Thursday, February 26, 2015

ምርጫ ለኢትዮጵያ ወታደርና ፓሊስ: – ለህወሓት ባርነት ወይስ ለኢትዮጵያ ነፃነት

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውትድርና ከፍተኛ ክብር አለው። ውትድርና ከሙያና ሥራ በላይ የነፃነትና የክብር መገለጫ፤ ሀገርን ከባዕድ ወረራ መከላከያ ጋሻ ነው ብሎ ያምናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ህግና ሥርዓት አክባሪ በመሆኑ ለፓሊስም ከፍተኛ አክብሮት አለው። የፓሊስ ሥራ ወንጀልን መከላከልና ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ ማቅረብ መሆኑ በኢትዮጵያ ባህል የተከበረ ቦታና እውቅና አለው።

በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ግን ይህ እየተቀየረ ነው። የህወሓት አዛዦች እየመሩት ያለው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ሀገርን ከባዕድ ጠላት ከመከላከል ጋር ምንም ዝምድና በሌላቸው ሁለት አበይት ተግባራት ላይ ተጠምዷል። በህወሓት አዛዦች የሚመራው ሠራዊት ዋነኛ ተግባር ለሰብዓዊ መብቶቻቸው መከበር እና ለፍትህ መስፈን የሚታገሉ ዜጎችን ማጥቃት ሆኗል። የጦሩ ሁለተኛው አቢይ ተግባር ደግሞ ለአዛዦች የግል ጥቅም ማካበቻ ገቢዎችን በሚያስገኙ ሥራ ላይ መሠማራት ነው።

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያዊያንን ማጥቂያ ሠራዊት መሆኑ ሲቪሉን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የሠራዊቱንም አባላትን ጭምር ለህሊና ወቀሳ የዳረገ ጉዳይ ነው። ሆኖም ግን ይህ በህሊና ወቀሳ ብቻ ሊታለፍ የማይችል ወንጀል ነው። ሠራዊቱ በህወሓት እየታዘዘ የሚዘምተው በገዛ ራሱ ልጆች፣ እህቶች፣ ወንድሞችና ወላጆች፤ በገዛ ራሱ ጥቅሞች እና በገዛ ራሱ ላይ መሆኑ መገንዘብ ይኖርበታል። በገዛ ራሱ ጥቅሞች ላይ የሚዘምት አንድም ህሊና የሌለው አሊያም ነፃነት የተነፈገው ሰው ብቻ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ሠራዊቱ እየተራበና እየታረዘ አለቆቹ የታላላቅ ህንፃዎች ባለቤቶች፣ ባለፋብሪካዎች፣ የባንክና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ባለአክሲኖች የሚሆኑበት ሥርዓት ከዳር ሆኖ የሚመለከት መሆኑ የሚገርም ነው። ሠራዊቱ ቤተሰቦቹን መመገብ አቅቶት እያለ የአዛዦቹ ልጆች ለሽርሽር ዓለምን ይዞራሉ። እንዴት ነው ሠራዊቱ እየደኸየና እየሞተ አዛዦቹ እየከበሩ የሚሄዱት? ይህ አዋራጅ ሁኔታ እንዲያበቃ መታገል የሠራዊቱ ግንባር ቀደም ኃላፊነት ነው። ሠራዊቱ ወይ ባርነትን አሜን ብሎ መቀበል አለበት አለበዚያም እሱም እንደነሱ ሰው መሆኑን ማሳየት መቻል አለበት። በኢትዮጵያ ውስጥ የህወሓት አገዛዝ ወድቆ የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት መመሥረቱ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚጠቅማቸው የኅብረተብ ክፍሎች ግንባር ቀደሙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው። በዚህም ምክንያት የሠራዊቱ አባላት ለሥርዓቱ መውደቅ በግልጽም በስውርም መታገል የዜግነት ብቻ ሳይሆን አዕምሮ ያለው ሰው ሆነው በመፈጠራቸው የተቀበሉት ግዴታ ነው።

ፓሊስን በተመለከተም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። ህወሓት የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍኖ ለመግዛት የቻለው በዋኛነት የፓሊስን ኃይል ለአፈናው ተግባር የሚጠቀም በመሆኑ ነው። የተቃውሞ ድምጾች በተሰሙ ቁጥር የኢትዮጵያ ፓሊስ በወገኖቹ ላይ የሚያወርደው ዱላ የሚዘገንን ሆኗል። ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት መግደልና ማቁሰል፤ አረጋዊያንን፣ ሴቶችንና ሕፃናትን መግደል፣ ማቁሰል፣ መደብደብ በዚህ ተግባር የተሠማሩ ፓሊሶችን በቡድንም በግልም በህግ የሚያስጠይቅ ከባድ ወንጀል ነው። በህወሃት እየተመራ ያለው የኢትዮጵያ ፓሊስ ተግባራት ተበዳዮችን ብቻ ሳይሆን ራሱ ፓሊስንም ጭምር አንገት የሚያስደፋ ተግባር ነው። ለመሆኑ አንድ ተራ የኢትዮጵያ ፓሊስ ባልደረባ ከህወሓት አገዛዝ ምን ተጠቀመ? መልሱ “ምንም” የሚል ነው። ይልቁንስ በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ፓሊስ የተናቀና የተዋረደ ሥራ ሆነ። በህወሓት አገዛዝ ፓሊስ እንደሰለጠነ አዳኝ ውሻ “ያዝ” ሲሉት የሚነክስ፣ የሚያደማ፣ የሚቦጭቅ ሆኗል። ይህ ለፓሊስ፣ ወንጀልም ውርደትም ነው። በህወሓት አገዛዝ መገርሰስ እና በምትኩ የህግ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓት መስፈን ፓሊስ ከሁሉ በላይ ተጠቃሚ ነው፤ ሰብዓዊ ክብሩን ያረጋግጥለታልና።

Wednesday, February 25, 2015

ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር!!

በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት ዳኝነትን እንስማ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር ስንት ጋዜጠኛ፣ ስንት የሃይማኖትና ስንት የፖሊቲካ መሪዎች ከየወህኒ ቤቱ ይወጡ ነበር! ሁላችንም እንደልባችን ሳንፈራ፣ ሳንፈራራ በሙሉ ነጻነት ችግሮቻችንን የወያኔን ጭቆና ጨምሮ ለመወያየትና መፍትሔዎችን ለመለዋወጥ የምንችልበት መድረክ፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ራድዮና ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ውስጥ ይኖረን ነበር፤ ስንት ሰው ሥራ ያገኝ ነበር፡፡

ከሁሉም በላይ በየመንገዱ ጠመንጃ የያዘ ሊያስፈራራን የሚሞክር ሆድአደር እያየን፣ እንደዚሁም በየጫካው ያሉትን እያሰብን ሰላማችንን ከምናጣ አበባውን ትተን፣ ሩዙን ትተን፣ የተወደደልንን ጤፋችንን እያመረትን አዲስ ኑሮ ብንጀምር የተሻለ ነበር፡፡

ግን አንድ እንቅፋት አለብን፤ እነዚህ ከየኪዮስኩ እውቀት ገዝተን አዋቂዎች ሆነናል የሚሉት እንትኖች እንመጀመሪያ ችግሩ እንዲገባቸው፣ ሁለተኛ መፍትሔው እንዲገባቸው፣ ሦስተኛ ጉልበትና እውቀት አንድ አለመሆናቸውን ብቻ ሳይሆን በጉልበት እውቀት የማይገኝ መሆኑን ማሳመን በረዶ እየወረደ የስሜን ተራራን መውጣት ነው፤ በረዶ ሳይኖር ወጥቼዋለሁ!

እነዚህን የጉልበት አዋቂዎች — ስለሽማጌሌዎችና አሮጊቶች ሳያስቡ፣ ስለመብራት ኃይል ሳያስቡ፣ ስለውሀ ሳያስቡ ሁሉም በጉልበት ፎቅ ይውጣ የሚሉ! ይባስ ብለው ለእስረኛውም ፎቅ እየሠሩለት ውጣ! ሊሉት ነው!

እነዚህ የጉልበት አዋቂዎች የአበሻ ኑሮ፣ ቡናው፣ ሙቀጫው፣ ምጣዱ፣ በርበሬው፣ ቁሌቱ፣ ቄጤማው፣ ዶሮና በግ ማረዱ፣ ኧረ ስንቱ! ሳይገባቸው ቻይና በነገራቸው የሚያውቁትን የሚረሱ ማን ያስተምራቸው! እናውቃለን ስለሚሉ እንዴትስ ይማራለ? በእውነት ለመማር ቢፈልጉስ ስንት ዓመት ሊያስፈልጋቸው ነው! እግዚአብሔር እንሱንም እኛንም በምሕረቱ ይጎብኘን! የሚያስተምር ጎረቤት አያሳጣን!

ሕወሃትና ሕግ ጠበኞች ናቸው – ግርማ ካሳ

የሚከተሉት በቀጥታ ከኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የተወሰዱ ናቸው።

አንቀጽ 20፣ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2

«ማንኛውም ሰው ያለምንም ጣልቃ ገብነት የመሰለዉን አመለካከት ለመያዝ ይችላል።

ማንኛውም ሰው ያለምንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው። ይህ ነጻነት በሀገር ዉስጥም ሆነ ከሀገር ዉጭ  ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሁፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማናኝዉም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛዉንም ዓይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል»

አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ ሐ

«ማንኛዉም ኢትዮጵያዉ ዜጋ፣ በቀለም፣ በዘር፣ በብሄር. በብሄረሰብ፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሰረተ ልዩነት ሳይደረግበት በማናቸዉም የመንግስት ደረጃ በየጊዜው በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥና የመመረጥ»

በርካታ የህወሃት ባለስልጣናትና ካድሬዎች ስለ ሕግ እየደጋገሙ ያወራሉ። ስለ ሕግ፣ ስለ ሕግ መንግስቱ የሚደረገዉን ዉይይት አንፈራም። በአንቀጽ 20 መሰረት፣ «ስለሚያገባን እንጦምራለን»  በድብቅ ሳይሆን በሶሻል ሜዲያው፣ ድብቅ ስም ይዘው ሳይሆን እናት አባቶቻቸው የሰጧቸውን ስም ይዘው፣ ፎቶዋቸውን ለጥፈው በይፋ አስተያየቶችን የሰጡ፣ የጦመሩ፣ ዞን ዘጠኞች ለምን ታሰሩ ? ብእር አንስተው በይፋ የጻፉ እነ ርዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ ዉብሸት ታዬ፣ ተመስገን ደሳለኝ የመሳሰሉት ለምን ታሰሩ ? አንቀጽ 20 «ማናቸውንም» የሚል ቃላት አካቶ የለም ወይ ? እስቲ ይመለስልን !!!

አንቀጽ 38 ማንኛውም ዜጋ የመምረጥና የመመረጥ መብት አለው። ታዲያ ከ200 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካዮች ተመራጭ እጩ እንዳይሆኑ ለምን ተሰረዙ ? ኦሮምኛ አትናገሩም ፣ የዚያ ደርጅት አባል ነበራችሁ ፣ እጣ አልወጣላችሁም .፣ ወዘተረፈ እየተባለ ዜጎች እንዳይመረጡ መሰረዝ ሕግ መንግስቱን በአፍጢሙ መድፋት አይደለም ወይ ?

ታዲያ ህወሃት፣  ራሱ የማያከብረዉን ሕግ፣  ሌሎች እንዲያከብሩለት ለምን ይጠበቃል ? ሕግ መንግስቱን በአፍጢሙ ደፍቶት ስለ ሕግ መንግስቱ የማዉራት ምን ሞራል ኦቶሪቲ አለው ?

አገር ዉስጥ ላሉ ድርጅቶች አንዳንድ ሐሳቦች – ናኦሚን በጋሻ

ህወሃት ሕግን የማያከበር አራዊተ ስርዓት ነው።ሕግን ከማያከበር ቡድን ጋር ሕጋዊ ትግል የራሱ ጠቃሚ አስተዋጾ ቢኖረዉም ዘልቆ አይሄድም። ታዲያ አገር ቤት ያሉ ሰላማዊና ሕጋዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ምንድን ነው ማድረግ ያለባቸው ? አንዳንድ ሐሳቦችን ላስቀምጥ፡

Monday, February 23, 2015

መልእክት ለወጣቶች፤ (በወጣቶች ጉዳይ መምርያ)

ወጣት ለአገር እድገትና ብልጽግና የሚያበረክተው አስትዋጾ ከፍተኛና በቀላሉ ለውጥ ማምጣት የሚችል ኃይል ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሆኑ ይታወቃል። ይህን በቀላሉ ለውጥ ማምጣት የሚችል ትውልድ ጊዜው በሚጠይቀውና ለአገራችን በሚበጅ መልኩ ማደራጀት፣ መምራትና ንቅናቄው ለሚያደርገው የነጻነት፣ የፍትህና ዲሞክራሲ ትግል ግንባር ቀደም ሁኖ እንዲሰለፍ ማስቻል የንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ተግባር ነው። ስለሆነም ንቅናቄያችን ወጣቱ ትውልድ ለአገር እድገትና ዲሞክራሲያዊ ግንባታ የያበረክተው አስትዋጾ ከፍተኛና አስፈላጊ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የወጣቶች ጉዳይ መምሪያን አቋቁሞ ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል ትግሉን እንዲቀላቀል በማድረግ ላይ ይገኛል።

መምርያው የተቋቋመበት ዋና ዓላማ ወጣቱ ትውልድ የወያኔን ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ፣ ኢ_ዲሞክራሲ፣ ኢ_ሰባዊ ድርጊት እና የሚያራምደውን የዘር ፖለቲካ በአጠቃላይ የወያኔን አምባገነናዊ ስርዓት በሚገባ እንዲገነዘብ በማድረግ እንዲሁም የንቅናቄያችንን ዓላማና ግብ በማስረዳት ለነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ለሚደረገው የሁለገብ ትግል ወጣቱ ትውልድ ድርሻውን እንዲወጣ ማድረግ እና ኢትዮጵያ አገራችንን ጠብቆና አስከብሮ ለትውልድ የማስተላለፉን ኃላፊነት እንዲረከብ ማስቻል ነው።

