Thursday, July 31, 2014

California Congressman demands the release of Andargachew Tsige

July 28, 2014 

Press Release

WASHINGTON – Rep. Dana Rohrabacher on Monday urged Ethiopia’s prime minister to release Andargachew Tsige, a native-born opposition leader with British citizenship who last month was extradicted to the African nation from Yemen under questionable circumstances.

In a letter to Prime Minister Hailemarian Desalegn, the California Republican wrote: “Mr. Andargachew is a British citizen and a leader for political reform in Ethiopia. He should be released and allowed to return to his family immediately. Any maltreatment or harm to him, or other prodemocracy activists, in your country only serves to widen the gap between our two countries.”

Andargachew was traveling from Dubai to Eritrea on June 23 when, stopping over in Yemen, he was forcibly flown back to Ethiopia, which he fled in 2005 following protests of the nation’s elections. He was granted asylum in Britain, where his wife currently lives. British officials have expressed concerns that his extradition was not properly handled.

The activist was charged with terrorism and sentenced to death in absentia. In his letter to the Ethiopian prime minister, Rohrabacher added concerns from the United States. His letter follows:

የወያኔ የጥፋት ሴራ በወጣቱ!


በቅዱስ ዮሃንስ

ከኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የያዘው በወጣትነት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው ሃይል ነው። ይህ የህብረተሰብ ክፍል ማንኛውንም ዓይነት እውቀት ለመቅሰም የሚያስችል ቀልጣፋና ብሩህ አእምሮ፣ ለምርታማነት ተግባር ሊውል የሚያስችል ጉልበትና በቀላሉ የማይዝል አካላዊ ጥንካሬ ያለው እንደሆነ ይታመናል። በዚያው ልክ በአግባቡ ካልተያዘ ከወጣትነቱ ተፈጥሮአዊ ሁኔታ ጋር ተዳምሮ ለተለያዩ አደጋዎች በቀላሉ ሊጋለጥ ይችላል። የወጣቱ ዝንባሌ የብዙ ጉዳዮች ድምር ውጤት ነው። ብዙ ጊዜ በወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ዜጎች መካከል በጣት የሚቆጠሩት ጥፋት በሚፈፅሙበት ወቅት ወጣቱን እንዳለ የማውገዝ፤ የማንቋሸሽና የማማረር አዝማሚያ ጎልቶ ይንፀባረቃል፡፡ የዘቀጠ፣ ደካማ፣ የሀገር ፍቅር የሌለው፣ አደገኛ ቦዘኔ፣ በንቀት የተወጠረ ወዘተ ትውልድ በማለት የወጣቱን ባሕሪይ መጥፎ ምስል የሚሰጡ ግለሰቦች ጥቂት አይደሉም፡፡

ኢትዮጵያን በቀኝ ግዛት የያዘው ፋሽስቱ ወያኔም እነዚህ ተቀፅላ ስሞች በመጠቀም የአገራችንን ወጣት አቅሙንና እውቀቱን በመጠቀም ተፈጥሮዊ ዝንባሌውንና አገራዊ ራዕዩን እንዳያሳካ እያሸማቀቀ ከየትኛውም ጊዜ በላይ መሰናክል እንደሆነበት የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡ ወጣቱን ረግጦና ከፋፍሎ ለመግዛት የተለያዩ ስልቶችን የሚጠቀመው የጉጅሌው ወያኔ የወጣቱን ሃይል በአገራዊ አጀንዳዎች ላይ ገለልተኛ ለማድረግና አካዳሚያዊ እውቀቱንም ጭምር የላሸቀ በማድረግ የፈረንጅ ባህል ተከታይ እና በተለያዩ ሱሶች በቀላሉ ተጠቂና ተጋላጭ በማድረግ ራዕይ የሌለው ወጣት ለመፍጠር ፖሊሲ በአገር ደረጃ ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ይሄ አይነቱ ሰይጣናዊ ድርጊት ደግሞ ትውልድን ከመግደል ጀምሮ በአገራዊ ጉዳይ ላይ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርግ ወጣት እንዳይፈጠር በማድረግ የአገዛዙን ዕድሜ ለማርዘም የተሸረበ እኩይ ሴራ እንደሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠንቅቆ ያውቀዋል ብየ አምናለሁ። የጉጅሌው ወያኔ አገዛዝ ለወጣቱ ጥራቱን የጠበቀ የትምህርት ፖሊሲ ሳይቀርፁለት፣ ጤንነቱን የጠበቀና ዘላቂ ህልውናውን የሚጠቅም የሥራ ዕድል ሳይፈጥሩለት፣ የዴሞክራሲና የልማት አጀንዳዎችን ሳይዘረለጉ እንዲሁ እንደዋዛ ትላንት ወጣት የነበረው ክፍል ዛሬ በከንቱ ጎልማሳ እየሆነ ዘመን ዘመንን እየተካው መኖር የተለመደ ሆኗል። በዚህ በ21 ኛው ክፍለ ዘመን በአለም ውስጥ ካሉት አገራት እንደ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ሁሉንም አይነት ዕድል የተነፈጋቸው፤ ለመከራና ለስቃይ ብቻ የተጋለጡ አሳዛኝ ፍጥረቶች የሉም ብል ፈፅሞ ማጋነን አይሆንም። እንደ ኢትዮጵያ ወጣት ጦርነት የሚለበልበው፣ ርሃብ የሚጨርሰው፣ እስርና ግርፋት የበዛበት፣ አገሩን ጥሎ መሰደድ ያንገሸገሸው፤ የመማርና ስራ የማግኘት፤ የዜግነት መብቱ የተገፈፈበት፣ ለጭቆና እና ለተለያዩ አደጋዎች የተጋለጠ በዓለም ላይ አለ ለማለት አያስደፍርም።

Thursday, July 24, 2014

Ginbot 7: Movement for Justice, Freedom and Democracy Special Statement and Call for Action – We Are All Andargachew Tsege!!!



Ginbot 7: Movement for Justice, Freedom and Democracy

Special Statement and Call for Action

We Are All Andargachew Tsege!!! 

The long and bitter struggle has now transitioned to a new chapter designated as “We are all Andargchew Tsege”. This communiqué briefly describes what this new chapter is about and what it constitutes. The tasks outlined here are not to be read and set aside rather a series of concrete plans to be put into action.

What does it mean to be Andargachew Tsege? Andargachew Tsege is our leader who stands for justice, freedom, democracy and equality, who has been paying and still paying the immeasurable sacrifices that the struggle requires. To be like Andargachew Tsege means to be humble but determined, patient but persistent, visionary and wise and always ready for action. What it means to be an Andargachew Tsege is to be that person ready to take the necessary measures to get rid of the brutal regime systematically destroying our country. To become an Andargachew Tsege means to be the salvation for our beloved country and our generation.

One of the reasons why the minority regime of the Tigrai People’s Liberation Front (TPLF) has targeted Andargachew Tsege is because he is a leader who has managed to establish close ties between the armed Oromo, Afar, Ogaden, Gambella and other ethnic based organizations and Ginbot 7, our movement in a manner that renders ineffective the tribal junta’s propaganda. Above all what has become a thorn on the side of the TPLF is the strong working relations that he has created with The Tigrai People’s Democratic Movement (TPDM). By collaborating with TPDM, Andargachew has made TPLF unable to ride on the backs of the people of Tigrai. Therefore, to be an Andargachew Tsege also means to be free from ethnic hatred. What it means to be an Andargachew Tsege is to whole heartedly believe in the struggle and work with strong conviction for equal rights for all Ethiopians.

To be an Andargachew Tsege does not necessarily require being a member of Ginbot 7. To be an Andargachew Tsege only demands readiness to pay the price for the success of worthy objectives, irrespective of which organization one belongs to. To be like Andargachew Tsege is to comprehend fully that a resolute struggle needs to be backed by a strong organization.

Finally, to be like Andargshew Tsege means to be Okilo Aquagne, Andualem Arage, Reeyot Alemu, Eskinder Nega, Bekelle Gerba, Olbana Lelisa and the countless other heroes and heroines of the struggle.

While we will frequently update the focus of the “We Are All Andargachew Tsege” campaign, the focus of the initial stage of the global campaign that will be implemented immediately is presented in three stages.

ለብሔራዊ አንድነትና ነፃነት – ህወሓትን ከትግራይ ሕዝብ መነጠል!!!

በአለፉት ጥቂት ሣምንታት በወያኔ የተፈፀሙ የእብደት ተግባራትን ስናጤን ከፊት ለፊት ኢትዮጵያችንን እየጠበቀ ያለው መንታ መንገድ አመላካች ነው። ይህ ከፊት ለፊት የሚጠብቀን መንታ መንገድ አንዱ ወደ ብሔራዊ አንድነት፣ ነፃነትና ብልጽግና ሌላው ወደ እርስ በርስ ትርምስና ውድቀት የሚያመሩ ናቸው። የአንድነት፣ የነፃነትና የብልጽግና መንገድ ለመያዝ መስመራችንን ማስተካከል ያለብን ከአሁኑ ነው።

ለመሆኑ ከላይ ያልነውን ለማለት ያስቻሉን በአለፉት ጥቂት ሣምንታት በወያኔ የተፈፀሙት ተግባራት ምንድናቸው?

አንደኛ፤ ወያኔ፣ ዓለም ዓቀፍ ህግንና ሥርዓትን በጣሰ መንገድ ከየመን ባለሥልጣናት ጋር በማበር የንቅናቄዓችንን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ማፈኑ በአለፉት ጥቂት ሣምንታት ውስጥ ውስጥ የተደረገ አብይ ክስተት ነው። ይህ የወያኔ የውንብድና ተግባር ኢትዮጵያዊያንን በእጅጉ አስቆጥቷል። ወያኔ፣ ለሀገር ነፃነትና ለእኩልነት የሚታገልን አንድ ታላቅ ሰውን ማፈንኑና ከእይታ ከልሎ እያሰቃየው መሆኑ በሕዝቡ ውስጥ ያለው ቁጣ ወደ መገንፈል አስጠግቶታል። አቶ አንዳርጋቸው በጠላት እጅ ከወደቀም በኋላ ኢትዮጵያዊያንን አሰባሳቢ ኃይል ሆኗል።

ሁለተኛ፤ ሰላምተኞቹን ብሎገሮችንና ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት በመክሰስ በቋፍ ላይ የነበረውን የወጣቶች ትዕግሥት እንዲሟጠጥ አድርጓል። ስለኢንተርኔት አጠቃቀምና ጥንቃቄ ሥልጠና መውሰድ በክስ ቻርጁ ውስጥ መካከቱ ሥርዓቱ ከእውቀት ጋር የተጣላ መሆኑ በግልጽ አሳይቷል። ከዚህም በተጨማሪ በህጋዊ ፓርቲዎች ውስጥ በንቃት የሚሳተፉ ወጣት መሪዎችን መርጦ በማሠርና በሽብርተኝነት በመወንጀል የወያኔ የአፈና መዋቅር ወጣቱ ላይ ማነጣጠሩ ግልጽ ሆኗል።

ሦስተኛ፤ እጅግ ሰላማዊና ጨዋነት በተሞላበት መንገድ አቤቱታቸውን በማቅረብ ላይ የነበሩትን ሙስሊም ወገኖቻችንን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በመደብደብ እና በጅምላ በማሠር በወያኔ መድብለ ቃላት ውስጥ “ሰላማዊ ትግል” የሚባል ነገር አለመኖሩ፤ ተቃውሞ ሁሉ “ሽብር” እንደሚባልና በሽብርተኝነት እንደሚያስከስስ በማያሻማ ሁኔታ አረጋግጧል። ይህም የሥርዓቱ አውሬዓዊ ባህሪ መገለጫ ሆኗል።

Wednesday, July 23, 2014

ይድረስ ለመላ ኢትዮጵያ ህዝብ – ኢትዮጵያ! ሸክህምህን አራግፍ! (ሥርጉተ ሥላሴ)


እጅግ የምትናፍኝ፤ የምሳሳልህ ክብሬና ማዕረጌ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!

2005 እንዴት ነህ ብዬ ለመጠዬቅ አቅም የለኝም። መከራ ባዘራ ሰቀቀን፣ ስቃይ በከተመበት ኑሮ፣ ራህብ ትንፋሹ ባደረገ ህይወት፣ መገለልን አብዝቶ በከዘነ አዬር፣ መቀጥቀጥን ውቅራቱ ባደረገ ማዕልት፤ ፍርኃትን በሸመተ ድቅድቅ ሌሊት እንዳላህ እረዳለሁ።

ዛሬ በአንድ የጎሳ አንባገነን አስተዳደር በትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት በአድሎ መከትከቱ፣ የቀደመው ማንንት ሁሉ ተቀዶ ማፍሰሱ፣ የነፃነት ትንፋሽነት በጦር መወጋቱ፤ በባዕት በባይተዋርነት ሁሉን ችሎ መተከዙ እስከመቼ? ሸክሙ የሚራገፍበት ሁኔታ እንዴት ይሰናዳ? እንዴተስ ቆርጠህ ግፍና በደሉን ማረገፍ ተሳነህ?

