Tuesday, July 23, 2013

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ETV ከዩቲዩብ (Youtube) ተባረረ




(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በዩቱዩብ የተለያየ ፕሮፓጋንዳዎቹን የሚያስተላልፍበት የዩቲብ ቻናል ተዘጋ። ዩቲዩብ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን ማባረሩን የገለጸበት መልዕክት “YouTube account ethiopiantv has been terminated because we received multiple third-party notifications of copyright infringement from claimants including: David Tesema” ይላል።


ከዚህ ቀደም በቴሌቭዥን ጣቢያው የአፍሪካ ዋንጫን ሰርቆ በማስተላለፍ የሃገሪቱን ስም አንገት ያስደፋው የኢትዮጵያ ቲሌቭዥን አሁንም ከዩቲዩብ የተባረረው በተደጋጋሚ በኮፒ ራይት ሲመከርና ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው አልሰማ በማለቱና ከድርጊቱም ባለመቆጠቡ እንደሆነ የዩቲብ አሰራር ያመለክታል።

ኢቲቪ ለዘፋኞች 5 ሳንቲም ክፍያ ሳይከፍል ሥራዎቻቸውን በሕብረትርዒት ላይ እንደሚያቀርብ፤ የውጭ ሃገር ፊልሞችንም ምንም ክፍያ ሳይፈጽም በታላቅ ፊልም ላይ እንደሚያሳይ የሚታወቅ ሲሆን ይህን ስርቆቱን በመቀጠል ዩቲዩብ ላይ ገንዘብ ለማካበትና ፕሮፓጋንዳውን ለማስተላለፍ መጠቀሙ እንዲባረር ምክንያት ሆኗል።

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የዩቲዩብ ቻናል ከፕሮፓጋንዳዎች በተጨማሪ ለአርቲስቶች ክፍያ የማይፈጸምባቸው ድራማዎች፣ ዘፈኖች፣ አስገራሚ ታሪኮችና ሌሎችም ይቀርቡበት ነበር። ይህን የሰሙ አስተያየት ሰጪዎች”ሕዝብን መስረቅ የለመደ መንግስት በኢንተርኔት እሰርቃለሁ ሲል እጅ ከፍንጅ ተያዘ” ሲሉ ተሳልቀዋል።

ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ ወደ ኢቲቪ የዩቲዩብ ቻናል በመሄድ እንዳረጋገጠቸው አካውንቱ ሲከፈት YouTube account ethiopiantv has been terminated because we received multiple third-party notifications of copyright infringement from claimants including: David Tesema” ይላል። ይህን ለማረጋገጥም፦

ZEHABESHA

No comments:

Post a Comment