Monday, June 30, 2014

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ



አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ

ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም

የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቷል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን የጉዞው መዳረሻ አልነበረም፤ ከየመን ጋርም የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ አልነበረውም። የየመን መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግቶ ለአንድ ሰዓት እንኳን ለማቆየት ምንም ምክንያት የለውም። በዚህም ምክንያት ያለአግባብ የታገተብን የንቅናቄያችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። እንዲያውም የየመን ባለስልጣናት አምባገኑን ወያኔ ለመርዳት ባለው ፍላጎት ሳቢያ መሪያችንን አሳልፎ ሊሰጠው ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮብናል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ጊዜውን፣ እውቀቱንና ጉልበቱን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ፤ ዝግጁነቱንም በተግባር ያሳየ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። የየመን መንግሥት ከዘረኛውና ፋሽስታዊው ወያኔ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ታጋይ መሪያችን ላይ እየፀመ ያለውን ደባ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅ የንቅናቄዓችን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወስኗል።

ትግላችን መስዋትነት እንደሚያስከፍል እናውቃለን። ከዚህ በፊትም ብዙ ጓዶቻችን መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ ወደፊትም ብዙ መስዋዕትነት መከፈሉ የማይቀር ጉዳይ ነው። አሁን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የደረሰውና ወደፊትም ሊደርስ የሚችለው ጉዳት ምሬታችን በማብዛት፣ ቁጣችንና ዝግጁነታችን ከማጠንከር በስተቀር ቅንጣት ታክል እንኳን ወደ ኋላ እንድናፈገፍግ እንደማያደርገን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለአባሎቻችንና ለደጋፊዎቻችን ሁሉ መግለጽ እንወዳለን።

መንግሥታት ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ። ኢትዮጵያና የመን ግን ጎረቤታሞች ሆነው መቆየታቸው የማይቀር ነው። የየመን መንግሥት የወያኔ እድሜ አጭር መሆኑ የተገነዘበ አይመስልም። በዚህም ምክንያት የየመን መንግሥት የሁለቱን አገሮች ሕዝቦች የቆየ ወዳጅነት የሚያደፈርስ እርምጃ ወስዷል። የየመን መንግሥት የየመንን የወደፊት የረዥም ጊዜ ጥቅም እንዲያሰላና ያገተብንን መሪ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንመክራለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በመሪያችን ላይ ጉዳት ቢደርስ ወይም ለወያኔ አሳልፎ ቢሰጥ የመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የማይሽር ቂም ውስጥ የምትገባ መሆኑን የየመን መንግሥት አውቆ በጥብቅ እንዲያስብበት እናስጠነቅቃለን።

በየመን መንግሥት አልሰማ ባይነት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለፋሽስቱ የወያኔ አገዛዝ ተላልፎ ቢሰጥ በአካሉና በሕይወቱ ለሚደርሰው ሁሉ የወያኔ ፋሽስቶችን ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ ከአሁኑ እናስጠነቅቃለን። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አካል፣ መንፈስና ሕይወት ላይ የሚደርሰው ማንኛውም ጥቃት ለነፃነታቸው ለመሰዋት ዝግጁ የሚሆኑ እልፍ አዕላፍ ታጋዮችን እንደሚፈጥር ጥርጥር የለንም። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አካል፣ መንፈስ እና ሕይወት ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ሁሉ በማንኛውም መንገድ በማንኛውም ቦታ የምንበቀል መሆኑንና ብዙ የወያኔ ሹማምንት ዋጋ የሚከፍሉበት እንደሚሆን እንዲያውቁት እናስጠነቅቃለን ።

በመስዋዕትነት ድልን እንቀዳጃለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

(መግለጫውን በPDF ከዚህ ላይ ያንብቡ)

አንጋፋው የነጻነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ግንቦት 7 አስታወቀ!!!

አንጋፋው የነጻነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ግንቦት 7 ዛሬ አስታውቋል!!!

ግንቦት 7 ዛሬ ለጋዜጠኞች እና ለአባላቶቹ በላከው መግለጫ የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለስራ በሚንቀሳቀሱበት ሰአት ትራንዚት በአደረጉበት በየመን አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ በፀጥታ ሃይሎች መወሰዳቸውን አስታውቋል።

ንቅናቄው የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን ለወያኔ አሳልፎ እንዳይሰጥ ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ የላከ ሲሆን ለሳምንት ያህል ውስጥ ለውስጥ ሲደረግ የነበረው ውይይትም በሁለቱ ወገኖች ሳይሳካ መቅረቱን በመግለጽ የመን ይህን ታሪካዊ ስህተት ብትፈጽም በወደፊቱ የሁለተዮሽ ሀገራት ግንኙነት ላይ የማይጠፋ ጠባሳ እና አስቸጋሪ ሁኔታ እንደሚፈጠር አስታውቋል፡፡

ድርጅታችን የሚያደርገውን የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል ከቶ ለአንዳፍታም ቢሆን አያቆምም ያለው ድርጅቱ፤ አቶ አንዳርጋቸው ራሳቸውን አሳልፈው ለሚወዷት ሀገራቸው እማማ ኢትዮጵያ መሰዋእት ለመሆን የተዘጋጁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጅ መሆናቸውን እና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ከጎናችን ሆኖ ትግሉን እንዲያጠናክርና በየመን መንግስት ላይ ህዝቡ በያለበት ጫና እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

እንደሚታወቀው በአለፉት ወራቶች የኢትዮጵያ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ የመግደል ሙከራ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ሙሉ መግለጫውን በሚቀጥለው እናወጣለን።

በዚህ አጋጣሚ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ለዚህ አንጋፋ የነጻነት ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ ተላልፎ እንዳይሰጥ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በየመን እና በአለም አቀፍ የተባበሩት ቢሮዎች የተቃውሞ ድምጻችን እንድናሰማ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡


Sunday, June 29, 2014

እያበበ የመጣዉ ህዝባዊ ትግል

ኢትዮጵያ ህዝብ ለብዙ ዘመናት እንወድሀለን በሚሉት ነገስታት ተረግጧል፤ ህብረተሰብዓዊነት አመጣንልህ ባሉት ወታደራዊ አምባገነኖችም ለ17 አመት እጅና እግሩን ታስሮ ተገዝቷል። እነዚህ ሁለት ለህዝብ ደንታ የሌላቸዉ መንግስታት ተራ በተራ በህዝብ ትግል ተንኮታኩተዉ የታሪክ ቅርጫት ዉስጥ ገብተዋል፤ ሆኖም ሁለቱንም መንግስታት በመራራ ትግል አሸንፎ የጣለዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የትግሉን ዉጤት ማስጠበቅ ባለመቻሉ ይህ ኃያልና የረጂም ዘመን ታሪክ ባለቤት የሆነ ህዝብ ዛሬም ነፃ አወጣንህ በሚሉት ዘረኛ አምባገነኖች እየተረገጠ ነዉ። አዎ! የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬም እየተረገጠ ነዉ። ዛሬም አየታሰረ ነዉ። ዛሬም እየተገደለ ነዉ። ዛሬም ይህንን ሁሉ በደል የሚያደርሱበትን የአንድ ወንዝና የአንድ መንደር ምርት የሆኑ ዘረኛ አምባገነን ገዢዎችን ከጭንቅላቱ ላይ ለማዉረድ እየታገለ ነዉ። በእርግጥም የኢትዮጵያ ህዝብ ከምን ግዜም በተለየ መልኩ የወያኔን ዘረኛ አገዛዝ አምርሮ እየታገለ ነዉ፤ በተለይ በዚህ በያዝነዉ አመት ወያኔንና ሃያ ሁለት አመት ሙሉ የገነባዉን ዘረኛ ስርዐቱን ለመደምሰስና ኢትዮጵያ ዉስጥ በፍትህና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ስርዐት ለመገንባት የሚደረገዉ የሞት የሽረት ትግል ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ወያኔ እግሩ አዲስ አበባን ከረገጠበት ግዜ ጀምሮ የጭቆና ተቋሞቹን በየቦታዉ ተክሎና ተደላድሎ ህዝብን እንዳሰኘዉ መርገጥ እስከጀመረበት ግዜ ድረስ አንዴ ሰዉ በላዉን የደርግ ስርዐት አስወገድኩላችሁ እያለ ሌላ ግዜ ደግሞ ፌዴራል ስርዐት መስርቼ ብሄር ብሄረሰቦችን ነፃ አወጣሁ እያለ ለተወስነ ግዜም ቢሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ቀልብ መሳብ ችሎ ነበር። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ያ በፌዴራሊዝም፤ በዲሞክራሲና በይስሙላ ምርጫ የተሸፈነዉ የወያኔ አስቀያሚ ገበና ይፋ እየሆነ መጥቶ ወያኔ አርግጫዉንና ግድያዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ትግሉን፤ እስሩንና ስደቱን ተያያዙት።

የወያኔን መሰሪ አላማ ገና ከጧቱ የተረዱ ኢትዮጵያዉያን ባለፉት ሃያ ሦስት አመታት ይህንን መሰሪ አገዛዝ በተደራጀ፤ ባልተደራጀ፤ በተባበረና በተበታተነ መልኩ ሲታገሉ ቆይተዋል። ሆኖም የአገራችንን የፖለቲካና የኤኮኖሚ መዋቅሮች ሙሉ ለሙሉ ከሚቆጣጠረዉ ወያኔ ጋር በቁጥር፤ በአይነትና በይዘት የሚመጥን ትግል ማካሄድ ባለመቻላቸዉና እንዲሁም ብትራቸዉን ወያኔ ላይ ብቻ ከመሰንዘር ይልቅ እርስ በርስ ስለሚላተሙበት ምንም አይነት ህዝባዊ ድጋፍ በሌለዉ ወያኔ ላይ የትግል የበላይነት ማግኘት አልቻሉም፡፡ ወያኔም እኛዉ ዉስጥ ከመካከላችን የበቀለ እሾክ በመሆኑና ደካማ ጎናችንን በሚገባ ስለሚያዉቀዉ በዚሁ ደካማ ጎናችን እየገባና እርስ በርስ እያባላን የስልጣን ዘመኑን እስከዛሬ ማራዘም ችሏል።

Saturday, June 28, 2014

ትንሽ ስለ እስክንድር ............

በቅዱስ ዮሃንስ

ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ የሆነው እስክንድር ነጋ ገድል ከነፃው ፕሬስ ውልደት ጀምሮ አሁን የመጨረሻው አፋፍ ላይ እስከ ደረሰበት ጊዜ የሚዘልቅ ነው። ብዙዎች ከእስክንድር ጋር ረጅሙን ጉዞ የጀመሩ ዛሬ አጠገቡ የሉም፡፡ ያ! እንደ እሳት የሚፋጀው የብእር ትሩፋታቸው ከአንባቢ ማእድ ከራቀ ዘጠኝ አመት ሞላው፡፡ አንዳንድ የብእር ገበሬዎች እስር ቤት ባፈራዉ ህመም ምክንያት መተኪያ የሌላት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ብዙዎቹ የሚወዷት ሀገራቸውን ጥለው ተሠደዋል፡፡ ለምሳሌ ጋዜጠኛ ቅዱስሀብት በላቸው፣ ፋሲል የኔያለም፣ የነፃው ፕሬስ ፊት አውራሪ የነበሩት አቶ ክፍሌ ሙላት፣ ከፍያለው ማሞ ይጠቀሳሉ፡፡ እስክንድርስ?

