Sunday, June 30, 2013

በ “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” የሚወዳደረው በአምላክ ለአገሩ ያለውን ፍቅር እየገለፀ ነው ተባለ

በዘንድሮ የ “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” አብሮ የመኖር ውድድር፣ በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ወሲብ በመፈፀም አነጋጋሪ ሆና የሰነበተችው ኢትዮጵያዊቷ ቤቲ ከውድድሩ ተሰናበተች፡፡ ውድድሩ ከተጀመረ አራተኛ ሳምንቱን የያዘ ሲሆን እስካሁን ቤቲን ጨምሮ ስድስት ተባርረው 20 ተፎካካሪዎች ቀርተዋል፡፡ ከእነሱም መካከል ሌላው ኢትዮጵያዊ በአምላክ ተስፋዬ (ቢምፕ) ይገኝበታል፡፡ ቢምፕ ለውድድሩ የሄደው አገሩን ስለሚወድና በተገኘው አጋጣሚ ስለ ኢትዮጵያዊነቱ ለመግለፅ ነው ያሉት እናቱ ወይዘሮ ደብሪቱ ሰለሞን፤ ባለፈው አንድ ወር በነበረው ቆይታ ይህንኑ ፍላጎቱን ሲያንፀባርቅ መቆየቱን ተከታትያለሁ ብለዋል፡፡ ‹‹ልጄ የአገር ፍቅር ስላለው በቢግ ብራዘር አፍሪካ ውድድር ፍቅሩን ለመግለፅ እድል አግኝቷል፡፡ ባንዲራው አብሮት ነው፡፡ ሁልጊዜም በሚለብሰው ካኒተራ ወይ ኮፍያ አሊያም በእጁ ላይ የአገሩ ባንዲራን ትቶ አያውቅም፡፡

የሚኖርበት መኝታ ቤቱ እንኳን በባንዲራ ያጌጠ ነው›› በማለት እናቱ ወይዘሮ ደብሪቱ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ልጃቸው በአኗኗሩ እያሳየ ያለው ባህርይ ከልጅነቱ ጀምሮ ያደገበት ስብእናው እንደሆነ የገለፁት እናቱ፤ ባለፉት አራት የውድድር ሳምንታት እንዲባረር አንድ ድምፅ ብቻ እንደተሰጠበት ገልፀው፤ የውድድሩን ውጣውረድ በመቋቋም ሳይሰላችና ለሌሎች ተወዳዳሪዎች እንክብካቤ ሳይነፍግ እስከመጨረሻው ምእራፍ ሊዘልቅና ሊያሸንፍ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ በ “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” ውድድር የኢትዮጵያውያን መሳተፍ ጠቀሜታ አለው የሚሉት ወይዘሮ ደብሪቱ፤ ውድድሩ የአገርን ባህል ለማስተዋወቅ እና ገፅታ ለመገንባት ሁነኛ መድረክ መሆኑን አስረድተው፤ ልጃቸው አብረውት ከሚኖሩት ተወዳዳሪዎች ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ጥያቄዎች እንደሚቀርቡለት እሱም ስለ ባህሏ ፤ስለ ታሪኳ፤ የሰው ዘር መገኛ ስለመሆኗ፣ ስለ ቡና፤ ስለእንጀራውና ስለሽሮው ሳይሰለች ሲያስረዳ ተመልክተነዋል ብለዋል፡፡ ከውድድሩ በወጣች ማግስት አስተያየት የሰጠችው ቤቲ ስላሳለፈችው ጊዜ ስትናገር ቤቱን ለቅቆ መውጣት ከባድ ነው፡፡

በጎንደር ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አባላት መታሰራቸው ቁጣን ቀሰቀሰ

አንድነት በየትኛውም የመንግስት ህገወጥ ጫና ሰልፉን እንደማይሰርዝ ይፋ አድርጓል

በጎንደር ቅስቀሳ ላይ የነበሩ 4 የአንድነት አባላት በፖሊስ መታሰራቸው በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡ አንድነት ምንም አይነት ህገወጥ እስር በጎንደር የተዘጋጀውን የተቃውሞ ሰልፍ እንደማያስቆመው አሳውቋል፡፡

ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ በጎንደር ሰኔ 30 የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ የሚመለከት በራሪ ወረቀት በማሰራጨት ላይ የነበሩት አለልኝ አቧይ፣ ዋኘው፣አብርሀም ልጅ አለም፣አንጋው ተገኝ የተባሉት የአንድነት አባላት ህገወጥ በሆነ መንገድ በአካባቢው ፖሊሶች መታሰራቸው የአካባቢው ነዋሪዎችን እንዳስቆጣ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመላክቷል፡፡ ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ወረቀት በመበተናቸው ብቻ የታሰሩት ግለሰቦች ሁኔታ የስርአቱን አምባገነንነት አመላካች ነው፡፡

የዞኑ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች “እስር ለጎንደር ነዋሪ በተለይም ለአንድነት አባላት አዲስ አይደለም” ካሉ በኋላ “የታሰሩት አባሎቻችንን ለማስፈታት ከምናደርገው ጥረት ጎን ለጎን የቅስቀሳ ስራው እንዳይስተጓጎል ተጨማሪ አባላት የቅስቀሳ ስራውን እንዲቀጥሉ ወደ ስፍራው ልከናል፡፡” ብለዋል፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሙላት ጣሰው ለሰሜን ጎንደር አስተዳዳሪ ለአቶ ግዛቴ አብዩ ስልክ በመደወል የታሰሩት የአንድነት አባላት በአፋጣኝ መፈታት እንዳለባቸው ተናግረው ገዢው ፓርቲ የሚያደርገው አፈና ከህዝባዊ ንቅናቄ እንቅስቃሴያችን አያስቆመንም በማለት አሳስበዋል፡፡

አንድነት ፓርቲ የሚጠበቅበትን ስለሰልፉ የማሳወቅ ተግባር አጠናቆ ቅስቀሳ የጀመረ ቢሆንም በበጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ የተቃውሞ ሰልፉን አላማ የሚያብራራ በራሪ ወረቀት በማሰራጨት ላይ የነበሩ አባላቱ በህገወጥ መንገድ ከመታሰራቸውም በላይ በተለያዩ አካባቢዎች የአንድነት ፓርቲ የቅስቀሳ ቡድን አባላት የሚደርስባቸውን ማስፈራሪያ ወደ ጎን ብለው ቅስቀሳውን አጠናክረው መቀጠላቸውንና የአከባቢው ነዋሪም በራሱ ተነሳሽነት በራሪ ወረቀቶችንና መረጃዎችን በማስተላለፍ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር ዞን አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት አስታውቀዋል፡፡

አንድነት ፓርቲ በጎንደር ለሚደረገው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የጎንደር ከተማና አከባቢው ነዋሪዎች በስፋት እንዲሳተፉ በቀየሰው ስትራቴጂ መሰረት ስኬታማ ቅስቀሳ እያደረገ ሲሆን ሁለተኛው የቅስቀሳ ቡድንም ዛሬ ወደ ጎንገር መንቀሳቀሱ ታውቋል፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት

Friday, June 28, 2013

! ..... ትግላችን ይቀጥላል ......!