በሰላማዊ ትግል የተሰለፉ ልጆችህ በተገኙበት ቦታ እዬታደኑ የአራዊት ፍትህወት መወጣጫ፤ የቂም መደቆሻ፤ የበቀል ማወራረጃ እዬሆኑ ዕንባን ሰንቆ ቀንን ማስለቱስ እስከመቼ ትቀጥልበት ይሆን?

መቼ ይሆን ይህ የመንፈስ መጋኛ የሆነ ዘር አጥፊ፤ ታሪክ ገዳይ፤ ትውልድን ደምሳሽ የዞግ ሥርዓት በቃህን በማለት ቁጣህን በህብረት የምትገልጠው? ከተቆጡትስ ጋር ተቀላቅለህ በስፋት ወጥተህ ፍዳህን – መከራህን ለዓለም አደባባይ የምታሳዬው ሰላማዊ የንቅናቄ የቁጣ እሳትህን መቼ ይሆን የምታነደው? ቀጠሮው እስከመቼ ነው?

ሴት ልጆችህ ለአራዊት እየታደኑ መጫወቻ ሆኑ። ወንድ ልጆችህም የግብረ ሰዶም ማርኪያ ሆኑ። ኢትዮጵያ ላይ የነነዌ ቀን እንዲህ ተፈቅዶለት እዬተጠበቀ ነው። የፈጣሪ ቁጣ ሲመጣ ሞገዱ አንተን ንዑዱን ከኃጢያተኛው ሳይለይ ይጨመርኃል። ስለዚህ ይህን የገማ ሥርዓት ከሥሩ ለመንቀል ከልብህ ሆነህ ሥርዓትህን ጠብቀህ የጠላኸው መሆኑን  በአንደበትህ እርግጡን ንገረው። ወያኔ ሲፈጠርም የአንተ አይደለም። አሲድ – ዲዲቲ ነው። መርዝ ነው ወያኔ።

እርግጥ ነው ጥቂቶች በልተው ያድራሉ። ውጭ ሀገር ልጆች ያላቸው። እነሱም እዬታፈኑልህ ነው። ተሰደውም ሰላም አልሰጣቸውም ሽፍታው ወያኔ። ስደት ላይ ያሉ ልጆችህ ሰላም አግኝተው እንደፈለጉት መንቀሳቀስ፣ ሠርተው ወጥተው መግባት እስካልቻሉ ድረስ ነገ ውጪ ሀገር ልጆች ያላቸው ቤተሰቦችም ቢሆን ጉሮሯቸው ይታነቃል። አፋኙ ወያኔ የውንብድና ተግባሩ ሆነ የማሳደድ ሥራው ከመቼውም በሰላ ሁኔታ በመሰሪ ደባ በውጭ ሀገርም እዬከወነው ይገኛል።

Monday, July 21, 2014

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የኢትዮጵያ የምንግዜም ጀግና!


በቅዱስ ዮሃንስ

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በበርካታ የታሪክ ምዕራፎች ብሄራዊ ውርደትን አስተናግደናል። አንደኛውና ሁላችንም የምናውቀው በጣልያን ወረራ ወቅት፤ በራሳችን ባንዳዎች የተፈጸመብን ውርደት ነው። ሁለተኛውን ውርደት የተከናነብነው በቀይ ሽብር ዘመን ወንድም ወንድሙን ገድሎ የፎከረበት ወቅት ሲሆን፤ ሶስተኛው ብሄራዊ ውርደት ደግሞ፤ አሁን አገራችንን በቀኝ ግዛት የያዘው የወያኔ አገዛዝ ያከናነበን የቅሌት ቡሉኮ ነው። የዛሬ ጽሁፍ መነሻዬ ስለያንዳንዱ ዘመን ብሄራዊ ውርደት ለመተንተን አይደለም። ይልቁንም በእንደዚህ አይነት የውርደት ዘመን አንገታቸውን ቀና አድርገው፤ ለህዝባቸው ነፃነነት፤ ፍትህና ዲሞክራሲን ሊያጎናጽፉ፤ በወያኔ የአገዛዝ ዘመን ጨርቅ ተብሎ ክብር የተነፈገውን፤ ቀደምት አባቶቻችን ነፍሳቸውን ሳይሰስቱ የገበሩለትን ክቡር ሰንደቅ አላማችንን ከፍ አድርገው በድል ሊያውለበልቡ፤ ለህይወታቸው ሳይሰስቱ ኑሮዋችውን በዱር በገደል አድርገው ስለነበሩት የኢትዮጵያ የምንግዜም ጀግና ስለ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጥቂት ለማለት ፈልጌ እንጂ።

እኛ ኢትዮጵያውያን በተረትና በባህላዊ ወጎች በርካታ የተለያዩ ጀግኖች አሉ፡፡ አንዳንዶች በሚያጋጥማቸው አደጋ ወቅት በሚያሳዩት የሞራል ጥናካሬ  ይጀግናሉ፤ አንዳንዶች ደሞ ለክብራቸውና ለዓላማቸው በመቆማቸው ይጀግናሉ፡፡ እንዲሁም አንዳንዶች ጠላቶቻቸውን በፍልሚያው ሜዳ በመግደላቸው ድል በማሸነፋቸው ጀግና ይባላሉ፤ ለፍቅር የተሰዉ ጀግኖችም አሉ፤ ዘመናዊና ባህላዊ ጀግኖችም ይታያሉ፤ ያልታወቀላቸውም ጀግኖች አሉ፤ ደግሞም የድል አጥቢያ ጀግኖችም አሉ፡፡  በዚህም ሆነ  በዚያ ሁሉም የሚጋሩት አንድ ባህሪ አላቸው፡፡መስዋእትነት፤ ታማኝነት፤ ጥንካሬ፤ ቆራጥነት፤ እርግጠኛነት፤ ያለማወላወል እና ሌሎችም ሁኔታዎች፡፡

ከዚህ ሁሉ በተለየ አኳኋን ግን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሁሉንም ባህሪያት የተጎናጸፉ ዘመን የማይሽራቸው የኢትዮጵያ የምንግዜም ጀግና ናቸው። አዎ! አቶ  አንዳርጋቸው ለቆሙበት ትግል ቆራጥነትንና መስዋዕትነትን፤ ለአላማቸው ታማኝነትን፤ ለመንፈሳቸው ጥንካሬን፤ ለድሉ የእርግጠኝነትን ዝናርን የታጠቁ የህዝባችን የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው። አቶ አንዳርጋቸው ለነፃነት፡ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የሚዋጉ ፋና ወጊ አርበኛ ናቸው፡፡ የህዝባችን ጭቆናና ድህነት ረፍትና እንቅልፍ የነሳቸው የነፃነት አርበኛ ናቸው፤ የወያኔ መሰረተ ቢስ መደለያና ማታለያም ሳይበግራቸው የወገናቸውን ፍቅር ያስቀደሙ አርቆ ተመልካች ባለራእይ ጀግና ማለት ክቡር አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ናቸው፡፡ ነገ የሚሆነውን ቀድመው ተመልክተው ሊመጣ ስላለው ክብር ክብራቸውን ሰውተዋል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ጀግና ናቸው፤ ሕዝባቸውን በወያኔ አገዛዝ እየደረሰበት ካለው መከራና ስቃይ ለማውጣት የራሳቸውን የተደላደለ ኑሮ የሰዎ፤ ወያኔዎቹ ፈርዖኖች የገነቡላቸውን የምቾት ዓለም ሳይቀር ለወገናቸው ፍቅር ሲል የናቁ ብልህ አርበኛ፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ማለት ሁሌም የወገናቸውን ጥቅም የሚያስቀድሙ፤ በእርሳቸው ሞት የሌሎችን ሕይወት የሚያደላድሉ፤ ወገኖቹ ነገ እንዲኖሩ ዛሬውን የሚሰው፤ ለሌላው ጥቅም ሲሉ የሚጎዱት ጉዳትንም እንደጥቅም የሚቆጥሩ፤ ስለከፈሉት መስዋዕትነት ፈጽሞ የማይጸጸቱ የነፃነት አርበኛ ናቸው፡፡

ምናምንቴዎች በሠለጠኑ ግዜ ህዝብ ያልቀሳል !!!

ኢትዮጵያ ላይ ጥቂት ምናምንቴዎች ሰልጥነው ህዝቡን እያስለቀሱት ነው። ኢትዮጵያዊያን ለብዙ ዘመን በብዙ ሃዘንና እንባ ውስጥ መኖራቸው የታወቀ ነው። የአሁኑ ሃዘን እንዲሁ ተራ ሃዘን፤ ልቅሶውም ተራ ልቅሶ አይደለም። መራር ሮሮ እንጂ። ይህን የህዝብ ሮሮ የሚሰማ መንግስታዊ አካልም የለም። በ“Global terrorist database” ውስጥ የሥም ዝርዝሩ ተመዝግቦ የሚገኘው “የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ” ነኝ የሚለው ቡድን መንግስ ነኝ ቢልም የመንግስት መልክና ባህሪይ ሊኖረው አልቻለም። ህወሃት መንግስታዊ አሸባሪ እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ለመሆን የሞራልም ሆነ የእውቀት ብቃት ያለው ቡድን አይደለም።

ህወሃት ከተፈጠረ ጀምሮ የብዙ ንፁህ ዜጎችን ደም አፍሷል። ብዙ ዜጎችን ለስቃይ እና ለስደት ዳርጓል። ብዙ ቤተሰብን በትኗል። በተለይ ጠላቴ ነው ብሎ የሚያምነውን የአማራ ህዝብ ለማጥፋት ሴቶችን መካን የሚያደርግ ክትባት እስከ መከተብ ደርሷል። በዚህም የአማራው ቁጥር ከነበረው ቀንሶ ተገኝቷል። ይህ አሸባሪ ቡድን በኦጋዴን፤ በአፋርና በጋምቤላ የፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ዓለም ያወቀው ነው። በኦሮሚያ የፈሰሰው የንፁሃን ዜጎች ደም ከምድር ወደ ሰማይ እየጮኸ ነው። በአዲስ አበባ እና በደቡብ የተበተነውን የቤተሰብ ብዛት ቆጥረን አንዘልቀውም። በትግራይ የሚገኙ ምርጥ ኢትዮጵያውያን በሙሉ አልቀዋል። የተረፉ ጥቂቶች ቢገኙም መግቢያ መውጪያ አጥተው በሁለት ሰይፍ የሚቆረጡ ሁነዋል።

የትግራይ ነፃ አውጪዎች ያተረፉልን ነገር ቢኖር ውርደት ነው። ውረድቱ የከበዳቸው ዜጎች ራሳቸውን በእሳት አቃጥለዋል። ገደል ውስጥ ራሳቸውን ወርውረው የሞቱም አሉ። ህወሃቶች ባሉበት ከምንኖር ብለው ስደተን መርጠው የበርሃ ንዳድ፤ የባህር ዐዞ እራት የሆኑ ብዙ ናቸው። በባእዳን አገር ውስጥም ማረፊያ አጥተው የሚንከራተቱም ቁጥራችው በቀላል የሚገመት አይደለም። ይህ የህወሃት መራር ፍሬ ነው።

አዎን በአገራችን ላይ እነዚህ እግዜርን የማያውቁ የሰይጣን ድንኳኖች ከሰለጠኑ ዘመን ጀምሮ የንፁህ ሰው ደም ሳይፈስ የዋለበት ቀን የለም። ህወሃቶች የትልቁንም የትንሹንም ደም በማፈሰስ የሚረኩ፤ ቤተሰብንም በትነው ድሃ አደግ በማድረጋቸው የሚደሰቱ ፍጡራን ስለመሆናቸው የእስከዛሬው ምግባራቸው ቋሚ ምስክር ነው። ለስልጣን ካላቸው ሥሥት የተነሳም ከባዕዳን ጋር እየተመሳጠሩና ብዙ ሚሊዮን ገንዘብ እየከፈሉ ነፍሰ ገዳዮችንና አፋኞችን ቀጥረው ዜጎችን እስከማሳፈን ደርሰዋል። የዚህ ዕኩይ ተግባር ሰለባዎች ብዙ ናቸው። ታላቁ ሰው አንዳርጋቸው ፅጌ የዚህ እኩይ ተግባር ሰለባ ከሆኑ ብዙ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ ነው።