እስክንድር ግን ፍፁም ለየት ያለ ባህሪ ያለው ሠው መስሎ ታየኝ፡፡ ከመልካም ቤተሰብ ፍቅርን ሲመገብ ያደገው ይህ ልበ ሙሉ ጋዜጠኛ የምቾትና የተንደላቀቀ ኑሮውን በመተው ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት ሲል ከአሁኑ እስር በፊት እንኳ ከሰባት ጊዜያት በላይ ወደ ወህኔ አምባ ተወርውሯል፣ አንድ ባልታደለች ማለዳ ላይ ደግሞ ባልታወቁ ሠዎች ተደብድቦ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ እስክንድር በእውቀት የመጠቀ ብቻ ሣይሆን የመልካም ባህሪ ባለቤትም ነው፡፡ ለዚህም ነው እንደ ጥጃ እያሠሩ የሚፈቱትን፣ በጋዜጠኝነት ሙያ እንዳይሰማራ ያገዱትንና የአይምሮው ጭማቂ የነበረውን መጽሀፍ ማሳተም አትችልም ያሉትን የዘመናችንን ፈርኦኖቹን አንድም ጊዜ በጥላቻ አይን ያላየው፡፡ ለዚህ ደግሞ ምስክሮቹ በጋዜጣ አሊያም በድረ-ገጽ ይጽፋቸው የነበረው በሣል ትችቶች ናቸው፡፡ እርግጥ ነው ይህን የለየለት የአመባገነን ሥርዓት በሠላ ሂስ በርካታ ጊዜ ሸንቁጦታል፡፡ ይህ ደግሞ ለእናት ኢትዮጵያ መፃኢ እድል ከመጨነቅና ከመጠበብ የተነሳ ነው፡፡ ‹‹አካፋን አካፋ›› ማለት ከአድርባይና ከባንዳ ጋዜጠኛ አይጠበቅም፡፡ እስክንድር ግን የእናት ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ እንቅልፍ የነሳው በመሆኑ የወያኔን የእውር ድንብር ጉዞን በተባ ብእሩ ኮንኗል፣ ሥርዓቱ በትክክለኛው ሀዲድ እንዲጓዝ ሞክሯል፡፡ ዘክሯል፡፡ ምላሹ ግን ከሥራ ማገድ፤ በመጨረሻም የከፋ የእስር ወሳኔ ተላልፎበታል፡፡ ሰውየው ጀግናው እስክንድር ነጋ ሆነ እንጂ ገዢዎቻችን በህይወት የመኖር መብቱን ገፈውታል፡፡ ይኼ ሁሉ ግን ከዓላማው አላዛነፈውም፤ ራሱን ለአገሩ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ኢትዮጵያን ከምለቅ ሞቴን ብሎ ጨቋኙን አገዛዝ በመጋፈጡ ለከፋ እስር ተዳርጓል። ይህ ጀግና አሁን ላለው ትውልድ የዓላማ ጽናት ተምሳሌ ነው፡፡

ጥቂት ነጥቦች በፍትህ ጉዳይ ላይ

በዶ/ር ታደሰ ብሩ

1. መግቢያ

ህወሓት በሥልጣን ላይ በከረመ መጠን የኢትዮጵያ ሕዝብ በፍትህ እጦት የሚደርስበት መከራ እየጨመረና እየመረረ በመምጣቱ “ፍትህ አጣን፤ የፍትህ ያለህ” የሚሉ እሮሮዎች ከቀድሞው በበለጠ መልኩ እየጎሉ መጥተዋል። በከተማውም በገጠሩም፣ ከእድሜ ባለፀጋውም ከወጣቱም፣ ከወንዱም ከሴቱ፣ ከክርስቲያኑም ከሙስሊሙም ወገኖቻችን የሚሰማው ጩከት “የፍትህ ያለህ” የሚል ነው። የፍትህ እጦት ነው ወገኖቻችንን በገዛ አገራቸው ተፈናቃይ ያደረጋቸው፤ የፍትህ እጦት ነው ገበሬዎች ማሳቸው ለባዕዳን ሲሰጥ አንጀታቸው እያረረ ዝም እንዲሉ የሚያደርጋቸው፤ የፍትህ እጦት ነው ነጋዴዎች ሱቆቻቸው በእሳት ሲጋዩ “ጉዳዩ ይጣራልን” ማለት እንኳን ያላስቻላቸው፤ የፍትህ እጦት ነው የእምነት ነፃነታችንን እንኳን ማስከበር ያላስቻለን።

ፍትህ ሰዎች በግልም በቡድንም ተሳስበው እና ተጋግዘው እንዲኖሩ የሚያደርግ የበጎ ሥነ-ምግባር መርሆች ስብስብ ነው። ፍትህ ነው ማኅበረ-ሰብን ከማኅበረ-አራዊት የሚለየው። ማኅበራዊ ኑሯቸውን በሥርዓት አደራጅተው የሚኖሩ እንስሳት መኖራቸው ቢታወቅም (ለምሳሌ የጉንዳን ሠራዊት፤ የንብ መንጋ) በእውቅ (Consciously) የተገነባ የፍትህ ሥርዓት ያለው የሰው ልጅ ብቻ ነው። ፍትህ ሰውኛ እሴት ነው።

ምንም ዓይነት ፍትህ የሌለበት ማኅበረሰብን ለማሰብ ብንሞክር በአዕምሮዓችን ሊመጣልን የሚችለው እያንዳንዱ ግለሰብ፣ ከፍ ካለ ቤተሰብ፤ ከዚህ በላይ ከፍ ካለ ደግሞ የተዛመዱ ቤተሰቦች የፈጠሩት ስብስብ ነው። እያንዳንዱ ግለሰብ ወይም በዝምድና የተሳሰረ ስብስብ የገዛ ራሱን ወይም ቡድኑን ለማኖርና ከጥቃት ለማዳን የሚጥርበት ሥርዓት እናገኛለን። በዚህ ሥርዓት ውስጥ “የሥጋ” ዝምድና (ለምሳሌ እናትና ልጅ) ብቸኛው ማስተሳሠሪያ ይሆናል። በሌላ አነጋገር ዘር ብቸኛ የስብስቡ ማስተሳሠሪያ ይሆናል። በማኅበረ-እንስሳት ውስጥ መንጋን የሚያስተሳስረው በዘር መነሻነት የተፈጠረ አብሮ ውሎ ማደር ነው። ፍትህ በሌለበት ማኅበረሰብም ውስጥ የሚዛመዱ ቤተሰቦች ራሳቸው በተለያየ ስያሜ ወደሚጠሩ ስብስቦች ማደግ ይችላሉ። ትልቅም ይሁኑ ትንሽ፣ ስብስቦቹን የሚያገናኛቸው ዝርያቸው ነው። በማኅበረ-እንስሳት ውስጥ በመንጋዎች መካከል የማያቋርጥ ትንንቅ ይኖራል። በማኅበረ-እንስሳት ደካማው ብቻ ሳይሆን ጠንካራውም ቢሆን ሕይወቱን በሰቀቀን ማሳለፉ የግድ ነው። ጠንካራው መንጋ ከሱ የባሰ ጠንካራ መንጋ እንዳይመጣበት እንደሰጋ ይኖራል። ፍትህ የሌለበት ማኅበረሰብም እንደዚያው ነው። ፍትህ በሌለበት፣ ሰዎች በዘር መደራጀታቸው ተፈጥሮዓዊ የመሆኑን ያህል እርስ በርሳቸው መጣላታቸውም እንደዝያው የማይቀር ተፈጥሮዊ ነው። በቡድኖች መካከል ያለው ጦርነት በአንዱ ቡድን ጊዜዓዊ አሸናፊነት ጋብ ሲል በቡድኑ ውስጥ ባሉ ቤተሰቦች መካከል ጦርነት ይነሳል፤ ያ ጋብ ሲል ደግሞ በእያንዳንዱ ግለሰብ መካከል ይጀመራል። ሲከፋ ወገንና ጠላት ያልለየ ሁሉም ከሁሉም ጋር (all against all) ጦርነት ውስጥ ይገባል። ይህ ዓይነቱ ሁኔታ ነው ህገ-አራዊት የሚባለው። ፍትህ በሌለበት የሰው ልጆች ሕይወት ወደ ህገ-አራዊት ያሽቆለቁላል።

Thursday, June 26, 2014

የወያኔን የጥፋት ድግስ እናምክን!

ኢትዮጵያን የሚገዛው ጉጅሌ ሀገራችንን እየወሰደበት ያለው አደገኛ አቅጣጫ አሳሳቢ ከመሆን አልፎ የአደጋውን መራራ ፍሬ ማየት ከጀመርን ሰነበትን። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ወሳኝ ከሆነው የወደፊቱ የጋራ ጥቅማቸውና ህልውናቸው በበለጠ ልዩነታቸውና ያለፈ ታሪካቸው እንደዋናው ነገር እየተቆጠረ ለሚሰበከው ስብከት የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይ ባይሆን ኖሮ እስካሁን ብዙ ጥፋት በደረሰ ነበር።

ህወሃት በህዝቡ ውስጥ የኖረውን ልዩነት የጠብ፣ የግጭትና የመፈራራት መሰረት በማድረግ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ካለው ምኞት የተነሳ በመደዴ ካድሬዎቹ አማካኝነት ለዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝብ በማቃቃር እኩይ ተግባር ላይ ተጠምዶ ይገኛል።

ህወሃት ይህን የማጋጨት ስራ በተለይ በስልጣን የመቆየት ፍርሃት ባባነነው ቁጥር የሚጠቀምበት መሳሪያ አድርጎታል። በባህርዳር ላይ የብሄረሰቦች ኳስ ጭዋታ ውድድር ምክንያት አድርጎ፣ መደዴ ካድሬዎቹን አሰማርቶ ስታዲዮም ውስጥ ኦሮሞዎች እንዲሰደቡ ካደረገ በኋላ ነገሩን ከማረጋጋት ይልቅ በኦሮሞኛ የቴሌቪዥንና ሬድዮ፣ ኦሮሞዎች በአማራዎች ተሰደቡ ብሎ ያስነገረው ለምንድን ነው? ከዚያ በኋላ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ቁጣና ጠብ ለመቀስቀስ ብሎም በዚህ ጠብ ውስጥ ገላጋይ በመምሰል የአንዱ ብሄር ጠባቂ መስሎ ለመታየት ጉዳዩን ባልተረዱ የዋሆች ውስጥ ለመግባት ይፈልጋል። በአማራ ተወላጆች አካባቢ እኛ ከሌለን ኦሮሞ ይፈጇቹኋል፤ በኦሮምያም በሶማሊያም እንዲሁ በተዘጋ በር ውስጥ በተቃራኒው ዘረኝነትንና መከፋፈልን በመስበክ ንጹሃኑ ህዝብ ከፍርሃት ተነስቶ ተገዥ ደጋፊዎቹ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ መሆኑንም ያልገባቸው የዋሆች ይኖራሉ። ህወሃትንና ባህርዩን በቅጡ ለምናውቀው ወገኖች ግን ይህ ተንኮሉ ትልቅ ሚስጥር አይደለም።

የጉጅሌው ቡድን የራሱን ስልጣንና የዝርፊያ ኢኮኖሚ ኮርቻ ለማደላደል እስከረዳው ወይም የሚረዳው መስሎ እስከታየው ድረስ ደሃ ገበሬዎችን ማፋጀትን፣ ህዝብን እርስበርስ ማናከስን፣ የቂም መርዝ መዝራትን የሚያየው እንደ ፖለቲካ ጥበብ ነው።

ጉጅሌው ብልጠት መስሎት የጎሰኝነትንና የማንነትን ደመነፍስ የሚነካ ፕሮፖጋንዳ በህዝቡ ውስጥ በመንዛት ሊያደርስ የፈለገው ጥፋት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ስላልሰራለት የራሱን ሎሌዎችና ተካፋይ መደዴ ካድሬዎችን በማሰማራት የጭካኔ ስራዎችን በማካሄድ ላይ መሆኑን በብዙ መረጃዎች አረገጋግጠናል። በአሁኑ ወቅት በየቦታው የሚካሄደውን የህዝብ ማፈናቀልና ግጭት የሚመራው ራሱ ህወሃት ያሰማራቸው ካድሬዎች እንጂ በራሱ በህዝቡ ተነሳሽነት እንዳልሆነ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል። በዚህ ሳይጣናዊ አካሄድ ለምትደርሰው ለያንዳንዷ ጉዳት ሀላፊነት የሚወስደውም ራሱ ህወሃት መሆኑን ግንቦት 7 አጥብቆ ያምናል።

Tuesday, June 24, 2014

የመጨረሻዉ መጀመሪያ

በቅርቡ በተከታታይ አገር ቤት ዉስጥ ቅርጽና ይዘት እየያዙ የምናያቸዉና ማንም አሌ የማይላቸዉ ግዙፍ እዉነታዎች ሁሉም በአንድነት የሚጠቁሙት አይቀሬዉ የወያኔ መጨረሻ መጀመሩን ነዉ። ከዚህ ቀደም በግልጽ እንዳየነዉ ወያኔ አንድ ቦታ ሲሸነፍ ሌላ ቦታ እያሸነፈ በጉልበትም በተንኮልም የፖለቲካ የበላይነቱን እንደያዘ ከሃያ ሁለት አመት በላይ ቆይቷል። ወያኔ ለአመታት ህዝብን ያታለለባቸዉ የዉሸት ክምሮችና ህዝባዊዉን ትግል ወደ ኋላ ለመጎተት የተጠቀመባቸዉ ስልቶች ዛሬ ሁሉም ሙጥጥ ብለዉ አልቀዉበት ዬኔ ነዉ ብሎ በሚመካበት ትግራይ ዉስጥ ጭምር መግቢያና መዉጪያዉ የጠፋዉ የተከበበ አዉሬ መስሏል። በያዝነዉ የ2006 ዓም ሁለተኛዉ አጋማሽ ወያኔ ጨካኙን የአግአዚ ኃይል እዚህም እዚያም አሰማርቶ ከሚቆጣጠራቸዉ ጥቂት አደባባዮች ዉጭ እንደቀድሞዉ በግልጽ ወጥቶ ወያኔን የሚያሞግስ ወይም የወያኔን የሌለ ገድል የሚናገር ሰዉ የለም። በሌላ በኩል ደግሞ በተለያዩ የትግል ስልቶች ወያኔን የሚታገሉ ኃይሎች አገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ ኃይላቸዉና ቁርጠኝነታቸዉ እየጨመረ መጥቶ ወያኔ ያንን የተለመደ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃዉን እዲወስድና የራሱን የመጨረሻ እሱ እራሱ ሳይወድ በግዱ እንዲያፋጥነዉ እያደረጉት ነዉ።