እኛ የምንታገለው ነፃነታችንን ለማረጋገጥ እንጂ የተቃዋሚ መሪዎች ለመደገፍ (ወይ ለመቃወም) አይደለም። ትግላችን ዓላማ መሰረት ያደረገ ነው። ዓላማችን ነፃነታችን ነው። የነፃነት ዓላማና ትግል ምን ግዜም አይሞትም።

የተቃውሞ መሪዎች ሊሳሳቱ ይችላሉ፤ ሊቀየሩ ይችላሉ፣ ሊያፈገፍጉ ይችላሉ። ግን የነፃነት ዓላማችን ህያው ሁኖ እስከተገኘ (ነፃነት እስከፈለግን) ድረስ እኛ በመስመራችን አለን።

እኛ የምንቃወምበት ምክንያት ነፃነት ለሰው ልጅ እንደሚያስፈልግ ስለምንረዳ እንጂ መሪዎች ለመቀየር ስለምንፈልግ አይደለም። ስለዚህ የተቃውሞ መሪዎች የፈለጉትን መንገድ ቢከተሉ የኛ የነፃነት መንገዳችን ሊያሰናክል አይችልም።

መሪዎቻችን በዓላማቸው ቢፀኑ መልካም ነው፤ ካልሆነ ደግሞ እኛ ራሳችን ነፃነታችንን እናስከብራለን። ስለዚህ የአንዳንድ የተቃውሞ መሪዎች ንግግሮች እያመጣቹ ትግላችንን ለማደናቀፍ አትሞክሩ (ወይ የሚደናቀፍ አይምሰላቹ)። የኛ ድጋፍ ለነፃነት ጉዛችን እንጂ ለመሪዎች የተሰጠ ውለታ አይደለም።

ነፃነታችንን ለመጎናፀፍ እንጂ የሰው ገዢዎች ለመቀየር አልተነሳንም። ስለዚህ ትግላችን ህያው ነው። (በመሪዎቻችን የተፈጠረ አዲስ ባህሪይ የለም)።

ድጋፋችን በፖለቲካ መሪዎቻችን ትከሻ የተንጠለጠለ የዛፍ ቅጠል አይደለም። የድጋፋችን መሰረት የነፃነት አምሮታችን ነው፤ ይህን ሊቀለብስ የሚችል ሃይል ከቶ ሊኖር አይችልም።

Freedom is the cause.

It is so!!!

ስብሃት ነጋ “እውነት” ሲያዳልጣቸው

ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡት “እውነት” አምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ « አላማና ግብ » አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ « .በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች ነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚሊዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፣ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ያታያሉ። » ብለዋል። « እንቆርጣለን » ያሉት መለስ ዜናዊ ናቸው፤ መለስ በአደባባይ ይህን ከመናገር አልፈው ሲያስፈራሩም እንደነበር እናስታውሳለን። መለስ ያንን ያሉት በ10ሺዎች የሚገመት ቡና ከመጋዘን ጠፋ በተባለበት ወቅት ነው። ያንን ቡና የሰረቁትና ባህር ማዶ ሸጠው ገንዙቡን ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጭ ተጠቅሶ ይፋ ተደርጓል። እናም ስብሃት “መቶ ሚሊዮን የሰረቁ..» ያሉት አዜብ መስፍንን ሲሆን፣ « ያስዘረፉ» ያሉት ደግሞ ባለቤታቸው አቶ መለስን ነው። « 10ሺህ የሰረቁ..» የተባሉት በቅርቡ የታሰሩት የጉምሩክ ሰዎችን ሲሆን..እነዚህን በንፅፅር ያስቀመጡት የአዜብ (ተላላኪዎች) ስርቆት መጠነሰፊ መሆኑን ለማመላከት ነው። ስብሃት እስካሁን አድፍጠው ቆይተው በዚህ ሰሞን ይህን መናገራቸው ..«አዜብ የከተማዋ ም/ል ከንቲባ ይሆናሉ» የሚባለውን በመስማታቸው ሆን ብለው ያደረጉት ነው፥ ይላሉ ታዛቢዎች። በተለይ ሽማግሌውን በቅርብ የሚያውቋቸው የፓርቲው ሰዎች « ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በቀለኛ ነው። ጥርሱ ውስጥ የገባን ሰው ካላስወገደ እንቅልፍ አይወስደውም፤ ብዙ ሰው አጥፍቶዋል። አሁንም አዜብን እግር በእግር የሚከታተለው ለዚሁ ነው» ይላሉ። በማስከተልም ፥ « ሙስና ከተነሳ ስብሃትም እስከአንገቱ ተነክሮበታል። በገርጂና ሳር ቤት የሚገኘው <ሉሲ አካዳሚ > በአሜሪካ በሚኖሩ ስጋ ዘመዶቹ ስም እንዲሁም በቀድሞ የአየር ሃይል ጄ/ል ሰሎሞን ስም የሚንቀሳቀስ ግን የስብሃት የግል ንብረት መሆኑን የማይታወቅ መስሎት ነው?....ጎንደር -ሑመራ ያለው የሰሊጥ እርሻ የስብሃት አይደለም?...በ10ሚሊዮን ብር በሚገመት በመቀሌ (አፓርታይድ መንደር) ስብሃት ዘመናዊ ቪላ እንደሚገነባ አይታወቅም ብሎ ይሆን?...» ሲሉ እነዚህ ወገኖች የስብሃትን ሙስና በከፊል ይጠቅሳሉ።

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄን እንርዳ!


ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ “Solidarity Movement for a New Ethiopia” (SMNE) “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ነጻ ሊሆን አይችልም” እና “ከጎሳ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ” በሚል መሪ መፈክር በአቶ ኦባንግ ሜቶ እየተመራ ድምጻቸው ለታፈነው ኢትዮጵያውያን ድምጽ መሆኑን ቀጥሏል።

በኢትዮጵያ የህወሀት/ኢህአዴግ ቡድን ዜጎችን አያት ቅድመ አያቶቻቸው ካወረሷቸው ቀዬ እያፈናቀለ ግልጽነት በሌለው መልኩ መሬታቸውን ለአረብ እና ህንድ ቱጃሮች በርካሽ ሲቸበችብ፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄና ኦባንግ ሜቶም በበኩላቸው አልተኙም። ዓለም በደሀውና ድምጹ በታፈነው ኢትዮጵያውዊ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እንዲገነዘብ ማድረግ ችለዋል። ኦባንግ ሜቶ ወደ ህንድ ሀገር ጭምር በመጓዝ በታላላቅ የህንድ ሚዲያዎች ስለጉዳዩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ኦባንግ ሜቶ አለምን እያቆራረጡ ኢትዮጵያውያን ድረሱልን ያሉበት ቦታ ሁሉ ይገኛሉ። አስከፊውን የአፈና ስርዓት ሸሽተው በጥገኝነት በሚኖሩባቸው ሀገራት ተጽእኖው ሲበረታባቸው አቶ ኦባንግ ሜቶ ዋስ ጠበቃ ሆነው ይከራከራሉ።

“ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ” በጥቂት ኢትዮጵያውያን የገንዘብ ድጋፍ እየታገዘ ይህን ሁሉ ማድረግ ከቻለ። ሁላችንም የአቅማችንን ብንረዳ ደግሞ ምን ያህል የተሻለ ስራ ሊሰራ እንደሚችል አያጠያይቅም።

ከ 110 በላይ ኢትዮጵያዊ ባህር ላይ ቀሩ


ስለ ስደተኛው የቁራሌው ጩኸት እስከ ጠ/ሚኒስትር ቢሮ….

