Thursday, April 30, 2015

ኤዶምንና ማህሌትን ብቻ ሳይሆን የ45 ሚሊዮን ሴቶች ክብርን ነው ያቀለሉት

 በግርማ ካሳ

ኤዶም ካሳዬ ጋዜጠኛ ናት። ማህሌት ፈንታሁን ደግሞ «ሰለሚያገባን እንጦምራለን» በሚል የአለም አቀፍም ሆነ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በሚፈቅድላቸው መሰረት፣ ብሎግ ከሚያደርጉ ዞን ዘጠኞች አንዷ ናት። ኤዴሞም ሆነ ማህሌት የጻፉት፣ የተናገሩት የተደበቀም ሆነ የተሸፈነ ነገር የለም። ለፍትህ ከመቆማቸው በቀር ያጠፉት ጥፋት የለም። ወንጀላቸው አገራቸውን መዉደዳቸው ነው። ሆኖም ሕወሃት «ሽብርተኞች» ብሎ ካሰራቸው ይኸው አንድ አመት ሆናቸው። ቢያንስ ከ27 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ተመላልሰዋል። አስቡት በአንድ አመት ዉስጥ ቢያንስ 27 ጊዜ !!!!!

የአገሪቷ ሕገ መንግስት በማረሚያ ቤት ያሉ እስረኞች በምን መልኩ መያዝ እንዳለባቸው በግልጽ አስቀምጧል። በአንቀጽ 19 ንኡስ አንቀጽ አንድ ላይ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ፣ እስረኞችን ጨምሮ፣ ኢሰብአዊ ፣ ጭካኔ የተሞላባቸዉና ክብርን የሚነኩ ቅጣቶች ሊቀበል እንደማይገባ ያስቀምጣል። ሆኖም ረእቡ ሚያዚያ 14 ቀን፣ የአዲስ አበባ ሰልፈኞች እንዳሉት፣ ለሕወሃት ሕገ መንግስቱ ወረቀት ብቻ ነው። እህቶቻችን ሞራላዊ፣ መንፈሳዊና የሴትነት ክብራቸውን በመድፈር ፣ ራቁታቸውን ሆነው በአረመኔ የሕወሃት ወንድ ምናምንቴዎች ፊት ስፖርት እንዲሰሩ መገደዳቸው ምን ያህል እንደ አገር መዝቀጣችንን የሚያሳይ ነው። በርግጥ ኤዶምና ማህሌትን ብቻ ሳይሆን ሕወሃቶች ከ40 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን የአገራችንን እናቶችና እህቶች ነው የደፈሩት።

ለሰብአዊ መብት ጉባኤ ኮሚሽን፣ ኤዶም ላሳዬና ማህሌት ፋንታሁን ከተናገሩት የተወሰነውን እንሆ፡

«ሙሉ ልብሴን እንዳወልቅ ተገድጄ ራቄቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፓርት አንድሰራ እገደድ ነበር ፡፡ “ሴትነትሽ አንዲህ ከሚዋረድ አመጽ እንዳነሳሳሽ እመኚ ተብያሁ”» ማህሌት ፋንታሁን

«በተለምዶው ከምመረመርበት ቢሮ ውጩ አንደኛ ፎቅ አዳራሽ ውስጥ ለምርመራ ተወስጄ ልብሴን እንዳወልቅ እና የተለያዬ ለመናገር የሚከብዱ ስፓርታዊ አንቅስቃሴዎችን እንድሰራ ተገድጃለሁ፡፡ እንዲህ ከምትዋረጂ አመጽ ልናስነሳ ነበር ብለሽ ለምን አታምኚም እያለ ይመታኝ ነበር » ኤዶም ካሳዬ

እንግዲህ የዛሬይቱ የሕወሃት ኢትዮጵያ ይች ናት። ይህ አይነቱን ኢሰብዊነት ማስቆም ካልቻልን እንደ አገር ሆነ እንደ ሕዝብ መቀጥል አንችልም። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፣ ይህ አይነቱ ብሄራዊ ዉርድት እንዲቆም መነሳት አለበት። ፈረንጆችን እንደሚሉት “We have to claim back our country from these monsters” ። በተለይም እናቶችና እህቶች ፣ አዉቃለሁ ብዙ ግርግር አትወዱም። ግን አሁን እናንተም ከወንዱ ባልተናነሰ የምትነሱበት ጊዜ ነው።

በኮምፒተር የኤሌትሪክ ገመድ የሚገርፍ አገዛዝ - ግርማ ካሳ


የኢትዮጵያ መንግስት ለሕግ የሚቆረቆር መንግስት እንደሆነ ብዙ ጊዜ ሲናገር ይደመጣል። የተባበሩት መንግስታት አባል ድርጅት እንደመሆኗም፣ ኢትዮጵያ፣ የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶችን ድንጋጌን የማክበር ግዴታ አለባት። እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ1976 የተደረገው፣ ቃልኪዳን ለሰብአዊና ፖለቲካ መብቶች ፣ The International Covenant on Civil and Political Rights (ICCPR) ዉል/ስምምንት ፈራሚ አገር ናት።

የ ICCPR ዉል አንቀጽ ሰባት እንዲሁም የተባበሩት መንግስት የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀጽ አምስት፣ በግልጽ እንዳስቀመጡት ፣ ማን ሰው በአካሉ ላይ ድብደባ፣ ጉዳት፣ ቶርቸርና ክብሩ የሚነኩ ተግባራት ሊፈጸሙበት እንደማይገባ ይደነግጋሉ። «No one shall be subjected to torture or to cruel, inhuman or degrading treatment or punishment» ይላሉ አንቀጾቹ።

በአገራችን ኢትዮጵያ ወዳሉት ሕጎች ስንመጣ ደግሞ፣ የሕጎች ሁሉ የበላይ ሕግ መንግስቱ እንጂ ከጥቂት የሕወሃት የደህንነት አባላት የሚመጣ መመሪያ እንዳለሆነ በግልጽ ተቀምጧል። የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 21 « በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰባአዊ ክብራቸውን በሚተበቁ ሁኔታዎች የመያዝ መብት አላቸው» ይላል።

ሆኖም በተለያዩ ጊዜያት ተቃዋሞ የሚያሰሙ ወገኖች ሕግ መንግስቱ ወረቀት ብቻ እንደሚሉት፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ለአገሪቷ ሕግ ደንታ እንደሌለው፣ የአለም አቀፍ ሕግጋቶችን የሚጥስ ፣ አደገኛው አሸባሪና የሕግ አፍራሽ እንደሆነ በግልጽ እያሳየ ነው።
ለሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ለሚባል ድርጅት ፣በማእከላዊ እሥር ቤት ስለደረሰባቸው ሁኔታ ዞን ዘጠኞች የተናገሩትን ላነበበ፣ በርግጥም ምን ያህል አገራችን በሕግ የማትተዳደር እንደሆነ መደምደም አያቅተውም።

«ከወንበሬ አንድነሳ አዘዙኝ፡። ከዚያም በቆምኩበት ግራ ብብቴን እና እጄን በአንድ እጁ አንዳልወድቅ ወጥሮ ይዞ በእግሩ ጭኔን በሃይል ደበደበኝ። ከድብደባው በማስከተል ደግሞ እግሬ መሃል እግሩን በማስገባት ወደግራ እና ወደቀኝ በመምታት ተዘርጥጬ እንድቆይ በማድረግ እጄን ወደላይ አድርጌ እግሬ ግራና ቀኝ ተዘርጥጦ ( በተለምዶ ስፕሊት በሚባለው) በግራ እና ከቀኝ በመደብደብ እጄን ወደላይ አድርጌ እነድመረመር ተደርጌያለሁ። ከዚህ ምርመራ በኋላ ለሁለት ቀን እያነከሰኩ ነበር» ሲል ነበር በፋቃዱ ሃይሎ ሰቆቃዉን የገለጸው።

አቤል ዋበላ በተራው የደረሰበትን ግፍ ሲያስረዳ «ድብደባውም ጨለማ ክፍል ውስጥ በማስገባት አፌ ውስጥ ካልሲ በመወተፍ እግሮቼን ከላይ፣ ውስጥ እግሬን እና ከውስጥ ባቴን ታፋዬን እንዲሁም ጀርባዬን በእንጨትና በኮምፒውተር ገመድ ገርፈውኛል። የምርመራ ክፍሉ ወለል ላይ በደረቴ አንዲሁም በጀርባዬ እያገላበጡ በማስተኛት መላ ሰውነቴን ረግጠው ተራምደውብኛል፡። አፌን ሳይቀር ረግጠውታል» ነበር ያለው።

Sunday, April 26, 2015

ሽብርን በማሸበር!! ሰማያዊ ፓርቲ “ሊታረድ ነው”