የአገራችንን አንድነት ሊያላሉና ኢትዮጵያ የሚለዉን ታሪካዊ ስም ከታሪክ ዉጭ ማድረግ ከሚችሉ አደገኛ የወያኔ ባህሪዮች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ዘረኝነቱና ለአገር አንድነትና ዳር ድንበር መከበር ያለዉ የግድየለሽነት ባህሪይ ነዉ። ዛሬ ወያኔ በአራቱም ማዕዘን በየቀኑ አየጨመረና እያየለ የሚሄደዉን የህዝብ ቁጣ ለማብረድና አፋፍ ላይ ለደረሰዉ ስርዐቱ ተጨማሪ ግዜ ለመግዛት የሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ከዚሁ ከዘረኝነት ባህሪይዉ የሚመነጪ እርምጃዎች ናቸዉ። ወያኔ ዕድሜዉ ሊበረክት የሚችለዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ኃይሎች መግባባት ሲያቅታቸዉ መሆኑን ያዉቃል፤ ስለዚህም በተቻለዉ መጠን ኢትዮጵያዉያንን የሚለያዩና ግጭት ዉስጥ የሚከትቱ አጀንዳዎችን አየፈጠረ ይወረዉርልናል። ከእነዚህ አገር አጥፊ የወያኔ አጀንዳዎች ዉስጥ አንዱ ህዝብን በዘር ከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዲጋጭ ማድረግ ነዉ። ለምሳሌ በቅርቡ ደቡብ ኢትዮጵያ ዲላ ከተማ ዉስጥ በንግዱ ህብረተሰብ ላይ የነጋዴዎችን አቅምና ትርፍ ያላገናዘበ ግብር በመጫን በአንድ በኩል ነጋዴዎቹ በዞኑ አስተዳዳሪዎች ላይ እንዲነሱ በማድረግ በሌላ በኩል ደግሞ የዞኑ አስተዳዳሪዎች ነጋዴዎቹን የምትሰሙን ከሆነ ስሙን አለዚያ ክልሉን ለቅቃችሁ ሂዱ የሚል አስነዋሪና የዜግነት መብትን የሚጋፋ መልስ እንዲሰጡ በመገፋፋት በጌዲኦ ብሄረሰብና በዲላና አካባቢዉ በብዛት በንግድ ስራ ላይ በተሰማራዉ የጉራጌ ማህበረሰብ መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ ለማድረግ ሞክሯል። ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥም እንደዚሁ የጋምቤላ ህዝብ ከጋምቤላ ዉጭ ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡትን ኢትዮጵያዉያን ክልሉ የእናንተ አይደለምና ለቅቃችሁ ዉጡ ብሎ እንዲያሰገድድ በመገፋፋት በኢትዮጵያዉያን መካከል ቂምና ጥላቻ እንዲፈጠር አድርጓል። ባለፉት አምስት አመታት ወያኔ ጋምቤላ ዉስጥ ገበሬዉን እያፈናቀለ መሬቱን ለዉጭና ለአገር ዉስጥ በተለይ ለትግራይ ባለኃብቶች በርካሽ ዋጋ ማስረከቡ የሚታወስ ነዉ። ይህ ባዕዳንን ጋምቤላ ላይ እያሰፈረ ኑና እረሱ እያለ የሚለምን ነዉረኛ አገዛዝ ነዉ ዛሬ ኢትዮጵያዉያንን ከጋምቤላ ዉጡ እያለ የሚያሰገድደዉ።

‹‹ …ያኔ በምወደው የጋዜጠኝነት ሙያ እየሰራሁ እቀጥላለሁ››

በኤሊያስ ገብሩ

ጀግናው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ (ከቃሊቲ እስር ቤት)

ቅዳሜ ሰኔ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ከታች በፎቶግራፍ የምንታይ [ፎቶግራፉን ያነሳው አብነት ረጋሳን ጨምሮ] fጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዓለም የጋዜጠኞች እና የዜና አታሚዎች ማኅበር የዓመቱ የወርቅ ብዕር የ "pen Golden of freedom 2014" ተሻላሚ በመሆኑ ‹‹እንኳን ደስ ያለህ›› ለማለት ኬክ አስጋግረን ወደቃሊቲ አምርተን ነበር፡፡

ቁጥራችን መብዛቱ በቃሊቲ ያሉ ፖሊሶችን ግር ማሰኘቱ አልቀረም ነበር፡፡ ተፈትሸን ስንገባ አንድ የፖሊስ ኃላፊ አስቁመውን ‹‹የመጣችሁበትን ነገር አውቀነዋል፣ ቀለበት ይዛችኋል›› አሉን - ቆጣ በማለት፡፡ እኛ አስክንድር ነጋን እና አንዷለም አራጌን ልንጠይቅ እንደመጣን አስረዳናቸው፡፡ በዕለቱ አንዲት በቃሊቲ የታሰረች ሙስሊም እና በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስሮ የሚገኝ ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት የሚያደርጉበት ፕሮግራም በመኖሩ መረጃው ለፖሊሶች በመድረሱ ነበር ፖሊሱ እኛን እንዲጠየቁ ያስገደዳቸው፡፡ [የሙሽሮቹን ጉዳይ ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን በፌስ ቡክ ገጹ ከሁለት ቀን በፊት ጽፎታል] ገሚሶቻችን እስክንድርን አስጠራን፡፡ የተወሰኑ ደግሞ አንዷለምን በማስጠራት እየተቀያየርን ሁለቱንም ለማነጋገር እንደተለመደው አቅደን ነበር፡፡ ሆኖም ፖሊሶቹ እስክንድርን ያስጠራን ጠያቂዎች ወደ አንድ ጥግ እንድንሆን ነገሩን፡፡ የአንዷለም ደግሞ በአንድ ሌላ ጥግ ላይ እንዲሆኑ ተደረገ፡፡ እስክንድር ተጠርቶ መጣ፡፡ በወቅቱ እስክንደርን ሳየው የ18 ዓመት ወጣት መስሎ ታየኝ፡፡ ጂንስ ሱሪ ከእጅጌ ጉርድ ሸሚዝ ጋር አድርጓል፡፡ ፊቱ ላይ ተፈጥሯዊ ወዙ ያንጸባርቃል፡፡ እውነተኛ ውስጣዊ ፈገግታውን ለሁላችንም ቸረን፡፡ በሽቦ ውስጥ አሳልፍን ጣቶቹን በየተራ ጨበጥናቸውና በዕለቱ ስለተደረገው የአጠያየቅ ሁኔታ ነገርነው፡፡ ‹‹ለምን እንዲህ ይደረጋል? በማለት አጠገቡ የነበረውን ፖሊስ ቆጣ ብሎ ጠየቀው፡፡ ‹‹ሰው ስለበዛ!›› የሚል አጭር ምላሽ ፖሊሱ ሰጠ፡፡ እስክንድር ደጋግሞ ጥያቄውን አቅርቦ ነበር፡፡ ‹‹በቃ የመጠየቂያዋ ጊዜ አጭር በመሆኗ ተወው›› አልኩት፡፡ ‹‹አይ! መሆን የለበትም፣ ኃላፊዎቹን ስመለስ አነጋግራለሁ›› ካለ በኋላ ከጠያቂዎቹ ጋር መጫወት ጀመረ፡፡

Saturday, June 21, 2014

ድርብ አኃዝ ዕድገት ወይስ ድርብ ድህነት?

በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ልማት ትምህርት ክፍል ሥር የኢኮኖሚ ጥናት የሚያካሂደው የኦክስፎርድ የድህነትና የሰብዕ ልማት ማዕከል (The Oxford Poverty and Human Development Initiative (OPHI)) ሰሞኑን ባወጣው የ2014 የጥናት መረጃ ደሃ ከሚባሉት አገራት ዝርዝር ኢትዮጵያ ከመጨረሻው ሁለተኛ መሆኗን ገለጸ፡፡ የጥናቱ ዘገባ ኢህአዴግ በየጊዜው ከሚያቀርበው የዕድገት ስሌት ጋር በግልጽ የሚጋጭ መሆኑ ተነገረ፡፡

በዓለማችን በሚገኙ 108 በማደግ ላይ ባሉ አገራት በየጊዜው ጥናት የሚያካሂደው ማዕከል ጥናቱን በሚያካሂድበት ጊዜ 10 መለኪያዎችን እንደ ግብዓት እንደሚጠቀም ይናገራል፡፡ እነዚህም በሦስት ዘርፎች የተጠቃለሉ ናቸው – ትምህርት፣ ጤና እና የኑሮ ሁኔታ፡፡ በተለይ በኑሮ ሁኔታ ሥር ኤሌክትሪክ፣ ጽዳት፣ የሚጠጣ ውሃ፣ የንብረት ባለቤትነት፣ ወዘተ በግብዓትነት ተወስደዋል፡፡

በዚህ ዓይነት እኤአ ከ2002 እስከ 2011 ድረስ ያለውን መረጃ በማጠናቀር በወጣው ዘገባ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ100 ሰዎች መካከል 87ቱ ድሃ ተብለው የሚጠሩ ሲሆን 58ቱ ሰዎች ግን መናጢ ደሃ ተብለው የሚጠሩ መሆናቸውን ይናገራል፡፡ ድህነቱ በገጠር እጅግ የከፋ እንደሆነ በመጠቆም ከ100 ሰዎች ውስጥ 96ቱ ደሃዎች እንደሆኑ፤ በከተሞች አካባቢ ግን ከ100 ሰዎች መካከል 46ቱ ደሃ ተብለው የሚጠሩ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአጠቃላይ የአገሪቷ ክፍሎች ከ100 ሰዎች መካከል 31ዱ በቀን ከ20ብር በታች በሚገኝ ገቢ እንደሚኖሩ ጠቁሟል፡፡

ድህነቱ የከፋባቸው “ክልሎች” ብዙም ልዩነት እንደሌላቸው የሚያሳየው የጥናቱ ዘገባ ከሁሉም ግን ሶማሊ በደሃነት ቀዳሚ ነው፡፡ በጥቂት ነጥብ ልዩነት ኦሮሚያ፣ አፋር፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል፡፡ በእነዚህ አምስት ክልሎች ከ100 ሰዎች ውስጥ 90 እና ከዚያ በላይ የሚሆኑት ደሆች መሆናቸው በጥናቱ ተዘርዝሯል፡፡

Friday, June 20, 2014

ቀና ብለን የምንሄድበት ጊዜ አየመጣ ነው! ጎበዝ ተነሳ!

ጉጅሌዎቹ አይገባቸውም እንጂ የኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች የለውጥን ደመና ኣርግዘዋል። ወንዞችም ተራሮችም የለውጥ ማዕበል ማቆብቆቡን አያበሰሩ ናቸው። የቀደሙት ገዢዎች መረጃ የሚያገኙት እረኛ ምን ይላል ብለዉ እየጠየቁ ነበር። የአሁኖቹ አገር አጥፊ ገዢዎች ምሳሌ ያደረጉት ካድሬዎቻቸውን ብቻ ሆነ እንጂ ዛሬም የአገራችን እረኞች የለውጥን መምጣት በሚያምር ቅላጽያቸው አያንጎራጎሩ እንዲህ አያሉን ነው፣

የሀገሬ ጉብል የሰማውን እንጃ

የጎንደሬው ጉብል የሰማውን እንጃ

ከብቱን አየሸጠ ገዛ ኣሉ ጠብመንጃ።

የወለጋው ጉብል የሰማውን እንጃ

ቡናውን ሻሽጦ ገዛ ኣሉ ጠብመንጃ።

መልእክቱ ግልጽ ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች አገራቸውን በክቡር ደማቸው ሊታደጓት ቆርጠው በመነሳት ወያኔን በማስወገድ የሀገራቸው ባለቤት ለመሆንና ያልተከፋፈለች ውብ ኢትዮጵያን ማየትን ለማረጋገጥ ጥርጊያውን መጀመራቸው ነው።

ላለፉት ፵ አመታት አምባገነኖች ባደረሱብን ጭቆና እና እንግልት የተነሳ የራሳችን የሆነ መንግሥት ሳይኖረን አንገታችንን ደፍተን ጀግኖቻችንን ስንገብር ኖረናል። በተለይም ባለፉት ፪፫ አመታት ጉጅሌዎቹ በአራት ኪሎ ከነገብን ጀምሮ በአንድ ላይ አንዳንቆም በማድረግና እና አርስ በራሳችን በማጋጨት ሲያባሉን ኖረዋል።

Wednesday, June 18, 2014

‹‹ይህ ሽልማት የእኔ ብቻ አይደለም፣ የእናንተም ነው›› እስክንድር ነጋ

በኤልያስ ገብሩ ጎዳና

‹‹ይህ ሽልማት የእኔ ብቻ አይደለም፡፡ የእናንተም ነው፡፡ …›› ‹‹በእስር ላይ የምትገኙ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ›› 