በግሩም ተ/ሀይማኖት

‹‹…ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ተቃዋሚ ሀይሎች ከጅቡቲ ወስደው መጠቀሚያ ሊያደርጓቸው ነበር፡፡ ብዙ እናውቀለን…›› ይህን በስደት ዙሪያ የአዞ እንባ ያነባው ኢቲቪ ለውይይት ከጋበዛቸው ውስጥ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ያዳለጣቸው ነው፡፡ ያዳለጣቸው ያልኩት መንግስት ያን ሁሉ ማስመሰያ ያደረገበት ምክንያት ምን እንደሆነ አባሳደሩ በግልጽ ሳያውቁ ስላስቀመጡት ነው፡፡ የስደተኛው ህይወት አሳዝኗቸው አይደለም፡፡ ተቃዋሚዎች ይዘው ሊጠቀሙባቸው ስለሚፈልጉ ወይም ስለሞከሩ ነገ ስልጣናቸውን ላለማጣት ነው፡፡ ያ-ካልሆነማ ስንት አመት በሙሉ በስደት ወገን ረገፈ ሲባል…ሲጮህ ዝም በዝምታ ብለው በስደተኛው የጣር ድምጽ ባላላገጡ ነበር፡፡ ግን የፈሩት ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የትጥቅ ትግል ሊያደርጉ መሰናዶ ላይ ስለሆኑ ከሆነ አንድ ሰሞን አራግበው ዝም ማለት ጦሱ እንደሚብስ ለምን ልብ አላሉትም? የወጣውስ በአግባቡ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ካልተደረገ ወዴት እንደሚያቀና እንዴት አላገናዘቡም? ይገርማል፡፡ ሳዑዲ አረቢያ እየተሰቃየ ያለው ህዝብ ወዴት እያመራ ይመስላቸዋል? ለምንስ ያን አያስቡም? እንደ ዜግነቱ የሀገሩ ኤምባሲ ሊከራከርለት ሲገባ፣ ወደ ሀገሩ ሊመልሰው ሲገባ ኮሚኒቲ የሚባለው ውስጥ ተፋፍጎ ሶስት እና አራት አመት እንዲቀመጥ የአእምሮ መታወክ እንዲገጥመው ሲደረግ፣ በሽተኛውም ጤነኛውም በአንድ ቦታ እንዲቆይ ሲደረግ…ትኬት የሚቆርጥልህ ቤተሰብ ከሌለህ…ያመጣችሁ ሰው ትኬት ይቁረጥላችሁ..ተብሎ ከእሱ ዜግነት ይልቅ ለብር ክብር ሲሰጥ ሲያይ..ሀገሬ ባላት ኤምባሲ ሲበደል ለምንስ አይከፋው? ለምንስ አማራጭ አይወስድ? አንድ ሰሞን ሆይ ሆይ ብሎ ፖለቲካ ለማሳመሪያ ፕሮግራም ማድመቂያ ማራገብስ ውጤት ያመጣል? አያመጣም፡፡ መንግስት ህዝብን እያታለለ እስከመቼ የሚጓዝ ይመስለው ይሆን? ህዝቡ እኮ ያውቃል፡፡ ሳዑዲያ ፣ የመን.. እየተጨቆነ ያለው ወገኑ አይደለ እንዴ? ቤተሰቡ አይደለ እንዴ? ታዲያ የአንድ ሰሞን የሚሊኒየም አዳራሽ እና የኢቲቪ ለቅሶ የአዞ እንባ አልሆነም? ሆነ፡፡

አስተዳዳሪዬ ባይላቸውም አስተዳዳሪህ ነን ብለው ላዩ የተጎበሩበት ሰዎች እስከ ጠ/ሚኒስትሩ ድረስ በውሸት ሲደልሉት፣ አፋቸው ሌላ ስራቸው ሌላ ሲሆንበት ቢጠላቸው ምን ሊደንቅ? ምንም፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለትጥቅ ትግል ስደተኞችን ሊጠቀሙባቸው ብቻ ሳይሆን ስደተኛው ሀገሩ መመለስ ካልቻለ እሱ ራሱ ተቃዋሚዎችን ፍለጋ በዳዴ መሄዱ አይቀርም፡፡ በተቃዋሚዎች ተጠቅሞ መታገሉም አይቀርም፡፡ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ካሉት ላይ ልበደርና ‹‹…ከጅቡቲ ወስደው ተቃዋሚዎች ለትግል ሊጠቀሙባቸው…›› ቀርቶ ስለ ስደተኞቹ መኖርስ ተቃዋሚዎች ያውቃሉ ወይ? እንደሚያውቁ አቃለሁ ግን እነሱ ‹‹..አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም..›› እንዲሉ ሆነዋል፡፡ ስደተኛው ኢትዮጵያዊ የሆነ እስከማይመስል ድረስ ተቃዋሚዎችም ረስተውታል፡፡ የተሻለ ሀገር ቢሆን የሚሰደደው እና ዶላር መቁጠር ቢጀምር ግን እኛ ያላንተ ይባል ነበር፡፡ ዛሬ ምን ሊያደርግ? መከራ እንጂ ዶላር ስለማይቆጥር አላስታወሱትም፡፡ መንግስት ግን መከራውን መስማቱን አይፈልግም እንጂ ከዚህ ችግር ተርፈው ከተማ ከገቡ ከኤምባሲው ምንም አይነት ግልጋሎት ቢፈልግ ጌሙ ፍራንካ ነው፡፡ ዜጋ ነህ ቅብርጥሴ…ምንትሴ አይሰራም፡፡ ገንዘብ ከያዘ የአማራ ልማት..የትግሬ ልማት..የእንትን ልማት…በቆዳ እስኪቀሩ መጋጡን እንደ ጅብ ይችሉበታል፡፡ እሰይ የወያኔ ኤምባሲ…ብራቮ ይህን ምስኪን ስደተኛ ተገፍቶም ተደፍቶም ያመጣውን በሰበብ አስባቡ ንጠቁ፡፡

ደሀን የሚያስብ፣ ግፍ የሚፈጸምበት ስደተኛን የሚያይ የሚያስተውል መንግስትም ሆነ ተቃዋሚ አልገጠመንም፡፡ ያው ሁሌም ዞረሽ..ዞረሽ እንደሚሉት አይነት ነው የሚገጥመን፡፡ ትላንት ከሶማሊያ ጋር አብረው ሀገራቸውን የወጉ ተቃዋሚዎች አይነት አሁንም አሉን ከግብጽ ጋር ለመሰለፍ ያቆበቆቡ፡፡ ሀገራቸውን ከጠላት ጋር ወግተው ስልጣን ማግኘት እንጂ የህዝቡ ቁስል ያላቆሰላቸው ተቃዋሚዎች አሁንም አፍርተናል፡፡ ኢትዮጵያን እንወዳለን፣ ሀገሬ ክብሬ.. የ3000 ዘመን ታሪክ እያሉ ቀረርቶ የሚያሰሙ መንግስት እና ተቃወዋሚ አሁንም አሉን፡፡ ባይኖሩ በቀሩብን፡፡ ኢትዮጵያ ሀገሬ ጋራሽ ሸንተረሩ ሜዳማ…የሚል ቀረርቶ እያንቃረሩ መሬትና አፈሩን የሚወዱ ህዝቡን ያላማከሉ መንግስትና ተቃዋሚ አሉን፡፡ አሉ ከተባለ….