Friday, July 18, 2014

አገራዊ ጥሪ ለመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት

ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላትን ከአለቆቻቸው ለይቶ ይመለከታል።

የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ከፍተኛ ሹማምንት ከህወሓት የተቀዱ፣ ለህወሓት ሥልጣን የቆሙ፣ ዘረኞች፣ ፋሽስቶችና ሙሰኖች መሆናቸው በገሃድ የሚታወቅና በተደጋጋሚ ጥናቶችም የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። በዘመነ ወያኔ የሠራዊት አዛዥነት ሹመት መሥፈርቶች ዘር፣ የፓለቲካ አመለካከትና ለህወሓት ያላቸው ታማኝነት ነው። በዚህም ምክንያት ሁሉም ቁልፍ የአዛዥነት ቦታዎች የተያዙት ሙሉ በሙሉ የህወሓት አባላት በሆኑ የትግራይ ተወላጆች ነው። እነዚህ የጦርና የፓሊስ ሹማምንት ኢትዮጵያን ወረው እንደያዙት አገር ሲዘርፉ፣ ሕዝቧንም ሲገሉና ሲገርፉ እንሆ 23 ዓመታት አልፈዋል። በእነዚህ 23 ዓመታት ትግራይን ጨምሮ በደል ያልደረሰበት የኢትዮጵያ ግዛት እና የኅብረተሰብ ክፍል የለም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእነዚህ ፋሽስቶች ተረግጧል፣ ተዋርዷል፣ ተግዟል። የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የነፃነት አርበኞች በእነዚህ እኩይ የሠራዊቱና የፓሊስ አዛዦች ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው። የወያኔ የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች አገራችን እያደሙ፤ ሕዝባችንን እያስለቀሱ ነው። በወያኔ ፋሽስት የጦርና የፓሊስ አዛዦች እና ሰላዮች ጥምረት ሰቆቃ የሚፈፀምበት የኅብረተሰብ ክፍል በየጊዜው እየጨመረ ይገኛል። የወያኔ ማሰቃያዎችን የሞሉት የፓለቲካና የሀይማኖት መሪዎች፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች መሆናቸው ለዚህ አንድ ማሳያ ነው።

የሠራዊቱ የበታች ሹማምንትና ተራ አባላት ጥንቅር ግን ከአዛዦቹ ፈጽም የተለየ ነው። የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ከመላው የኢትዮጵያ ግዛቶች የተውጣጡ፤ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በነፃነት እጦት፣ በመብቶች መገፈፍ እና በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩ ዜጎች ናቸው። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዦቹ እየታዘዘ ወገኑን የሚበድል ቢሆንም ራሱ ከመበደል ግን አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር በወያኔ አዛዡ ታዞ ሌላኛውን ወገኑን ቢያስርም ሹሙ ፊቱን ባዞረበት ጊዜ እራሱ ደግሞ ከመታሰር አይድንም። የኢትዮጵያ ወታደር ወያኔ አዞት ምስኪኖችን ይደበድባል፤ ራሱ ደግሞ በወያኔ ይደበደባል። የኢትዮጵያ ፓሊስ በወያኔ ትዕዛዝ ንጹሀን ዜጎችን ያስራል፣ ያሰቃያል፤ እራሱ ደግሞ በወያኔ ይታሰራል፣ ይሰቃያል። ይህ ምን የሚሉት ባርነት ነው? የወያኔ ሹማምንቶች በሚመሩት የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በህወሓት የሚደርስባቸው በደል ሌላው ኢትዮጵያዊ ከሚደርስበት ይብስ እንደሆን እንጂ የሚያንስ አይደለም።

Thursday, July 17, 2014

የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሂደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ!

አምሳሉ amsalugkidan@gmail.com

ይሄንን ጽሑፍ ታች አምና ከጉራፈርዳና አካባቢው አማራ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ሕጋዊነታቸውን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ይዘው እያለ ሕጋዊ ሆነው የየክልሉ መንግሥት አውቋቸው በሥርዓቱ ግብር እየከፈሉ እየኖሩ የነበሩ ምስኪን ገበሬዎችን “ሕገ ወጥ ሰፋሪዎች”  በሚል ሕገ ወጥነታቸው አግባብነት ባለው የሕግ አካል (ፍርድቤት) ክስ ተመስርቶባቸው ሳይረጋገጥባቸው በጅምላ በግፍና በሕገ ወጥ መንገድ ንብረታቸውን ሁሉ ተወርሰው እንዲወጡ በተደረገ ጊዜ ጽፌው ለጥቂት መደበኛና ኢመደበኛ (Conventional and Social Media) ልኬው ነበር እስከማውቀው ድረስ ለሕዝብ ይፋ አድርገውት ያስነበቡት ወይም ያስደመጡት አልነበሩምና ሕዝብ ሊያውቃቸው የሚገባ በርካታ ቁምነገሮች ስላሉት እንዳያመልጣቹህ በማሰብ ወደ እናንተ አድርሸዋለሁ መልካም ንባብ፡፡

የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ መንግሥታዊ (official) ቋንቋ ማለትም ከውጭ መንግሥታትም ይሁን ከሀገር ውስጥ ነገሥታት መልዕክት ይጻጻፉ የነበረው የቤተ መንግሥት ሥራቸውን ይሠሩ የነበሩት በአማርኛ ነበር፡፡ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ትግሬ ሆነው ሳለ ይሄንን ማድረጋቸው ቅር ያሰኛቸው የትግሬ ሹማምንት በራስዎ በትግርኛ ቋንቋ የማይጠቀሙት ለምንድን ነው? ብለው ጠየቋቸው ዐፄ ዮሐንስ 4ኛም አማርኛ የአክሱማዊያን ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ለእነሱ በማስታወስ ይህንን መለወጥ እንደማይኖርባቸውና እንደማይገባም በመግለጽ ለሹማምንቶቻቸው ምላሽ ሰጡ፡፡ ይህ አክሱማዊያን አማሮች ነበሩ ወይም አማርኛ የእክሱማዊያን ቋንቋ ነው የሚለውን ታሪክ አክሱም አካባቢ ሄዳችሁ ብትጠይቁ የአክሱም ሰዎች በትውፊት ይዘውት እንደመጡ ማለትም አባቶቻቸው አማርኛ የአክሱም ነገሥታት ቋንቋ መሆኑን ይነግሯቸው እንደነበር ይገልጹላቹሀል፡፡ በላይ ግደይ የተባሉ ጸሐፊም “አክሱም” በተባለው መጽሐፋቸው ይሄንን ገልጸውታል፡፡

ታዲያ ጉዳዩ እንዲህ ከሆነ አማራን ወይም አማርኛን ከአክሱምና አከባቢዋ ማንና እንዴትስ አጠፋው ለሚለው ተገቢ ጥያቄ ታሪክ አጥኝዎችና ተመራማሪዎች እስከአሁን አልደረሱበት ሆኖ ይሁን? ወይም አውቀውት ነገር ግን በአንድም በሌላም ምክንያት መግለጽ ስላልፈለጉ? ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡ ከዚህ አኳያ ይህ ጽሑፍ እስከ አሁን ያልተገለጸ ከታሪክ ኩነት መዞ ወይም ገልጦ መረጃ ይሰጣል፡፡

ጥንት ቋንቋቸው አማርኛ ኖሮ ዛሬ ላይ ቋንቋቸው ትግርኛ የሆነ አክሱሞች ብቻ አይደሉም፡፡ ከዚያው ከአጠገባቸው የወልቃይትና ከፊል ጠገዴን ሕዝብ ታገኛላቹህ፡፡ የእነኚህን አካባቢ ሰዎችን ማንነታቸውን ብትጠይቋቸው አማራ ጎንደሬ እንደሆኑ ይነግሯችኋል፡፡ የሚናገሩት ቋንቋ ግን ትግርኛ ነው፡፡ አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሀገራቸውን ከጎንደር ቆርጦ ወደ ትግራይ ሲቀላቅልባቸውም ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደተቃወሙ ነው፡፡ በተለያዬ ጊዜ በውጭም በሀገር ውስጥም ያሉ ወልቃይቶች የዚህ መንግሥት አመራርና ነባር ታጋይ የሆኑትም ሳይቀሩ ለመንግሥት ሥራ እውጭ ባሉበት “እኛ ትግርኛ ስለተናገርን ብቻ እንደ ትግሬ ልንቆጠር አይገባም ማንነታችን ይጠና እኛ ትግሬ አይደለንም” በማለት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተደጋጋሚ በተቃውሞ ሰልፉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

የአክሱም ነገሥታት አማርኛ የቤተመንግሥት የሚስጥር ቋንቋ አድርገው ከመፍጠራቸው በፊት ቋንቋቸው ሙሉ ለሙሉ ግእዝ ነበር፡፡ አማርኛ ሊቀድም እንደሚችልም የሚያመላክቱ አንዳንድ ጠቋሚ ነገሮችም አሉ፡፡ የአክሱም ነገሥታት ስሞቻቸውን ያዬን እንደሆነም በተለያዩ ምክንያቶች በባዕዳን ማለትም በዕብራይስጥ፣ በጽርእ፣ በሮማይስጥ ስሞች ከተጠሩት ውጪ ስሞቹ ግእዝ ካልሆኑ አማርኛ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ ብዙዎቹ የጠፉ ወይም የተረሱ የአማርኛ ቅላት ሆነው ለመረዳት የሚያስቸግሩ አማርኛዎች ቢበዙም አሁንም ድረስ በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ባሉ ቃላት የሚጠሩ የአክሱም ነገሥታት ስሞች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ጥቂቶቹን ብናነሣ ምኒልክ (ምንይልክ) ቅ.ል.ክ 982-957፣ ዙዋሬንብረት 1ኛ ቅ.ል.ክ. 599-558፣ ዙዋሬንብረት 2ኛ ቅ.ል.ክ. 276-260፣ ግርማአስፈር 77-86 ዓ.ም፣ አርፍድ (ገ/መስቀል) ከ357-361 ዓ.ም፣ ወሰንሰገድ 557-572 ዓ.ም፣ ጉም 693-717 ዓ.ም፣ አስጎምጉም ከ717-722 ዓ.ም፣ ለትም ከ722-738 ዓ.ም፣ ተላተም ከ738-759 ዓ.ም፣ አይዞር ለ6 ሰዓታት፣ ውድማአስፈር ከ787-817 ዓ.ም፣ አንበሳውድም (አንበሳአውድም) ከ882-902 ዓ.ም ድልነአድ 902-912 ዓ.ም፣ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ጋዜጠኞቹና ጦማሪያኑ ፍ/ቤት ሳይቀርቡ የምርመራ መዝገቡ መዘጋቱ ሕገወጥና አደገኛ መሆኑ ተገለጸ

"አሁን ታስረው የሚገኙበት ሁኔታ ሕገወጥና አደገኛ ነው" ጠበቃ አመሐ መኮንን

በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በክስ ላይ የሚገኙት ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ጦማርያን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ፖሊስ ‹‹ምርመራዬን ስለጨረስኩ መዝገቡ ይዘጋልኝ›› በማለት መዝገቡ እንዲዘጋ ማድረጉ ሕጉን ያልተከተለና አደገኛ መሆኑን ጠበቃቸው አስታወቁ፡፡

ተጠርጣሪ ጋዜጠኞች ተስፋለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪያንና የሕግ መምህር ዘለዓለም ክብረት፣ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃኔ ሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የሚቀርቡበት ዕለት ነበር፡፡ እንደወትሮው ሁሉ የተጠርጣሪዎች ቤተሰቦች፣ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጋዜጠኞች፣ ጓደኞቻቸውና የተለያዩ የችሎት ታዳሚዎች በጠዋት ማልደው በፍርድ ቤት ግቢ የተገኙ ቢሆንም፣ እስከ ቀኑ 5፡30 ሰዓት ድረስ ፖሊስም ሆነ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ችሎቱ አልመጡም፡፡ ከ5፡30 ሰዓት በኋላ ሌሎች ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ተጠርጣሪዎቹና ፖሊስ ችሎት ቆይተው ሲወጡ፣ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን፣ ደንበኞቻቸው ፍርድ ቤት መቅረብ አለመቅረባቸውን ለማጣራት የዕለቱን ተረኛ ዳኛ ለማነጋገር ገቡ፡፡ ጠበቃው ስለደንበኞቻቸው ፍርድ ቤቱን ሲጠይቁ፣ ፖሊስ ምርመራውን መጨረሱን በማሳወቅ መዝገቡ እንዲዘጋለት ጠይቆ መዘጋቱን ሲያስረዳቸው፣ ‹‹እንዴትና በምን ሁኔታ?›› የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ከመዘጋቱ ውጪ ምንም ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

እስረኛ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ የምርመራ መዝገቡ ሊዘጋ እንደማይችል የሚናገሩት ጠበቃ አመሐ፣ ተጠርጣሪዎቹ ከሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ መሆናቸው፣ በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት ምንም ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ በመሆኑ ድርጊቱ ሕገወጥና አደገኛ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ ምርመራውን ካጠናቀቀ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ይዞ በመቅረብ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳትና ክስ እስከሚመሠረትባቸው ድረስ በዋስ እንዲቆዩ ወይም የሕግ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሠረት ስለሚቆዩበት ሁኔታ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መስጠት እንደነበረበት አስረድተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ባልሰጠበት ሁኔታ ተጠርጣሪዎቹ ባሁኑ ወቅት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ የሚናገሩት ጠበቃው፣ በወንጀል ሕጉና በሕገ መንግሥቱ በተጠሰው አካልን ነፃ የማውጣት መብት (ሐቢየስ ኮርፐስ) ክስ ሊመሠርቱ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

Sunday, July 13, 2014

ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ የጀመረው እስር በአምባገነንነት መስመሩ ለመቀጠል የቆረጠ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው!!!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እና ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ የጀመረው እስር በአምባገነንነት መስመሩ ለመቀጠል የቆረጠ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው!!!
በፖለቲካ አመለካከታቸው እና እምነታቸው የታሰሩ ዜጎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ በድጋሚ እንጠይቃለን!!

