Wednesday, July 24, 2013

በሲዳማ ምድር የሠላም አየር መተንፈስ ጀመረ!!

መላው የሲዳማ ህዝብ በዘመነ ሺፈራው ሽጉጤ ግፊኛና አሳር የበዛበት አገዛዝ ከባድና ዘግናኝ እንዲሁም ጭካኔ የተሞላበት በደል ሲደርስበት ከርሟል ፡፡

1. የ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ስም ሲታነሱ ተደርሶባችኋል ተብሎ ሰዎች ከሥራ ይባረራሉ፤ ይታሠራሉ፤ ከሚወዱአቸው ቤተሰባቸው ይለያሉ ወይም

2. የአቶ ሽፈራው ሽጉጤን ወንበር ተቀናቅናችኋል ተብሎ ሰዎች ከሥልጣን ይባረራሉ፤ ይታሠራሉ /ያውም እድሜ ልክ እስራት/፤ ቤተሰባቸው ይበተናሉ እንዲሁም ለጎዳና ተዳዳሪነት ይዳረጋሉ፤

3. በአቶ ሽፈራው ላይ የግድያ ሙከራ አድርጋችኋል እንዲሁም ይህን አመለካከት ተሸክማችኋል ተብሎ ሕዝብ በሙሉ አውጣጭኝ ይቀመጣል፤ ገበረው፤ ነጋደው፤ ተማሪ፤ የመንግስት ሠራተኛ፤ ባለሥልጠኑ ይሳቀቃል/ ይሸማቀቃል፤ ኑሮውን ከሚመራበት መደበኛ ሥራው ይስተጓጎላል፤ እራሱንና ቤተሰቡን ለችግር ይጋለጥበታል፡፡
ከአውጣጭኙ በኋላ ብዙዎቹ እድሜ ልክና በብዙ ዓመታት ተፈርዶባቸው ሥቃይ ይቀምሳሉ፤ ይጎሳቆላሉ፤ ቤተሰባቸው ይበተናሉ፤

4. የማስፈጸም አቅም አላቸው ተብሎ የሚገመቱና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ግለሰቦችን፤ በተለይ ምሁራንና ቀደም ተብሎ ህዝብን በቅንነት በማገልገል ልማት ያስመዝገቡትን፤ በደኢህዴን/ ኢህአዴግ የሚጨፈለቁ ህገ-መንግስታዊ የህዝብ መብቶች ላይ እንደእርሱ በሁለቱ እጃቸውና በሁሉቱ እግሮቻቸው የማያጨበጭቡትንና እንዲሁም በህግ በላይነት የሚያምኑትን አንጡራ የህዝብ ልጆችን ባጠቃላይ የመንግስት ጠላት ናቸው ብሎ በመፈረጅና በጀሌዎቹ በማስፈረጅ እንዲሁም ከፍ ብሎ በአዲስ አበባ ለተሰየሙ ለሥርዓቱ መሥራቾች በማዋጋት ሠርተው እንዳይኖሩ በማድረግ፤ በማሳደድ፤ በማሳሰር ወ.ዘ.ተ የሲዳማ ህዝብ ወላጂ መካን እንዲሆን አድርጓል፡፡

5. የሲዳማ ህዝብን ልማት ጎድቷል ፤ መሬቶቹን ለድንበርተኛ ህዝብ አሳልፎ ሽጦአል፤ የህዝብ ደም እንዲፈስና ሠላም እንዲደፈርስ አድርጓል፤ የሲዳማን ህዝብ ወዳጂ ህዝቦች ጋር የማጋጨት ሥራ ሠርቷል፡፡

6. በአጠቃላይ በአቶ ሺፈራው ሽጉጤ ቅኝ አገዛዛዊ ዘመን ሲዳማ በታሪክ የማይረሳውና ማንኛውም መድሃኒት የማይሽረው ጠባሳ ተፈጥሮበታል፡፡

ህዝቡ ባደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ይህንን የመከራና የሥቃይ ማለትም የግንጥ አለንጋ የሆነውን ግፈኛ፤ ሕሊውና የሌሽ፤ ሰው መሳይ አውሬ ከሲዳማ ምድር በማባረር ያገኘውንና መተንፈስ የጀመረውን የሠላም አየር እያጣጣመ ለቀጣዩና ለዋነኛው ህገ-መንግስታዊ ክልል የመሆን ትግሉን አጠናቅሮ እየቀጠለ ይገኛል፡፡

ይሁንና አንዳንድ አድር ባይ አመራር ተብዬዎችና ከእርሱ ጋር የጋራ የሚነግዱ ነጋደዎች በራሱ የዘረፈውን ገንዘቡ የሚጠቀምበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሽፋን ለመስጠት በሽኝት ስም ገንዘብ እየሰበሰቡለት መሆኑን ስለተደረሰባቸው መንግስት ለኪራይ ሰብሳቢነት አመቻቺ ባለሥላጠናትንና ነጋዴዎችን ከእኩይ ድርጊታቸው በመግታት የጀመረውን የኪራይ ሰባሳቢነት ዘመቻውን እንዲያጠናክር ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡

by፡ Sidaamaho Maganu No

ምንጭ፡ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

No comments:

Post a Comment