Friday, August 29, 2014

በድርጅቶች ውህደትና ቅንጅት አገርን ማዳን!!!

ኢትዮጵያዊያንን በዘር እና በሀይማኖት ለያይቶን እርስ በርስ እያጋጨን በመግዛት ላይ ያለውን ወያኔን ለማሸነፍ እና ከምትኩም ከራሷ ጋር የታረቀች፤ ፍትህ የሰፈነባት፤ እኩልነት የተረጋገጠባት እና በኃያላን አገሮች እርጥባን ሳይሆን በራሷ አቅም የምትተማመን ጠንካራ ሀገር እንድትኖረን የነፃነትና የዲሞክራሲ ኃይሎት መተባበር እንዳለባቸው ሲነገርና ሲወተወት ቆይቷል። ይሁን እንጂ በህወሓት የከፋፍለህ ግዛው ፓሊሲ እና በፓለቲካ ባህላችን ኋላቀርነት ምክንያት እስካሁን የተደረጉ የትብብር ጥረቶች የተፈለገውን ውጤት ሳያስገኙ ቀርተዋል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ቀድሞ የተደረጉት ጥረቶች የተጠበቀውን ውጤት አለማስገኘት ተስፋ ሳያቆርጠን ከእያንዳንዱ ጥረት ልምድ እየወሰደን የኢትዮጵያዊያን አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ አዳዲስ የትብብር ጥረቶችን ማድረግ ያለብን መሆኑ ያምናል። በዚህም መሠረት የትብብር መርህ ነድፎ ትግል ውስጥ ካሉ ሁሉም የፓለቲካ ድርጅቶች ጋር ሲነጋገር እና ሲደራደር ቆይቷል። እንደሚታወቀው የንቅናቄዓችን አበይት የትብብር መርሆች ሁለት ናቸው። መርህ አንድ፣ ለውጥ እንዲመጣ የምንታገለው ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥ መሆኑ ማመን ነው። መርህ ሁለት ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም እርከኖች የመንግሥት ሥልጣን መያዝ የሚገባው በሕዝብ ነፃ ምርጫ ብቻ መሆኑን መቀበል ናቸው።

በምድር ላይ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ኃይሎች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ሁለቱንም መርሆዎች የሚያሟሉ ናቸው። እነዚህ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ከንቅናቄዓችን የተለየ አቋም የላቸውም። በአለፉት ሁለት ዓመታት ድርጅቶቹ ተቀራርበው እንዲሠሩ በመደረጉ ከአመራር አልፎ አባላት መካከል መልካም ወዳጅነት መመሥረት ተችሏል። የነፃነት ትግላችን የደረሰበት ደረጃ እና የድርጅቶቹም ቅርርብ በመገምገም ሶስቱ ድርጅቶች ማለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄና እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ መዋሃዳቸው ትግሉን ያራምዳል ተብሎ ታምኖበታል። በዚህም መሠረት ሶስቱ ድርጅቶች ለመዋሃድ ተስማምተን ስምምነታቸንን ይፋ አድርገናል። ድርጅቶቹን የማዋሃድ ዝርዝር ሥራም ተጀምሯል።

Monday, August 25, 2014

የወያኔን እድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሠራለን

ቀን 19/12/2006 

የወያኔን እድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሠራለን 



በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ የተንሰራፋውን ዘረኛና በታኝ ሥርዓት ለመቀየርና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ለማውረድ በተለያየ ጎራ ተከፍለው የሚታገሉ ድርጅቶች ቁጥር ከምንጊዜውም በላይ እየበረከተ መምጣቱ የጎጠኛውን ቡድን እድሜ በማራዘም ረገድ ጉልህ ሚና መጫወቱ አሌ የማይባል ሀቅ ነው።

ወቅቱ የሚጠይቀውና አገራችንና ሕዝባችን ያሉበትን ደረጃ በአንክሮ የተረዳ አገርና ሕዝቡን አፍቃሪ የሆነ ድርጅትም ሆነ ቡድን ቆም ብሎ ሊያስብ የሚገባበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን የሚያሳይ ነው።