እንደሚታወቀው የአንድ አገር ቀጣይነት ያለው እድገት የሚለካው በአላት መሠረተ ልማት፣ ቁሳዊ ሃብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን በዋናነት ይህን ተረክቦ በአደራ ለትውልድ ማስተላለፍ የሚችል ትውልዳዊ ትስስር ሲኖር ነው። ይህንንም የአገርና የህዝብ አደራ ድልድይ ሆኖ ከትውልድ ወደ ቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፍ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ስለሆነ ኢትዮጵያን ከወያኔ የጨለማ ቡድን መታደግ ለነገ የማይባይል አገራዊ ግዴታ መሆኑን ተገንዝቦ ወጣቱ ትውልድ ኃይሉንና አቅሙን ተጠቅሞ የእራሱን ነጻነት በእራሱ ማወጅ እንደሚችል መምርያው ያሳስባል።

በማንኛውም አገር፣ ጊዜና ዘመን እያንዳንዱ ትውልድ የአገሩ ወራሽ፣ ተተኪና ተረካቢ፣ ጠባቂና ለሚቀጥለውም ትውልድ የማውረስ፣ የማስተላልፍና የማስረከብ ኃላፊነትና ግደታ አለበት። ስለሆነም አገርን ከእነ ሙሉ ክብራ ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፍ የእኛ የወጣቶች የዜግነት ግዴታ መሆኑን ተረድተን ጥልቅ በሆነ አገራዊ ስሜት በሦስቱም ዘርፍ ማለትም በማህበራዊ፣ በምጣኔ ሃብታዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አገራዊ ተጽዕኖ ማድረግ እንደሚቻል በእርግጠኝነት የወጣቶች ጉዳይ መምርያ በድጋሚ በአጽንኦት ያሳስባል።

ውድ የአገራችን ወጣቶች ሆይ፤

የምንወዳትና የምንሳሳላት ብርቅዬ የጀግኖች አገር ኢትዮጵያ በባንዳዎች ወያኔ ለ24 ዓመታት የጥፋት ዘመቻ እየተካሄደና እየተፈጸመባት ሉዓላዊነቷ ተንቆ ትገኛለች። አምባገነኑ የወያኔ ቡድን በጠበንጃ ኃይል ስልጣን ከያዘበት ጀምሮ ሰብአዊ መብታችን ተጥሶ፣ ዲሞክራሲያዊ መብት ተነፍጎን፣ ተፈጥሮአዊ መብታችን ተነጥቆ፣ የዜግነት ማንነታችን ባንዲራችን ሳይቀር ተቀይሮ፣ ብሔራዊ ሃብትና ንብረት እየተዘረፈ፣ የአገራችን አርሶ አደር ለም መሬቱ እየተሸጠ፣ እተነጠቀና እየተባረረ፣ ለአገር የሚታገለው ንጹህ ዜጋ ፀረ ሰላም ፀረ ህግ ፀረ መንግሥት በመባል የሽብርተኛ ሕግ ወጥቶለት እየታሰረ፣እየተገደለና እየሞተ፣ እየተፈናቀለና እየተሰደደ፣ በግፍና በጭቆና ላይ መሆኑን ለአንተ ንቁ ህልሊና ላለህ ወጣት ትውልድ የተሰወረ አይደለምና በጽኑ በአስቸኳይ ታገለው። ነጻነትን አውጅ፤ ፍትህን ተቀዳጅ!ታሪክህን መልስ! ወያኔን ይብቃህ ከህዝብ ላይ ውረድ በለው።

ውድ የአገራችን ወጣቶች ሆይ፤

አገራችን ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዘመናት በነፃነት በቀደሙ አባቶቻችን ተጠብቃ የቆየችው በአካልና በደም ዋጋ ነው። በዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ ቆራጥነትና ፅናት አገርን በነፃነት መጠበቅ በዓለም ፊት ትልቅ ምሳሌነትን ያተረፈ፣ ዛሬ ለአለነውና ለመጭውም ትውልድ የሚኰራበት ሕያው የታሪክ አለኝታ፣ መመኪና ክብር ያለን ውድ ህዝቦች ነን። ይህ አኩሪ ታሪክ ፣ የዘላለም ሃብታችን በመሆኑ ጠብቀንና አስከብረን ለትውልድ ለማስረከብ ኃላፊነቱ በዋናነት የእኛ ወጣቱ ነው። ይህን እውነታ ተቀብሎ አገርን በነፃነት ለመጠበቅ ደፋ ቀና ከሚሉ ኢትዮጵያውያን ጋር አገራዊ ኃላፊነትንና ግዴታን ለመወጣት ዝግጁና ብቁ ሆኖ መታገል በእጅጉ ያስፈልጋል። ስለዚህ የአገራችን ወጣት ሁላችሁ ሰላም፣ ነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባትና አገራዊ ድርሻንም ለመወጣት በህብረት ተነስ!፣ ታጠቅ!፣ ሰው ሁን! ታሪክህን መልስ!አረመኔው ወያኔን በቃህ በለው!

ከህወሃት ምርጫ የሚገኘው ትርፍ ውርደት ብቻ ነው

ህወሃት ኢሕአዴግ የተባለውን ጭንብል አጥልቆ አገሪቷን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር ካስገባ ግዜ ጀምሮ በኢትዮጵያዊያን ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ፈርጀ ብዙ ናቸው። እነዚህ ፈርጀ ብዙ ወንጀሎች በልዩ ልዩ ተቋማት እና ግለሰቦች በማስረጃ ተደግፈው ተመዝግበው ተቀምጠዋል። ከሰሞኑ እንኳ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ በተደረገው አንድ ጉባኤ ላይ ግራሃም ፔብል የተባሉ ታዋቂ ሰው ህወሃቶች የፈፀሟቸውን ወንጀሎች በማስረጃ አስደግፈው ከዘረዘሩ በኋላ ህወሃት “አሸባሪ መንግስት” ነው ብለዋል። ይሄ እውነት ነው። ኢትዮጵያ ከአምባገነን ገዥዎች ተላቃ የምታውቅ አገር አለመሆኗ የታወቀ ቢሆንም እንደ ህወሃት ያለ የህዝብ ጠላት መሆንን መርጦ የገዛ ህዝቡን የሚያሸብር መንግስት ነኝ የሚል አካል ግን አልታየም።

ህወሃት አሸባሪ ነው። ይሄ አሸባሪ ቡድን በሚያካሂደው ምርጫ ውስጥ የተሳተፈ ሁሉ እድል ፈንታው ውርደት፤ እስራት፤ ስደት እና ግዲያ መሆኑን እሰክ ዛሬ በተካሄዱት ምርጫዎች አይተናል። ህወሃት ኢሕአዴግ የተባለውን ጭንብል አጥልቆ በምርጫ ሰበብ የብዙ ንፁህን ዜጎችን ደም አፍስሷል። በምርጫ ሰበብ ያፈረሰው ቤት፤ የበተነው ቤተሰብ ብዙ ነው። አገራችን በፖለቲካ እስረኞች ብዛት አቻ ያልተገኘላት ሁናለች። በስደተኛ ብዛትም የመሪነቱን ደረጃ ይዛለች። ይህን ሁሉ ግፍ ያዩ የውጭ ታዛቢዎች ኢትዮጵያን ከውዳቂ አገራት መካከል መድበዋታል።

ህወሃቶች በታሪክ አጋጣሚ ከተቆናጠጡበት ወንበር ከሚወርዱ ሞታቸውን እንደሚመርጡ ደጋግመው በአደባባይ ተናግረዋል። ለዚህም እነርሱ ምክንያት የሚሉት ይህን ወንበር ያገኘነው በደማችን ነው። በደም ያገኘነውንም ወንበር እንዲሁ የምናስረክብ አይደለንም ይላሉ። ወንበሩን አንለቅም ብለው ቢያቆሙ መልካም ነበር፤ ወንበሩን የምንለቅ ከሆነ አገሪቷን እንበትናታለን የሚለውን ነውር ሃሰብ ማቀንቀናቸው ደግሞ ህወሃቶቹ አንዳች ዓይነት የአዕምሮ ቀውስ ውስጥ መግባታቸውን ያመለክታል። የእነዚህን ቡድኖች ነውረኛነት በ1997 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ ደህና አድርገን ታዝበናል። በሌብነት እና በሌላ ነውር ምክንያት ከድርጅቱ የተባረሩት ሳይቀሩ ተሰባስበው ህወሃትን ለማዳን የሚል የጥፋት ዘመቻ በአገሪቷ ላይ መክፈታቸው የሚረሳ አይደለም። ህወሃት ወንበሩን የሚለቅ ከሆነ ተመልሰን ወደ ጫካ እንገባለን ማለታቸው የአደባባይ ሚስጢር መሆኑም የሚረሳ አይደለም።

እስከ አሁን በተደረገው ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ ያተረፈው ነገር ቢኖር ውርደት እንጂ ክብር አይደለም። ህወሃቶች ምርጫ እያሉ ህዝቡን እያዋረዱ፤ የአገሪቷንም ሃብት እየበዘበዙ፤ እነርሱ ከህግ በላይ ሌላው ከእነርሱ ጫማ ስር ሁኖ የሚኖርበትን ሥርዓት እየሰሩ ኑረዋል። ይህ እነርሱ ለእነርሱ የሠሩት ሥርዓት እንዲሁ እንዲለወጥ ይፈልጋሉ ብሎ ከማሰብ የምናተርፈው ነገር ቢኖር ውርደት ብቻ ነው። ህወሃቶች የተፈጠሩበትም ምክንያት አገሪቷንና ህዝቧን ለማዋረድ ነው ለማለት የሚያስችሉን ከበቂ በላይ ምክንያቶች አሉ።

ህወሃቶች እንደ ጤነኛ ሰው ለማሰብ የሚያስችላቸው ስብዕና የሌላቸው መሆኑ ይታወቃል። እኛ ከስልጣን የምንወርድ ከሆነ አገሪቷን እንበትናታለን በሚል ቅዥት ውስጥ የመገኘታቸው ምስጢርም የስብዕናቸውን የዝቅጠት ደረጃ የሚያመላክት ነው።በሰላማዊ መንገድ ተወዳድረው እና ተመርጠው ስልጣን ለመያዝ በጎ ራዕይ ያላቸውን ሁሉ በጠላትነት ፈርጀው እና የአሸባሪነት ካባ ደርበውላቸው በጎ ራዕያቸውን እያመከኑ እንደሆነ እያየን ነው። አሁን በአንድነት እና በመኢህአድ ላይ የተወሰደው እርምጃ የዜጎችን በጎ ራዕይ የማምከን ተግባር መገለጫ ሁኖ ሊጠቀስ ይችላል። ህወሃቶች ራዕይ አልባ ናቸው።ለኢትዮጵያ በጎ ራዕይ ቢኖራቸው ኑሮ “እኛ ከሌለን አገሪቷን እንበትናታለን” አይሉም ነበር። ራዕይ ያለው ከእኔ የተሻለ ካለ ይሥራ ይላል እንጂ እኔ ካልሆንኩ ሞቼ እገኛለሁ አይልም። ህወሃቶች ቅዥታቸውን ራዕይ ብለው ይጠራሉ። በቅዥት ዓለም ውስጥም እንደሚኖሩ የሚነገራቸው ከተገኘም ዘራፍ ብለው አሸባሪ ይላሉ እንጂ ለማድመጥ ችሎታ እና ትዕግስት የላቸውም።

አዋራጅ ሰልፎችና ድግሶች እንዲያበቁ ህወሓት ይወገድ!

ድግሶችን፣ ወታደራዊ ሰልፎችንና ሀውልቶችን ማብዛት የአባገነኖች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው። ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝም በሕዝብ እየተጠላ፣ እያረጀና እየወላለቀ በሄደ መጠን በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ደግሶ መብላት፤ ወታደራዊ ሰልፍና የመሣሪያ ጋጋታ ማሳየት እና በየመንደሩ ሀውልት መመረቅ ሙያው አድርጎት ቆይቷል።

የህወሓት ድግሶችና ፌሽታዎች የአገራችን ሀብት ከማሟጠጣቸውም በላይ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ የአርሶ አደሮችንና የአነስተኛ ነጋዴዎችን ኪስ እያራቆቱ ናቸው። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች በእስር ቤቶች እየማቀቁ በሚገኙበት ሁኔታ፤ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ የአማራ አርሶአደሮች ተፈናቅለው እያለ፤ በጋምቤላና በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋዎች እየተደረጉ፤ በአፋር፣ በሲዳማ፣ በቦረና፣ በወልቃይት እና በመላው ኢትዮጵያ ግጭቶች በበዙበት፤ ሕዝብ እያለቀሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት “የብሔር፣ ብሔረሰቦች መብት ተከበረ” እያሉ እነዚህኑ በደል እየደረሰባቸው ያሉ ዜጎችን ማስጨፈር እና ለእነዚህ ጭፈራዎች በርካታ ሚሊዮኖች ብር ማውጣት በእጅጉ ያስቆጫል። እነዚህ ጭፈራዎች ለህወሓት ሰዎች የገቢ ምንጮች መሆናቸው ጥርጥር የለውም፤ ለድሀው ኢትዮጵያዊ ግን መራቆቻዎች ናቸው። ከዚህም አልፎ በዘረኝነት እየተበደለ ያለ ሕዝብ ስለእኩልነት ዝፈን ማለት ክብረ ነክ ተግባር ነው። ዘንድሮ በአሶሳ የተደረገው አገር አቀፍ ድግስ ካለቀ ጥቂት ወራት በኋላ አገራችን በሌላ ዙር የህወሓቶች ድግስ ተወጥራለች።

