Wednesday, July 10, 2013

የኢትዮጵያ ፀረ ሽብር አዋጅ መሻሻል ለምን? (ክፍል ፩)

 በሚኪያስ በቀለ

 “Any law that uplifts human personality isjust. Any law that degrades human personality is unjust. One has not only alegal but a moral responsibility to obey just laws. Conversely, one has a moralresponsibility to disobey unjust laws… for an unjust law is no law at all.” Dr.Martin Luther King

የመንግሥት ወይስ የሕዝብ ሕግ?

በኢትዮጵያ ውስጥየፀረ ሽብር አዋጅ የወጣው በ2001 ዓ.ም ላይ ሲሆን የአዋጁ ረቂቅ የተለያዩ የአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ደርጅቶች እናየተቃዋሚ ፓርቲዎች አዋጁ የዜጎችን የሰብኣዊ መብቶች አደጋ ውስጥ ስለሚከት መስተካከል እንደሚኖርበት ድምፃቸውን አሰምተው ነበር፡፡ነገር ግን መንግሥት ትችቶቹን ከቋፍ ሳይከት አዋጁን በ2001ዓ.ም ከ547 የፓርላማ አባላቶቿ ውስጥ 378ቱ በተገኙበት በ268የአዎንታ ድምጽ፣ በ91 ተቃውሞ እና በ1 ድምፀ ተአቅቦ የፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 ኅብረተሰቡን ከአደጋ ለመጠበቅ በሚልአወዛጋቢውን ሕግ አውጥቶ ማስፈጸም ጀምሯል፡፡

አዋጁ በወጣበት ቀን"ባለራዕዩ" የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴት መለስ ዜናዌ የአዋጁን ትክክለኛነት (Ligitimacy) ለፓርላማው ሲያብራሩ"... አዋጁን ስናረቀቅ ከአሜሪካ፣ ከእንግሊዝ እና ከአውሮፓ አገራት ጥሩ ጥሩውን ቃል በቃል....ለምሳሌ በነዚህ ሃገራትባለው ሕግ አሸባሪ ብሎ የመፈረጅ ሥልጣን የሕግ አስፈፃሚው ሲሆን እኛ ግን የሕግ አውጪው ሥልጣን እንዲሆን አድርገናል..."ብለው ነበር፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር በዓለማችን የሕግ የበላይነት ከሰፈነባቸው አገራት የፀረ ሽብር አዋጁን "ቃል በቃል"መገልበጣቸው ሕጉን ትክክለኛ ሊያስብለው እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ ለሰው ልጆች ሁሉ የሚሠራ የተፈጥሮ ሕግ (Universallaw) እንደመኖሩ አንድ ሕግ
ሲወጣ ሀገሪቷ ካላትሁኔታ እና በሕጉ ከሚተዳደሩት ማኅበረሰቦች አንፃር መሆን እንዳለበት (Capable of being complied with) በማወቅይሁን ባለማወቅ ጠ/ሚኒስትሩ የዘነጉት መሠረታዊ የሕግ አወጣጥ መርሕ ነው፡፡ የሰው ልጅ የመኖር (የሕ.መ.አ.15*) እና ከማንኛውንየአካል አደጋዎች የመጠበቅ (የሕ.መ.አ.16*) በዓለማችን ላይ ሁሉ ዕኩል የሚሠሩ የተፈጥሯያዊ መብቶች አሉት፡፡ ነገር ግን እነዚህንመብቶች ለመጣስ በየሃገራቱ ብቻ አይደለም በየኅብረተሰቡ የተለያዩ አደጋዎች እንደመኖራቸው መብቶቹን ለማስጠበቅ የሚወጡት ሕጎች (እንደፀረ ሽብር ሕግ) ከቦታ ቦታ እና ከጊዜ ጊዜ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የተለያዩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሕግ ሲረቀቅየሌላ ሀገሮች ተመሳሳይ ሕግጋት (raison d’etre) መመልከት ተገቢ ቢሆንም በሕጉ የሚተዳደረውን ማኅበረሰብ ጥያቄ መመለስዋነኛው አላማው ነው፡፡ (Law must deliberately meet one of the prevalent ‘needs’ of the society)የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ የራሱ የሆነ የአስተሳሰብ እና የአኗኗር ዘይቤ አለው፡፡ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ፣ እንግሊዝ ወይም አውሮፓ ዕኩልለሽብር ጥቃት የተጋለጡ አገሮች አይደሉም፡፡ የኢትዮጵያ የፀረ ሽብር አዋጅም ኢትዮጵያን ከሽብር አደጋዎች ለመጠበቅ እንዲያስችልተደርጎ መረቀቀ ይኖርበታል እንጂ ከሌላ ሀገር ሕጎች ላይ ቃል በቃል መገልበጥ የለበትም፡፡

