Friday, August 30, 2013

“በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ” እንዳይሆን እንጠንቀቅ

ቢከፍቱት ተልባ የሆነውና ላይ ላዩን ሲያዩት ልማት የሚመስለው የወያኔ ኢኮኖሚ “ልማትና እድገት” የገንዘብ ካፒታል የሚያገኘው እንደሌሎቹ በእድት እንደሚገሰግሱ ታዳጊ አገሮች የእንዱስትሪ ሸቀጥ አምርቶ ለአለም ገቢያ አቅርቦና ሽጦ አይደለም። ተሰራ የተባለው ብልጭልጭ ነገር ሁሉ የሚሰራው የድህነት ጌቶች “Lords of Poverty” በሆኑት አለም አቀፍ ተቋሞችና ሀገሮች በሚገኝ እርዳታ ነው። ወያኔ እራሱ በፈጠሩ ችግር ተሰዶ በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊም ለወዳጅ ዘመድ የሚልከው የውጭ ምንዛሬም ሌላው የወያኔ የገንዘብ ምንጭ ነው። በዚህ ላይ የሀገሪቱ የተፈጥሮ ሀብት የሆነውን ለም መሬት በገፍ ለባዕድና ለሀገር ውስጥ የወያኔ ቤተኞች በመቸብቸብ የሚገኝ ገንዘብ አለ። መቼም ኢትዮጵያዊው በገዛ ሀገሩ የኩርማን መሬት ባለርስትና መብቱ ከተነጠቀ ቆይቷል። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለርሰተቹ ወያኔና ጉጅሌዎቹ ብቻ ናቸው።

የሀገሪቱ የገንዘብ ሀብት ብዙ ጊዜ የሚገባው ከግርጌው በተቀደደ ቋት ውስጥ ስለሆነ ለዘላቂ ልማትም ሆነ ገንዘቡን ለሚቀራመቱት ወያኔዎች በቂ አልሆነም።

ይህንን ቀዳዳ ቋት ለመሙላት ወያኔ ሰሞኑን የፈጠረው ዘዴ ህዝቡን የቤት ባለቤት ላደርግህ ስላሰብኩ አስቀድመህ ገንዘብህን አምጣ የሚል ዘዴ ነው። ሃያ-ሰማኒያ አርባ-ስልሳ ወዘተ የሚል ዘዴ ተገኝቷል። ይህ አርባ ስልሳና ሃያ ሰማንያ የሚሉት ፈሊጥ የኢትኦጵያ ደሃ ህዝብ ነገ ያልፍልኛል እያለ ሆዱን ቋጥሮና አንጀቱን አስሮ ያፈራትን ገንዘብ እንዲሰጣቸው የታለመ የጮሌዎች የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘዴ ነዉ።

በተለይ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል ተብሎ የታመነበት 40/60 የሚባል ዘዴ በየኢምባሲው በወረቀት ላይ በተሰሩ ቆንጆ የቤትና የኮንዶሚኒየም ንድፎች አሸብርቆ መጥቷል።

ይህችን የጭልፊት ኢኮኖሚ ማየት የተሳናቸው የዋህ ኢትዮጵያውያን በየባዕድ ሀገሩ ለፍተው ያፈሯትን ጥሪት ይዘው በየኢምባሲው ለምዝገባ ሲጋፉ ማየት እጅግ በጣም ያሳዝናል። ብዙ ኢትዮጵያውያን ይህንን የዝርፊያ ኢኮኖሚ የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ በሚል ፈሊጥም የገቡበት አሉ። ራሳቸውንም ሀገራቸውንም እያዘረፉ መሆኑ የገባቸው አይመስልም። ወያኔ ይልቁንም የገቢያው መድራት ስላስጎመጀው ለውጭ ነዋሪ ያዘጋጀውን 40/60 አቁሞ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ መንገድ እያሰላ ነው።

ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህን የድቡሽት ላይ ቤት እንሰራለን ብለው ያሰቡ ወገኖች ሁሉ የወያኔን ቀዳዳ ኪስ ከመሙላታቸው በፊት ጥቅሙን፤ ጉዳቱንና ትርጉሙን አገላብጠው እንዲያዩ ይመክራል። በተለይ በወያኔ ስር በሚገኝ ንብረት ያልፍልኛል ብለው በስደት ኑሮ ያፈሩትን ገንዘብ የነጻነታቸዉ መያዣ ተደርጎ ለባሰ ውርደት እንዳይዳርጋቸው ግንቦት ሰባት ወገናዊ ምክሩን ይመክራል።

ቤት አልባ ሆኖ በየመንገዱ ላይና በየደሳሳ ጎጆዉ ታጉሮ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወገናችን በየዕለቱ እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከነሱ እየተዘረፈ በሚሸጥ ንብረት ሀብት ለማፍራት መሞከር ለህሊናም የሚቀፍ ነው።

የወያኔ የቤት ስራ ፕሮጀክት ገንዘብ መልቀሚያና ጥቂት ባለሟሎቻቸውን መጥቀሚያ እንጂ ለዚህ ሁሉ የውጭ ነዋሪ የሚደርስም አይደለም። ወያኔ አስቀድሞ ከወለድ ነጻ የሆነ ገንዘብ ከሰበሰበ በኋላ ገንዘቡን ተጠቅሞ ከአምስትና አስር
አመት በኋላ ቤቱንም ገንዘቡንም ማግኘት ላይቻል ይቻላል። ወያኔም ተጠያቂነትን የማይወድ አገዛዝ መሆኑን ካሁኑ አለመገንዘብም ራስን ጨፍኖ ለመሞኘት መፍቀድ ነው።

የወያኔ 40/60 ገንዘብ መሰብሰቢያ እንጂ ህዝብ መጥቀሚያ አይደለም። ወያኔዎች ሊጠቅሟቸው የሚፈልጉ ዜጎችን ከፈለጉ በየጎዳናው ላይ ያገኟቸዋል ለምን እነሱን አየረዷቸዉም?

በተለይ በውጪ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በፍጹም ድህነትና የወያኔ ዝርፊያ ተዋርዶ የሚኖረውን ህዝባችንን እያየን የዚህ ግፈኛ መንግስት መሳሪያ ከመሆን አልፈን ራሳችንንም ለተዋራጅነት እንዳንዳረግ እንጠንቀቅ!

ድል ለኢትዮጵያ ሀዝብ!!

Thursday, August 29, 2013

የእኛ “መንግስት”

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም” ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1 ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡

እናም የስርዓቱን የአስተዳደር ዘይቤ ያለፍርሃት አደባባይ ካዋልነው የቀድሞ ገዥዎቻችን የተጓዙበትን ጎዳና እየተከተለ መሆኑን ለመተንተን የምሁራንን ጥናት መጠበቅ ግድ አይለም፤ ምክንያቱም ለዓመታት የተመለከትነው እውነታ የሚነግረን የአመራሩን እና በዙሪያው የሠፈሩ የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦችን ብልፅግና ታሳቢ ያደረገ፣ ከታግሎ መጣል ህግ የተቀዳ፣ የራስ ሀገርንና የራስ ሕዝብን በምርኮ ያስገበረ ፖለቲካ መንበሩን ነው፤ ገብር፣ ገብር፣ ገብር…!!

ዛሬ መንገድ ዳር ረሀብ አዙሮ የጣለው ወንድምህ ስቃይ እንደ ጥላ የሚከተልህ፤ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ በጠኔ ተሸንፈው መመልከቱ የሰርክ አሳዛኝ ክስተት የሆነብህ ከሰው ሰራሽ ችጋር፣ ከሰው ሰራሽ የቀዬ ፍንቀላ፣ ከሰው ሰራሽ እርዛት… የመነጨ መርገምት እንጂ የሰማይ ቁጣ አይምሰልህ፤ እመነኝ መለስም ሆነ ተተኪዎቹ ስኬት አድርገው የሚሰብኩትም ይህንን ነው፤ ‹ሀገር አቀናን!› የሚሉትም ይህንን ነው፤ ሰሞኑን የሚያሰለቹህ ተረኛ ምሁራንም ‹‹ትምህርትና ጤናን በተመለከተ መለስ ‹እልል› የሚያስብል ሥራ ሰርቷል›› የሚሉህ ጣራና ግድግዳ እየቆጠሩ ነው፤ ይህ አይነቱ መደዴ ሙገሳም ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ሪፖርት ለማዘጋጀት ከሚረዳ ቁጥር የዘለለ አበርክቶ አንደማይኖረው አትዘንጋ፡፡

እውነት እውነት እልሀለሁ፡- ይህ የሆነበት ብቸኛው ምክንያት መንግስት በስልጣን ላይ ስለሚቆይበትመንገድ ብቻ መጨነቅን ግዴታው በማድረጉ ነው፤ ይህንን ለመረዳትም እያገባደድን ባለው ክረምት የመንግስት ትኩረት በምን ላይ አንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃን ጨርፌ ላሳይህ፡፡

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የእስልምና እምነት ተከታዮች መንግስት በሃይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱን በመቃወም እና የታሰሩ ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቅ እያደረጉ ያለውን ትግል በሰላማዊ መንገድ አጠንክረው ሲቀጥሉ፤በተቃራኒው ‹‹ፀጥታ አስከባሪዎች›› አንዳንዴ በጥይት፣ አንዳንዴ በአስለቃሽ ጢስ፣ አንዳንዴ በማጋዝ…ምላሽ ሲሰጡ…

በርግጥ መንግስት ከኃይል እርምጃው በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን (በምን አግባብቶ ወይም በምን አስፈራርቶ እንደሆነ ባይታወቅም) ወደ አደባባይ በማስወጣት መብት ጠያቂዎቹን ከ‹‹አክራሪ››ነት እና ‹‹ወሃቢዝም››ነት ጋር አያይዘው የውግዘት በረዶ እንዲያዘንቡባቸው እያደረገ ነው፡፡ ኢቲቪም ይህንን ኩነት እየተከታተለ ማራገቡን ቀጥሎበታል፤ ‹‹የቲፒ ከተማ ነዋሪዎች ‹አክራሪዎችን አወገዙ››፤ ‹‹በደቡብ ወሎ ኩታ በር ዞን አንድነት ፓርቲ ህገ-ወጥ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰልፍ ተካሄደ››፤ ‹‹የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ‹የሼሁ ግድያ ድራማ አይደለም› አሉ፣ ‹የሼህ ኑሩ ኢልም ነው፣ የአሸባሪዎች ብር ነውም›ብለዋል››፤‹‹የመርሀቤቴ ነዋሪዎች ፅንፈኞችን በመቃወም የአቋም መግለጫ አወጡ››፤…

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- አንድነት ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የ‹‹ፀረ-ሽብር ሕጉ›› እንዲሰረዝና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ እና የአዳራሽ ስብሰባዎችን እያካሄደ ነው፤ መንግስትም አንዳንዴ የአፀፋ የድጋፍ ሰልፍ ሲያካሄድ፤አንዳንዴ የአዳራሽ ስብሰባዎች ከመካሄዳቸው አስቀድሞ ‹መጋኛ› ሲሆንባቸው፤ አንዳንዴም የአስተባባሪዎቹን መኪና ጎማ ሲያፈነዳ፤ አንዳንዴም አዳራሽ ከልክሎ ሲያደናቅፋቸው… መዋሉ ፋታ የነሳው ይመስላል፤ በወላይታ የተጠራውን የአዳራሽ ስብሰባም ‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ ቦታ እንዴት ተደርጎ!›› ያሉ ካድሬዎች የአንድነት ሰዎችን አዋክበው ስብሰባውን አክሽፈዋል፤

ክረምቱእንዲህእየተገባደደነው፡-ገዥው ፓርቲ ‹የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ አንደኛ ሙት ዓመት አከብራለሁ› በሚል መላ ኢትዮጵያን ችግኝ መትከያ፣ መላ ዜጎቿን ደግሞ ወደ አርሶ አደርነት በአስማት የቀየራቸው አስመስሏቸዋል፤ቴሊቪዥንና ራዲዮንም አስፈላጊነታቸው በየመንደሩ ችግኝ መተከሉን እየተከታተሉ መዘገብ ብቻ እስኪመስል ድረስ እንዲህ ሲሉ ጀምበር ወጥታ ትጠልቃለች፡- ‹‹የላይ አርማጮህ ነዋሪዎች ችግኝ ተከሉ››፣ ‹‹በመቀሌ ከተማ ‹ዘመቻ መለስ› በሚል የችግኝ ተከላ ተካሄደ››፣ ‹‹አቃቂ ኮረብታ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ችግኝ በኦሮሚያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ተተከለ፤ ቦታውም ‹መለስዜናዊ ኮረብታ› ተብሎ ተሰይሟል››፣ ‹‹በምዕራብ ሀረርጌ አስራ ሰባት ሚሊዮን፣ በወልበራ አስራ አራት ሚሊዮን ችግኝተ ተክሏል››፣ ‹‹በመንዝ ላሎ ወረዳ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግኝ ተከላ ተደርጓል››፣ ‹‹የብአዴን አመራርና ካድሬ በባህር ዳር ከተማ በቢሊዮን የሚቆጠር ችግኝ ተከሉ፤ በፕሮግራሙ ላይ ጓድ አዲሱ ለገሰ ‹ችግኝ የምንተክለው አገሪቱ በአረንጓዴው ልማት በአለማችን ማግኘት የሚገባትን ቦታ እንድታገኝ ለማድረግ ነው› ሲል፣ ጓድ በረከት ስምዖን ደግሞ ‹ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአለማችን በአንድ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ችግኝ እየተከሉ ያሉባት ብቸኛ ሀገር ናት› ብሏል››፤‹‹ዝክረ መለስ 1ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ከሐምሌ አስራ አምስት ቀን ጀምሮ ሁሉም ቀበሌዎች በስሙ ‹ፓርክ› ሰይመው ችግኝ ተከላ እያካሄዱ›› መሆኑን ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ መግለፁን የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፤ ‹‹በወልቂጤ ከተማ በተደረገው ችግኝ ተከላ ላይም አንዲት ወጣት ‹መለስ ለሴቶች የተለየ አመለካከት ነበረው›› ማለቷም በዘገባው ተጠቅሷል፤ …ማን ነበር የመለስ ራዕይ ‹ችግኝ መትከል ነው› ያለው? …ኢህአዴግ ይሆን?

ከዚሁ ጎን ለጎን (አሁንም ሙት ዓመቱን ለማሰብ) በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የእግር ጉዞ ተደርጓል፣ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትም ተካሄዷል፤መነሻውን መቀሌ፣ መድረሻውን አዲስ አበባ ያደረገ ‹‹የመለስ ቱር አረንጓዴ ልማት›› የብስክሌት ውድድርም ሊጠናቀቅ ገና አንድ ሳምንት ይቀረዋል፤ በብሄራዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ቀንለሃያ አንድ ጊዜ ይሰማ የነበረው የመድፍ ድምፅም፣ የመለስን አንደኛ ሙት ዓመት ለማብሰር ተተኩሷል፤ …በግድ አልቅሱ፣ በግድ ተዝካር አውጡ፣ በግድ ችግኝ ትከሉ፣ በግድ ተወያዩ፣ በግድ አደባባይ ውጡ፣ በግድ የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ጎብኙ፣ በግድ.. ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ ለሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ከፍተኛ መምህራን ‹የአቅም ግንባታ ስልጠና› እየሰጡ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምሁራኖቹን ማሰልጠን ያስፈለገበት ምክንያት ‹‹ብቃት ያለው ምርጥ የተማረ ኃይል ለማፍራት››መሆኑን ቢነግርህ አይግረምህ፤ ይህ ኢትዮጵያ ነውና የዐዋቂነት ማረጋገጫው መማር፣ ማንበብ፣ መመራመር… አይደለም፣ የፖለቲካውን ኃይል መያዝ እንጂ፤ ‹ስልጣን ላለው ሁሉምሚስጥረ-ጥበብይገለፅለታል› እንዲል አብዮታዊ ዲሞክራሲ መለስ ዜናዊም በሁሉም መስክ ‹አስተማሪ› ነበር፤ የህግ ባለሙያዎችን ሰብስቦ የሀገሪቱን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ትርጓሜ ሲተነትን ደጋግመህ ሰምተኸዋል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ለግብርና ባለሙያዎች ከውሃ ማቆር እስከ በላብራቶሪ የሚዳቀል ምርጥ ዘር ድረስ ባሉጉዳዮችዙሪያ የሁለት ቀን ማብራሪያ መስጠቱን ታስታውሳለህ፤ እመነኝ ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ነው እያደረገ ያለው፤ የሆነ ሆኖ ኃ/ማርያም ለምሁራኖች ከሙያቸው ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ጭምር በሰጣቸው ስልጠና ላይ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር ‹‹የኢንዱስትሪዎች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ፣ በክፍል ውስጥ የምናስተምረውን ንድፈ ሃሳብ በተግባር ለማሳየት እንቅፋት ሆኖብናል››፤ በርግጥጠቅላይ ሚንስትሩ‹‹መፍትሄ››ያለውን የተናገረው ብዙም ሳይጨነቅ ‹‹እኔ ኢንዱስትሪን ‹ዲፋይን› የማደርገው ግብርናም ኢንዱስትሪ ነው ብዬ ነው››በማለት ነበር፤…ግና!ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በተጨባጭ አላብራራም፡፡ለምሳሌ ህክምና የሚያጠና ተማሪ በምን መልኩ በሞፈርና ቀንበር የተግባር ልምምድ ማድረግ እንደሚችል፤ወይም ፖለቲካ ሳይንስ የሚያጠና ተማሪ የተግባር ልምምዱን በግብርና ኢንዱስትሪ እንዴት ሊወጣው እንደሚችል? ማለቴ ነው፡፡

ለዓመታት በርካታ ምሁራን ብቃት አልባ ተማሪዎች እንደ ሰማይ ከዋክብት የመብዛታቸው መንስኤን ከትምህርት ፖለሲው ጋር የሚያነፃፅሩበትን ሀቲት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ባገኘው የሀገር መሪነት ስልጣን ገልብጦ በዩንቨርስቲ ቆይታው መምህራኖቹ የነበሩትንም ጭምር ‹‹አቅም አንሷችኋልና-እገነባችኋለሁ›› ሲል ከመስማት የከፋ እንደ ሀገር ክሽፈት የለም (በነገራችን ላይ ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ ቴውድሮስ አዳህኖም፣ ሶፍያን አህመድ በአጠቃላይ ሁሉም የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አንድ ህንዳዊ ፕሮፌሰር በኢህአዴግ ጽ/ቤት ‹‹ልማታዊ መንግስት›› እንዴት ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ሲተነትንላቸው፣ እነርሱም ደብተርና እስክርቢቶ ይዘው በንቃት ሲከታተሉ የቴሌቪዥ ዋና ዜና ሆኖ የቀረበበትን ምክንያት ዛሬም ድረስ ሊገለፅልኝ አልቻለም፤ በተለይም ፕሮፈሰር እንድርያስ እሸቴ ‹‹በቃሉ የፀና…›› በሚል ርዕስ መለስን አስመልክቶ በተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም ላይ ‹‹በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልማታዊ ስርዓተ መንግስት ‹ዴሞክራሲያዊ ሊሆን ይችላል፤ መሆንም አለበት› ብሎ በአደባባይ የተከራከረው እኔ እስከማውቀው ድረስ መለስ ነበር›› ማለቱን፣ ተተኪዎቹ ፍልስፍናውን ገና እየተማሩት ከመሆኑ አንፃር ስናየውሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ጉዞው ወዴት ነው? ያስብላል፡፡ …ከቶስ በተማሪ ፖለቲከኛ የሚተዳደር ሕዝብ ከኢትዮጵያ በቀር ወዴት ይኖራል?)

ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የህዳሴውን ግድብ ከዳር ለማድረስ በቂ ገንዘብ ስላልተገኘ ተደጋጋሚ የቦንድ ሽያጭ እየተካሄደ ነው፤ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞችም በካድሬ ባልደረቦቻቸው ጫና በድጋሚ ቦንድ ለመግዛት መወሰናቸው ተሰምቷል፤ በርግጥ ከፍተኛ የኢህአዴግ የአመራር አባላት በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቦንድ እንዲገዙ ለመቀስቀስ የአዘጋጇቸው ስብሰባዎች ‹‹ቅድሚያ የዜጎች መብት ይከበር›› ባሉ የሀገራችን ልጆች መክሸፉም የክረምቱ የመንግስት ዋና ሥራ ነው፤ ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- በነቢብ የኢትዮጵያ፣ በገቢር የገዥው ፓርቲ የግል ንብረት የሆነው ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፉት ሶስት ወር ብቻ ከሃያ በላይ ‹‹ዶክመንተሪ ፊልም›› አሳይቷል (ገና ይቀጥላልም) በርዕሳቸው እንደሚከተለው እንዘርዝራቸው፡- ‹‹ኢፍቲን›› በሶማሊያ ላይ የሚያጠነጥን፣ ‹‹የጥቁር ህዝቦች ልሳን (መለስ በአፍሪካ)››፣ ‹‹ከፓን አፍሪካ እስከ አፍሪካ ህዳሴ›› የጠቅላይ ሚንስትር መለስን ህይወት የሚዳስስ፣ ‹‹ዘመነ አፍሪካ››፣ ‹‹የአፍሪካ ልሳን-መለስ››፣ ‹‹መለስ ማን ነው?››፣ ‹‹ሀገሬ-ቤቴ››፣ ‹‹ባለራዕዮቹ›› ስራ ፈጠራ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ደውል›› እና ‹‹ደውል 2›› ህገወጥ-የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ (በተለያያ ጊዜ የተላለፉ)፣ ‹‹የዲያስፖራ የልማት እንቅስቃሴ››፣ የካርታ ስራ ድርጅትን በተመለከተ፣ ‹‹የጥልቅ አስተሳሰብ ባለቤት›› በፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን፣ ምድር ባቡር ኮርፕሬሽንን በተመለከተ፣ ‹‹ያልተለመደ ጉብኝት›› የአዲስ አበባ አስተዳደር የአምስት ዓመት የመንግስት ግንባታዎችን በተመለከተ፣ ‹‹ሼህ ኑር ለምን ሞቱ?›› የደሴውን ሼህ ኑር ይማምን ግድያ በተመለከተ፣ ‹‹የተስፋ ስንቅ››፣‹‹በቃሉ የፀና›› በድህረ መለስ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ያልተጠኑ ገፆች›› በመለስ ዜናዊ ህይወት ዙሪያ (በርግጥ በዚህ ፊልም እህቱ ጠላ፣ ወንድሙ አንባሻ በመሸጥ መተዳደራቸውን በምስልም በድምፅም ማቅረቡ ምን የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል፤ …ምናልባት እንዲያ እየዘረፈ ለቤተሰቦቹ ‹ሶልዲን› የማይሰጥ ‹ቆነቋና› ነበር ለማለት ይሆን? ወይስ ለአዜብ መስፍን ‹የወር ቀለባችንን እንቸገራለን› የአንድ ሰሞን ማስተዛዘኛ ምስክር ፍለጋ ነው?