ሰሞኑን በባህር ዳር በተደረገው የጦር ሠራዊት ሰልፍ እና ሰልፉን ተከትሎ በነበረው የድግሶች ግርግር ከሁሉም በላይ የተሰደበውና የተዋረደው የሠራዊቱ አባል ነው። አዛዦቹ መቶ በመቶ የህወሓት አባላት የሆኑበትን ሠራዊት “የኢትዮጵያ መከላከያ” ተብሎ መጠራቱ ራሱ የሚያሳፍረው ኢትዮጵያዊ ወኔ በልባቸው ውስጥ እየተንቀለቀለና እልህ እየተናነቃቸው ያሉ የሠራዊቱን አባላት ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንዴት የኢትዮጵያ ጠላቶች በሆኑ የህወሓት ካድሬዎች ይመራል? እንዴት የአስር አለቃ እንኳን ሊሆን የማይገባው የህወሓት ካድሬ “ጄኔራል” ተብሎ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮችን እንደ ሎሌው ያዛል? እንዴት አንድ የህወሓት ሎሌ ሹመት ተሰጥቶት እየፏለለ በልምድ፣ በትምህርትና በእውቀት የሚበልጠውን ኢትዮጵያዊ ተንቆ ይዋረዳል? ይህ ቁጭትና እልህ ሠራዊቱ የዘረኛውን ህወሓት ሰልፍ አድማቂ መሆኑ የሚያከትምበት ጊዜ ይበልጥ እንዲናፍቅ የሚደረገው ነው። አልያማ ሰልፍ ያሳመረ ሠራዊት ሁሉ አሸናፊ እንዳልሆነ የታወቀ ነው። በሰልፍ ብዛትና በመሣሪያ ትዕይንት ማሸነፍ ቢቻል ኖሮ የትም አገር አምባገነኖች ባልወደቁም፤ ህወሓት ራሱን ስልጣን ላይ ባልወጣም ነበር።

የህወሓት ምሥረታ 40ኛ ዓመት ድግስም ሌላው የታሪክና የሀብት ውድመት የሚያስከትል ክስተት ነው። የካቲት 11 ቀን 1967፣ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን እናታቸውን ኢትዮጵያን ለመግደል ያሴሩበት እና ልጆች በእናታቸው ላይ ቢላዋ የሳሉበት ዕለት በመሆኑ በሀዘንና በሱባኤ እንጂ በድግስና በጭፈራ የሚታሰብ ዕለት አይደለም። ሲነሳ ምንም ይሁን ምን ዛሬ በደረስንበት ሁኔታ ሲገመገም፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ህወሓትን የመሰለ መሠሪና አድርባይ ድርጅት ገጥሟት አያውቅም። እነሆ ዘንድሮም ይኸው አድርባይ ድርጅት የመሪዎቹን የሀብትና ዝና ረሀብ ለማስታገስ ሲል ያልነበረ ታሪክ እየፈጠረ በድግስ ስም ከድሀው ገንዘብ እየሰበሰበ

ድል የአላማ ጽናት እንጂ የመሳሪያ ጋጋታ ዉጤት አይደለም

ጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ዉስጥ ዋና ከተማዋን ከተለያዩ የጣሊያን ከተሞችና ጣሊያንን ከፓሪስ፤ከሙኒክ፤ከጄኔቫና ከቪዬና ጋር የሚያገናዉና በአመት ከ 150 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን የሚያስተናግድ አንድ ትልቅ የባቡር መስመር አለ። ይህ የባቡር መስመር የሚጠራዉ ሮማ ተርሚኒ እየተባለ ሲሆን የባቡር መስመሩ አድራሻ ደግሞ የአምስት መቶዎቹ አደባባይ በመባል ይታወቃል። ወደዘህ ትልቅ ባቡር መስመር ሲገባ አንድ እጅግ በጣም ትልቅ ሀዉልት ወለል ብሎ ይታያል፤ ይህም ሀዉልት የአምስት መቶዎቹ አደባባይ ወይም ፒያዛ ዴ ቺንኮቼንቶ በመባል የታወቃል። የፒያሳ ዴ ቺንኮቼንቶ መታሰቢያ ሀዉልት የተሰራዉ ወራሪዉ የጣሊያን ጦር አገራችንን ለመወረር ሲመጣ ዶጋሌ ላይ በራስ አሉላ ጦር የተገደሉትን አምስት መቶ የጣሊያን ወታደሮች ለማስታወስ ነዉ። በ1877 ዓም ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ ጦርና ጎራዴ በታጠቀዉ የራስ አሉላ ጦር ዉርደት የተከናነበዉ የጣሊያን ወራሪ ሠራዊት ብድሩን ለመመለስ በ1888 ዓ.ም ብዛት ያለዉ ካባድ መሳሪያ፤ መድፍና መትረየስ ታጥቆ አድዋ ድረስ ቢመጣም በዳግማዊ ሚኒሊክ የተመራዉ ጀግናዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት እንደገና ዉርደት አከናንቦት በጥቁር ህዝብ ታሪክ ዉስጥ ትዝታዉ ምንግዜም የማይደበዝዝ ድል አስመዝግቧል። የኢትዮጵያ ሠራዊት ዶጋሌና አድዋ ላይ እስካፍንጫዉ የታጠቀዉን የጣሊያን ወራሪ ጦር ደጋግሞ ያሸነፈዉ በመሳሪያ በልጦ ወይም የተሻለ የዉትድርና ችሎታ ስለነበረዉ ሳይሆን ከወራሪዉ ጦር የበለጠ ቆራጥነትና የአለማ ጽናት ሰለነበረዉ ነዉ።

በሃያኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን የተደረጉ ሌሎች የነጻነት ትግሎችን ስንመለከት በወቅቱ የአየር ኃይል ያልነበራት ትንሿ አገር ቬትናም በባህር፤ በአየርና በየብስ ጦርነት የገጠማትን ትልቁን የአለማችን ሀይል አሜሪካንን አሸንፋ ነፃነቷን ያስከበረችዉ በመሳሪያ ጋጋታ ሳይሆን የዛፍ ላይ ቅጠልና የተቦጫጨቀ ጨርቅ በለበሱ ነገር ግን ከፍተኛ የአላማ ጽናት በነበራቸዉ ጀግኖች ልጆቿ አማካይነት ነዉ።

አለማችን ትልቅ የጦርነት አዉድማ ናት ቢባል አባባሉ እምብዛም ከእዉነት የራቀ አባባል አይደለም። በእርግጥም አለም የጦርነት መድረክ ናት። ወደድንም ጠላን ወይም ብናምንም ባናምንም ጦርነቶች ሁሉ የተካሄዱት የህዝብን ነፃነት በሚደፍሩ ኃይሎችና መብቴንና ነጻነቴን አትንኩ በሚሉ ኃይሎች መካከል ነዉ። የአለማችን ታሪክ ወለል አድርጎ እንደሚያሳየን ደግሞ ይዋል ይደር እንጂ ሁሉም ዘለቄታዊ ድሎች የተመዘገቡት የአላማ ጽናት ባላቸዉ መብቴንና ነጻነቴን አትንኩ በሚሉ ኃይሎች ነዉ እንጂ የመሳሪያ ጋጋታ በተሸከሙ ኃይሎች አይደለም። የመሳሪያ ጋጋታ የተሸከመና ብዛት ያለዉ ወታደር ያሰለፈ ነገር ግን ለምን እንደሚዋጋ የማያዉቅና የአላማ ጽናት የሌለዉ ሠራዊት ግዜያዊ የጦር የጦር ሜዳ ድል ለያገኝ ይችላል፤ ሆኖም ጦርነቱን አሸንፎና የህዝብን ነጻነት ቀምቶ መዝለቅ በፍጹም አይችልም።

የአለም ታሪክ በነጭ ወረቀት ላይ በጥቁር ቀለም ቁልጭ አድርጎ የጻፈዉ አንድ ግዙፍ ሀቅ ቢኖር እልፍ ታንክና እልፍ አዕላፋት መድፎች ቢታጠቁም አምባገነኖች ለግዜዉ እንደተቆጣ ነብር ያስፈራሉ እንጂ ህዝባዊ አለማና ጽናት ያለዉ ጦር ፊት ሲቆሙ ፀሐይ እንደገላመጠዉ በረዶ ሟሽሸዉ የሚጠፉ ደንባራ ፈረሶች ናቸዉ። ለዚህም ነዉ ህዝብ አምባገነኖችን የወረቀት ላይ ነብር እያለ የሚጠራቸዉ።

ዛሬ ዕድሜዉ 35 እና ከዚያም በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚኒልክን ቤ/መንግስት ተቆጣጥረዉ የረገጡትን፤ የገደሉትንና መብቱንና ነጻነቱን ገፍፈዉ ያዋረዱትን ሁለት የወረቀት ላይ ነብሮች ያስታዉሳል የሚል ሙሉ እምነት አለን። ደርግ በ1967 ዓም “ያለ ምንም ደም እንከኗ ይዉደም” እያለ ወደ ሥልጣን ሲመጣ በፊዉዳሉ ስርዐት ጀርባዉ የጎበጠዉን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ደስ አሸኝቶ ነበር። እየቆየ ሲሄድና የተደበቀ ትክክለኛ መልኩ አደባባይ ሲወጣ ግን ያንን “ያለ ምንም ደም” የሚለዉን መፈክሩን ረስቶ ኢትዮጵያን የደም ገንዳ ሲያደርጋት በኢትዮጵያ ህዝብ ተጠልቶ አይንህን ለአፈር ተባለ። በሩሲያ ሰራሽ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች አስካፍንጫዉ የታጠቀዉና በቁጥሩና በወታደራዊ ብቃቱ አፍሪካ ዉስጥ ትልቁን ሠራዊት የገነባዉ ደርግ “እንደ ዉኃ የሚያጥለቀልቅ ኃይል አለኝ” እያለ ቢፎክርም እሱ እራሱ ተጥለቅልቆና በያለበት ተሸንፎ አገራችን ኢትዮጵያን ለዘረኛ አምባገነኖች ያስረከበዉ ለእግሩ ጫማ ለወገቡ መታጠቂያ በሌለዉ የገበሬ ጦር ተሸንፎ ነዉ። ደርግ እንደታጠቀዉ መሳሪያ ብዛት፤ እንዳደራጀዉ ወታደራዊ ብቃትና እንደ ወታደራዊ መሪዎቹ ችሎታ ቢሆን ኖሮ ደርግን እንኳን ተዋግቶ ለማሸነፍ በዉግያ ለመግጠምም የሚያስብ ኃይል በፍጹም አይነሳም ነበር፤ ነገር ግን ድል ምን ግዜም ቢሆን የመሳሪያ ጋጋታ ዉጤት ሳይሆን የራዕይ ጥራትና የአላማ ጽናት ዉጤት በመሆኑ በወቅቱ ይህንን የተገነዘቡ ኃይሎች ህብረትና አገር ዉስጥ የተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ ቁጣ አንድ ላይ ሆነዉ ደርግን ጠራርገዉ የታሪክ ቆሻሻ ዉስጥ ሊጨምሩት ችለዋል።

Friday, February 20, 2015

እውን ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚደነቅ የሚከበር ነገር አለውን?

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

በእስካሁኑ ግፍ ያልጠፋኸው ነገር ግን ለማይቀርልህ ወገኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! እንኳን ለአጥፊህ ለወያኔ ሐርነት ትግራይ 40ኛ ዓመት የልደት በዓል አደረሰህ! የዚህች ሀገር ነቀርሳ በውስጧ የበቀለበት 40ኛ ዓመት እነሆ ከነገ ወዲያ እሮብ የካቲት 11 2007ዓ.ም. ይከበራል፡፡

ግን ወያኔ ማን ነው? እውን የሚከበር የሚያኮራ ማንነት አለው? ነው ወይስ የሚረገምና የሚያሳፍር? ከዚህ ቡድን ውስጣዊ ታሪክ እንደምንረዳው ይህ ቡድን በርዕዮተ ዓለምና በአስተሳሰብ ልዩነት በግል ጥቅምና በሥልጣን ሽኩቻ አንዱ ሌላውን እየበላ አንዱ በሌላው እየተበላ እርስ በእርስ እንደ አውሬ እየተባላ እየተጠፋፋ በመጨረሻ በአውሬነቱ የበረታው የበረታው አስከፊው አስከፊው ቀርቶና ተቧድኖ ለዚህ የደረሰ እኩይ ሰይጣናዊ ቡድን ነው፡፡

የወያኔን የትግል ታሪክ ስናይ ከቀደምቶቹ የሕወሀት አባላት ጥለው ከወጡትም ካሉትም ከተገለሉትም በተለያየ ጊዜ በሰጡት ቃለ መጠይቆቻቸውና በጻፉት መጻሕፍቶቻቸው ላይ እንደተረዳነው ወያኔ እዚህ ለመድረስ ተጀምሮ እስኪጨረስ ድረስ አብዛኛውን ጊዜ ከዓረብ ሀገራት ከሸአቢያ በተለይም ከሱዳን ለሚያደርገው የትጥቅ ትግል ምድሯን እንደፈለገ እንዲጠቀምበት ፈቅዳ ለወያኔ መሸሻ መሸሸጊያ መሠልጠኛና መደራጃ የተለያዩ ዓይነት ድጋፍ እርዳታዎችን ያገኝ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ደርግ በበቀል 800ኪ.ሜ. ድረስ ወደ ሱዳን ዘልቆ እየገባ በጦር አውሮፕላን የሚደበድብበት ሁኔታ ነበር፡፡ ሱዳን ከወያኔ የምትፈልገው ብዙ ነገር ነበርና በወያኔ ትግል ወቅት ለወያኔ ብዙ ዋጋ ከፍላለች፡፡ ወደ ኋላ አካባቢ ደግሞ ወያኔ ድጋፍ እርዳታን ከአውሮፓና ከአሜሪካ ያገኝ ነበር፡፡