የሰብኣዊ መብት የሚያስከፍል የሽብር ጥቃት በኢትዮጵያ?

የሰብዓዊ መብት መንግሥትበመልካም ፍቃዱ አይሰጠንም፣ የሰው ልጆች ሆነን ስለተፈጠርን ብቻ የምናገኘውና በቀለም፣ በዘር፣ በሀብት እና በመሳሰሉት ሳንለያይያለምንም አድሎ የምንጠቀመው በነጻ በእግዚያብሄር አማሳል ስለተፈጠርን ብቻ የሚኖረን መብት ነው፡፡ መንግሥት መብቱን ባይሰጠንምየመጠበቅ ኃላፊነቱ ግን የሱ፤ የሀገር (የመንግሥት) ኃላፊነት እንጂ የግለሰቡ (የእኛ) ኃላፊነትም አይደለም፡፡ የሰብኣዊ መብትንየመጠበቅ ኃላፊነት የመንግሥት ነው ስንል መብቶቻችን እንዳይገፈፉ በሕግ አግባብ የመጠበቅ፣ መብቶቻችን ሲገፈፉ አግባብ ባለው የፍርድአካሄድ የማስጠበቅ እና ሕግ የተላለፈውን መቅጣት አለበት እንደ ማለት ነው፡፡ ችግሩ የሰብኣዊ መብቶቻችን የማስጠበቅ ኃላፊነቱ የመንግሥትእንደመሆኑ መብቶቻችንንም ለመጣስ የመጀመሪያው እራሱ መንግሥት ነው፡፡


ይሄም የሥልጣን ፍቅርያሰከረው፣ ሥልጣን እና/ወይም መሣሪያ ከሕዝብ የሚበልጥ መስሎ የሚታየው መንግሥት ላይ በብዛት ይታያል፡፡ መንግሥት የሰብኣዊ መብቶችሊጥስ ከሚችልባቸው አጋጣሚዎች ዋነኛው የኅብረሰቡን ጥቅም (Public interest) ለማስጠበቅ የተወሰኑ ግለሰቦች የሰብኣዊ መብትመጣስ ይኖርባታል በሚል ነው፡፡ የኢትዮጵያው የፀረ ሽብር አዋጁም የብዙኃኑን ሠላም ለማስጠበቅ በሚል የግለሰቦችን ሰብኣዊ መብትእየጣሰ መፈፀም ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ነገር ግን የተላየዩ ሰብኣዊ መብቶችን የሚያስጥስ የሽብር አደጋዎች በኢትዮጵያ ውሰጥየሉም፡፡ ይልቁንም ከአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ በዊኪሊኪስ ድረ ገጽ አማካኝነት ሾልኮ የወጣው መረጃ (Ref. No.#06ADDISABABA2708) ተፈፀሙ ከተባሉት የሽብር ጥቃቶች በጳጉሜ 1 ቀን 1998 ዓ.ም ተፈፀመ የተባለው ሦስት የቦንብ ጥቃትእራሱ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደፈፀማቸው እና ኤርትራንና ኦነግን ተጠያቂ እንዳደረገ ይገልጻል፡፡