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

‹‹አሁን ደስተኛ ነኝ›› ‹‹እስክንድርን ምግብ ማብሰል እያለማመድኩት ነው››

አቶ አንዷለም አራጌ

ከትናንት በስትያ ሰኔ 03 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ከቅርብ ጓደኛዬ እና የሙያ ባልደረባዬ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት [እስር ቤትም ነው] አምርተን ነበር- ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆኑትን አቶ አንዷለም አራጌን ለመጠየቅ፡፡ የተለመደውን የፖሊስ ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ስንዘልቅ የሰማያዊ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፈ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ፣ አቶ ሳሙኤል የተባሉ አባልና የ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እስክንድርን ሊጠይቁ ቀድመውን ደርሰው ነበር፡፡

…እስክንድርን እና አንዷለምን አስጠራናቸው፡፡ ሁለቱም ሲያዩን ደስ አላቸው፡፡ በተለይ በተለይ የእስክንድር ፈገግታ በጣም ደማቅ ነበር፡፡ ተከፋፍለን ከሁለቱም ጋር ሃሳቦችን መለዋወጥ ጀመርን፡፡

እስክንድር በዓለም የጋዜጠኞች እና የዜና አታሚዎች ማኅበር የዓመቱ የወርቅ ብዕር የ “pen Golden of freedom 2014″ ተሸላሚ በመሆኑ ‹‹እንኳን ደስ ያለህ›› አልኩት፡፡ ‹‹አመሰግናለሁ፡፡ ትናንት አንድ ልጅ ሊጠይኝ መጥቶ ነግሮኛል›› ካለን በኋላ ደግመን ስለሽልማቱ በጋራ ሃሳብ መለዋወጥ ቀጠልን፡፡ እስክንድር ሽልማቱ አዲስ መሆኑን አላወቀም ነበር፡፡

ለጊዜ ቀጠሮዉ ሌላ ጊዜ ቀጠሮ


ፍቃዱ አንዳርጌ

በአንድ ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር የዋለን ሰዉ የያዘዉ አካል ወዲያዉኑ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ ፍርድ ቤት የመቅረቡ ዋና አብይ ጉዳይ የእስሩን ህጋዊነት ለማረጋገጥ ከመሆኑም በተጨማሪ ቀጣዩን ሂደት ለአቅጣጫ ለማስያዝ ነዉ፡፡ ተጠርጣሪዉ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ ጉዳዩ የምርመራ ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ሲያምን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊፈቅድ ይችላል፡፡ የጊዜ ቀጠሮ መሰረተ ሃሳብ የሚጀምረዉ ከዚህ ደረጃ ላይ ነዉ፡፡ የጊዜ ቀጠሮ ቀጥተኛ ትርጉም በህጉ ተገልፆ የማናገኘዉ ሲሆን በተለምዶ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች ለምርመራ የሚቆዩበትን ተጨማሪ ጊዜ በተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ እያልን እንጠቀምበታለን፡፡

የኢፌዲሪ ህግ መንግስት አንቀፅ 19(4) የተያዙ ሰዎች ስላለቸዉ መብት ፍርድ ቤት የተያዙ ሰዎች በጥበቃ ስር እንዲቆዩ ወይም ምርመራ ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ ሲጠየቅ አስፈላጊ በሆነ መጠን ብቻ ሊፈቅድ እንደሚችል ይናገራል፡፡ ይህ የህገ መንግስት ድንጋጌ ጊዜ ቀጠሮ ሊፈቀድ የሚገባዉ አስፈላጊ በሆነ መጠን ብቻ ነዉ በማለት ሲያስቀምጥ የተጠየቀዉን ሁሉ ስለተጠየቀ ብቻ መፍቀድ በተያዘዉ ሰዉ መብት ተቃራኒ መቆም መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ የምርመራ ጊዜ ፈቃድ አሰጣጥ አሁን ባለዉ የህግ ስርዓት በሁለት መልኩ ከፍሎ ማየት የሚቻል ሲሆን በተሻሻለዉ የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ የሚታዩ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግን መሰረት አድርገዉ እና በፀረ-ሽብርተኝነት የሚታዩ ጉዳዮች ናቸዉ፡፡በሁለቱም ህጎች ጊዜ ቀጠሮን የሚሰጡት በማረፊያ ቤት ለምርመራ የሚቆይበት ጊዜ በማለት ነዉ፡፡ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህጉ ለአንድ ጊዜ ምርመራ አስራ አራት ቀን ጊዜ ያለገደብ የተቀመጠ ምርመራዉ እስካላለቀ ድረስ ጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ መኖርን የሚፈቀድ ነዉ፡፡ በፀረ-ሽብርተኝነት ህግ የአንድ ቀጠሮ የምርመራ ጊዜ ሃያ ስምንት ቀን ሆኖ በአራት ወር የተገደበ ነዉ፡፡

Sunday, June 15, 2014

የኑረዲን ሃሰን ደም በከንቱ አይቀርም

ጉጅሌዎቹ ኢትዮጵያን መግዛት ከጀመሩ ዘመን ጀምሮ በአገራችን የንፁህ ሰው ደም ሳይፈስ የዋለበት ቀን የለም። ኢትዮጵያችን በየቀኑ የንፁህ ሰው ደም የሚፈስባት አገር ሁናለች። ዜጎችም ይሄን የለመዱት ስለሆነ ሰው ሞተ ሲባል ብዙም አይደነቁም። ጉጅሌዎቹ ደግሞ አንድ ያለፈባት ብሂል አለቻቸው እንዲህ የምትል፤

ግደሉ ግደሉ ሰው መግደል ይበጃል፤

ሰው ያልገደለ ሰው ሲሄድ ያንጎላጃል።

ይህች የአንድን ማህበረሰብ የስነ ልቦና ቀውስ ደህና አድርጋ የምታሳይ ቅኔ የህወሃቶች ስንቅና ትጥቅ ነች። ይህችን ቅኔ ታጥቀው በየደረሱበት የንፁህ ደም ሲያፈሱ የሂሊና ወቀሳ የለባቸውም። እዚህም ይገድላሉ፤ እዚያም ይገድላሉ። ለህወሃቶች ሰው መግደል ክፉ ነገር አይደለም። ሰው መግደል ለስልጣን የሚያበቃ፤ ስልጣን ላይም እስከ ፍፃሜው የሚያቆይ የጎበዝ ምግባር ነው የሚል የማይናወፅ እምነት አላቸው። ይህን ዕምነታቸውንም የገለጡበትን መንገድ ትንሽ ወደ ኋላ ሂዶ በሃውዜን ህዝብ ላይ ያስፈፀሙትን ጭፍጨፋ ማስታወስ በቂያችን ይሆናል።

ጉጅሌዎቹ ጥልቅ በሆነ የስነ ልቦና ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ። ከግል ህይወታቸው ጀምሮ እስከ ጨበጡት የስልጣን እርከን ድረስ ንፅህና የጎደላቸው፤ በንፁሃን ደም እጃቸው የተጨማለቀ ነው። ይህ ነውራቸውም ሁሉንም እንዲፈሩ፤ በሁሉም እንዲደነግጡ አድርጓቸዋል።ከዚህ ፍርሃትና ድንጋጤም ለመላቀቅ የተዘፈቁበት የወንጀል መዓት የሚያስችላቸው አልሆነም። እነርሱም ከጥፋታቸው ተምረው እንደ ሰው ልጅ ለማሰብ ፍላጎቱ የላቸውም። የጉጅሌዎቹ የልብ ድንደና የመፅሃፍ ቅዱሱ የፈርዖንን ልብ ድንደና ይመስላል። የፈርዖንን የመጨረሻ ታሪክ ያየ ግን ልቡን ከማደንደን ይልቅ የህዝቡን ጩኽት መስማትን ይመርጥ ነበር። ይሄም ቢሆን ብልህነትን ይጠይቃል።አገራችን ከተደቀኑባት ብርቱ ተግዳሮቶች መካከል ዋነኛው ጉጅሌዎቹ ብልህነት ያልፈጠረባቸው ሁሉንም በጠብ-መንጂያ እናሸንፈዋለን ብለው ከልባቸው ማመናቸው ነው። ይሄም እምነታቸው ነው በህግ ጥላ ሥር ያሉትን እንኳ ሳይቀር ቀጥቅጠው እንዲገድሉ የሚያደርጋቸው።

ጄኔራል ሰዓረና ጋዜጠኛ እስክንድር


ሰኔ 1 ቀን 1997ዓ.ም፤ በአዲስ ከተማ ት/ቤት የተጀመረው ተማሪዎችንና ንጹሃን ዜጐችን በግፍ የመግደል እርምጃ ተከትሎ አብዛኛው ባለስልጣናት ልጆቻቸውን ከየት/ቤቱ በአጃቢ ያስወጡ ነበር። ወደ ካቴድራል ት/ቤት በሁለት ኮብራ ተጭነው የተላኩ 20 ልዩ የፌዴራል ፖሊሶች የጄ/ል ሰአረና የጄ/ል ብርሃነ (ወዲ መድህን) ሴት ልጆችን አጅበው ሄዱ። ሁለቱ ሴት ልጆች በማግስቱ አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ተመቶላቸው ዓርብ ሰኔ 3 ቀን በረሩ። የብዙ ባለስልጣናት ልጆች በተመሳሳይ እንዲወጡ ተደረገ። ..29ሺህ የአሜሪካ ዶላር በተርም እየተከፈለላቸው መማር ቀጠሉ። የአዜብ ልጅና የእህቷ ልጅ፣ (በነገራችን ላይ አርአያ መኮንን ይባላል፤ በ1995ዓ.ም ቦሌ ከሩዋንዳ ፊት ለፊት ጥቂት ገባ ብሎ አዜብ ለዚህ ወጣት በ7 ሚሊዮን ብር ቪላ ቤት ገዝታ በስጦታ አበርክታለች። የቪላው ኪራይ ሂሳብ በስሙ ባንክ ይገባለታል) ..የአርከበና ስብሃት ልጆች በቨርጂኒያ፣ የሽፈራው ጃርሶ ልጆች በካሊፎርኒያ፣ የፖሊስ ኮሚሽነር የነበረው ወንጀለኛውና 5ሚሊዮን ዶላር ሰርቆ የወጣው ተስፋዬ መረሳ ልጆች በኒዮዎርክ….ወዘተ በተቀማጠለ ኑሮና በውድ ክፍያ መማር ያዙ። ባለፈው አመት በነርስ የተመረቀችው የጄ/ል ሰአረ ልጅ ሐመልማል ሰዓረ የምርቃት ፕሮግራም ላይ ጄኔራሉ ተገኝተው ነበር።…ወደ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንለፍ። እስክንድር በላባቸው ሰርተው ሃብት ካፈሩ ጥሩ ቤተሰቦች የተገኘ ልጅ ሲሆን የተማረው በሳንፎርድ ት/ቤት ነው። ከዚያም አሜሪካ መጥቶ ትምህርትና ህይወቱን ቀጠለ። “አገር አማን” ብሎ በዘመነ ኢህአዴግ አገር ቤት ገባ።

Saturday, June 14, 2014

ማን ይንገርልን – ማን ይመስክርልን

በጸጋዬ ገብረ መድኅን አርአያ

እንደ ልጄ የምቆጥረውና ከበኩር ልጄ ከዩሐንስ ጋር ያደገው ሳምሶን በሕክምና ኮሌጅ ይማር በነበረበት ዘመን በምሽቱ ሰዓት ላይ የ‹‹ፈገግታ ጊዜ›› በምንለው ግማሽ ሰዓት ያጫውተን ነበር፡፡ አዎን ሕይወት ውጥርጥር ባለበትና ጭንቀት ከቀበሌ ከሚወረወር ቀስት፣ ጭንቀት ከየካድሬውና ከየፖለቲካው ኅቡዕ ድርጅት ከሚወረወር ሌላ ቀስት፣ ጭንቀት፣ ከመስሪያ ቤት ጭንቀት፣ ከበላይ አካል ጭንቀት፣ ከበታች አካል ጭንቀት፣ ጭንቀት —- አንድ የድሮ ማስታወቂያ ሚኒስትር እንዳሉት ከላይ ከመሳፍንቱና ከመኳንንቱ በሚለቀቅብህ እሳት፣ ከታች ከሕዝቡና ከሠራተኛው ከሚነድድብህ እሳት የገና ዳቦ ትሆናለህ፡፡ ስለዚህ ‹‹በታይም አውት›› (ፋታ ልበለው) መልክ ከሳሚዬ ጋር የማደርገው የግማሽ ሰዓት ውይይት (ጨዋታ) ለእኔ “ማሳጅ” ነበር፡፡ መታሻ!