እነኝህ አካላት ሁሉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍና እርዳታ ለወያኔ ሲሰጡ እንዲሁ በነጻ ያለ ጥቅም ከሱ የሚፈልጉት ነገር ሳይኖር አልነበረም፡፡ ሁሉም ከወያኔ እንዲሰጣቸው ወይም እንዲደረግላቸው የሚፈልጉትና ወያኔም ሊያደርግላቸው ቃል የገባላቸው የየራሳቸው ጥቅሞች አላቸው፡፡ የሚያሳዝነው ሁሉም እንዲደረግላቸው የሚፈልጉት ነገር ሁሉ የሀገራችንንና የሕዝቧን ብሔራዊ ጥቅሞችና ሉዓላዊነት በእጅጉ የሚጎዱ መሆናቸው ነው፡፡ እነኝህ አካላት የፈለጉት ምንም ከባባድ ነገር ቢሆንም ቅሉ ከራሱ ጥቅም የሚበልጥበት ምንም ነገር ለሌለው ለወያኔ የወንበዴ ቡድን ግን ኢምንት ነውና እንደየፍላጎቶቻቸው ተቀብሎ አስተናግዷቸዋል፡፡ ለምሳሌ የሱዳንን ብናይ ወያኔ የገባላትን ከጎንደር እስከ ጋንቤላ በ1600 ኪ.ሜ. እርዝመት ከ40 እስከ 60 ኪ.ሜ. ስፋት የሚያህልን ከአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት በእጅጉ የሚልቅ መሬት ከሀገራችን ቆርሶ በሰነድ ደረጃ አስረክቧታል፡፡ ይህ በሰነድ አረጋግጦ የሰጣትን መሬት ግን መሬት ላይ ተፈጻሚ አድርጎ ወደ ሱዳን ለመቀላቀል በተደጋጋሚ ተሞክሮ ከሀገሬው በተነሣ የቆረጠ ቁጣ ሌላ መዘዝ እንደሚያመጣበት ስለሠጋ የራሱን ምቹ ጊዜ እየጠበቁለት ይገኛሉ፡፡ ሸአቢያም ከሚፈልገው በላይ አሰብን ያህል ወደብ ከነምርቃቱ አግኝቷል፡፡ ቢዘረዘር ሐተታው ብዙ ነው ብቻ ሁሉም የየድርሻቸውን አግኝተዋል እያገኙም ይገኛሉ፡፡

እንግዲህ የታሪክ አተላዎቹ፣ የወራዶቹ፣ የደናቁርቱ፣ የባንዳ ውላጁ ሁሉና የደዳብቱ ኩራት ወያኔ “አይ! ይሄማ እንዴት ይሆናል? እናንተስ እንዴት ደፋሮች ብትሆኑና እንዴትስ ብትንቁን ነው ኢትዮጵያዊያን መሆናችንን እያወቃቹህ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ የምትጠይቁን?” የሚልበት ጉዳይ አንዲት እንኳን ሳይኖረው የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅሞች አሳልፎ በመስጠትና ለመስጠትም ቃል በመግባት በሀገር ክህደት ወንጀሎች እስከ አፍንጫው ተነክሮበት ነው ለዚህ ስኬቱ የበቃው፡፡ እኔን የሚገርመኝ በእነኝህ ሁሉ አካላት ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ምቹ ሁኔታዎች ተደግፎ 17ዓመታትን ያህል ዘመን መፍጀቱ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ሕወሀት ምን ያህል ደካማ እንደነበረ ነው፡፡ ወያኔ ከጠላት ያገኝ የነበረውን ድጋፍና እርዳታ እርም ስለሆነ እሱን ተውትና እንዲያው ተገን ብቻ

Tuesday, February 17, 2015

የ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› ትግል የሁላችንም ነውና በጋራ እንነሳ!

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ትብብራችን ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሠላማዊ ትግል ፕሮግራም ካደረገው እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የተከሰቱትን ወቅታዊ ሁኔታዎች በመገምገም ሁለተኛ ዙር ፕሮግራሙን ነድፎ ለምርጫ ዕጩዎችን የማስመዝገብ ተግባር ጎን ለጎን ለተግባራዊነቱ በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ የዚህ የሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ማጠቃለያም የካቲት 15 /2007 በተመረጡ 15 የአገራችን ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ የሚደረጉ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በመነሳት የዛሬው መግለጫ ለየካቲት 15 የታቀደውን በ15 ከተሞች የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ፕሮግራም በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ወደ የካቲት 22/07 መተላለፉን ለማሳወቅና ትብብራችን እስከ ዛሬ ያደረገውን ሰላማዊ ትግል አስፈላጊነት፣ወቅታዊነትና ትክክለኝነት በተጨባጭ በማረጋገጥ፣የተያያዝነውን ሰላማዊና ህዝባዊ ትግል እንዴት ማስቀጠልና ውጤታማ ማድረግ ስለሚቻልበት የገዢዎቻችንን ከግምት ያለፈ የፍርኃትና ስጋት ደረጃን ያገናዘበ ስልት መቀየሳችንን ፣ የቆምንበትን ህገመንግስታዊነትና ህጋዊነት እንዲሁም የትግሉን ትኩረት የሚመለከቱ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የደረስንበትን ጭብጥ ለህዝባችን በዝርዝርና በስፋት በማቅረብ ለቀጣዩ ትግል ጥሪያችንን ለማቅረብ ነው፡፡

በዚሁ መሰረት የተደረሰባቸው ጭብጦች፡-

1.ገዢው ፓርቲ/መንግስት የቱንም ያህል አሰቃቂና አረመኔያዊ የአፈና እርምጃዎች ቢወስድ የህዝብ ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ድረስ ህዝባዊ ትግሉን ማዳፈን እንጂ ማስቆም እንደማይችል ይልቁንም ተጠናክሮ በረቀቀ ስልት እንደሚቀጥል የሙስሊም ማኅበረሰቡ ታህሳስ 10/07 ዓ.ም በኑር መስጂድ፣ የካቲት 06/07 በአንዋር ካሰማውና የትግሉን ቀጣይነት ካረጋገጠበት ፍጹም ሠላማዊ በሆነና አንድም ጉዳት ባልደረሰበት የተሳካ የተቃውሞ ድምጽና ክንዋኔ ተረድተናል፤

2. በታህሳስ 10/2007 ዓ.ም ተመሳሳይ ዕለት የባህር ዳር ከተማ ህዝብ ሃይማኖት፣ ዘርና ሌሎች ልዩነቶችን ወደጎን አድርጎ ፣ገዢው ፓርቲ በዘረጋው የአንድ ለአምስት የደህንነት መዋቅር ሳይጠለፍና ሳይገታ፣ በአንድነት ያሳየው ህዝባዊ እምቢተኝነትም አፈና የቱንም የህዝብ ጥያቄ የማፈን አቅም የሌለው መሆኑን ይልቁንም ትግሉን ወደ ግብታዊነት ሊመራ እንደሚችል ተገንዝበናል፤

3. ገዢው ፓርቲ/መንግስት በመንግስት መዋቅሮችም ሆነ በህዝቡ ማኅበራዊ ግንኙነት እያደረሰ ያለው ጭቆና/የመብት ረገጣው፣ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት…/ እና ከህዝብ የመሸከም አቅም በላይ የሆነው የኑሮ ውድነት፣የመከፋፈልና የጥላቻ ፖለቲካ … የህዝቡን የለውጥ ፍላጎትና የትግል ተነሳሽነት እያሳደገው መምጣቱን ፣የተባበረና የተቀናጀ አመራር ካገኘ ህዝቡ ለለውጥ ያለውን ጥማትና ዝግጁነት አስገንዝቦናል፤

እነዚህ ሲጠቃለሉም-ገዢው ፓርቲ/መንግስት ስለመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ከቃላት ያለፈ እምነትም ሆነ ቁርጠኝነት የሌለው በመሆኑ ለዚህ የተቋቋመውን የዲሞክራሲ ተቋም -የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በቁጥጥሩ ሥር በማዋል በጠንካራ ፓርቲዎች የውስጥ ጉዳይ በማስገባት ከመጪው ምርጫ ለማግለል ቆርጦ መነሳቱን ፣ ለዚህም አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎችን በሚመለከት በቦርዱ የተላለፈው ፖለቲካዊ ውሳኔና ፍጻሜው ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ በተጨማሪም ለቀጣዩ ምርጫ ዕጩዎችን ለማስመዝገብ በተንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ላይ በተለይ በኦሮሚያ፣በአማራና በደቡብ ኢትዮጵያ እየተፈጸሙ ያሉት ተመሳሳይ ህገወጥ ተግባራት ነገ ወደ ትብብራችን አባላትና ሌሎች ፓርቲዎች ውስጥ በግልጽና በቀጥታ የማሸጋገር አቅጣጫ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ኢቢሲ ያቀረበው በህገመንግስታዊው የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካዊ ሥርዓት የተቀመጠውን የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የመኖር ትርጉም ዋጋ የሚያሳጣው ‹‹መንግስትንና የመንግስት አስፈጻሚዎችን ከተቻችሁ፣ካላከበራችሁ ወይም ጸጥ ለጥ ብላችሁ የምርጫ አጃቢ ካልሆናችሁ እስከ 15 ዓመት ትታሰራላችሁ›› የሚል አንድምታ ያለው በ ‹‹ባለሙያዎች ትንታኔ ›› ሥም የተላከው የማስፈራሪያ መልዕክትና የሌሉ የፈጠራ ክሶችን ለመፈብረክ በአባል ፓርቲዎቻችን ላይ ‹‹የሞተ ጉዳዩን ከመቃብር

Monday, February 16, 2015

ዋ ለረዣዢም በቆሎዎች! (ታሪኩ አባዳማ)

ታሪኩ አባዳማ

ከ1990ዎቹ የቀዝቃዛ ጦርነት ፍፃሜ ወዲህ የአምባገነኖች ባህሪ እንኳ ተለውጦ እንደ አዲሱ ዘመን ሁሉ እነሱም ስልጣን ላይ የተቀመጡት በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያውም በህዝብ ፈቃድ መሆኑን ለማሳየት ተግተው እየሰሩ ነው። በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ይታይ እንደነበረው አይነት ሁሉን ነገር በይፋ ጨፈላልቆ በማን አለብኝነት በብቸኛ ፓርቲ ስልጣን ላይ መቀመጥ የሌጅትመሲ ጥያቄ ከማስነሳቱም በላይ አስተማማኝ እንዳልሆነ ጠንቅቀው ተገንዝበዋል። በመሆኑም ጨካኝ አምባገነኖች ሳይቀሩ ምርጫ ሲጠሩ ፣ መድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዓት መፈጠሩንም ሲሰብኩ ማየት እና መስማት እየተለመደ ነው። ለምርጫው ሂደት ፣ ለውድድሩ ድራማ ብሎም ለማይቀረው የመጨረሻ ውጤት አዋጅ የተቀነባበረ አሰራር ቀይሰዋል።

የምዕራቡ እና ምስራቁ ዓለም ፍጥጫ በረድ ብሎ የፖለቲካው አየር የሚነፍስበት አቀጣጫ ሲቀየር ከወጀቡ ጋር ተቀላቅሎ ከማዝገም ሌላ አማራጭ አልተገኘም። ስለሆነም ከዲሞክራሲያዊ ባህሪያት አንዱ የሆነውን ምርጫ የተቀበሉ ስልጡኖች መሆናቸውን ለለጋሽ የምዕራቡ ዓለም ለማሳየት ደፋ ቀና ብለዋል። ህዝባቸው እንደሚወዳቸው ፣ እንደሚመካባቸው እንደሚመርጣቸውም ደጋግመው ያስተጋባሉ።

አሸነፍን ያሉቱ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ ወንበር በተቆጣጠሩበት ፓርላማ ባንድ ጀምበር ህግ አርቅቀው ያውጃሉ ፣ ህጉን ራሳቸው ይፈፅሙታል ወይንም ይጥሱታል… ተሸነፉ የተባሉት ፀባይ አሳምረው ፣ አንገት ደፍተው ካልተቀመጡ ህገ ረቂቅ ይፃፍባቸዋል… አሸባሪ ተብለው ወህኒ ይጋዛሉ… ስለዚህ አምባገነኖች ምርጫ ለመጥራት አይፈሩም ፣ አያፍሩም… እንደሚያሸንፉም አይጠራጠሩም። ምክንያቱም ድል የሚታወጀው በብቸኛው መገናኛ በራሳቸው ራዲዮና ቲቪ ነውና!!

የኢንዶኔዢያው ሱሀርቶ ፣ የዛምቢያው ካውንዳ ፣ የኬንያው ሞይ ዓለም አቀፍ ፖለቲካው ባሳደረው ግፊት ምርጫ ጠርተው ተሸንፈው ስልጣናቸውን ለተመረጡ ዜጎች አስረክበዋል ፤ የግብፁ ሙባረክ እና የቡርኪና ፋሶው ካምፓዎሬ ምርጫ መጥራት ማለት ማሸነፍ ሆኖ ስላገኙት ያለገደብ ስልጣን ላይ ለመቀመጥ የሚያስችል ህግ ከልሶ ለማርቀቅ ሲሰናዱ ህዝብ በቃ ብሎ በቁጣ አስወግዷቸዋል ፣ የዙምባቤው ሙጋቤ የዩጋንዳው ሙሰቬኒ እና ሩዋንዳው ካጋሜ ዛሬም ምርጫ እየጠሩ ተፎካካሪያቸውን በብረት እያደቀቁ በስልጣን ላይ ናቸው – ምርጫ ሳይተጓጎል በየዓምስት አመቱ ሲጠሩ ውነትም ዲሞክረሲ የሰፈነ ይመስላል።የአይቮሪኮስቱ ሎሬት ባግቦ እና የኛዎቹ ወያኔዎች ምርጫ መጥራት ባይታክቱም ተወዳዳሪን በምርጫ ሳጥን ብቻ ሳይሆን በሬሳ ሳጥን መሸኘት ላይ የተካኑ ሆነው ተገኝተዋል።

እነኝህ ሁሉ የድህረ ቀዝቃዛ ጦርነት ዘመን ወጀብ የሚቀዝፉበትን አቅጣጫ እንዲሞርዱ ካስገደዳቸው መካከል ናቸው። ሁሉም በገዛ ህዝባቸው ላይ ሰቆቃ የፈፀሙ ፤ የዘረጉት መንግስታዊ መዋቅር በዘር እና አድልዎ ላይ የተገነባ ፤ ሙስና እስከ አንገታቸው የዋጣቸው ፣ ስልጣንን አላንዳች ተጠያቂነት በመዳፋቸው ጨምድደው ለመዝለቅ ቅንጣት የማያመነቱ ገዢዎች መሆናቸውን ህዝባቸው ፣ አለምም ይመሰክራል።

የኢሳያስ ቃለመጠየቅና የብሔርተኞች ጫጫታ

ቶኮላ

ኢሳት ወደ ኤርትራ ተጉዞ የኤርትራውን ፕሬዝዳንት ማናገሩ ከተሰማ ወዲህና በተለይም የቃለመጠይቁ ቅንጣቢ ከቀረበ ቦኋላ እየበገኑ ያሉት ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ በወያኔ የብሄር ፖለቲካ እናተርፋለን ብለው ሲዳክሩ አመታት ያስቆጠሩ ብሄርተኞች ጭምር መሆናቸውን ጭፍሮቻቸው በሶሻል ሚዲያ ላይ ለማስተጋባት ከሚሞክሩ አስተያየቶች ለማየት እየቻልን ነው:: “በሚንልኪ ዘመን የደነቆረ በሚንልክ እየማለ ይኖራል” እንደተባለው እነዚ ሰዎች ከመንደርተኝነት ተላቀው አለማችን ከቀዝቃዛው ጦርነት ፍጻሜ ወዲህ የደረሰቺበትን እድገት ምነው መረዳት ተሳናቸው? የሚል ጥያቄ ያስጨንቀኝ ጀምሮአል:: በኤኮኖሚ የበለጸጉት የአውሮጳ አገሮች ብንዋሃድ ነው በአለም ውስጥ ተገቢ ስፍራችንን ይዘን መቀጠል የምንችለው በማለት አንድ ለመሆን ሲጣደፉ የኛዎቹ በቋንቋ ተካለን የየራሳችንን የፖለቲካ ጎጆ ብንቀልስ ነው የሚበጀን ማለታቸው የጤና ነው?