በሰቀቀን ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ተሳቆ መውጫ ቀዳዳ ጠፍቶት፣ ሀገሩን መርገጫ መላ አጥቶ ያለውን ዜጋ ማን አስታወሰው? ማንም፡፡ የመን ውስጥ ሀረጥ የሚባለው የአለም አወቀፉ ስደተኞች ድርጅት ካምፕ ውስጥ ያለውን ስደተኛ ቁጥር ማን ይቀንሰው? የኢትዮጵያ መንግስት ከስደተኛ ቢሮው ጋር በመተባበር ዜጎቼን እየሰበአሰብኩ ነው ሲል ይቃዣል፡፡ ከዚህ ቅዠት ግን መቼ እንደሚነቃ እና እንደሚሰራ ነው ግራ የገባን፡፡ ስደተኛው አሁንም ስቃይ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ስደተኛው አሁንም ባህር እየተሻገረ ነው ያለው፤ ስደተኛው አሁንም ባህር ላይ እየሰመጠ ነው የለው፡፡ ከሳምንት በፊት ከጅቡቲ ወደ የመን ድንበር እየገሰገሰ ያለ ጀልባ በመሳሪያ ተመቶ ሰጥሟል፡፡ የጫናቸው ዜጎቻችን በሙሉ ባህር በልቷቸዋል፡፡ ወደ 120 ሰው እንደሞተ ወዲያው ሰማሁ እና ለማጣራት አለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት ውስጥ እና ሜዲካል ሳን ፍሮንቴን (ድንበር የለሽ የህክምና ቡድን) ሰራተኞች ጋር ስልክ መታሁ፡፡ እነሱም ወሬውን አማቱት፡፡

በመሳሪያ ነው የተመታው ስለተባለ ማን ነው የመታው የሚለውን ጨምሮ እንዲመልሱልኝ በመጠየቄ የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ እንድንል ነገሩን አድበስብሰው እንዲያውም መረጃ ካገኘህ ስጠን አሉ፡፡ በሰዓቱ አስከሬን በመልቀም ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ ሰው ነው ደውሎ መረጃውን የመረጀኝ፡፡ ከሌሎች አካላት ለማጣራት እንደሞከርኩት ደግሞ በመሳሪያ ተመቶ ሳይሆን በአሁኑ ወቅት ሀይለኛ ንፋስ(ማዕበል) ያለበት ወቅት በመሆኑ ያሰጠማቸው ማዕበል ነው በመሳሪያ አልተመታም ብለውኛል፡፡ ጀልባው ተመታም አልተመታም ለእኛ ወገኖቻችንን አጥተናል፡፡ ባንዴ 120 አካባቢ አርግፈናል፡፡ ይሄ መንግስት ፍካሬውን ሳይጨርስ የሆነ ሁነት ነው፡፡ ያሳፍራል፡፡ መንግስት የስልጣን ዘመኑን ማራዘሚያ የወቅቱን ፖለቲካ ማስከኛ ለፈፈው የሳምንት ሆይ ሆታ ሳይፈዝ ይሄ መሆኑ ያወራል እንጂ መቼ ይሰራል፡፡ ማውራት እና መስራት ለየቅል ናቸው ያሰኛል፡፡


የአብዬን ወደ እምዬ



ወያኔና ከወያኔ አፍ የሰሙትን ሁሉ እንደበቀቀን እየደጋገሙ የሚያነበንቡ ሎሌዎች የራሳቸውን መልክ የሚያዩበት መስታወት የተቸገሩ ይመስላል። ወየኔና ሎሌዎቹ እራሳቸውን ማየት ስለተሳናቸው ህዝብም ልክ እንደ እነሱ ኣራሱን የማያይና እነሱንና እኩይ ስራቸዉን የማያዉቅ እየመሰላቸው ሄዷል፡፡ ለዚህም ነዉ በግፈኛ አገዛዛቸው ተንገፍግፎ የሚቃወማቸውን ሁሉ ጥላሸት ለመቀባትና በራሳቸው ስም ለመጥራት ሲንጠራሩ የሚታዩት።

የወያኔ ዘረኞች የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ኃይሎች በሙሉ በፀረ-ኢትዮጵያዊነትና የአገርን ጥቅም ለባዕድ አሳልፎ በመሸጥ ሲከስሱ ስንሰማ አይናቸዉንና ፊታቸዉን ታጥበዉ አይነ ደረቅ ለመመሰል ስንት ኪሎ ጨው እንደፈጀባቸዉ መገመት ያዳግታል።

በአገራችን ታሪክ ውስጥ እንደወያኔ በኢትዮጵያ ህልውናና በወሳኝና ዘላቂ ጥቅሞቿ ላይ የዘመተ ኃይል ኖሮም ተፈጥሮም አያውቅም። ለመሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጀግኖች አባቶቻችን አጽም ያረፈበትን መሬት በስጦታ ለጎረቤት አገር እናካችሁ ብሎ የሰጠ ማነዉ? ማነው በሽፍትነት ዘመኑ ለተደረገለት ውለታና ተቀናቃኞቹን እንዲጠብቁለት በማሰብ የኢትዮጵያን ድንበር እንደ ዳቦ እየገመሰ ለባዕዳን የሸጠው?

ማነው የገዛ ወገኑን ከአያት ቅድመ አያት አጽመ ርስቱ ላይ እያፈናቀለ አንድ ሲኒ ቡና በማይገዛ ገንዛብ ለምለም መሬታችንን ለባእዳን የሚያቀራምተው? ማነው በህዝብ ስም በልመናና በችሮታ የተገኘን ገንዘብ እየዘረፈ ከአገርና ከህዝብ ደብቆ የባእድ አገር ባንኮችን የሚያደልበው? ኢትዮጵያ በሶማሊያ በተወረረችበት በ1970ዎቹ አመታት የሞቃዲሾን ፓስፖርት ተሸክመው ይንጎማለሉ የነበሩት የዛሬዎቹ የወያኔ አለቆች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ህዝብ ገና አልረሳዉምኮ!

