Thursday, December 10, 2015

Op-ed: The world must not forget the jailed journalists of Ethiopia

Today, on International Human Rights Day, the Ethiopian journalist Eskinder Nega, who was convicted on trumped up terrorism charges, will have spent more than four years in jail. Eskinder is just one of many Ethiopian journalists currently languishing behind bars, merely for doing their job. But unlike other journalists incarcerated on spurious terrorism charges such as the Al-Jazeera journalists freed from Egyptian prison earlier this year, the plight of jailed journalists in Ethiopia attracts little attention from the international community and the media.

Whilst the Aljazeera journalists, Peter Greste, Mohamed Fahmy and Baher Mohamed, became household names, few people outside of Ethiopia will have heard the names of Eskinder Nega, Temesghen Desalegn, Solomon Kebede, Yesuf Getachew, Woubshet Taye, Saleh Edris, and Tesfalidet Kidane. They have all fallen foul of Ethiopia’s 2009 Anti-Terrorism Proclamation, which criminalizes any reporting deemed to “encourage” or “provide moral support” to groups and causes which the government considers to be “terrorist”.

Tuesday, December 8, 2015

በገዛ አፈ-ሙዙ መቃብሩን የሚቆፍር የሽንፈትን ጽዋ ይጎነጫል!

ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማንና ዙሪያን ለማከለል ከወጣው የማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ፤ ገቢራዊነትና ሃሳቡን የተቃወሙ የኦሮሞ ተወላጆች እና የዕቅዱ ተቃዋሚዎች፣ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጆች እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲሁም የየከተማዎቹ ነዋሪዎች ላይ የኃይል እርምጃ እየተወሰደ እንዳለ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡

ዜጎች እያሰሙት ያለውን ተቃውሞና የሃሳብ ልዩነት በኃይልና በጠብ-መንጃ ለመመለስ የተደረገውም አግባብነትና ኃላፊነት የጎደለው ጭፍን ተግባር እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት በጽኑ ያምናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፣ መቶ-በመቶ ሁሉንም ተቋማትና መንግሥታዊ መዋቅሮች በጠቅላላ እንደልቡ የሚያዘውና ያሻውን የሚፈጽመው የኢህአዲግ መራሹ ኃይል፣ ልማትንና እድገትን በኃይልና በጉልበት እፈጽማለሁ እንዲሁም አስፈጽማለሁ ብሎ መነሳቱም መሠረታዊ የእብሪት ተግባር መሆኑም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳምሮ ያውቀዋል፡፡

በተለይም ደግሞ፣ ኢህአዲግ መራሹ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር ላይና በኢትዮጵያውያን ላይ የተከለው የጎሳ ፌዴራሊዝም ችግር ምን ያህል አስከፊ እንደሆነና ውጤቱም የዜጎችን ሞት፣ እስራት፣ ስደት፣ የንብረት ውድመትና የትምህርት መስተጓጎል ማስከተል እንደሆነ ታይቶበታል፡፡ በመሆኑም፣ የአዲስ አበባ ዙሪያ ነዋሪዎችም ሆኑ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉት ልማትም ሆነ እድገት በ“እኔ አውቅልሃለሁ” ባዩ የኢህአዲግ አንባገነናዊ ልማትና የጎሳ ፌዴራሊዝም ሳይሆን፣ በሕዝብ-ለሕዝብ-ከሕዝብ ፍላጎትና ስምምነት ላይ የተመሠረተን ልማትና እድገት ብቻ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡

ከዚህ ዓላማና ግብ ውጪ የሚተገበር ማንኛውም የልማት ዕቅድና የከተማ ማካለልም ሁሉ የኢህአዲግ መራሹ መንግሥት አንባገነናዊ አስተዳደር ሁነኛ መገለጫ በመሆኑ አጥብቀን እንቃወመዋለን፡፡ በተከሰተው ብሔራዊ ቀውስና ችግር ዙሪያም በቀጥታ ለችግሩ ተጋላጭ ከሆኑት ዜጎች ጋር ሆነ ችግሩ በዋነኛነት ከሚያሳስባቸው የአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያ ነዋሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት ተማሪዎች ጋር ባስቸኳይ ውይይትና ንግግር እንዲደረግ እያሳሰብን፤ አንባገነኑ የኢህአዲግ መንግሥት እየተከተለው ያለውን የዜጎችን ጥያቄ በኃይልና በጉልበት ለማፈን ከሚያደርገው ፀረ-ዲሞክራሲያዊ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን፡፡