ከሁሉም የሚገርመው ሰው በሰውነቱ በተከበረበት አለም እየኖሩ ለአገራቸውና ለህዝባቸው ግን የሚመኙት ሰው በቋንቋ ማንነቱ እርስ በርሱ የሚጠፋፋበትን የጥንትዮሽ ዘመን አይነት አስተዳደር መሆኑ የሰው ደም የሚያስጠማቸው ምን አይነት መንፈስ ብጠናወታቸው ነው? ያስብላል:: ቋንቋና ባህል ሰው በተወለደበት ህብረተሰብ ውስጥ የሚማረውና ይዞት የሚያድገው ትርጉምና ጥቅም የሚሰጠውም በዚያው ህብረተሰብ ውስጥ እስከተኖረ ድረስ ብቻ ሆኖ ሳለ ሌላው ቀርቶ አሜሪካና አውሮፓ ውስጥ ከአብራካቸው የሚወለዱት ወይም የተወለዱት ሳይቀሩ እነርሱ የኛ ነው የሚሉትን የማይወርሱ መሆናቸውን እያወቁ ለምንድነው አመለካከታቸውን መቀየር የተሳናቸው?

እኔን የሚያሳዝነኝ የመልካም አስተዳደር እጦት ለምድራዊ ጉስቁልና የዳረገው መከረኛ ህዝብ በቋንቋና በባህል ልዩነት ምክንያት እርስ በርሱ ቢገዳደል ምንድነው ጥቅሙ? የምሥራቅ አውሮፓዎን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ትተን አይናችን ፊት በሩዋንዳ፤ በቡሩንድ፤ በሱማሌ ወዘተ ህዝብ እርስ በርስ መጠፋፋት ማን ተጠቀመ? እንዴት ከዚህ መማር ይሳነናል?

አያት ቅድሜ አያቶቻችን በመሰዋዕትነት ባስረከቡን ነጻ አገር ውስጥ ተወልደንና አድገን የአስተዳደር በደል ያስከተለውን ኢፍትሃዊነት ከመዋጋትና የጋራ ቤታችንን ከድህነትና ከመብት ረገጣ የጸዳ ከማድረግ ይልቅ እራሳችንን የሚያሳንስ ለሌላው ግን የሌለ ኩራትና ክብር የሚፈጥር ” የጥቁር ቅኝ ገዥ” ታሪክ በራሳችን ላይ መፍጠር ለምን አስፈለገ?

መለስ ዜናዊና የበታቸኝነ ስሜት የፈጠራቸው ጥቂት የትግራይ ጉጂሌዎች ከፋፍሎ ለመግዛት በሸረቡት ሤራ ተተብትበን እስከመቼ እንታለላለን? በኔ አስተያየት በብሄርተኝነት ዙሪያ ጫፍ የረገጥ ፖለቲካ የሚያቀነቅኑ ሰዎች በተለያየ ምክንያት በግለሰብ ደረጃ የበታቸኝነት ስሜት ውስጥ የተዘፈቁ ናቸው:: ምናልባት ዘመናዊ ትምህርት ችግሩን ሳያባብሰው አልቀረም:: የሥነልቦና ሙያተኛም ባልሆን የበታቸኝነት ስሜት የሚጠፋው ከውስጥ ተኮትኩቶ በሚወጣ የራስ መተማመን ብቻ ነው ብየ አምናለሁ:: እራስን ማከም ለሚቻል የስነልቦና ችግር አንድ ሚስኪን ከሌላው ሚስኪን የአገሩ ዜጋ ጋር እንዲገዳደል ማነሳሳት ወንጀል ነው::

Sunday, February 15, 2015

የወቅቱ ሰራዊት ‹‹ክብረ በዓል›› ይገባዋልን?

ጌታቸው ሺፈራው

እየተከበረ በሚገኘው የ‹‹መከላከያ ሰራዊት ቀን›› በደርግ ወቅት የነበረው የአገራችን ሰራዊት አባላት እንደ ኢትዮጵያዊ ሳይሆን እንደ ውጭ ወራሪ ተቆጥሮ ሞቱና ቁስለቱ ላይ እየተፎከረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከአሁን ቀደም ዳር ድንበሯን ያስጠበቀ ይጠብቅ፣ ታሪክ የሰራ ሰራዊት እንዳልነበራት ተደርጎ የአሁኑ ሰራዊት ብቻ እየተወደሰ ነው፡፡ ሆኖም በደርግና በኢህአዴግ መካከል የነበረው ጦርነት የእርስ በእርስ ጦርነት እንጂ ሌላ አገራዊ አላማን ያነገበና ይህን ያህል የሚኮራበት ተጋድሎ አይደለም፡፡ በተቃራኒው እልቂቱ የሚያሳዝን ጠባሳው የታሪካችን አንድ አካል ነው፡፡ እስካሁን የመከላከያ ሰራዊት በዓልን ከሚያከብሩ አገራት መካከል የእርስ በእርስ ጦርነትን ተከትሎ የአንድ ፓርቲ ወይንም ሸማቂ ሰራዊቱ ድል በማድረጉ በዓልን የሚያከብር አገር የለም፡፡

ከኤርትራ ጋር በተደረገው ጦርነት ኢትዮጵያ ያጣችው የሰው ሀይል፣ ኢኮኖሚና የባህር በር ሲታይ እነ አሉላ አባነጋ በዶጋሊና በሌሎቹ የጦር ሜዳዎች ያስመዘገቡት ድል ጋር በአላማም ሆነ በድል በምንም መልኩ አንድ ሚዛን ላይ የሚቀመጥ አይደለም፡፡ የመከላከያ ሰራዊት በዓል በፓርቲ ፍላጎት የሚከበር ሆኖ እንጂ የአሁኑ የመከላከያ ሰራዊታችንም እራሱ አስመዘገብኩት ከሚለው በተሻለ ለዶጋሊ፣ አድዋና ማይጨው እውቅና ቢሰጥ የሚከፋው አይመስልም፡፡ የአሁኑ የመከላከያ ሰራዊት ራሱ ሊያዝን በሚችልበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ታሪክ ተረካቢ ሆኖ እንዳይታወስ ተደርጓል፡፡ ለዚህም ኢህአዴግ በአሁኑ ወቅት ይጠቅመኛል ያለውን መከላከያ ሰራዊት ብቻ በመዘከር ሰራዊቱን ይበልጥ ወደ ፖለቲካው ለመዘፈቅ የሚደረግ ጥረት ነው፡፡
ኢህአዴግ የመከላከያ በዓሉን አላማ ሲገልጽ «የመከላከያ ሰራዊቱ ከ1988 ዓ/ም በኋላ ለሰላምና ለአገራቸው ሉዓላዊነት ህይወታቸውን ያጡ የሰራዊቱ አባላት ለመዘከር፣ «የብሄር ብሄሮችን» ተዋጽኦ ያካተተና መብታቸውን የሚያስከብር ሰራዊት መመስረቱን አስመልክቶ፣ ሰራዊቱ በልማቱ መስክ እያበረከተው የሚገኘው አስተዋጽኦ፣ የህዝብ ሰራዊት መሆኑን ለማሳየት» በሚል ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ እነ አጼ ቴወድሮስ፣እነ አሉላ፣ እነ ጦና፣ እነ ገበየሁ፣ እነ ጎበና የመሩት ሰራዊት በህዝብ ለአንድ ቀን ለመዘከር የግድ ኢህአዴግ በከለለው የቋንቋ ድንበር ስርና ማዕቀፍ ውስጥ መገኘት ነበረባቸው፡፡

በሌላ በኩል አንድ ሰራዊት የልማት ሰራዊት መሆኑን የሚጠላ የለም፡፡ ሰራዊቱ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን መላመዱም ሆነ የውጊያ ብቃቱን ማጠናከሩ ለዘመናት በተደረገው ወታደራዊ ታሪክ ለሚኮራው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስደስት ነው፡፡ ሆኖም በመካኒካል ኢንጅነሪንግ የተመረቀ የዩኒቨርሲቱ ተማሪ በጥቃቅንና አነስተኛ እየተደራጀ፣ ድንጋይ እንዲያነጥፍ እየተገደደና ከዚህም አለፍ ሲል በስራ አጥነት ቤቱ ቁጭ ብሎ እየዋለ «ወቶ አደሩ» መኪና መጠጋገኑን ከሚገባው በላይ አግንኖ ማውራት ሌሎች ችግሮችን መቅረፍ ያልቻለው ኢህአዴግ በመከላከያው ስም እየነገደ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በወታደሩ ስም የቀረበው ስራ የሲቪሉ ውጤት ቢሆንም ኢህአዴግ አገሪቱን በወታደራዊነት ስር ለማስተዳደር በመፈለጉ ብቻ ለወታደሩ የይስሙላህ ክብር እየሰጠ ነው፡፡ በአገሪቱ ዘመናዊ የህክምና ተቋም በጤና ጥበቃ ሚኒስተር ስር መመስረት ሲገባው «የመጀመሪያው ዘመናዊ ሆስፒታል» ተብሎ በመከላከያ ስም መገንባቱን ሰምተናል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሲቪል ከሚባለው የጤና ጥበቃ ይልቅ ሰራዊቱ ታዕምር ሰራ ቢባል የኢህአዴግ በተለይም መከላከያውን በበላይነት የሚቆጣጠረው ህወሓት ውጤታማ ስራ እያከናወነ መሆኑን በማሳየት ቅቡልነትን ለማግኘት ታስቦ ነው፡፡ በተጨማሪም መብታቸውን ሊያስጠብቅ ከሚችለው ሲቪል ይልቅ ከላይ የመጣ ትዕዛዝን እንደ ወታደርነቱ ከማስፈጸም ወደኋላ የማይለው መከላከያ ሰራዊት ወደ ፖለቲካው በመዘፈቅ አገሪቱን ለመቆጣጠር ነው፡፡ ይህ ችግራችን እንዳለ ሆኖም ቢሆን የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በራሱ የሙያ መስክ ከዚህ በላይ ጥረት የሚጠበቅበት ሰራዊት ነው፡፡ የአባል ፓርቲዎች ተዋጽኦ በቀዳሚነት የሚነሳ ሆኖ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ለመከላከያው ሁለት አይነት አመለካከት ይስተዋላል፡፡ አንደኛው ያልተማረ እንደሆነ የሚጠቅስ ነው፡፡

የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ፣ ተዓማኒና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ የማይፈልጋቸውን መሪዎች መሻር፤ የሚፈልጋቸውን ደግሞ መሾም የሚያስችሉትን መሠረቶች ለመጣል የሚታገል ንቅናቄ ነው። እንደሚታወቀው የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት የሚገለጽበት እውነተኛ ምርጫ እንዲኖር ገለልተኛና ቀልጣፋ የፍትህ ሥርዓት፣ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ሊኖሩ ይገባል። ነፃ የሚዲያ ተቋማትና በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማኅበራት መኖርም መታለፍ የሌለባቸው አቢይ ጉዳዮች ናቸው። አማራጭ ፓሊሲዎችን ማቅረብ የሚችሉ በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከሌሉም አማራጮች የሉምና ምርጫ ትርጉም የለውም። ይህ ሁሉ ቢሟላ እንኳን ምርጫውን የሚያስፈጽመው አካል ገለልተኛ፣ ሀቀኛና ተዓማኒ ካልሆነ የሚደረገው ምርጫ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ሊሆን አይችልም።

ከላይ የተዘረዘሩትን የምርጫ እሴቶች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንኳን የተወሰኑትን በመጠኑም ቢሆን ያካተተ ምርጫ እንዲኖር መጣርና በሂደት የምርጫውን አፈፃፀም ማሻሻል ይቻል ይሆናል በሚል እምነት የዲሞክራሲ ኃይሎች በህወሓት የሴራ ምርጫዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል። ሆኖም በህወሓትና በእውነተኛ ምርጫ መካከል ያለው ተቃርኖ እያደር እየሰፋ ሲሄድ እንጂ ሲጠብ አልታየም። በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር በሚካሄድ ምርጫ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ለውጥ ሊመጣ ይችላል የሚለው እምነት ለአርበኞች ግንቦት 7 ፈጽሞ የተሟጠጠው ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ ነው። በግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታላቅ የለውጥ ተስፋ የሰጠው ድምጽ በህወሓት የተዘረፈው ከላይ የተዘረዘሩት ተቋማት ያልነበሩ በመሆናቸው፤ ስለዚህም ከምርጫ በፊት ተቋማቱን መገንባት፤ ተቋማቱን ለመገንባት ደግሞ ህወሓትን ከስልጣን ማስወገድ ይገባል ብሎ በማመኑ ነው አርበኞች ግንቦት 7 በሁለገብ የትግል ስልት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው።