በጥቅሉ ለኢህአዴግ ሕዝብን የማስተዳደር፣ ሀገርን የመምራት መገለጫ ይህ ነው፤ ሌላ አይደለም፤ ግና! ለዘመናት ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ዛሬም መጮኻቸውን አላቋረጡምና እነሆ እንዲህ ቀጥለዋል፡- ሀገር ማስተዳደር ‹መለስ ጀግና ነበር› እያሉ ማሰልቸት ነውን? የመንግስትስ ስራ (ግዴታ) ምንድር ነው? ሀገሪቱን ‹‹መለስ-ፓርክ›› ወደሚል ስያሜ ከመቀየራችሁ በፊት፣ ለጤፍ ዋጋ አለቅጥ መናር ምክንያቱን ስለምን መመርመር ተሳናቸው? ሀገሪቱን በ‹አራጣ› እንደያዘ ስግብግብ ነጋዴ በሚሊዮኖች ህይወት ላይ የማይሞላ ‹ሳፋ› ደቅኖ አዋጣ፣ ግዛ፣ ክፈል፣ ገብር… እያለ የሚያስጨንቀው ማን ነው? ስለመለስ ‹የሃሳብ ምጡቅነት› መስካሪ ምሁራኖቻችን ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ስንት ሚሊዮን እንደደረሱ እና እልፍ አላፍት ታዳጊዎቻችን በሴተኛ አዳሪነት እንደተሰማሩ የምትነግሩን መቼ ነው?እንዲህ የመሆኑ ምክንያትስ በማን ይሆን? ‹የሁለት ዲጂቱ›ዕድገት ሸክምን የማለዘብ አቅም ከሌለውፋይዳው ምንድር ነው? ‹ሳቅ ትዝታ› ስለሆነባቸው ጎጆዎች ለምን አትነግሩንም? መለስ ‹ያለመለማት› ኢትዮጵያ ወዴት ትሆን? ‹ፖለቲካ› ማለትስ ይህ ነውን? …ነጋ ድራስ ገ/ህይወት እንዳሉት ‹‹…መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡›› የመተራረሚያው ጊዜም በጣም ያለፈ ይመስለኛል፡፡ አገዛዙን ‹እንደ መንግስት› መቀበሉም እንዲሁ፡፡

የሕወሐት ባለስልጣናት የአሜሪካ ቆይታ፤ የከዱ አሉ!!

ከኢየሩሳሌም አርአያ

በአባይ ወልዱ የሚመራውና ሰባት ከፍተኛ የሕወሐት ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን በአሜሪካ አራት ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠመው በስፍራው የተገኙ ምንጮች አስታወቁ። ቡድኑ በዋሽንግተን ኢትዮጲያ ኤምባሲ በጀመረውና በመቀጠል በላስቬጋስ፣ ሲያትልና ካሊፎርኒያ ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ “አላማ” አድርጎ የያዛቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነሱም፥ “የመለስ ፋውንዴሽን፣ የአባይ ግድብና የ40/60 የቤቶች ግንባታ.” ሲሆኑ፣ ለነዚህ ማስፈፀሚያ “ገንዘብ አዋጡ” የሚለው ዋናው ግብ እንደነበር አስረድተዋል። በተለይ ደግሞ « በትግራይ ተወላጁ ዘንድ ሕወሐት የለም፣ ተከፋፍሏል፣ ተዳክሟል፣ ፓርቲው ሰው የለውም፤» የሚለውን እራሱ ቡድኑ በማንሳት ለገዛ ጥያቄው መልስ ሲሰጥ « ሕወሐት አሁንም ሃይል አለው፤ አልተዳከመም» በማለት አድራጊ- ፈጣሪ በመሆን ስልጣኑን በበላይነት ተቆጣጥሮ እንደያዘና ቡድኑ የመጣውም “አይዟችሁ” ለማለት እንደሆነ መገለፁን በቅርብ የተከታተሉት ምንጮች አስታውቀዋል። ቡድኑ በተጨማሪም ፥ « ልማት አልምተናል፤ ትግራይ እየለማ ነው፤ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረገነው ነው» ከማለቱ ባሻገር « በትግራይ ተወላጁ ላይ አደጋ ተደቅኗል፤ የሙስሊሙ፣ የትምክህተኞችና የሽብርተኞች አደገኛ እንቅስቃሴ እያንዣበበ መሆኑን፣…የተደቀነብህን አደጋ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤ ያለበለዚያ ግን ሊያጠፉህ ነው፤» ሲሉ መናገራቸውን የገለፁት ምንጮች አክለውም፣ « አባላት የሆናችሁ ተወደደም ተጠላ መሬትና መኖሪያ ቤት እንሰጣችኋለን፤ ለዚህም ከእኛ ጎን መሰለፍ አለባችሁ» በማለት ሊሸነግሉ መሞከራቸውን ጠቁመዋል።

ከዋሽንግተን ስብሰባ (ለሁለት ተከፍሎ ነው የተካሄደው) በኋላ ወደ ሶስቱ ከተሞች ተከፋፍለው እንደሄዱ ሲታወቅ፥ ሲያትል አቶ ብርሃነ ማረት፣ እንዲሁም ላስቬስጋስ አባይ ወልዱና ተክለወይኒ አሰፋ መሄዳቸው ታውቋል። በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ የገጠማቸው እነአባይ ስብሰባው ከቀኑ 2፡00 ሰዓት ይጀመራል ተብሎ ከአራት ሰዓት በኋላ ዘግይቶ አመሻሽ ላይ መጀመሩን ምንጮች ገልፀዋል። ስብሰባው ሲጀመር ከላይ የተገለፁትን ጉዳዮች ያደመጠው ተሰብሳቢ ተከታዮቹን ጥያቄ አቀረበ፤ « ዴሞክራሲ አለ ትላላችሁ፣ ነገር ግን ዴሞክራሲ የለም፤ በሃሳብ የሚቃወማችሁን ታስራላችሁ፣ ታንገላታላችሁ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ ታካሂዳላችሁ፤ ከእናንተ የተለየ ሃሳብ ያለውን ትፈራላችሁ፤ ለምንድነው ይህን ሁሉ የምታደርጉት?….በማ.ረ.ት.(ማህበር ረድኤት ትግራይ) በትግራይ ሕዝብ ስም የምትሰበስቡትን ገንዘብ ለአራጣ ብድር እና ለፖለቲካ መጠቀሚያ በመሳሪያነት እያዋላችሁት ነው። ለምን?….ትእምት (ኤፈርት) ማነው ባለቤቱ?..በማን ነው የሚመራው?..ማነው የሚቆጣጠረው?..ለመሆኑ ኦዲት ተደርጎ ያውቃል ወይ?..እነማናቸው እየተጠቀሙበት ያለው?» የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ጥያቄዎች እንደነበሩ ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን፣ አባይ ወልዱ « እኔ አልመልስም፣ ተ/ወይኒ መልስ ይስጥበት» ቢሉም ነገር ግን ግልፅና አግባብ ያለው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ወደ ማመናጨቅና ቁጣ ያመሩት ተ/ወይኒ በዚህ ድርጊታቸው በርካታ ተሰብሳቢዎችን እንዳሳዘኑ አስረድተዋል። በዚህ የተበሳጨው ተሰብሳቢ « ጥያቄያችን አልተመለሰም» በማለቱና ሁከትና ያለመደማመጥ በማየሉ ስብሰባው እንዲቋረጥ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮች፣ የጥያቄና ተቃውሞው መብዛት ያስደነገጣቸው ባለስልጣናቱ የመረጡት ማምለጫ በላስቬጋስ ተወካያቸው በሆነውና መድረክ ሲመራ በነበረው አቶ ተወልደ በኩል፥ « አዳራሹን የተከራየንበት ሰአት አብቅቷል፤ ስለዚህም ስብሰባው አብቅቷል » በማለት በአስቂኝ ሰበብ መቋረጡን አያይዘው ገልፀዋል። እነአባይ ከአዳራሹ ሲወጡ ቀድሞ ውጭ ሆኖ ይጠብቃቸው በነበረው ተሰብሳቢ ውግዘትና ስድብ እንደደረሰባቸው ያስታወቁት ምንጮች « ሌባ..ሌባ…ሙሰኞች..» የሚሉ ተቃውሞዎች ጎላ ብለው እንደተሰሙ አመልክተዋል።

ስብሰባዎቹን የታዘቡ ወገኖች በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል፤ « በአንድ በኩል ልማት እያካሄድን ነው፤ እያሉና ገንዘብ እየጠየቁ በሌላ በኩል “ትግራዋይ አደጋ ተደቅኖብሃል፣ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤” ማለት እርስ በርሱ የሚጋጭና ድጋፍ የማግኛ የፖለቲካ የፖለቲካ ቁማር ነው። ያልተጠየቁትን የፓርቲውን ህልውና (ስለ ሕወሐት) አንስቶ መነገሩም አስገራሚና አጠያያቂ ነው።» ሲሉ ትዝብታቸውን የጀመሩት እነዚህ ወገኖች በማያያዝም፥ « እነዚህ ሰባት ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ የመጡት ከነዘመዶቻቸው፣ ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ሲሆን፣ ባለስልጣናቱ የመንግስት ወኪሎች እንደመሆናቸው – በማን ገንዝብ ነው የሚንቀሳቀሱት?..የሚለው መጠየቅ አለበት። በሕዝብ ገንዝብ እየተንፈላሰሱ እንደሆነ ግልፅ ነው። የትግራይ ተወላጁን ብቻ ለይተው ስብሰባ የሚጠሩት ለምንድነው?…በእርግጥ ስላሰቡለት ነው?…የሚሉት ሲፈተሹ .መልሱ በጭራሽ አይደለም ነው። አላማቸውና ትኩረት የሰጡት የትግራይ ተወላጁን እየተንከባከቡት እንደሆነና ተጠቃሚ መሆኑን ለማሳየት በመፈለግ፣ እግረ-መንገዳቸውን ከቀሪው ኢትዮጲያዊ ወገኑ ጋር በመነጠል..ድጋፍ ለማግኘትና በውስጣቸው የተፈጠረውን ቀውስ በዚህ በኩል ቀዳዳውን ለመድፈን የሚደረግ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ስልት ነው። ..ደግሞስ ሕወሐት “አጋር” ከሚላቸው ብ.አ.ዴ.ን፣ ኦ.ህ.ዴ.ድ.፣ ደቡብ ሕዝቦች ተለይቶ፣ በሕዝብ ገንዘብ ስብሰባ የሚጠራበትና ያሻውን የሚያደርግበት አግባብ ምንድነው?..የሚለው ከዚህ ጋር መታየት ያለብት ነው። ፖለቲካዊ ፍጆታና ማንአለብኝነት በፓርቲው በመነገሱ እንደሆነ ደግሞ ግልፅ ነው።» ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ አሜሪካ ከመጡት ሰባት የሕወሐት ባለስልጣናት መካከል- ማለትም አባይ ወልዱ፣ ብርሃነ ኪ/ማሪያም፣ ተ/ወይኒ አሰፋና ዳንኤል አሰፋ በዋነኛነት ሲጠቀሱ፣ ከሰባቱ ሶስቱ ስብሰባውን ሳያካሂዱ ከቡድኑ ተገንጥለው በአሜሪካ መቅረታቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል። ቤተሰቦቻቸውን ይዘው (ልጆቻቸውን ጭምር) በመምጣት አሜሪካ ጥገኝነት ጠይቀው መቅረትን የመረጡት ባለስልጣናት ውስጥ የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባላት እንዳሉ ያረጋገጡት ምንጮች በቅርቡ ዝርዝሩን ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

ምንጭ፡ ecadforum.com

ህዝበ-ሙስሊሙን ያለአግባብ በስጋት መፈረጅ፤ ማዋከብና መግደል በአፋጣኝ ይቁም!!

የነፃነት ጐህ

የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት አንቀጽ 11 ቁጥር 3 ”መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ ሀይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ” ይላል፡፡በሀገራችን ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ በወታደራዊው ደርግ እንዲሁም አሁን ስልጣን ላይ ባለው ወያኔን ጨምሮ ሁሉም ሀይማኖቶች ከመንግስት ጣልቃገብነት ነፃ ሆነው አያውቁም። ፍትህ፣ ነጻነት፣ እኩልነት እና አንድነት ለብዙ ሀይማኖቶች መሰረታዊ እሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ እሴቶች ላለፉት 22 ዓመታት በዘረኛው የወያኔ መንግስት እየተሸረሸሩ እና እየተመናመኑ ዛሬ ከነአካቴውም ለመጥፋት ተቃርበዋል፡፡ ስለመሰረታዊ የሰው ልጅ መብት እና ነጻነት እንዳይወራ የወያኔ የጥይት አፈሙዞች በእያንዳንዱ ሰው እና የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ተደቅኗል፡፡የእምነት ቦታዎችንም ሳይቀር በመድፈር ህዝበ-ምዕመኑ የኔ የራሴ የሚለው የአምልኮ ቦታ እና የአምልኮ ስርዓት እንዳይኖረው እያደረገ ነው።

ወያኔ አምባገነናዊ ስርአቱን ለማስቀጠል ሲል የዕምነት ተቋማትንና መሪዎቹን በቁጥጥሩ ስር ሲያደረግ ኖሯል፡፡ ይህ አንባገነናዊ ድርጊት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይም ተግባራዊ በመደረጉ ምዕመናኑ የመንግስትን ድርጊት በመቃወም ላለፉት ሁለት ዓመታት ጠንካራ ሰላማዊ ትግል አድርገዋል፤ እያደረጉም ይገኛሉ፡፡ መንግስት አለመግባባቱን ለመፍታት የቀረቡለትን ሶስት ጥያቄዎች ከመፍታት ይልቅ በማን አለብኝነት የትግሉን ግንባር ቀደም መሪዎች ከማሰር ባለፈ በምዕመናኑ ላይ ኢሰብአዊ ጥቃቶችን ማድረሱ የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡  ለወያኔ ህገመንግስትን የመጣስ ድርጊት አዲስ ባህሪው ባይሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣውን ማጠናከሩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል፡፡ ይህ የመንግስት ሀይሎች ድርጊት ችግሩን ከማባባስ ባለፈ የሚያመጣው መፍትሄት አይኖርም፡፡

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላነሷቸው ግልፅ የመብት ጥያቄዎች ብልሀት የተሞላበት ምላሽ መስጠት ያቃተው ወያኔ እየወሰዳቸው ያሉት ኢህገመንግስታዊ እርምጃዎች፤ በሙስሊሙ ሕብረተሰባ ላይ እየደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ከመንግስት ሌላ ተጠያቂ የሚደረግ አካል አይኖርም፡፡ ስለሆነም ይህ አይነቱ ህገወጥና ሀላፊነት የጎደለው ድርጊት እንዳይቀጥል ማድረግ ከተጠያቂነት ያድናል፡፡ መንግስት የተበደሉ ዜጎችን ቅሬታ በማጣራትም በህገወጥ ድርጊት በፈፀሙ ሃይሎቹ ላይ በአፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡

ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ችግሮች ሲከሰቱ ሃይማኖታዊ ወይም መንፈሳዊ የሆኑ መፍትሔ ማፈላለግ ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡ በእምነት ተቋማት ውስጥ ለሚነሱ ጥያቄዎች ፖለቲካዊ መልስ መፈለግ ችግሩን ከማስፋፋትና ወደ አላስፈላጊ ውዝግቦች ከመክተት ውጪ የሚፈጥረው በጎ ለውጥ አይኖርም፡ ፡ የቤተ-ክርስቲያን አለመግባባቶችን ቤተ-መንግስት ለማስታረቅ ሲሞክር ምን ይፈጠር እንደነበር ታሪክ ደጋግሞ አሳይቶናል። በቅርቡ እንኳ በዋልዳባ ገዳምና በምእመናኑ ላይ የተቃጣው ሰይጣናዊ፤ በትዕቢትና በማናለብኝነት የእምነትን ቀይ መስመርን በመጣስ የተወሰደ ጥቃት ሁለቱንም የወያኔ ቁንጮዎች መለስ ዜናዊንና አባ ፓውሎስን ግብአተ መሬት ማፋጠኑ ይታወሳል። መንግስታዊ ጣልቃ ገብነቶች ከእለት ወደ እለት እየገዘፉና እየጠነከሩ ሲመጡ የችግሮች ስር መስደድም የዚያኑ ያህል እየከፋ ይመጣሉ፡፡ ስለዚህ በእስልምና እምነት ላይ እየተደረገ ያለው መንግስታዊ ጣልቃ ገብነት በሀገሪቱ ህገ-መንግስት ላይ የተገለፀውን መንግስትና ሀይማኖት መለያየታቸውን የሚጥስ በመሆኑ አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃ ይወሰድ ዘንድ ግድ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በክርስትና እምነት እንደተደረገው ሁሉ፤ የህዝበ ሙስሊሙ ፀሎትና ልመና ጣልቃ ገብተው እየበጠበጡ ያሉ አምባገነኖች ላይ መቅሰፍት እንደሚያወርድ ጥርጥር የለውም።

በአወሊያ መጅሊሱ እንዲወርድ ሲባል የተጀመረው ሰላማዊ አቀራረብ አሁን ከአዲስ አበባም አልፎ ወደሌሎች ክፍለ ሀገራት  ደርሶ መሳሪያ አማዟል፡ ፡ ለዚህም ማሳያ በቅርቡ በመዲናችን አዲስ አበባ፤ ደሴና ኮፈሌ ላይ የመንግስት ሃይሎች በንፁሃን የሙስሊም ወገኖች ላይ ያደረሱት መጠነ ሰፊ ጥቃትና ግድያ መጥቀስ ይቻላል። በዚህም ሊያበቃ እንደማይችልም ሁኔታዎችን ተመልክቶ መገመት ይቻላል፡፡ ፖለቲካዊ ማንነት ባላቸው ግለሰቦችና ካድሬዎች ቤተ-እምነቶችን መምራት የኋላ ኋላ ይዞ የሚመጣው መዘዝ ሀገራዊ ቀውስ ነው፡፡ ለተቃውሞ የወጣውን ህዝበ ሙስሊም ሰለፊያ በሚል ቅፅል መጠሪያ ስም በመስጠት ዓላማቸውንም ከሽብር ጋር በማያያዝ መፈረጅ ሁኔታውን ከማባባስ ውጪ ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም፡፡

ሕጋዊ መብትን በግልም ሆነ በኅብረት መጠየቅ ሽብርተኛ አያደርግም፤ ሽብርተኛ የሚያደርገው መብታቸውን የሚጠይቁትን መግደል፣ መደብደብና ማሰር ነው፤ ዓለማዊውን ሥርዓት የማይነካውን፣ ከአምላኬ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር የመረጥሁትን መንገድ አክብሩልኝ፤ በሌላ መንገድ ወደአምላኬ እንድሄድ አታስገድዱኝ ማለት ሽብርተኛነት አይደለም፤ ሽብርተኛነት የሚሆነው በሰዎች ላይ ባዕድ የሚሉትን እምነት መጫን ነው፤ ሽብርተኛነት የሚሆነው አትጫኑብኝ እያለ በሰላማዊ መንገድ የሚጮኸውን ሰው መደብደብ፣ ማሰርና መግደል ነው፤ ሽብርተኛነት የሚሆነው የሰዎችን ቅዱስ ቦታ በጥይትና በደም ማርከስ ነው፤ ሽብርተኛነት የሚገለጠው ሰላሜን ጠብቁልኝ እያለ በሚጮኸው ሰው ሳይሆን በጉልበቱ ብቻ ተማምኖ ሰላምን በሚያደፈርሰው ነው፤ ሕዝብ ሰላምን ሲያገኝ ይሠራል፤ ያመርታል፤ ኑሮውን ያሻሽላል፤ ይዝናናል፤ ይህ ሁሉ ጥጋብን ያመጣል፤ ሲጠግብ የሚያስቸግረውን እንዳይጠግብ መበጥበጥ የሚፈልጉ አይጠፉም፡፡ ጮሌነት ዕድሜ አለው፤ የጮሌነት ዕድሜ በጣም አጭር ነው፤ ነገር ግን ጠንቁ ከነኮተቱ በልጅ ላይ ያርፋል፤ የጮሌው ኃጢአት ልጁን አዋርዶ ያቃጥላል፤ ማንም ለማንም የሚመኘው መንገድ አይደለም፡፡

ስለዚህ ሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄያቸውን ህገ-መንግስቱ በፈቀደላቸው በሰላማዊ እና ህጋዊ መንገድ እስካቀረቡ ድረስ መንግስት አግባብነት ያለውን መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ የሃይማኖቶች ነፃነትን በዚህ አካሄድ እየጨፈለቁ መሄድ ትርፉ ስርዓታዊ ኪሳራ ብቻ ነው፡፡ የሃይማኖቱ ተከታዮች ይወክሉናል ብለው የመረጧቸውን የአመራር አባላትንም ሆነ ምዕመኑን ማሰር፤ ማንገላታትና መግደል በሀገሪቱ ውስጥ ህገ- መንግስታዊነት እና የህግ የበላይነት ያለመኖሩ ማሳያ ነውና ይኼ አምባገነናዊ እርምጃ በአስቸኳይ መቆም አለበት።

ድል ለጭቁኑ ህዝበ ሙስሊም!!