እንደ ወትሮው የዛሬው ወጋችን በክፍል ውስጥ ስለነበረው አጋጣሚ ነበር፡፡ በዚያው ዕለት በሕክምናው ኮሌጁ የመጀመሪያው ሰዓታት (ሦስት) አስተማሪው ዶክተር አሥራት ወልደየስ ነበሩ፡፡ “ዛሬ የማስተምራችሁ ስለ ጦር ሜዳ አነስተኛ የቀድዶ ሕክምና ነው” ይላሉ፡፡ አከታትለውም የጦር ሜዳውን “ሰገሌ እንበለው” ይላሉ፡፡ ይቀጥላሉ፡፡ ተፋላሚዎች በወሎው ጦር በኩል “ንጉሥ ሚካኤል” —- ይሉና ቆም ብለው ይመለከቱ ጀመር፡፡ እንዳጋጣሚ ከፊት ለፊት የተቀመጠውን አንዱን ተማሪ “ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስን ታውቃቸዋለህ? ብለው ይጠይቁታል፡፡ “አንተዋወቅም” ይላል፡፡ ሁለተኛው ጊዜ ሳይፈጅ ወደ መርካቶ ሲኬድ መግቢያው ላይ ድልድይ ያላቸው ሰውዬ ናቸው” ይላቸዋል፡፡ ሦስተኛው በሙሉ የአዋቂነት ኩሩ ስሜት ‹‹የአጤ ኃይለሥላሴ ቅድመ አያት ናቸው፡፡ ከአያቴ ጋር በጣም ይተዋወቁ ነበር›› አለ፡፡ ሌላው የፕሮፌሰር አሥራትን ከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት የበለጠ ለማጋጋል ፈለገና ይልቁንም እሳቸው በዛሬው ፕሮግራማቸው ስለጦር ሜዳ ሕክምና ለማስተማር የተዘጋጁ መሆናቸውን ስለተናገሩ “ኢትዮጵያ ከእንግሊዞች ጋር በተዋጋች ጊዜ የጦር መሪ የነበሩት አጭር፣ ፉንጋ ሰው ነበሩ፡፡ አጤ ኃይለ ሥላሴ ሠላሳ ዓመታት አሠሩአቸው” ይላል፡፡ ፕሮፌሰሩ ትንሽ ይደንቃቸውና “ኢትዮጵያ ከእንግሊዞች ጋር የተዋጋችው ትራፋልጋር ላይ ነበር ወይስ ወተርሉ ላይ ነበር?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ አራዳው ተማሪ “የለም ሰገሌና አንኮበር ላይ ነበር” ይላቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ እንግሊዞች በወተርሉና በትራፋልጋር ላይ ጦርነት የገጠሙት ከፈረንሳዩ መሪ ከናፖሊዮን በናፖርት ጋር ነበር፡፡) ፕሮፌሰሩ ቀልዱንም ሞክረውት ጥርሳቸው ሊላቀቅ አልቻለም፡፡ በጎጃም ቅኔ ቤት የሚወራ ጨዋታ ነበር፡፡

አንዷን ቅዳሜ በፍርድ ቤት (ጽዮን ግርማ)

ወጣቶቹና- ቅዳሜ፣ አንዷን ቅዳሜ በፍርድ ቤት

ጽዮን ግርማ (tsiongir@gmail.com)

 ለአብዛኛው ወጣት አዲስ አበባ ላይ ‹‹ቅዳሜ›› ትርጉም አላት፡፡ የሣምንቱን የሥራ ቀናት በየፈርጁ ያሳለፈው ኹሉም ወጣት ‹‹ቅዳሜ››ን ደግሞ እንደየ ምድቡ ይውልባታል፡፡ እንደሰማኹት ከኾነ ለዞን ዘጠኝ አባላትና ጓደኞቻቸውም ቅዳሜ ልዩ ቀን ናት፡፡ ለወጣቶቹ አብሮነት የጡመራ መድረኩ ቢያግዛቸውም ከዛ በላይ ግን ጓደኝነታቸው ቤተሰባዊነትን ፈጥሮላቸው አብዛኛውን ቅዳሜ እንደየ ቅርበታቸው አብረው ያሳልፋሉ፡፡

አብረው እስረኛ ይጠይቃሉ፣የታመመን ያጽናናሉ፣በጋራ ምሳ ይቋደሳሉ፣የተለየ ዝግጅት ካለም አብረው ይሳተፋሉ፡፡ ከዚህ የተረፈ ጊዜ ካላቸው ደግሞ ፈጣንንና ነጻ የገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት በሚገኝበት ሆቴል ገብተው ዓለም በምን ኹኔታ ላይ እንዳለች ለመከታተል ይሞክራሉ፡፡ አገሪቷ ውስጥ ባለው ከፍተኛ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ችግር ምክንያት አብዛኛው ጋዜጠኛና ጥቂት ወጣቶች የእነዚህ ትልልቅ ሆቴሎች ገመድ አልባ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው፡፡ በቅዳሜ ወደእነዚህ ሆቴሎች ጎራ ያለ ከጦማሪያኑ ወይም ከጋዜጠኛ አንድ ሰው ሊያገኝ ይችላል፡፡ በቃ ሲገናኙ ሰላም ተባብለው መቀላቀል ነው፡፡እናም በአንድ ጉዳይ ጨዋታ ጀመራል፡፡ አብዛኛው ጨዋታ በአገር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሊኾን ይችላል፡፡ ኮምፒዩተሮቻቸውን እየነካኩ ስለ አገራቸው ግድ ያላቸውን ይነጋገራሉ፣ይከራከራሉ አሊያም ይጨቃጨቃሉ፡፡መሄጃው ሰዓት የደረሰበት ደግሞ ተሰናብቶ ይሄዳል፡፡በእነዚህ ሆቴሎች በቀጠሮ የሚገናኝ ሰው የለም፡፡‹‹የት ነህ? የት ነሽ?›› የሚለው የስልክ ጥያቄም ለመገናኘት በቂ ነው፡፡

Thursday, June 12, 2014

የወያኔ ግፍ ለከቱን አልፏል!

የወያኔ ጉጅሌ ራሱ ከሳሽ፣ ፖሊስና ዳኛ ሆኖ በሚገዛት ሀገራችን ውስጥ የሚያካሂደው ግፍ አንድ ህዝብ ሊሸከመው ለሚችለው በላይ ሆኗል።

የወያኔ ሹማምንትና በዘር ለዝርፊያ የተሰማራው ድርጅታቸው በቅርቡ ደግሞ ስዘርፍ አያችሁኝ በሚል ቁጣ ከአንደበታቸው በላይ ምንም ባልታጠቁ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ከአካሄደው ጅምላ ጭፍጨፋ አልፎ ግለሰብ ተማሪዎችን በማሳደድ ሰቆቃ መፈጸሙን ቀጥሎበታል። በዚህ ሰአት በርካታ ተማሪዎች በታወቁና ባልታወቁ እስር ቤቶች ታጉረዋል። ብዙዎቹ ከትምህርት ገበታ ካላንዳች ጥያቄ ተባረዋል እየተባረሩም ይገኛሉ።

ከወያኔ ግፎች ሁሉ በእጅጉ የሚዘገንነው ሌሎችን በመወንጀል ማሰቃየትና መግደል በፈለገ ቁጥር ራሱ ወንጀል ከፈጸመ በኋላ ወንጀሉን በሌሎች ላይ ለማመኻኘትና ለመቅጣት የሚጠቀሙበት የሃሳብ ዘዴ ነው።

በአለምያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተሰበሰቡበት አዳራሽ ውስጥ የደህንነት አባሎች ቦንብ አፈንድተው ጉዳት ካደረሱ በኋላ የሚፈልጓቸውን ወጣቶች ቦንብ ሲያፈነዱና ሲጠምዱ ያዝናቸው በማለት ከዚህ በፊት በዊክሊክ መረጃ እንደተለቀቀው የተለመደ በሰው ልጆች ላይ ሰቆቃ ይፈጽማሉ። ሌላው ቀርቶ ቦምብ አፈነዱ ተብለው የተከሰሱት ተማሪዎች በገዛ ጓደኞቻቸው ላይ ቦምብን የሚወረውሩበት ምክንያት የላቸውም።

ወያኔ ተማሪዎቹን አረመኔና እብድ ለማስመሰል የሰራው የራሱ ትንሽዪ ድራማ ወይም ሌላኛው አኬልዳማ መሆኑ ግልጽ ነው።

ወያኔ ደግሞ እንዲህ አይነት የወሮበላ ስራ እንደሚሰራ እንዳላዪ የሚያዩት ለጋሽ ሀገሮች ሁሉ ያጋለጡት፣ የሚያውቁት የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሰንብቷል።

የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን ማን ይፈራቸዋል? (ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የእስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችን…የዴሞክራሲያዊ መብት የመጠቀም የትግል እንቅስቃሴ ሲመለከት እንደሚዳቋ እየበረገገ የሚስፈነጠረው ማን ነው?

የኢትዮጵያ የነጻው ፕሬስ እና ጦማርያን ቁንጮ የሆነው እስክንድር ነጋ ሀሳቡን በነጻ በመግለጹ ብቻ በአምባገነኑ የወሮበላ ቡድን ስብስብ የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት የ18 ዓመታት እስር ተበይኖበት በገዥው አካል የማጎሪያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ሟቹ መለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ እስክንድር ነጋ በቁጥጥር ስር እንዲውል እና የ18 ዓመቱ የሸፍጥ እስራት እንዲበየንበት ተደርጓል፡፡ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ማናቸውም ጋዜጠኞች የበለጠ እስክንድር ነጋን ይፈራዉና ይጠላው ነበር፡፡ ዝሆን አይጦችን “ይፈራል” ከሚለው ኢ-ስነ አመክንዮ አንጻር በተመሳሳለ መልኩ መለስም እስክንድር ነጋን እንደጦር ይፈራው ነበር፡፡

በቅርቡ እስክንድር ከማጎሪያው እስር ቤት ለ8 ዓመት ልጁ ለናፍቆት እንዲህ የሚል ግልጽ ደብዳቤ ጽፏል፣ “እንዲያው ሁኔታውን ሳየው እያለሁ የሌለሁ የዘፈቀደ አባት ሆኛለሁ፣ ምክንያቱም በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፈረንሳዮች ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍቅር እያሉ ደጋግመው ይጠሯቸው የነበሩትን ሶስት ቀላል ቃላትን በመውሰድ እኔም በሀገሬ ነጻነት፣ እኩልነት እና ፍቅር እንዲሰፍን በማሰብ እነዚህን ቃላት በማስተጋባቴ ነው በሸፍጠኞች ለእስር የተዳረግሁት“ ብሏል፡፡ እስክንድር ለነጻነት፣ ለእኩልነት እና ለአብሮነት ፍቅር ጦማሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ለእኔ የጀግናዬ ተምሳሌት የሚሆነው!

የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ቀንዲል ጀግናዋ የ34 ዓመቷ ወጣት ርዕዮት ዓለሙ በተመሳሳይ መልኩ በአቶ መለስ ዜናዊ የ14 ዓመታት እስር በይኖባታል፡፡ ይህች ጀግና ወጣት በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ “እውነት ተናጋሪዋ ኢትዮጵያዊት እስረኛ” በመባል ትታወቃለች፡፡ ርዕዮት ለእስር የተዳረገችው የግድብ ፕሮጀክት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን በተመለከተ በገዥው የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ጠንካራ ትችት በማቅረቧ እና በቅርቡ በህይወት የተለዩት የሊቢያ አምባገነን መሪ ሙአማር ጋዳፊ እና መለስ ዜናዊ ከአንድ ባህር የሚቀዳ ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው መሆናቸውን በይፋ በመግለጿ ነው፡፡ ርዕዮት በእስር ቤት ተዘግቶባት እና አፏን ተሸብባ ለመቀመጥ ባለመፍቀድ በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ ስልጣኖቻቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በህገወጥነት ለሚጠቀሙት ህገወጦች እና ትዕቢተኞች እውነት እውነቱን እንዲህ በማለት እቅጬን ተናግራለች፣ ”የተሻለች ኢትዮጵያን ለማየት እኔ በግሌ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ማበርከት አለብኝ የሚል እምነት አለኝ፣ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ኢፍትሀዊነቶች እና ጭቆናዎች ተንሰራፍተው ስለሚገኙ እነዚህን እኩይ ተግባራት በምጽፋቸው ትችቶቸ ማጋለጥ እና ከንቱ መሆናቸውን መቃወም አለብኝ… ለዚህ በጎ ዓላማ በድፍረት ትግል በማካሂድበት ወቅት ሊያስከፍለኝ የሚችለውን ዋጋ ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ“ በማለት ከእስር ቤት አፈትልከው በሚወጡ የእጅ ጽሁፎቿ ገልጻለች ጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ፡፡ በማይበገረው እና በማይንበረከከው ትክክለኛ የጽናት አቋሟ ምክንያት ገዥው አካል ሰብአዊነት የሚባለውን ክቡር ነገር በመደፍጠጥ የህክምና አገልግሎት እንዳታገኝ ቅጣት ጥሎባታል፡፡ መቀመጫውን ሎንዶን ያደረገ የህግ መከላከል የተነሳሽነት ሜዲያ/Media Legal Defense Initiative የተባለ ተቋም በአልጃዚራ ባቀረበው ዘገባ መሰረት ርዕዮት “በሰውነት አካሏ ላይ የተከሰተ እብጠት የተገኘ ቢሆንም ተገቢ የሆነ ህክምና እየተሰጣት እንዳልሆነ ግልጽ አድርጓል፡፡ ምንም ዓይነት የሰመመን መስጫ ማደንዘዣ ሳይሰጣት በጡቷ ላይ የቀዶ ህክምና ስራ በማከናወን የቀዶ ህክምና መስፊያ ክሩ ከጡቷ ሳይወጣ ከዓመት በላይ ከመቆየቱም በላይ ከደህረ ቀዶ ህክምናው በኋላም ቢሆን ተገቢ የሆነ ህክምና የተሰጣት አይደለም“ ብሏል፡፡ ለእኔ ርዕዮት የጀግና ተምሳሌታዬ ናት!