ያም ሆኖ ግን በምርጫ ላይ ያላቸው ተስፋ ፈጽሞ ያልተሟጠጠ ፓርቲዎችን በማክበርና ሥራቸውንም አስቸጋሪ ላለማድረግ ሲባል ከምርጫ 97 ወዲህ የነበሩ ብሄራዊም ሆነ ክልላዊ ምርጫዎችን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምርጫ ዉጭ ያሉ ሌሎች አማራጮችን ብቻ እንዲመለከት አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ አድርጎ አያውቅም ነበር። አሁን ግን የአገራችን ኢትዮጵያ የፓለቲካ ሁኔታዎች ይህንን የቆየ አቋም በሚያስቀይር መንገድ፤ የአገራችንን የወደፊት ዕድል ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ያካባቢውን ሰላም በሚጎዳ መልኩ ተቀይሯል። የሰሞኑ የወያኔ እርምጃዎች ትንሽ ተስፋ ያደርግ የነበረውን የዴሞክራሲ ወገንተኛ ተስፋም እምሽክ አድርጎ በልቶታል:: እየተቃረበ ያለው ዓይነት የፌዝ ምርጫ ወያኔ እንደ እንጄራ የራበውን የተቀባይነት እጦት ለአጭር ጊዜ ያስታግስለት ይሆናል እንጂ የሀገሪቱን እያደር እየተወሳሰበ የመጣ ችግር ለጊዜውም እንኳን የሚያስታግስ አይሆንም፤ ይልቁንም ጊዜው በገፋ ቁጥር ችግሩ መቋጠሪያ የጠፋው እየሆነ ይሄዳል::

የሁኔታውን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር የወቅቱን የአገራችን የፓለቲካ ሁኔታ በጥንቃቄ መርምሮ የሚከተሉት ግንዛቤዎች ላይ ደርሷል።

1. ህወሓት ብዙዎች እትዮጵያዊያን የተሰውላቸውን አንድነት ፓርቲንና መኢአድን በመበተን የድርጅቶቹን ስምና ንብረት ለአገልጋዮቹ መስጠቱ፤ ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው የመራጭን ድምጽ መስረቅ ሳይበቃው የምርጫ ተወዳዳሪንም መዝረፍ መጀመሩን አመላካች ነው። ይህ ተግባር ህወሓት የምርጫ ውጤትን ብቻ ሳይሆን ተወዳዳሪዎችንም እሱ ራሱ ለመምረጥ መወሰኑን ያሳያል፤ ከዚህ በተጨማሪ የሴራ ምርጫውን ከጅምሩ ጀምሮ አስቀድሞ እስከተወሰነለት መዳረሻው ድረስ ለምንም ዓይነት ያልተጠበቀ አጋጣሚ (በምርጫው ወቅት የሚደረጉትን ክርክር ተብዬዎች ጨምሮ) እድል ላለመስጠት ወስኖ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፤

2. ይህ እኩይ ውሳኔ በምርጫ ቦርድ ፊርማና አንደበት ቢነገርም ምንጩ የህወሓት ፓሊት ቢሮ መሆኑን የሚከተሉት ተግባራት ይጠቁማሉ፤

2.1. በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲገለጽ የተወሰነው እርምጃ ለማስመሰል ያክልም ቢሆን የህጋዊነት ሽፋን እንዲኖረው አለመደረጉ ውሳኔው ፍጹም እብሪተኛ በሆነ አካል መወሰኑን ያመለክታል። እንዲህ ዓይነቱ እብሪተኛ አካል ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ነው። ውሳኔውን ለማስፈፀም የነበረው ጥድፊያም ይህንኑ ያጠናክራል።

2.2. ለማስመሰያ ያክል እንኳን ምንም አይነት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይኖር ፓሊስ የአንድነትና የመኢአድ ቢሮዎችን መውረሩ፤ ህወሓት አንድነትንና መኢአድን አጥፍቶ የድርጅቶቹን ስሞችና ንብረቶች ለሚፈልጋቸው ሰዎች ሰጥቶ በአስቸኳይ ለምርጫ ድራማው በፊት መስመር ሊያሰልፋቸው መወሰኑን አመላካች ነው። እንዲህ ዓይነት ከባድ ውሳኔ የሚሰጠው ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ብቻ ነው።

Tuesday, February 10, 2015

Ethiopia’s stifled press

 By: Washington Post Editorial Board

February 8

WHILE ENJOYING its status as an international development darling, Ethiopia has been chipping away at its citizens’ freedom of expression. The country now holds the shameful distinction of having the second-most journalists in exile in the world, after Iran. That combination of Western subsidies and political persecution should not be sustainable.

According to a new report by Human Rights Watch, at least 60 journalists have fled the country since 2010, including 30 last year, and at least 19 have been imprisoned. Twenty-two faced criminal charges in 2014. The government closed five newspapers and a magazine within the past year, leaving Ethiopia with no independent private media outlets. With the country headed toward elections in May, the pressure on the media has undermined the prospect of a free and fair vote.

Ethiopia has long been known for its censorship and repression of the media, but the situation has deteriorated in recent years. According to the Committee to Protect Journalists, the country has since 2009 “banned or suspended at least one critical independent publication per year.” After the death of prime minister Meles Zenawi in 2012, successor Hailemariam Desalegn has tightened the regime’s stranglehold on the press. Even Ethiopia’s rival Eritrea looks better: It released several imprisoned journalists last month.

As Human Rights Watch documents, journalists and media outlets who dare publish critical articles routinely receive threatening phone calls, texts and e-mails from party officials and security personnel. Journalists’ movements are often restricted outside of the capital, Addis Ababa. Sources who talk to foreign journalists and human rights organizations can face threats and detainment.

The repression extends across the media ecosystem. State agents harass printers and disrupt distribution processes associated with critical publications. Journalists who flee into neighboring countries are tracked and threatened. The government blocks Web sites from the Ethiopian diaspora, and it has jammed signals of foreign broadcasters, including Voice of America.

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ደብዳቤ

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ደብዳቤ
===========================
ቀን 02/06/2007 ዓ.ም
ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የልጄ ተመስገን ደሳለኝን ጉብኝት ይመለከታል

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአብራኬ የወጣ ሁለተኛ ልጄ ነው፡፡ ገና ከህፃንነቱ ጀምሮ ለሰው አሣቢ፣ ሀገር ወዳድና ታታሪ ስለመሆኑ ከእኔ በላይ የሚያውቁት ይመሰክራሉ፡፡ ልጄ ተመስገን ለወገኔ አሰብኩ ባለ በእስር ቤት ያለጎብኚ እየተሰቃየብኝ ይገኛል፡፡ መቼም፣ የእናት ሆድ አያስችልምና እባካችሁ ልጄን ታደጉት፡፡ እባካችሁ ቢያንስ ካለበት እየሄድኩ የልጄን አይን እንዳይ እንዲፈቀድልኝ ተባበሩኝ፡፡ የልጄን ድምጽ ከሠማሁ ይኸዉ አንድ ወር ሞላኝ፡፡ ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለወንድሙ ብሎ የቋጠረዉን ምሣ ይዞ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ቢሄድም በማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ተደብድቦ የያዘውን ምግብ እንኳ ሣያደርስ ሜዳ ላይ ተደፍቶ ተመልሷል፡፡ መቼም እናንተም ልጆች ይኖራችኋል፤ ደግሞም የልጅን ነገር ታውቁታላችሁ፡፡ እኔ አሁን በእርጅና ዕድሜዬ ላይ እገኛለሁ፡፡ ከአሁን በኋላ ብቆይም ለትንሽ ጊዜያት ነው፡፡ በዚህች ጊዜ ውስጥ ልጄን እየተመላለስኩ እየጠየኩ፣ ድምፁን እያሰማሁ፣ አይዞህ እያልኩ ብኖር ለእኔ መታደል ነበር፡፡ እባካችሁ እርዱኝ የልጄ ድምጽ ናፈቀኝ፡፡ እሱን መጎብኘት የተከለከለበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንኳን እስካሁን አላወቅሁም፡፡ ከወንድሙ ድብደባ በኋላም ጥር 10 ወደ ጠዋት አካባቢ የሄዱት ጓደኞቹ እና ወንድሞቹ ሳያዩት ተመልሰዋል፡፡

ተምዬ ስታመም የሚያስታምመኝ፣ “አይዞሽ እማዬ” የሚለኝ ረዳቴ ነው፡፡ ሌላ ዘመድ የለኝም፡፡ የምተዳደረውም ልጆቼ ለፍተውና ደክመው በሚያመጧት ትንሽ ብር ነው፡፡ ዛሬ ግን ይኸዉ ልጆቼም ወንድማቸውን ለማየት እየተንከራተቱ ነው፡፡

በእናታችሁ ይዣችኋለሁ፤ ከቻላችሁ ልጄ እንዲፈታልኝ እና እኔም ያለችኝን ቀሪ የእድሜ ዘመን አይን አይኑን እያየሁ እንድኖር እንድታደርጉልኝ፤ ይህን ማድረግ ከአቅም በላይ ከሆነ ደግሞ ካለበት ድረስ እየተመላለስኩ እኔና ሌሎች ልጆቼ እንዲሁም ወገኖቹ እንዲጠይቁት ቢደረግልኝ ስል በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ፡፡ ልጄን አውቀዋለሁ፡፡ አንድ ነገር ሲገጥመዉ ሆድ ይብሰዋል፡፡ ቢያንስ እንኳን ቤተሰቦቹን ሲያይ ስለሚፅናና ይኸዉ እንዲፈቀድልኝ እማፀናለሁ፡፡ እኔ ምንም አቅም የሌለኝ አሮጊት ነኝ፡፡ ሁሉንም ለናንተ ሠጥቻችኋለሁ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር እንደምታስተካክሉልኝ እና እንደገና የልጄን ፊት እንዳይ እንደምታደርጉኝ ሙሉ ተስፋ አለኝ፡፡
እንግዲህ የየካዉ ቅዱስ ሚካኤል ይከተላችሁ፡፡ መቼም የእናትን ሆድ ታውቁታላችሁ፤ የልጅ ነገር አያስችልም፡፡ ሆድም ቶሎ ይሸበራል፡፡ ስለዚህ እባካችሁ እኔንም ልጆቼንም እርዱን እንላለን፡፡

Sunday, February 8, 2015

ለወያኔ ዉንብድና መልሱ ህዝባዊ እምቢተኝነትና ህዝባዊ አመጽ ነዉ!

ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎ የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን ጨብጠዉ በኖሩባቸዉ ባለፉት ሃያ አራት አመታት የአገራችን የኢትዮጵያን የፖለቲካ መድረክ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እጅግ በጣም ከዘቀጠና ከረከሰ የወያኔ ድራማ ዉጭ ሌላ ምንም ነገር የማይታይበት አለባሌ መድረክ አድረገዉት ቆይተዋል አሁንም እያደረጉት ነዉ። አንድ ቋንቋ የሚናገሩትና ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸዉ የወያኔ መሪዎች ኢህአዴግ የሚባል አጋሰስ የሽፋን ድርጅት ፈጥረዉ በኢትዮጵያ ህዝብ ሰብዓዊ መብትና ነጻነትና ላይ ተነግሮም ተጽፎም የማያልቅ ግዙፍ ግፍና በደል ፈጽመዋል። ህጻን፤አዛዉንት፤ ወንድና ሴት ሳይለዩ መብቴን አትንኩ ያለቸዉን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያለምንም ርህራሄ በጥይት ጨፍጭፈዋል። ሴቶች እሀቶቻችንን እጅና እግራቸዉን አስረዉ ጡታቸዉን በመቆንጠጫ እየቆነጠጡ በሴትነታቸዉ ላይ የዉርደት ተግባር ፈጽመዋል። ወንዶች ወንድሞቻችንን ደግሞ ዉስጥ እግራቸዉን ገልብጠዉ እየገረፉ ጥፍራቸዉን አይናቸዉ እያየ በጉጠት እየሳቡ ነቅለዋል። ባጠቃላይ የወያኔ ዘረኞች በዛሬዉ ዘመን አንኳን ወገን በወገኑ ላይ የዉጭ ጠላትም በህዝብ ላይ የማይፈጽመዉ በደል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ፍጽመዋል።

ወያኔ ስልጣን እንደያዘ “አባይ ትግራይ” ወይም “ታላቋ ትግራይ” የሚለዉን ህልሙን ለማሳካት ወልቃይት ጠገዴን ከጎንደር ቆርሶ ከትግራይ ጋር ቀላቅሏል። ስልጣን ይዞ ከተደላደለ ከአመታት በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያን ገበሬ ከመሬቱ አፈናቅሎ ለምለም መሬቱን በርካሽ ዋጋ ለባዕዳን ሽጧል፤ ከዚህ አልፎ ተርፎም የአባቶቻችን አጽም ያረፈበትን የአገራችን ዳር ድንበር ቆርሶ ለጎረቤት አገር ገጸ በረከት አቅርቧል። ይህ አገራቸዉንና የሚመሩትን ህዝብ በሚጠሉ ጠባቦች የተሞላ ድርጀት ባለፈዉ ሳምንት የኢትዮጵያን ህዝብ ብቻ ሳይሆን ደጋፊዎቹንና በአንቀልባ ታዝለዉ አስከዛሬ ያቆዩትን ምዕራባዉያን ጭምር ግራ ያጋባ ፀረ አገርና ፀረ ህዝብ እርምጃ ወስዷል። ድርጅት እያፈረሰና በፓርቲ ላይ የራሱን ተለጣፊ ፓርቲ እያቋቋመ ዛሬ ላይ የደረሰዉ ወያኔ ምርጫ የሚባል ድራማ በደረሰ ቁጥር የሚይዘዉ በሽታ ዘንድሮም ይዞት አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲንና መላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን አፍርሶ በምትካቸዉ የራሱን መኢአድና የራሱን አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ፈጥሯል። ይህ ወያኔ ከሰሞኑ የወሰደዉ የፖለቲካ እርምጃ በየትኛዉም አለም በተለይ የመድበለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዐትን እንከተላለን በሚሉ አገሮች ዉስጥ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ እጅግ በጣም ትልቅ የፖለቲካ ሸፍጥ ነዉ።