ፀሃፊውን በኢሜል yentsanetgohe@gmail.com ያገኙታል።

Wednesday, August 28, 2013

ኢትዮጵያ ጉድ የማያልቅባት አገር ናት!!

ከማስረሻ ማሞ

ኢትዮጵያ ጉድ የማያልቅባት አገር ናት። ጉድ የማያልቅባት ከጉድም ጉድ የኾኑ ገዢዎች ስለሚፈራረቁባት ነው። ሕዝባቸውን አያከብሩም። ለዜጎቻቸው መብት እና ፍላጎት አይጨነቁም። ስለዚህ ጉደኛ የኾኑ ክስተቶችን በየጊዜው ያመጡብናል። ይፈጥሩብናል።

በሚቀጥለው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሠማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ላይ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ዕቅድ ካወጣ ሰንብቷል። በዚሁ ቀን መንግሥትም ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ። "ጽንፈኝነትን እና አክራሪነትን እንቃወማለን" የሚል መፈክር ለደጋፊዎቼ አስይዤ አዲስ አበባን በሠላማዊ ሰልፍ አጥለቀልቃታለሁ የሚል ዕቅድ አውጥቶ። 
መንግሥት አስፈጻሚ፣ አድራጊ ፈጣሪ፣ ገዢ እና ገናዥ በኾነበት አገር ላይ መንግሥት ሠላማዊ ሰልፍ ይጠራል። ወለፈንድ ማለት ይኼ ነው። ራሱ ቤት ለቤት ዞሮ “ጽንፈኝት እና አክራሪነትን” ለመቃወም “ኑ ዉጡ!” ብሎ በሕዝብ ሀብት እና ንብረት ላይ ከቀለደ በኋላ መልሶ “ሕዝቡ ጽንፈኝነትን እና አክራሪነትን ተቃውሞ ሠላማዊ ሰልፍ በማድረግ፤ መንግሥት ሐላፊነቱን እንዲወጣ ጠየቀ” ብሎ ሊወስድ የሚፈልገውን ርምጃ ልብስ ማልበስ ይፈልጋል። የዚህ ሠላማዊ ሰልፍ ጥሪ የስትራቴጂው ዋና ነጥብ ይኼ ነው።

በእኔ እምነት ጽንፈኝትን እና አክራሪነትን የማይቃወም ሕዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራል ብዬ አላስብም። ጽንፈኝነት እና አክራሪነት መፍትሄ ያመጣል ብለው የሚያስቡ እና መስመሩን ዓላማቸው አድርገው የያዙ ጥቂቶች አይኖሩም የሚል ጅላጅል አስተሳሰብም ኾነ አቋም የለኝም። ሊኖሩ ይችላሉ። ካሉ እነዚህን ጥቂት ሰዎች ፈልጎ እና ፈልፍሎ የማውጣቱ ሥራ የመንግሥት ነው። አገሪቱ ትክክለኛ ለሕዝብ ሰላም የሚጨነቅ የደህንነት መሥርያ ቤት ካላት ሕዝብ ሳይሰማው እና ሳያውቀው መጨረስም ይችላል። ለጊዜው የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግሥት በሁለት እግሩ ቆሞ ሥራውን እንዲሠራ በቀረጥ እና በግብር ሐላፊነቱን ከተወጣ በቂው ነው። እንደገና ምን በወጣው ነው መንግሥት የቤት ሥራውን ባለመሥራቱ ለሚጨቁነው መንግሥት ደግፎ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጣው? 

ነገሩ ወዲህ ነው። አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ከእውነተኛዎቹ ጽንፈኞች እና አክራሪዎች ይልቅ በአሸባሪነት እና በጽንፈኝነት መንግሥትን የሚተካከለው እና የሚወዳደረው የለም፤ ይህን ዓላማውን እንዴት ማሳካት እንደሚችል ስለሚያስብ ሕግን ከማስከበር እና ከማስጠበቅ ወጥቶ ሠላማዊ ሰልፍ ጠሪ ለመኾን በቅቷል። አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በፈለገበት በተመሳሳይ ቀን እኔም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እፈልጋለሁ ማለት እብደት ነው። ሐላፊነት የጎደለው አካሄድ ነው። ሁለት የተለያየ ሐሳብ ያላቸውን ቡድኖች የሚከተሉ ደጋፊዎች በአንድ ቀን ወደ አንድ ቦታ እንዲወጡ ማድረግ ራሱን የቻለ የጽንፈኝነት እና የሽብር መገለጫ ነው። 

መንግሥት ይህን ለምን ማድረግ ፈለገ? 

እኔ ሲመስለኝ፦ 

1ኛ) በሠላማዊ ሰልፈኞቹ መካከል ግጭት እንዲፈጠር፤
2ኛ) ከግጭቱ በኋላ ሊፈጠር የሚችለውን አጋጣሚ በመጠቀም “ያልኳችኹ እውነት ነው” ብሎ ከዚህ በኋላ ማንኛውም ተቀዋሚ ፓርቲ ምንም ዐይነት ሠላማዊ ሰልፍ እንዳይጠራ ለማድረግ፤ ቀስ በቀስ የብዙ ሰዎችን ትኩረት በመሳብ ላይ ያለውን የሠላማዊ ሰልፍ ጉዳይ እግረ መንገድ እስከወዲያኛው ለማኮላሸት። 

3ኛ) በሁለቱም ወገን ሠላማዊ ሰልፈኞቹ ምንም ዐይነት የገጭት አዝማማያ ሳያሳዩ በሰላም ሊያጠናቅቁ የሚችሉበት ክፍተት ከተፈጠረ፤ የተመረጡ እና የተመለመሉ ሰዎችን በሠማያዊ ፓርቲ ሰልፈኞች መካከል በማስረግ በኢሕአዴግ ደጋፊዎች ላይ ትንኮሳ እንዲያካሂዱ ማድረግ ናቸው። 

ስለዚህ ይህ የሁለት ተቃራኒ ቡድኖች የሠላማዊ ሰልፍ ጥሪ ምን መኾን አለበት?

አሁንም እኔ ሲመስለኝ፦

መንግሥት ሐላፊነት በጎደለው አኳኋን ለሰላማዊ ሰልፈኞች ጥበቃ እና ከለላ በመስጠት ፈንታ፤ ራሱ የጫዎታው ተሰላፊ በመኾን ከላይ በጠቀስኳቸው ነጥቦች መሠረት ኹኔታውን ወደ ግጭት እንዲያመራ የሚያደርግ ከኾነ፤ ለሕዝብ ተቆርቋሪ የኾነ ሐላፊነት የሚሰማው ሌላ አካል ያስፈልጋል ማለት ነው። በዚህ የሠላማዊ ሰልፍ ፍጥጫ ላይ ሊፈጠር የሚችለውን አላስፈላጊ የኾነ ግጭት ለማስወገድ ይህ አጅግ አስፈላጊ ነገር ይመስለኛል። 

* ስለዚህ ሰማያዊ ፓርቲ የእሁዱን የሠላማዊ ሰልፍ ጥሪ ለሌላ ጊዜ አስተላልፌዋለሁ ማለት ይኖርበታል። 

1ኛ) የመንግሥትን ሐላፊነት የጎደለው አካሄድ ለመቀልበስ፤
2ኛ) በሠላማዊ ሰልፍ ሰበብ ሊፈጠር የሚችልን አላስፈላጊ ግጭት ለማስወገድ፤ 
3ኛ) ቀጣይ የኾኑ ሰላማዊ ሰልፎች እንዲኖሩ ሩቅ አሳቢነቱን ለማሳየት
4ኛ) በሠላማዊ እና በሠላማዊ በኾነ መንገድ ብቻ መብትን እና ነጻነትን ለዜጎች ማሳየት እና በማስተማር እንደሚቻል ለማሳወቅ።

ሰማያዊ ፓርቲ በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ላይ ተቃውሞ አቀረበ

ፓርቲው ከ33ቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ ጋር ተለያየ


በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. የመጀመሪያውን የተቃውሞ ሠልፍ ያካሄደው ሰማያዊ ፓርቲ፣ በመጪው እሑድ በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በተዘጋጀው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ተቃውሞ አቀረበ፡፡


ሁለተኛውንና በርካታ ሰዎች እንዳሚሳተፉበት ሲገልጽ የከረመውን ሰላማዊ ሠልፍ የሚያካሄደው ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. እንደነበር ፓርቲው አስታውቆ፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በተደራቢነት በዕለቱ ሠልፍ እንደሚያደርግ ያስተላለፈው ጥሪ ትክክል አይደለም ብሏል፡፡

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ያስተላለፈውን፣ ‹‹አክራሪነትና ጽንፈኝነትን እናውግዝ›› የሚል የሠልፍ ጥሪ የተቃወመው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ከአንድ ወር በላይ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ሲያስተዋውቅና ጥሪ ሲያደርግ መክረሙን ገልጿል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ ቀድሞ ማሳወቅ ለሚገባው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በደብዳቤ ማስገባቱን፣ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌታሁን ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡
‹‹እኛ በጠራነው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ሌላ ሠልፍ እንዲጠራ መፍቀድ መንግሥት በትንሹ የከፈተውን ቀዳዳ ለመዝጋት ፈልጐ ነው፤›› የሚሉት ሊቀመንበሩ፣ በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ሰላማዊ ሠልፍ መጥራት ለምን እንዳስፈለገ ግልጽ እንዳልሆነላቸውና መንግሥት የጉባዔውን ሠልፍ እንዲሰርዝ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት የተጠሩ ሁለት የተለያዩ ዓላማና ይዘት ያላቸው ሰላማዊ ሠልፈኞች ሲገናኝ ወደ ግጭት ሊያመሩ ስለሚችል፣ መንግሥት ፓርቲው ቀድሞ መጥራቱንና ለሚመለከተው አካል ማሳወቁን በመገንዘብ ዕርምጃ እንዲወስድ፣ ፓርቲው ነሐሴ 21 ቀን 2005 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ መግለጫ ማውጣቱን ኢንጂነር ይልቃል ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሰማያዊ ፓርቲ ለበርካታ ወራት አንድነት ፓርቲን ጨምሮ ከ33 ፓርቲዎች ስብስብ ጋር ኅብረት ፈጥሮ ሲሠራ የቆየ ቢሆንም፣ ሰሞኑን ከስብስቡ እንዲወጣ መደረጉ ተሰምቷል፡፡ ከ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ መገለሉን በሚመለከት አስተያየታቸውን ለሪፖርተር የሰጡት ኢንጂነር ይልቃል፣ ‹‹የሚያግባባን ነገር ሲገኝ በጋራ ሆነን ለመሥራት ተስማማን እንጂ፣ ማንም ተባራሪና አባራሪ የለም፡፡ መሰብሰባችን በስምምነት እንጂ የሕግ ድጋፍ ኖሮት የተደረገ ስምምነት አይደለም፤›› ብለዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሲሰጡ፣ ‹‹ለኢትዮጵያ ሕዝብና ፖለቲካ የሚመጥን የፖለቲካ ፓርቲ አለ ብለን አናምንም፤›› ማለታቸውና ሰማያዊ ፓርቲ እየጣረ ያለው ክፍተቱን ለመሙላት መሆኑን መናገራቸው ሌሎቹን ማስከፋቱ ይነገራል፡፡

የ33 ፓርቲዎች ስብስብ፣ ‹‹እንዴት እንደሌለን እንቆጠራለን?›› የሚል ጥያቄ አንስቶ እንደነበር መስማታቸውን የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ ለምን እንደተናገሩ ጠርተው ሳያናግራቸው ስንቶቹ ተሰብስበውና በስንት ድምፅ ወስነው አብረው መቀጠል እንደማይችሉ ሳይገለጽላቸው ስለመለያየት ማውራት፣ ለእሳቸው የልጆች ጨዋታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹እኛ ከወጣን ከ33 ፓርቲዎች ስብስብ ውስጥ ሰው የሚያውቀውና ስሙ የሚታወቅ ፓርቲ ይኖራል እንዴ?›› ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እውነትን በአደባባይ መናገር ስላልተለመደ እንጂ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ለምን ተናገረ?›› በሚል አብሮ አለመሥራትን ማወጅ፣ ሕዝቡን ተስፋ ከማስቆረጥ ያለፈ ጥቅም እንደሌለው ኢንጂነር ይልቃል ጠቁመዋል፡፡ 

ምንጭ: ሪፖርተር

"… በህጋዊ መብቱ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ሆን ብሎ ለመረበሽና አቅጣጫውን ለማስቀየስና በዜጐች መካከል ግጭት ለመፍጠር የታቀደ ስለሆነ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ መንግሥት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብና የሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁት…” – ሰማያዊ ፓርቲ

በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ሰማያዊ ፓርቲ እና ኢህአዴግ በየፊናቸው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተከትሎ አዝማሚያው ወደ ውጥረት እያመራ መሆኑን ታዛቢዎች ገለጹ።

ነሃሴ ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ካሉት ጊዜያት ጀምሮ ለነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓመተምህረት ሰልፍ እንደሚጠራ አስታውቆ የቅስቀሳ ሥራ መሥራት በጀመረበት ጊዜ፤ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሰሞኑን  በዚያው ቀን ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ማቅረቡ ያታወቃል።

በተለይ በኢህአዴግ የሰልፍ ጥሪ  የሴትና ወጣት ማህበራት፣የመንግስት ሠራተኞች፣ የሀይማኖት ተቋማትና  ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጭምር በግዳጅ እንዲወጡ መታዘዛቸው፤ ሁኔታውን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ይወስደዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ሰማያዊ ፓርቲ፤የ አፍሪካ መሪዎች አዲስ አበባ ላይ በተሰበሰቡበት ወቅት ሰልፍ ለማድረግ  ወስኖ ሳለ፤  የአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ክፍል ፤ወቅቱ የመሪዎች ስብሰባ ከመሆኑ አንፃር በዕለቱ በቂ ሀይል እንደሌለውና ሰልፉን ለሳምንት እንዲያሸጋግሩ በጠየቀው መሰረት፤ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን ማሸጋገሩ ይታወሳል።

ይሁንና ያን ውሳኔ ያሳለፈው የመስተዳድሩ የሰልፍ ፈቃድ ክፍል ፤ ኢህአዴግ-ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ሊያደርግ ባቀደበት ተመሣሳይ ቀንና ከተማ ውስጥ ሰልፍ ለማድግ ሢነሳ ምንም አለማለቱ ታዛቢዎችን አስገርሟል።

ኢህአዴግ-የሸህ ኑሩን ሞት ተከትሎ በሌሎች ክልሎች እንዳደረገው ሁሉ በአዲስ አበባ ሊያደርገው በተዘጋጀው ሰልፍም የሙስሊሞችን የመብት ይከበር እንቅስቃሴ ከሽብርተኝነትና ከጽንፈኝነት ጋር በማያያዝ በሰልፈኛው ለማስወገዝ መዘጋጀቱ ታውቋል።

ከዚህም ሌላ የገዥው ፓርቲ ተቃዋሚዎች ሰልፍ በሚወጡበት ዕለት -ኢህአዴግ የከተማዋን ነዋሪዎች በግዳጅ “እኔን ደግፋችሁ ውጡ”ማለቱ፤ በህብረተሰቡ ዘንድ አላስፈላጊ መቃቃርን፣ መወጋገዝንና መለያዬትን  ለመፍጠር በማሰብ  ጭምር ነው የሚሉ አስተያየቶችም እየተሰነዘሩ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ  መንግስት  የጠራውን ሰልፍ እንዲሰረዝ ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ።

ፓርቲው፦”መንግሥት ለተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ እንጠይቃለን!!”በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤ ሰማያዊ  ፓርቲ ግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉን አስታውሶ፦” መንግሥት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች በሦስት ወር ውስጥ መልስ የማይሠጥ ከሆነ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ ጥያቄያችንን በድጋሚ በህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ እንደምናቀርብ በግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. በተደረገው ሠልፍ ላይ ለህዝብ ቃል በገባነው መሠረት ነሃሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም. በድጋሚ ሰልፍ ጠርተን አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረግን መሆኑን ለህዝብ በልዩ ልዩ መገናኛ ዘዴዎች ገልፀናል” ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ለሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግልን አዋጁ በሚጠይቀው መሠረት ለአዲስ አበባ መስተዳድር ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማስታወቂያ ክፍል ጉዳዩን እንዲያውቀው አድርገናል ብሏል-ሰማያዊ ፓርቲ።

ይሁን እንጂ ፓርቲያችን የተቃውሞ ሰልፍ በጠራበት ግዜና ቦታ ላይ በሌላ አካል ሰልፉ መጠራቱን በትናንትናው ዕለት ነሀሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በመንግሥት ቴሌቪዥን ዜና ሰምተናል ያለው ሰማያዊ ፓርቲ፤ከዚህም በላይ  የመ
ንግሥትን መዋቅር በመጠቀም  ዜጐች በዚህ ሰልፍ ይገኙ ዘንድ  በግድ እንዲፈርሙ እየተደረገ መሆኑን ከአዲስ አበባ ኗሪዎች አረጋግጠናል ሲል አትቷል።

ሰማያዊ ፓርቲ አስፈላጊውን የህግ ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ ነሐሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ለህዝብ ያሳወቀና አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቀ በመሆኑም፤ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ሠዓት በሌሎች አካላት የተጠራው ሰልፍ ከመረጃ እጥረት ከሆነ እንዲሠረዝ እንጠይቃለን ሲልም  ኢህአዴግ የጠራውን ሰልፍ እንዲሰርዝ  ጠይቋ ል።

ሰማያዊ ፓርቲ በማያያዝም፦”ይህ ካልሆነ ግን ሰማያዊ ፓርቲ በህጋዊ መብቱ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ሆን ብሎ ለመረበሽና አቅጣጫውን ለማስቀየስና በዜጐች መካከል ግጭት ለመፍጠር የታቀደ ስለሆነ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ መንግሥት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብና የሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁት በአፅንዖት እንገልፃለን፡፡” በማለት አሣስቧል።

እሁድ ሰማያዊ ፓርቲና ኢሕአዴግ በመስቀል አደባባይ የጠሩት ሰልፍ እያወዛገበ ነው!!