Wednesday, June 11, 2014

የፌስ ቡክ ላይ ተሳዳቢዎች – በታደሰ ብሩ

ናይ ፌስቡክ ተፃረፍቲ

መንደርደሪያ

ፌስ ቡክ ላይ ህወሓትን (ወያኔን) የሚተች ጽሁፍ ሲወጣ ስድቦችን “በብርሃን ፍጥነት” የሚያዥጎደጉዱ ሃያ ያህል ሠራተኞች ሬድዋን ሁሴን  ቢሮ ውስጥ መኖራቸውን ሰምቼ ነበር። ይህ ራሱ እየደነቀኝ እያለ ሰሞኑን ሌሎች ዜናዎች ተከታትለው መጡ።

በፌስ ቡክና መሰል ማኅበራዊ ሚዲያዎች ለሚቀርቡበት ትችቶች ፈጣን የስድብ ምላሽ የሚሰጡለት 235 “ባለሙያ ተሳዳቢዎችን” ኢህአዴግ አሠልጥኖ ማስመረቁ ከግንቦት 27 ቀን 2006 ዓም የኢሳት ዜናሰማሁ።  ዜናው እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ኢሳት በነበረው መረጃ  ሰልጣኞቹ 2, 350 የፊስ ቡክ፣ የቲውተር እና የብሎግ አካውንቶችን ከፍተዋል።

የኢሳት ዜና ከተሰማ ጥቂት ቀናት ቆይታ በኋላ ደግሞ 300 ብሎገሮች ለተመሳሳይ ተግባር  በባህር ዳር ሠልጥነው የመመረቃቸውን ዜና ሴቭ አዲና የተባለው የፌስ ቡክ ባልደረባዬ አጋራን።  እሱ ባለው መረጃ መሠረት ደግሞ  ሠልጣኞች 3 000 የፌስ ቡክ አካውንቶች ከፍተዋል።

ህወሓት ይህን ልምድ ከየት አመጣው? ይህ ነገር የት ያደርሰናል? ለዚህ ምላሻችን ምን መሆን ይኖርበታል? ይህ አጭር ጽሁፍ እነዚህ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያገለግሉ ውይይቶችን ለመቀስቀሻነት የሚረዱ ሀሳቦችን ይወረውራል።

የቻይና 50 ሣንቲም ፓርቲ

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በኦክቶበር 2004 አንድ የቻይና የክልል የሕዝብ አስተዳደር ቢሮ በማኅበራዊ ሚዲያ የደረሰበት ወቀሳ ለመቋቋም ከመንግሥት ጎን ወግነው የአፀፋ አስተያየቶችን የሚጽፉ ሠራተኞችን ቀጠረ። ይህም የተቀጣሪ የማኅበራዊ ሚዲያ ተሳዳቢዎች ጅማሮ ሆነ። በአስተዳደሩ ላይ ወቀሳ ያቀርቡ የነበሩ ሰዎች በተራ ስድቦች ተሸማቀው ዝም ማለታቸውን የተመለከቱ ሌሎች የአስተዳደር ቢሮዎችን ይህ ልምድ ለእነሱም እንደሚጠቅም አስተዋሉ።

Tuesday, June 10, 2014

በአንድነት እና በመኢአድ መካከል የተደረገው ውህደት በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ (የሰሜን አሜሪካ የአንድነት የድጋፍ ማህበራት)

ተሰናክለን ነበር፤ አሁን ግን ጸንተናል!

«ዉጊያዉን ተሸነፍን እንጂ ጦርነቱን አልተሸነፍንም» ነበር ያሉት የፈረንሳዩ የ2ኛው ዓለም ጦርነት መሪ፤ ጀነራል ቻርለስ ደጎል፣ አገራቸው በናዚዎች ሥር በወደቀች ጊዜ። ልክ እንደ ዉትድርናዉም፣ በሰላማዊ ትግል ዉስጥ መሸነፍ፣ መዉደቅ፣ መሳሳት አለ። መነሳትም እንዲሁ፡፡ ታላቁ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ እንዳሉትም፤ «በሕይወት ውስጥ ትልቁ ነገር ፈትሞ አለመውደቅ ሳይሆን፤ በወደቁ ቁጥር መነሳት ነው»

በአገራችን የሰፈነዉን አምባገነንነት በመቃወምና በአገራችን ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ ላለፉት አያሌ አመታት ትእግስት አስጨራሽ ትግል ቢደረግም፤ የተደረጉ ጥረቶች የተፈለገውን ዉጤት ሳያመጡ ቀርተዋል፡፡

በተለይ በምርጫ ዘጣና ሰባት ወቅት፣ በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚያነቋንቅ ትልቅ ሥራ ተሰርቶ የነበረ ቢሆንም፣ ቅንጅትን በመሰረቱ ድርጅቶች መካከል ልዩነቶች ስለተፈጠሩ፣ የቅንጅት አመራር አባላትም በተለያዩ ምክንያቶች ስለተከፋፈሉ፣ የአገዛዙ አፈናና የረቀቀ ከፋፋይ ሴራ ተጨምሮበት፣ ያኔ የነበረዉ የቅንጅት አብዮት እንዲቀዘቅዝ ሆኗል፡፡። ይህም የአምባገነኖች ደስታ ሆኖ ቆይቷል።

ነገር ግን ደጎል እንዳሉት፤ ለግዜው ተሰናክለን ወደቅን እንጂ ተስፋ አልቆረጥንም። ተነሳን እንጂ፤ ወድቀን አልቀረንም፡፡ ላለፉት ሶስት አራት አመታት የመቀራረብና አብሮ የመስራት መንፈስ በተቃዋሚዎች መካከል ሥር እየሰደደ ሲመጣ ታዝበናል። አገር ቤት አሉ ከሚባሉ ጠንካራ ደርጅት መካከል፣ የአንድነት ፓርቲ፣ ከብርሃን ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጋር ከሶስት አመታት በፊት ውህደት የፈጠረ ሲሆን፣ አንድነት ከሌላው አንጋፋ ድርጅት መኢአድ ጋር ለመዋሃድ ንግግሮችን ሲያደርግ ቆይቷል።

“ነጻነትነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም!”

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች ያስተላለፈው ግልጽ መልዕክት

የተወደዳችሁ በኢትዮጵያ የምትገኙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች

በቅድሚያ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የአክብሮት ሰላምታ በማቅረብ በትግሉ መስክ የምትከፍሉትን መስዋዕትነት የሚያደንቅ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ምህዳሩ እጅግ ጠብቦ የለም የሚባልበት ደረጃ በደረሰበት ወቅት በምታገኙት ስንጥቅ ሁሉ እየተጠቀማችሁ ለህዝባችሁ የብርሃን ጭላንጭል ስለምትፈነጥቁ አኢጋን ሥራችሁን ያደንቃል፤ ያከብራል፡፡ እኛ በሥራችሁ ስኬት የምንመኘው ለቆማችሁለት የፖለቲካ ዓላማ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት አቅቷቸው መፈናፈኛ ላጡትም የመወሰን ኃይል እንደምትሰጧቸው በማመን ነው፡፡

ሽንፈት ላይ እያተኮሩና የጠላትን ኃይለኛነት እየሰበኩ ድል አይገኝም፡፡ ልዩነትን እያራመዱ ኅብረትና አንድነት ተግባራዊ መሆን አይችልም፡፡ ለአገራዊ ዕርቅ እንሰራለን እያሉ በፓርቲ መካከል ከዚያም በታች በግለሰብ ደረጃ መተራረቅ ካልተቻለ ብሔራዊ ዕርቅ ከቀን ቅዠት አያልፍም፡፡ እያንዳንዳችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ፣ መኢአድ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ ኦህኮ፣ አረና፣ እና ሌሎች እጅግ በርካታ ፓርቲዎች የተቋቋማችሁትና ዓላማ ያደረጋችሁት ኢህአዴግን እየተቃወማችሁ ለመኖር እንዳልሆነ የፓርቲ ፕሮግራማችሁ ይመሰክራል፡፡ ወይም ዓላማችሁ የራሳችሁን የፓርቲ ምርጫ የማድረግና ፕሬዚዳንት (ሊቀመንበር)፣ ምክትል፣ ሥራ አስፈጻሚ፣ … በመምረጥ አዙሪት ውስጥ ራሳችሁን ላለማሽከርከር እንደሆነ ከማንም በላይ ራሳችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ከዚህ አንጻር በጥንቃቄና በብዙ ጥናት የተቀመጠው የፓርቲያችሁ ፕሮግራምና ዓላማ ለአገራችን አንዳች ለውጥ ሳያመጣ እንደዚሁ እንዳማረበት ቢቀመጥ ለሕዝብ የሚያመጣው ትርፍ ምንድርነው? እናንተንስ ለመቃወም ብቻ የምትሰሩ አያደርጋችሁምን? … [ሙሉውን መልዕክት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ] አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ የበርካታዎች ጥያቄ “ህወሃት/ኢህአዴግን በምን ዓይነት የተሻለ አስተዳደር እንዴት መለወጥ ይቻላል የሚለው ነው?” ይህ ጥያቄ “እኛ ኢትዮጵያውያን የዘርና የጎሣ ትንንሽ አጥሮቻንን አፍርሰን ሁሉን አቀፍ ትግል ለማድረግ ተዘጋጅተናል ወይ?” ብለን ራሳችንን መልሰን አንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ እንዲሁም ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠት ሁሉም ነጻ ሳይወጣ ራሳችንን ነጻ ለማውጣት እንችላለን ወይ? ብለንም እንድንጠይቅ የሚያስገድደን ነው፡፡

ሰማዕታትን እንዘክር፤ እራሳችንንም እንጠይቅ!

ሰኔ 1997 በዘረኝነት፣ በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ሥልጣን የተለከፉ የትግራይ ገዢ ጉጅሌ አባላት ጭካኔ በይፋ የታየበት ወቅት ነው። ለዓመታት በማስመሰያ ጭንብል ተሸፋፍኖ የቆየው የህወሓት እውነተኛ ባህርይ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት በወርሃ ሰኔ አደባባይ ወጣ። በሀውዜን ላይ የደረሰውን የግፍ ጭፍጨፋ ሲያወግዝ የቆየው ቡድን ሌላ ሀውዜን አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈጠረ።

ይኸኛው ሀውዜን ግን በአንድ ቦታ ተወስኖ የቀረ አልነበረም። ጭፍጨፋው በአዲስ አበባ ተጀምሮ ወደ አዳማ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ አዋሳ፣ ሃረር፣ ድሬዳዋ እና ሌሎች ከተሞችና ገጠሮች ተዛመተ። “አግዓዚ” የተሰኘው ገዳይ ሠራዊት በሰላማዊ እናቶችና አባቶች፤ ወጣቶችና ህፃናት ላይ ዘመተ። ደብተርና እርሳሶቻቸውን እንደያዙ ከትምህርት ቤት የሚመለሱ እምቦቃቅላ ህፃናትን ሳይቀር በጥይት ግንባርና ደረታቸውን እየመታ ጣለ።

በ1997ቱ ሚያዝያ መጨረሻና ግንቦት መጀመሪያ ላይ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በደስታና ተስፋ ተሞልቶ ነበር። የሚያዝያ 30 ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ እና የግንቦት 7 ጨዋነት የተላበለው ምርጫ የፈጠሩት ተስፋ ቃላት ሊገልጹት በሚችሉት በላይ ነበር። ሆኖም በህወሓት የተመራው የሰኔው ጭፍጨፋ ያንን ሠናይ ስሜት አደፈረሰው፤ አጨለመው።

በዘረኝነት፣ በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ሥልጣን የታወረው ወያኔ ከራሱ አባላት ሌላ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው መኖሩ አይታየውም። በህወሓት ጎጠኞች እሳቤ መሠረት ወጣት ሽብሬ፣ ህፃን ነቢዩ፣ ወ/ሮ እቴነሽ፣ ሌሎች እናቶችና አባቶች ሰዎች አይደሉም። ስለሆነም ያለአንዳች ምክንያት ተገደሉ። እስከዛሬ ድረስም ከገዳዮች መካከል አንዱ እንኳን ተጠያቂ አልሆነም። በግልባጩ ገዳዮች በመግደላቸው ተሾሙ፤ ተሸለሙ። ይህ ሁሉ ያሳምማል።

በአገሩ ጉዳይ የሚያገባው ትውልድ ፍለጋ!!