* ሕዝብ ዋስትናና መተማመን አጥቷል

ረቡዕ ዕለት ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ዜጎች ስሜታቸውን ሲያንጸባርቁ የተሰጣቸው ምላሽ ሽብርን በአሸባሪነት አመጣጥኖ የመመለስ አይነት እንደሆነ ተጠቆመ፡፡ የሰላማዊ ሰልፉ አጠቃላይ ገጽታና የሕዝብ ስሜት በአገሪቱ የዋስትና ማጣት ስሜት እየገዘፈ መሄዱን የሚያሳይ ሆኗል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሊታረድ ነው፤ በሰሜን አሜሪካ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ባሉት ይልቃል ላይ እዚያው እንዲቀሩ ተጽዕኖ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በአይሲስ የታረዱትና የተረሸኑትን “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያጣራሁ ነኝ” ሲል የነበረው ኢህአዴግ እንዴት እንዳጣራ ለሕዝብ ባያሳውቅም ወዲያው ሕዝባዊ ለመሆን በመመኘት በአገሪቷ ላይ የሐዘን ቀን ከማወጅ በተጨማሪ ሕዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጣ ጥሪ አድርጎ ነበር፡፡ አንድ የጎልጉል አስተያየት ሰጪ “ሕዝቡ ለ24 ዓመታት በሐዘን ላይ ነው ሦስት ቀንማ ምን አላት” በማለት እንደተሳለቁት የተሰጠውን ትዕዛዝ ተከትሎ ሕዝቡ ገና ከጠዋቱ ጀምሮ ተንቀሳቅሷል፡፡ በየቦታው የኢህአዴግ ካድሬዎችና ፖሊሶች መሰለፍ የሚገባውን ከማይገባው ለመለየት ሙከራ ቢያደርጉም በእጅጉም አልተሳካላቸውም፡፡

ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ ከሕዝቡ በተጨማሪ ኢህአዴግ የደፈነባቸውን የፖለቲካ ምህዳር በራሳቸው እያሰፉ የሚንቀሳቀሱት ጥቂት የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ድጋፍ ሰጥተውታል፡፡ መድረክ እና ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን እንደሚያከብሩ ድጋፍም እንደሚሰጡ በይፋ ባወጡት መግለጫዎች አስታውቀው ነበር፡፡ ይህም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚደረገውን ሽብር የሚቃወሙ መሆናቸውን ለሚያሸብራቸው ኢህአዴግ በአገራዊ አጀንዳ ላይ አብረው እንደሚቆሙ ኅብረት ያሳዩበት እንደሆነ በብዙዎች ተስተውሏል፡፡
ይሁን እንጂ ሰልፉ ኢህአዴግ ቀደም ሲል በቀላጤው ሬድዋን አማካኝነት የሞቱት “ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው” ዕውቅና ነፍጎ በሰጠው መግለጫ የተቆጣው ሕዝብ የሰልፉን ዓላማ ኢህአዴግ ከተመኘውና ከፈለገው ውጪ አድርጎታል፡፡

ከለቅሶ ቤት ጀምሮ “መንግሥትን አንፈልግም” በማለት ቁጣ የተሰነዘረ ሲሆን አብዛኞች ግን “መንግሥት የለንም” ሲሉ ድርብ ሃዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

ገዳዩ ባለካራው አሸባሪ ድርጅት ለፈጸመው ወንጀል ይሉኝታ ሳይዘው እንደ ታላቅ ገድል በቪዲዮ አስደግፎ ሲያቅራራ ዓለም ምስሉን ባደባባይ አይቷል፡፡ ሚዲያዎችም ተቀባብለውታል፤ መንግሥት ነን ብለው የተቀመጡት እነሬድዋን እንደ አንድ ሰው ሚዲያዎችን ተከታትለው መረጃውን አግኝተውታል፡፡

በኢህአዴግ ቋንቋ “ህገወጥ” የሚባሉት ሥራ ፈላጊዎች ድንበር አቋርጠው ሲወጡ ህጋዊ የጉዞ ሰነድ የላቸውም፡፡ ኢህአዴግ በሊቢያ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት የለውም፡፡ አፈቀላጤውና “የፌስቡኩ ሚ/ር” ዶሮ እንኳን የሞተች ሳይመስላቸው “እውነት ኢትዮጵያውያን ሞተው እንደሆነ እናጣራለን” በማለት የተናገሩት ከካራም በላይ የሕዝብን ስሜት ያረደ ስለመሆኑ አብዛኞች ይስማማሉ፡፡ የረቡዕ ተቃውሞና ቁጣም ብዙ የተከማቹ መነሻዎች ቢኖሩትም አስኳሉ ጉዳይ ግን ክህደቱ እንደሆነ ይታመናል፡፡

“ያገር አንበሳ የውጭ ሬሳ”፣
“እግዚአብሔር ነው ለእኛ ኃይላችን አንመካም በጉልበታችን”፣
“ደማችን ይመለስ፣ ይታፈስ”፣
“አቤት ቆሻሻ”፣
“አይሲስ በካራ እናንተ በዱላ”፣
“አትመጣም ወይ መንጌ አትመጣም ወይ”፣ …

”ያዋረደን፣ በአይ ሲስ ቢላዋ ያሳረደን ህወሓት ነው” – ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረቡት አስቸኳይ ጥሪ-

የተከበራችሁ ወገኖቼ፤ ከሰላሳ በላይ የሆኑ ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ከትናንት ወዲያ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ደርሶን ኢትዮጵያዊያን በያለንበት በመሪር ሀዘን ውስጥ ነን። ዛሬ “እግዜር ያጥናህ” ወይም “እግዜር ያጥናሽ” የሚባል ሰው የለም። ሁላችንም ሀዘንተኞች ነን። ካጣናቸው ቁጥራቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ወገኖቻችን አሁንም በአራዶች መዳፍ ውስጥ መሆናቸው ሀዘናችን እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ሆኖም በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ሊቢያ ውስጥ ናቸው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ናቸው። ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ደግሞ በየመን ከሰማይም ከምድርም በቦንብና በጥይት እየተማገዱ ነው።

ለምንድነው ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እሳት ውስጥ ለመማገድ የምንደፍረው? መልሱ ግልጽ ነው። አገር ውስጥ ተስፋ የለም፤ ወያኔዎች ተስፋችንን አጨለሙት። ከሳዉዲ በመከራ የተመለሱ ወንድሞቻችን ናቸው በሊቢያ በኩል ለመሰደድ ሲሞክሩ በአይ ሲስ ተይዘው የታረዱት። ወያኔዎች አገራችንና ክብራችን ዘረፉን። ወያኔዎች ስብዕናችንን ገፈፉን።

የዘመኑ ጥቂት የህወሓት ቱጃሮች ፎቆችን እየገነቡ በነሱ መጥገብ እኛ እንድናገሳላቸው ይፈልጋሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ መራቡ፣ መታረዙ፣ መደህየቱ እውነት ነው፤ ሆኖም ግን “ተራብኩ”፣ “ታረዝኩ”፣ “ደኸየሁ” ብሎ መናገር አይችልም። እውነት መናገር ያስቀጣል፣ ያስወነጅላል። በፍርደ ገምድል ችሎት እውነት መናገር “ሽብርተኛ” ያስብላል። እስር ቤቶችን የተሞሉት ለእውነት፣ ለፍትህ፣ ለነፃናትና ለእኩልነት በቆሙ ሰዎች አይደለምን?

በአይ ሲስ ያሳረደን ማነው? መልሱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ ነው። ያዋረደን፣ በአይ ሲስ ቢላዋ ያሳረደን ህወሓት ነው። እንደ አገርና እንደ ሕዝብ የደረሰብን ውርደት የትም ብንሄድ የምናመልጠው አልሆነም። በአገር ውስጥ የደረሰብንን ውርደት ለማምለጥ ስንሰደድ ውርደት ተከትሎን ይመጣል።

ወገኖቼ፤ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለች አገር ሊኖረን አይችልም። ዛሬ የመሸሻ ጊዜ አይደለም። አገራችንን ከወያኔ ነጥቀን፤ በአገራችን ኮርተን በሰላም መኖር እንሻለን። ይህ መብታችን ነው። አገራችን የኛ ነች። አገራችን የጥቂት ወያኔዎች መፈንጫ አይደለችም።

ወገኔ፤ ዛሬ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም በአርበኖች ግንቦት 7 ስም የማደርግልህ ጥሪ አድምጠኝ። በሀይማኖት፣ በብሔር፣ በጾታ ልዩነት ሳታደርግ ዛሬ በአንድነት እንደተሳህ አንድነትህን እንደጠበቅህ ቀጥል። አንድነትህን ለመሸርሸር ወያኔ የማይፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም፤ ለወያኔ ዱለታ ጆሮህን አትስጥ። የወያኔ አገዛዝ እንዲያበቃ በአንድነት ተነስ። ዛሬ የጀመርከው ትግል እዳር ሳይደርስ እረፍት የለንም።

Monday, April 20, 2015

በግፍ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን በተመለከተ የአርበኖች ግንቦት 7 መግለጫ

ሀያ ስምንት ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ዛሬ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደርሷል። ይህ አሰቃቂ መርዶ ልብን የሚሰብር ነው። አይ ሲስ በጥንት በጭለማ ዘመን እንኳን ባልነበረ ጭካኔ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሰዎችን በማረድ የሚደሰት፤ በሰው ዘር ሁሉ ላይ የመጣ አውሬ መሆኑን ነብዩ መሐመድ አትድረሱባቸው ያሏቸውንም ኢትዮጵያዊያንን ጭምር በማረድ አረጋገጧል። ይህ አሰቃቂ ተግባር ምንም ዓይነት አመክኖ ሊቀርብለት የማይችል አረመኔዓዊ የሽብር ጥቃት ነው።

አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው አሰቃቂ ግድያ  የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፤ ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል። ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አይ ሲስን በጥብቅ እንዲያወግዙ፤ በአመቻቸው መንገዶች ሁሉ እንዲታገሉት አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል።

በዚህ አጋጣሚ የአይሲስን የሽብር ተግባራት ከእስልምና እምነት ጋር ማያያዝ ፈጽሞ ትክክል እንዳልሆነ፤ ብዙሃን ሙስሊሞች የአይሲስና መሰል ቡድኖችን አካሄድ የሚቃመው መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ማስገንዘብ ይሻል። ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር ተዋደውና ተፋቅረው የኖሩና እየኖሩ ያሉ ሲሆን የሁለቱ ሀይማኖቶች ተከታዮች ተደጋግፎ መኖር ለሀገራችን ህልውና ወሳኝ  ጉዳይ መሆኑ የአርበኞች ግንቦት 7 እምነት ነው።

በያዝነው ሣምንት በወገኖቻችን ላይ እልቂት ሲደርስ የሊቢያ ብቸኛ ክስተት አይደለም። በደቡብ አፍሪቃ ወገኖታችን ከነሕይወታቸው በእሳት ተቃጥለው ተገድለዋል፤ በስለት ተዘልዝለዋል፤ ንብረታቸውን ተዘርፈዋል። በዛሬው ዕለት 700 ዜጎች የሜዲተራኒያን ባህር በጀልባዎች ሲሻገሩ መስመጣቸው ተሰምቷል። በየመን ደግሞ በርካታ ወገኖታችን በጦርነት እሳት ውስጥ እየተማገዱ ናቸው።

ኢትዮጵያዊያን በአገራችን የሰፈነውን የነፃነት እጦት፣ የፍትህ መጓደልና የኑሮ መክበድ ሸሽተን በሄድነት አገር ሁሉ የሚጠብቀን አሰቃቂ ሞትና ውርደት ሆኗል። ኢትዮጵያ ለኑሮ ያልተመቸችን በህወሓት አገዛዝ ብሉሽነት መሆኑ ጥርጥር የለውም። ይህንን ብልሹ አገዛዝ አስወግደን በምንወዳት አገራችን ተከብረን መኖር እንችላለን። ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለም።

Sunday, April 19, 2015

እግዚያብሄር አንድ ሊያደርገን ይሆን ይህን ሁሉ ሰቆቃ የሚያሳየን?


አንድ ወቅት ፕሮፌሰር መስፍን “የኢትዮጵያውያን እንባ ከመብዛቱ ሰማይን እራሱ አደፍርሶታል (አጨቅይቶታል )” ብለው ነበር ::

ዛሬም ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ከአንረ ዘር ከመጡ ጎጠኞች የሚደርስባቸው ስቃይ እና መከራ እንግልት ግድያ አልፎ መሄጃ አጥቶ ለግዜውም መጠግያ ይሆነኛል ለግዜውም ሆነ ለዘለቄታው ብሎ በስደት ከከተመበት አፍሬካ ሀገራት እስከ ቃረብ ሀገራት ዛሬም እንደ ትናቱ በኢትዮጵያውያን እንባ እና ደም እንደተሞላ ነው::South Africa

ከጥቂት ግዚያት ጀምሮ ደግሞ ዘግኛኝ ነው ስለ ኢትዮጵያውያን የሚሰማው የሚታየው የሚነገረው ኬንያ በህገወጥ ገቡብኝ ያለቻቸውን እኢትዬጵያውያን አሰረች ….አንጎላ ….ዝምባቡዬ ፍርዳቸውን ሲጨርሱ ወደ ሀገራቸው እመልሳለው አለች ከዛ የከፋው ደግሞ የኢትዮጵያውያን ኦርጋን በየመን ዘላኖች እየተቀደደ ይሸጣል የደፈራል ብሎ አልጀዚራ በድምጽ እና በምስል አስደግፎ አሳይቶናል እንደወሻም ታስረው ቀጣይ እጣቸውን የሚጠብቁ እትዮጵያውያንን አስይቶናል :: ይሄ አይተንአይናችን ደፍርሶ እስከ መቼ እንደዚ ብለን ሳንቸርስ ሰብሳቢ የለሌ ህዝብ እና ደራሽ የለው ምስኪን በሳውዲ መንገዶች እየታረደ ደሙ ሲፈስ እህቶቻችችን እየደፈሩ ተቃጥለው በየ ቆሻሻው ገንዳው ሲጣሉ እስር ቤቱ ሲታጎሩሩ በታሰሩበት እስር ቤት ሲደፈሩ ድረሱልን ብለው ኡ ኡ ኡ ብለው ድምጻቸውን ሲያሰሙ ድማቸውን የሚሰማ እንባቸውን የሚያብስ ሳይሆን በስልክ እርዳታ የምትፈልጉ ደወሉልን እያሉ የሚያላግጡ ዘረኞች ኢትዮጵያን እየመራን ነው ብለው ሲናገሩ የከረፉኛ ::

ሰብሳቢ እና መሬ የሌው ህዝብ ዛሬም በየመን እንግልት እና መከራ እየደረሰበት ከዛሬ ነገ ምን ይገጥመኝ ይሆን እያለ በሰቆቃ እያሳለፈ ነው እንደ መንግስት ምንም የተደረገለት ነገር የሌው ኢትዮጵያዊ እነ ሱዳን እነ ኤርትራ ኬንያ ሱማልያ ያደረጉትን 0000000.1% እነኩዋን ለማረግ ፍላጎትም ሞራልም የለው ኢትዮጵያን እየመሩ ኢትዮጵያን የሚጠሉ የበዘር ስካር በሽተኞች ናቸው እና በስደት ያለ ኢትዮጵያዊ ግን ወገን ለወገን ደራሽ ነው እና የተቻለውን በሚችለው መንገድ ጥረቱን እያድረገ ነው ከሰልፍ እስከ ኢኮነሚ እርዳታ እና ጥበቃ ከለላ የሚያገኝኡበትን አካባቢ ወይም ሀገር ፍለጋ እላይ እታች እያለ ባለበት ወቅት ሌላ መካራ ሌላ ስቃይ ሌላ የድረሱልን ጥሬ………..

አቀንቃኙ አረ አይነጋም ወይ ኢትዮጵያዬ ያለው ያለፈው እና መጪው መከራ ታይቶት የሆን? ትንቢት ነጋሬ የሆነልን ? አዎ ይፈጠራል በለን በአይናችን ይሄን አይነት ለዛውም በጥቁር አፍሬካውያን ወንድሞቻችን የዚ አይነት ግፍ ይፈጸማል ብሎ የሚያስብ አፍሬካዊ አልነበረም እኔ ጨምሮ ይሄን አይነት ስሜት የፈጠረልኝ ከመሬት ተነስቼ አይደለም ትናት በቀኝ ግዛት ያንን አይነት መከራ ሲቀበል እና ሲገደል የነበረ እህቱና እናቱ ልጁ በዘረኛ ነጮች አይኑ እያየ በሀገሩ ስትደፈር እንደ ፌልም እያየ ምንም ማረግ ባለ መቻሉ ደም ያለቀሰ ጥቁር ደቡብ አፍሬካዊ በቤልጀም ብራስልስ እና በሌሎች አውሮፓ ከተሞች እንደ እንስሳ የብረት ሳጥን ተሰርቶለት ከተማ መሀል እጁ ታስሮ ለህዝብ እንዲጎበኝ ሲደረግ የነበረ ህዝብ ያሲደረግበት ይቃወምለት የነበረን ኢትዮጵያዊ በዘረኞች ሲገደል ለም እያለ ከማንን ቀድሞ ይጮህለት የነበረን ኢትዮጵያዊ ዛሬ በዚ ዘመን ታየቶ በማይታወቅ ጭካኔ ሲገድል ሲያሰቃይ ሳይ አነባወ ….. ለዛሬ ነጻነቱ ያበቁትን መሬወቹን በማስተማረ በመርዳት ከዛም አልፎ ኢትዮጵዊ ፓስፓርት በመስጠት ለዛሬ ማንነታቸው ትልቃ አሻራ ያደረገውን ኩሩ እና ጀግኛ ኢትዮጵያዊ ዛሬ ቀን ጥሎት በሀገሩ የመኖር ህልውናው ሲጠፋ ቀን እስኪያልፍ ብሎ ትናት ባለው ነገር የረዳቸው ዛሬ እንደሀገር ከፍ ማለታቸው ሚስጢር ላይ ትልቅ አሻራ ያለውን ኢትዮጵያዊ ሰማ ሰባሬ የሚያካክል ድንጋይ ሲጭኑበት ሳይ ጎማ ውስጥ አስረው ከነ ሂወቱ ሲያቃጥሉት ስመለከት እንደ ስጋቤት ስጋ በቆንጨራ እየበለቱ ሲሰነጥቁት የሚመለከት የሰው ልጅ ምን እንደሚል እኔጃ እንደ ኢትዮጵያዊ ግን እኔ ያንን መከራ እና ግፍ ሲፈጸም ሳይ ቃላትም አቃተኝ አስመረረኝም ::

Friday, April 17, 2015

የእሥርና እንግልት መበራከት የነጻነት ትግሉን ያጠናክራል እንጅ አያዳፍነውም!