‘‘ቀድመን ሰልፍ የጠራነው እኛ ነን’’
   ሰማያዊ ፓርቲ

‘‘የቀደምነው እኛ ነን’’

- የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

‘‘ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ የሚያካሂደው ሰልፍ ህገ-ወጥ ነው’’

- የአ.አ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ የስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት

በዘሪሁን ሙሉጌታ

በመጪው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በማወዛገብ ላይ ነው። ቀደም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በበኩሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አድርጓል።

ይህንን ተከትሎ በፓርቲው እና በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መካከል የቀደምኩት እኔ ነኝ በማለት በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት በበኩሉ፤ ሰልፍ እንደሚካሄድ ቀድመው ያሳወቁት የሃይማኖት ተቋማቱ በመሆኑ በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ የሚካሄድ ከሆነ ህገወጥ ነው ብሏል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ጉዳዩን በማስመልከት ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደተናገሩት ፓርቲው ከወር በፊት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ማድረጉን በማስታወስ ፓርቲያቸው ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ በቅድሚያ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል።

እንደ ፓርቲው ሊቀመንበር ገለፃ ፓርቲው አስቀድሞ ቀን መቁረጡንና በተባለውም ቀን ሰልፉን ለማካሄድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ ስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ጭምር የማሳወቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ተናግረዋል። በወቅቱ ጽ/ቤቱ ደብዳቤውን ለመቀበል ፍላጎት ባያሳይም በህጉ መሠረት ማሳወቅ ብቻ በቂ በመሆኑ ደብዳቤውን በጽ/ቤቱ አስቀምጠው መመለሳቸውንና በኋላም ጽ/ቤቱ በፖስታ ቤት በኩል በሬኮማንዴ ለፓርቲው ሰልፍ የት እንደሚያካሂድ፣ ምን ያህል ሰው እንደሚሳተፍ ማብራሪያ በመጠየቁ ፓርቲው በበኩሉ ለጽ/ቤቱ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል። ሆኖም ጽ/ቤቱ በህጉ መሠረት በ48 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ መስጠት ሲገባው ዝምታን በመምረጡ፣ ዝምታው ደግሞ ሰልፉ እንደተፈቀደ የሚጠቁም በመሆኑ በሰልፉ ዙሪያ ፓርቲው ዝግጅት ማድረግ መቀጠሉን አስታውቀዋል።

ከጽ/ቤቱ እስካሁን (ነሐሴ 21 ቀን 2005 ዓ.ም) ምላሽ ባለመገኘቱም ፓርቲው በዕለቱ የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ከማካሄድ ወደኋላ የሚመልሰው የህግ መሠረት ባለመኖሩ ሰልፉን እንደሚያካሂድ አስታውቀዋል። ፓርቲው ከነገ ሐሙስ ጀምሮ በአምስት ተሽከርካሪዎች በአስሩም ክፍለ ከተማ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ ለማካሄድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። በመላ ከተማዋና በአካባቢዋም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ወረቀት እንደሚበተንና ሰልፉም ካለፈው ሰልፍ ልምድ በማግኘት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ይሁን እንጂ ባለፈው ሰኞ (ነሐሴ 20 ቀን 2005) በዋና ጽ/ቤቱ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ያስታወቀው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን እንደማያውቁና ጽ/ቤታቸውም ቀደም ብሎ ሰልፉን ሲያዘጋጅ መቆየቱን ተናግረዋል።

የወያኔ መንግስት የግንቦት 7 ቡድን አባላት ናቸው ብሎ የጠረጠራቸው ላይ ክስ መሰረተ

የግንቦት 7 አሸባሪ ቡድን አባላት ናቸው በሚል የተጠረጠሩ 10 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው ።

ተከሳሾቹ ዘመኑ ካሳ በዕውቄ የግንቦት ሰባት ልዩ ሃይል ታጣቂ ፣ አሸናፊ አካሉ አበራ ፣ ደህናሁን ቤዛ ስመኝ ፣ ምንዳዬ ለማ ፣ አንሙት የኔዋስ አለኽኝ ፣ሳለኝ አሰፋ ወንድምአገኝ ፣ የአማራ ክልል የማረሚያ ቤት ረዳት ሽፍት መሪ ምክትል ኢንስፔክተር ሙሉዬ ማናዬ ረታ፣ፀጋው ካሳ እንየው ፣ የአለም አካሉ አበራ እና ሙሉ ሲሳይ መቆያ የተባሉ ተጠርጣሪዎች  ናቸው ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት  ከፈረጀውና እራሱን ግንቦት ሰባት እያለ ከሚጠራው ድርጅት አመራሮች ጋር በመገናኘት ለሽብር ስር በጋራ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ነው  የፌዴራሉ አቃቤ ህግ ክስ የመሰረተባቸው ።

የፌዴራሉ አቃቤ ህግ መረጃዎችን ሰብስቦ ነሃሴ 13 ክስ መስርቶባቸው ትላንት በአቃቂ ጊዜያዊ 4ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን፤ተከሳሾቹ ጠበቃ የማቆም አቅም ስለሌላቸው የመንግስት ጠበቃ እንዲቆምላቸው ችሎቱ አዟል።

ችሎቱ  1ኛ ተከሳሽ በሌለበት ክሱ በመቅረቡ በጋዜጣ እንዲጠራ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ክሱን ለመስማትም  ችሎቱ ለህዳር 2 ቀን  2006 ዓመተ ምህረት ቀጠሮ ይዟል ።

በሹመኛ የመጅሊስ አባላትና በመንግስት መካከል አለመግባባት መንገሱ ተሰማ!! (ድምፃችን ይሰማ)

ረቡእ ነሐሴ 22/2005

አንዳንድ የወረዳ መጅሊስ ሹመኞች ‹‹መንግስት በሚያዘጋጀው ሰልፍና ስብሰባ ዲናችንን አናሰድብም›› የሚል አቋም ይዘዋል!

በመጪው እሁድ ነሀሴ 26 መንግስት በግዳጅ ሊያካሄደው ካሰበው ሰልፍ ጋር በተገናኘ በሹመኛ የመጅሊስ አባላትና በመንግስት መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ተሰማ፡፡ አለመግባባቱ የተፈጠረው በመንግስት የቅስቀሳ ስብሰባዎች ላይ በእስልምና ሃይማኖት ላይ ተደጋጋሚ ዘለፋ እና የማንቋሸሽ ተግባራት በመበራከቱና መንግስትም ሁኔታውን ለመግታት ፈቃደኛ ባለመሆኑ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ባለፈው እሁድ የመንግስት ሀላፊዎች ከመጅሊስ የወረዳ ሹመኞች ጋር ባደረጉት ስብሰባ እና ግምገማ የመጅሊሱ ሹመኞች ለመጪው እሁድ የመንግስት ሰልፍ በቂ ቅስቀሳ እያደረጉ እንዳልሆነና ይህ መስተካከል እንዳለበት ያሳሰቡ የመንግስት ሀላፊዎች የሰጡትን ገለጻ ተከትሎ ሹመኞቹ ባደረጉት ንግግር ‹‹በየስብሰባው የሚገኙ የመንግስት ሰዎች ዲናችንን እየተሳደቡብን ሞራላችን እየተነካ ነው›› ያሉ ሲሆን ‹‹በዚህ አቅጣጫ ህብረተሰቡ አግልሎን በዚህ በኩል ደግሞ መንግስት ዲናችንን እያሰደበብን ከመሀል ሆነን እየተጎዳን በመሆኑ መንግስት ዘለፋውን ያስቁምልን›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በስብሰባው የተገኙ የመንግስት ሀላፊዎች በበኩላቸው የመጅሊሱን ሹመኞች በሰጡት አስተያየት ምክንያት የገሰጿቸው ሲሆን ተሳታፊዎች የፈለጉትን አስተያየት የመሰንዘር መብት አላቸውም ብለዋል፡፡ የመጅሊስ ሹመኞቹ ‹‹ካድሬዎቹ እየሰጡ ያሉት ስሜታዊ አስተያየት ሙስሊሙን እየጎዳ ስለሆነ ሊቆም ይገባል›› በሚል መረር ያለ ወቀሳ ቢያቀርቡም የመንግስት ሀላፊዎች ‹‹የሀገር ጉዳይ ስለሆነ ማንም በስሜት ቢናገር አይፈረድበትም›› በሚል ምላሽ ሰንዝረዋል፡፡ ሀላፊዎቹ አክለውም ሰልፉ ወሳኝ ምእራፍ የሚከፈትበት በመሆኑ ሁሉም የመጅሊስ አባል ከነቤተሰቡ መሳተፍ እንዳለበት አስጠንቅቀው ሰልፉ መንግስት ጠላቶቹን የሚለይት በመሆኑ በሰልፉ አለመሳተፍ የሚያስከፍለው ዋጋ ከፍተኛ እንደሆነ በዛቻ መልክ አስረድተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በስድስት ኪሎ ስብሰባ ማእከል የአዲስ አበባ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ባዘጋጀው ስብሰባ ተሳታፊ የመንግስት ካድሬዎች የእስልምናን ክብር የሚያራክሱ ዘለፋዎችና የእምነቱን ተከታዮች ክብር የሚያናንቁ ውንጀላዎች መሰንዘራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በርካታ የመጅሊስ ሹመኞችም አንገታቸውን ደፍተው ከስብሰባው ለመውጣት ተገደዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰኞ እለት ከቀኑ አስር ሰአት ላይ የክፍለ ከተማ ሃላፊዎች በዚሁ ሰልፍ ጉዳይ ላይ ከየወረዳው መጅሊስ ሹመኛ አባላት ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ስብሰባ መንግስት አስደንጋጭ ሪፖርት ቀርቦለታል፡፡ በተለይም በየካ፣ በአራዳ፣ አዲስ ከተማና ቦሌ ክፍለ ከተሞች ያሉ አንዳንድ የመጅሊስ አባላት ባቀረቡት ሪፖርት አባላቱ እንኳን ታች ወርደው ህብረተሰቡን ለመቀስቀስ ቀርቶ የራሳቸው የመጅሊስ አባላቶች እንኳ ለመሳተፍ ፈቃደኞች እንዳልሆኑና ‹‹መንግስት በሚያዘጋጀው ሰልፍና ስብሰባ ዲናችንን አናሰድብም›› የሚል ምላሽ እንዳቀረቡ ታውቋል፡፡ የመጅሊስ ሹመኞቹ የሰልፍ ተሳታፊዎችን ቃል እንዲያስገቡበት በመንግስት በተሰጣቸው ፎርም ምን ያህል ሰው እንዳሰፈሩ የመረመሩት የመንግስት ሀላፊዎች አንዳንዱ እራሱንና ቤተሰቦቹን ብቻ ያስመዘገበ መሆኑና ሌሎቹ ደግሞ ባዶ ወረቀት ማስረከባቸው ሀላፊዎቹን በብስጭት እንዲወራጩ አድርጓቸዋል፡፡

Monday, August 26, 2013

መንግስት ለመጪው እሁድ ሰልፍ ጠራ! (ድምፃችን ይሰማ)

ለተሳታፊዎች ዳጎስ ያለ አበል ተዘጋጅቷል!

የግል ድርጅት ሀላፊዎች ከእነ መኪናቸውና ሰራተኞቻቸው በሰልፉ እንዲገኙ ግዳጅ ተጥሎባቸዋል!

መንግስት በመጪው እሁድ ሰልፍ ሊያካሄድ ነው፡፡ መንግስት በክልሎች ሲያካሄድ ያቆየውን ይህንኑ የግዳጅ ሰልፍ በአዲስ አበባ ለማድረግ ለወራት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያካሄድ ቆይቷል፡፡ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ለማካሄድ የታሰበው ሰልፍ በዋነኝት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ያነሳውን የእምነት መብት ጥያቄ በክራሪነት ለመወንጀልና ‹‹ሕዝቡ መንግስት እርምጃ ይውሰድልን›› አለ በሚል ለሚዲያ ፍጆታ ለመጠቀም ነው፡፡

በዚህ ሰልፍ በርካታ ሰው እንዲገኝ ለማድረግ ያስችል ዘንድ የመንግስት ሰራተኞች፣ የፓርቲ አባላት፣ የሴቶች ሊግ፣ የወጣቶች ሊግ እንዲሁም በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት አባሎች፣ በኮብል ስቶን የሰለጠኑ ወጣቶች እንዲገኙ የግዳጅ መመሪያ ተላልፏል፡፡ እነዚህ የተጠቀሱ ሁሉ በሰልፉ ላይ ለመገኘት ፊርማቸውን እንዲያኖሩ በዚሁ ሳምንት ሊጠየቁ እንደሚችሉ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

እሁድ ዕለት ነሐሴ 26/2005 ኢሕአዴግ በጠራውና ‹‹አክራሪነት››ን ማውገዝ ዋነኛው አጀንዳው ነው በተባለለት ሰልፍ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትም እንዲሳተፉ መንግስት ጫና በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከሃይማኖት ተቋማት በተጨማሪ የተለያዩ የግል ድርጅቶች በተለይም የጅምናስቲክ፣ የማርሻል አርትና የቴኳንዶ ስልጠና የሚሰጡ ድርጅቶች ሰልጣኝ ተማሪዎቻቸውን በሰልፉ ይዘው እንዲገኙ በየወረዳው አስተዳዳሪዎች ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል፡፡

ከየክፍለ ከተማው አስከ አስር ሺ ሰው እንዲሳተፍበት በተላለፈው መመሪያ መሰረት የወረዳ ቢሮዎች ኮታውን ለመሙላት ይሄን ሳምንት ሙሉ ጊዜያቸውን ለዚሁ ስራ በመስጠት ከፍተኛ የቅስቀሳ እና የግደጅ ስራ ለመስራት ተዘጋጅተዋል፡፡ መንግስት በክልል ከተሞች ሲያካሄደው እንደነበረው ሁሉ ለዚህ ሰልፍም ከፍተኛ ባጀት መድቧል፡፡ ለሰልፉ ተሳታፊዎችም ዳጎስ ያለ አበል እንደሚቆረጥላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት በአዲስ አበባ የሚገኙ የግል ድርጅት ሀላፊዎችን መንግስት በዚሁ አጀንዳ ጉዳይ ጠርቶ ማነጋገሩ ታውቋል፡፡ ድርጅቶቹ መኪኖቻቸውን ከእነሰራተኞቻቸው ይዘው ‹‹አሸባሪነትን እንቃወማለን›› በሚል በሰልፉ እንዲገኙ በየአካባቢው ያነጋገሯቸው የመንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎች በማስጠንቀቂያ መልክ ገልጸውላቸዋል፡፡ የመንግስት ኋላፊዎቹ ቁጥጥር እንደሚያደርጉና አንድም ሰራተኛ መቅረት እንደሌለበት አሳስበዋልም፡፡

መንግስት መሰል ሰልፎችን በግዳጅ በመጥራት በሚዲያው ግን በተቃራኒው ‹‹ሕዝቡ በራሱ ፈቃደኝነት ሰልፍ ወጣ›› የሚል ዜና ሲሰራ ቆይቷል፡፡ የመሰል ሰልፎችና ስብሰባዎች የአቋም መግለጫዎች ከስብሰባውና ሰልፉ ቀናት በፊት ተዘጋጅተው የሰልፉ ተሳታፊዎች ያወጡት መግለጫ በሚል በእለቱ እንዲነበብና ለፕሮፖጋንዳነት እንዲውል ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

አላሁ አክበር!

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፈ መልዕክት!!

ለተከበረው የኢትዮጵያ  ህዝብ በሙሉ

በኢትዮጵያ ሀገራችን የአገር አንድነት ከተናጋና የዜጎች መብት ከተደፈጠጠ አነሆ 22 ዓመታትን አስቆጥረናል። ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ሀብትና ንብረት እንዳያፈሩ አስቸጋሪ የሆነ ሁኔታ ተፈጥሮባቸዋል። ካፒታልና እውቀት ከቦታ ቦታ በመዘዋወር ዜጎችን እንዳያገለግሉ በክልል ድንበር ታግደዋል። ዜጎችም ለብዙ ዓመታት ከሰፈሩበት ቦታ አገርህ አይደለም በሚል ሰበብ የዘር ግንዳቸው መነሻ ወደሆነው ክልል እንዲሜለሱ ይገደዳሉ። በዚሁ መሰረትም በዚሁ ዓመት ብቻ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ልጆች ከቤንሻንጉልና ከጉራፈርዳ በኢሀዴግ ካድሪወች ተፈናቅለዋል። ሃብት ንብረታቸውም ተዘርፈዋል። የአፋርና የጋንቤላ ልጆችም መሬታቸው ለባዕድ ስለተሸጠባቸው የመኖር መብታቸው ተገፏል፣ ለስደትም ተዳርገዋል።

ዝርዝሩን ያንቡ የቀረበውን ሊንክ በመጠቀም http://welkait.com/wp-content/uploads/2013/08/mead130824.pdf



Sunday, August 25, 2013

በሮቢ ዉጥረት በጣም ጨምሯል !

«በሮቢ ደም ሊፈስ ይችላል»

አንድነት ሰላማዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነዉ። አገዛዙ ግን ሕገ መንግስቱን በመርገጥ የሰለጠነን ሳይሆን፣ የዛቻን ፖለቲካ እያራገበ ነዉ። በማለት ማስፈራሪያዊች እየቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊሲስ ሰልፍን የምታደርጉ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስድ አሳዉቀዋል።

የሮቢ የአገዛዙ አስተዳዳሪዎች፣ 20 ሰዎች የሚገኙበት የ«ሽማግሌዎች» ቡድን አቋቁመዋል። ይሀ ቡድን ከጥቂት ሰዓት በኋላ ከሚሊየነም ድምጽ ለነጻነት ግብረ ኃይል ጋር ዉይይት ያደርጋል።

ኮምቴዉ፣ ስብሰባው ከተደረገ ብጥብጥ ተፈጠሮ ደም ሊፈስ እንደሚችል ስጋት ያላቸው ይመስለላል። ነገር ግን በስብሰባዉ የግብረ ኃይሉ መሪዎች ሰልፍ ሰላማዊ እንደሆነ ለማሳመን እንደሚሞክሩ ሰልፉን ለመሰረዝ ፍቃደኛ እንዳለሆኑ ያሳዉቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ፖሊስ፣ «ሰልፉ ሕገ ወጥ ስለሆነ፣ አስፈላጊዉን እርምጃ እንወስዳለን » የሚል ከፍተኛ ማስፈራሪያና ዛቻ ለአንድነት አመራሮች የሰጠ ሲሆን፣ የፓርቲው አመራሮች ግን፣ የፖሊስን ማስፈራሪያ ዉድቅ አድርገዉታል። ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት እንደሆነ የገለጹት አንድነቶች፣ ሰልፉ በታቀደበት ቀን እንዳይደረግ ከተፈለገ፣ ፖሊስ ምክንያቶችን በመስጠት እንዲራዘም የመጠየቅ እንጂ፣ ሕገ መንግስቱን በመናቅ የዜጎችን መብት መዳፈር እንደሌለበት አሳስበዋል።

የአንድነት ፓርቲ በጎንደር፣ በደሴ፣ በባህር ዳር፣ በአርባ ምንጭ፣ በጂንካ ሰላማዊ ስለፎች ያደረገ ሲሆን፣ ሁሉም ፍጹም ሰላማዊ ፣ በንብረትም ሆነ በሰው ሕይወት ላይ አንዳች አደጋ ያላደረሰ መሆኑ ይታወቃል።

ምንጭ፡ abugidainfo.com

ሕወሐት በአዜብ ጉዳይ ተወጥሯል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶ መለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ። አዜብ ከኤፈርት እንዲወገዱ የተደረገው ግን በነቴዎድሮስ ሃጎስ ሳይሆን ስብሃት ነጋ ባቀነባበሩት ጣልቃ ገብ ውሳኔ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀዋል። በኤፈርት የተለያዩ ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች አዜብ በመባረራቸው ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ አያይዘውም ደስታቸውን በስብሰባ ጭምር ከመግለፅ ባለፈ፥ « አዜብ ከኤፈርት ጀምሮ ለፈፀሟቸው የሙስና ወንጀሎች በሕግ መጠየቅ አለባቸው» በማለት አቋም እስከ መያዝ መድረሳቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ በስተጀርባ በበቀለኝነታቸውና የጥፋት ሴራ በማቀነባበር የሚታወቁት ስብሃት ነጋ እንዳሉበትና ከኤፈርት ስልጣናቸው ያስነሷቸውን አዜብ ከጨዋታ ውጭ ከማድረግ ባለፈ በሙስና እንዲጠየቁ በየአቅጣጫው ጫና እያሳደሩ መሆኑን ምንጮቹ አስረድተዋል። በአዜብ ተፈፀሙ ተብለው ከተነሱት የሙስና ወንጀሎች በኤፈርት ስም 200 ከባድ ተሽከርካሪዎች አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር ቀረጥ ሳይከፍሉ እንዲያስገቡ ማድረጋቸውን፣ በሚሊዮን የሚገመት ቀረጥ ሊከፈልባቸው የሚገቡ የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች፣ በኤፈርት ገንዘብ ሶስት መርከብ ስሚንቶ የፍራንኮ ቫሉታን ሕግ በመተላለፍ ቀረጥ ሳይከፈልበት አገር ውስጥ መግባቱ፣ ክሶች እንዲቋረጡ ትእዛዝ በመስጠት..የሚሉት በዋነኛነት መነሳታቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል። ( አዜብ ከኤፈርት እንደሚነሱ ከዚህ ቀደም በወጡ ዘገባዎች ምንጮችን በመንተራስ መገለፁ ይታወሳል)

ይህ በእንዲህ እንዳለ – በአዜብ ቦታ የተተኩት ብርሃነ ኪ/ማርያም (በቅፅል ስማቸው ብርሃነ “ማረት”) ሲሆኑ፣ ከመለስ በፊት የአዜብ ፍቅረኛ የነበሩና ከሱዳን ተያይዘው በመምጣት ሕወሐትን እንደተቀላቀሉ ምንጮች አስታውሰዋል። ድርጅቱን ከተቀላቀሉ ከጥቂት ወራት በኋላ ሁለቱ (አዜብና ብርሃነ) የፍቅር ግንኙነታቸውን እንዲያቋርጡ ከበላይ አመራር መወሰኑን፣ አዜብ ከመለስ ጋር ግንኙነት መቀጠላቸውን ይገልፃሉ። ፓርቲው ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ብርሃነ በመቀሌ ማዘጋጃ ቤት ተመድበው ሲሰሩ «ለመንገድ ስራ ከተመደበ ገንዘብ አምስት ሚሊዮን ብር ተዘርፏል» በሚል በሙስና እንዲባረሩ መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል። አዲስ አበባ የመጡት ብርሃነ ብዙ ጥረት አድርገው አዜብ ዘንድ (ቤተ መንግስት) የመግባት አጋጣሚ ያገኛሉ። ባቀረቡት አቤቱታና ተማፅኖ መሰረት ሲቪል ሰርቪስ እንዲገቡ አዜብ ትእዛዝ ያስተላልፋሉ። ከኰሌጁ እንደወጡ የማ.ረ.ት. ሃላፊ ተደርገው በመለስ የተሾሙት ብርሃነ፣ በተለይ ከ1993ዓ.ም በኋላ የመለስ ቀኝ እጅ በመሆን በአውሮፓና አሜሪካ ያለውን የፓርቲውን መዋቅርና ስለላ በመምራት፣ አምባሳደሮችን በማስፈራራት፣ በማዘዝና ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ በማሳለፍ ታማኝ አገልጋይ ሆነው እንደቆዩ ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሞት በኋላ ግን የስብሃት ነጋ ተከታይና አስፈፃሚ በመሆን አሰላለፋቸውን ቀይረው እንደቀጠሉ አያይዘው ገልፀዋል። ስብሃትና ብርሃነ ዝምድና እንዳላቸው የጠቆሙት ምንጮች፣ አዜብን በማስነሳት ብርሃነ እንዲቀመጡ ያደረጉት ስብሃት መሆናቸውን አመልክተዋል።