የሌለን ሽብር መፍጠርይልሃል ይህ ነው፡፡ ስለዚህ የሽብር ጥቃት በማያሰጋበት እና "አሸባሪ" በሌለባት ኢትዮጵያ የተለያዩ የሰብኣዊ መብቶችንእየገፈፉ የፀረ ሽብር አዋጅን ማስፈፀም ከአደጋ የሚጠብቀው ሕዝቡን ወይስ መንግሥትን? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በመጀመሪያ የፀረሽብር አዋጁ በሕገ መንግሥት ውስጥ ከተካተቱት የሰብኣዊ መብቶች ውስጥ የትኛዎቹን ይጥሳል? የሚለውን መመለስ ያስፈልጋና ጥቂቶቹንእንሆ፡፡

ከፍተኛ ጥንቃቄ (Due Deligence) ለሰላማዊሰልፍ

የሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግሲታሰብ ንብረቶችን ማጥፋት፣ በፖሊስ ላይ ጥቃት መፈፀም እና የመሳሰሉት ወንጀል ከመሆናቸው ባሻገር ሠላማዊ የሚለውን ጽንሰ ሐሳብይሸረሽሩታል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ተግባራት ወንጀል ቢሆኑም ሽብር አይደሉም፡፡ ይልቁንም "ማንኛውንም ሰው ወይም ቡድንየፖለቲካ፣ ሃይማኖታዊ፣ ወይም የአይዲዎሎጂ ዓላማን ለማራመድ በማሰብ በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር... የሕዝብ አገልግሎት ለከፍተኛአደጋ ያጋለጠ፣ የያዘ፣ በቁጥጥር ስር ያደረገ፣ ያቋረጠ፣ ወይም ያበላሸ እንደሆነ..." የሽብር ድርጊት እንደተፈፀመ የፀረሽብር አዋጁ ይደነግጋል (የፀ.ሽ.አ.አ.3(6)*) ነገር ግን የሕዝብ አገልግሎት ማቋረጥ ኅብረተሰቡን ምን ዓይነት አሳሳቢ አደጋ፤ለዛውም እንደ ሽብር የሚቆጠር አደጋ ውስጥ እንደሚጥል ግልጽ አይደለም፡፡ ደግሞም የሠላማያዊ ሰልፍ ሲደረግ በመቶዎች፣ በሺሕዎችወይም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ በወጣበት የትራንስፖርት እና የመሳሰሉት የሕዝብ አገልግሎቶች ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ የቴሌኮሙኒኪሽን፣የመብራት ኃይል፣ የውኃና ፍሳሽ ወይም ሌላ የመንግሥት ሠራተኞች ተቃውሞ ኖሯቸው ከሥራ የመቅረት አድማ ቢያደርጉ የሕዝብ አገልግሎትሊቋረጥ ይችላል፡፡ በዚህ ዓይነት የሠላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉት ሆኑ የሥራ መቆም አድማ ያደረጉት የሽብር ድርጊት ፈፀሙ ሊባል ነው?የሠላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት (የሕ.መ.አ.30(1)*) በተዘዋዋሪ ተገፈፈ ማለት ይሄ ነው፡፡ ለዚህም ነው የተለያዩ ባለሙያዎችእና ድርጅቶች አዋጁ የሽብር ድርጊቶችን ሲያብራራ አደናጋሪ (vague) እና ሰፊ (broad) ስለሆነ መሻሻል ይገባዋል እያሉ የሚጮሁት፡፡እንደዚህ ዓይነት ሰፊ ክፍተት መተው በፍ/ቤቶች የተለያዩ ትርጉሞች እንዲሰጡት ከማድረጉ ባሻገር የፍትሕ ሚኒስቴር የፈለገውን ሰውእና/ወይም ድርጅት በሽብር ወንጀል ከሶ ችሎት ለመገተር መንገዱን ክፍት ያደረገዋል፡፡

የመረጃ ነጻነት እንደዋዛ

ታዋቅው የሕግ ሊቅእና ፈላስፋ Seneca የሰው ልጅ ከተፈጥፎ ጋር በነጻነት ያለማንም ጣልቃ ገብነት መኖር ይኖርበታል ይላል፡፡

"Manis a sprit and his ultimate goal is the perfection of his reason in that sprit.Because man is a rational animal, his ideal state is realized when he hasfulfilled the purpose for which he was born. And what is it that reason demandsof him? Something very easy – that he live in accordance with his ownnature."