በመሆኑም ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ መድረሳችንን፤ የወያኔን ቡድን በሁለገብ ትግል እየተፋለምን ያለን ድርጅቶች ተጣምሮና አንድ ሆኖ መታገል እንዳለብን ካመንን በአሁኑ ወቅት ከላይ የጠቀስናቸው ሂደቶች ምላሽ አግኝተው አገራችንና ሕዝባችንን ከአዘቅት ለማውጣት በመጣመር ብቻ ሳይሆን በውህደት አንድ ሆነን አገራችንንና ሕዝባችንን አንድ በማድረጉ ረገድ አስፈላጊው መስዋዕትነት በመክፈል የትግል እድሜ እናሳጥር በሚል ለውህደት የሚያደርሰንን ውይይት ለመጀመር የሚያስችል ሂደቶችን አጠናቀን ወሳኝ ወደሆነው ሂደት ውስጥ መግባታችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ወዳጆች ማብሰር እንፈልጋለን።

Saturday, August 23, 2014

እስክንድር ነጋን ተመልከቱ!

(በላይ ማናዬ)

በአምስት ወራት ብቻ 16 ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ሀገራቸውን ለቅቀው፣ ከስርዓቱ ሸሽተው ወደ ውጭ ሀገር ተሰድደዋል፡፡ አንዳንዶቹ በእውነትም በሀገራቸው ለመስራት ባለመቻላቸውና በመንግስት ክስ የበረገጉ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ሙያቸውን እንደ ሽፋን ተጠቅመው ከሀገር ለመውጣት ያላቸውን ምኞት ያሳኩ ናቸው ማለት እችላለሁ፡፡ (ድፍረት ሳይሆን በትክክል በማውቀው ጉዳይ ላይ ተመስርቼ ነው ይህን የምለው፡፡ ከተሰደዱት ውስጥ በግል የማውቃቸው ስለሚበዙ አቋማቸውን መታዘብ ችዬ ስለነበር የስደታቸው ምክንያት ሊያሳምነኝ ስለማይችል!)

በግሌ ስደትን እንደ መፍትሄ አልቆጥረውም፤ በስደትም ከጋዜጠኝነት መሸሸት የሚቻል አይሆንም፡፡ ጋዜጠኝነት ውስጥ (በተለይ በአምባገነን ስርዓት) የትኛውም አይነት ፈተና አለ፡፡ እስከሞት ድረስ የሚዘልቅ ፈተና፡፡ እስራት፣ ዛቻ፣ ድብደባ፣ ስድብ… ቀላሎቹ ፈተናዎች ናቸው፡፡ ደግሞስ ከማን ነው የሚሸሸው? ከስርዓቱ ወይስ ከራስ እውነት? ከራስ ሸሽቶማ ወዴት ይኬዳል?

ለማነኛውም እስኪ እስክንድር ነጋን ተመልከቱ!
ከሰባት ጊዜ በላይ በመለስ ዜናዊ የአምባገነን መንግስት ታስሯል፡፡ ሀገር ክህደት ከእነሱ ብሶ በሀገር ክህደት ወንጅለው እስር ቤት ልከውታል፡፡ ሲፈታ ሲታሰር፣ ‹ከእንግዲህስ አንተን ማሰር ሰለቸን› ብለውታል፡፡ ግን አልሰለቹም…‹‹አሸባሪ›› ብለው ለ18 ዓመታት ማጎሪያ ቤት እንዲቆይ ፈርደውበታል፡፡ እስክንድር ግን ይህን ሁሉ መከራ ለእውነቱ ሲል፣ ለጋዜጠኝነት ስብዕናው ሲል፣ ለሀገሩና ለወገኑ ሲል…ሁሉንም ነገር ተቀብሎ በጽናት አስተናግዶታል፤ እያስተናገደውም ይገኛል፡፡ ሂዱና ቃሊቱ እስር ቤት ውስጥ እስክንድርን ጠይቁት፡፡ ገና ወደእናንተ ሲመጣ ምትሃታዊ ፈገግታውን ይመግባችኋል፡፡ ደግሞ ውስጡ ሰላም እንደሚሰማው አግኝታችሁ ስታናግሩት ትረዱታላችሁ!