ምንጭ፡ ecadforem.com

ትንሽ ስለ ‘መለሲ-ዝም’: ከኢህአዴጎች የምስማማበት ነጥብ

በአብርሃ ደስታ

ሳስበው ሳስበው ስለ ‘መለሲዝም’ ሰበካ የተጀመረ ይመስለኛል። በመለስ ማመናቸው ችግር የለብኝም። ግን መለስ ፈጣሪያቸው መሆኑ እየነገሩን ነው። ብዙ ነገሮች በሱ ስም እየተሰየሙ ናቸው። እነሱ እንደሚነግሩን ከሆነ የኢህአዴግ ፖሊሲ የመለስ ነው፣ መለስ ወታደራዊ መሃንዲሳቸው ነበር፣ መለስ አንቀሳቃሽ ሞተራቸው ነበር፣ የኢህአዴግ ሓሳብና ተግባር የመነጨው ከመለስ ነበር፣ ባጠቃላይ መለስ ሁለመናቸው ነበር።

ለዚህም ነው የኢህአዴግ አባላት አውቀውም ሳያውቁም መለስ የተናገረውን እንደ ፓሮት የሚደግሙት። በራሳቸው ማየት ሳይችሉ መለስ በመራቸው ይጓዛሉ። ለዚህም ነው መለስ ያወጣውን ፖሊሲ መተግበር የማይችሉ። ፖሊሲው መተግበር ያልቻሉበት መንገድ ማየት ስለሚሳናቸው ፖሊሲው ጥሩ መሆኑ ተናዘው ችግሩ ያለው ግን አፈፃፀሙ ላይ መሆኑ ይለፍፋሉ።

ግን አንድ ትክክል ወይ ጥሩ የሆነ ፖሊሲ እንዴት ላይፈፀም ይችላል? ፖሊሲ’ኮ አፈፃፀም ነው። ፖሊሲ ከህልም የሚለይበት ዋነኛው መስፈርት ስለሚፈፀም ነው። ስለዚህ አንድ ፖሊሲ አፈፃፀም ላይ ችግር ካጋጠመው ፖሊሲው ትክክል አይደለም ማለት ነው። ግን የመለስ ልጆች ‘ፖሊሲው ስህተት ነው’ ብለው የማጋለጥ ዓቅሙና ድፍረቱስ አላቸው? አይመስለኝም። ምክንያቱም ፖሊሲው የመለስ ነው። ፖሊሲው ስህተት እንደሆነ መናገር ማለት መለስ እንደሚሳሳት መመስከር ነው። መለስ ደግሞ ፈጣሪያቸው ነው። ለዚህም ነው ከነ ስህተቱ ‘የመለስ ሌጋሲ ወይ ራእይ’ እያሉ የመለስን የተሳሳተ የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅጣጫ ለማስቀጠል የሚባዝኑ።

ከኢህአዴግ አባላት የምስማማበት ነጥብ አለኝ፤ መለስ ሁለመናቸው ነው። እሱ የተናገረውን ያደርጋሉ፣ ይፈፅማሉ። ከነሱ ጋር የምስማማበት ነጥብ ይሄ ነው። ይሄንን ነጥብ ትርጓሜ እንስጠው። 

የኢህአዴግ አባላት (እነሱ ራሳቸው እንደሚነግሩን) መለስ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ዕይታ ምንጫቸው ነው። አዎ! ነው። ይህ ማለት አባላቱ ምን መስራት እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው መለስ ይነግራቸው ነበር ማለት ነው። እነሱም ‘የታላቁ ባለራእይ መሪ’ ትእዛዞች ተቀብለው ይተገብሩ ነበር ማለት ነው። 

የመለስና የአባላቱ ግንኙነት እንዲህ ከነበረ መለስ dictate ያደርጋቸው ነበር ማለት ነው። በእንግሊዝኛው አጠራር ሌሎችን dictate የሚያደርግ መሪ Dictator ይባላል። ስለዚህ ከተግባራዊ ትርጓሜው ተነስተን መለስን ስንገልፀው Dictator ነበር ማለት ነው። “Dictator’ ወደ አማርኛ ስንመልሰው ‘አምባገነን’ (ብትግርኛ ‘ዉልቀ መላኺ’) የሚል ትርጓሜ ይይዛል። ስለዚህ ‘ሁሉም ወይም አብዛኞቹ የፓርቲው ስራዎች የመለስ ነበሩ’ በሚል ከተስማማን ‘መለስ አምባገነን ነበር’ በሚልም መስማማት ይኖርብናል።

እኔ ‘መለስ አምባገነን ነበር’ ሲል ‘የሁሉንም አድራጊ እሱ ነበር’ እያልኩኝ ነው። እናንተም በራሳቹሁ ሚድያና አንደበት ተመሳሳይ ነገር እየነገራችሁን ነው። ስለዚህ ሓሳባችን አንድ ነው። ተስማምተናል። በመለስ ስራና ስያሜ ላይ ልዩነት የለንም። 

(ስለ መለስ ላለመፃፍ ዕቅድ የነበረኝ ቢሆንም የመንግስት ሚድያዎች ግን ስለሱ እያስታወሱ አስቸገሩኝ)

It is so!!!

Saturday, August 24, 2013

በምዕራብ አርሲ ዞን በኮፈሌ ከተማ በመንግስት ወታደሮች የተጨፈጨፉት ንፁሃን ሙስሊሞች ስም ዝርዘር ይፋ ሆነ!!


በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን በኮፈሌ ከተማ በመንግስት ወታደሮ የተጨፈጨፉት ንፁሃን ሙስሊሞች መካከል የ14ቱ ሙስሊሞች ስም ለማወቅ ተችሏል።


በሻሸመኔ አጠቃላይ ሆስፒታል በተገኘ መረጃ መሰረት የተገደሉት ሙስሊሞች ቁጥር 16 መሆናቸው የታወቀ ሲሆን የ14ቱን ሙስሊሞች ስም ለማግኘት ተችሏል። እንደሚከተለው ይቀርባል:-

1.አደም ጀማል

2.ሌንጮ ጂልቻ

3.ሃቢብ ዋቤ

4.ጋቻኖ ቱሴ

5.ሙሃመድ ደ በልኡሶ

6.ጀማል አርሾ አርሲ

7.ሙሃመድ ኢዳዎ

8.አማን ቡሊ

9.ሙሃመድ ሃሰን

10.ረሺድ ቡርቃ

11.አቡሽ ኢብራሂም

12.ማሙሽ ኢብራሂም

13.ቱኬ በሶ

14.አብዱልከሪም አብዲኑር ሽፋ መሆናቸው ታውቋል፡፤

አላህ በጀነተል ፊርዶስ ያበሽራቸው!!!

ድል ለኢትዬጲያ ሙስሊሞች!!!

አላሁ አክበር!!!

ምንጭ: Abu Dawd Osman

የሌላውን ትግል ለማዳፈን መሯሯጥ ለውድቀት!

ነሃሴ 18 ቀን 2005

ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ የገባው የሰማያዊ ፓርቲና የ‘33ቱ’ ፓርቲዎች የውዝግብ ዜና የተስፋ ጭላንጭል የተፈጠረለትን የዋህ ህዝብ እጅግ ቅር ያሰኘና ያሳዘነ እንደሆነ ከራሳችን የተጎዳ ስሜት በመነሳት ስለተረዳን፤ ‘የተቃዋሚ ድርጅቶቻችን ይማሩበት ዘንድ’ በሚል የየዋህ መንገድ ይህችን ኣጭር መልዕክት ለማስተላለፍ ተገደድን።

በሃገራችን የፖለቲካ ታሪክ ድርጅቶች በሰለጠነ መንገድ ልዩነታቸውን በውይይት መፍታት ሲችሉ አልያም በልዩነታቸው ተቻችለው ሲጓዙ ሰምተን አናውቅም። ተቃዋሚ ድርጅቶቻችን በጋራ ለነፃነት ከመታገል ይልቅ እርስ በእርስ ከመናቆር ጀምሮ እስከመጠላለፍ ሲደርሱ ማየት የተለመደ ሆኗል። ይህ የድርጅቶች የእርስ በእርስ ግጭት የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነትና ፍትህን እየናፈቀ እንዲኖርና ገዢዎች በማናለብኝነት ያሻቸውን እየፈጸሙ፤ ህዝብም ሰባዊነቱን ተገፎ፣ አንገቱን ደፍቶ፣ እንዲኖር ከማድረግ ሌላ ምንም ፋይዳ እንዳላስገኘ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቃል። ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመኘው ድርጅቶች መጠላለፉን ትተው በጋራ የሚሰሩበትንና በመቻቻል የሚኖሩበትን ጊዜ ብቻ ነው። እዚህ ላይ ተቃዋሚ ድርጅቶቻችን ሊረዱት የሚገባው፤ እነርሱ እርስ በእርስ ሲጠላለፉ፤ ስንቱ ንጹህ ዜጋ በማያውቀው ሃጥያት በዘረኛው የወያኔ መንግስት እየተደበደበ፣ እየተገደለ፣ እየተሳቀቀ፣ በገዛ ሃገሩ እያለው እንደሌለው በረሃብና በእርዛት እያለቀ እንደሚገኝ፣ ሳይወድ በግዱ በቁጭት ባዶ ተስፋን እያለመ እንደሚኖር ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በምናያቸው የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች በሚያደርጉት ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች ያልተደሰተ ፍትህ ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብለን መገመት እጅግ ከባድ ነው። እኛም እንደ ኢትዮጵያዊነታችን ስንመኘው ለነበረው የትግል አቅጣጫን ስላመላከተን በቅርበት ከመከታተል ጀምሮ እስከ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን የምንችለውን ሁሉ ልናበረክት ቃል በመግባት እየተንቀሳቀስን እንገኛለን። ይህ የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እንቅስቃሴ በዚሁ ከቀጠለ የምንናፍቀውን ዲሞክራሲ፣ የምንመኘውን ነፃነትና፣ የምናልመውን የህዝብ የበላይነት ከማየት የሚያግደን አንዳችም ምክንያት አይኖርም። ስለሆነም ድርጅቶቻችን ሊወደሱና ተግባራቸውም እሰየሁ ሊባልና ሊበረታታ ይገባል እንላለን።

ምንም እንኳን እያንዳንዱ የፖለቲካ ድርጅት በትግሉ ዙሪያ መሳተፍ የራሱ የሆነ አስተዋፅዎ ቢኖረውም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሌላውን ለመጥለፍና ትግሉን ለማሰናከል ቅርብ የሆኑ ተቃዋሚዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ግልፅ ነው። አበው እንዳሉት “እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር” ይበጃልና፣ ህገመንግስቱ የሚፈቅድለትን መብት በመጠቀም በዘረኛው የወያኔ መንግስት የተጫነብንን አመታት ያስቆጠረውን የተቃውሞ ሰልፍ የማድረግ እገዳን በመስበር ፍርሃታችንን መሰባበር የቻለውን የሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባላትን ልናመሰግን እንወዳለን። በዚህ ኣጋጣሚ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባላት ነፃነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝምና በርቱ እያልን፤ ለሌሎች የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎቻችን የዲሞክራሲን የመናገርና የመፃፍ ነፃነት ምን ማለት እንደሆነና እንዴት ማስተናገድ እንዳለባቸው ቀድመው ማወቅ ይገባቸዋል ብለን እናምናለን።ይህ ካልሆነ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ስርዓት ለይቶ እንደማያያቸው እናምናለን። የኢትዮጵያ ህዝብ እውነትን የመለየት ችሎታውም፣ ብቃቱም፣ ልምዱም እንዳለው ሁላችንም ልንረዳ ይገባል። ስለሆነም ተቃዋሚ ድርጅቶቻችን የዲሞክራሲን ምንነት ለማወቅና ስ ህተታቸውን ለማስተካከል ቢሞክሩ እጅግ የተሻለ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ሌላ ዲክታተር የሚያስተናግድበት ጫንቃና ጀርባ ከእንግዲህ የለውም።ስለዚህ ከምቾትና ከፍርሃት ዞናቸው በመውጣትና በመተባበር ህዝብ ለነፃነቱ የሚያደርገውን ትግል ሊቀላቀሉ ይገባል። ይህ ካልሆነ ደግሞ ቢያንስ በመሬት ላይ ጥሩእየሰሩና እየሞከሩ የሚገኙትን ለመጥለፍና ትግሉን ለማፈን ከመሞከር ቢታቀቡ እጅግ መልካም ነው ስንል ምክራችንን እንለግሳለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ስምንቶቹ

መንግስት የሙት ዓመትና ተዝካር ማለት ትቶ ትኩረቱን ለሐገራዊ መግባባት ቢሰጥ – (ግርማ ሠይፉ ማሩ)

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ኢሕአዴግ ሆይ፤ በህግ አምላክ! ሕግ ይግዛህ!!

ቀጥሎ የሚታዩዋቸው ግለሰብ የመ/አ መሰቦ ማዳልቾ ይባላሉ፡፡ በደቡብ ክልል ጋሞ ጎፋ ዞን ከቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ማለትም ከፍትህ/ከመልካም አስተዳደር፤ ከማንነት/ከብሔር እና ከልማት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ዛሬ በአርባ ምንጭ ወህኒ ቤት ይገኛሉ፡፡ 

እርሳቸውን በሚያውቁት ዘንድ ተወዳጅ፤ ከማያውቁት ዘንድ ቶሎ ተግባቢ፤ በአጠቃላይ በአቀራረባቸው ትሁቱ፤ በባሕርያቸው መካሪና አስታራቂ፤ እንዲሁም ደግና ለተቸገሩት ደራሽ ባለ ሀብት እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ በተለይ መለያቸውም ይህ ነው፡፡ ባለሀብቱ የቁጫዎችን ጥያቄ በሚመለከት ከአሜሪካ ሬዲዮ (VOA)፤ ከጀርመን ሬዲዮ (DW)፤ እና ከሌሎች የፕሬስ የሚዲያዎች ጋር ቃለ-ምልልስ አድርገሃል፤ በዚህም “ሕዝብን ለአመጽ አነሳስተሃል”፤ በሚሉና በተያያዥ ክሶቸ የጋሞ ጎፋ ዞን ፖሊስ በቁጥጥር ሥሩ የዋሉት ባለፈው ቅዳሜ ነሐሴ 11ቀን 2005 ዓ.ም ማለዳ ላይ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ እንደሰማሁት ከሆነ፤ ፖሊሶች ግለሰቡን ለማሠር የፈለጉበት ምክንያት ምንም ይሁን ምን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተከተሉት መንገድ የሕግ አግባብነትን የተከተለ ነበር የሚል ድምዳሜ አለኝና ለሠራዊቱ አባላት ምስጋናዬ ይድረሳቸው፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከሌሎች እስረኞች ጋር ማለትም የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው በፍ/ቤት ተወሰኖላቸው ግን ማረሚያ ቤቱ ከሌሎች ተቋማትና ከተቋማቱ ሥራ ኃላፊዎች ጋር በማበር አልፈታም በማለት እስከ ዛሬዋ ቀን ማለትም ነሐሴ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ያልሆነበትን ሁኔታ የተለያዩ ሚዲያዎች በተደጋጋሚ ዘግበውበታል፡፡ የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና የፖለቲካ ድርጅቶች በቁጫ እየተፈፀመ የለውን ህገወጥ ድርጊት ያወገዙት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 13-እስረኞችን=ለ27-ቀናት፤ እንዲሁም 25-እስረኞችን ደግሞ=ለ19ቀናት አስሮ ካስቀመጣቸው እና ገና ዕጣ ፋንታቸው ካልታወቀላቸው ስመ ጥር የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በአንድ ላይ አርባምንጭ ወህኒ ቤት ይገኛሉ፡፡ ባለሀብቱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ወላይታ ሶዶ ከተማ ነበር፡፡ ወደ ሶዶ ከተማ የመጡትም ለሆቴላቸው፣ ለፋርማሲያቸው፣ ለእርሻዎቻቸው እና ለሌሎች ንግድ ተቋማቶቻቸው የሚሆኑ ቁሳቁሶችንና ለመግዛትና ሠራተኛ ለማፈላልግ እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የመ/አ መሰቦ ማዳልቾን ፖሊሶች ሲይዙዋቸው፣ ወላይታ ሶዶ ከሰላምበር ከ62-65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኝ ከተማ ሆኗን በማስታወስ፡- “ይህንን ያህል ኪ.ሜ ተጎዞ መምጣትንና ነዳጅ ማቃጠልን፤ ጎማንና የመኪና ውስጥ አካላትን (spare parts) መጉዳት ለምን አስፈለገ? እኔምኮ ቁርስ እንደበላሁ ወደ ሰላምበር ልመለስ ነበረኮ ለምን ይህንን ያህል ሽፍታ ለመያዝ እንደተሠማራ ኃይል ሌሊቱን በብርድና በውርጭ እንቅልፍ አጥታችሁ ለፋችሁብኝ” በማለት ለፖሊሶቹ ያለቸውን ርኅራኄ ገልጾላቸው የነበረበትን ሁኔታ ያጫወተኝ ሰው ለራሱ ከመሳቁም ባሻገር እኔንም ፈገግ አድርጎኝ ነበር፡፡

አቶ ዳንኤል ሺበሺ
የአንድነት ፓርቲ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ናቸው

- ምንጭ፡ www.fnotenetsanet.com

የአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ፤ ስላቅ እና ሀቅ

በአቤ ቶክቻው

ሰላም ወዳጄ… ተጠፋፍተናል ግዴለም እቅ….ፍ አድርጌ ሰላም ልበልዎት… እንዴት አሉልኝ.. እኔ የምለው አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሞቱ እንደዋዛ አንድ አመት ሞላቸው አይደለም እንዴ… ወይ ጉድ ጊዜው እንዴት ይሮጣል ጃል… ምን እንደሚያመጣልን እንጃለቱ፤ አሯሯጡ ግን ወርቅ በወርቅ እንደሚያንበሻብሽ አትሌት ነው፡፡ ይሁና እኛ እንደሆነ “በርታ ግፋ” እያልን ከመደገፍ ወደ ኋላ አንልም… አረ እንደውም ጊዜ ሆይ፤ …ሩጥልኝ ልጄ አምልጠልኝ ልጄ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ለኔውም አልበጄ… ብለን እንደ ዶክተር ፈቃደ አዘዘ እንቀኛለን፤

እናልዎ ወዳጄ ዛሬ የመጣው ይምጣ ብዬ ሙት ወቃሽ አታድርገኝም ሳልል የአቶ መለስ መሞት ለሰፊው ህዝብም፣ ሰፊ መሆን ለተሳነው ኢህአዴግም፣ መጠን አልባ ለሆኑት ተቃዋሚዎችም በጣም ስንሳለቅ ደግሞ ለወይዘሮ ሀዜብ ሳይቀር በርካታ ጥቅማጥቅሞች አሉት ብዬ ልሟገትልዎ ነው…!

በ22 ዓመት ውስጥ ያየናቸው አቶ መለስ እንደው ዝም ብለው የእነ ስምሃል አባት እንደው ዝም ብለው የነ ወይዘሮ አዜብ ባለቤት እንደው ዝም ብለው የአቶ ዜናዊ አስረስ ልጅ ብቻ አልነበሩም፡፡ አቶ መለስ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ኢህአዴግ ሊቀመንበር ከዛም ውስጥ ደግሞ እጅግ አደገኛ የሚባለው ህውሃት አባወራ የሀገሪቱ ጦር ሃይሎቹ አዛዥ (አሃ ለካስ ጦር ሃይሎች የድሮው ነው… እንደው የድሮ ስርዓት ናፋቂ የሆንኩ ሰውዬ… አሁን መከላከያ ነው ማለት ያለብን… በመከላከያው ውስጥ ጦር አለ ከተባለ እንኳ ጦሩ አቶ መለስ ነበሩ… ስለዚህ የጦር ሃይሎች አዛዥ ሳይሆኑ በመከላከያ ውስጥ ጦር የሆኑ ሰውዬ ነበሩ ብሎ አለመመስከር ጡር ነው… ) በጥቅሉ ሰውዬው የመላዋ ኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ ነበሩ፡፡

አሁን እኒህ ሰውዬ ሞተዋል… እስቲ ከተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ጋር አያይዘን የሞታቸውን ጥቅማ ጥቅሞች እንዘርዝር…

ለአባይ ግድብ ሲሉ አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!