‹‹የአሁን እኛ?››

በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ምሽቶችን የሚያደምቁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጫወታዎን የሚታደሙ፣ ከዚያም አልፈው ጎራ ለይተው የሚሰዳደቡና የሚወቃቀሱ፣ የባሰ ዕለት ደግሞ በትልልቅ ጫወታዎች መልክ ጎራ ለይተው የሚቧቀሱ ወጣቶችን ማየት የከረመ አገራዊ ትዕይንት ሆኗል፡፡ ቅጥ ባጣ የፈረንጅ እግር ኳስ ፍቅር፣ ‹‹ከብርሃን ፍጥነት›› በላይ እየተስፋፉ ባሉ ‹‹የሱስ መሰረተ ልማቶች›› ውስጥ በመጥፋትና በቸልተኝነት የሚታማው ይህ ትውልድ ከላይ በተጠቀሱ ‹‹አደንዛዥ›› ጉዳዮች ተጠልፎ ካልወደቀም በጥልቅ ‹‹ራስን የማዳን›› ስሜት በመዋጥ አገሩን የረሳ፣ ፖለቲካ የማይገደው፣ ምርጫ የማያሳስበው ትውልድ ነው ተብሎ ይታማል፤ አለፍ ሲልም ደግሞ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስደት ወደተገኘው አገር ለመጓዝ ልቡ የቆመ፣ በአገሩ ተስፋ የቆረጠ፣ በየትኛውም አጋጣሚ አገር ጥሎ ለመሄድ ጓዙን ጠቅልሎ የተሰናዳ ወጣት እንዴት አገርን ይረከባል? ሊረከብስ ቢዘጋጅ ከማን እና እንዴት ይረከባል? ይህችን አገር ከእኛ የሚወስዳት ማነው የሚሉ ‹‹አባቶችም›› መኖር ሌላው ነባራዊ ሐቅ ነው፡፡

ለዚህ ዓይነቱን ትውልድ መፈጠር (ዓይነቱ ይሄ አይደለም ብለው የሚከራከሩ ባይጠፉም) ኃላፊነት የማይወስዱበት ‹‹የጎረቤት ልጅ›› ይመስል እዚህ ለመድረሱ ኃላፊነትን አንወስድም ዓይነት አንድምታ ያላቸውን ሐሳቦች መስማት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ እንደውም አልፈው፣ ተርፈው ‹‹በእኛ ዘመን ቀረ!››ን ልክ እንደ አንድ የታሪክ ኩራት መገለጫ ያደረጉና ትውልዳዊ ኃላፊነታቸውን የረሱ ፖለቲከኞች ስለምክንያቱ ከማውራት ይልቅ ውጤቱን መውቀስ ይቀናቸዋል፡፡

Saturday, June 7, 2014

እየራበንም ቢሆን በምግብ እራሳችንን ችለናል – ኃ/ማሪያም ደሳለኝ

ወያኔ ስልጣን በያዘባቸዉ አመታት በተለይም ባለፉት አስር አመታት የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በድርብ አኃዝ አደገ፤ ኢትዮጵያ በ2015 ዓም መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ አገሮች ተርታ ትሰለፋለች፤ በኤሌክትሪክ ኃይል እራሳችንን ችለን ለጎረቤት አገሮች እንተርፋለን፤ በቅርቡ ደግሞ በምግብ ምርት እራሳችንን ቻልን የሚሉ በአይን የማይታዩና በእጅ የማይዳሰሱ የ”ላም አለኝ በሰማይ” ክምሮች እየከመረ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመደለል ሞክሯል። የአገሩ ኤኮኖሚ በእጥፍ አደግ ሲባል ችግርና መከራዉ በሦስት እጥፍ የጨመረበት የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንኳን መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ አገሮች ተርታ ሊሰለፍ ከሦስቱ ዕለታዊ ምግቦች አንዱን በቅጡ መብላት ተስኖት መብራት በሳምንት አንድ ቀን ብቻ እያገኘ “ጽድቁ ቀርቶብኝ በወጉ በኮነንከኝ” እያለ ጨለማ ቤት ዉስጥ ቁጭ ብሎ የመከራ ዘመን መቁጠር ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንመራሀለን ከሚሉት የወያኔ መሪዎች እጅ እጅ ብሎ የሰለቸዉ ነገር ቢኖር እንደሰዉ በእግሩ ቆሞ የሚሄደዉ ዉሸታቸዉና ቅጥፈታቸዉ ነዉ። የወያኔ መሪዎችና እዉነት አንድ ላይ ታይተዉ ስለማያዉቁ ህዝብ አይኑ እያየ የሆነዉን ነገር አልሆነም ወይም ጭራሽ ያልተሞከረዉን ነገር ሆነ ብለዉ ሲዋሹ ለአፋቸዉም ለሰብዕናቸዉም አይሳሱም። ለምሳሌ ሠላማዉ ዜጎችን በጅምላ ገድለዉ ብርድልብስ ጠቅልለዉ እየቀበሩ ማንንም አልገደልንም፤ መብቱን የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፈኛ በጥይት እየጨፈጨፉ – ባንክ ተዘረፈ፤ መሬታችንን ለምነዉ ለሱዳን እየሰጡ – የተሰጠ መሬት የለም፤ አኝዋክን ከመሬቱ አፈናቅለዉ መሬቱን ለባዕዳንና ለቤተሰቦቻቸዉ በርካሽ እየቸበቸቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ የመሬት ቅርሚያ የለም እያሉ የዋሿቸዉ ግዙፍ ዉሸቶች ከብዙዎቹ ቂቶቹ ናቸዉ።

ከአስራ ሰባት አመት የጫካ ዉስጥ ቆይታ በኋላ አዲስ አበባ የገቡት ዋና ዋናዎቹ ወያኔዎችም ሆኑ እነሱ መለምለዉ ያሰለጠኗቸዉ ምስለኔዎች የተካኑበት አንድ ትልቅ ነገር ቢኖር ዉሸት መደርደርና ከበስተኋላዉ ምንም ትርጉም የሌለዉ ቁጥር እየደመሩ የኢትዮጵያን ህዝብና አለም አቀፉን ማህበረሰብ ማታለል ነዉ። አዎ! የወያኔ መሪዎች ከምንም ነገር በላይ ቁጥር ይወዳሉ። የሚናገሯቸዉ ቁጥሮች እነሱን የሚጠቅሙ ከሆነ ለጥጠዉ ለጥጠዉ ሰማይ ያደርሷቸዋል፤ የቁጥሮቹ ማነስ የሚጠቅማቸዉ መስሎ ከታያቸዉ ደግሞ ይጠቅሙናል ብለዉ ባሰቡት ልክ ያሳንሷቸዋል። ለምሳሌ አለም አቀፍ ዕርዳታ ሰጪ አገሮችና ተቋማት 6 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ተርቧልና አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልገዋል ብለዉ ሲያስጠነቅቁ . . . . ወያኔ ደግሞ የለም የተራበዉ ህዝብ ከአንድ ሚሊዮን ያነሰ ነዉ ይላል። ለወያኔ ትልቁ ቁም ነገር የኢትዮጵያ ህዝብ የረሃብ አደጋ ላይ መዉደቁ ሳይሆን እራሱን ሞቶ ከተቀበረ ስርዐት ጋር ማወዳደርና የተሻለ መስሎ መቅረብ ብቻ ነዉ።

Friday, June 6, 2014

የእናት ሀገር የድረሱልኝ ጥሪ ???…


(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ባለፈው ሰሞን ወያኔ ኢሕአዴግ ላለመው የጥፋት ተልእኮ ወሳኝ ክንውኑን መተግበሩ ይታወሳል፡፡ ወያኔ ለጥፋት ተልእኮው በእጅጉ የሚረዳውን ወሳኝ የጥፋት ሥራ የመሥራቱን ያህል ከእምነተ-አሥትዳደር (ፖለቲካ) ፓርቲዎች (ቡድኖች) አንሥቶ እስከ ሕዝባዊ ማኅበራት (Civic organizations) ድረስ ያሉ ሁሉ ልብ ሳይሉት ወይም በቅጡ ሳይረዱት ቀርተው ይሁን ምን አላውቅም ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡት ሲቀሩ ሳይ እጅግ ተገርሜያለሁ፡፡

ወያኔ በአሩሲ ሔጦሳና በሐረር ጨለንቆ ላይ ፋሽትት ጣሊያን ለሰበው የቅኝ ግዛት ይዞታ ዘለቄታ ሲል በነበረው ስልት (Strategy) ተአማኒነት እንዲኖረው በእውነተኛው ታሪካችን ላይ ሆን ብሎ በክፋት የፈጠረውን ፈጠራ በርዞ የሕዝባችንን አንድነት፣ ሰላም፣ ጥምረት፣ ወንድማማችነት (እኅትማማችነት)፣ መተማመን ለመፈረካከስና ለአገዛዙ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲጠቀምበት የነበረውን ድርሰት ወያኔ ሐሰት እንደሆነ እያወቀ ነገር ግን ላለው ተመሳሳይ የጥፋት ዓላማ ከወደቀበት በማንሣት የፈጠራ ሠማዕታትን የሚዘክር የመታሰቢያ ሐውልት አስገንብቶ አስመርቋል፡፡ እንደሚታወቀው ፋሺስት ጣሊያን አስቀድሞ የኢትዮጵያን ሰሜናዊ ክፍል በኋላም መላውን ኢትዮጵያን ይዞ በነበረበት ወቅት ሕዝቡን አዳክሞ ቅኝ አገዛዙን ለማጽናት እንዲያስችለው በፋሺስታዊና የቅኝ አገዛዝ ስልት (Strategy) ሕዝቡን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በሞያ ወይም በሥራ ዓይነቶች ሳይቀር ከፋፍሎ ያናቁር ለማፋጀትና ለማባላት ይጥር እንደነበር ታሪክ ዘግቧል፡፡

ፋሺት ጣሊያን ይህ እኩይ ሴራው ያሰበውን ያህል ሳይሠምርለት ቀርቶ በጀግኖች አርበኞቻችን ድል ተመትቶ ተባረረ፡፡ ነገር ግን ሰላዮቹ ሚሲዮኖችና ሀገር አሳሾቹ ሀገራችንን ለመበቀል ሰላምና አንድነት እንዳይኖራት ለማድረግ ብዙ እኩይ ፈጠራዎቻቸውን እውነት አስመስለው በመጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ዛሬ አሸባሪዎቹ ወያኔ ኦነግና ሻቢያ የኦሮሞን ሕዝብ በሔጦሳና በጨለንቆ ተፈጽሞብሀል የሚሉትን በጅምላ ጡት እጅና ብልት የመቁረጥ ቅጣት ወይም ግፍ ተፈጽሟል ብሎ የጻፈ ሚሲዮን ወይም አሳሽ አንድ እንኳን የለም፡፡ እነዚህ የጥፋት ኃይሎች እከሌ እከሌ የተባለ ታሪክ ጸሐፊ እንደዚህ በሚለው መጽሐፍ እነደጻፈው እያሉ የጠቀሷቸውን መጻሕፍትም ከሀገር ውጪ ያሉ ወዳጆቻችንን ሳይቀር አስቸግረን መጻሕፍቱ አሉበት በተባሉ ቦታዎች አፈላልገን ስናነብም በሚገርም ሁኔታ ከሚሉት ጋራ ጨርሶ የማይገናኝና የሌለ ፈጠራ ሆኗል፡፡ ይሄ ምንን ያመለክታል ወገን?

Thursday, June 5, 2014

ዶ/ር ብርሀኑን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየሁት


ግንቦት 97 ዓ.ም ለሐገራችን ፖለቲካ ተስፋን ይዞ የመጣ ትልቅ እድል ነበር የምርጫው እለት እኔም በአሁኑ ሠዓት አውስትራሊያ ከሚኖር ወዳጄ ጋር በመሆን በጠዋት ወጥተን በያዝኳት አንድ ካርድ ኢህአዴግን ለመጨረሻ ጊዜ ከስልጣን በማባረሩ ሒደቱ ተሳታፊ ለመሆን ምርጫ ጣቢያ ደርሰናል በድንገት ግን አንድ ተዐምር ተከሠተ ዶ/ር ብርሐኑ ነጋ የሠፈራችን ምርጫ ጣቢያ ለቅኝት ተገኘ አካባቢው በፉጨት ተናጋ እልልታ ጭፈራው ደራ፣ ሰው ሁሉ ዶ/ር ብርሐኑ እየሮጠ ላይ መጠምጠም ጀመረ እኔና ጓደኛዬ ሁኔታውን በአድናቆት መከታተል ያዝን ወዲያውም በአካባቢው ይገኙ የነበሩ ሠዎች ኮተቤ ደጃዝማች ወንድራድ ት/ቤት አካባቢ በሚገኝ አንድ ግሮሠሪ በመውሰድ ምግብ ሊጋብዙት እንደሚፈልጉ ነገሩት ያ ድንቅ ሠው ዶ/ር ብርሐኑ ግን አሻፈረኝ መሄድ አለብኝ ሲል ቢናገርም አንድ አዛውንት ጠጋ ብለው እንዲህ አሉት ”የኛን ግብዣ ንቀህ ካልሆነ በቀር እምቢ የምትልበት ምንም ምክንያት የለም አንተ ነፍስህን ለእኛ ስትል ለመክፈል የተዘጋጀህ ነህ እኛ ለምሳ ብንከፍልልህ ምን አለበት” ሲሉት ዶ/ር ብርሐኑ ላይ የትካዜ እና የፍቅር ፊት አነብ ነበር፡፡

ዶ/ር ብርሐኑ በሰው ተከቦ ምግቡን ከበላ በኋላ ህዝቡ ዶ/ር ብርሀኑ መኪናው ውስጥ እስኪገባ ድረስ ግማሹ በለቅሶ ግማሹ በደስታ ተሸክመውት ይጨፍሩ ነበር እኔም ህዘቡ ብርሐኑን ምን ያህል እንደሚወዱት ባየሁኝ ጊዜ ይህንን ድንቅ ኢትዮጵያዊ እግዚአብሔር እንዲጠብቀው እና የህዝቡን ልብ የሚያረካ ድርጊት እንዲፈፅም ሲል ከልብ ተመኘው ምንአልባት ያ የኮተቤ አካባቢ ህዝብ ፍቅር በብርሐኑ ህሊና ውስጥ እየመጣ ይሆናል ብርሐኑን እንደዚህ በየመድረኩ ህዝቡን ለማገልገል ቃል እንደገባ እንዲናገር ያስቻለው፡፡

አሁን ዶ/ር ብርሐኑ ወደ መኪናው ገብቷል የኮተቤ ህዝብ ግን ለዶ/ር ብርሐኑ ያለውን ፍቅር መግለፅ አላቆመም

ይለያል ይለያል ይለያል ዘንድሮ

የወያኔ ኑሮ
……………………

ወጣቶች እየመጡ ነው!!!