በተመሳሳይ መልኩም፣ በጎንደር ከተማ በሚገኘው ማረሚያ ቤት ላይ ተከስቶ የነበረውን የእሳት ቃጠሎን ተከትሎ ኢህአዲግ መራሹ መንግሥት የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ በማጥፋት፤ በሕግ ቁጥጥር ሥር የሚገኙትን ዜጎች ሕይወትና ደሕንነት ለመታደግ መሯሯጥ ሲገባው፣ ሕይወታቸውን ከቃጠሎው ለማዳንና ለሞከሩት ዜጎች የጥይት እሩምታ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ከዚህ መንግሥታዊ ተግባርና ቸልተኝነት ተነስተን እንደምንረዳው ከሆነ፣ አገዛዙ ለማንኛውም ዜጋና አገራዊ ጉዳይ የሚሰጠው ምላሽ ከጠብ-መንዣና ከጉልበት የማይዘል መሆኑን በግልጽ አስመስክሯል፡፡ ይህንንም መሰሉን ኢ-ሰብአዊና ኢ-መንግሥታዊ ተግባር የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት በቸልታ እንደማይመለከተው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመግለጽ ይገደዳል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤትም መንግሥት የሚፈጽማቸውን ኃላፊነት የጎደላቸው ተገባራት እስኪያቆሙ ድረስ፣ አንባገነናዊው ሥርዓት የሚፈጸመው የሕገ-አራዊት ተግባራት እስካለቆሙ ድረስ፣ ሕጋዊና ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ – የዘመናችን ሙሴ!

ታዬ ብርሃኑ ከቨርጂንያ

በመጽሐፍ ቅዱስ ካሉ የቅዱሳን ታሪኮች ውስጥ የሙሴን ታሪክ አብዛኛው ኢትዮጲያዊ እንዳነበበው ስለማምን የሙሴን ታሪክ በዚህ ጽሁፍ ላይ መተረኩ አያስፈልገኝም። ሆኖም የዕብራውያን መልእክት ዕምነት ምን ማለት እንደሆነ የሚያስተምርበትን 11ኛው ምእራፍ ላይ ሌሎች ቅዱሳንን ጨምሮ የሙሴን ታላቅ እምነት ይጠቅሳል። ሙሴ በግብጽ ፈርዖን ቤተ መንግስት ውስጥ ጮማ እየቆረጠ፣ ጠጁን እየተጎነጨ፤ በወርቅና በገንዘብ ተከቦ መኖርን ትቶ በባርነት ከሚሰቃዩት ወገኖቹ ጋር መከራ መቀበልን እንደመረጠ ይተርካል። የንጉሱን ቁጣ ሳይፈራ በጊዜዋ ልዕለ ኃያል ሃገር የነበረችውን የግብፅን አገር ኑሮ ትቶ ከወገኖቹ ጋር የኤርትራን ባህር ተሻግሮ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመሄድ የወሰነው በእምነት ነበር። እምነት ማለት የማይታየውን እንደሚታይ አድርጎ በተስፋ መነጽር ማየት ነው።

ባለፉት አራት አስርት ዓመታት የሀገራቸን ኢትዮጵያ ጉዳይ በሁሉም ዘርፍ ከድጡ ወደ ማጡ እንደሆነ የዓይን ምስክር ነን። ሞት፣ ርሃብ፣ ስደት፣ ጎጠኝነትና የፍትህ እጦት የዘመናችን ታሪክ ነው። ወደድንም ጠላንም በየትኛውም ጎራ ብንቆምም፤ በፍትህ እጦት እየተገደሉ መንገድ ላይ ሬሳቸው ይጣል የነበሩት ወጣቶች፣ ተረሽነው በአንድ ጉድጓድ ውስጥ የተቀበሩት 60 ሚኔስትሮች፣ አገርን የባህር በር ማሳጣት፣ ድምጻቸው እንዲከበር ሊጠይቁ አደባባይ ሲወጡ በአጋዚ አልሞ ተኳሾች የተገደሉት የእነ ህጻን ነቢዩ ታሪክ የዚህ ትውልድ ታሪክ ነው። በአማራው፣ በኦጋዴንና በአኝዋኩ ላይ የተካሄደው የዘር ማጥፋት ዘመቻም የኛ ታሪክ ነው። ለአገር ለምድር እንደ ታቦት የሚከብዱና እድሜ ልካቸውን ቤተክርስቲያናቸውን እና አገራቸውን ያገለገሉት የኦርቶዶክስ ቤ/ክ አባቶች ስደትም የዚህ ትውልድ ታሪክ ነው።