ሕወሓት/ኢህአዴግ ለአለፉት 23 ዓመታት ወደር የሌለው የዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋና የሰብአዊ መብት ረገጣ በዜጎች ላይ ሲፈጽም መቆየቱና አሁንም በዚያው የአፈናና እስር መንገድ መቀጠሉን ዓለም የሚያውቀው እውነታ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይም በሚቀጥለው ዓመት የሚካሔደውን ሀገራቀፍ ምርጫ ተከትሎና ሁለቱ ፓርቲዎች የጀመሩትን የውህድት ጉዞ ለማደናቀፍ ባለመ መልኩ የሰብአዊ መብት ረገጣና ድፍጠጣ እንዲሁም ማሰሩና ማዋከቡ በእጅጉ ተባብሶ ወደ መንግሥታዊ ሕገ ወጥነት ጥቃት ተቀይሯል፡፡ ዜጎች መንግሥት እንዳሰማራቸው በሚጠረጠሩ የደህንነት ኃይሎች ስርዓቱን በሃይል ለማስቀጠል በመቁረጥ ዜጎች ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በጅምላ መታሰራቸውን፣ መደብደባቸውንና በስውር እስር ቤቶች ተወርውረው ደብዛቸው እንዲጠፋ መደረጉ ቀጥሏል፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሕገ ወጥነት ደግሞ ምርጫ ሲቃረብና የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰባሰብ ብሎም መዋሃድ ሲገለፅ ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነ ከዚህ በፊት ከነበሩ ተሞክሮዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡

ሕወሓት/ኢህአዴግ ለባለፉት 23 ዓመታት ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ ምርጫ ሲደርስ አባሎቻችንን ከመደብደብና ከማሳደድ በተጨማሪም በምርጫው ዋዜማ በተለመደውና አሰልቺ ፍረጃው ተደግፎ አመራሮቻችንን ማሰር ጀምሯል፡፡ እስሩም በፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን ሰሞኑን ብቻ አንድነት የስራ አስፈፃሚ አባልና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ሀብታሙ አያሌውን፤ የምክር ቤት አባልና የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺን፤ የአረና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነውን አቶ አብርሃ ደስታን እና የሰማያዊ ፓርቲ ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ የሆነውን አቶ የሽዋስ አሰፋን አስሯል፡፡ በተጨማሪም ሰብዓዊ መብታቸውን በመግፈፍ ከ48 ሰዓት በላይ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡ በጠበቃም ሆነ በወዳጅ ዘመዶቻቸው አይጎበኙም፡፡ በአካላቸውም ሆነ በስነ ልቦናቸው የደረሰባቸውን ጉዳት ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ፓርቲዎች እንደዚህ አይነቱን ሃላፊነት የማይሰማውና የጭካኔ ተግባር ማውገዝ ብቻ ሳይሆን እስከመጨረሻው ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ አምርረን የምንታገለው መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡

የሰሞኑ እስር እንደተለመደው የተቀነባበረ የስርዓቱ ድራማ ከመሆኑም በተጨማሪ የ2007ን ሀገራቀፍ ምርጫ በተለመደው ማሸማቀቅና ማወናበድ ለመውሰድ የተጀመረ የመጀመሪያ ርምጃ ነው ብለንም እናምናለን፡፡ የተቀነባበረ ድራማም በሚቆጣጠራቸው ስማቸው የህዝብ ተግባራቸው ግን የኢህአዴግ የፓርቲ መገልገያ በሆኑ ሚዲያዎች ማቅረቡን እንደሚቀጥልም እናውቃለን፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና ድራማ የሚከናወነው ከአፍ ባለፈ መተግበር ያልቻለውን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማስመሰያነት ለመጠቀምና የቀጣዩን ዓመት ምርጫ በለመደው ሁኔታ ከቻለ አስሮና አደናግሮ ካልተቻለ ጉልበቱን ተጠቅሞ ለመጠቅለል ነው፡፡

በተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ የሚደረገው ማዋከብ ይቁም፣ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ አሁኑኑ ይፈቱ!!!

shengo

ማክሰኞ ኅምሌ 1፣ 2006 ( July 8፣ 2014) የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ በህጋዊነትና በሰላማዊ መንገድ  የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች አመራር አባላት ከሆኑት ውስጥ አቶ ሀብታሙ አያሌውንና አቶ ዳንኤል ሽበሽን ከአንድነት  ፓርቲ፣ አቶ የሽዋስ አሰፋን ከሰማያዊ ፓርቲ እንዲሁም አቶ አብረሀም ደስታን ከአረና ፓርቲ ማሰሩን ተረድተናል።  የተጠቀሱት ግለሰቦች በሀገራችን ውስጥ ያለው የመብት መረገጥ፣ የፍትህ መጥፋት፣ የህግ የበላይነት አለመኖር ፣ ግፍ  ስቃይና መከራ እንዲያበቃ ምሳሌ የሆነ ትግል በሰላማዊ መንገድ ሲያካሂዱ የቆዩ ለመሆናቸው እጅግ ብዙ መረጃ መጥቀስ  ይቻላል።

 [ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]


እኔም አንዳርጋቸዉ ነኝ!

አንድን ሰዉ ጀግና የሚያሰኙ ብዙ መለኪያዎች አሉ፤ የእነዚህ መመዘኛዎች ስፋትና ጥልቀት ደግሞ እንደያገሩ ባህልና ወግ ይለያያል። የጀግንነት ትልቁ መለኪያ ጦር ሜዳ ዘምቶ ጠላትን ቁጭ ብድግ እያሰኙ መቅጣት ነዉ ብለዉ በሚያምኑ ኢትዮጵያን በመሳሰሉ አገሮች ዉስጥ “ ጀግንነት” የሚለዉን ጽንሰ ሀሳብ ጽንሰ ሀሳቡ በሚነካካዉ ሁሉም መልኩ መግለጽ አስቸጋሪ ነዉ። አንዳርጋቸዉ ጽጌ ግን በዬትኛዉም አገርና ባህል አንድን ሰዉ ጀግና ሊያሰኙ የሚችሉ መስፈርቶችን በሙሉ ከወጣትነት ዘመኑ ጀምሮ ያሟላ ሙሉ ህይወቱን ለፍትህ፤ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ አሳልፎ የሰጠ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነዉ። አገርህን አድን እያልንም ሆነ ወይም በርዕዮተአለም እየቀሰቀስን እልፍ አዕላፋትን ወደ ጦር ሜዳ ማዝመት ተችሏል፤ ለወደፊትም ይቻላል። ግን ይህ ስራ በራሱ ብዙም ጀግንነት የሚጠይቅ ስራ አይደለም። ለጦርነት ከቀሰቀስናችዉ ሰዎች ጎን ተሰልፈን ጦር ሜዳ ድረስ መዝመት ግን እሱ አሱ ወደር የለሽ ጀግንነት ነዉ። አንዳርጋቸዉ ጽጌ የነጻነትና የፍትህ አርበኞችን ያፈራ ብቻ ሳይሆን እሱ እራሱ አንደ አንድ አርበኛ ዉግያዉ ወረዳ ድረስ ሄዶ አብሯቸዉ ሊዋደቅ የተዘጋጀ ቆራጥ ሰዉ ነዉ።

አንዳርጋቸዉ ፍትህ በሌለባቸዉ ቦታዎች መኖርን የሚጸየፍ ፍትህን የቀመሙትን ሰዎች ወይም ተቋሞች ደግሞ ባሉበት ቦታ ሁሉ በጽናት የሚታገል አሁንም የፍትህና የነጻነት ጠላቶች በመታገል ላይ እንዳለ በየመን ከሀዲዎች አዉሮፕላን ጣቢያ ዉስጥ ታግቶ ለወያኔ ዘረኞች ተላልፎ የተሰጠ ዘመን ስራዉን የማያደበዝዘዉ ጀግናና የኢትዮጵያ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ ነዉ።

አንዳርጋቸዉ ጽጌ ዕድሜዉ ከሃያ አመት በታች ከነበረበት ግዜ አንስቶ የፊዉዳሉን ስርዐት፤ የደርግን ስርዐት ዛሬ ደግሞ የዘረኞችን ስርዐት የተቃወመ ብቻ ሳይሆን የተፋለመ እዉነተኛ ጀግና ነዉ። አብረዉት ትግል የጀመሩ ግለሰቦች የራሳቸዉ ህይወት ከህዝብ አደራ በልጦባቸዉ ከትግል አለም ሲለዩ፤ አንዳንዶች በቃን ደከመን ብለዉ ወኔ ሲከዳቸዉ ፤ አንዳንዶች ደግሞ ለስልጣንና ግዜያዊ ጥቅም ሚኒልክ ቤ/መንግስትን ከተቆጣጠረ ሁሉ ጋር ቤተኛ ሲሆኑ አንዳርጋቸዉ ግን በአካሉም በመንፈሱም ያልተሸነፈ፤ ለገንዘብም ለስልጣንም ሲል ህሊናዉን ያልሸጠ ህዝብና አገር የሰጡትን የፍትህና የነጻነት አደራ እንደተሸከመ ከአርባ አመታት በላይ ጸንቶ የቆመ እዉነተኛ የነጻነት አርበኛ ነዉ። እንዳርጋቸዉ ጀግና ብቻ ሳይሆን በዘመናት ዉስጥ አንዴ ብቅ ብለዉ ሰማይን በብርሃን አድምቀዉ አንደሚሰወሩ ሰማያዊ አካላት ወይም ከዋክብት ለዚህ ዘመን ኢትዮጵያዉያን በድፍረት የነጻነት ችቦ የለኮሰ የህዝብ ባለአደራ ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት የሆኑት የወያኔ ዘረኞችም ይህንን የህዝብ ልጅ አፍሪካ አዉሮፓና መካከለኛዉ ምስራቅ ዉስጥ በየሄደበት የተከታተሉትና በመጨረሻም እነሱን በመሳሰሉ ከሀዲ መንግስታት አማካይነት እንዲያዝ ያደረጉት አንዳርጋቸዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የለኮሰዉ የፍትህና የነጻነት ችቦ እንደሚያጋልጣቸዉ ብቻ ሳይሆን ጠራርጎ እንደሚያጠፋቸዉም ስለሚያዉቁ ነዉ።

አገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ “እባብን መመታት ጭንቅላቱን ነዉ” የሚባል የቆየ አባባል አለ። በእርግጥም እባብን ለመግደል ከጭንቅላቱ የበለጠ ጉዳት የሚያደርስበት ሌላ ቦታ የለም። ሆኖም እዚህ ላይ አንድ መርሳት የሌለብን ነገር አለ፤ እሱም እባብን ጭንቅላቱን መትተን ስንገድለዉ የሚሞተዉ አንድ እባብ ብቻ ነዉ፤ ብዙ እባቦች በህይወት ይኖራሉ፤ አዳደሶች ደግሞ ይወለዳሉ።

Saturday, July 12, 2014

አንዳርጋቸው ኢትዮጵያዊ ነው !!! በልጅግ ዓሊ

ወንድሙን ሲገሉት ፣ ወንድሙን ካልከፋው፣
ሱሬውን አምጡለት፣ ደሙ እንዲገለማው።

በጉን በጉ በላው በድዱ ጎትቶ ፣
ለማን አቤት ይሏል፣ ሰሚስ የት ተገኝቶ።

የሕዝብ ግጥም

አንዳርጋቸው በሁለት ወንጀለኛ መንግሥታት ትብብር ታፈነ፣ ተወሰደ ፣ ታሰረ ፣ ተሰቃየ።

ይህ አሳዛኝና የሚያበሳጭ ዜና ነው። በዚህ ቅጥፈት በሞላበት ዓለም ውስጥ ሕዝባቸውን በየቀኑ የሚያስሩ፣ የሚገድሉ፣ የሚያፍኑ መንግሥታት ቢተባበሩ ምንም የሚገርም ጉዳይ አይሆንም። አንዱ የሌላውን እከክ ማከኩ የተለመደ ነው። ይህ የመጀመሪያ ሳይሆን የተደጋገመ የወያኔ ዘረኛ አገዛዝና የአካባቢው ወንጀለኛ መንግሥታት የተለመደ ወንጀል ነው። ወያኔ ገና ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ እንዲሁም ከዚያ በፊት ጀምሮ ያስራል ፣ ይገድላል ፣ ያሰቃያል።

በዚህ ሰሞን በተፈጸመው ግፍ ውስጥ አንዳንድ የሕዝብ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የማነበው ሆነ የምሰማው አንድ በጣም መስተካከል ያለበት አስገራሚ ሃሳብ አለ። “አንዳርጋቸው እንግሊዛዊ ስለሆነ የመኖች አስረው ለወያኔ ማስተላለፍ አይችሉም“ የሚል ንግግርም ይሁን ጽሁፍ አንዳንዴ ብቅ ይላል። እግሊዛዊነቱስ እሺ ኢትዮጵያዊስ ቢሆን? ይችላሉ ማለት ነው? ለማስፈታት በምናደርገው ጥረት ማናቸውንም መንገድ መጠቀም ይገባ ይሆናል። ግን ደግሞ ዓላማችንን አዘናጊ፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ጎጂ ሊሆን አይገባም።

ለመሆኑ ዜግነታችን ምንድነው?