የዛሬዎቹ የወያኔ መሪዎች ትናንት የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት ማየት ከማይፈልጉ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ጋር እጅና ጓንት ሆነዉ የኛን የጎሳ ድርጅት እስከረዳችሁ ድረስ ኢትዮጵያን እናደክምላችኋለን የሚሉ ጸረ አገርና ጸረ ህዝቦች ነበሩ።እነዚህ የለየላቸዉ ከሀዲዎች ዛሬ አይናቸዉን በጨው አጥበዉ እራሳቸዉን የኢትዮጵያ ጥቅም አስከባሪ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነትና ለአገር አንድነት መከበር የሚታገሉትን ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች የአገር ጠላት ብሎ ለመጥራት የሚያበቃ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያክል የሞራል ብቃት የላቸውም።

ወያኔዎች ስልጣን በያዙ ማግስት በጻፉትና እነሱን ሲጠቅም በሚጠቅሱት አገርንና ህዝብን ሲጠቅም ግን እየዳጡ በሚያልፉት ህገመንግስት ዉስጥ ደደቢት በረሃ የወሰዳቸዉን ዋነኛ አላማ መገነጣጠልን እንደ አገር ጥቅም በጹሁፍ ካልሰፈረ ብለው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ የነበሩበትን ጊዜ እኛ የኢትዮጵያ ነገር የሚቆረቁረን ወገኖች አልረሳነውም። ለመሆኑ ሌሎችን በጸረ-ኢትዮጵያዊነት የሚከሰው ወያኔ እውነት ኢትዮጵያን ከወደደ መገነጣጠልን ለምን ተመኘላት? መገነጣጠልን የመሰለ አደጋ እንደ ብሔራዊ የአገር ጥቅም አይቶ የራሱን ምኞት በህግመንግስት ደረጃ ያጸደቀዉ ወያኔ እንዴት ሆኖ ነው ለኢትዮጵያ አንድነትና ክብር የሚጋደሉና የሚታገሉ ልጆቿን በሀገር ጠላትነት የሚከስሰው? የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ጋር የሚደረገዉን ትግል ከመብትና ከነጻነት ትግል ባሻገር እንደ አገር አድን ትግል አድርጎ የሚመለከተዉ ይህንኑ ወያኔ በአገራችን ብሄራዊ ጥቅሞች ላይ በተደጋጋሚ ያሳየዉን ጠላትነት በመገንዘብ ነዉ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ተቃዋሚ ኃይሎችን በጅምላ የአገር ጠላት ለማስመሰል በሚቆጣጠራቸዉ የመገናኛ አዉታሮችና በታማኝ ሎሌዎቹ በኩል የጀመረዉን የስም ማጥፋት ዘመቻ ከወዲሁ ተረድቶ “የአብዬን ወደ እምዬ” ብሎ ትግሉን ከቀጠለ ዉሎ አድሯል። ወያኔና ለሆዳቸው ያደሩ ሎሌዎች ሁለመናቸውን የወረሰውን የፀረ-ህዝብና ጸረ ኢትዮጵያዊነት እከክ ማንም ላይ ማራገፍ አይችሉም። ድፍን ኢትዮጵያ ማንነታቸውን አሳምሮ ያውቃልና።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Thursday, June 27, 2013

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

ሕዝባዊ ንቅናቄያችን የመጀመሪያውን ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ያደርጋል!!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት ህዝባዊ ንቅናቄ የትግል ስልት በመንደፍ እንቅስቃሴ መጀመሩን በይፋ መግለጹ አይዘነጋም፡፡ የህዝባዊ ንቅናቄው የመጀመሪያ የአደባባይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍም ሰኔ 30/10/2005 በጎንደር ከተማ ይደረጋል፡፡ የአገሪቱ ህገ መንግስት በሚደነግገው መሰረትም ፓርቲው ከህዝቡ ጋር የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ማወቅ ለሚገባው አካል የፓርቲያችን መዋቅር አሳውቆ ወደ ቅስቀሳ ገብተዋል፡፡

በሰላማዊ ሰልፉ ላይም በጎንደር እየተፈጸመ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ሰዎችን በአደራ ማሰር፣ ለሱዳን ከህዝቡ እውቅና እና ፈቃድ ውጪ መሬት መሰጠቱን፣ በነጋዴዎች ላይ የሚፈጸመውን ኢ-ፍትሃዊ አሰራር፣ ለስራ የደረሱ ወጣቶች የፓርቲ አባል ካልሆኑ በስተቀር ስራ የማያገኙበትን ሁኔታ፣ በዘር ላይ የተመሰረተን ማፈናቀልና የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ ህዝቡ የተቃውሞ ድምጹን በነቂስ ወጥቶ ያሰማል፡፡ እንዲሁም የጸረ ሽብር ህጉ የዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ በመሆኑ እንዲሰረዝ ይጠየቃል፡፡ ብዙ ሺ የከተማው ኗሪዎችም የተቃውሞ ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉን በጎንደር ከሚገኙ የፓርቲው አባላትና አመራሮች ጋር የተሳካ ለማድረግ አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና ቢሮ አስተባባሪ አባላት የተላኩ ሲሆን የቅስቀሳ ስረቸውንም ጀምረዋል፡፡ ቅዳሜም ሁለተኛው ቡድን ወደ ጎንደር ያቀናል፡፡ የፓርቲያችን ስራ አስፈጻሚ፣ የብሄራዊ ምክር ቤትና በየመዋቅሩ ያሉ አባላቶቻችን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ለመገኘት ወደ ጎንደር ያመራሉ፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ጎንደር ከሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ቅርንጫፍ ቢሮ ተነስቶ ወደ መስቀል አደባባይ በማምራት በመስቀል አደባባይ በሚደረግ ልዩ ልዩ ፕሮግራም የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ በጎንደር መስቀል አደባባይ ለሚገኘው ህዝብ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችና ታዋቂ ግለሰቦች የሰላማዊ ሰልፉን ዓላማ የሚገልፅ ንግግር ያደርጋሉ፡፡

ፓርቲያችን አንድነትም የሦስት ወር ሕዝባዊ ንቅናቄያችንን ይፋ ካደረግን ጀምሮ ሕዝቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ተቋማት፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ የሚዲያ ተቋማት፣ የፀረ-ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ ፔቲሽን ለፈረሙትና ከጎናችን ለቆሙ ታዋቂ ግለሰቦች በአክብሮት ምስጋና እያቀረብን አሁንም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሀገራዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ሰኔ 20 ቀን 2005 ዓ.ም

አዲስ አበባ

- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=4723#sthash.6ivp2S3J.dpuf

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ


ታሪክ እንደሚያስረዳው የጎንደር ህዝብ ለኢትዮጵያ አንድነት ብዙ ዋጋ የከፈለ አሁንም እየከፈለ ያለ ነው፡፡ ለሀገር አንድነትና ሉአላዊነት ደንታ የሌለው የኢህአዴግ ስርአት የጎንደርን ድንግል መሬት ለሱዳን አስረክቧል፡፡ አባቶቻችን በደም የዋጁትን የሀገራችንን መሬት ለባዕዳን ያስረከቡ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለህግ እንዲቀርቡ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በተለይም የጎንደር ነዋሪ የመጠየቅ ታሪካዊ ግዴታ አለበት፡፡ ኢህአዴግ ተጨማሪ መሬቶችን ለእየቆረሰ ላለመስጠቱ ምን ማረጋገጫ አለን? ሚሊዮኖች ሆነን ድምፃችንን ከፍ አድርገን የምንጠይቅበት ጊዜው አሁን ነው፡፡