በተለያየ ጊዜና ቦታ የሚኖሩ አንባገነን ገዥዎች በሙሉ ከሚመሳሰሉባቸው ባህሪያት አንዱ በሥልጣናቸው የሚመጣባቸውን ተቃወሚ ለማጥፋት በቁጥጥራቸው ሥር የሚገኘውን ማንኛውንም ዓይነት ሃይልና ጉልበት ከመጠቀም ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸው ነው።

የሌላውን አገር ትተን በአገራችን የታየውን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ብቻ ብንመለከት ለወያኔ መፈጠርና ለድል መብቃት ምክንያት የሆነው ደርግ ለሥልጣኑ የሚያሰጉት የመሠሉትን ሁሉ መንጥሮ ለመጣል ከጅምላ እስርና ግርፋት እስከ ጎዳና የሽብር እርምጃ ብዙ ጉዳቶችን አድርሶአል ። አውሮጳና አሜሪካ ድረስ ተጉዘው ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ ቦኋላ ለአገራቸው ባላቸው ፍቅር የመልካም አስተዳደር ጉድለት በምድራችን ያስፈነውን ድህነትና ሃላቀርነት ከሥር መሠረቱ ለመቀየር ተስፋ ሰንገው ራዕይ ሰንቀው የተመለሱ በርካታ ወጣቶች ሳይቀሩ የሥልጣን ተቀናቃኝ ተደርገው እንደቅጠል እንዲረግፉ ተደርገዋል።

ከደርግ እስር፡ ግርፋትና ግዲያ አምልጠው መሳሪያ በማንሳት ደደቢት በረሃ የተሰባሰቡት የዛሬ ገዥዎቻችንና ነባር አባላቱ ምን ያህል ሠላማዊ ሕዝብ ህወሃትን ትደግፋላችሁ እየተባሉ እንደታሠሩ፤ እንደተገረፉ፤ እንደተገደሉና የቁም ስቅላቸውን እንዳዩ አሁን አሁን በምቾት ብዛት ዘንግተውት ካልሆነ በቀር ያኔ ትግል ላይ በነበሩበት ዘመን ነጋ ጠባ ሲያራግቡት የነበረ ጉዳይ ነው። በለስ ቀንቶአቸው የመንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠሩ ቦኋላም በተለይ በመጀመያዎቹ የድል አመታት ታስረው ሰቆቃ የተፈጸመባቸውን በቴለቪዥን መስኮት እያቀረቡ ብሶት ከማናዘዝ አልፈው የሟቾችን አስከሬን እያስቆፈሩ በማውጣት አለም ጉድ እስኪል ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ በእንባ እንዲራጭ አድርገዋል ። ይህንን ድርጊታቸውን የተመለከተ በርካታ ህዝብ ከአሁን ቦኋላ በአገራችን ምድር የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም ሲባል የሚታሠር፤ የሚገረፍ ሰቆቃ የሚፈጸምበትና ለሞት ወይም ለስደት የሚዳረግ አንድም ዜጋ አይኖርም ሲል ተስፋ አደርጎ ነበር።

ደርግ እስከነ ወንጀሉ ወደ ታሪክ ትቢያነት ከተቀየረ ቦኋላ ላለፉት 24 አመታት በዓይናችን እየተመለከትነው ያለው ገሃዱ እውነታ ግን፣ ሕዝብ ተስፋ ያደረገውና የጠበቀው ሳይሆን ግልባጩ ሆኖ በሌላ ዙር የአምባገነንነት የሃይል እርምጃ ሥር ቁም ስቅሉን እያዬ ነው። ድህረ ምርጫ 97 በአዲስ አበባና በሌሎች ትላልቅ ከተሞች አጋዚ በተባለ ልዩ ቅልብ ጦር የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ፤ በጋምቤላ አኝዋኮች ላይ የደረሰው አሳዛኝ የዘር እልቂት፤ በኦጋዴን ሱማሌዎች ላይ ላለፉት አመታት በተከታታይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ፤ በሠላም ከሚኖሩበት የደቡብ ክልል አማርኛ ተናጋሪዎችን ለማፈናቀል የተወሰደው የሃይል እርምጃ ያስከተለው መጠነ ሰፊ ጉዳት ፤ አንድን የህብረተሰብ ክፍል ከተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት ጋር በመፈረጅ በኦሮሚኛ ተናጋሪዎች ላይ የወረደው እስርና እንግልት ብዛት፤ በየማጉሪያው ተወርውረው ያሉት ጋዜጤኞችና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች፤ የፖለቲካ ድርጅቶች አባላት ፤ ደጋፊዎችና መሪዎች ብዛት ወያኔ ከደርግ ያልተናነሰ እንዳውም በአንዳንድ መልኩ የባሰ አምባገነን ሆኖ መውጣቱን የሚያረጋግጡ፣ ማስረጃዎች ናቸው።

በርካታ የትግራይ ወጣቶች ግንባር ቀደም የህይወት መስዕዋትነት የከፈሉበት የእኩልነትና የፍትህ ትግል በጥቂት የህወሃት መሪዎችና የሥልጣን ጥቅም ተካፋዮቻቸው ተቀልብሶ ዜጎች ለነጻነታቸውና ለክብራቸው ሲሉ ወደ ሌላ ዙር ጦርነት እየተገፉ ባለበት በአሁኑ ሰዓት በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶችና ጎልማሶች ተቃዋሚን ትደግፋላችሁ በሚል ጭፍን ውንጀላ ወደ ተለያየ የማጎሪያ ካምፖችና እስር ቤቶች እየተጋዙ ስቃይ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ማየትና መስማት ከማሳዘን አልፎ የሚያስቆጭ ተግባር ሆኖአል ።

Wednesday, April 15, 2015

ህዝባዊ እምቢተኝነት ለነጻነት (የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል)

የኢትዮጵያ ህዝብ እሩብ ምእተ አመት በትከሻው ላይ የተሸከመው የባርነት ቀንበር እየተነቃነቀ ነው። እኛን ያስጨነቀን ደም ጠገቡ የወያኔ ስርዓት ወይስ ሃገራዊ ህላዌ ነው መንኮታኮት ያለበት? በኛ ልብ ውስጥ ከሚነደው የሃገር ፍቅር እሳት ብንነሳ መልሳችን የሚሆነው እየተነቃነቀ ያለው ስርዓቱ ነው ፤የሚንኮታኮተውም የስርዓቱ አራማጅ ህወሃት ነው የሚል መልስ እንሰጣለን። ይህ መልስ ግን ከቀቢጸ ተስፋ ወይም ከነጻነት ጥማት የመነጨ ምኞት ሳይሆን የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታን ተመርኩዘን በየአቅጣጫው ፈነዳሁ ፈነዳሁ የሚለውን ህዝባዊ አመጽ መነሻ በማድረግ ነው።

ባለፉት ፳፬ አመታት በተካሄዱ ፭ ሃገራዊ በሚባሉ ግን ወያኔያዊ በሆኑ ምርጫ ተብዬዎች የተከፈለውን መስዋዕትነት እንጂ የበቀለ የድል ፍሬ ሳናይ ዘመናት አስቆጠርን። ከተመክሮ እንዳየነው ምርጫ ዲሞክራሲን እንደማያመጣ ፤ ዲሞክራሲ እንጂ ፍትሐዊ ምርጫን የሚያመጣ ብለን ብንደመድም የተሳሳትን አይመስለንም፤ፍትሐዊ ምርጫ ይመጣ ዘንድ ወይም ድምጻችን አይሰረቅ በማለት በአካል፣በመንፈስ፣በቁስ፣በህይወት የተከፈሉትን መስዋዕትነት ብናደንቅም በምንም ተዓምር በወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ ካልሆነ በስተቀር ፍትሐዊ ምርጫ ተካሄዶ ህዝብ ያሻውን የሚያወጣበት ሲሻው የሚያወርድበት ስርዓተ መንግስት ይቋቋማል ብለን በፍጹም የህወሃት ስርአት ግፍ እና በደል ከስሩ ካልተነቀለ በስተቀር አናምንም። ዛሬም ለ፭ኛ ግዜ ምርጫ እየተባለ በኢትዮጵያዊያን ላይ ለሚሰራውን ወንጀል አድማቂ በመሆን በተቃዋሚነት ያሉት ዋንኛውን ሚና የሚጫወቱ መሆናቸው መሰመር አለበት።

ያለፈውን ለጊዜው ብንዘለው እንኳን ዛሬ በወህኒ ቤት አስከፊ ሰቆቃ ውስጥ የሚገኙትን በርካታ የነጻነት ታጋዮችን ምርጫ ባልሆነ ምርጫ ውስጥ በመሳተፉ ስቃያቸውን አናባብስ፤ አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት በኛ እምነት ከዚህ ካለቀለት ስርዓት ለመገላገል ከህዝባዊ እንቢተኝነት ሌላ አማራጭ አለ ብለን አናምንም ይህንንም የትግል ተመክሮ ለመቅሰም ብዙ ከህወሃት ጋር መጓዝ አያሻንም፤ ስለዚህ ተቃዋሚ ድርጅቶች ለውጥ ከማያስገኝ ምርጫ በተቻለ ፍጥነት እራሳችሁን በማግለል በህዝባዊ እንቢተኝነት የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማምጣት በሚደረገው ትግል በጋራ በመሆን ትግሉን እንድናጠናክር እናሳስባለን።