አባይን አቶ መለስ እንዴት እንዴት ይገደብ ብለው እንደጀመሩት ተነጋግረን ተነጋግረን መቼም ከስምምነት ላይ የደረስን መስለኛል፡፡ አባይዬ ድንገት ያለ ዕቅድ… ያቺ እነ ሙባረክን እንደ ሾላ ፍሬ ርግፍ ርግፍ ያደረገች አብዮት ወደ እኛም ትመጣ ይሆናል… በሚል ስጋት ነው ለማስቀየሻ ተብላ ነው የተጀመረችው፡፡

ለዚህ ዋና ማስረጃ በአምስት አመቱ ትራስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ አለመፃፏ ሲሆን ሌላው ደግሞ የፕሮጀክቷ ስም አሁንም አሁንም መቀያየሩ ድሮውንም ቃሚዎች “በምርቃና” እንደሚሉት አይነት የታሰበች ድንገቴ ስራ መሆኗን ያሳብቃል፡፡ በነገራችን ላይ አሁንም ጭምር በተለይ ውጪ ሀገር የሚኖሩ “የኢህአዴግ ወጣት ክንፎች” የአባይን ግድብ “ሚሊንየም ዳም” ነው የሚሏት…! ህዳሴ መባሏን ከነጭርሹም አለሰሙም!

የሆነው ሆኖ አባይን አቶ መለስ ድንገት እንደጀመሯት ሁሉ ድነገት ያቋርጧታል የሚል ስጋት ሰቅዞ የያዛቸው ብዙዎች ነበሩ… (ብዙዎች ያልኩት አካብዶ ለማውራት እንዲመቸኝ ብዬ እንጂ… እንዲህ የሚያስቡት ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ ስታስቲክስ አልሰራሁም፡፡ ነገር ግን ያናገርኳቸው ሁሉ የሰጡኝ ማብራሪያ አሳማኝ ነበር፡፡)  እንደሚታወቀው አባይን ለመገደብ የሚጠይቀው የገንዘብ አቅም ቀላል አይደለም፡፡ በየመስሪያቤቱ በጥፊም በርግጫም የሚደረገው መዋጮ አስከምን ድረስ እንደሚያስኬድ የሚያውቁት እርሳቸው ብቻ ነበሩ… እናም የሆነ ቀን የሆነ ቀን ማጣፊያው ያጠራቸው ቀን መለኛው መሌ በሆነ መላ ግንባታው እንዲቋረጥ ያደርጉ ነበር የሚለው ነገር ውሃ የሚያነሳ ሆኖ አግኝቼዋለሁ… ይህንን እያንሰላሰልን ታድያ ምን ይበጃል እያልን ስንጨነቅ አቶ መለስ ሞቱ… ለአባይ ሲባልስ እንኳን ሞቱ! ልክ እርሳቸው ሲሞቱ ሌጋሲን ማስቀጠል በሚለው መርህ ከዋናዎቹ አንዱ አባይ ግድብ አይቋረጥም የሚለው ሆነ፡፡ እሰይ እንኳንም አልተቋረጠ፡፡ እንኳንም ሞቱልን…!

ለተቃዋሚዎች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!

ተቃዋሚዎች በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግን ሲቃወሙ ከሁሉ በላይ የሚበረታባቸው የአቶ መለስ ግልምጫ ሽሙጥ እና እርምጃ ነበር፡፡ ሲያሻቸው ጣት እንቆርጣለን እያሉ ሲያሰኛቸው ሰብስበው እስርቤት እየላኩ አቶ መለስ ተቃዋሚዎች ላይ እንደሚጨክኑት ኢህአዴግ አይጨክንባቸውም፡፡ እውነቱን እንበለው ካልን ደግሞ መጨከን ብቻም ሳይሆን በፖለቲካው ቼዝም አቶ መለስን ተቃዋሚዎቹ አይችሏቸውም ነበር፡፡ ተቃዋሚዎቹ ፈረሳቸውን ቆስቁሰው ገና “ቼ…” ብለው ሮጥ ሮጥ ማለት ሲጀምሩ መለስ በወታደሮቻቸው ፈረሶቻቸውን እየሰነከሉ፤ ንግስታቸውን “ቼዝ” እያሉ ተቃዋሚዎቹን መላወሻ አሳጥተዋቸው ነበር፡፡

አሁን አቶ መለስ ሞተውላቸዋል፡፡ ተቃዋሚዎች መቼም ጨካኞች እንዳይባሉ ሰግተው በአቶ መለስ ሞት ሀዘናቸውን ሲገልፁ ቢሰማም ውስጥ ውስጡን ግን እሰይ ግልግል እንደሚሉ ማወቅ አያቅተንም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ተቃዋሚዎቹ ትንሽ ጠንከር ካሉ ኢህአዴግ ውስጥ ክፉኛ የሚገዳደራቸው አለ ብሎ ማመን ይቸግራል፡፡ ስለዚህም ለተቃዋሚዎች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!

ለራሱ ለኢህአዴግ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!

በተለይ ከሆነ ጊዜ በኋላ ይመስለኛል ህውሃት ለሁለት ቃቃቃ…ቃ ብሎ ከተሰነጠቀ ጊዜ በኋላ የኢህአዴግ ስብዕና ኮስምኖ የአቶ መለስ ዜናዊ ስብዕና ደግሞ እጅግ በጣም የጎላበት ወቅት ነበር፡፡ አረ ከነጭርሹ መለስ ከልለውን ኢህአዴግን ማየት ተስኖን ነበር…! በዛ አያያዙ ጥቂት አመታት ቢገፉ ኖሮ ኢህአዴግዬ መለስ በተባለ ቅብ ተሸፍና እሰከመፈጠሯም እንረሳት ነበር፡፡

አሁን ግን መለስ ሞቱ ኢህአዴግ የሚባል ፓርቲም ምን አይነት ቅርጽ እና መልክ እንዳለው ሊታወቅ በቃ፡፡ ታድያ ለኢህአዴግ ሲባል ቅርፀ ግንባሯ እንዲታይ ሲባል፤ ያለ መለስ መኖር እንደምትችል ለማሳየት ሲባል፣ እንኳን መለስ ሞቱላት ብንል ምን ግፍ ተናገርን ይባላል፡፡

ወላ ለወይዘሮ አዜብ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!

መጣች ስላቋ… ወይዘሮ አዜብ ቀላል ክብሮ ሆኑ እንዴ…! ክብሮ ማለት አራዶቹ ከበረ ከሚለው አማርኛ ቃል የወሰዷት ስትሆን የተከበረ ለሚባል ሰው የሚሰጥ ማዕረግ ነው፡፡ አዎ ወሮ አዜብ ክብሮ ሆነዋል፡፡ የመለስ ፋውንዴሽን ፕረዘዳንትነት አቶ  መለስ ባይሞቱ ኖሮ ከየት ይመጣ ነበር… አረ እንኳን ሞቱላቸው… (እዝችጋ እንኳ ጨክኛለሁ ይቅር ይበለኝ!) የምር ግን ወይዘሮ አዜብ እንደልቸው መልካም ገፅታቸውን እንዲገነቡ የአቶ መለስ ሞት ትልቅ እድል ሰጥቷቸ
ዋል ብዬ አምናለሁ… ዝም ብለን ከመረመርን ወይዘሮ አዜብ በአቶ መለስ ሞት ጉዳት እንደገጠማቸው ሁላ በርካታ ትቅማጥቅሞችንም እንዳገኙ ግን መጠርጠር አያቅተንም!

ለችግኝ ተከላ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!

አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት ዘመናቸው እና በበትረ ስልጣናቸው ጊዜ ሰዎች አጥብቀው የሚያማርሯቸው በችግር ተከላ ነበር፡፡ አሁን ግን ሞቱ፣ አመትም ሞላቸው በስማቸውም በርካታ ችግኞች እየተተከሉላቸው ነው፡፡ በእውኑ ለእነዚህ ችግኞች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ ብንል ማነው እርኩስ የሚለን…! ማንም!

የደህንነትና የፖሊስ ሀላፊዎች የሙስሊሙን ህብረተሰብ የመብት ጥያቄ ለማዳፈን እንደሚሰሩ ገለጹ!

ድምፃችን ይሰማ

ቅዳሜ ነሐሴ 18/2005

‹‹መንግስት መስጂዶችን ከአክራሪዎች ቀምቶ ለእኛ ሊሰጠን ይገባል›› የመንግስታዊው ሃይማኖት አቀንቃኝ ግለሰብ

የደህንነትና የፖሊስ ሀላፊዎች የሙስሊሙን ህብረተሰብ የመብት ይከበር ጥያቄ ለማኮላሸት መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡ ሀላፊዎቹ ይህን የገለጹት ለሁለት ቀናት በተካሄደ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ ረቡእና ሐሙስ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማእከል በተደረገው በዚህ ስብሰባ ህዝብ ያወረዳቸው የመጅሊስ ሹመኞች፣ የመስጂድ ኮሚቴዎች፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ ኢማሞች፣ ሙአዚኖች እና የመንግስታዊው ሃይማኖት አቀንቃኞች የተገኙ ሲሆን ዋነኛ አጀንዳውን ያደረገውም ‹‹አክራሪነት በመከላከልና ጸጥታን በማስፈን›› ርእሰ ጉዳይ መሆኑ ታውቋል፡፡ መድረኩን ይመሩ የነበሩትም ከፍተኛ የደህነት ሹሞች መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ በዚሁ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉ ቀድመው የተመረጡና መናገሪያ አጀንዳ የተያዘላቸው ግለሰቦች ‹‹አክራሪዎችን ልንታገስ አይገባም፣ ድምጻችን ይሰማ የሚሉት የአክራሪዎችን ድምጽ ነው›› የሚሉና መሰል ዘላፋዎችና ዛቻዎችን ሰንዝረዋል፡፡

መንግስት ትእግስቱ በዝቷል፣ አክራሪዎችን ልንታገሳቸው አይገባም በሚል ሀሳባቸውን የገለጹትና በተሰብሳቢዎች መካከል ተሰግስገበው እንዲገቡ የተደረጉት ግለሰቦች አንንዶቹ የፖለቲካ ስራ የሚያከናውኑና የእስልምና እምነት ተከታይ ያልሆኑ ጭምር መሆናቸው ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በመድረኩ ንግግር ሲያደርጉ የታዩት አንዳንዶቹም በየእለቱ በኢቴቪ የአዲስ አበባ ሙስሊም ነዋሪ እየተባሉ ለዜና ግብአትነት የሚውሉ ናቸው፡፡ የመንግስታዊው ሃይማኖት አቀንቃኝ ግለሰብ በበኩሉ ‹‹መንግስት መስጂዶችን ከአክራሪዎች ቀምቶ ለእኛ ሊሰጠን ይገባል›› በማለት የጠየቀ ሲሆን የመንግስት ሀላፊዎቹም ተቃውሞውን ለማፈንና በየሰፈሩ ያሉ ሙስሊሞችን ተቃውሞ ለመግታት ማሰራቸውን እንደሚቀጥሉ አሳስበዋል፡፡ በስብሰባው የተሳተታተፉ ብዙዎቹ ኢማሞች ሀሳባቸውን ከመግለጽ በመቆጠብ ስብሰባውን በፍርሃት ተካፍለው የጨረሱ ሲሆን በዚህ ስብሰባ ያልተገኙ ኢማሞችንም መንግስት በትእግስት እንደማይመለከታቸው ከመድረኩ የነበሩት የደህንነት ሃለፊዎች ተናግረዋል፡፡ 

አላሁ አክበር!

ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአንድ ዓመት 100 ዳኞች ለቀቁ!!

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ

“መረጃው የተሳሳተና ከእውነት የራቀ ነው” የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት

ዘንድሮ ብቻ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በዳኝነት ሙያ ያገለግሉ የነበሩ መቶ ዳኞች ስራ መልቀቃቸውን ምንጮች ገለፁ፡፡ ከ86 በላይ ዳኞችም የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው መልስ እየተጠባበቁ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ የኔነህ ስመኝ በበኩላቸው፤ መረጃው የተሳሳተና ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ “እንደማንኛውም መስሪያ ቤት አንዳንድ መልቀቂያዎች ይገባሉ፤ ይስተናገዳሉ” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በተጠቀሰው መጠን ዳኞች ስለመልቀቃቸውም ሆነ መልቀቂያ ስለማስገባታቸው የማውቀው ነገር የለም ብለዋል፡፡

ዳኞቹ በደሞዝ ማነስ ፣በጥቅማጥቅም ማጣት፣በእርከን እድገት አለመኖርና በስራቸው ላይ በሚደርስባቸው ጣልቃ ገብነት ከስራ ለመልቀቅ መገደዳቸውን ምንጮቹ ገልፀው፣ በቅርቡ የገቡ መልቀቂያዎች ከሶስት ወር በፊት እንደማይስተናገዱ እየተነገራቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ “በክልላችን የዳኛ ደሞዝ ከፖሊስ ደሞዝ ያንሳል” ያሉት አንድ ስራ የለቀቁ ዳኛ፤ የፖሊስ የስራ ሂደት 2800 ብር ደሞዝ ሲያገኝ ዳኛ ግን 2639 ብር ብቻ እንደሚያገኝ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የዳኝነት ስራ የህሊና ስራ እንደመሆኑ አንድ ዳኛ ለአድልኦና ለጉበኝነት እንዳይጋለጥና ፍትህ እንዳያዛባ ምቹ ሁኔታዎች ሊፈጠሩለት ይገባል ያሉት ምንጮቹ፤ በክልሉ ይህ ስለማይመቻች ፍትህ ከማዛባት ስራውን መልቀቅና መቸገር ይሻላል በሚል ዳኞች ስራ እንደለቀቁና ሌሎችም ለመልቀቅ ማመልከቻ እያስገቡ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ም/ቤቱ የዳኞች በብዛት መልቀቅ ስላሳሰበው ስብሰባ ካደረገ በኋላ ዳኞች በስራቸው ላይ እንዲቆዩ ጭማሪ ይደረግላቸው ብሎ መወሰኑን የጠቆሙ ሌላ ሥራ የለቀቁ ዳኛ፤ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላሉት 500 ብርና ከዚያ በላይ ሲጨመርላቸው ታች ሆነው ብዙ ለሚሰሩትና ለሚደክሙት ግን በ150 ብር ጭማሪ ብቻ መሸንገላቸው ዳኞችን አበሳጭቷቸዋል ብለዋል፡፡ ይህም ለመልቀቃቸው ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ፍ/ቤቱ በየአመቱ ከስልጠና ማዕከል የሚወጡ ዳኞችን እንደሚቀበል የገለፁት ምንጮቹ፤ እነዚህ ዳኞች ሲቀጠሩ በፍ/ቤት ሁለት አመት የማገልገል ግዴታ እንዳለባቸውና ሁለት አመቱን ሳይጨርሱ ከለቀቁ 50 ሺህ ብር እንደሚቀጡ ጠቁመው፤ ሙያተኛው ላይ የሚደረግ ጫና መቆም አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “ከሙያው ስነ-ምግባር የተነሳ ዳኛ ትርፍ ስራ መስራት አይችልም” ያሉት እነዚሁ ዳኞች፤ በዚህ የተነሳ የዳኛው ህይወት ከኑሮ ውድነቱ ጋር መጣጣም አልቻለም ብለዋል፡፡ በሌላው የመንግስት መስሪያ ቤት የተለያዩ ማበረታቻዎችና የደሞዝ እርከን ጭማሪ እንደሚደረግ ጠቁመው፣ በፍ/ቤት አካባቢ ይህ አይነት አሠራር የለም፣ አስር አመት የሰራም ሆነ ዛሬ የተሾመ ዳኛ እኩል ደሞዝ ነው ያላቸው ብለዋል፡፡

አንድነት በፍቼ ከተማ አባላቱ መደብደባቸውን አወገዘ

“ወደ ስፍራው ከመድረሳቸው በፊት ጥበቃ እንዲደረግላቸው አላሳወቁም”

- (የዞኑ ኦህዴድ ጽ/ቤት)

አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ነገ በፍቼ ከተማ የሚካሄደውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማስተባበር በስፍራው የተገኙት ሁለት አባላቱ መደብደባቸውን አወገዘ፡፡ የፓርቲው የህግ ክፍል ድርጊቱን በፈፀሙ አካላት ላይ ክስ ለመመስረት ወደ ስፍራው እንደሚጓዝ ተገልጿል፡፡

የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ነብዩ ባዘዘው እና ባልደረባቸው አቶ መሳይ ትኩ፤ ነገ የሚካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስተባበርና አንዳንድ ዝግጅቶችን ለማድረግ ረቡዕ አስር ሰዓት ተኩል አካባቢ ፍቼ ከተማ መድረሳቸውን የገለፁት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ፤ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ ባረፉበት ሆቴል በከተማው የፀጥታ ዘርፍ ምክትል ሃላፊና ሌሎች ፊታቸውን በሸፈኑ 11 ሰዎች ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸውና ራሳቸውን ሲስቱ ጥለዋቸው መሄዳቸውን ገልፀዋል፡፡ “በስፍራው የደረሰው ፖሊስ ህገ ወጥ ድርጊት የፈፀሙትን ይዞ ወደ ህግ ማቅረብ ሲገባው፣ ዱላቸውን ቀምቶ ወደቤታቸው መሸኘቱ አይን ያወጣ የህግ ጥሰት ነው” ያሉት አቶ ዳንኤል፤ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀስ ህጋዊ ፓርቲ አባላትን በዚህ መልኩ ማሰቃየቱ የህግ የበላይነት እየተጣሰ መሆኑን ያመላክታል ብለዋል፡፡ 

ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድና ክስ ለመመስረት የፓርቲው የህግ ክፍል ወደዞኑ እንደሚያመራም አቶ ዳንኤል በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ አንድነት የጀመረው የሶስት ወር የህዝብ ንቅናቄ አካል የሆነውን ሰላማዊ ሰልፍ ነገ በባሌ ሮቤ፣ በአዳማና በፍቼ ለማከናወን እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ዳንኤል፤ ይህን እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ የፍቼ ከተማ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊዎችና ግብረ አበሮቻቸው ያደረሱትን ህገ-ወጥ ድርጊት ፓርቲው በቸልታ እንደማያልፈው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ድብደባ ተፈፀመባቸው ወደተባሉት አቶ ነብዩ ባዘዘው ደውለን በሰጡን መረጃ፤ የከተማው የፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ የሆኑት አቶ ሃይለየሱስ በየነና ሌሎች 11 ሰዎች እንደደበደቧቸው ገልፀው፤ “በመጀመሪያ እኛ የያዝነውን አልጋ ካልያዝኩ የሚል አንድ ሰው ልከው ነገር ፈለጉን፤ ግን እኛ ዝም አልን” ብለዋል፡፡ 

የሆቴሉ ባለቤቶች “መጀመሪያ አከራይተነዋል፤ አሁን ለመጣ ሰው እንዴት እንሰጣለን” በሚል በተነሳ ክርክር፣ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊው እና ግብረ አበሮቻቸው ከፍተኛ ድብደባ እንዳደረሱባቸው የተናገሩት አቶ ነብዩ፤ እነዚህ ሰዎች ደብድበዋቸው ከሄዱ በኋላ ፖሊሶች ወደመኝታቸው ገብተው የፓርቲውን የፍቃድ ወረቀት፣ መታወቂያቸውን፣ ቃለ ጉባኤና ሌሎች ቁሳቁሶችን በመውሰዳቸው ምንም አይነት ስራ ለመስራት መቸገራቸውን ጠቁመዋል፡፡ በድብደባው እሳቸውም ሆኑ ባልደረባቸው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ጠቁመው፤ ባልደረባቸው አቶ መሳይ ትኩ በግራ እጃቸው ላይ ስብራት እንደደረሰባቸው ሀኪሞች መናገራቸውን ገልፀዋል፡፡ 

የሰሜን ሸዋ ዞን የኦህዴድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሰለሞን መኮንን ጋር ቀርበው ልብሳቸውን በማውለቅ የደረሰባቸውን ጉዳት ማሳየታቸውን የተናገሩት አቶ ነብዩ፤ ሃላፊው ይህ ህገ ወጥ ድርጊት ነው፤ ፓርቲያችንም ሆነ መንግስታችን አይቀበለውም፤ በአስቸኳይ ኮሚቴ አቋቁመን ድርጊቱን የፈፀሙ ግለሰቦች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንወስዳለን፤ እናንተም ክስ መስርቱ ብለውን ይህን እያደረግን ነው ብለዋል፡፡ 

“ፖሊሶችም፤ ደብዳቤዎቹን ወደ ህግ ሳያቀርቡ በሰላም መሸኘታቸው በፓርቲያችን ላይ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሴራ እየተፈፀመ መሆኑን ማሳያ ነው፤ እኛ ግን ሰላማዊ ትግላችንን እንቀጥላለን” ብለዋል አቶ ነብዩ፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን የኦህዴድ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰለሞን መኮንን በበኩላቸው፤ ጉዳቱ የደረሰባቸው የአንድነት ፓርቲ ሰዎች ቀደም ብለው ወደ ከተማው ስለመምጣታቸው ለኦህዴድ ጽ/ቤትም ሆነ ለፀጥታ አካሉ አለማሳወቃቸውን ገልፀው፤ ይህን ቢያደርጉ ኖሮ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይችል እንደነበር አብራርተዋል፡፡ 
“በተፈፀመው ድርጊት እንደግለሰብም እንደ መንግስት አመራርም በጣም አዝኛለሁ” ያሉት የጽ/ቤት ሀላፊው፤ ጉዳቱን ያደረሰባቸው አንድ ግለሰብና የባጃጅ ሹፌር እንደሆነ መስማታቸውንና ይህም ግለሰብ በሀገሪቱ ህግ መሰረት ተጠያቂ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡ 

የፀጥታ ዘርፍ ም/ሀላፊውና ሌሎች የፖሊስ አካላት የፓርቲውን አባላት ደበደቡ የተባለውን ግን አቶ ሰለሞን አስተባብለዋል። የማሳወቂያ ደብዳቤውን በተመለከተ፤ ሰዎቹ ለከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት ያስገቡት ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ መሆኑን ከከንቲባው ጽ/ቤት መስማታቸውንም ሀላፊው አብራርተዋል፡፡ 

“ያስገቡት ደብዳቤ ፎርማሊቲውን ያሟላ አያሟላ ባላውቅም ደብዳቤው መስፈርቱን አሟልቶ ሰልፉ ከተፈቀደ የፀጥታ አካሉ ጥበቃ ያደርግላቸዋል” በማለት አረጋግጠዋል፡፡ መደብደባቸውን ከተናገሩ በኋላ ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ 
ጉዳት የደረሰባቸው የፓርቲው አባላት ድብደባውን በፈፀሙ ግለሰቦች ላይ መረጃ አሰባስበው ክስ መመስረት እንደሚችሉም አቶ ሰለሞን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ

Friday, August 23, 2013

ምን ያልተባለ ነበር ?-- ሰሚ ጠፋ እንጂ፤ ዋሾ በረከተ እንጂ!

ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ ወቅታዊ ሐተታ!

ሊንኩን በመጫን ዳውን ሎድ አድርገው ሃተታውን ያንብቡ።

http://articles2u.files.wordpress.com/2013/08/finote-commentary-august-a1.pdf

ለእምነት ነፃነት የምናደርገውን ትግል ለሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ ለዜግነት ክብር እና ለሀገር ነፃነት ከምናደርገው ትግል ጋር እናቀናጅ!!!

ትንሽነቱ በፈጠረበት ስጋት ምክንያት ሁሉንም ነገር ካልተቆጣጠረ በጉልበት የያዘውን ሥልጣን የሚያጣ የሚመስለው እና በዚህም ሳቢያ ሁሉም ነገር ውስጥ እጁን የሚነክረው ወያኔ ራሱን በገዢነት ከሾመበት እለት ጀምሮ የሃይማኖት ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እንደተጋ ነው። በእኛ በኢትዮጵያዊነት ዳተኝነት ታግዞም ትጋቱ ውጤት እያስገኘለት ነው።

ወያኔ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክህነትን ከፓትሪያርክ ጀምሮ እስከ ደብር አለቆች ድረስ ያለው መንፈሳዊ ሹመት ተቆጣጥሯል። አሁን የቀየረው የቤተክርስቲያኒቷን ሃይማኖታዊ ቀኖናን መቀየር ነው። ወያኔ በሥልጣን ላይ ከቆየ ይህንንም ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን በእስልምና እምነት ላይ ተግባራዊ እያደረገ ካለው መገንዘብ ይቻላል።

ልክ እንደ ክርስትናው ሁሉ ወያኔ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን (መጅሊስ) በራሱ ካድሬዎች ሞልቶት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮታል። እስልምና ላይ ግን የሃይማኖት ተቋማትን ከመቆጣጠር አልፎ በቀኖና ጉዳይ በመግባት የራሱን “ምርጥ እስልምና” እያስተዋወቀ ነው። ዛሬ በሙስሊሞች ላይ የመጣው ነገ በክርስቲያኖችም ላይ የሚመጣውን አመላካች ነው።

እርግጥ ነው ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች የወያኔን ጥቃት በፀጋ አልተቀበሉትም። ሁሉም በየራሳቸው መንገድ የወያኔን ሁሉን-ጠቅላይ አገዛዝ እየተቃወሙትና እየታገሉት ነው። ዛሬ የወያኔ ጥቃት የደረሰበት ደረጃ ግን የሁለቱን ሃይማኖቶች አማኖችን ኅብረት የሚጠይቅ ሆኗል። ወያኔ ደግሞ በበኩሉ ይህ መከባበርና መተባበር እንዳይኖር ጥረት እያደረገ ነው።

የሁለቱም ትላልቅ ሃይማኖቶች ምዕመናን ለእምነታቸውና ለእምነት ተቋሞቻቸው ነፃነት በሚታገሉበት በአሁኑ ሰዓት “ጅራፍ እራሱ ገርፎ ራሱ ይጮህ” እንዲሉ ወያኔ ድምፃቸውን ቀምቶ በደሉን ለማጠናከር እየተጠቀመበት ነው። እፍረት ያልፈጠረባቸው የወያኔ ሹማምንት “መንግሥት በእምነታችን ጉዳይ ጣልቃ አይግባብን” እያሉ አቤት የሚሉትን ምዕመናንን “በፓለቲካ ጉዳይ ጣልቃ ገባችሁ፤ ይህ ደግሞ በኛ ሕግ ክልክል ነው” እያለ ይከሳቸዋል።

“ሃይማኖት በመንግሥት፤ መንግሥትም በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ አይገቡም” የሚለውን ሰፊ ተቀባይነት ያለው መርህ ወያኔ መሠሪ በሆነ ተንኮሉ “ሃይማኖት በፓለቲካ፤ ፓለቲካም በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም” ወደሚል እጅግ አደገኛ መርህ እየቀየረው ነው።

“በሃይማኖትና መንግሥት” እና “በሃይማኖትና ፓለቲካ” መካከል ያለው ግዙፍ ልዩነት ለአብዛኛው ምዕመን ግልጽ አይደለም በሚል ግብዝነት ነገሮችን በማጣመም ምዕመናንን በማደናገር ለፍረጃ ያመቻቻቸዋል።

አዎ ሃይማኖትና መንግሥት መለያየት አለባቸው። ኢትዮጵያዊ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች እየጠየቁ ያለውም ወያኔ ይህንን መርህ እንዲያከብር ነው። “ወያኔ ሆይ!!! በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ አትግባብን!” እያሉት ነው።

ሃይማኖትና ፓለቲካ ግን በብዙ ክሮች የተቆላለፉ ነገሮች ናቸው። ለሃይማኖት ነፃነት መከራከር ራሱ ፓለቲካ ነው። ለሰብዓዊ መብቶች መከበር መከራከርም ትልቅ ፓለቲካ ነው። የሁለቱ ሃይማኖቶች አማኞች ይከባበሩ፤ ይተባበሩ ማለትም ፓለቲካ ነው። ይህ እንዳይፈጠር ነው ወያኔ ሃይማኖትና ፓለቲካ እሳትና ጭድ አድርጎ ሊስላቸው የሚዳዳው።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢትዮጵያዊያን ምዕመናን በሃይማኖትና ፓለቲካ አንድነትና ልዩነት ላይ የጠራ አቋም መያዛቸው ትግላችን ያግዛል ብሎ ያምናል።

ሃይማኖትና መንግሥት መለያየታቸው ተገቢ ነው። ሃይማኖትና ፓለቲካ ግን አንድ ባይሆኑም በብዙ መንገዶች የሚደጋገፉ ናቸው። ሃይማኖቶች ለእምነት ነፃነት፣ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ ለዜግነት ክብር፣ ለሀገር ነፃነት እና መሰል ጉዳዮች በግንባር ቀደም መታገል ይኖርባቸዋል። በታሪካችን ውስጥ ታቦቶች ጦር ሜዳዎች ዘምተው አርበኞችን አበረታተዋል። ይህ ዛሬም ሊደረግ የሚገባው የተቀደሰ ተግባር ነው።

በዛሬ የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ሃይማኖትና የሃይማኖት ተቋማትን ከወያኔ መዳፍ ማውጣት ሀገርን ከወያኔ
መዳፍ ከማዳን ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ጉዳይ ሆኗል። ስለሆነም ለሃይማኖት ነፃነት የምናደርገው ትግል ለሀገራችንም የምናደርገው ትግል አካል ነው።

ወያኔ በሃይማኖቶቻችን፣ በሀገራችን ብሎ በራሳችን ላይ የመጣ እኩይ ኃይል ነው።

ስለሆነም፣ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሃይማኖት ነፃነት የምናደርገውን ትግል ለሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ ለዜግነት ክብር እና ለሀገር ነፃነት ከምናደርገው ትግል ጋር እንድናቀናጅ ወገናዊ ጥሪ ያደርጋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

አምስተኛው ባርነት – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

በጥንቱ ስርዓት፣ አንድ ሰው ከአራቱ በአንዱ መንገድ ባሪያ ይሆናል። የመጀመሪያው በጦርነት ተሸንፎ ከተማረከ ፣ ሌላው እዳውን መክፈል አልችል ብሎ በእዳ ከተያዘ ፣ ሶስተኛው ከባሪያ ቤተሰብ የተወለደ ከሆነ በውርስ፣ አራተኛው ደግሞ ባሪያ ፈንጋዮች ይዘው ከሸጡት ነው። በዚህ ዘመን የባሪያ ንግድ ቢጠፋም፣ ባርነት ግን አልጠፋም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንዲያውም አምስተኛውን የባርነት መንገድ እያየን ነው፤ ይሄ ባርነት በባህሪው እስከዛሬ ከታዩት ሁሉ የተለየና አስገራሚም ነው። እመለስበታለሁ።

ባሪያ ማለት፣ የጌታውን እጅ አይቶ የሚያድር፣ በራሱ ነጻነት የሌለው፣ ሰምቶ የመቀበል እንጅ ሰምቶ የመመለስ መብት የሌለው፣ በግዑዝና በነጻ-ሰው መካከል ያለ ፍጥረት ነው። ባርያ ሰውን ሰው የሚያደርገውን ነጻነት ሙሉ በሙሉ የተገፈፈ በመሆኑ፣ ከሰው ተርታ የሚመደበው ስለሚመገብ፣ ስለሚለብስ፣ መጠለያ ስላለው፣ ቋንቋ ስለሚጠቀም እና አውራጣት ስላለው ብቻ ነው፤ ከዚያ በተረፈ ግን የጭነት እንስሳ ማለት ነው። ባሪያ በእግዚአብሄር አምሳል በመፈጠሩ ክፉና ደጉን የመለየት ስልጣን ቢሰጠውም ፣ ስልጣኑን በጌታው በመነጠቁ ፣ ሁልጊዜ የጌታውን ደግ ነገር ብቻ እያየ እና እያመሰገነ የሚኖር ፍጥረት ነው።

በአሁኑ ጊዜ የሚታየው አምስተኛው የባርነት መንገድ 40 በ60 ከሚባለው የቤት ግንባታ ጋር የተያያዘ ነው፤ በዚህ የባርነት መንገድ ለመጓዝ የወሰነው ደግሞ ዲያስፖራው ( በውጭ የሚኖረው) ኢትዮጵያዊ ነው። መንግስት ለዲያስፖራው 40/በ60ን ሲያዘጋጅ ሁለት አላማዎችን ታሳቢ አድርጎ ነው- ዲያስፖራው ጥሮ ግሮ ያገኘውን ሀብት ሰብስቦ ደቋናውን ለመሙላት እና ዲያስፖራው ስለነጻነቱ እንዳይጠይቅ ወይም መንግስትን እንዳይቃወም አፍ ለማዘጋት።

40 /በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራ እናት እና አባቱ፣ እህትና ወንድሙ፣ በአጠቃላይ የአገሩ ሰዎች ቢገደሉ፣ ቢታሰሩ ፣ ቢሰደዱ፣ ቢራቡ ፣ ቢጠሙ፣ ” ለምን?” ብሎ አደባባይ ወጥቶ የመጠየቅ እና የመቃወም ነጻነት አይኖረውም፤ ነጻነቱን በ40/በ60 ተገፎአል። ለሌላው መብት ሊሟገት ቀርቶ፣ በጥፊ ቢመታም እንኳን፣ “ጥፊው እንዴት ይጣፍጣል፣ እባክህ ግራ ጉንጨንም ድገምልኝ” ከማለት ውጭ፣ “ለምን ትመታኛለህ?’ ብሎ የአባትና እናቱን ወኔ ቀስቅሶ ብድሩን የመመለሻ ልብ አይኖረውም። እስክንድር ነጋ፣ አበበ በለው፣ ብርሀኑ ነጋ፣ እና ሌሎችም፣ ከስጋቸው ድሎት ነጻነታቸውን ያስቀደሙ በርካታ ኢትዮጵያውያን፣ ባርነት በቃን በማለታቸው፣ ጥረው ግረው ያፈሩትን ሀብት ተነጥቀዋል።

40/በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራ ስለወገኑ ለመጮህ ከእንግዲህ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ከተሞች እጅግም አይታይም፣ ለይሉንታ ቢታይ እንኳ ፊቱን በወረቀት ሸፍኖ ከሁዋላ ከመሰለፍ የዘለለ ሚና አይኖረውም። በነጻነት አገር እየኖሩ ገንዘብ ከፍሎ፣ በፍላጎት ባርነትን መምርጥ ማለት ይህ አይደለምን? የሚገዛ የለም እንጅ እነዚህ ሰዎች እኮ መንግስት ቢሸጣቸው እንኳ ምንም የሚናገሩ አይደሉም። ገንዘብ ተከፍሎ ባሪያ አድርጉን ብሎ የሚጠየቅበት አሰራር በታሪክ ታይቶ ይታወቃልን?

በአገር ቤት ያለው ህዝብ ለ 20/በ80 ቢመዘገብ አይገርመኝም፤ በባርነት ውስጥ የሚኖር ህዝብ በመሆኑ፣ አንድ ቀን ራሱን ነጻ እስኪያወጣ፣ ለጊዜው ተመችቶት ይኑር። ባሪያም እኮ ልብሱን ይቀይራል፣ የምኝታውን ሳር ተባይ ሲወርበት በሌላ ሳር ይተካዋል፤ ባበርነት ስር ያለው የአገር ቤት ሰው በነፍሱም በስጋውም ሊበደል አይገባውም፤ ቢያንስ እስከ ጊዜው በስጋው ይደሰት። ዲያስፖራው ግን የኢትዮጵያን ምድር ከለቀቀባት ጊዜ ጀምሮ ከባርነት ነጻ ወጥቷልና በነጻነት መኖር የሚችለበት እድል አለው፤ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም ነጻነት ለመታገል ሁኔታው ተመቻችቶለታል፤ ይህን ነጻነቱን ግን እራሱ ገንዘብ ከፍሎ ሊሸጠው ይደራደራል። ፍርፋሪ እየተጣለለት ወደ ቄራ የሚወሰድ እሪያ መጨረሻው ሞት እንደሆነው ሁሉ፣ 40/በ60 የተመዘገበ ዲያስፖራም መጨረሻው ባርነት ነው። አምስተኛው ባርነት!

Wednesday, August 21, 2013

ሃይማኖትና ፖለቲካ በኢትዮጵያ (ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ)

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

1. መግቢያ:

ካለፈው ሁለት አመት ግድም ጀምሮ “መንግሥት በዲናችን ጣልቃ አይግባብን” በሚል ሰፊ ማእቀፍ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እየተደረገ ያለው ትግል፤ Ginbot 7 movement chairman Dr. Berhanu Nega በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ደግሞ ሁለት አስርት አመታትን ያስቆጠረ ከቀኖናው ውጭ መንግሥት የቤተክርስቲያኑን መሪ አይምረጥብን በሚል በመሰረታዊ ሀሳቡ ከሙስሊሙ ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጉዳይ በተነሳ ውዝግብ ቤተክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላ ያለችበት ሁኔታና በዚህም ምክንያት በመንግሥት የተገፋው “ስደተኛው ሲኖዶስ” በራሱ ላይ የደረሰውን ሁከት በመቃወም የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ተዳምረው ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ ጤነኛ የሆነው የሀይማኖትና የፖለቲካ ግንኙነት ምንድን ነው? ወይንም ደግሞ የመንግሥትና የሀይማኖት ግንኙነት ምን መሆን አለበት? የሚለውን ጥያቄ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የሀይማኖቱ ተከታዮች አልፎ ያጠቃላይ የፖለቲካ ማህበረሰቡ (የሀገሩ) ትልቅ የመወያያ አርዕስት እየሆነ ነው:: ይህ ጉዳይ ግን ጥቅል ከሆነ ያመለካከትና የንድፈ ሀሳብ ጥያቄ በተጨማሪ ጥልቅና አስቸኳይ የሆነ የተግባር ፖለቲካ ጥያቄም ነው ይዞ የመጣው::



የሰማያዊ ፓርቲ ያላቻ ጋብቻ

ከይድነቃቸው ከበደ


መንግስት ተግባሩን ሣይወጣ ቀርቶ መንደርተኛና ቧልተኛ ሲሆን እንዴት ያሳፍራል ! ይህን ለመፃፍ ያነሣሣኝ አዲስ ዘመን ጋዜጣ “ የሰማያዊ ፓርቲ ጥቁር ተግባራት ” በሚል በገፅ 3 አጀንዳ ላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪን በተጨማሪ ዛሚ ሬዲዮ ጣቢያ የክብ ጠረጴዛ ውይይት እና በሬዲዮ ፋና በዜና እና በልዩ ዘገባ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች፤በተለያዩ አካባቢዎች በሚካሄዱ ጥቃቅን አነስተኛ ስብሰባዎችና ሰልፎች የሚሰሙ መፈክሮች የመንግስትን ፍርሃቱን እና ውንጀላ በሚገባ የሚያሳዩ በመሆናቸው ነው፡፡


መንግስት ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ለጥያቄ አቅራቢዎች የሚያስርበት እና የሚያሰቃይበት አዋጅ ማውጣት ይቀለዋል፤ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም መነሻውን 4 ኪሎ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት መድረሻውን ኢትዮ-ኩባ አደባባይ ያደረገ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ ተደርጓል፡፡ በዕለቱም ለመንግስት የቀረበለት ጥያቄ የሰብዓዊ ጥሰቶች እንዲስተካከሉ፣የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣በዓይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንዲቆም በዚህም ምክንያት የታሰሩት እንዲፈቱ፣የኑሮ ውድነቱ ማሻሻያ እንዲደረግበት እና የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚል ጥያቄዎች ናቸው፤እጅግ በሰለጠነ እና ሠላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄው ለመንግስት የቀረበ ሲሆን መንግስትም ለዚህ ምላሽ የሦስት ወር የጊዜ ገደብ ተሰጥቶታል፡፡

ይሁን እንጂ መንግስት ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ስም ማጥፋት ዘመቻውን ቀጥሎበታል፤መንግስት ስም ለማጥፋት ብሎ ያነሳቸው አንኳር ሀሳቦች መሰረታዊ የሰው ልጅ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስት ይህን ለመረዳት ተጨማሪ 22 ዓመታት ቢያስፈልገውም ህዝብ ግን ያጣውን ነፃነት ለማግኘት ትግሉን ይቀጥላል፤ ለህዝብ የመብት ጥያቄ የሆኑት መንግስት ለመወንጀል የሚያነሳቸው ሃሳቦች በጥቂቱ እንመልከት፡፡

1ኛ. “በ1997 ዓ.ም በቅንጅት ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ዛሬ ደግሞ በአዲስ ኮፍያ የሚንቀሳቀሱ” የተባለው ቁጥር አንድ ውንጀላ ነው፤ ምላሹ ደግሞ ፡- ይህ ሀሳብ ከእውነት የራቀ አይደለም ከዛሬ 8 ዓመት በፊት በሺዎች የሚቆጠሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ይቅሩና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ለነፃነት እና ለመብት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የተደረገበት ወቅት ነው፤ በወቅቱ ለሚፈለገው ነፃነት ደም ተከፍሎበታል፡፡ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ባዶ እጁን አደባባይ ወጥቶ “ድምፃችን ይከበር” በማለቱ አገርን ሊወር እንደመጣ ጠላት በመከላከያ ሠራዊት ለዛውም በሰለጠኑ ነፍሰ ገዳይ ታሪክ ሁሌም የሚዘክራቸው ኢትዮጵያውያን በግፍ ገሏል፤ በዚህም ምክንያትና በሌሎች የሚፈለገው ነፃነት ታጥቷል፡፡ እናም ያኔ ያጣነውን ነፃነትና መብት መንግስት በአዲስ ኮፍያ ቢለውም እጅግ በሠለጠነና ሠላማዊ በሆነ መንገድ በአዲስ እስትራቴጂ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፈቀደው መልክ ተደራጅቶ ይህን አምባገነን ስርዓት ታግሎ ለማሸነፍ የሚያደርገው ጥረት ወንጀል የሚሆነው ምኑ ላይ ነው?