አዎ፣ እስክንድርን ተመልከቱ! ልጁ በእስር ቤት ተወልዷል፡፡ አሁን ከልጁ ናፍቆት ጋር በሰላም መኖርን ጠልቶ አይደለም በእስር የሚማቅቀው፡፡ ስለእውነት፣ ስለሀገር፣ ስለወገን ሲል ነው፡፡ እስክንድር አሁን የተፈረደበትን የ18 አመታት እስር ቆይታ መጨረስ ግድ ከሆነበት ከእስር ሲወጣ ልጁ ናፍቆት 25 ዓመት ይሞላዋል፡፡ ተመልከቱ! እስክንድር ከልጁ ናፍቆት ጋር ከእስር ቤት ውጭ የሚገናኘው ናፍቆት 25 ዓመት ሲሆነው ነው ማለት ነው፡፡

Friday, August 22, 2014

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ስብሰባዎች በዓለም ሃያ ስድስት ታላላቅ ከተሞች

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በመላው ዓለም ላይ ከሚገኙ አባላት፣ ደጋፊዎቹና በአጠቃላይ ከኢትዮጵያውያን  ጋር በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ለመመካከር ዝግጅቱን አጠናቋል።

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት 26 የዓለም ታላላቅ ከተሞች ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ተጠርቷል።

በላስቤጋስ                   ዩ ኤስ አሜሪካ              ረቡስ ኦገስት 27 ቀን
በሂውስተውን               ዩ ኤስ አሜሪካ              ቅዳሜ ኦገስት 30 ቀን
በአትላንታ                   ዩ ኤስ አሜሪካ              እሁድ ኦገስት 31 ቀን
በዋሺንግተን ዲሲ                     ዩ ኤስ አሜሪካ              እሁድ ኦገስት 31 ቀን
በቦስተን                    ዩ ኤስ አሜሪካ              እሁድ ኦገስት 31 ቀን
በሎስ አንጀለስ              ዩ ኤስ አሜሪካ              ቅዳሜ  ሴፕተምበር 6 ቀን
በሳንቲያጎ                   ዩ ኤስ አሜሪካ              እሁድ ሴፕተምበር 7 ቀን
በቶሮንቶ                    ካናዳ                        እሁድ ኦገስት 31 ቀን
በካልጋሪ                    ካናዳ                        ሴፕቴምበር 1 ቀን
በደርባን                     ደቡብ አፍሪቃ               እሁድ ኦገስት 31 ቀን
በጆሃንስበርግ                ደቡብ አፍሪቃ               እሁድ ኦገስት 31 ቀን
ቬሪኒንፍ                    ደቡብ አፍሪቃ               እሁድ ኦገስት  31 ቀን
ሩስተምበርግ                ደቡብ አፍሪቃ               እሁድ ኦገስት 31 ቀን
ፍራክፈርት                  ጀርመን                     ቅዳሜ ኦገስት 30 ቀን
ሙኒክ                       ጀርመን                     እሁድ ኦገስት 31 ቀን
ሄልሲንኪ                   ፊንላንድ                    ቅዳሜ ኦገስት 30 ቀን

ከወያኔ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስልጠናዎች የተረዳነው:- ወጣቱ ለለውጥ ዝግጁ ነው፤ የቀረው ድርጅት ነው

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመሠረቱበት ዓላማ የእውቀትና ጥበብ መበልፀጊያና ማስፋፊያ እና የምርምር ማዕከላት እንዲሆኑ ነው። እውቀትና ጥበብ እንዲበለፅጉ እና የምርምር ሥራዎች እንዲዳብሩ የአካዳሚ ነፃነት መኖሩ ቁልፍ ጉዳይ ነው። የአካዳሚ ነፃነት ሳይኖር መምህራኑም ተማሪዎቹም በነፃነት ማሰብ፣ አስቸጋሪ ጥያቄዎችን ማንሳት እና ለጥያቄዎቻቸው መልስ ለመሻት መመራመር አይችሉም። የአካዳሚ ነፃነት ሳይኖር የተለያዩ እይታዎችንና ንድፈሀሳቦችን በገለልተኛነትና በሀቀኝነት መመርመር አይቻልም። በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የአካዳሚ ነፃነት እንዲኖር ተቋማቱ ከፓርቲ ፓለቲካ ገለልተኛ መሆን ይኖርባቸዋል። አንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም አራማጅ ከሆነ ተቋሙ የፓርቲው ካድሬዎች ማሰልጠኛ ሆነ ማለት ነው። ዛሬ በአገራችን የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙበት ሁኔታ ይህ ነው። የአገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወያኔ ካድሬዎች ማሰልጠኛ ሆነዋል። ይህ አጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ ህወሓት ካድሬ ማሰልጠኛነት መዝቀጥ አንድ ተጨባጭ ማስረጃ ሰሞኑን ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፕላዝማ ቴሌቪዥን አማካይነት በመሰጠት ላይ ያለው ፕሮፖጋንዳ ነው። በዚህ ፕሮፖጋንዳ ያልተጠመቀ ተማሪ የሚቀጥለው ዓመት መደበኛ ትምህርት አይቀጥልም በማለት ተቋማቱ ለካድሬ ማሰልጠኛነታቸው እውቅና ሰጥተዋል።