Tuesday, April 14, 2015

በአሉቧልታ ማሳ ላይ ቅጥፈት ዘርቶ እያዘመረ ጫን ጫን ውሸት የሚያመርተው መንግስት


በኢትዮጵያችን የመንግስታት ታሪክ ውስጥ በቅጥፈት የወያኔን አገዛዝ ከቶም የሚስተካከለው አይገኝም፡፡ ሲጀመር የስርዓቱ ህዋስ ህወሓት ልክ እንደ አሜባ በሀሰት እግሮቹ እየተራመደ ከደደቢት ወደ ምኒልክ ቤተ መንግስት የመጣ ነው፡፡ ለድፍን 24 ዓመታት ሲጓዝ በባጀባቸው የቅዠት ዓለም ጎዳናዎችና የመንደር ውስጥ መንገዶች ላይም በራሱ እግሮች ሲጓዝ መቸም ቢሆን የተከሰተበት ጊዜ ፈጽሞ የለም፡፡ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደህዴን የሚሰኙ የብሄር ድርጅት ስሞች አሉ፡፡ ነገር ግን በፖለቲካ ስጋና ደም ርዕዮተ ዓለም ጥምረት ቆመው ነብስ የዘሩ አካላት ሳይሆኑ ግዑዛን ናቸው፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ የሚሉት የፖለቲካ ድርጅት የተንዘረፈፈ የሀሰት ሙዝ ዛፍ ነው፡፡ ከላይ የሚታዩት ሰዎችም ቢሆን በገሀዱ አለም ፈልገን ልናገኛቸው የማንችል ቀይ መፅሐፍ ተንተርሰው በማሸለብ ለዘላለሙ አንቀላፍተው በረሀ ላይ የቀሩ ናቸው፡፡ የተዳበለ ስብዕና ባለቤቶች ስለሆኑ እለት ከዕለት የሚፈጽሙትን ስህተት በውል አይረዱትም፡፡

ወያኔ እንደ አንድ የአገር መንግስት ሰይሆን ከአንድ ግለሰብ ያነሰ ተክለ ቁመና ባለቤት ነው፡፡ ወያኔ ራሱን ይዋሻ፤ አባላትና ደጋፊዎቹን ይዋሻል፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ይዋሻል፤ ዓለምን በጠቅላላ ይዋሻል፤ ሌሎች ተቀብለው እንዲዋሹለትም ያገሪቱን አንጡራ ሀብት ይከሰክሳል፡፡ ስሙን ቀይሮ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ይበለው እንጂ የሚከተለው ርዕዮተ ዓለም ውሸት ነው፡፡
ቅጥፈት ከወያኔ ብልሹ ባህሪያት ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ወያኔ ልዩ ልዩ ፋብሪካዎችን በማቋቋም ፋንታ ራሱ የውሸት ማምረቻ ፋብሪካ ሆኗል፤ ወያኔ ውሃ በቧንቧ በማሰራጨት ፋንታ በአየር ሞገድ አማካኝነት ያለማቋረጥ ውሸት ያሰራጫል፡፡

ወያኔ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ብሄራዊና ዓለማቀፋዊ ውሸቶችን ሲዋሽ ኖሯል፡፡ ረሃብ፣ ጥማትና እርዛት በአንድ እየዶሎቱ በችጋር ዱላ ለዘመናት ከደበደቡት የኢትዮጵያ ህዝብ ገላ ላይ ታትሞ በጉልህ የሚታየው የድህነት ጠባሳ ዋና አስረጅነቱ እንዳለ ሆኖ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሪፖርት የዘመነ ወያኔ ኢትዮጵያን ከአስሩ መናጢ ድሃ አገሮች ተርታ አሰልፎ ከኒጀር ቀጥሎ በዓለም በድህነቷ ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ በጥናቱ እያረጋገጠ ወያኔ በጎን ይዋሻል ያስዋሻል፡፡
ኢትዮጵያ በመከላከያ ተቋሟ ከምድራችን ከሚገኙ አገሮች ጋር ተወዳድራ በሰው ኃይልና በመሳሪያ ብዛትና ጥራት ከአፍሪካ አራተኛ ከዓለም ደግሞ 46ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች ተብሎ በራሱ በወያኔ እንድ የማህበራዊ ድረ ገፅ የወጣው የሰሞኑ ወሬ ደግሞ ሌላኛው ዓለም አቀፋዊና ከ2007 ዓ.ም ታላላቅ ውሸቶች አንደኛው ነው፡፡

ግሎባል ፋየር ፓወር ተቋም በ2015 ዓ.ም የ106 አገሮችን ወታደራዊ አቅም በደረጃ አስቀመጠና ኢትዮጵያ 340 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ በጀት፣ 2300 ታንክ፣ 81 የጦር አውሮፕላንና 182 ሺህ ሠራዊት አላት ተብሎ በወያኔ ማህበራዊ ድረ ገፆች የተለቀቀው ይህ ወሬ ነጭ ውሸት መሆኑን ይናገራል የቀድሞው የአየር ኃይል የተዋጊ ሄሊኮፕተር ስኳድሮን አዛዥና የበረራ አስተማሪ የነበረው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ፡፡

Monday, April 13, 2015

የአክራሪዎች፣ የተስፈንጣሪዎችና የአሸባሪዎች ዘመን

ይሄይስ አእምሮ (አዲስ አበባ)

ወቅቱ ለክርስቲያኖች የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል ሰሞን እንደመሆኑ በዓሉ የሚመለከታቸውን አንባቢ ወገኖቼን “እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው [በሰላም] አደረሳችሁ” ማለትን እወዳለሁ፡፡ የደርግ ጊዜ አንድ ትዝታ አለኝ፡፡ በአብዛኛው በሀገር ወዳድ ደናቁርት የታጨቀው የደርግ መንግሥት ሠለጠንኩ ብሎ ሃይማኖተቢሱንና ሃይማኖተኝነትን ከልካዩን የሶሻሊዝም ሥርዓት ካወጀባት ጠማማ ዕለት ጀምሮ በዓል በመጣ ቁጥር በተለይም የአብዮቱ በዓል በሚከበርበት ወቅት “እንኳን ደረሳችሁ” ይል ነበር – ያ ለአገራችን ባዕድ የነበረ የአገዛዝ ሥርዓት አንዲት ፊደል ላይ እንዲያ ይጨነቅ የነበረው፣ ሰው ለበዓሉ የደረሰው በራሱ እንጂ በፈጣሪ እንዳልሆነ ለማጠየቅ ነበር፤ የሥርዓቱ አቀንቃኞች በአብዛኛውና በግልጽ ይዞታቸው ሶሻሊስትና ኮሚኒስት እንጂ የሃይማኖት ሰዎች አልነበሩም – አንዳንዶች አምልኮታቸውን በኅቡዕ ያከናውኑ እንደነበርና ልጆቻቸውን ሣይቀር በድብቅ ክርስትና ያስነሱ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በመሠረቱ አንድ ሰው ምንም ዓይነት እምነት ላይከተል ይችላል፡፡ መብቱም ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን ሃይማኖት አልባነትን በግድ መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ በማጫፈር በእምነትና በሃይማኖት ጸንቶ የኖረን ሕዝብ በአንዴ እግዜርን ወይም አላህን ወይም የምታመልከውን ሌላ መንፈሣዊ አካልን ክደህ ኮሚኒስት ሁን ማለት የደርግን ብልህነት ሣይሆን ጅልነት የሚያሣይ ነበር – ሠለጠነች ቢሏት ጊዜ የባሏን መጽሐፍ ያጠበችውን ሴት ዓይነት ጅልነት፡፡ መጨረሻው ባለማማሩ ይከተለው የነበረውንም የአካሄድ ሥርዓት አይረቤነት በእግረ መንገድ መረዳት አይከብድም፡፡ እንዲያው ትዝ ብሎኝ ነው፡፡

ርዕሴን በእንግሊዝኛ ብጽፈው ኖሮ “The Age of Terrorists, Extremists and Deviants” በሚል እንዲነበብ አደርገው ነበር፡፡ ያለንበትን ዘመን ከየአቅጣጫው ስንቃኘው ጥቂት የማይባሉ አክራሪዎች፣ ተስፈንጣሪዎችና አሸባሪዎች ዓለማችንን እያተረማመሱ እንደሚገኙ መገንዘብ አያስቸግርም፡፡ ሌላውን ዓለም ለአሁኑ እንተወውና ወዳገራችን ተስፈንጣሪዎችና ምናምንቴዎች እንመለስ፡፡ በነሱ ነውና መቅኖ አጥተን የቀረነው – “ትንቢትሰ ይቀድሞ ለነገር” የምትለዋን ሐረግ እንድታስታውሱልኝ ግን ልማጠን፡፡

