Friday, July 5, 2013

በወ/ሮ አዜብ መስፍን ላይ የሚቀርቡ የሙስና አቤቱታዎች ጨምረዋል የሚል ወሬ ሰማን

የእነ መላኩ ፋንታን መታሰር እና የአቶ ገብረዋህድ ምርመራ ተከትሎ በአዜብ መስፍን ላይ የሚቀርቡ የሙስና አቤቱታዎች ጨምረዋል እየተባለ ነው::

የሙስና ኮሚሽን በአቶ ገብረዋህድ ቤት ባደረገው ፍተሻ እንዲሁም ከኣሁን ቀደም በመርማሪ ደህንነቶች ክትትል በተደረገ የስልክ ጠለፋ የቀድሞ ሟች ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ባለቤት እና የኤፈርት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከአቶ ገብረዋህድ ባለቤት እና እህት ጋር በከፍተኛ ደረጃ የቢዝነስ ስራ ይሰሩ እንደነበር እና ከታሰሩት ባለስልጣናት እና ባለሃብቶች ጋር የንግድ አጋርነት እንዳላቸው አረጋግጧል የሚል ወሬ እየተናፈሰ ይገኛል::

ይህንን የሚጠቁሙ ሰነዶች እና ከተለያዩ ወገኖች የሚቀርቡ ጥቆማዎች እና አቤቱታዎች ምርመራው ወደ አዜብ መስፍን አምርቶ ለጥያቄ እንደሚፈለጉ ፍንጭ እየሰጠ ነው መባሉን ከጸረ ሙስና ኮሚጽሽን የውስጥ አዋቂ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

ለሙስና ኮሚሽን ከደረሱት አቤቱታዎች ከፊሎቹ :- ”ኤፈርትን ተገን በማድረግ የተለያዩእቃዎችን ካለቀረጥ እያስገባች ነው:: ኤፈርት ለመንግስት መክፈል የሚገባውን ህጋዊ የግብርም ሆነ ሌላ ክፍያዎች እንዳይፈጸም አድርጋለች:: ዩዲ ኒሳን ዲዝል ገልባጭ መኪኖችን ካለቀረጥ ነጻ በማስገባት በአቶ ከተማ ከበደ/ኬኬ/ ስም ሸጣለች” የሚሉ ይገኙበታል::

”ከዚህ ቀደም እያሱ በርሄ ጋር በኋላም ከኮሎኔል ሃይማኖት ጋር የተከለከሉ የቴለኮሚኒኬሽን ኬብሎችን እና ቴክኖሎጊካል የመገናኛ መሳሪያዎችን ካለቀረጥ በማስገባት ሰርታለች::በነጻ ትሬዲንግ በኩል የተለያዩ ዘመናዊ መኪኖችን ካለቀረጥ እያስገባች በአቶ ነጋ ገ/ዝጌር ስም ትሸጣለች::በሰበታ አለምገና አከባቢ የአበባ ሰፊ እርሻዎች አላት :: በህገወጥ የዶላር እና የኢሮ ዝውውር ውስጥ መሪ ተሳታፊ ናት” የሚሉ ወቀሳዎችም ተሰምተዋል::

ሌሎች ወሬዎች ”ባንክ ኦፍ ማሌዥያ እና የሲንጋፖር ባልሃብቶችን እንዲሁን ቻይናውያንን በህገወጥ አለማቀፍ የገንዘብ ዝውውር ተባባሪ አድርጋ እየሰራች ነው:: በተለያዩ አረብ አገራት እና በሃገር ውስጥ ባስቀመጠቻቸው ደላሎች ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በሱዳን እና በየመን አድርጋ ወደ አረብ አገራት ትሸጣለች:: በተለያዩ የቤተሰብዋ አባላት ስም ባወጣችው የኮንስትራክሽን ንግድ ፍቃዶች ጨረታዎችን በጉልበት ከመቀማት እየሰራሽ ሲሆን ሌሎች ባለሃብቶችን በስማቸው በመጠቀም የተለያየ ቢዝነሶችን እያካሄደች ነው የሚሉ አቤቱታዎች እና ጥቆማዎች ለሙስና ኮሚሽን የመርማሪዎች ቡድን ደርሷል” የሚሉ ይገኙበታል::

ይህንን ተከትሎ በርካታ የኢህአዴግ አባላት በወይዘሮ አዜብ መስፍን ላይ ምርመራ እንዲደረግ ግፊት እያደረጉ እንደሆነ ሲወራ ወይዘሮዋ በአሁን ሰአት ራሳቸውን በተለያየ መንገድ ገኖ ለማውጣት ከፍተኛ ስራ እየሰሩ ናቸው የሚሉ ወሬዎችም በስፋት ይወራሉ::

በሌላ ወገን ይህ እሳቸው እና በዙሪያቸው ያሉ ቡድኖች በሃገሪቱ እና በፓርቲው የፖለቲካ አሰላለፍ ላይ ያላቸውን የሃይል ሚዛን ለመለካት ወይም እሳቸው ምን ያህል ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም እንዳላቸው ለማወቅ የሚደረግ ሙከራ ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩም አሉ።

ሌሎች ደግሞ መንግስት ከዚህ ለወደፊት ላለው አሰራሩ አካሄዱን ለማስተካከል፡ የሃገሪቱን ዕድገት የሚያስተጓጉሉ ስህተቶች እንዳይደገሙ እና የሙስና ችግር እንዲቀረፍ መሰረታዊ ስራ መስራት ስለፈለገ እንጂ በማንም ላይ አሉታዊ አጀንዳ ይዞ እንዳልሆነ የሚናገሩም ይገኙበታል።

እነዚህ አካላት የምሁራን ወገኖች ሲሆኑ የጥርጣሬ እና ነገሮችን በአፍራሽ አዝማሚያ ማየት ያለመሰልጠን አተያይ ነው ይላሉ፡፡ በተጨማሪም ወ/ሮ አዜብን እንደ አንድ አፍራሽ አካል ማየት እና በክፉ ማሰብ በራሱ ገና ለገና በመረጃ ባልተጣራ ወቀሳ ፈራጅ መሆን ነው። እሳቸው እንደማንኛውም ግለሰብ ወቀሳ ካለ በህግ ወይም አግባብ ባለው መንገድ ሊስተናገዱ እንጂ በጎሪጥ ሊታይባቸው አይገባም የሚል ሃሳብም ይሰነዝ
ራሉ ምሁራኑ።

ምንጭ፡ wolaita.com

No comments:

Post a Comment