2ኛ. “በውጭ ከሚገኙ ፅንፈኛ አክራሪ ኃይል ጋር በመቀናጀት በአረቡ ዓለም የታየውን አብዮት ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት” ይህ ሁለተኛው ውንጀላ ነው፤ ሌባ አባት ልጁን አያምንም የሚባለው ተረት ለዚህ ውንጀላ ተስማሚ ይመስለኛል ምክንያቱም ያሁን መንግስት የበፊት አማፅያን (ወያኔዎች) ከሱዳን፣ ከሶሪያና ከግብጽ ከመሳሰሉት አገራት የጦር መሣሪያና ስልጠና እንዲሁም መሸሸጊያ በማግኘት አዲስ አበባ ቤተ መንግስት መግባታቸውን የሚታወቅ ነው፤ እነሱ በክደት የፈጸሙት ሁሉ ሌላው ያደርገዋል የሚል ከንቱ አሳብ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የተመሠረተው በኢትዮጵያውያን ነው ትግሉም ሆነ ዉጤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፤ ሌላው ደግሞ በአረቡ አለም የታየው አብዮት ኢትዮጵያውያን ከ8 ዓመት በፊት በአስደናቂ ሁኔታ የተገበርነው ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ ከ8 ዓመት በፊት ያጣነው አብዮት መንግስት አልሰማና አልለወጥ ካለ የአረቡን አብዮት በኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታና ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ሠላማዊ በሆነ መንገድ በመስቀል አደባባይ ወጥተን ብናደርገው ወንጀሉ ምኑ ላይ ነው?

3ኛ. “ከውጭ አሸባሪ ግንቦት ሰባት ቴሌቪዥን ጣቢያ ‘ኢሳት’ ጋር በመቀናጀት” ይሄ ደግሞ ሦስተኛ ውንጀላ ነው በመሠረቱ በአገር ቤት ያለው የዳኝነቱ ስርዓት እውነተኛ ፍትህ የሚሠጥ ቢሆን ኖሮ “መልካም ስምና ዝናን በማጉደፍ በተጨማሪም መረጃን የማግኘት መብት በመንፈግ” የወንጀል ክስ መመስረት ይቻል ነበር ግን ምን ዋጋ አለው?፡፡ ይህን ለማለት የፈለኩት አንደኛ ኢሳት መረጃን ለተጠሙ በዓለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጲያውያን አይንና አንደበት የሆነ ሚዲያ እንጂ የግለሰብ ወይም በተወሰኑ ቡድኖች የሚንቀሳቀስ ሚዲያ አይደለም፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሚዲያው የእገሌ ድርጅት ነው መባሉ የስም ማጥፋት ወንጀል ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ መረጃን ማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት ነው፤ ይሁን እንጂ በአገራችን እኛ የመረጥነው ሳይሆን መንግስት የመረጠልን ሚዲያ ነው የምንመለከተው፣ የምንሰማውና የምናነበው ለዚህም ማሳያ በአገር ውስጥ ትክክለኛ መረጃ የሚያስተላልፉ ጋዜጠኞች መጨረሻቸው ስደት ወይም እስራት ነው፤ ከሀገር ውጭ ያሉ ሚዲያዎች ደግሞ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ይታፈናሉ በዚህ ምክንያት መረጃ የማግኘት መብታችን በኃይል ተከልክለናል፡፡

Year After Leader Dies, Ethiopia Is Little Changed

ADDIS ABABA, Ethiopia August 20, 2013 (AP)
By KIRUBEL TADESSE Associated Press

Residents in Ethiopia's capital awoke to the sound of a 21-gun salute Tuesday to mark the first year anniversary of the death of long-time ruler Meles Zenawi.

The ritual underscores the approach Meles' successors have employed during the last year: a continued lionization of the late prime minister, whose portrait still appears in every public office across the country.

Candlelit vigils and the launch of over two dozen parks were organized across the country for the late leader. In the capital a cornerstone for the Meles Zenawi Memorial Museum was laid in a televised ceremony.

During the ceremony, attended by regional leaders such as the presidents of Somalia and Sudan, Meles was praised as "Africa's voice." His successor Prime Minister Prime Minister Hailemariam Desalegn praised Meles as a "champion of the poor."

"Meles did a remarkable endeavor in the green economic development. He also led a successful party and government to establish a widely defined democratic system that has recognized and observed rights of individuals and groups at the same time," Hailemariam said in a speech.

Meles became president in 1991 after helping to oust Mengistu Haile Mariam's Communist military junta, which was responsible for the deaths of hundreds of thousands of Ethiopians. Meles became prime minister in 1995, a position he held until his sudden death last year.

The United States long viewed Meles as a strong security partner and gave Ethiopia hundreds of millions of dollars in aid over the years. U.S. military drones that patrol East Africa — especially over Somalia — are stationed in Ethiopia.

David Shinn, the U.S. ambassador to Ethiopia from 1996 to 1999, says he hasn't detected any changes in the U.S.-Ethiopian relationship since Meles' death.

"From the U.S. side, the policy seems to be one of maintaining cordial but not excessively warm relations. This situation varies somewhat from topic to topic. There continues to be especially close collaboration on issues such as counterterrorism and regional conflicts in Sudan, South Sudan and Somalia. At the same time, there are significant concerns about the future of democratization and human rights practices," said Shinn, now a professor at George Washington University's Elliott School of International Affairs.

Ethiopia is increasingly looking to China as a model. Chinese companies are behind the country's drive to expand infrastructures such as road and telecom networks. In recent months Chinese companies have signed two billion-dollar deals with state companies to expand the country's telecom and power lines.

Thought credited for advancing Ethiopia's economy, Meles was accused of killing and jailing opposition members and rigging elections. Rights groups say the oppression carried out under Meles has continued in the East African nation. Meles was responsible for the closure of 72 independent newspapers, according to the press freedom watchdog the Committee to Protect Journalists.

Sunday, August 18, 2013

ፍረጃውና ውንጀላው መፍትሄ አይወልድም! አገር በተቀነባበር የሐሰት ድራማ አይመራም! (ድምፃችን ይሰማ)

[ከሰሞኑ የመንግስት የፕሮፖጋንዳ ዘመቻዎችና አካሄዶቹን አስመልክቶ የተዘጋጀ የአቋም ማብራሪያ ጽሁፍ ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርቧል፡፡ ጽሁፉ በድምጽ (ኦዲዮ) ተዘጋጅቶም ይለቀቃል፡፡ ሁላችንም በማንበብና ለሌሎች በማስነበብ እንዲሁም በማድመጥና ለሌሎች በማስደመጥ ሀላፊነታችንን እንወጣ፡፡] 


ፍረጃውና ውንጀላው መፍትሄ አይወልድም!

እሁድ ነሐሴ 12/2005

አገር በተቀነባበር የሐሰት ድራማ አይመራም! 

የመንግስት ፍረጃና እምነትን ከእምነት የማጋጨት እንቅስቃሴ በቀጠለበት በዚህ ወቅት ሌላ አዲስ ድራማ ተቀናብሮ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርቧል፡፡ ይህ ድራማ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ በርካታ የመንግስት ድራማዎች ተመሳሳይ ሐሳብ ያንጸባረቀ ቢሆንም አዳዲስ ጭብጦችንም አሳይቶናል፡፡ በዚህ ‹‹ሼህ ኑሩን ማን ገደላቸው?›› የሚል ርእስ በተሰጠው ድራማ የተንጸባረቁትን ጉዳዮች በተወሰነ መልኩ መዳሰስና ለመንግስት አካል እርምት መስጠት ተገቢ በመሆኑ የተወሰኑ ነጥቦችን እናነሳለን፡፡ 

የሙስሊሙ ማህበረሰብ ያነሳቸው ጥያቄያዎች እና እንቅስቃሴው የፈጠረው ስሜት መንግስት ሊቋቋመው ከሚችለው በላይ እየሆነ መምጣቱ እሙን ነው፡፡ መንግስት የተነሱለትን ሕጋዊና ሕገ መንግስታዊ ጥያቄዎች በበጎ ለማየት ከመፈለግ ይልቅ ከመጀመሪያው ወቅት ጀምሮ ሲያደርጋቸው የነበሩ እንቅስቃሴዎች በጣም ተገቢ ያልነበሩ መሆናቸው ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ ሆኖም የህብረተሰቡን ግፊትና ጫና በመመልከት መሪዎቻችንን በሚኒስቴር ደረጃ ቀርቦ ለማነጋገርና ለመደራደር የመንግስት ፈቃደኝነት መታየቱና የጥያቄዎቹን ህጋዊነትም አምኖ መቀበሉ አንድ መልካም ጅምር ተደርጎ ታይቶ ነበር፡፡ 

ሆኖም የመንግስት ፍላጎት የነበረው የተነሱትን ጥያቄዎች በአጉል ሽንገላ አለባብሶ ሙስሊሙን በሐይል ወደ ቤት ማስገባት ሆኖ መገኘቱ መንግስት ቀድሞውንም ችግሩን ለመፍታት ፈቃደኛ አለመሆኑን፣ እንዲሁም የችግሩ ዋነኛ ፈጣሪ መሆኑን አመላክቷል፡፡ መሪዎቻንን እንደ ሕዝብ ተወካይነታቸው ተቀብሎ በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ ሲያወያይና ሲደራደር የቆየው መንግስት እነዚያኑ ሰዎች ስም ቀይሮ ‹‹አሻባሪ›› ብሎ ለመሰየም አንድ ወር እንኳ አልፈጀበትም፡፡ የመንግስት ፍላጎት በአጉል ሽንገላ እና የፖለቲካ ብልጣብልጥነት ህዝበ ሙስሊሙን ወደ ቤቱ ማስገባት፣ ልሳኑንም መዝጋት ነበር፡፡ ይህ ግን ሊሳካ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም የመንግስት ረዣዥም እጆች ሁሉም ሙስሊም ቤትና መስጂድ መድረስ ጀምረው ነበርና፡፡ በመሆኑም ህዝቡ በአቋሙ ጸና፡፡ ‹‹እጅህን አንሳልን! አዲስ ሃይማኖት እንድንቀበልህ አታስገድደን!›› እያለ ደጋግሞ ህዝቡ ድምጹን በሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ መንግድ አሰማ፡፡ ያኔ ነው መንግስት የጭቃ ጅራፉን ደጋግሞ ማጮህ የጀመረው፡፡

መንግስት ራሱ በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች የተነሱትን ጥያቄዎች ተገቢነት እንዳልገለጸ፣ የመሪዎቻችንን ሰላማዊነት እንዳላብራራ በአንዴ 180 ዲግሪ ተሽከርክሮ መሪዎቻችንን በአሻባሪነት በመፈረጅ ‹‹ጸረ ሰላም ኃይሎች፣ ጸረ ልማት፣ የመቻቻል ጸር›› ወዘተ የሚሉ አሉታዊና የፖለቲካ ትርፍ ማስገኛ ቃላትን በመጠቀም የተጠናከረ ዘመቻ ጀመረ፡፡ በባለፈው ዓመት መጋቢት ወር የጀመረው ይህ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ከአንድ ዓመት በላይ ቢዘልቅም የመንግስት ትርፍ አሁንም በዜሮ እየተባዛ ነው፡፡ በቁጥር ይህ ነው የማይባሉ የሰልፍ ኢንቨስትመንቶች፣ የዜና ዘገባዎች፣ የዶኩመንተሪ ድራማዎች ቅንብር፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎችና ተዘርዝረው የማያልቁ ተግባሮች ሁሉ ማጣፊያው ያጠረው መንግስት ከዓመት ለዘለለ ጊዜ ሲያከናውናቸው የቆያቸው ተግባራት ናቸው፡፡ ሆኖም የመንግስት ትርፍ አሁንም ምንም ነው! የዚህም ዋነኛው ምክንያት የኢትዮጵያውያን ግንዛቤ መንግስት ከሚያስበው በላይ የላቀና መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ የሚያስተውልና የሚገነዘብ በመሆኑ ነው፡፡ የዚህ የተቀናጀ ዘመቻ ቀጣይ ተደርጎ የቀረበው የሰሞኑ የሼኽ ኑሩ ግድያ ላይ ያተኮረ ድራማ ያስተላለፈው መልእክትም ከቀዳሚዎቹ ብዙም የተለየ ባይሆንም በዚሁ ድራማ ላይ የተንጸባረቁ ሐሳቦች ላይ ተገቢውን ማብራሪያ መስጠቱ ግን ጠቃሚ ይመስለናል፡፡ 

በቀዳሚነት መንግስት አሁንም ያሉና የሚታዩ ችግሮችን መፍትሄ ከመሻትና ከመቅረፍ ችግሮቹን በመካድ ቪዲዮዎችን አቀነባብሮ ብቻ ወደ ሕዝብ በመልቀቅ ህብረተሰቡን ለማታለል ጥረት ማድረግ ምርጫው ማድረጉ እንደ አንድ የኅብረተሰብ ክፍል በጣም ያሳስበናል፡፡ ከዚህ ቀድም እንደነበሩት ሁሉ ታሳሪዎች ከፍርድ ቤት ውሳኔ በፊት ነጻ ሆኖ የመገመት መብታቸውን በመንጠቅ፣ በሕግ ጥላ ስር ያሉ ታሳሪዎችን መንግስት በሚፈልገው መልኩ በማናዘዝ የሚሻውን በሚዲያ እንዲሉለት ማድረግ መቀጠሉ የችግሩን ቁልፍ አንደማይፈታው እሙን ነው፡፡ የሕዝብ ሐብት ሊሆን የሚገባው ብሔራዊ ቴሊቪዥንና ሌሎች በመንግስት ይዞታ ስር ያሉ ሚዲያዎች በድብደባ የደከሙ ታሳሪዎች ኑዛዜዎች ቆርጦ በመቀጠልና በማቀናበር ያላቸውን ‹‹ልምድ›› በመጠቀም የሚያቀርቧቸው ፕሮግራሞች የኅብረተሰቡን ችግር ከመፍታት ይልቅ በሕዝቡ ውስጥ ቂምና እልህ እንዲበረታ እያደረገው ነው፡፡ ለካሜራ እንደሚፈለገው ‹‹ፈገግና ፈታ ብለህ አላወራህም›› እየተባለ በድብደባ የሚሰራው የምርመራ ክፍል ድራማ ሕዝብን ፈጽሞ ሊያታልል አይችልም፡፡

መንግስት ለመንፈቅ ያህል በለፋበት ‹‹ጂሐዳዊ ሐረካት›› ድራማ መታየት ማግስት የታየውን የህዝብ እልህና ቁርጠኝነት ማስታወስ ብቻ ፊልም ማቀናበር መፍትሄ አንደማይሆን ለማገናዘብ በቂ ነበር፡፡ መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ በማስመልከት ያፈሰሰው የፕሮፖጋንዳ ኢንቨስትመንት ውጤቱ ዜሮ ብቻ መሆኑን አሁን ያለውን ሁኔታ ብቻ መመልከት በቂ ነው፡፡ ‹‹የሸሪአ መንግስት ለመመስረት የሚፈልጉ ኃይሎች›› የሚለው ተረት ከተጣለበት ቦታ ተነስቶ እንደ አዲስ የሚራገበው ቀድሞውንም አሳመኝ ሳይሆን ቀርቶ መጣሉን ማስተዋል ተስኗቸዋል፡፡ የተሰሩ የፕሮፖጋንዳ ናዳዎች ሁሉ የመንግስት ተአማኒነት ሸርሽረው ወሰዱት እንጂ ይህ ነው የሚባል ጥቅም ሊሰጡት አልቻሉም፡፡ በጣም በሚያሳዝን መልኩ መሪዎቻችን ከዚህ ቀደም ያለ ፈቃዳቸው እንዲሁም ሕገ መንግስቱን በመጣረስ፣ የፍርድ ቤቱንም ትእዛዝ በመተላለፍ ራሳቸውን ወንጀለኛ አድርገው እንዲቀርቡ ተገደው የነበረበትን ትእይንት መንግስት እንደ አዲስ አሁንም አሳይቶናል፤ መንግስት ከሕግ በላይ መሆኑንም በተገቢው መልኩ መልእክት እያስተላለፈልን ነው፡፡ የሕግ የበላይነት ማረጋጋጫ የሆነው የተጠርጣሪዎች ከፍርድ በፌት ነጻ ሆኖ የመታየት መብት ተደጋግሞ እየተሸረሸረ አይተነዋል፡፡ 

በመሰረቱ የሼህ ኑሩ ግድያ የትኛውም ሰው ሊያወግዘው የሚገባ ተግባር መሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ ሼኽ ኑሩ ስራቸውም ሆነ አስተሳሰባቸው የፈለገውን ያህል የተለየ ቢሆን እንኳ በዚያ አቋም ላይ የመቆየት ህገ-መንግስታዊ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊም መብት አላቸው፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብም ለፖለቲካ ገበያ ማሟሟቂያነት በመንግስት ሰልፍ እንዲወጣ ከመገደዱ በፊት ድርጊቱን አውግዟል፡፡ የዚህም ምክንያቱ ሁለት ነው፡፡ የመጀመሪያው በእምነታችን አንዲትን ነፍስ ማጥፋት ወንጀልነቱ በራሱ ግዙፍ መሆኑ ነው፡፡ ይህም በቁርአን በዚህ መልኩ ተገልጿል፡፡ 

‹‹እነሆ ያለ ነፍስ (መግደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው›› (ሱረቱል ማኢዳህ ቁጥር 32)

በሁለተኛ ደረጃ ይህ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሰላማዊነትን ብቻ የሚሰብክና ለመንግስት አካል በሰላማዊ መንገድ ብቻ ጥያቄውን ሲያቀርብ የቆየና ከማንኛውም የሀይል እርምጃ የተቆጠበ መሆኑ ነው፡፡ 

መንግስት በሼህ ኑሩ ግድያ ደጋግሞ በሰራው ፖሮፖጋንዳ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ግለሰቡን እንደገደሉ አድርጎ አቅርቧል፡፡ ሆኖም ይህን አጸያፊ ተግባር ሙስሊሙ ህብረተሰብ ፈጽሞ ሊፈጽመው እንደማይችልና በዚህ አይነቱ መሰል ተግባር እንደማይሳተፍም እሙን ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ባካሄድነው ሰላማዊ ተቃውሞ ምክንያት ይህ ቀረሽ የማይባል ዱላ ከመንግስት ወገን ተሰንዝሮብናል፡፡ በርካታ ሙስሊሞች ታስረዋል፣ ተደብድበዋል፣ በወህኒ አሰቃቂ ቶርች ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ከ30 የሚበልጡ ዜጎችም ተገድለውብናል፡፡ ለዚህ ሁሉ የመንግስት የጭካኔ ተግባር ምላሻችን ሰላም ብቻ ነበር፡፡ ከሰሞኑ የዒድ በዓል እለት የመንግስት ታጣቂዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ያንን ያክል አጸያፊ የጭካኔ እርምጃ ሲወስዱም ምላሻችን ሰላም ነበር፡፡ እንኳን አንድ የ80 ዓመት አረጋዊ ለመግደል ይቅርና ወንድሞቻችንን በቀን ብርሃን የገደሉ የፖሊስ ሀይሎች ላይ እንኳ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ድንጋይ አላነሳም፡፡ 

የተቃውሞ መርሐ ግብሮች ሲወጡ የሚገለጹት ዋነኛ የጥንቃቄ መርሆች ሰላማዊ መሆንና የጸጥታ አካላትን ትእዛዝ ማክበር የሚሉት ሁሌም እንዲከበሩ ሙስሊሙ ያላሳለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ፖሊስ ትንኮሳ ቢፈጽም እንኳ ከስሜታዊነት መራቅና ምንም አይነት አጸፋ አለመስጠት ወሳኝ እንደሆነ በመርህ ደረጃ የታመነበትና ተተግብሮም ውጤታማ የሆነ ነው፡፡ በመሀከል ሊያውኩ የሚገቡ አካላት እንኳ ካሉ ለጸጥታ አካላት ተላልፈው መሰጠት እንዳለባቸው፣ የሀይል አማራጭ መቼም አመራጫችን እንዳልሆነ መሪዎቻችን ከመታሰራቸው በፊት ደጋግመው ለህዝቡ ያስተላለፉትና ከእስራቸው በኋላም ህብረተሰቡ መርሁን በምልአት ሲተገብር የቆየ መሆኑን በተግባር አስመስክረናል፡፡ ከዚያ ይልቅ መንግስት እጅግ ዘግናኝ እርምጃዎችን ሙስሊሙ ላይ በአደባባይ በመውሰድ ህዝቡ በአፀፋ ወደ አመፅ እንዲገባ ሲገፋፋ ቆይቷል፤ መንግስት ይህን የሚያደርገው አመጽን ለፖለቲካው ትርፍ ሊጠቀምበት ስለሚሻ ነው፡፡ ሆኖም የህዝቡ ንቃት መንግስት ከሚያስበው የላቀ በመሆኑ ፈጽሞ በዚህ አይነቱ ተግባር ውስጥ ባለፉት ሁለት ዓመታት ተጠምዶ አልታየም፡፡ የተቃውሞ መርሐግብሮች በሚካሄድባቸው ቦታዎች የመንግስት አውቶብሶችን በብዛት በመደርደር የ‹‹ንብረት አውድሙ›› ጥሪ ደጋግሞ ከመንግስት ተላልፏል፣ የህዝቡ ምላሽ ግን በአንድነት ‹‹አንሰብርም›› የሚል ነበር፡፡ ምክንያቱም መንገዳችን ሰላም፣ ጥያቄዎቻችን ምላሽ እንዲያገኙ የምንሻው በሰላማዊ መንገድ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ የዚህ ሰላማዊ ትግል መርህ የሆነው ‹‹የምንገድልበት አላማ ባይኖረንም የምንሞትለት ዓላማ ግን አለን›› የሚለው ሐይለ ቃል የሚያስተላልፈው ግልጽ መልእክትም የሰላማዊነታችንን ዳርቻ ጭምር ነው፡፡