በዚህ ብዙ የአገር ሀብትና ጊዜ በፈሰሰበት ቅስቀሳ፣ የወያኔ ካድሬዎች ዘረኛና ከፋፋይ ፓሊሲዎቻቸውን ማር ቀብተው ወጣቱን ለመጋት እየጣሩ ነው። ለፓርቲ ቅስቀሳ የመንግሥትን መዋቅር መጠቀም በራሱ ወንጀል ቢሆንም ከዚህ በላይ ጉዳት ያለው ደግሞ የፕሮፖጋንዳው ይዘትና ዓላማ ነው። ወያኔ/ኢሕአዴግ ሁሉንም ነገር የሚያውቅ፤ ሁሉንም ነገር ማድረግ የሚችል ተደርጎ የተዘጋጀው ፕሮፖጋንዳ በትውልድ ላይ የሚያስከትለው የእውቀትና የሥነ ልቦና ኪሳራ ከፍተኛ ነው።

‹‹ይድረስ ላንቺ›› (ዘላለም ክብረት ከቂልንጦ ማረሚያ ቤት)

ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ ዘላለም ክብረት (ከቂልንጦ ማረሚያ ቤት)

ወዳጄ ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እውን እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ ዘዴ አጥተን ወደ snail mail እንመላለሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ለማንኛውም እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣ ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡

‹‹ ….ደብዳቤ ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣

እንገናኝ እና ልንገርሽ ሁሉንም….››

የደላው! ቢያሻው በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም ቅንጦት ነው (ወይ ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ ሊገደብ ይችላል)፡፡ቆይ ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡

እመቤት ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ (Ethiopian by choice) ዱቼ ሞሶሎኒ እትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡ በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›… እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ› ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ? ፤ በፍፁም! ጌቶች እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi

ቧልቱ ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡ ‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡ ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን እያነሳሁ እነግርሻለሁ፡፡ወይ ትስቂያለሽ (ሳቅሽ እንዴት ያምራል?) ወይ ደግሞ ታዝኛለሽ (እኔን!)

ይህንን ደብዳቤ የመፃፍ መብት

እነሆ ላንቺ ስለሆነው ሁሉ ላጫውትሽ ስጀምር፤ በመነሻው ያሰብኩት ነገር ይሄን ደብዳቤ የመፃፍ ሕጋዊ መብት አለኝን? የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህም መነሻዬ አሁን ያለሁበት ሁኔታ ነው፡፡ በመጀመሪያ “ሕገ-መንግስታዊ ስርአቱንና ሕገ-መንግስቱን በሀይል ፣በዛቻና በአድማ ለመናድ በመምከር/ በመናድ” ወንጀል ተጠርጥሬ የታሰርኩ ቢሆንም፤ በታሰርኩ በ23ኛው ቀን ወንጀል ወንጀልን፤ ጥርጣሬ ሌላ ጥርጣሬን እየወለደ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ለማሴርና ለማነሳሳት ወንጀል ተጨማሪ ጥርጣሬ በፓሊስ ዘንድ በማሳደሬ የክፋት ልኬ ከፍ ያለ ሲሆን፤ በመጨረሻም ሕገ-መንግስቱን እንደ እያሪኮ ግንብ ለመናድ በመሞከር፤ ሕብረተሰቡን ደግሞ ከሚተነፍሱት የሰላም አየር ለማቆራረጥ ከማሰብ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ ተይዟል በሚል ወንጀሎች ተከስሼ በማረፊያ ቤት እገኛለሁ፡፡ ይሄን ሁሉ የምነግርሽ ‹ለ አንቺ› አዲስ ነገር ነው በማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ያለሁበት የእስር ሁኔታ ደብዳቤ ካንቺ ጋር እንዳልፃፃፍ ይከለክለኛልን? የሚለውን ለማስረዳት በማሰብ ነው፡፡

Thursday, August 21, 2014

መለስን ቅበሩት!