ይሄ ትውልድ ይህንን ታሪክ ፈቅዶ አይደለም የሰራው። ጠብመንጃን መከታ ባረጉት በገዢው መንግስት ጫና ምክንያት ነው። ዝምም ብሎ አላየም። ይህንን ታሪክ ለመቀየር ከፕሮፌሰር አስራት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሁሉም በሚችለው ሞክሯል። አብዛኛው የመታሰር፣ ሌላውም የስደትና የሞት ጽዋ ደርሶታል። እስከ አሁን ድረስ የተከፈለው መስዋዕትነት ዘረኛውን የወያኔ መንግስት ሊገረስሰው አልቻለም። ምናልባትም የትግሉ ስልት ሁሉን አቀፍ ወይም ሁሉንም የትግል ተልዕኮ ያላካተተ ስለ ነበር ይሆናል። አሁን ግን ከምስራቁ የአሜሪካ ክፍል የኢትዮጵያውያንን የትግል ተልእኮ በአንድ ላይ አካትቶ፣ የኤርትራን ባህር አሻግሮ፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር በመውሰድ የዚህን ትውልድ ታሪክ የሚቀይር ልባምና አስተዋይ መሪ የዘመናችን ሙሴ አግኝተናል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በተመቻቸ ህይወት ይኖርባት ከነበረው ምድረ አሜሪካ፣ የደለበ ደሞዝ የሚያገኝበትን የፕሮፌሰርነትን ስራ ትቶ በወያኔ የአፓርታይድ መንግስት የሚሰቃዩት ወገኖቹ ነጻ ይወጡ ዘንድ መከራን መረጠ። ከሁሉም በላይ ሞትን ሳይፈራ እንደ ዓይን ብሌን የሚሳሳላቸው ቤተሰቦቹን ትቶ ምትክ የማይገኝለት ህይወቱን ለኢትዮጵያ ሀገሩ ሊሰዋ ወስኖ ወደ ትግል ሜዳ ሄደ። አስከፊ ታሪክ ያለው የዚህ ዘመን ትውልድ የሚያስደስትም ታሪክ አለው። የዘመናችን ሙሴ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዚህ ትውልድ ታሪክ ነውና። ፕሮፌሰር ብርሃኑ እና የትግል አጋሮቹ ነጻነትን እምነት አርገው የድል ተስፋን ሰንቀው ዱር ቤቴ ብለዋል። እኛስ ምን እያደረግን ነው?

ይህችን አጭር ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ሰሞኑን የወያኔዎችን ደም ያንተከተከው የፕሮፌሰር ብርሃኑ ለአውሮፓ ፓርላማ የሰጠው የምስክርነት ቃል ነው። ሁላችን እንዳያነውና እንዳነበብነው በርቱዕ አንደበቱ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ኢትዮጵያው ውስጥ ያለውን ችግር ነቅሶ በማውጣት አቅርቦታል። በዚህ ትንታኔው ውስጥ የኔን ትኩረት የሳበውን ኃይለ ሃሳብ መጥቀስ እወዳለሁ። ፕሮፌስር ብርሃኑ ወያኔ በቤተ እምነት ውስጥ ጣልቃ እንደሚገባ አስረድቶ በኦርቶዶክስ ቤ/ክ አባቶች ላይ እስከ መሰደድ ያደረሰውን የወያኔ ጥፋት በአለም አደባባይ ይፋ አርጎታል። በተቃዋሚ የትግል ጎራ ያሉ መሪዎች ስለተሰደደችው ቤ/ክ እና አባቶች ከዚህ በፊት ሲያነሱት አለመስማቴ ሁሌም ያሳዝነኝ ነበር። የተሰደደችው ቤ/ክ ወይም ህጋዊ ሲኖዶስ ሰብዓዊ መብት፣ የህግ የበላይነት እና ፍትህ በምድረ ኢትዮጵያ እንዲከበር ከአውደ ምህረትም እሰክ ዓለም በአደባባይ ድምጻቸውን እያሰሙ የትግሉ አካል ተደርገው አለመወሰዳቸው ይገርመኝ ነበር። ሽማግሌ በሀገሪቷ ስለጠፋ እንጂ ከልጅነት እስከ ሽምግልና ቤተክርስቲያንን ያገለገሉ አባቶች በባእድ አገር ሲሰደዱ እንዴት ዝም ይባላል? ዳሩ ሽምግልና የእንጨት ሽበት የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል። እነዚህ አባቶች ስደታቸውን ባርኮ በስደት ያለውን ህዝብ ቢሰበስቡም አያሌ አብያተ ክርስቲያናትን ቢመሰርቱም በየአውሮፕላን ጣቢያ በሽምግልና እድሜአቸው ሻንጣ እየተሸከሙ ህዝባቸውን ለማገልገል ቀና ደፋ ሲሉ ማየት ያቆስላል። የዮሴፍን ስደት የባረከ አምላክ የእነርሱንም ባርኳል። ፕሮፌስር ብርሃኑ ያገኘውን በረከት ቀድሞ የቅንጅት አሁን ደግሞ ህብረ ብሔር ፓርቲ የሆኑት አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች አላገኙትም። ወደፊት የወያኔ መንግስት በሌሎች ቤተ እምነቶች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ሲያወግዙ ወያኔ በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ላይ የፈጸመውን የቀኖና መደፍጠጥ፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የተሾመን መንበር ለስደት ማብቃቱን ማውገዝ ይገባቸዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለሌሎች ታጋዮች ተምሳሌት ሆኗል።