የወያኔን ታሪክ ተወልዶ ካደገበት ከደደቢት በረሃ እስከ ሚኒልክ ቤ/መንግስት ድረስ ያደረገዉን ጉዞ ስንመለከት ወለል ብሎ የሚታየን አንድ ሐቅ አለ፤ እሱም ወያኔ ሁሉንም ነገር በዘር መነጽር ብቻ የሚመለከትና ህዝብን በወዳጅና በጠላት ጎራ ለይቶ ወዳጅ አይደለም ያለዉን ሁሉ እንደ ሩሲያዊዉ ዮሴፍ ስታሊን እየገደለ የመጣ ድርጅት ነዉ። በእርግጥም ወያኔ ጫካ ዉስጥ እያለም ሆነ ዛሬ ከተማ ገብቶ የሚቃወመዉንና በሀሳብ የማይግባባዉን ድርጅትም ሆነ ግለሰብ እያፈረሰና እገደለ ባፈረሳቸዉ ድርጅቶች ምትክ ደግሞ የራሱን ተለጣፊ ድርጅት እየፈጠረ የመጣና ከዲሞክራሲያዊ አሠራርና ከስልጣኔ ጋር የማይተዋቅ ድርጅት ነዉ።

በመርፌ የተጠቃቀመ ቁምጣና ጥብቆ ለብሶ አስራ ሰባት አመት ጫካ ለጫካ የተጓዘዉ ወያኔ ጎንደር፤ ጎጃምና አምቦ እያለ ወደ አዲስ አበባ ሲጠጋ ከተገነዘባቸዉ ነገሮች አንዱ የለበሰዉ የተጠቃቀመ ቁምጣ የትም እንደማያደርሰዉና ለከተማ ኑሮ የሚስማማ አዲስ ልብስ እንደሚያሰፈልገዉ ማዉቁ ነዉ። በጥላቻ ተረግዞ በክፋት ላደገዉ ወያኔ ቢበቃዉም ባይበቃዉም ወይም ቢያምርበትም ባያምርበትም ይህንን ለከተማ ዉስጥ ኑሮ የሚያስፈልገዉን አዲስ ልብስ ለማዘጋጀት ብዙ ግዜ እልወሰደበትም። የሚሰርቅና የሚስቅ ምን ግዜም ተባባሪ አያጣም እንዲሉ ወያኔ የአዲስ አበባን መሬት የረገጠዉ ጦር ሜዳ ላይ የማረካቸዉን ወታደሮችና አገር ዉስጥ ያገኛቸዉን ደካማ ሰዎች ሰብስቦ በፈጠረዉ ኢህአዴግ በሚባል ፈረስ ጀርባ ላይ ተፈናጥጦ ነበር። ትግራይን ነጻ አወጣለሁ ብሎ ትግል የጀመረዉ ወያኔ ኢህአዴግን የፈጠረዉ ወያኔነቱን ለመተዉ ሳይሆን እራሱን በዚህ በኢትዮጵያ ስም በፈጠረዉ ድርጅት ዉስጥ ሸሽጎ እዉነተኛ ባህሪዩን ለመደበቅ ነበር።

Saturday, February 7, 2015

ኢህአዴግ በጋራ ንቅናቄው መንበርከኩን አመነ!

“አሜሪካ በህወሃት/ኢህአዴግ ላይ ፖሊሲዋን ልትቀይር ይገባታል”

* ኢንቨስተሮች “የደም ከፈን” ላለመግዛት ወሰኑ

በኦሞ ሸለቆ ድሆችን ከመሬታቸው በማባረር የሚያመርተውን ጥጥ ወደ ውጭ ለመላክ ከስምምነት ደርሶ የነበረው ኢህአዴግ ባለፈው ሰሞን ያልጠበቀው ምላሽ ደርሶታል፡፡ ምላሹን ተከትሎ የጥጥ ግብይቱ የጨነገፈው በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መሆኑን በገሃድ አመነ፡፡ በኢህአዴግ ስትራቴጂክ በሆኑ ቁልፍ አካሄዶች ላይ አስቀድሞ የመልስ ምት በመምታት ፈተናው ውስጥ የከተታቸው አኢጋን እና መሪው ኦባንግ ሜቶ መዋቅራቸው ሊገኝ አለመቻሉ ኢህዴግን እንዳስጨነቀው ተሰማ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በሰማሁት ተዝናንቻለሁ ብለዋል፡፡ በዛሬው ዕለት አቶ ኦባንግ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አሜሪካ መከተል የሚገባትን አካሄድ በመዘርዘር ለፕሬዚዳንት ኦባማ ፖሊሲ ሊያስቀይር የሚችል ደብዳቤ ልከዋል፡፡

ኢህአዴግ ነዋሪዎችን እያፈናቀለ በቦታቸው ላይ ጥጥ እያበቀለና ጨርቅ እየሰፋ ለምዕራባዊ ኩባንያዎች ለመቸርቸር የገባውን ውለታ ያጠፉበት ሁለቱ ኩባንያዎች ዓለምአቀፋዊው የስዊድን ጨርቃ ጨርቅ ሻጭ ኤች ኤንድ ኤምና የጀርመኑ ቼቦ ናቸው፡፡ ባለሃብቶቹ ከኦሞ ሸለቆ ሰብዓዊ መብታቸው እየተገፈፈ መሬታቸው በተነጠቀባቸው ዜጎች መኖሪያ ላይ ጥጥ ተመርቶ የሚፈበረከው ጨርቃጨርቅ “የደም ከፈን” አድርገው በመቁጠር ስምምነታቸውን መሰረዛቸውንና ውሉ መጨናገፉን ያመኑት የኢህአዴግ ጨርቃ ጨርቅ ተቋም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ባንተ ይሁን ገሠሠ ለሪፖርተር ባለፈው ሰሞን በተናገሩበት ወቅት ነው፡፡

“የሰብዓዊ መብት አቀንቃኝ ነን ባዮች” በማለት የንግድ ስምምነቱ ውል ቀለሙ ሳይደርቅ፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ድርጅት በጉዳዩ ላይ ሃሳብ ሳይሰጥ፣ በተቋም ደረጃም ይሁን በፖለቲካ ፓርቲ መግለጫ ሳይሰጥበት፣ በአገር ውስጥም ይሁን በተለይ በውጭ የሚገኙ “አክቲቪስቶች” ድምጻቸውን ሳያሰሙበት ጉዳዩን የራሱ አድርጎ በቀጥታ ለኤች ኤንድ ኤምና ለዋና ሥራ አስፈጻሚው “የደም ከፈን” በማለት ኩባንያው ራሱን ከዚህ ዓይነት እርም የተላበሰ ስምምነት እንዲያጸዳ ማስጠንቀቂያ የላከው አቶ ኦባንግ የሚመሩት አኢጋን ነበር፡፡

ይኸው በዋና ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ጥቁሩ ሰው” ተፈርሞ የተበተነው የማስጠንቀቂ ደብዳቤ ቅድሚያ የተዘገበውም በዚሁ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ነበር፡፡ ይህ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ኤች ኤንድ ኤም ሲደርሰው በወቅቱ “በመልካም የንግድ ተግባር” ዓለምአቀፋዊ ሽልማት በዋሽንግተን ዲሲ የሚቀበልበት ወቅት ላይ ነበር፡፡ በወቅቱ የጋራ ንቅናቄው ለኤች ኤንድ ኤም ከጻፈው ደብዳቤ በተጨማሪ ከጀርመኑ ቼቦ ጋር ቀጥተኛ ባልሆኑ መንገዶች በመነጋገርና ተጽዕኖ በማድረግ የፈረመውን ውል በአንክሮ እንዲከታተል ማስጠንቀቂያ እንዲደርሰው አድርጎ እንደነበር የጋራ ንቅናቄው ለጎልጉል አስታውቋል፡፡

የኢህአዴጉ ሹመኛ ለሪፖርተር ቃላቸውን ሲሰጡ ስም አይጥሩ እንጂ “ነን ባዮች” ሲሉ የገለጹት በቅድሚያ አቶ ኦባንግ የሚመሩትን አኢጋን ስለመሆኑ ጥርጥር እንደሌለ ከአዲስ አበባ የጎልጉል መረጃ አቀባይ አመልክቷል፡፡ ከዚሁ አዲስ አበባ የተገኘው መረጃ እንደሚመለክተው አቶ ኦባንግ በኢህአዴግ ቁልፍ አካሄዶች ላይ አስቀድመው መረጃ በማውጣትና በማጋለጥ “ደንቃራ” እንደሆኑባቸው ታውቋል፡፡

ለኢህአዴግ ከሚያገለግሉ ቁልፍ ሰዎች መካከል የተገኘ መረጃ እንደሆነ በመጥቀስ እንደተጠቆመው ኢህአዴግ የአቶ ኦባንግን እና አኢጋንን አሠራር እንዲሁም ያለውን የግንኙነት ደረጃ በተጨባጭ ለመሰለል እንዳቃተው ታውቋል፡፡
በተለይ በዳያስፖራው የፖለቲካ ስልጠት (ሲስተም) ያለው የህወሃት/ኢህአዴግ አደረጃጀት ኦባንግ እና ድርጅታቸውን አስመልክቶ የሚሰበስበው መረጃ አቶ ኦባንግ በፌስቡክ ከሚለቁት ብዙም ያልተለየ በመሆኑ ብዥታን ፈጥሮባቸዋል፡፡ በታላላቅ ቦታዎች፣ በከፍተኛ ስብሰባዎች፣ “አንቱ” በሚጠሩ ተጽዕኖ ፈጣሪ ኃይሎች፤ ግዙፍ በሚባሉ የዓለም ተቋማት፣ በታላላቅ መንግሥታት ወዘተ ኢትዮጵያን በብቸኝነት እየወከሉ ፖሊሲ እስከማስቀየር የደረሱት አቶ ኦባንግ “ለኢህአዴግ ራስ ምታት ሆነዋል” በማለት የአገዛዙ ባለሥልጣን መናገራቸውን ከመረጃ ሰዎቻችን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Thursday, February 5, 2015

የትግራይ ሕዝብንና የኢትዮጵያ ፓሊስን በኢትዮጵያዊያን ለማስጠላት የሚደረገው ጥረት ከሽፏል!

ህወሓት ንፁሀንን ለመደብደብ የሚያበቃ በቂ ክፋት ያለው ልዩ ጦር ሲያሰለጥን ቆይቷል። ይህን ልዩ ጦር የፓሊስን መለያ እያለበሰ ነውረኛ ሥራዎችን እንዲሠራ በማድረግ በአንድ በኩል ንፁሀንን የመጉዳት በሌላ በኩል ደግሞ ፓሊስን በሕዝብ የማስጠላት መንታ ግቦችን ለማሳካት ተጠቅሞበታል። ይህ ልዩ ጦር በአለፉት ጥቂት ሳምንታት ባዶ እጃቸው ለተቃውሞ በወጡ ነብሰ ጡር ሴቶች ላይ ሳይቀር ባሳየው ጭካኔ፣ በሰማያዊ እና በአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ባደረሰው ድብደባ መጠን እና ባካሄደው የግለሰብ ንብረቶች ዝርፊያ የሥርዓቱ ባህርይ ፈጽሞ ከሰውኛ ተፈጥሮ እየወጣ እንደሆነ አመላካች ነው። በእነዚህ ድብደባዎች ወቅት በትግራይ ተወላጆች ላይ የተለየ ትኩረት በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስባቸው ተደርጓል። በትግራይ ተወላጆች ላይ የተለየ ትኩረት የተደረገው በደብዳቢዎቹ የግል ውሳኔ ሳይሆን ከበላዮቻቸው በተሰጠ ትዕዛዝ ነው ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ያምናል።

በአርበኞች ግንቦት 7: እምነት መሠረት የፓሊስ ከፍተኛ አዛዦች ህወሓቶች ቢሆኑም አብዛኛው የሠራዊቱ አባል በህወሓት ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ የተማረረ፤ የሥርዓቱ መለወጥ የሚፈልግና ሥርዓቱን ለመለወጥ የሚደረገውን ትግል የሚደግፍ ኃይል ነው። ስለሆነም ህወሓት የተለየ ጦር አሰልጥኖ የፓሊስ ልብስ በማልበስ ነውረኛ ወንጀል በማሠራት ፓሊስን ለማስጠላት የሚያደርገው ሴራ ሊጋለጥ ይገባል ብሎ ያምናል። የፓሊስ ሠራዊት አባላትም በስማቸውና በደንብ ልብሳቸው የሚደረገውን ደባ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እንዲያጋልጡ አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል።

ህወሓት እንደሚያስበው እና የኢትዮጵያም ሕዝብ እውነት አድርጎ እንዲቀበለው እንደሚፈልገው የትግራይ ሕዝብ በጅምላ የህወሓት አፍቃሪና ደጋፊ አይደለም። እንዲያውም በተፃፃሪው ህወሓት ከትግራይ ተወላጆች ልብ እየተነቀነ ነው። የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን/ደምህት) ከትግራይ የበቀለ፤ ህወሓትን በአመጽ ለመፋለም የቆረጠ ኃይል ነው። አርበኞች ግንቦት 7 በትግራይ ውስጥ ብዙ ደጋፊዎች ያሉት መሆኑ የምናውቀው ሀቅ ነው። አረና ትግራይ ህወሓትን በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተነሳ ተሰሚነቱን በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የመጣ እና አቶ አብርሀ ደስታን የመሰለ ወጣት ኢትዮጵያዊ የፓለቲካ መሪ ያወጣ ድርጅት ነው። ህወሓት አንድነት ፓርቲ ላይ የመረረ አቋም ከወሰደባቸው ምክንያቶች አንዱ በትግራይ ውስጥ ያለው ተቀባይነት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱ ነው። ህወሓት የትግራይን ሕዝብ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በጅምላ ለማጣላት የሚያደርገው ጥረት ማክሸፍ ይኖርብናል ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል፤ ለዚህም ተግቶ ይሠራል። አርበኞች ግንቦት 7 ከትግራይ የዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር በመተባበር ፀረ ህወሓት ትግል በትግራይ ውስጥ መቀጣጠል ይኖርበታል ብሎ ያምናል። በዚህም መሠረት ትግራይ የህወሓት መቀበሪያ የመሆኗ ጊዜ ሩቅ አይደለም።

Wednesday, February 4, 2015

አብዮት መንታ ነው (ሄኖክ ታደሰ ጆሃንስበርግ)