ትናንት አንድ ወዳጄ ቤቴ መጥቶ በላፕቶፑ ከዩትዩብ ያወረዳቸውን አንዳንድ ድንቃድንቅ ቃለ መጠይቆችና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች አስኮመኮመኝ፡፡ ሁለቱን ተስፈንጣሪዎችና ጠብ ጫሪዎች የተመለከትኩት በዚያን ጊዜ ነው፡፡ አንደኛው ተስፈንጣሪ መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ ይባላል፡፡ እኔን የታሪክ ተመራማሪ ያድርገኝና የታሪክ ተመራማሪ እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ አፄ ቴዎድሮስን እንዴት አድርጎ እንደሚስላቸው ብታዩ ትደመማላችሁ፡፡ አበሻቅጦ፣ አበሻቅጦ ነው የለቀቃቸው፡፡ ሲናገር ደግሞ ታሪክን እንደሚተርክ ሣይሆን በስሜት እየተወራጨና ክፉኛ እየተቆጣ እዚያው እቦታው ላይ ያለ ያህል ሆኖ ነው፡፡ የታሪክ ተመራማሪና ተንታኝ – በኔ ጥራዝ ነጠቅ ግንዛቤ – ትንታኔውንና ሀተታውን ማቅረብ ያለበት በጥላቻና በበቀል ስሜት እየተንዘረዘረ ሣይሆን የሆነውን ነገር እንዳለ በተረጋጋና አድልዖ በሌለበት ሁኔታ ነው – ታሪክ ነዋ! የዛሬ ሣይሆን የዱሮ ዘመን ድርጊት ነው፡፡ ዛር ከፈረስ የመሆን ወገንተኝነት ለታሪክ ተመራማሪ የሚፈቀድ አይመስለኝም፡፡ ይህ የታሪክ ተመራማሪ ግን አንድ ቦታ ሲናገር እንደሰማሁት አንሻፍፌም ቢሆን እጠቅሳለሁ፤ “ሀፄ ዮሐንስ ምኒልክን ቢያስሩት ኖሮ ጥሩ ነበር፡፡ መታሰር ነበረበት፡፡ ሀገር ከሃዲና ሻጭ ስለነበረ የሀፄ ዮሐንስ መኳንንትና መሣፍንት ‹ይህን ሰው ነገር ሳያመጣ እንሰረው› ሲሉ ሀፄው በምሕረት ማለፋቸውና ‹መኳንንቴ ሊያስሩህ ይፈልጋሉና አምልጣቸው› ብለው የሸዋን ንጉሥ እንዲያመልጥ ማድረጋቸው ትክክል አልነበረም፡፡…” እኔ የታሪክ ተማሪ አይደለሁም፡፡ ባልሆንም ግን እንዲህ ያለ ጭራሽ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ የታሪክ ትንተናና ቅጥ ያጣ ዘረኝነት ስመለከት የምናደድና ምሁር ተብዬውን የምቃወም መሆኔን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴን የተቸበትንም መንገድ ስመለከት አዝኛለሁ፡፡ ባህሩ ዘውዴ ኢትዮጵያ በአጸደ ሕይወት ካሏት ብርቅ የታሪክ ተመራማሪዎች አንዱ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ሁሉም ነገር ለከት ሊኖረው ይገባል፡፡

ዐፄ ምኒልክንና ዐፄ ቴዎድሮስን ለማቋሸሽና በሕዝብ እንዲጠሉ ለማድረግ ይህን ያህል ዘመቻ ማድረግ ትርፉ ለጊዜው ትዝብት ብቻ ቢሆንም እውነቱ ባለበት ይኖራልና የማስተባበሉን ዋና ኃላፊነት ለባለሙያዎቹ መተውን መርጫለሁ – አልተከታተልኩ ሆኖ እንጂ በጊዜው መልስ ተሰጥቶበትም ሊሆን ይችላል፡፡ ሰውዬው ግን በግብዝነቱ አሳዘነኝ፡፡ ደግሞም ሁለት ፀጉር ያበቀለ እንደኔው ትልቅ ሰው ይመስላል፡፡ ለምን ይህን ያህል ርቀት ተጉዞ ራሱን ትዝብት ውስጥ ማስገባት እንደፈለገ አልገባኝም – የእውነት አንጻራዊነት ደግሞ አስደነቀኝ፤ እውነት ሺህ ጊዜ አንጻራዊ ትሁን እንጂ ደግሞ ይህ ሰው ይህን ያህል ማፈንገጡ በሰዎች ተፈጥሮ እንድገረም አስገድዶኛል፡፡ ነገሥታቱን በዘራቸው ምክንያትም ይሁን በሌላ አይጥላቸው ወይም በግድ ይውደዳቸው ማለቴ አይደለም፤ ነገሥታቱ ምንም ጥፋት የሌለባቸው ምሉዕ በኩልሄ ናቸው ማለቴም አይደለም – ሰዎች እንደመሆናቸው እንደማንኛችንም ተራ ዜጎች ያጠፋሉ፤ ያለማሉም፡፡(በነገራችን ላይ ስለትግራይ ነገሥታትም ሆነ መሣፍንት እንዲሁም ስለ ዳግማይ ወያኔ የአስተዳደር በደል አንድም ነገር ትንፍሽ አላለም፤ ይህ ደግሞ ፍጹማዊ አድልዖና ወገናዊነትን ያሳያል፤ ምራቅ ከዋጠና ፈሪሃ እግዚአብሔር ካለው ጨዋ የትግራይ ሕዝብ የተገኘ የታሪክ ተመራማሪ እንዲህ ያለ ጭፍን አስተያየት ይሰነዝራል ተብሎ በጭራሽ አይጠበቅም – በኔ ግምት ንግግሩ ደመ-ሞቃታዊ ግልብ አስተያየት እንጂ በምርምር የተደገፈ እውነተኛ ታሪክ ነው ማለትም ያስቸግራል)፡፡

እኔ እምለው ታዲያ ጥላቻችንንም ይሁን ውዴታችንን የምንገልጽበት መንገድ አግባብ ይኑረው ነው ፡፡ ስንወድ፣ ስንወድ ሰዎች ባልዋሉበት ጦር ሜዳ ሺዎችን እንደገደሉና እንደማረኩ እያስመሰልን የምንኳሽ ፣ ስንጠላ ስንጠላ ደግሞ ጥቁሩን ነጭ፣ ነጩን ጥቁር እያደረግን ጥላሸት የምንቀባ ከሆነ አመክንዮታዊ ተፈጥሯችንን ገደል ከተትነው ማለት ነው፤ እንዲህ ስናደርግ ታሪክ ሣይሆን ኩሸትና ምናባዊ ገድል እየጻፍን ነው – እንደዚህ ያለ ነገር መጻፍ ወይ መናገር ካማረን ደግሞ በታሪክ ትምህርት አሳብበን ሣይሆን በልቦለድ ውስጥ ስሜታችንን መግለጽ እንችላለንና ወደዚያ መግባት ነው – የሰውዬው አካሄድ አህያን ተገን አድርጎ ጅብን እንደመውጋት ነው – ትልቅ የስብዕና ኪሣራ፡፡ ሰው የተባለ ፍጡር ደግሞ እንዲህ እንዲሆን አይጠበቅበትም፡፡ እንስሳ ብንሆንም ማሰብና ማመዛዘን የምንችል የሌሎች እንስሳት አለቃዎች በመሆናችን የማስተዋል ጥበብን እስከዚህን ድረስ በወረደ ሁኔታ ልንነጠቅ አይገባም፡፡ የዘረኝነትን ጭምብል አውልቀን፣ የሆድ አምላኪነትን ምኩራብ አፍርሰን፣ የጥላቻን ግምብ ንደን በሃቅ መፍረድ ካልቻልን ሰው መሆናችን ይቀርና በአንዲት አጥንት ሣቢያ የሰገሌን ጦርነት እንደሚያስታውሱን ውሾች እንሆናለን፡፡ ይህ ደግሞ ከንቱነትና እንደነቢዩ ሰሎሞን አነጋገር ንፋስንም እንደመከተል ያለ ሞኝነት ነው፡፡ ለምኑ ብለን? ነገ ጧት ሁሉም እርግፍ ብሎ ለሚቀረው? አቅል ጀባ መምህር ገብረ ኪዳን! ከጥቂት ጊዜ በኋላ ትግሬና አማራ ይቅርና የሰው ዘር በአጠቃላይ የሚበጠርበትና የሚበራይበት ዘመን ይመጣል፡፡ ያኔ እውነት የምትነግሥበት፣ ሀሰት የምትዋረድበት አዲስ ዘመን ይብታል፡፡ ያኔ ላለማፈር አሁን ትንሽ ስንቅ መያዝ ይገባናል፡፡ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ መስበሩን ካላቆመ ድንጋዩም ቅል ለመሆን እንደሚመኝ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ከኅሊና መታወር አምላክ ይሠውረን!

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባሎች እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያ በሙሉ!