በአንድ ወቅት ከአንድ ጓደኛ ጋር ከሲዊዘርላንድ ወደ ጀርመን በባቡር ስንጓዝ ነበር ። በባቡሩ ባዝል የሚባል የጀርመን ግዛት ሲደርስ የጀርመን ፖሊሶች ገቡና ባቡሩ ውስጥ የተሳፈሩትን ነጮች ማንንም ሳይጠይቁ እኛ ጋ መጥተው መታወቂያ ጠየቁ። እኔ የስደተኛ ፓስፖርቴን ሰጠሁ ። ጓደኛዬ ጀርመናዊ ሆኖ ነበርና የጀርመንን ፓስፖርት ሰጠ። የእኔን ትንሽ ተመልክቶ መለሰልኝ። ጓደኛዬን ግን አብጠርጥሮ ጠየቀው። የጓደኛዬን ብስጭት ሳይ ሳቄ መጣ ። ሳቄ ደግሞ ምክንያት ነበረው ።

ጓደኛዬ ዜግነቱን የቀየረበት ምክንያት ቪዛ ሳይጠየቅ በአውሮፓና በአሜሪካ እንደፈለገ መንደላቀቅ ስለሚችል መሆኑን ብዙ ጊዜ ሲያወራ ሰምቼው ነበር። ያ የተንደላቀቀበት የጀርመን ዜግነት ፓስፖርት መታወቂያ ሳይሆን መጠየቂያ ሆነበት። ።ከዜግነት የሚያገኘው የቪዛ ጥቅም እንኳን በጥቁርነቱ ተሸፈነ። እሱ በጥያቄ ተንገፍግፎ እኔ ግን በስደተኛ መታወቂዬ በሰላም ታለፍኩ። ይህ ቁጥጥር በባቡሩ ላይ ጥሩ ውይይት አጫረ። ጀርመኖች በተከፋፈለ ሁኔታ ሰለ ጀርመንነት. ስለ ስደተኝነት ፤ እሱንም ተከትሎ ስለሚደረገው ወንጀል እንደ ተዐምር ተወራ። እኛም ዘረኞች ብለን ተሳደብን፣ እነሱም በጥቁር ጀርመንነታችን አሹፈው ተሳለቁብን።

“መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም!!!” ሰማያዊ ፓርቲ

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት መሪዎችን እና በአገዛዙ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰሩን፣ ማሰቃየቱንና ግድያውን ተያይዞታል፡፡ በህገ መንግስቱ የተካተቱ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በሙሉ የሚጥሰውና የአምባገነንነት ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ያፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ ከፀደቀበት እለት አንስቶ ኢህአዴግ ለስልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ፍፁም ሰላማዊ ታጋዮችንና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በድፍረት የፃፉ ጋዜጠኞችን ብሎም የእምነት ነፃነታችን ይከበር ብለው የጠየቁ የሀይማኖት መሪዎችን በጠራራ ፀሃይ ያለምንም ወንጀል በዚሁ ህገ ወጥ አዋጅ ‹‹የፀረ ሽብር ግብረ ሀይል›› በሚባል ማንነቱ በማይታወቅ የጨለማ ቡድን ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛል፡፡

ይህን የሚያጋልጡ ሚዲያዎችንም ለማፈን እስር ቤቶችን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያፈሰሰ የአየር ሞገድ ያውካል፤ በዚህ ሳያበቃ በሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ፖለቲከኞችን ለማሸማቀቅ እንደ ኢሳት ያሉ ሚዲያዎችን የአሸባሪ ልሳን ብሎ በመፈረጅ ሚዲያውን የሚጠቀሙትን ደግሞ ከአሸባሪዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው አድርጎ መወንጀሉን ቀጥሎበታል፡፡ እንደሰማያዊ እምነት ማንም አካል መልእክት የሚያስተላለፍበትን የሚዲያ ተቋም ሊመርጥለት እንደማይችል መንግስት እንዲገነዘበው ከዚህ በፊት በግልፅ ያሳወቀ ሲሆን አሁንም ፓርቲው በዚሁ የፀና አቋሙ እንደሚቀጥል በድጋሚ ይገልፃል፡፡

ባጠቃለይ የዚህን ገዢ አካል የእውር ድንብር ሀገር የማስተዳደር ጉዞ ለመታገል በርካቶች በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም በህወሓት/ኢህአዲግ ግፍና መከራ ተገፍተው ስርዓቱን በሃይል እናስወግዳለን ብለው ሀገር ጥለው የተሰደዱ ዜጎችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የህወሓት/ኢህአዲግ ማናለብኝነትና የስልጣን ጥመኝነትም በግለሰቦች ላይ ከሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ በላይ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትን አስከትሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ይህ ገዢ ፓርቲ የፈጠረው ስርዓት የሀገሪቷን ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳር በማጥበብ ሀገራችንን ወደ አልተፈለገ አለመረጋጋትና ቀውስ እየመራት ይገኛል፡፡ፓርቲያችንም እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም በቅርቡ እየተፈፀሙ የሚገኙ ህገ ወጥ ድርጊቶች ስላሳሰበው ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገዷል:-

2nd Letter to H.E. Field Marshall Abdu Rabu Mansour Hadi President Republic of Yemen



H.E. Field Marshall Abdu Rabu Mansour Hadi

President Republic of Yemen Sana’a, Yemen

Re: Extradition of Andargachew Tsege, Secretary General of Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy from Yemen to Ethiopia

Your Excellency:

We are writing to you condemning in the strongest words possible the deplorable actions taken by your government to abduct and then extradite Andargachew Tsege, to the minority ethnic dictatorship in Ethiopia. On July 1, 2014, we had written a letter to you expressing our grave concern over the illegal abduction and detention of Andargachew Tsege while in transit at Sana’a International Airport on June 23, 2014.

In our letter dated July 1 that was hand delivered to your embassies around the world. it was made abundantly clear that Mr. Tsege a well-known pro-democracy icon and human rights advocate in his ancestral homeland, Ethiopia, presented no threat, what so ever, to Yemen or to the Yemeni authorities.

We had stated in the letter that the continued illegal detention of Mr. Tsege, a renowned critic of the Ethiopian government is politically motivated and against international law. We had also requested that you use the powers vested in your office to stop any illegal renditions the regime in Ethiopia may have requested.

ፋሽስታዊ ፕሮፖጋንዳው እና ምላሻችን!


ፋሽስታዊ ፕሮፖጋንዳው እና ምላሻችን!( pdf )

ሐምሌ 3 ቀን 2006 ዓ.ም.

ዘረኛውና ፋሽስታዊ ወያኔ፣ የኢትዮጵያዊያንን የትግል መንፈስ ለመስበር እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነትና ለፍትህ የሚያደርገውን ትግል ወኔ ለመስለብ ያቀደበትን የመጀመሪያውን ፕሮፖጋንዳ ለቀቀ። የህግ ልጓም የማያውቀው ፋሽስት በግፍ የያዛቸውን ሰዎችን እይስሙላው ፍርድ ቤት እንኳን ከመቅረባቸው በፊት “ወንጀለኛ” እያለ እንዲህ ዓይነቱ ፕሮፖጋንዳ እንደሚነዛባቸው ተደጋግሞ የታየ በመሆኑ ይህ ፕሮፖጋንዳ የሚጠበቅ ነበር። ሆኖም ግን ፕሮፖጋንዳው ያዘጋጁ ሰዎች ተስፋ ያደረጉትን ውጤት ያመጣ አልሆነም። ወደፊት ደግሞ ሌሎች ሙከራዎች ይደረጉ ይሆናል፤ ውጤታቸው ግን ከዚህኛው የተለየ እንደማይሆን ይገመታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኢቲቪ የእውነት ጥፍጣፊ እንኳን እንደማይገኝ ያውቃል።

በአሁኑ ተቆራርጦ በተለጣጠፈ ፊልም በታጀበው ፕሮፖጋንዳ ውስጥ፣ መሪያችን አንዳርጋቸው ጽጌ በምግብና ውሀ እጦት ብቻ ሳይሆን በተፈጸመበት የተለያዩ የማሰቃያ ወንጀሎች ብዛት አካሉ መዳከሙ ይታያል። ያም ሆኖ ግን ከእሱ ወጥተው እንድንሰማቸው የተደረጉት ቃላት የመንፈሱን ጥንካሬ ገላጮች ናቸው። እሱ ሥራውን መጨረሱንና በዚህም ምክንያት ህሊናው የተረጋጋ መሆኑን ነው የሰማናቸው ቃላት የነገሩን። በዚህ አጭር አጋጣሚ እሱ ግዴታውን ማጠናቀቁ፤ ሀገራችን ከወያኔ ፋስሽቶች ነፃ የማውጣት ኃላፊነቱ በእኛ ትከሻ ላይ መውደቁን ነገረን። ለዜናው ማጀቢያነት የገቡት ፎቶግራፎችም መሪያችን ፈታኝ በሆነ የተፈጥሮ አካባቢ የከፈለውን መስዋዕትነት የሚመሰክሩ ሆነው ተገኙ።

ጀግናው አንዳርጋቸው ጽጌን በተጎሳቆለ ሁኔታ ማየት ስሜትን የሚጎዳ ቢሆንም የመጀመሪያው ስሜት ካለፈ በኋላ ከፊልሙ በአዕምሮዓችን የሚቀረው ከላይ በአጭሩ የተገለፁት ጥንካሬውና ኃላፊነትን ወደ እኛ በይፋ ያስተላለፈበት አጋጣሚ መሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተሠራው የመጀመሪያ በምስል የተደገፈ የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ከታለበት ዓላማ በተፃራሪ የወያኔን ሹማምንት አውሬነትና የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ትልቅነት አሳይቷል።

Friday, July 11, 2014

ወያኔ አንዳርጋቸው ያፈነበት እለት የሚረግምበት ቀን ሩቅ አይደለም!