Man is arational animal! የሰው ልጅ የሚያገናዝብ እንስሳ ነው፡፡ የሚያግናዛበው በአካባቢው ከሚያገኛቸው እውነታዎች አንፃር ነው፡፡ስለዚህ የሰው ልጅ ስለፈለገው ነገር ማወቅ ይፈልጋል፡፡ ከፈለው መረጃ ላይ፡፡ ያገኘውን መረጃ አገናዝቦ የፈለገው አቋም የመያዝመብትም አለው፡፡ መንግሥትን ጨምሮ ማንም ሰው ይህንን ዕወቅ ይህንን አትወቅ እንዲለው አይፈልግም፡፡ የማወቅ፣ የማገናዘብ፣ አቋምየመያዝ ብቻ አይደለም አቋሙን ለፈለገው ሰው ያለምንም ፍርሐት የማሳወቅ መብት አለው፡፡ ምክንያቱም ሰው ነውና፡፡

መንግሥትን ከራሱአማካሪዎች ይልቅ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የነጻው ፕሬስ ካልተቸው ሁሌም ትክክል ነኝ ማለቱ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም ትክክል መሆንሥልጣን ላይ ለመቆየት ብቸኛው አማራጭ ነውና፡፡ እንኳን በዚህ ፓርላማው፤ የአንድ ፓርቲ ግለሰቦች በሞሉበት ሀገር እና የጦፈ ክርክርባለበት ፓርላማም የኅብረተሰቡ እና የፕሬስ ትችት ለመንግሥት የሥራ ወሳኝ ነው፡፡ የፀረ ሽብር አዋጁ አንቀጽ 6 እንዲህ ይለናል፡፡"...የሽብር ድርጊት እንዲፈፅሙ ወይም ለመፈፀም እንዲዘጋጁ ወይም በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያበረታቸው ወይምበማናቸውም ሌላ ሁኔታ የሚገፋፋቸው እንደሆነ አድርገው ይረዱታል ተብሎ ሊገመት የሚችል መልዕክት ሆን ብሎ ወይም በግዴለሽነት ያተመወይም ያሳተመ እንደሆነ...." ሽብርተኝነትን ማበረታታት ስለሆነ ከ10 እስከ 20 ዓመት ያስቀጣል፡፡ የሽብር ድርጊትንበቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የሚያበረታታ መልዕክት ምንድነው? ለሚለው አዋጁ ለሽብር ድርጊት ይገፋፋል ተብሎ የሚገመት መልዕክት ነውብሎ ይመልሳል፡፡ ማን ነው አንድን መልዕክት ለሽብር ይገፋፋል የሚለውን ግምት የሚሰጠው? መንግሥት ወይስ ማን? ከሽብር ጋር ቀጥታግንኙነት ያለው መልዕክት ሲያስተላልፍ ማለት ሲቻል ሽብር ይገፋፋል ተብሎ የሚገመት መልዕክት ነው ብሎ እስከ 20 ዓመት እስር መቅጣትለምን አስፈለገ? በዚህ ዓይነት አቃቢ ሕግ ሽብርን ያበረታታል ብሎ ካሰበ ማንኛውንም የመንግሥት ትችት የሽብር ድርጊትን አበረታታብሎ ሊከሰው ነው ማለት ይሆናል፡፡ ለዛውም የሽብር ድርጊት በሚያወዛግብ ሁኔታ በተብራራበት የሕግ ማዕቀፍ፡፡