ኢትዮጵያዊን እንደ ወያኔ ዘመን የተዋረዱበት የተናቁበትና የተበደሉበት ጊዜ የለም። በአሁኑ ወቅት አገሪቱ ና ህዝቧ ከፊታቸው የተጋረጠው ችግር የመሰረታዊ የዲሞክራሲ ና የሰብኣዊ መብቶች አለመከበር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሕልውና ጥያቄ ና ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠልና ያለመቀጠል ጉዳይ ሆኖዋል።

በመሆኑም በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያውያን ይህንን ወቅቱ የሚጠይቀውን ታሪካዊ እና አንጸባራቂ የትግል ድጋፍጥያቄ አቅማችን በፈቀደው መንገድ ለመደገፍ የዲሞክራሲዊለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በፕሪል18፣2015 ታላቅ ህዝባዊ ስብስባ ና ድጋፍ ማስባሰቢያ ዝግጅት አዘጋጅቶል እርሰወም በዝጅቱላይ አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታረጉ በአክብሮት እየጠየቅን በማያያዝም በዚህ ፕሮግራም ላይ በመገኘት እንዲሁም ሌሎችንም በመጋበዝ ታሪካዊና ወቅታዊ አገራዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ቀኑ፣ አፕሪል 18፣ 2015
ሰአት፣ 14፣00 ጀምሮ
ቦታ ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋር በቅርብ ቀን ይገለጻል

ጓደኛዎትን በኤቨንቱ ላይ ይጋብዙ፣
ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኖራለች !!!

Friday, April 10, 2015

የመን ለሚገኙ ወገኖቻችን እንድረስላቸው!

የመን የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን አደጋ ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የመብት አፈና፣ ሥራ አጥነት፣ ችጋርና ተስፋ ማጣት ለመሸሽ የራሳቸውንና የዘመዶቻቸውን ጥሪት አሟጠው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ለሚሰደዱ ወገኖቻችን የመን መሸጋገሪያቸው ናት። ዛሬ የህወሓት ወዳጅ የሆኑም ያልሆኑም የየመን አምባገነን ገዢዎች እርስ በርሳቸው እየተላለቁ፤ ከምድር እሳት እየነደባት መሆኑ ሳያንስ ከሰማይም እሳት እየዘነበባት ነው።

እንኳን አሁንና በሰላሙም ጊዜ የመን ለኢትዮጵያዊያን ምቹ አልነበረችም። በበረሀ ጉዞ የዛሉ እግሮች፤ ከአቅማቸው በላይ በጫኑ ታንኳዎች ባህር በመሻገር የታወኩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የመን ጠረፍ ላይ የሚጠብቃቸው ተጨማሪ እንግልት፣ ስቃይና መደፈር ነበር። የመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሕይወት እኛ ኢትዮጵያዊያን እንደ አገር የደረስበት አሳፋሪ ደረጃ መገለጫ ሆኖ ቆይቷል። በየመን፣ ወገኖቻችን ተደብድበዋል፤ አካላቸው በስለት ተዘልዝሏል፤ ሴቶች ብቻ ሳይሆን ወንዶችም ተደፍረዋል፤ ጓዳችን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታፍኖ ለህወሓት ተላልፎ ተሰጥቶብናል። አሁን የመን እየነደደች ነው።

እጅግ የሚያሳስበን ቁጥራቸው ከመቶ ሺህ ይበልጣሉ ተብሎ የሚታሰበው በአሁኑ ሰዓት የመን ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችን እጣ ፈንታ ነው። የሌሎች አገሮች ዜጎች መንግሥቶቻቸው ደርሰውላቸው ከእቶኑ አውጥተዋቸዋለሁ። የኛ ወገኖች ግን የሚደርስላቸው መንግሥት የላቸውም።

ወገኖቻችን በዚህ ጭንቅ ውስጥ ባሉበት ሰዓት የህወሓት አገዛዝ ያንዣበበባቸው አደጋ የሚያባብሱ ተግባራትን እየወሰደ ነው። ሌሎች አገሮች በየመን ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም በይፋ ከማሳወቃቸው በፊት ዜጎቻቸውን አስወጥተዋል። ህወሓት ግን ወገኖቻችን ለማዳን አንዳችም ጥረት ሳያደረግ ኃላፊነት በጎደለው መንገድ አንዱን ተፋላሚ ወገን በይፋ በመደገፍ በመቶ ሺህ የሚገመቱ ወገኖቻችን ከወላፈኑ ወደ እቶኑ ወርዉሯቸዋል። ገንዘብ የሚያገኝበት ከሆነ ወያኔ ወታደር ከመላክም ወደ ኋላ አይልም። እናም ለወገኖቻችን ካለ እኛ ማን አላቸው?

ስለ የመን ብቻ ሳይሆን ስለ ስደተኝነት በተነሳ ቁጥር አዕምሮዓችን ውስጥ የሚጉላላ ቁም ነገር አለ። እኛ ኢትዮጵያዊያን አገራችን ውስጥ ያለውን ሥርዓት ለውጠን፤ በምንወዳት አገራችን ውስጥ በክብር እንደመኖር እስመቼ አገራችንን ለህወሓት ወንበዴዎች ትተን እየሸሸን እንኖራለን? ስቃይና ሞት ተሸሽቶም አልተመለጠም። ሞት ኢትዮጵያዊያንን ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ሱዳን፣ ሰሀራ በረሃ፣ ሜዴትራኒያን ባህር፣ ቀይ ባህር፣ ሳውዲ አረቢያ እና የመን ውስጥ መሽጎ ይጠብቀናል። ኢትዮጵያዊያን በስደት ላይ እያለን

Sunday, April 5, 2015

የት ሂዱ ነው? ፕሮፍ መስፍን ወ.ማርያም


"ኑሮዬም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም እዚሁ ነው፤ ከኢትዮጵያ አፈር የሚለየኝ የለም"

ዓለም ሁሉ ጠላን፤ በየትም አገር እየሄድን “የሙጢኝ!” ከራሳችን መሬት በጉልበት እየተነቀልን፣ ከራሳችን ቤት እየተባረርን፤ ከተወለድንበትና ከአደግንበት አካባቢ እየተፈናቀልን፣ ጭራውን ቆልምሞ እንደሚሮጥ ባለቤቱ እንዳባረረው ውሻ በአገኘነው አቅጣጫ እየሮጥን፣ እጃችንን እያርገበገብን “የሙጢኝ!” እንላለን፤ የፈራነውን ሞት በየመንገዱ እናገኘዋለን፤ ሞትን ሸሽተን ሞት ያጋጥመናል፤ የሞቱ ልዩነት አይታየንም፤ በየመንገዱ የሚያጋጥመው ሞት የውርደት ሞት ነው፤ የብቸኛነት ሞት ነው፤ ዘመድ-ወዳጅ ለቀብር የማይገኝበት ሞት ነው፤ ሠለስት፣ አርባ፣ ሙታመት የማይወጣበት ሞት ነው፤ ባዕድ ምስጥ ያላሳደገውን አካል የሚበላበት ነው፤ የሞት ሞት ነው፡፡

ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ከአገር አስወጥቶ ባዶ መሬት ብቻ ይፈልግ ይመስል የወያኔ ሎሌዎች በማስፈራራት ሁሉም አገሩን እየተወላቸው እንዲሄድ ያቀዱ ይመስላል፤ ጥንት ኢሰመጉ በምሠራበት ጊዜ በየጊዜው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን በማስፈራራት ሰላማቸውን ለመረበሽ ወደስደት ወይም ወደወንጀል ተግባር የሚመሩ የወያኔ አባሎች ነበሩ፤ አሁን እንደገና ብቅ ማለት ጀምረዋል፤ ሕጋዊ ሥርዓት እየላላ ጉልበተኞች በግላቸው ለዘረፋና ለቅሚያ እየተሰማሩ ይመስላል፡፡

ስለራሴ ላውራ፤ ከእኔ የሚፈልጉት ምን እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም፤ የሚፈልጉት የምኖርበትን አፓርትመንት እንደሆነም አላውቅም፤ በእኔ ቤት ያለ ሀብት የሚባል ለወያኔ አገልጋዮች የሚጠቅም ሁለት የገብረ ክርስቶስ ስዕሎች ብቻ ናቸው፤ (በዚህ አጋጣሚ እነዚህን ስዕሎች ለመግዛት የሚፈልግ ያነጋግረኝ)፤ ከዚህ ሌላ ለወያኔ ዋጋ የሌላቸው መጻሕፍት ናቸው፤ ስለዚህም አሁን በእኔ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት እኔን ወደስደት ለመግፋት የሚደረግ ሙከራ ይሆናል፤ በ1992 ግድም ተሞክሮ ነበር፤ አልሠራም፤ ዛሬ ይበልጥ አይሠራም፤ ለማናቸውም ምክንያቱን በትክክል ለማወቅ ባልችልም በእኔ ላይ ዘመቻ መጀመሩን አንድ በቅርብ ከማውቀው ወያኔ በትክክል ተረድቻለሁ፤ ይህንን ዘመቻ በመምራት ላይ ያለውንም ሰው ማንነት ተነግሮኛል፡፡

ይህ አገር የአንድ ጉልበተኛ ቡድን ነው ብዬ አልቀበልም፤ የአባቶቼና የእናቶቼ፣ የአያቶቼና የቅድማያቶቼ አጥንትና ደም የገነባው አገር ነው፤ ማንም ለስደት አይዳርገኝም፤ ማንም አስፈራርቶ ኢትዮጵያዊነት መብቴን መግፈፍ አይችልም፤ አልፈቅድለትም፤ በግልጽ በማያጠራጥር ቋንቋ ኑሮዬም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም እዚሁ ነው፤ ከኢትዮጵያ አፈር የሚለየኝ የለም፡፡

‹‹በማላውቀው ምክንያት ፓስፖርቴን ተነጥቄ ጉዞዬ ተስተጓጉሏል››

‹‹በማላውቀው ምክንያት ፓስፖርቴን ተነጥቄ ጉዞዬ ተስተጓጉሏል›› ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