ህወሃት ጉጅሌ እንደማንኛውም አምባገነን ከፊት ከነበሩ አምባገነኖች ቅንጣት ትምህርት አልተማረም። ወያኔዎች በእብሪት የያዙት ስልጣንና ከህዝብ የዘረፉትን ንብረት የሚያጡት እየመሰላቸው በባነኑ ቁጥር የነጻነት አርበኞችን በማፈን በመግደልና በማሰቃየት ፍርሃታቸው የተወገደ ይመስላቸዋል።

ወያኔ የእኛ መሪና የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት አርበኛ በሆነው አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ያካሄደው አፈና ከአፈናውም በሆላ በሚያደርሱበት አካላዊ ስቃይ ፍርሃታቸው የሚወገድ ወይም ስርአታቸው ከሞት የሚተርፍ መስሏቸው ከሆነ በእጅጉ ተሳስተዋል። አንዳርጋቸው ዛሬ በእጃቸው ሆኖ በነጻነት ይኖር ከነበረበት በበለጠ የሚለበልባቸው የውስጥ እግር እሳት ይሆናል።

አንዳርጋቸው ሰበአዊ ምቾቱንና ለራሱና ለቤተሰቡ መኖርን አቁሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ነጻነት በህይወቱ ሊጋፈጥ ከቆረጠ ቆይቷል። እኛ የትግል ጓዶቹና ለህዝብ ነጻነት የቆሙ ሃይሎች ሁሉ አንዳርጋቸውን እናውቀዋለን። ወያኔ በአካሉ ላይ የለመደውን ስቃይ ጀምሮበታል፣ ከዚህ የበለጠም ጉዳት እንደሚያደርስበትም እናውቃለን። የአንዳርጋቸውን ታላቅ የነጻነት ሰውነትና ክብረ ህሊናውን፣ በአርበኝነቱ የሚሰማውን የኩራት ስሜቱን ለግፈኞች ያለውን ንቀትና መጸየፍ ሊለውጡ እንደማይችሉ አስረግጠን እናውቃለን።

አንዳርጋቸው እንደሁላችን ሰው ነውና በፈሪዎች በትር የሚደርስበት አካላዊ ስቃይ ግን ለህዝባችን የገባነውን ቃል ውሳኒያችንን እና አቋማችንን እንደብረት ያጠነክረዋል እንጂ አያላላውም።ይልቁንም በአንዳርጋቸው መታፈን ምክንያት ከመላ ሀገራችን በአለም ዙሪያ ከተበተነው ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች የነሰታነት ሃይሎች የምንሰማውና እየሰማን ያለነው የሚያስገመግም ህብረ ድምጽ ከብረት የሚያጠነክር ሃይል ሆኖኗል።

አንዳርጋቸው የዘራው የነጻነት የአርበኝነት ዘር ከመብቀል አልፎ እየጎመራ በመሄድ ላይ ነው። አንዳርጋቸው ሺ አንዳርጋቸውን ተክቷል። ወያኔ አንዳርጋቸውን በማፈንና በእጁ አስገብቶ በራሱ መስኮት ቲቪ ስቃዩን እንግልቱን በማሳየት ሊያላምጠው የማይችል የብረት እንክብል ነው የነከሰው። ይህንንም ሳይውል ሳያድር ያየዋል፡፡

መላው ህዝባችን በእልህና በቁጭት ላይ ያለህ ወገናችን ና የሀገራችን የነሰታነትና የዴሞክራሲ ሃይሎች በሙሉ፡- በአንዳርጋቸው ላይ ወያኔ የፈጸመው የአሸባሪዎች ውንብድና በየአንዳንዳችን ላይ የተፈጸመ በደል ግፍ ነው።

ይህንን የሽብርና የውንብድና ስርአት ለማስወገድ አብረን ከመነሳት ውጪ አማራጪ የለንም። የልዩነታችንን አጥር አፍርሰን የወየኔን እድሜ እንድናሳጥር ግንቦት 7 ለሁላችንም ጥሪውን ያቀርባል።

አንድ ሆነን የአንዳርጋቸውን ስምና ምግባር እንሁን!

አንዳርጋቸው የዘራው እና እየጎመራ ያለው የአርበኝነት ንቅናቄ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ወያኔ አንዳርጋቸውን ያፈነበት ቀን የሚረግምበት ጊዜ ከዚህ በኋላ ሩቅ አይሆንም፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Sunday, July 6, 2014

ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና ተግባሪዊ የመጀመሪያ እርከን የትግል ጥሪ
ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!

ሰኔ 29 ቀን 2006 ዓ.ም

በየጊዜው እየከረረና እየገረረ የመጣው ትግላችን “ሁላችን አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ወደ ተባለ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ይህ ጽሁፍ የዚህን የትግል ምዕራፍ ምንነትና ይዘት በአጭሩ ያብራራል። በዚህ ጽሁፍ ላይ የሰፈሩት ዓረፍተ ነገሮች ተነበው የሚታለፉ ሳይሆን በተግባር የሚተረጎሙ ሥራዎች ናቸው።

አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ምን ማለት ነው? አንዳርጋቸው ጽጌ ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲና ለእኩልነት በጀግንነት የቆመ፤ ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ሲከፍል የነበረና አሁንም እየከፈለ ያለ መሪያችን ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ልክ እንደሱ ትሁት ሆኖም ግን ቆራጥ፤ ሆደ ሰፊ በዚያው ልክ ደግሞ መራር፤ አስተዋይና ብልህ ሆኖም ተግባር ተኮር መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ወያኔን ለማስወገድ መደረግ የሚገባውን እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀ ሰው መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ለአገርና ለትውልድ ቤዛ መሆን ማለት ነው።

ወያኔ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ካተኮረባቸው ምክንያቶች አንዱ የወያኔን የዘር ፓለቲካና ፕሮፖጋንዳ በሚያመክን መልኩ በተግባር ትግል ውስጥ ካሉ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የኦጋዴን፣ የጋምቤላ እና ሌሎች ዘውግ ተኮር ድርጅቶች ጋር ንቅናቄዓችን ተግባራዊ ትብብር ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ድረስ ማቀራረብ የቻለ መሪ መሆኑ ነው። ከሁሉም በላይ ለወያኔ የጉሮሮ ቁስል የሆነበት ደግሞ ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ጋር ግንቦት 7 የፈጠረው ጠንካራ ትብብር ነው። በትህዴን ጋር በመሆን አቶ አንዳርጋቸው ወያኔ በትግራይ ሕዝብ ጀርባ መንጠልጠል እንዳይችል አድርጎታል። እናም አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ከዘረኝነት ፀድቶ መገኘት ማለትም ጭምር ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት በኢትዮጵያዊያን እኩልነት እና እኩል ባለመብትነት ከልብ ማመን እና ለእኩልነት በጽናት መታገል ማለት ነው።

አንዳርጋቸው ጽጌን ለመሆን የግድ የግንቦት 7 አባል መሆንን አይጠየቅም። አንዳርጋቸው ጽጌን ለመሆን ለመልካም ዓላማዎች መሳካት ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀትን እንጂ የግድ ከአንድ ወይም ከሌላ ድርጅት ጋር መወገንን አያሻም። ያም ሆኖ ግን አንዳርጋቸው ጽጌን የሆነ ሰው በጠንካራ ድርጅት የታገዘ ትግል አስፈላጊነት ይረዳል።

በመጨረሻም አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ኦኪሎ ኦኴኝ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ እና እዚህ ዘርዝረን ልንጨርሳቸው የማንችላቸው ጀግኖቻችንን ሁሉ መሆን ማለት ነው።

“የሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ዘመቻ ትኩረቶችን በየጊዜው የምንገልጽ ሲሆን ከነገ ጀምሮ በሥራ ላይ መዋል ያለበት የዓለም ዓቀፍ ዘመቻው የመጀመሪያ እርከን ትኩረቶች በዚህ በታች ቀርበዋል

አዋጅ አዋጅ !!!………..ልብ ያለዉ ልብ ይበል ጆሮ ያለዉ ይስማ !!

አዋጅ አዋጅ !!!

ልብ ያለህ ልብ በል ጆሮ ያለህ ስማ !!

የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በየመን መታገት አስመልክቶ አጭር መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል::በመግለጫችን የመን ታጋዩን ልታግት የምትችልበት የጸጉር ስንጣቂ  የምታክል  ምክንያት እንደሌላት ሊኖራትም እንደማይችል ስለሆነም ታጋዩ  ባስቸኳይ  እንዲለቀቅ በተደጋጋሚ ጠይቀን፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ  የነጻነት ታጋዩ ለፋሽስቱ የወያኔ ቡድን ተላልፎ  ቢሰጥ የመን የማይሰረዝ ታሪካዊ ስህተት የምትሰራ  መሆኑን ህዝባዊ ሃይላችንም የበቀል እርምጃዎችን  እንደሚወስድ አሳውቀን ወያኔም ምናልባት ትግሉን አስቆማለሁ በሚል የሞኝ  ስሌት  ያደረገው ከሆነ  ድርጊቱ  ትግሉን በዕልህ  እና  በበቀል አጅቦ ከመውሰድ እና  ከማፋጠን የዘለለ ትልቁ የሃሳብ አባት አንዳርጋቸው በሃገሪቱ  ሰማይ ላይ  የለቀቀውን የኢትዮጵያዊነት ጸረ ወያኔ መንፈስ አስሮ አሰቃይቶ፣ገሎ ማስቆም እንደማይችል አሳስበን አስገንዝበን ነበር:: መግለጫችን የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ ግን የየመን መንግስት  እንደሰጋነው ትልቁን የቁርጥ ቀን ልጅ ለወያኔ አሳልፎ መስጠቱን አውቀናል::

የተከበርከው የታላቅ ታሪክ ባለቤት የሆንከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ  አሁንስ  ምን ትጠብቃለህ?? ምንቀረህ ?? ያለህበትን ሁኔታ የሚገልጽ ከዚህ በላይ ገላጭ ነገር ከቶ ከወዴት ይመጣል??ወያኔ የአንዳርጋቸው በእጁ መግባት ለጊዜውም ቢሆን ከሚፈጥርለት ፌሽታ  ጎን ለጎን እገታው በይፋ  ከተገለጸበት ቅጽበት ጀምሮ ግን  የሚፈራው የሚጠላው ነገር ብቅ ብሏል፦የአንድነት መንፈስ!!  የጋራ ድምጽ!!እገታው ለኢትዮጵያ  ህዝብ  በይፋ  ከተነገረ በኋላ በሁሉም አቅጣጫ የሚኖር መላው ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ  አመለካከት እና  ፍልስፍና  ሳያግደው ለአንዳርጋቸው ያለውን ድጋፍ እና  ያገባኛል ባይነቱን አሳይቷል፣እያሳየ ነው፤ገልጿል እየገለጸ ነው::

ይህ መጥፎ አጋጣሚ ለተቃውሞ  የፖለቲካ  ትግሉ ይዞት የመጣው መልካም ሁኔታ እና ክስተት ይኸው ነው:፤ተባብሮ መጮህ!! የተባበረ ነጎድጓዳዊ ቁጣ!!

በእውኑ ከዚህ በላይ ወያኔን የሚያሸብር ዙፋኑን የሚያርድ ጉዳይ ከወዴት ይገኛል?? የትም::

የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ከቶ በምን አይነት አመክንዮ እና የታሪክ ምጸት ነው ወያኔን የመሰለ አንድ ተንቀሳቃሽ የሽፍታ ቡድን ተሰደን  እንኳን መተንፈስ እንዳንችል አድርጎ ለ 23 ዓመታት ቀጥቅጦ እና  አዋርዶ ሊገዛን የቻለው??

እራሳችን በዘር፣በሃይማኖት፣በፖለቲካ  አመለካከት ልዩነት ከፍለን የተባበረ ክንዳችን የጋራ ጠላታችን ላይ ማንሳት ባለመቻላችን አይደለምን?? ነው እንጅ!!!

የግንቦት 7 ህዝባዊ  ሃይል በዚህ  ታሪካዊ ወቅት የታሪክ ጠርዝ ላይ ቆሞ የሚያስተላልፈው መልዕክት አለው፦

እስከመቸ ነው ጥቁሩን በሬ ጅብ ሲበላው ነጩ በሬ  ሳይደንቀው፣ያጣማጁ ደም ሳይሸተው ፣ ነጩን በሬ  ጅብ ሲከበው ጥቁሩ  በሬ አደጋውን የነጩ ብቻ  አድርጎት ጉዳዩን ችላ  ሲለው በመጨረሻ  ግን ሁለቱም የጅብ መንጋ  ሲሳዮች ሲሆኑ ተረት እየተተረተብን የምንጓዘው???? ሃገራችን ጨርሳ እስክትጠፋ ማህበረሰባችን እስኪበተን ነውን?? ብዙዎቻችን የምናውቀውን አንድ ታሪክ እዚህ ላይ ብንጠቅስ ያለንበትን ሁኔታ  በተወሰነም ደረጃ  ቢሆን ለማሳየት  የሚረዳ ይመስለናል::ናዚ ወደ ስልጣን ሲመጣ እና  የስልጣን ማማ ላይ ቆሞ የሚሰራውን እየሰራ  በነበረበት ወቅት ላይ የወቅቱ የጀርመን ልሂቃን ዝምታ የገረመው አንድ አስተዋይ ታላቅ ሰው ይህን ታዝቦ ነበር፦

በቅድሚያ  ኮሚንስቶች ላይ አነጣጠሩ

የዚያን ጊዜ ኮሚንስት  ስላልነበርኩ ዝም አልኩ

ቀጥለው በሶሻሊስቶች ላይ አነጣጠሩ

የዚያን ጊዜ ሶሺያሊስት  ስላልነበርኩ ዝም አልኩ

ለጥቀው ወደ ሰራተኛው  ማህበር አነጣጠሩ

የዚያን ጊዜ  የሰራተኛው ማህበር አባል ስላልነበርኩ ዝም አልኩ

በመጨረሻ  ወደ  እኔ መጡ በዚያን ጊዜ ለኔ  የሚጮህልኝ አንድም ሰው አልተረፈም ነበር ::

እስከመቼ ነው አንዳንችን ለአንዳችን እና  ተባብረን እንዳንጮህ የዘር፣የእምነት እና  የፖለቲካ  አስተሳሰብ ልዩነት አሎሎ ትናጋችን ውስጥ ተቀርቅሮ በጩሀት እንኳን እንዳንደጋገፍ የሚያንቀን???? በ እውኑ ከላይ  የተቀመጠው ትዝብት በትክክል ወቅታችንን አያንጸባርቅምን??!