Ø  ኢትዮጵያ ዜጎች ሰርተው የሚኖሩባት፣ነግደው የሚያተርፉባት፣ልጅ ወልደው የሚያሳድጉባትና አስተምረው ለስራ ማብቃት የሚችሉባት ሀገር አልሆነችም፡፡ ስራአጥነት ተንሰራፍቶባታል፤ ዜጎች ዲግሪ ይዘው ኮብል ስቶን ፈላጭ ሆነዋል፣ በሀገራቸው ሰርተው መኖር ያልቻሉ ወጣቶች አስፈሪ የባህርላይና የበረሀ ጉዞዎችን በማድረግ ሀገር ጥለው ተሰደዋል፣በዋጋ ንረት አብዛኛው ዜጋ ያቃስታል፡፡ የነዚህ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምንጭ ኢህአዴግ የሚከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ ነው፡፡ የስርአቱ ቁንጮዎች የተዘፈቁበት ሙስና ለችግሮቹ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ በየጊዜው ከሀገራችን በህገወጥ መንገድ በኢህአዴግ ባለስልጣናት የሚወጣው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ገንዘብም ከደሃው ጉሮሮ የተነጠቀ እንደመሆኑ ለህዝባችን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበታል፡፡ ከስርአቱ ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ጥቂት ግለሰቦች ተንደላቀው ሲኖሩ የተቀረው ህዝብ ግን በመኖርና ባለመኖር መካከል ይንገላታል፡፡ ታዲያ እስከመቼ በዋጋ ንረት ተቆራምደን፣በስራአጥነት ተንገላተን፣በስደት ክብራችንንና ህይወታችንን አጥተን፣ የበዪ ተመልካች ሆነን እንቀጥላለን? በሀገራችን ኢኮኖሚ እኩል ተጠቃሚ የመሆን መብታችንን ለማስከበር ጊዜው አሁን መሆን አለበት፡፡

በፀረ ሽብር ህጉ ሰበብ ከፌደራል መንግስት ተልከን መጥተናል የሚሉ የደህንነት ሀይሎች ጎንደር ላይ የፈለጉትን ሰው ማሰርና እንደዕቃ በአደራ ማስቀመጥን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ በርካታ ዜጎች በቤተሰቦቻቸውና በወዳጆቻቸው ሳይጎበኙ በተለያዩ እስር ቤቶችና ስውር ማሰቃያ ስፍራዎች አበሳቸውን እያዩ ይገኛሉ፡፡ በአፋኙ የኢህአዴግ መንግስት የታሰሩ ወገኖቻችንን እንዲፈቱ አስቀድሞ ጥያቄ ለማቅረብ ከጎንደር ህዝብ የሚቀድም ማን ይኖራል? የፀረሽብር ህጉ እንዲሻርና በዚህ ኢህገ መንግስታዊ ህግ የታሰሩ ዜጎች በነፃ እንዲለቀቁ ለመጠየቅ የጎንደር ህዝብ በአደባባይ ድምፁን ያሰማል፡፡
   
Ø  ኢህአዴግ ለዘመናት አንድ ሆኖ የኖረውን የጎንደር ህዝብ በዘር ለመካፋፈል ደፋ ቀና እያለ ነው፡፡ የስርአቱ ማለሟሎች በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ለ22 እንዳደረጉት ሁሉ በጎንደርም አንዱን ቅማንት ሌላውን አማራ በማለት በነገድ ለመለያየት የሚያደሩት የክፋት ድር መበጣጠስ ያለበት አሁን ነው፡፡ አንድነታችንን ለማጥፋት የሸረቡትን ሴራ በአደባባይ ለማጋለጥ ጊዜው አሁን ነው፡፡
አንድነት ፓርቲ በነዚህና ሌሎች ህዝባዊ ጥያቄዎች ዙሪያ የጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ በገዢው ፓርቲ ላይ የማያቋርጥ ጫና ለመፍጠር ሀገር አቀፍ ተግባራዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ነው፡፡ በመሆኑ የዚህ ንቅናቄ አካል በመሆን ድምፃችንን በጋራ እንድናሰማ እንጠይቃለን፡፡

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ

ምንጭ፡ millionsofvoicesforfreedom

Wednesday, June 26, 2013

ሚሚ ስብሃቱና አያ ጅቦ

እንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በቅርቡ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል አቢይ ርዕስ የህዝባዊ ንቅናቄ ጥሪ ለህዝብ ማስተላለፉ አይዘነጋም፡፡አንድነት በዚህ ህዝባዊ ንቅናቄ የአንድ ሚልዮን ዜጎችን ፊርማ በማሰባሰብ የዜጎችን የማሰብ፣ የመናገር ፣በነጻነት የመደራጀትና ሃሳብን የመግለጽ መብቶችን ጨምሮ ከህገ መንግስቱ ጋር ይጋጫል ያለውን የጸረ ሽብር ህግ እንዲሰረዝ ህጋዊ መስመርን በመከተል ጫና እንደሚያደርግ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ ይህንኑ መግለጫ ተከትሎ የዛሚዋ ሚሚ ስብሃቱ በምትመራው ‹‹የጋዜጠኞች የክብ ጠረጴዛ ››የውይይት መ
ድረክ የአንድነትን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከግብጽና ከግንቦት 7 ጋር በማቆራኘት ‹‹ፓርቲው ይህንን እንቅስቃሴ ያደረገው የህዳሴው ግድብ እንዳይሳካ ከሚፈልጉ ሀይሎች የገንዘብ ድጉማ ተደርጎላቸው ነው፡፡››በማለት የወረደና የተለመደ ፍረጃዋን አስደምጣለች፡፡ አንድነትን ለፍርፋሪ ያጩት እነ ሚሚ አልገባቸውም ወይም ሆን ብለው የሚሰማቸው ካለ ለማሳሳት አልያም አፍቅሮተ ኢህአዴግነታቸው ከኢህአዴግም በላይ ራሳቸውን እንዲያስቀምጡ አድርጓቸው ይሁን በተለየ መንተገድ የአንድነትን የሰላማዊ ትግል ጥያቄ አንድ ከረጢት ውስጥ በመክተት ፓርቲውን ለማስወንጀል ደንጊያ ለማቀበል ታትረዋል ግን አንድነት ለምን የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ ይታገላል; ኢትዮጵያስ የሽብር ህግ አያስፈልጋትም የሚል አመለካከት አንድነት አለውን; ይህ ምላሽ ሁለት ጆሮዎቿን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የደፈነችውንና በነጻ ሚዲያ ስም የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ያገኘችውን ሚሚንና ሁለቱን ደንገጡሮቿን አይመለከትም፡፡

1)አንድነት በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ከኢህአዴግ ጋር በተቃራኒነት ስለተሰለፈ ብቻ ለማንም አሳልፎ አይሰጥም፣የአገሪቱን ጥቅም ከሚጎዳ የትኛውም ቡድን ጋርም የሚፈጽመው ምንም አይነት ስምምነት አይኖርም፡፡አንድነት በዚህ በኩል ጽኑ ኢትዮጵያዊ አቋም አለው፡፡እንዲህ አይነት ልምድና ታሪክ ያለው አሁን በገዢነት መንበር ላይ የተቀመጠው ኢህአዴግ እንጂ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማያወላውል አቋም ያለው አንደነት አይደለም፡፡ለገዢው ፓርቲም የሚበጀው የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ ከወቅታዊ ሁነቶች ጋር በግድ በማዛመድ ትርጉም መስጠት ሳይሆን ለመነጋገርና እውነታውን ለመቀበል መዘጋጀት ብቻ ነው፡፡

ወያኔ ሕወሃት የደደቢቱን አስታውስ!