ማበረታታት (Encouragement)ከሚል ማነሳሳት (Incitement) በሚል ጠንካራ እና ሕጋዊ መርሕ መተካት ይቻል ነበር፡፡ ማነሳሳት (Incitement) የወንጀልሕጋችን ሲያብራራው "ሌላውን ሰው በመጎትጎት፣ ተስፋ በመስጠት፣ በገንዘብ፣ በስጦታ፣ በማስፈራራት ወይም በማናቸውም ሌላዘዴ አንድ ወንጀል እንዲያደርግ ያግባባ እንደሆነ..." አነሳሹ የሚቀጣው ወንጀሉ ቢያንስ ተሞክሮ (Attempt) እንደሆነ"(የወ.ሕ.አ.36(1)*) ነው ይላል፡፡ ሌሎች ወንጀሎችን ማነሳሳት እንደዚህ ባለው ጠባብ ሕግ ለዛውም የተባለው ወንጀል ዝግጅትን(Preparation) አልፎ ወንጀሉ ቢያንስ ከተሞከረ ብቻ (Attempt ላይ ከደረሰ) እያስቀጣ ሽብርን ያህል ለኅብረተሰቡ አደገኛየሆነ ወንጀል "ሽብርን ያበረታታል ተብሎ ስለታሰበ" ብቻ እስከ 20 ዓመት ማስቀጣቱ አግባብ አይደለም፡፡

ይህ ሲባል የነጻውፕሬስ የሕትመት መልዕክቶች በሙሉ ሽብርን አይቀሰቅሱም እና አያስቀጡም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን የሚያስቀጣው መልዕክት ከሚያደርስውየአደጋ አጣዳፊነት (Imminent) እና ወሳኝነት (Neccessity) አንፃር መመርመር ይኖርበታል፡፡ አደገኛ መልዕክትን መተርጎምለፍ/ቤቶች ብቻ ሳይሆን ጠበብ ባለ የሕግ ማዕቀፍ መካተቱ ለሀገሪቷ የሚጠቅሙትን መልዕክቶች በተቃራኒው አደገኛ ናቸው ብሎ ከመቅጣትይሰውራልና ቢታሰብበት አይከፋም፡፡ ከዓለማችን የተሰባሰቡ የሕግ ሊቆች እና ከተባበሩት መንግሥታት የተሾሙ ባለሙያዎች በተገኙበትበተረቀቀው የጁሃንስፐርጉ መርሕ ላይ ለኅብረተሰቡ አደጋ የሚያጋልጡ መልዕክቶች ማስቀጣት ያለባቸው ሦስት ሁኔታዎችን (Preconditions) ሲያሟሉ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ "መልዕክቱ አፋጣኝ አደጋን ለማድረስ የተሳበ ከሆነ (Immenint)፣መልዕክቱ አደጋውን ማድረሱ እርግጥ ከኖነ (Probable) እና በመልዕክቱ እና በሚደርስው አደጋ መካከል የተቀራረበ ግንኙነት ካለው(Cause and Effect)" ናቸው፡፡ የፀረ ሽብር አዋጁ ግን እነዚህን መዘርዝሮች ማሟላት አይደለም አንዱንም አያካትትም፡፡እነ ውብሸት ታዬ፣ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና የመሳሰሉት ነገ ጠባ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ ለኅብረተሰቡ መረጃን በማድረስ፣በመንግሥት ላይ ትችት በማቅረብ የሚሠሩ ታታሪ ጋዜጠኞች ናቸው ብለው የዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ሲሸልሟቸው የደከሙላት ኢትዮጵያ ግንየሽብር ድርጊትን አበረታታቹኋል ብላ ማረሚያ ቤት የላከቻቸው፡፡ አራሚዎቹን ወደ ማረሚያ፡፡ ይህ አካሄድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ29 የተገለፀውን የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ መብት ከመጣሱ ባሻገር ኅብረተሰቡ በፍትሕ ስርዓቱ ላይ ያለውንአመኔታ እንዲያጣ ምክንያት ሆኗል፡፡

* የምህፃረ ቃላትመፍቻ፡-
ሕ.መ - የኢፌድሪሕገመንግሥት አዋጅ ቁጥር 1/1987፣
የፀ.ሽ.አ - የፀረሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001፣
የወ.ሕ - የ1997ቱየወንጀል ሕግ
አ. - አንቀጽ
-----
ጸሐፊውን ለማግኘትበኢሜይል አድራሻቸው mikiyaslaw@gmail.com ይጻፉላቸው፡፡
----
የዚህ ጽሑፍ ዋና ቅጂ በኢትዮጵያ እንዳይነበብበታገደው በዞን ዘጠኝ ጦማር ላይ ይገኛል፡፡

No comments:

Post a Comment