ስለዚህ የአንዳርጋቸው መታገት  እና  ለወያኔ  ተላልፎ መሰጠት የፈጠረው የአንድነት ስሜት በስርዓት ተኮትኩቶ  በፍጥነት ፋፍቶ ወያኔን ወደመጣል እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት ዋና  ዓላማችን ድረስ ሊወስደን  ይገባል::ምንድን  ነው የምንጠብቀው? እንዴትስ ነው በዚህ ደረጃ  ያፍዝ ያደንግዝ የተደገመብን??ምን ዓይነት  የመንፈስ ክሽፈት ነው እግር ከዎርች ያሰረን??

ምናልባት የምናሳድጋቸው ልጆች  ይኖሩናል::አንዳርጋቸውም እኮ  እንደሰው የወለዳቸው ህጻን ልጆች አሉት ::አንድም ቀን አብሯቸው ውሎ  አያቅም እንጅ::እዚህ በረሃ  ውሃ እና  ትርፍ ስዓት ሲገኝ የታጋዩን ልብስ የሚችለውን ያህል  ያጥብ ነበር፣የልጆቹን ልብስ  እንዳላጠበ  ግን እርግጠኝ ሆኖ መናገር ይቻላል:፡ከ ዓመት በላይ  በረሃ  ውስጥ ከረሃብ እና ጥም ጋር ሲታገል ልጆቼ የሚል ቃል  ካፉ ወጥቶ  አያቅም :: እንደሰው  ልጆቹን  ስለማይናፍቅ ግን አይደለም::ለዚች መከረኛ ሃገር ሙሉ ራሱን ስለሰጠ የልጅና  የቤተሰብ ናፍቆት የመሰሉ ሰዋዊ ፈተናዎችን ታላቅ ራዕይን በሰነቀች ልቡ ውስጥ አስቀምጦት እንጅ::እና አንዳርጋቸው  ልጆቹን ስለሚጠላ አይደለም የት እንደሚሄድ እንኳን ሳይነግራቸው ወደ በረሃ ሹልክ ያለው::ልጁን ማን  ይጠላል!!የአንዳርጋቸው ጭንቀት ልጆቻችን ያለ ሃገር ወልደናቸው ምን ሊሆኑ ነው የሚል ነበርና ሃገር ሰርቶ ፣ማህበረሰብ ገንብቶ የማስረከብ ስራውን  ቅድሚያ  ሰጠው::

ምናልባት ሃብት፣ትዳር ይኖረን ይሆናል::ግን ያለሃገር እና  ያለነጻነት ሃብትና  ትዳር ምንምን ይላል?? ይጣፍጣል?? አይመስለንም::በዘርህ  እና  በፖለቲካ  አስተሳሰብ ልዩነትህ  ምክንያት ከሞያሌ አሜሪካ ፣ከጎንደር አውስትራሊያ ፣ከጋምቤላ ካናዳ ድረስ በምትሳደድበት እና በምትታደንበት ሁኔታና ዘመን ውስጥ እስከ  አፍንጫ ተነክሮ ሃብትና  ትዳር ምንድን ናቸው??ምናልባት እንደቀንድ አውጣ ራሳችንን የምንቀብርባቸው ቅርፊቶች ካልሆኑ በስተቀር::አንዳርጋቸው ለዚች ጣጣዋ ያላላቀ ሃገር፣ለዚች የምትንገላታ ባንዴራ ኪሱ ውስጥ 5  የአሜሪካን ዶላር እስኪቀረውና አላላውስ እስኪለው ኢትዮጵያዊ እምነቱን ለመግለጽ፣ለማስተማር፣ለመቀስቀስ ዞሯል ወጥቶ ወርዷል::

ምናልባት_________እያልን ብዙ  እንደምክንያት የሚጠቀሱ ነገሮችን ስንደረድር  ልንውል  እንችላለን::አንድን ሃገር እና  ትውልድ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ እየጣረ  ያለ  ስርዓትን በግልጽ  እስከ ህይወት መስዋዕትነት ላለመታገል ብዙ  ምክንያት  እያነሳን ራሳችን ልንሸነግል እንችላለን:: ከቁም ሞት  እያዳነን አይደለም እንጅ!!

ከቶ በምን ዓይነት ተፈጥሯዊ ወይ ሰው ሰራሽ ተጠየቅ ይሆን አንድ የሽፍታ ቡድን 97 ሚሊዮን  ህዝብ ለ 23 ዓመታት አምበርክኮ ለገዛ የሚሞክረው?? ለቆመ አይደለም ለሞተ የሚገርም ጉድ አይደለምን??ከዚህ በላይ አሳፋሪ ነገርስ በየትኛው የዓለም ጫፍ ቢታሰስ ይገኛል???ይህ አዋጅ ለተደራጁ  የፖለቲካ  ሃይሎች ብቻ አይደለም፣ለሲቪክ ተቋማት ብቻ  አይደለም፣ለወጣቱ ሃይል ብቻ አይደለም፣ለወንዶች  ብቻም  አይደለም::ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የታወጀ አዋጅነው:: ተነስ !!! መሳሪያ አንሳ !!! ወያኔን በጉልበትህ ከራስህ ላይ አውርድ!!!የመከራ እና  የውርደት ዘመን ይብቃ !!!ያለበለዚያ ሁለት ምርጫዎች እጃችን ላይ አሉ፦አንድ በጋራ ታግለን ነጻነታችን ማዎጅ ሁለት ባርነትን መርጦ ፣ባርነትን ተቀብሎ እንደባሪያ መገዛት!! በቃ !!

አንድ አለመሆናችንን የታዘቡ እናም የናቁን ፣በየስርቻው መወሸቃችንን የተገነዘቡ እናም የተጸየፉን የተጻፈ እና ያልተጻፈ  የረጅም ጊዜ ፖሊሲ ያላቸው የብሄራዊ ቤተሰብ ምስረታ  ሂደታችን  አደናቃፊ ብሄራዊ ጠላቶቻችን ነጻነታችንን  ስለማይፈልጉ ቅኝ ገዝዎቻችን ሌት ተቀን እየተባበሯቸው ነው::የሚፈልጉትን ሰው አንስተው እየሰጧቸው ነው::

እልፍ አዕላፍ ኢትዮዮጵያዊያን ከተጠጉበት እየታደኑ  ለእርድ ሲቀርቡ ይሀው ድፍን 23 ዓመት ሞላን::አንዱ ከሆነ ሃገር ሲያዝ  እና  ተላልፎ  ሲሰጥ እንደነጩ በሬ የጓዳ አጋራችን ደም አልከረፋ  ሲለን፣እኔ  ምን አገባኝን ስንቀኝ፣ይህ እኮ የኮሚኒስቶች ጉዳይነው፣የነከበደ ጣጣ ነው እዛው ይወጡት ስንል በየተራ  እየተለቀምን እያለቅን ነው::

አንዳርጋቸው ለዕርድ  ቀርቧል!!ምናልባት ታሪካዊ ጠላቶቻችን የእርድ ቢላዎቻቸውን ስለው ደም  በቋጠረ  የበቀል አይን ከበው እያዩት ይሆናል::ሊያርዱት!!እንደታሳሪ  ፈርቶ  ሳይሆን መልካም ስራ  ሰርቶ  ክርስቶስ/አላህ ዙፋን ፊት እንደቀረበ ጻድቅ በኩራት ቆሞ አንገቱን እንደሚሰጥ ግን ጥርጥር የለንም::ታዲያ  የኛ አዋጅ አንኳር መልዕክትም ያለው እዚህ ጋር ነው::አንዳርጋቸው በየሰርጡ እና  በየእርሻው እየዞረ  የዘራው የአንድነት፣የኢትዮጵያዊነት፣የነጻነት፣የፍትህ ፣የዴሞክራሲ ዘር የሱ በድን ላይ ይብቀል፣ደሙን ጠጥቶ  ይፋፋ ከሱ በኋላ ግን ይብቃ  የሚል ነው ::ኢትዮጵያዊዪ አንድ ሆኖ ተቆጥቶ  እንደ አንበሳ  ያገሳ ዕለት የሰሜን ነፋስ እንደነካው ጉም በነው  እንደሚጠፉ እናውቃለን::ያውቃሉ::ማድረግ ያቃተን ተደጋግፈን መቆም፣እጅለ እጅ መያያዝ፣አንድ ላይ መጮህ አንድ ላይ የቁጣ  ክንዳችን መሰንዘር ብቻ  ነው::ታዲያ  ካሁን በኋላ  የአንዳርጋቸውን አንገት የቆረጠ ካራ ለሌሎች ተረኞችም ተስሎ  እንዲቀመጥ እንፈልጋለን?? የማንፈልግ ከሆነ  እጆቻችንን እርስ በርስ አጣምረን መብረቅ  እናስተፋቸው፣ነጎድጓድ  እንሙላቸው::ከዚያ  ውጤቱን በታሪክ ገጽ ላይ ጎልቶ  ተጽፎ  እናየዋለን::ያለበለዚያ ኢትዮጵያዊያን የለንም ጨርሰን ጠፍተናል ማለትነው::ስለዚህ  ከዛሬ  ጀምሮ አዋጅ አዋጅ፣ ልብ ያለው ልብ ይበል ፣ጆሮ ያለው ይስማ !!!ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ሳትጠፋ ጠላቶችህን አጥፋ !!!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Saturday, July 5, 2014

የኢትዮጵያ ወጣቶች ንቅናቄ “የአቶ አንዳርጋቸው መስዕዋትነት ለትግላችን መፋፋም ወሳኝ ምዕራፍ ነው” አለ!!!

የአቶ አንዳርጋቸው መስዕዋትነት ለትግላችን መፋፋም፣ ለትብብራችን ተግባራዊነትና፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት እውን መሆን ወሳኝ ምዕራፍ ነው!

ጋዜጣዊ መግለጫ

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ በተፈጠረው ልብ የሚሰብር ክስተት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ፤ ይህ ፋሽስት የወያኔ/ኢህአዴግ ሥርዓት የፈፀመውን አሳፋሪና ህገወጥ አፈና በከፍተኛ ምሬት፣ ቁጭትና፣ እልህ አጥብቆ እንደሚቃወም ያሳውቃል። የጎረቤት ሃገራት አቶ አንዳርጋቸውን ጨምሮ በስደት ላይ በሚገኙ አያሌ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ የአፈና ወንጀልን በመፈፀም ንፁሃን ዜጎችን ለሰው በላው የወያኔ/ኢህአዴግ ሥርዓት አሳልፈው ሲሰጡ በተደጋጋሚ ሰምተናል አይተናልም። ድርጅታችን ይህ የወንበዴ መንግስታት አይን ያወጣ ወንጀል ነፃነቱንና ህልውናውን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ጀግንነትንና ጀብድን በመፈፀሙ፤ ለአለም ጥቁር ህዝቦች ብቸኛው የነፃነት ምሳሌ ሆኖ በአለም አቀፍ ደረጃ ለዘመናት በክብር የኖረው መላው የኢትዮጵያ ህዝብን የናቀና ያዋረደ፤ የሃገሪቱን ሉአላዊነትና ክብር በጅጉ የደፈረ፤ ይቅር የማይባል ብሄራዊ ወንጀል መሆኑን በፅኑ ያምናል። በመሆኑም ሥርዓቱ እየፈፀመ በሚገኘው አስከፊና አሳፋሪ ወንጀል ወደፊት ከመጠየቅ በፍፁም እንደማይድንና ምናልባትም እጅግ የከፋ ዋጋ እንደሚያስከፍለው ተገንዝቦ፤ ከዚህ የወንጀል ድርጊቱ በመታቀብ አቶ አንዳርጋቸውንም ሆነ ሌሎች በተመሳሳይ መልኩ ከጎረቤት ሃገራት ታፍነው በየእስርቤቱ የሚማቅቁ አያሌ ንፁሃን ዜጎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ ከወዲሁ በጥብቅ ያስጠነቅቃል።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እርምጃ እወስዳለሁ አለ!!!