በሚያስደንቀው የሀገራችን ምርጫና ከዚሁ የምርጫ ሳጥን በሚገኝ የሕዝብ ድምጽ፤ በሰላማዊ መንገድ ወያኔ ሕወሃትን እናሸንፋለን ብለው ቀን ከሌት ከሚደክሙትም ሆነ ሰላማዊው አማራጭ አዋጭ አይደለም በማለት በነፍጥ ወያኔን ለማንበርከክ እየታገሉ ያሉ ኢተዮጵያዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም ሆነ ድርጅቶችን በሀገር ፍቅር ማጣትም ሆነ ተቆርቋሪነት፣ በሕዝብ ክብር መጉደልም ሆነ ሀላፊነትን መዘንጋት ለመውቀስ የሚያበቃ የሞራል ልዕልና ወያኔ ሕወሃት የለውም። ሌላው ቀርቶ በጫካ ዘመን አስተሳሰቡና ምግባሩ ይቅርና መንግስት ነኝ ካለ በሗላ ባሳያቸውና እያሳያቸው ባሉት ምግባሮቹ እንኳ ቢገመገም በሀገራችን ካሉት ሀገራዊም ሆኑ ክልላዊ ፓርቲዎች እንዲሁም በነፍጥ እየታገሉ ካሉት ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ጋር ለመወዳደር የሚያበቃ ተክለ ሰውነት እንዲሁም የሀገርና የሕዝብ ፍቅር አልታየበትም።

እነዚህን ፓርቲዎች ወይም ድርጅቶች አንድ ጊዜ የሀገራችንን ጥቅም አሳልፈው የሸጡና ከአሸባሪ ጋር የወገኑ ሌላ ጊዜ ከሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ያበሩና ሀገር ለማፈራረስ የተዘጋጁ እያለ ለመክሰስ እራሱ ወያኔ ሕወሃት ማነው? እንዴትስ አሁን ላለበት የገዥነት ወንበር በቃ? በነማን እርዳትነት? አሁንስ ስለ ሀገራችንና ሕዝባችን ያለው አመለካከት ምንድን ነው? እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች መመልከት ተገቢ ይሆናል።

በመጀመሪያ ደረጃ ለሕዝባችን በሰላማዊም ሆነ በሌላ አማራጭ እየታገሉ ካሉት ድርጅቶች ፍጹም የተለየ በነበረው እንቅስቃሴው በዓለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪ ተብሎ ተፈርጆ የሀገራችን ማፈሪያ የነበረው ድርጅት ራሱ ወያኔ ሕወሃት እንጅ ሌሎች የሀገራችን ፓርቲዎች ድርጅቶች ወይም ንቅናቄዎች አልነበሩም። የህ የወገንና የሀገር ማፈሪያ የሆነው ቡድን ወያኔ ሕወሃት በተለይ ከ1968 እስ 1982 ዓ/ም በነበሩት ዓመታት በሕዝባችንና በሀገራችን ላይ በፈጸማቸው አስር የከፉ የአሸባሪነት ስራዎች ምክንያት ስሙ በዓለም አቀፉ የአሸባሪዎች ዳታ ቤዝ ተመዝግቦ ይገኛል። “የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” እንደሚባለው ሆነና ዛሬ ግን ራሱ ተመልሶ እንደፈለገ በሚያዘው ፓርላማው በመጠቀም ስለ ሕዝባቸው አርነት ስለ ሀገራቸው ነጻነት እየታገሉ ያሉ ድርጅቶችን አሸባሪ የማያስቡና ለሕዝባቸው ደንታ የሌላቸው ለማለት በቃ።

ዛሬ በሂወት የሌሉትም ሆኑ በአካለ ስጋ የሚንጠራወዙት አብዛኞቹ የወያኔ ቁንጮዎች ያኔ በጫካ ዘመናቸው በዓለም ዙሪያ ለልመና ይንቀሳቀሱ የነበሩት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ከነበረችው ሶማሊያ ጋር በማበርና ከሶማሊያ በተገኘ ፓስ ፖርት በመጠቀም እንደነበር ሲታወስ ወያኔ ሕወሃት በተቃዋሚዎች ላይ አፉን ለማላቀቅ ምን የሞራል ብቃት አለው? ያስብላል። ከዚህ በተጨማሪም ከጎረቤት ሱዳንና ግብጽን ጨምሮ ከአብዛኞቹ አረብ ሀገሮች ከፍተኛ እርዳት ይፈስለት የነበረው ወያኔ ሕወሃት ከታሪካዊ ጠላታችን ሱዳን ግዛት እየተንደረደረም የሽብር ጥቃቱን በሕዝባችን ላይ ይፈጽም እንደነበር መቼም የማንረሳው የሃዘን ትዝታችን ነው። ይህንን የሱዳን እርዳታም ከውሌታ በመቁጠር ይመስላል ርዝመቱ 1600 ኪሎ ሜትር ስፋቱ ደግሞ እስከ 60 ኪሎ ሜትር የሚደርሰውን ሰፊና ለም የሀገራችንን መሬት ቆርሶ ለሱዳን ማስረከቡስ ምናልባት ከሀገር ፍቅርና ወዳድነት ለወገን ክብርና ሞገስ ከማሰብ ይሆን ይሆን?

ከወያኔ ሕወሃት በፊት የነበረው አንባገነን ገዥ ደርግ በድንበር ይገባኛል ምክንያት በ1969 ዓ/ም ሀገራችንን በግፍ ወርራ ከነበረችው ሶማሊያ ጋር ጦርነት ገጥመን በነበረበት ወቅት ከጠላት ጋር በማበር ሀገራችንንና ሕዝባችንን ከሌላ አቅጣጫ ይወጉትና ያሰቃዩት የነበሩት እነዚሁ ያዛሬዎቹ ጉዶች ወያኔ ሕወሃቶች ለመሆናቸው የታሪክ መዛግብቶች ያስረዳሉ። ሌሎች የሀገራችን ሰላማዊም ሆኑ በሌላ አማራጭ ወያኔን ለመታገል የወሰኑት የዛሬዎቹ ድርጅቶች ግን በእንዲህ አይነት ቅሌት በማስረጃ በተደገፈ መልኩ አንዳቸውም ሲታሙ አልሰማንም። ሕዝባችንን ያለማቋረጥ እየወጋ ካለው ወያኔ ሕወሃት ጋር ከሚያደርጉት ትግል በስተቀር።

