Friday, July 12, 2013

ሰበር ዜና፡ በደሴና አካባቢዋ ትራፊክ ፖሊሶች የአንድነት ፓርቲን ቅስቀሳ እያወኩ ነው

በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሐይቅ ከተሞች ያሉ የትራፊክ ፖሊሶች ከመደበኛው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴዎች ቁጥጥርና ክትትል በተጨማሪ የአንድነት ፓርቲ ለፊታችን እሑድ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ለጠራው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርገውንም ቅስቀሳ እንዲቆጣጠሩና እንዲከለክሉ በመታዘዛቸው መደበኛ ስራቸው መስተጓጎሉ ተገለፀ፡፡

በተለይ ማክሰኞ ደሴ በነበረው ቅስቀሳ ላይ የትራፊክ ፖሊስ መስፍን ንጋቱ የፓርቲው አመራሮች፣አባላትና ደጋፊዎች ቅስቀሳ ሲያደርጉ ከመከልከላቸው በተጨማሪ ለከተማው ፀጥታ ኃላፊ እዛው ሆነው ደውለው በመንገር ፖሊሶችን አስጠርተው አመራሮቹን ኣሳግተዋል፡፡

ዛሬ ሐምሌ 5 ቀን 2005ዓ.ም. ደግሞ በደሴ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ሐይቅ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በተለይም በፓርላማ ብቸኛው የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካይና የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ግርማ ሰይፉና የፓርቲው ኤዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በላይ ፈቃዱን ጨምሮ ሌሎች የአካባቢው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ቅስቀሳ ሲያደርጉ በከተማዋ ትራፊክ ፖሊስና ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኢንስፔክተር ሰይድ ተፈራ ሊያስሯቸው እንደነበር ለመታዘብ ችለናል፡፡
በወቅቱ የፓርላማው ብቸኛው የህዝብ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉን ወደፖሊስ ጣቢያ ለመውሰድ ሲሞክሩ አቶ ግርማም የፓርላማ አባልነት መታወቂያቸውን በማሳየት “ወንጀል ሳልሰራ ማንም ከመሬት ተነስቶ ሊያስረኝ አይገባም፣ ሌሎች ዜጎችንም ቢሆን ፖሊስ እንዲህ ማድረግ አይችልም” የሚል መልስ በመስጠት የተከራከሩ ሲሆን በመጨረሻም የትራፊክ ፖሊስ አባሉና የከተማው የፖሊስ አዛዥ ከተማው ላይ የፖለቲካ ፓርቲ ቅስቀሳም ሆነ የሰላማዊ ሰልፍ አይቻልም፣ ከከተማው ለቃችሁ ሂዱ፤ አለበለዚያ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩትን በሙሉ እናስራለን በማለት እንዲወጡ አድርገዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በከተማዋ ባሉ ሸዋበር፣ አረብ ገንዳ እና ዳውዶ በሚባሉ መስኪዶች በዛሬ በአርቡ መደበኛ የሶላት ፀሎት ስነ ሰርዓት ጭር ብለው የሚሰግድባቸው ሰዎችን አለመታየታቸውን ለመታዘብ ችለናል፡፡ የዚህን ምክንያት የጠየቅናቸው የከተማው የሐይማኖቱ ተከታይ አንዳንድ ነዋሪዎች እንደ ነገሩን ከሆነ አሸባሪ በሚል መንግስት የኃይማኖቱ ተከታይ ወጣቶችን እያሰረ በመገኘቱ እና አዲስ አበባ ቃሊቲ ወህኒ ቤት በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች መታሰራቸውን በመቃወም መሆኑ ተገልፆልናል፡፡ በተለይ ትናንት ሐምሌ 4 ቀን 2005ዓ.ም. ልዩ ቦታው ሸዋ በር በሚባል መስኪድ አካባቢ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የካሜራ ባለሙያ እና ጋዜጠኛ ሰኔ 27 ቀን 2005ዓ.ም. የተገደሉት ሼህ ኑሩ ይማም መኖሪያ ቤት አካባቢን ጨምሮ ማንም ተጠያቂና ተናጋሪ ሳይኖር የተለያዩ ቀረፃዎችንን ሲያደርጉ መታዘብ ችለናል፡፡ በወቅቱ እኛም ከእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የከተማውን ነዋሪ በማነጋገር ቀረፃ ስራ ላይ ነበርን፡፡
በደሴና አካባቢዋ ትራፊክ ፖሊሶች የአንድነት ፓርቲን ቅስቀሳ እያወኩ ነው

No comments:

Post a Comment