በአሜሪካ ከሚገኙ የሰማያዊና የአንድነት ለፍሕትና ለዴሞክራሲ (አንድነት) ፓርቲ አባላት ጋር በተለያዩ ስቴቶች ለመወያየት ወደዚያ ለማቅናት ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ያመሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ባላወቁት ምክንያት ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው ጉዟአቸው እንደስተጓጎለ ገለጹ፡፡

መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ወደ አሜሪካ ለመብረር ሁሉን ነገር አሟልተው ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሳቸውን የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ የአውሮፕላን መሳፈሪያ ሰዓት እስከሚደርስ ሊሸኟቸው አብረዋቸው ከነበሩ ጓደኞቻችው ጋር ሲጨዋወቱ አምሽተው ወደ ውስጥ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

የመጨረሻውን ፍተሻ አልፈው ወደ አውሮፕላን መግቢያ በር ለማምራት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ፍተሻ ጋ ሲደርሱ ፓስፖርታቸውን ሰጥተው የይለፍ ማረጋገጫ ለማግኘት እየተጠባበቁ ሳሉ የኦፕሬሺን ሠራተኛዋ ‹‹ከዚህ ቀደም ሌላ ፓስፖርት ነበረዎት?›› የሚል ጥያቄ እንዳቀረበችላቸው ገልጸዋል፡፡ እንደነበራቸውና ከዚህ በፊትም ወደ አሜሪካ ለመሄድ እዚያው ፍተሻ ላይ ሲደርሱ ‹‹ከፓስፖርትዎት መካከል አንድ ገጽ ጎድሏል፤›› ተብለው መመለሳቸውን እንደነገሯት አክለዋል፡፡ ለ20 ደቂቃ ያህል በኢንተርኔት ላይ አንዳንድ ነገሮችን ስታነብ የነበረችው ሠራተኛዋ፣ ‹‹አለቆቼን ላነጋግር›› ብላቸው ወደ ቢሮ መግባቷንና ወዲያው በፍጥነት ተመልሳ ሥራዋን በመቀጠል ‹‹ይጠብቁ እያዩት ነው›› እንዳለቻቸውና ለ50 ደቂቃዎች ያህል መጠበቃቸውን ኢንጂነር ይልቃል ገልጸዋል፡፡

ከረዥም የደቂቃዎች ቆይታ በኋላ አንድ ሰው ከቢሮ ወጥቶ ‹‹እርስዎ ዛሬ መሄድ አይችሉም፤›› ብሏቸው ስማቸው፣ ዜግነታቸውና የፓስፖርት ቁጥራቸው ተጽፎ፣ የታገዱበት ምክንያት ያልተገለጸበት ወረቀት እንደሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲጠይቁ ‹‹እኛ የኦፕሬሽን ሠራተኞች ነን፣ ምክንያቱን አናውቅም፡፡ ነገ መጋቢት 24 ቀን ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ መጥተው ከአለቆቻችን ምክንያቱን ያውቃሉ፤›› ብለዋቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡

በማግሥቱ መጋቢት 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ሲሄዱ ‹‹በዚህ ወረቀት መግባት አትችሉም፡፡ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ሄደው ይጠይቁ፤›› ብለው እንደመለሷቸውም አስረድተዋል፡፡ ኢንጂነር ይልቃል በዕለቱ ወደ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መምሪያ ዋና መሥሪያ ቤት የሄዱ ቢሆንም፣ ‹‹ሰዓቱ መሽቷልና ነገ ጠዋት ይመለሱ፤›› ተብለው ሳይሳካላቸው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡

Thursday, April 2, 2015

ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው!

ለገዛ ራሱ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ቅን የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሓትን ለማስወገድ ተግባራዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑን፣ ፋሽስቱን ህወሓት እንደመደገፍ ይቆጠራል።

ዛሬ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ የመሰማራት ሰፊ እድል ተፈጥሮለታል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ በረሃዎችና ተራራዎች አቅንተዋል። ብዙዎች በመንገዱ ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን ተቋቁመው እየተቀላቀሏቸው ነው። በደል የመረራቸው ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በቡድን ለነፃነታቸው ዘብ ቆመው በህወሓትና አገልጋዮቹ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ይህ የሚበረታታ እና ተቀናጅቶ ሊጠናከር የሚገባው ጉዳይ ነው።

አሁን ያለንበት ጊዜ ልዩ የትግል ወቅት ነው። ትናንት በከተሞች ይካሄድ የነበረው ፀረ ወያኔ ትግል ዓይነተኛ መታወቂያው ሕዝባዊ ተቃውሞ ነበር። ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። በተለይ በአገዛዙ ፈቃድ የሚደረጉ ተቃውሞዎች ፋይዳ ቢስ ሆነዋል። በአገዛዙ ፈቃድ በሚደረጉ ተቃውሞዎች ለውጥ እንደማይመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ተረድቷል። ስለሆነም ትግሉ ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድጓል።

ዛሬ ከዚህ በፊት ያልተሞከሩ የትግል ስልቶች ተግባራዊ እየሆኑ ነው። በዚህ ረገድ የሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የተቀናጁ ርምጃዎች በአርዓያነት የሚጠቀሱና የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ የሚሹ ናቸው። እነዚህ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ተግባራት የእምነት አጥር ሳይለያየን ፍትህ የተጠማን ዜጎች ሁሉ ልንተገብራቸው የሚገቡ ናቸው።

ለምሳሌ፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በተወሰኑ ቀናት መዝጋት በተቀናጀ ሁኔታ ከተደረገ ከፍተኛ ውጤት ሊያመጣ የሚችል፤ በሙስሊም ወገኖቻችን ግንባር ቀደም መሪነትና አስተባባሪነት ተሞክሮ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል መሆኑ የታየ አንድ የትግል ስልት ነው።

በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ በመደረግ ላይ ያለው ሣንቲሞችን የመሰብሰብ ዘመቻም ሌላ ከዚህ በፊት ያልተሞከረ፤ በተጨማሪ እርምጃዎች ከታገዘ ህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን ገንዘብ መቆጣጠር የማይችልበት ደረጃ ላይ ሊያደርስ የሚችል ጉልበት ያለው ስልት ነው። ውሳኔው ሣንቲሞችን ብቻ ሳይሆን የወረቀት ኖቶችንም ሲያካትት በዝውውር ላይ የሚኖረውን ገንዘብ ብዛት የሚቆጣጠረው ህወሓት ሳይሆን በደል ያንገሸገሸው ሕዝብ ይሆናል። በባንኮች ያለ ተቀማጭ ገንዘብ በማውጣትም የህወሓት የፋይናንስ ተቋማትን ማሽመድመድ ሌላ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ስልት ነው። በእነዚህ እርምጃዎች የተለማመደ ሕዝብም ወደ ግዢ እቀባ፤ ለተወሰኑ ቀናት ከቤት አለመውጣት ብሎም “ግብር አልከፍልም” ወደማለት ሊሸጋገር ይችላል።

Wednesday, April 1, 2015

Exposed: Tedros Adhanom’s chief advisor is a phony prof from Bowie


(Addis Voice) The chief advisor of Ethiopia’s Ministry of Foreign Affairs and the minister, Tedros Adhanom, is a self-appointed professor with a PhD in “international studies” from a “university” labelled by a U.S. congressional investigation as a diploma mill, AV can reveal.

“Professor” Mekonnen, who also served PM Hailemariam Desalegn as his chief adviser, claims publicly, as well as in his official biography posted on the ministry’s website, that he was a professor at Maryland-based Bowie State University for 15 years. “At Bowie State University (1991-2006), he gave courses in modern political philosophy, political science, international relations and African-American history in the Department of History and Politics,” his official biography says. Founded as a historically black college in Maryland, Bowie State is one of the ten oldest in the United States, according to its website.

But Bowie State, where Mekonnen claims to have served as a professor of history and politics for fifteen years, told Addis Voice that it has no record of employment let alone his appointment as a professor. In response to AV’s formal request for information in accordance with the Maryland Public Information Act, Sheila Hobson, Senior Director of Human Resources, formally replied to the request in writing and by phone stating that the university has no record of the professor.

“We have searched our records for Dr. Mekonnen Haddis but have been unable to locate a current or former employee by that name,” she wrote in an email. . She also checked a card system that the HR department used to keep before it computerized its system. But the search did not find any records of the top Ethiopian government official.

Hobson also talked to the Chairman of the Department of History and Government, Professor Sammye Miller, who remembered him to have taught for one or two semesters long time ago. He also confirmed to this reporter what he had already told the HR director. Hobson explained that HR does not keep brief stints by graduate assistants and instructors as employment records.

Professor William Lewis, who also served for over three decades at the same department like Sammye Miller, remembered Mekonnen not as a professor but as a student. “He did his Master’s degree at the university and gave a couple of courses. That was it as far as I know,” he said. Both veteran professors refuted Mekonnen’s claim that he was a professor at Bowie State and taught a range of courses from 1991 to 2006.

What was even more puzzling was the fact that no academic writing or paper published under his name at any university can be traced. Academic appointment at any serious university is normally a lengthy process based on substantial and proven academic work, teaching, research and publishing records to advance knowledge in a given field.