ጥቁር ሕዝብ ነጭን ሊያሸንፍ አይችልም የሚለውን የተሸናፊነት መንፈስ ጣሊያንን በተደጋጋሚ በመንበርከክ ለዓለም አዲስ ምእራፍ የከፈተችና የጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነችን ሀገራችንን ልጆቿ ነን የሚሉት ወያኔዎች ግን አፋቸውን ሞልተው “ኢትዮጵያ በታሪኳ አንድም ጦርነት አሸንፋ አታውቅም” በማለት ዓለም የሚያውቀውን ድንቅ ታሪካችንን ሲያራክሱና የሀገራቸንን ማንነትና የሕዝባችንን ጥንካሬ ብዙ ጊዜ ለማንኳሰስ ሲሞክሩ ታይተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በዓመተ ዓለም በሽህ የሚቆጠሩ ዘመናትን በሀገርነት ያሳለፈችውንና በዓመተ ምህረትም ላለፉት ሁለት ሽህ ዓመታት በሀገርነት የምትታወቀዋን ክቡር እድሜ ጠገብ ሀገራችንን ጎማምደው የመቶ ዓመት ያገር ጎረምሳ በማድረግም ወያኔ ሕወሃትን የመሰለ እኩይ ጎጠኛ ቡድን የትም አልታየም። ዛሬ የምናውቃቸው የሀገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ግን በእንዲህ ያለው ጉዳይ ሲታሙ ተሰምቶ አይታወቅም።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባዎ

• በሚኒስትር ማዕረግ ሦስት ምክትል ከንቲባዎች ይሾማሉ እየተባለ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀጣይነት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ በሚሾም አንድ ከንቲባና በሚኒስትር ማዕረግ በሚሾሙ ሦስት ምክትል ከንቲባዎች እንደሚመራ ምንጮች ጠቆሙ፡፡

ምንጮች እንደሚሉት፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ለከተማው ከንቲባ ሆነው የሚሾሙት አቶ ድሪባ ኩማ ናቸው፡፡ አቶ ድሪባ በአሁኑ ወቅት የትራንስፖርት ሚኒስትር ሲሆኑ፣ መሰንበቻውን ከወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ጋር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየታዩ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የከተማው ቀጣዮቹ ምክትል ከንቲባዎች የሚሆኑት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩርያ ኃይሌ፣ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበውና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ናቸው ሲሉም ምንጮች ይገልጻሉ፡፡

ነገር ግን ወ/ሮ አዜብ በየትኛውም ቦታ መሾም እንደማይፈልጉ እየገለጹ መሆናቸውን ምንጮች ያስረዳሉ፡፡ ሪፖርተር በዚህ የመዋቅር ለውጥና ሹመት ጉዳይ ማረጋገጫ ለማግኘት ለአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ቢያቀርብም፣ እየተካሄደ ያለውን ሥራ በዝርዝር መግለጽ ባለመፈለጉ አልተሳካም፡፡

ምንጮች እንደሚያብራሩት፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ ቢሮዎችን በኃላፊነት የሚመሩት ዕጩ ተሿሚዎች በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ እንደሚሾሙ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር የሚፈቅደው አንድ ምክትል ከንቲባ በመሆኑ፣ ከአንዱ ዕጩ ተሿሚ በስተቀር ሁለቱ ተሿሚዎች በምክትል ከንቲባ ማዕረግ እንደሚሾሙ አመልክተዋል፡፡

ምንጮች እንደሚገልጹት፣ ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ይህንን ያደረገበት ምክንያት አዲስ አበባ ላይ የተጀመሩና በቀጣይ የሚጀመሩ የልማት ሥራዎች ሰፊ በመሆናቸው፣ ይህንን የሚሸከም የአስተዳደር የሥልጣን እርከን ማደራጀት ያስፈልጋል በሚል ነው፡፡

የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጀማል ረዲ መዋቅሩንና አሿሿሙን ባይገልጹም፣ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አዲስ አበባን የሚያስተዳድረው የሰው ኃይል በከፍተኛ ደረጃ እየተዘጋጀ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ በማደግ ላይ ያለች ከተማ ብትሆንም፣ በከተማዋ ውስጥ አፋጣኝ ምላሽ የሚፈልጉ ጥያቄዎች በርካታ ናቸው፡፡ ኅብረተሰቡ አምርሮ ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች መካከል የመኖርያ ቤት እጥረት፣ የኑሮ ውድነት፣ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግር፣ የትራንስፖርት እጥረትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

የከንቲባ ኩማ ደመቅሳ አስተዳደር እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ተግባራትን ቢያከናውንም አዲስ አበባውያን ሊረኩ አልቻሉም፡፡ ኢሕአዴግ የኅብረተሰቡን ችግሮች ለመቅረፍ መወሰኑን በሚያመለክት ደረጃ ለአዲስ አበባ ከተማ ትኩረት እየሰጠ እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት ይናገራል፡፡

ኢሕአዴግ ከፍተኛ አመራሮቹን ከፌደራል ወደ አዲስ አበባ በሚያዝያ ወር በተካሄደው ምርጫ አማካይነት ቢያዛውርም፣ በእነዚህ ሹማምንት ምክንያት የተፈጠረውን የፌዴራል መንግሥት የአመራር ክፍተት የመሙላት ሌላ የቤት ሥራ ይጠብቀዋል፡፡

ምንጭ፡ Freedom4Ethiopia

ማነዉ ፈሪዉ ተቀዋሚ ወይስ ህወሃት/ ኢህአደግ..

ሰሞኑን በ20/06/2013 በአሜሪካ ኮንግረስ በኮንግረስ ማን የተከበሩ ሚስተር ስሚዝ ኢትዮጵያ ከመለሰ በኋላ ፦የወደፊት ዲሞ ክራሲና የሰበአዊ መ ብት በሚ ል ርዕስ በተደረገዉ  የም ስክርነት ቃል ላይ የተከበሩ አም ባሳደር ያማ ማ ቶ በተቃዋሚ ዎች ዙሪያ ሲናገሩ በራሳቸዉ  ስለማይተማ መኑና ስለሚፈሩ ነዉ ብለዉ መናገራቸዉን አድምጠናል።

በዚህ ጉዳይ ብዙ ማለት ይቻላል ፤ ይሁንና ለዛሬ በቅርብ የሆኑትንና በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ላተኩር።

እዉነት አምባሳደር ያማማቶ እንዳሉት ፍርሃት ያለዉ በተቀዋሚ ጎራ ነዉ ፤ በህወሃት አካባቢ ነዉ ፤ ወይስ አሜሪካ የኢትዮጵያ ጉዳይ እያስፈራት መጣ?ጉዳዩን ለፖለቲካ ጠበብቶች እተወዋለሁ ።

እድሜ ለሰማያዊ ፓርቲ አምባሳደር ያማማቶ ከመናገራቸዉ በፊት ቀደማቸዉ እንጂ ሁሉንም ፈርታችሁ ነዉ ይሉ ነበር። አንድ ነገር አምባሳደር ያማማቶን ልጠይቃቸዉ ለመሆኑ ፍርሃት ዝም ብሎ ይመጣል? ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ  ህዝቡ ግንባር ግንባሩን እየተባለ ሲገደል ባያዩ እንኳን አልሰሙም ?ታዲያ አሁንስ ህወሃት ጥቅሞቹ እንዳይነኩበት ለ39 ዓመታት ያከማቸዉን የጭካኔ ልምድ የሰማና ያየ ለምን አይፈራ ?