖስ ላይ በተገነባውና የቱጃሩ አልወሊድ ቢንጣለል ንብረት በሆነው “ኪንግደም” ባለ4 ኮከብ እጅግ ዘመናዊ ሆቴል እንደተገናኙ፣ እንዲሁም ሌላኛው የአንድ ቢሊየን ብር ባለሃብት ሆኖ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ አዜብ ማድረጋቸውን ምንጮቹ አጋልጠዋል።
የአቶ ገ/ዋህድ ማንነት በተመለከተ ምንጮቹ ይህን ይላሉ፤ « ገ/ዋህድ የኢሰፓ አባል ሆኖ በአስመራ እስከ 1982ዓ.ም ያገለግል ነበር። በዚሁ አመት መጨረሻ በራማ በኩል አድርጎ ሕወሐትን ተቀላቀለ። በወቅቱ በመቀሌ እንዲቋቋም በተደረገውና የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ መኮንኖች (ምርኮኛ) የተካተቱበት <ኢዴመአን> የተባለ ድርጅት መስራች አባል ነበር – ገ/ዋህድ። በ1983 ዓ.ም የሁለት ሳምንት ወታደራዊ ስልጠና ወይም በድርጅቱ አጠራር “ተአለም” ከወሰደ በኋላ በአጋጣሚ ፓርቲው መላ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ምንጮቹ ያመለክታሉ። በሲቪል ሰርቪስ አልፎ ደቡብን ከጀርባ እንዲመሩ ከተመደቡት አቶ ቢተው በላይ ጋር በአዋሳ ተመደበ። በ1993ዓ.ም በተፈጠረው የፓርቲው መሰንጠቅ አመቺ አጋጣሚ የተፈጠረለት ገ/ዋህድ የክል
ሉን ፕ/ት አቶ አባተ ኪሾን፣ ቢተው በላይና ሌሎችም እንዲታሰሩ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫወተ። ለዚህ ታማኝነቱ የላቀ ቦታ በመለስ ማግኘት እንደቻለና ከዛ በኋላ በየቀኑ ከአዜብና መለስ ጋር በስልክ ይገናኝ እንደነበረ በፈለገው ጊዜ ቤተመንግስት ይገባና ይወጣ እንደነበረ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በአዜብ መልካም ፈቃድ በጉምሩክ ወሳኝ ስልጣን እንዲጨብጥ መደረጉንም አክለው ገልፀዋል። ከአዜብና ሸሪኮቻቸው ጋር በመነጋገርና በመመሳጠር ስሚንቶና ሌሎች ቁሳቁሶች በህገወጥ መንገድ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው አገር ቤት እንዲገቡ በማድረግ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ገ/ዋህድ፣ በሚሊዮን የሚገመት ሃብት ከዘረፋው እንዳተረፈም ተመልክቷል። ባለቤቱ ኮ/ል ሃይማኖትም እንዲሁ አዜብ በሚመሩት የሴቶችና ፀረ-ኤድስ ተቋም በምክትል ሃላፊነት እንዲመደቡና በየአመቱ ከአሜሪካ ብቻ እስከ 240 ሚሊዮን ዶላር በእርዳታ መልክ የሚገኘውን ገንዘብ በግልፅ በመዝረፍ ተባባሪ ሆነው መቆየታቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።ከኢየሩሳሌም አርአያ
No comments:
Post a Comment