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ኢሕአግ/የተሰጠ መግለጫ

የማፈኛ መዋቅሩን መሰረት በማድረግ በርካቶች ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን እጅግ በከፋና በሚዘገንን ሁኔታ በማጥፋት እኩይ ተግባሩ የሚታወቀው አረመኔው የወያኔ ስርዓት በአገራችን የተንሰራፋውን መጠነ-ሰፊ ተግዳሮት ከመሰረቱ ለመንቀል በሚደረገው ትግል ብርቱ ጥረትና እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን መንግስት ጋር በማበር የአንድን ሰው ከአገር አገር የመንቀሳቀስ መብት በመጣስ የየመን መንግስት ለወያኔው ማስረከቡ አጥብቀን የምናወግዘውና የምንቃወመው ሲሆን ድርጅታችን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በደረሰው አፈና መሰረት በማድረግ ማንኛውንም አይነት እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን አበክረን እናስታውቅለን።

ለአገርና ለወገን ዕድገት ብልጽግና ሲሉ በመታገላቸው ሳቢያ የየመን መንግስት እሳቸውን አፍኖ በማስረከቡ ምክንያት አገር ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ትግል ለአንድም ደቂቃ ቢሆን የሚገታው አለመሆኑን እብሪተኛው ቡድን ሊረዳው ይገባል።

በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በደረሰው የተቀነባበረ አፈና ዛሬ ላይ መግለጫ የማውጣታችን ምክንያት ጉዳዩ እስኪረጋገጥ በሚል እንጂ ቀደም ባሉት ቀናቶች መግለጫ ማውጣት ይጠበቅብን እንደነበረ እናምናለን ስለሆነም መላው የአገራችን ለውጥ ናፋቂ ወገናችን ሁሉ ይሄንኑ ሃሳባችንን በቅጡ እንዲረዳልን እናስገነዝባለን።

እንደ አንድ ታጋይና አታጋይ እሳቸውን በተቃውሞ ትግል ማጣታችን ቃላት ሊገልጸው ከሚችለው በላይ በውስጣችን ቁጣን ፈጥሯል ። አገዛዙ አቶ አንዳርጋቸውን ከየመን መንግስት መረከቡ ለውጥ ናፋቂው ሕዝብ በፍርሃት ተሸብቦ ለትግል እንዳይነሳሳና ማንኛውም ተቃዋሚ የትም ሄደ የትም ከገባበት ገብተን በእጃችን ለማስገባት የሚያስችለን የዲፕሎማሲ ግንኙነት አለን በሚል ስጋት ለመፍጠር የተሰራ ቀመር ስለመሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም ።

Friday, July 4, 2014

ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግል አይሞትም!!!


ጆሴፍ ስታሊን ስልጣኔን ይቀማኛል፣ ወንበር አሳጥቶ ያሳንሰኛል ብሎ ጥምድ አድርጎ የያዘዉን አስተዋዩን ምሁር ፣ማርክሳዊ አብዮተኛ ፣የንድፈ ሃሳብ ወጣኝ፣ የቀዩ ጦር መስራችና መሪ የነበረዉን ድንቁን ሌዮን ትሮትስኪይን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት እንደእብድ ተነሳስቶ እግር በእግር እየተከታተለ ከሞስኮ አንስቶ ካዛኪስታን ፣ቱርክ፣ፈረንሳይ ፣ኖርዌይ ኦስሎ ድረስ ሌት ከቀን አሳደደው ።በመጨረሻም የፖለቲካ ጥገኝነት ተሰጥቶት እሚኖርበት ሜክሲኮ ድረስ ገዳዮች አሰማርቶ ጥይት በማርከፍከፍ ቤቱን አስነዳድሎ ኢላማው ባይሰምርለት፣ የስፓኝ ተወላጅ በሆነ ቅጥረኛ በበረዶ መፈቅፈቂያ መሮ አናቱን አስጨቅጭቆ በማስገደል ለፍፃሜ አበቃው ።ቤተሰቦቹንም በተናጥል አድኖ ድራሻቸዉን አጠፋቸው ።

የወያኔ አገዛዝም በሳሉን የፖለቲካ ሰው ፣የነፃነት ታጋዩን ፣አስተዋዩንና ቆራጡን አንዳርጋቸው ፅጌን እንዲሁ ሃብቱን ጠርጎ ወርሶ፣ቤተሰቦቹን ሁሉ አስሮ በዘግናኝ ሁኔታ አሰቃይቶ፣የሰማንያ ዓመት አዛዉንት አባቱን በስተርጅና በማረፊያ በመጦሪያ ጊዜያቸው አዋክቦ አስሮ አንገላቶ ፣በኢሰብአዊ መንገድ ወንድሙን አስሮ አሰቃይቶ አካሉንም አጉድሎ ወህኒ የዘላለም ቤቱ እንዲሆን ፈረደበት ። አንዳርጋቸዉን ወህኒ ለሁለት አመታት አግቶ፣መግቢያና መዉጫ አሳጥቶ ከሀገር አባሮ፣ ኤርትራ በረሃዎች ድረስ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች አስታጥቆ ልኮ ነፍሱን ሲጥ ለማድረግ ያቀደው እቅድ ባይሳካለት ፣ አድብቶና አስልቶ የመን ላይ ትራንዚት ሲያደርግ አሳፍኖ ወደ አዲስ አበባ ወስዶታል ።

አዎ አንዳርጋቸው በወያኔ ፍትህ አልባ ፍርድቤት ፍርደገምድል ችሎት በሌለበት ሞት የተፈረደበት ሰው ነው ። አንዳርጋቸዉ ጭራቆቹ እጅ ገብቶ የሚጠብቀዉን ግርፊያ፣ስቃይ ለመገመት ነቢይ መሆን አያሻም ።ወያኔ ያልተረዳው ነገር ቢኖር፣ይህ ትግሉን እንደሰደድ እሳት ዳር እስከዳር ያቀጣጥለዋል እንጂ አያበርደዉም።ያፋፍመዋል እንጂ አያከስመዉም።

የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለወያኔ ፋሽስቶች አሳልፋ መስጠቷን በማስመልከት የወጣ መግለጫ



የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለወያኔ ፋሽስቶች አሳልፋ መስጠቷን በማስመልከት የወጣ መግለጫ 

ሰኔ 27 ቀን 2006 ዓ.ም

የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቶ መቆየቱ ማስታወቃችን ይታወሳል።

የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቄዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል። በዚህም ሳቢያ የየመን መንግሥት ይቅርታ የማያሰጥ፤ ዘመን የማይሽረው ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወዳጅ ጎረቤት ትሁትና ቀና ቢሆንም ጥቃት በሚያደርስበት የቅርብም ሆነ የሩቅ ጎረቤት ላይ ግን ቁጣውን የሚመጥን የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ያውቅበታል።

የወያኔ ፋሽስቶች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማሰቃየት ትግላችንን ማቀዝቀዝ እንደማይችሉ ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን። እንዲያውም በግልባጩ ቁጣና እልሃችን በእጥፍ ድርብ በመጨመር ትግላችንን ያጦዘዋል። ወያኔ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በውንብድና ጠልፎ መውሰዱ የትግሉን ሜዳ አስፍቶታል፤ የትግሉንም ዓይነት አብዝቶታል። ይህ ደግሞ የወያኔ ፋሽስቶችን ከፍ ያለ ዋጋ ያስከፍላቸዋል።

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ህገ ወጥ እገታ ከተሰማ ዕለት ጀምሮ የፓለቲካ ልዩነት አጥር ሆኖ ሳይከልላችሁ ከጎናችን ለቆማችሁ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማኅበራትና ዜጎች ሁሉ ምሥጋናችንን እናቀርባለን። በወገናዊ ተግባራችሁ ልባችን ተነክቷል። ከዚህ በላይ ደግሞ ለቀጣዩ ወሳኝ ፍልሚያም እንደምንቆም እና የወያኔን እድሜ እንደምናሳጥር እምነታችን አጠንክሮልናል።

ከዛሬ ጀምሮ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንዳርጋቸው ጽጌን ሆኗል። ዛሬ ዘጠና ሚሊዮን አንዳርጋቸው ጽጌዎች በአንድነት ተነስተዋል። በአንድ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የደረሰው ጥቃት ሰበብ ሆኖ የተቀሰቀሰው የሕዝብ ቁጣ የወያኔ ፋሽስቶችን ይጠራርጋል። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ለደረሰውና ለሚደርሰው ጥቃት እያንዳንዱ የወያኔ ሹም በግል ዋጋ ይከፍላል። ከእንግዲህ በምሬት የተነሳሳው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂው ራሱ ወያኔ መሆኑን እውን ሆኗል። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስር የክተት አዋጅ ታውጇል። ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለሀገር፣ ለእኩልነት ግድ ያለህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተነስ!!!

በመስዋዕትነት ድልን እንቀዳጃለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Thursday, July 3, 2014

አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም!!! የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል መግለጫ

በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከታዩ አርቆ አሳቢ፣ አስተዋይና ብልህ ፖለቲከኞች አንዱ የሆነው ታላቁ የነፃነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለሥራ ጉዳይ ሲንቀሳቀስ የመንን እንደመሸጋገሪያ በሚጠቀምበት ወቅት በሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. በየመን ሰንዓ ከተማ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በሀገሪቱ መንግሥት ትዕዛዝ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል:: ምንም አይነት ምድራዊም ይሁን ሰማያዊ መነሻ ምክንያት ለአቶ አንዳርጋቸው በየመን መንግሥት መታገት እና መታሰር ምክንያት ሊሆን እንደማይችል እንደማይገባም በመግለጽ የየመን መንግሥት የነፃነት ታጋያችንን ባስቸኳይ እንዲለቅ ላለፉት ተከታታይ ቀናት የተደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ውጤት አላስገኘም:: ከዚህም በመነሳት አቶ አንዳርጋቸው ለዘረኛው እና ከፋፋዩ የወያኔ ቡድን ሊሰጥ ይችላል የሚለው ስጋታችን ቀን በገፋ እና ምላሽ በራቀ  ቁጥር እየጨመረ መጥቷል::

በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል በኩል የነፃነት ታጋዩ ለወያኔ ተላልፎ መሰጠቱን መቶ በመቶ እስከምናረጋግጥበት ቅጽበት ታጋዩን የማስለቀቅ ጥረቱ መቀጠል እንዳለበት በጽኑ እናምናለን:: አንዳርጋቸውን ማሰር ይቻላል፤ ምናልባትም በዚህ ቅጽበት ተችሏል፤አንዳርጋቸውን ማሰቃየት ይቻላል፤ ምናልባትም በዚህ ቅጽበት ተችሏል፤ አንዳርጋቸውን መግደል ይቻላል። ሞትን ፈርቶ ወደ ትግል አልገባምና አንዳርጋቸውን በማሰር የአንዳርጋቸውን እንደ እቶን የሚያቃጥል የፍትህ፣ የነፃነት፣ የዴሞክራሲና የእኩልነት መንፈስ ግን ለሴኮንዶች እንኳን ማሰር አይቻልም። አንዳርጋቸውን በማሰቃየት ያን ዘመን ተሻጋሪ የሆነ የትውልዱን መንፈስ የሚገዛ የሁላችንም የምትሆን የጋራ ኢትዮጵያን የመፍጠር ንጹህ ራዕዩን ግን ፈጽሞ ማቁሰል አይቻልም!!! አንዳርጋቸውን በመግደል ዕንቁ ዓላማውን መግደል ከቶ አይቻልም፤ የታሪክ መዛግብት ገጾች ለዚህ ሃቅ በሚመሰክሩ እውነታዎች የተሞላ ነውና። አንዳርጋቸውን በመግደል “ከአባቶቹ የማይበልጥ ትውልድ እንዳልተፈጠረ  ይቆጠራል፣ ልጅ አባቱን ሩጦ መቅደም አለበት፣ ስለዚህ እናንተ ወጣቶች እኛን ሩጡ እና ብለጡ ቅደሙን፣ ቀናዎች ሁኑ፣ ርስ በርስ ተዋደዱ፣ ያለፉት ትውልዶች የሰሩትን ስህተት ላለመድገም ታሪክን ከስሩ ተረዱ፣ ያለማወቅ ጠንቅ ከሚያመጣው ጥፋት ለመዳን ሁሌም ለእውቀት ጉጉዎች ሁኑ። ለማወቅ ጣሩ፣ የማይቀረው ሞታችሁ ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲ እና  ለነፃ ኢትዮጵያ ይሁን” እያለ ላለፉት በርካታ አመታት ያስተማራቸው እና የኮተኮታቸው የነፃነት ታጋይ አርበኛ  ወጣቶችን እና እሳት መንፈሳቸውን መግደል አይቻልም::

Letter to Yemeni Presidnt on the Detention of Andargachew Tsege, Secretary General of Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy




June 30, 2014

H.E. Field Marshall Abdu Rabu Mansour Hadi

President,

Republic of Yemen

Sana’a, Yemen

Your Excellency:

Re: Yemeni: Detention of Andargachew Tsege, Secretary General of Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy

We are writing to express our grave concerns regarding the unlawful and unwarranted detention of Andargachew Tsege, Secretary General of Ginbot 7 Movement for Justice Freedom and Democracy while in transit at Sanaa International Airport on June 23, 2014.

We are particularly concerned that the continued illegal detention of Mr. Tsege, a renowned critic of the Ethiopian government is politically motivated and against international law.

We urge the Government of Yemen to release him immediately and unconditionally.

Mr. Tsege a well-known pro-democracy and human rights advocate in his ancestral homeland, Ethiopia, presents no threat to Yemen or to the Yemeni authorities.

Mr. Tsege was imprisoned in Ethiopia for his political activities during the ill-fated election of 2005 and has escaped assassination attempts by the dictatorship whose brutality, is well documented even by the United States State Department.