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ “ወጣት፤ የነብር ጣት!” በሚል ርዕስ ጥር 26 ቀን 2003 ዓ.ም. በቁጥር 142 ባወጣው ርዕሰ አንቀጹ “ወጣት በነብር ጣት መመሰል ያንሰው እንደሆን እንጂ አይበዛበትም። የኢትዮጵያም ወጣት የነብር ጣት ሆኖ ያውቃል … አሁንም ነው” ብሎ ነበር። በዚያ ጽሁፍ እና በሌሎችም አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ እንዳብራራው ግንቦት 7 በወጣቱ ችሎታና ተነሳሽነት ላይ ከፍተኛ እምነት አለው። የወደፊቷ ብቻ ሳይሆን የአሁኗ ኢትዮጵያም የወጣቱ መሆኗን ግንቦት 7 ያምናል። ግንቦት 7: ወጣቶችን ለማሳተፍና ለመሪነት ለማብቃት የሚጥር፤ ራሱም በወጣቶች የተገነባ ድርጅት ነው።

ኢትዮጵያ አገራችንና ሕዝቧን ከወያኔ አደንቋሪ አገዛዝ ለማላቀቅ ቆርጠው የተነሱ ወጣቶች እየበረከቱ መምጣታቸው የግንቦት 7 እምነትን የሚያጠናክር ሆኗል። አምባገነኑን የወያኔ አገዛዝን በትጥቅ ትግል መፋለም ይኖርብናል ብለው የተነሱ ወጣቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተደራጁ መሆናቸውን እንሰማለን። እድሜያቸው በሀያዎችና በሠላሳዎች መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ለጋ ወጣቶች ናቸው የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የሚባለውን የትግል ድርጅትን የፈጠሩት። ይህ ኃይል ሰሞኑን ለአራተኛ ጊዜ እጩዎችን አሰልጥኖ ማስመረቁን በተለያዩ ሚዲያዎች ባሰራጨው ዜና ገልጿል። በተመሳሳይም የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን አሰልጥኖ ለወሳኝ ትግል ዝግጁ መሆኑን አብስሯል። የኢትዮጵያ አርበኖች ግንባርም በወጣቶች የተሞላ ለትግል የተዘጋጀ ድርጅት ነው። ሌሎችም አሉ። እነዚህን ድርጅቶች ድርጅት ያደረጓቸው ወጣቶች ናቸው።

በሰላማዊ የትግል ዘርፍም ወያኔ የሚያደርስባቸው እስር፣ ዱላና እንግልት እየተቋቋሙ በየእለቱ እየበረቱ የመጡ ጀግኖች ወጣቶችን ማየት ችለናል። ወያኔ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ብሩህ አዕምሮና ልብ ያላቸው ወጣቶችን አስሬ፣ አሸማቅቄ ጨረስኩ ሲል ከዚያ የባሱ እየፈለቁ ነው። በነፃነት ሲጽፉ የነበሩ እነ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታየ እና ርዕዮተ ዓለሙ በሀሰት ክስና ምስክር ሲታሰሩ ወያኔ ተስፋ እንዳደረገው ወጣቶች በፍርሃት ተሸማቀው ልሳኖቻቸውን አልዘጉም። እንዲያውም ከነሱ የባሱ፣ የበሰሉ ጦማርተኞች መጡ። ሰላማዊ ታጋዮቹ እነ አንዱ ዓለም አራጌና ናትናኤል መኮንንን ሲያስር ከእነሱ የበለጡ ወጣት ወንድና ሴት ታጋዮች መጡ። እስከ ድል ድረስ ይህ ዑደት ይቀጥላል፤ ኢትዮጵያ ወጣት ጀግኖችን ማፍራቷ አያቋርጥም።

Monday, June 2, 2014

ግንቦት 20፡ የኢትዮጵያዊያን ጠላት መሆንን የመረጠ ጉጅሌ ለስልጣን የበቃበት ታሪካዊ ቀን፤

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወርሃ ግንቦት የተለየ ሥፍራ አላት።ከወርሃ ግንቦት ግንቦት ሰባትንና ግንቦት ሃያን በተለይ አንረሳቸውም። ግንቦት ሃያ ጎጠኝነት፤ እኔ ብቻ ባይነት፤ አስመሳይነት ፤ስግብግብነት እና ሌብነት ተደምረው የወለዱት ቡድን ብሶት ወለደኝ ብሎ በትረ ስልጣኑን የተቆጣጠረበት ቀን። ብሶት ወለደኝ ብሎ ግንቦት 20 ዕለት በትረ ስልጣኑን የጨበጠው ቡድን ግንቦት ሰባት ዕለት ብዙ ህፃናትን፤ ብዙ ወጣት ሴትና ወንዶችን፤ ብዙ አረጋዊያንን ገድሎና በደም ሰክሮ የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን ለማዳፈን የሞከረበት ቀን። አዎን ግንቦት ሃያ የኢትዮጵያ ጠላት መሆንን የመረጠ ጉጅሌ ለስልጣን የበቃበት ታሪካዊ ቀን።

ህወሃትን ስልጣን ይዞ አገርን ሊመራ እንደሚችል የፖለቲካ ተቀናቃኝ ድርጅት አድርጎ ማየት ከስህተት ይጥላል። ስህተቱ ደግሞ ለነፃነት፤ ለእኩልነት እና ለፍትህ የሚደረገውን የትግል አቅጣጫ ያዛባል። የትግሉ አቅጣጫ እንዳይዛባ ህወሃት የህዝብ ጠላት መሆንን የመረጠ ጉጅሌ መሆኑን አጥብቆ መያዝ ያስፈልጋል። ህወሃትን ከህዝብ ጠላትነት ዝቅ አድርጎ ማየት በማንኛውም መለኪያ ስህተት ነው።

በዚህ ወቅት ጉጅሌው ህወሃት የህዝብ ጠላት መሆኑን የሚጠራጠር ኢትዮጵያዊ እውነቱን ለመቀበል የማይፈልግ፤ ለነፃነት የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈል የማይፈልግ ሰነፍ አልባሌ ሰው ነው። እንዲህ ዓይነት ሰነፍ ሰዎች ጉጅሌዎቹ ሠላም ያመጣነው እኛ ነን ሲሉ ያምኗቸዋል። ልማትም ከመቼውም ግዜ በላይ ለኢትዮጵያ ያመጣንላት እኛ ነን ሲሉ እውነት ነው ይላሉ። እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትበታተናለች ብለው ሲደነፉም ይደነግጣሉ።እንዲያውም ህወሃቶች ከሌሉ ማን አገሪቷን ሊመራት ይችላል ብለው ለመከራከር ይዳዳቸዋል።

ህወሃቶች በማንኛውም መስፈርት አገር ለመምራት ብቃት ያላቸው ቡድኖች አይደሉም። አገር የሚመራ ኃይል ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነትን ለማጥፋት ሳይታክት አይሠራም። ጉጅሌዎቹ ከተመሸጉባቸው የጎሳ ፖለቲካ ክበብ ውስጥ ሁነው ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነትን ለማጥፋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ፤ያልቧጠጡት ዳገት የለም። ጉጅሌዎቹ የማያውቁት አንድ እውነት ግን ኢትዮጵያዊ ማንነት በፀና መሠረት ላይ የቆመ ተሸርሽሮ የማያልቅ ፅኑ ዓለት መሆኑን ነው። ግንቦት ሃያ ዕለት ስልጣኑን የጨበጠው ጎጠኛው ነፃ አውጪ ቡድን ከሃያ ዓመት በኋላም ሥሙን እንኳን ሳይቀይር “እኔ ካልገዛኋችሁ ኢትዮጵያ ትበታተናለች” እያለ ያሟርታል። ህወሃትን የህዝብና የአገር ጠላት የሚያሰኘው አንዱ አንጓም ይሄው ነው።”እኔ ያልኩት ካልሆነ አገሪቷን አፈርሳታለሁ፤ የጎሳ ግጭት ተነስቶ ህዝቡ እርስ በርሱ እንዲተላለቅ አደርጋለሁ” እያለ መዛቱ። እንግዲህ “እኔ ከሌለው አገሪቷን አፈርሳታለሁ” የሚል ቡድን በምን መሥፈርት አገርንና ህዝብን መርቶ ወደ ተሻለ ደረጃ ሊያደርሳት እንደሚችል “ህወሃቶች ከሌሉ አገሪቷን ማን ይመራታል” ብለው የሚጨነቁ ሰዎች መልሰው መልሰው ራሳቸውን እንዲጠይቁ እንመክራቸዋለን። ለማንኛውም ከግንቦት ሃያ መራራ ፍሬዎች መካከል አንዱ “እኔ ያልኩት ካልሆነ አገሪቷን እበትናታለሁ” የሚል ክፉና ጎጠኛ ጉጅሌ በአገራችን ጫንቃ ላይ መጫኑ ነው።

Sunday, June 1, 2014

ሦስተኛዋን ‹‹እሁድ››- በአራዳ ምድብ ችሎት


በጽዮን ግርማ (tsiongir@gmail.com)

 የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ተጠርጣሪዎቹን እሁድ ለሚሰየም ተረኛ ችሎት መቅጠሩን የተለመደ አድርጎታል፡፡ ከቀናት በፊት በሦስቱ ብሎገሮች ላይ በተሰጠው የዐሥራ አራት ቀናት የጊዜ ቀጠሮ መሠረት የቀጠሮው ቀን ዛሬ ነበር፡፡ ዛሬ በዚህ ፍርድ ቤት ተገኝቼ የነበረውን ሁኔታ መከታተል ባልችልም ምንጮቼ የነገሩኝን ዝርዝር እንዲህ ጽፌዋለሁ፡፡

ጠዋት

የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰቦች እንደተለመደው የአራዳውን ምድብ ችሎት የጓሮ በር እያለፉ ወደ አሮጌው ፍርድ ቤት ግቢ መግባት የጀመሩት ጠዋት ሦስት ሰዓት ከመሙላቱ አስቀድሞ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ከፍርድ ቤቱ ከፍ ብሎ በሚገኘው ማዕከላዊ ለሚገኙት እስረኛ ልጆቻቸው ቁርስ የማድረሻ ሰዓት ስለኾነ ዛሬም ከቁርስ መልስ ሰብሰብ ብለው ነበር ወደ ፍርድ ቤት ግቢ የገቡት፡፡
ፍርድ ቤቱ ሲደርሱ ግቢው በጸጥታ የተሞላ ነበር፡፡አንድም የተከፈተ የችሎት በር አልነበረም፣ግቢውን ከሚጠብቀው አንድ ፖሊስ በስተቀር ሌላ ሰው የለም፡፡ ጠባቂው ፖሊስ ‹‹ዋናዎቹ›› ሲመጡ አንድ ላይ መሰብሰባቸው አይቀርም ብሎ ይመስላል የሚገባውን ሰው በሙሉ አንድ ላይ እንዲሰበሰብ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ሰዓቱ ረፈድ እያለ ሲመጣና ጸሐዩ ሲበረታ ግን ግቢው ውስጥ የቆመው ሰው ተበታትኖም ቢሆን ጥላ ፈልጎ እንዲቀመጥ ፈቀደ፡፡ የቀጠሮው ሰዓት እስኪደርስ ድረስ ሁሉም አመጣጡ እንደገጠመለት እየተቧደነ ባገኘው ነገር ላይ ተቀምጦ ፖሊስ ሊጠይቅ ይችላል ያሉትንና ፍርደ ቤቱ ሊሰጠው ስለሚችለው ትእዛዝ ግምታዊ መላምቱን እያስቀመጠ ጭንቀቱን በተስፋ ለማራገፍ ውይይቱን ቀጥሏል፡፡