“የአብዮት ያለህ!”፥ አትበሉ ባ’ገሬ፣
በአብዮት መሃል፥ አብዮት አይጠሬ፣
ምስጋና ቢስ ትውልድ፥ ሆነነው ነው እንጂ፣
የግፈኛን ቀብር፥ የምናበጃጅ፣
የሚሞቱልንን፥ የደም ዋጋ ንቀን፣
በአብዮት መሃል፥ ካ’ብዮት ርቀን፣
በአርበኞች መሃል፥ ባ’ርበኝነት ስቀን…

“ደሃ ህዝብ አስፈጁ”፥ ስንል ተሰምተናል፣
“አመሉ ሲታወቅ”፥ ብለን አድንቀናል፣
‘ያስፈጀው’ ሲወገዝ፥ ፈጂውን ትተናል፣
አህያ እየፈራን፥ ዳውላ መ’ተናል።

ልንገርህ ወገኔ፥

አብዮት ሁለት ነው፥ መንታ ነው ፍጥረቱ፣
እርግጥም አብዮት፥ ስም ያገኘበቱ፣
በዳዮችን ሲጥል፥ ስርአት ሲዘረጋ፣
ሙሉ ሥም ያገኛል፥ አቢዮት እዚህጋ።
ነገር ግን ሲመታ፥ በበዳይ ፍላጻ፣
አቢዮት ተሽሮ፥ ይባላል አመጻ።
“አብዮት የለም” አንበል፥ አብዮት አለን እኛ፣
ግዞት ቤቱ የሞላው፥ በአብዮተኛ።

“There are accepted revolutions, revolutions which are called revolutions; there are refused revolutions, which are called riots.” — Les Miserables/ Victor Hugo

ማክሰምና መሰንጠቅ – ባንዳና ባርነት (የጎልጉል ርዕሰ አንቀጽ)

ህወሃት በዘረፈውና በሚዘርፈው ሃብት ተጠቅሞ ለወዳጆቹ የሚያኮራ፣ ትውልድ ለሚላቸው የሚበጅ ተግባራት እያከናወነ እንደሆነ ይነግረናል፤ ይነግሩናል። ውስን ባለሥልጣናትና አበሮቻችው በሃብት ተመንድገዋል። በንዋይ ሰከረው የሚያደርጉት እስኪጠፋቸው ናጥጠዋል። የት ጋር አንደሚያበቃ ባይታወቅም፣ የተደሰቱ፣ የተከፉ፣ የተናቁ፣ የተሰረቁ፣ የሚሰረቁ፣ እየሰረቁ ያሉ፣ የተትረፈረፈላቸው፣ በስማቸው የሚነገድባቸው፣ ባሪያዎችና ባንዳዎች፣ ቀን የሚጠብቁ፣ ጥርሳቸውን የነከሱ፣ … ወዘተ “አብረው” አሉ፡፡

ዘመን፣ ወራትና ቀናት ቅዠትን በመሰሉበት ዓለም፣ ቁራሽ ለሚሞላው ከርስ ራሳቸውንና ማንነታቸውን፣ ከዚያም አልፎ የትም የማይደበቁትን ኅሊናቸውን ያቆሸሹ፣ የአገር “እንግዴ ልጆች” ወይም “ውርጃዎች” ለህወሃት የማከሰምና የመግደል ሴራ ተላላኪ ሆነው የህዝብን ክብር ሰልበው ረክሰው ያረከሳሉ። ከዚህም በላይ ነገ እንደ ውዳቂ ላንቲካ መጣላቸውን እያወቁ፣ አሽከርነት፣ ከሃዲነት፣ ውርደት፣ መለያቸው እንዲሆን መርጠው ተሳቅቀው ይኖራሉ። እነሱን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባመነበት መንገድ እንዲጓዝ ለመታገል የሚውተረተሩትን ተኩላ ሆነው ያስበሏቸዋል።

ቅንጅትን በሉት። ቅንጅትን አሳረዱት። ተቀራመቱተ። የውስጥ ችግሩ እንዳለ ሆኖ እነርሱ ግን ዕጣ መድበው ተጣጣሉብት። አየለ ጫሚሶና ባልደረቦቻቸው “የክህደት ዋንጫ” ተሞላላቸው። ከዚያም ተጣሉ። አሁን “ምርጫ” ደርሷል፤ ድንጋጤ ጨምሯል፤ የሕዝብ ሱናሚ አስፈርቷል፤ የህንጻውና የመንገዱ ሁኔታ አልበቃም፤ የሰዉ ህይወት ከመቅለሉ የተነሳ ለሚዛን አልበቃ ባለበት አገር ህይወቱ “በቀላል ባቡር ሊቀልል” ሽር ጉድ ይባላል፤ “ሥራ ላይ ነን፤ ምርጫ ደርሷላ”፤ አስተናጋጇ ህወሃት በለመደችው መንገድ ልታባብል ብዙ ትጥራለች፤ በየማዕዘኑም እያደባች ነው፤ እስከ “ምርጫ” ቤቷን አሳምራ ቄጠማ ጎዝጉዛ፣ ፈንዲሻ ነስንሳ፣ ዕጣኗን አጫጭሳ “እንኮምር” እያለች ነው፡፡ ግን አልበቃትም፤ አላመነችም፤ ተጠራጥራለች፤ ተጨንቃለች፤ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በተለይም አንድነትን ለማጥፋት “ቡና ጠጡ” በማለት የሚላላኩላት የቦርዱ “ምሁራን” ላይ ታች እያሉ ነው። ኃላፊው ለምን ይህንን የተላላኪነት ሥራ እንደፈለጉት ባይታወቁም የቦርዱ አሽከርካሪ ምክትላቸው ግን “የዜግነት” ድርሻውን እየተወጣ ነው፡፡ “ለወገን ደራሹ ወገን” አይደል የሚባለው! ስለዚህ ህወሃት የሰፈረውን “የሚያገለማ ጽዋ” ለመጋት ርኩቻው ደርቷል። ፕሮፌሰርነት ከሚሰጠው ክብር ይልቅ “ተላላኪነት” ኩራት ሆነ!
ሶስት ዓይነት ባርነት

በአገራችን ሶስት ዓይነት ባርነት እንዳለ ይነገራል፡፡ የእነዚህ ባሪያዎች (ባንዶች) ማንነት ገፍቶ የሚወጣው “ምርጫ” በደረሰ ጊዜ ነው፡፡ አንደኛውና የመጀመሪያው ባሪያ “ምርጫ ቦርድ” የሚባለውና ሌሎች መሰል “የተቋም ባሮች” ናቸው፡፡ ሁለተኛው ባሪያ ምርጫ ቦርድን እና ተመሳሳይ ተቋማትን የሚመሩ አመራሮች ናቸው፡፡ ሦስተኞቹ ባሮች ደግሞ ህዝባቸውን ለንዋይ ሲሉ የሚሸጡ አገልጋዮች ናቸው፡፡ በሌላ ቋንቋ ህወሃት የጠፈጠፋቸው፣ ያቦካቸው፣ የሚነዳቸው፣ ሲፈልግ አዋርዶ የሚያባርራቸው ናቸው፡፡ የዘመንና የትውልድ ሁሉ ተጠያቂ ባንዳዎች!

Tuesday, February 3, 2015

ወያኔ የጋረደብንን የመበታተን አደጋ ለማክሸፍ ትግላችንን ማቀናጀትና በአንድ የአመራር ጥላ ሥር ማሰባሰብ ወቅቱ የሚጠይቀን እርምጃ ነው

ትግራይን ከተቀረው የአገራችን ክፍል ለመገንጠልና የትግራይን ሪፑፕልክ ለማቋቋም ራዕይና ተልዕኮ ሰንቆ የዛሬ 40 አመት ደደቢት በረሃ ውስጥ የተፈጠረው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ፡ በለስ ቀንቶት የመንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ ወዲህ፡ በስሙ የሚነግድበትን የትግራይን ህዝብ ጨምሮ በአገራችንና በመላው ህዝባችን ላይ የፈጸማቸው ወንጀሎችና ያደረሳቸው ሰቆቃዎች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም::

ከነዚህ ወንጀሎች ሁሉ የከፋውና ምናልባትም የሚቀጥለውን ትውልድ ጭምር ዋጋ ያስከፍላል ተብሎ የሚፈራው ምዕራባዊያን ቅኝ ገዥዎች አህጉራችን አፍሪካን በተቀራመቱበት ወቅት የአገዛዝ ዘመናቸውን ለማራዘምና ቅኝ የገዙዋቸውን ህዝቦች ሃብትና ንብረት ለመዝረፍ እንዲመቻቸው የተጠቀሙበትን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊስ በምድራችን ተግባራዊ በማድረግ ለዘመናት የተገነባውን የህዝብ አንድነትና የአገር ሉአላዊነት ሊያናጋ በሚችል መልኩ በዘር፤ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍለን የጎሪጥ እንድንተያይ የተፈጸመብን ደባ ነው::

በዚህ ደባ ምክንያት ዛሬ በአገራችን ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሆኔታ ኦሮሞነት፤ ሱማሌነት፤ ትግሬነት፤ አማራነት ፤ ስዳማነት፤ አፋርነት፤ ወላይታነት ፤ ከምባታነት ወዘተ ከዘግነት በላይ ገዝፎ የማንነት መለያና የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚና ማህበራዊ መብቶች መሠረት ሆኖአል:: በዚህም የተነሳ የኦሮሞ ከብት አርቢ ለከብቶቹ ግጦሽ ፍለጋ ወደ ሱማሌ ድንበር ከተሻገረ እንደ ባዕድ ተቆጥሮ ተኩስ ይከፈትበታል፤ አፋር ወደ ኢሳ ከተሻገረ ይገደላል፤ ለቤነሻንጉል በተከለለ ክልል የሰፈረ የአማራ አርሶ አደር የደከመበትን አንጡራ ሃብት ተቀምቶ ይባረራል፤ አኝዋክ ለዘመናት ተከባብሮና ተቻችሎ ከኖረው ከኑዌር ወንድሙ ጋር እንዲጋጭ ተደርጎ በገላጋይነት ሥም የፈደራል ፖልስና የጸጥታ ሃይል በጅምላ እንዲጨፈጭፈው ይፈረድበታል :: በመልካም አስተዳደር እጦት የደረሰበትን መከራና ስቃይ አብሮ ሲጋፈጥ የኖረው የወልቃይት ጠገደ ህዝብ አንተ አማራ አንተ ትግሬ በሚል የዘር ክፍፍል ለመገዳደል ካራውን ስሎ ተቀምጦአል :: ይህ አልበቃ ብሎም የአንድ ብሄር አባላትን በጎሳ ሸንሽኖ የጉጂ ኦሮሞ ከአርስ ወንድሙ ጋር ደም እንዲቃባ ተደርጎአል:: የኦጋዴን የተለያዩ ጎሳዎችም ላይ እንዲሁ::

ወያኔ በጉልበት የጫነብን የመከፋፈልና የመለያየት አደጋ አንድ ቀን ሲያበቃ የነጻነት ብርሃን ፈንጥቆ በሠላምና በመቻቻል የምንኖርበት አገር እንኳ እንዳይኖረን በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች መጠነ ሰፊ የሆነ ድንግል መሬታችንን ለህንድ፤ ለቻይናና ለአረብ ከበርቴዎች በርካሽ ዋጋ በመቸብቸብ በገዛ አገራችን የባዕዳን አሽከሮች ሆነን እስከ ዘለአለሙ እንድንኖር መሠረት ተጥሎአል::

ይህ ሁሉ በደልና መከራ እንዲያበቃ በአገዛዙ ላይ የተቃውሞ ድምጹን ያሰማ ከሥራውና ከኑሮው ተፈናቅሎ በድህነት አረንቋ ውስጥ እንዲጣል አለያም እየታደነና የሽብርተኝነት ታፔላ እየተለጠፈበት ወደ የማጎሪያ ጥቢያዎች እንዲወረወር ተደርጎአል:: በዘርና በቋንቋ በተከለለልን ክልል በፈረቃ የሚደርስብንን አፈናና ሰቆቃ በህብረት ለመቃወም የሚደረጉ ጥረቶች በሙሉ “የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂ፤ ትምክህተኛ ፤ አክራሪ/ጽንፈኛ፤ ጸረ ልማት ወዘተ ” በሚሉ የማሸማቀቂያና የመወንጀያ ቃላቶች ጋጋታ እንዲደናቀፍ ለማድረግ ተሞክሮአል::

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄና የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ጥር 2 ቀን 2007 አመተ ምህረት የፈጸሙት ውህደት ዋናው ምክንያት ከላይ የተዘረዘሩትን ግፎች ለማስቆም በተናጠል ከሚደረግ ትግል በህብረት የሚደረገው ትግል ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑ የፈጠረው ግንዛቤ ነው :: የወያኔ የጥቃት ክንዶች የፈረጠሙት በራሱ ጥንካሬ ወይም የሚተማመንበት ህዝባዊ ድጋፍ በደጀንነት ኖሮት ሳይሆን በኛ መከፋፈልና መለያየት ብቻ እንደሆነ ህዝባችን ከተረዳው ውሎ አድሮአል::

አርበኞች ግንቦት 7 በሚል መጠሪያ ሁለቱ ድርጅቶች በቅርቡ የፈጠሩት ውህደት ከድህረ ምርጫ 97 ጀምሮ ህዝባችን ከደረሰበት ስቆቃ ለመገላገል ተቃዋሚዎችን “ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ” በማለት ሲያቀርብ ለኖረው የድረሱልኝ ጥሪ የተሰጠ የመጀመሪያው ተግባራዊ ምላሽ ነው:: ሁለቱም ድርጅቶች እስከ ዛሬ ምድር ላይ ያደራጁትን የሰው ሃይል ፤ እውቀትና ንብረት አዋህደው በአንድ አመራር ሥር ትግሉን ከዳር ለማድረስ መወሰናቸው በአላማና ግብ ለሚመሰሉዋቸው ሌሎች ተቃዋሚ ሃይሎች ብቻ ሳይሆን ወያኔን ከህዝብ ጫንቃ ላይ በማውረድ ፍትህና እኩልነት በአገራችን እንዲሰፍን እንታገላለን ለሚሉት ሃይሎች ሁሉ አርአያነት ያለው እርምጃ መሆኑ እየተነገረ ነው :: የአርበኞች ግንቦት 7 ውህደት በተፈጸመበት ሥነሥርዓት ላይ አገራቸውን ነጻ ለማውጣት ነፍጥ