ተመስገን ደሳለኝ 

ከኢትዮጵያ ሀገሬ የደቀቀ ኢኮኖሚ ላይ በማን አህሎኝነት ወጪ ተደርጎ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ በመላ አገሪቱ እየተከበረ ስላለው የቀድሞ አምባገነን ጠ/ሚኒስትር ሁለተኛ ሙት ዓመት ዝክርም ሆነ ሰውየውን ዛሬም በአፀደ-ህይወት ያለ ለማስመሰል እየሞከሩ ላሉት ጓዶቹ አንዲት ምክር ብጤ ጣል ማድረጉ ተገቢ ነው ብዬ ስለማስብ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፡-

አብዮታዊው ገዥ-ግንባር ግንቦት ሃያ፣ የህወሓት ምስረታ፣ የብአዴን አፈጣጠር፣ የኦህዴድና የደኢህዴን ውልደት፣ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል፣ የባንዲራ ቀን፣ የመከላከያ ሳምንት፣ የፍትሕ ሳምንት፣ የሕዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት… ጅኒ-ቁልቋል እያለ ዓመቱን ሙሉ በማይጨበጥ ተራ ፕሮፓጋንዳ ማሰልቸትን መንግስታዊ ኃላፊነት አድርጎታል፡፡ ይህ እንግዲህ ለቁጥር የሚያታክቱ፣ በነጭ ውሸት የታጨቁ እና በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቅኝት የተንሸዋረሩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞቹ›ን ረስተንለት ነው፡፡

ይህ ሁሉ ያልበቃው ‹‹ጀግናው›› ኢህአዴግ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት ወዲህ፣ ወርሃ-ነሐሴንም እንደ ግንቦት ሃያው ሁሉ የሟቹን ታጋይነትና አብዮታዊነት፤ ሕዝባዊነትና አርቆ አስተዋይነት፤ የርዕዮተ-ዓለም ተራቃቂነትና የአየር ንብረት ተካራካሪነት፤ በፖለቲካ ቢሉ በኢኮኖሚ ቁጥር አንድ ጠቢብነትና ባለራዕይነት፤ ፍፁም ፃድቅነትና ሰማዕትነት…. የሚተረክበት ሲያደርገው ቅንጣት ታህል ሀፍረት አልተሰማውም፡፡ ሰሞኑን በ‹‹ኢትዮጵያ›› ቴሌቪዥን ግድ ሆኖብን ተመልክተንና ሰምተን በትዝብት ካሳለፍናቸው ‹‹መለስ፣ መለስ›› ከሚሉ የከንቱ ውዳሴ አደንቋሪ ድምፆች በተጨማሪ፣ የኦሮሞን ባሕላዊ ልብስ ሲያለብሱት፣ ሐረሪዎች ጋቢ ሲደርቡለት፤ በደቡብ የሚገኙ ብሔሮች የየራሳቸውን ባሕል የሚወክሉ አልባሳት ሲሸልሙት፣ ስለወላይታነቱ ሲመሰክሩለት… ደጋግመን ለመመልከት ተገደናል፤ ይሁንና ድርጅቱ ስለ ቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አልፋና ኦሜጋነት ለመስበክ ዙሪያ ጥምዝ ከዳከረለት ከእንዲህ አይነቱ የተንዛዛ ፕሮፓጋንዳ ይልቅ፣ በዚሁ የቴሌቪዥን መስኮት የቀረበ አንድ ጎልማሳ ‹‹መለስ ሁሉም ማለት ነው›› ሲል የሰጠው አስተያየት፣ ቅልብጭ አድርጎ ይገልፅለት ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ የዚህ አይነቱ ምጥን አስተያየትም በጥራዝ ነጠቅነት ዘላብዶ የኋላ ኋላ በሀፍረት ከማቀርቀር ያድናል፡፡ ለምሳሌ እናንተ የግንባሩ ካድሬዎች ስለመለስ ምሁርነት ለመናገር ስትዳዱ ሁሌ የምትደጋግሙት፣ ያንኑ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አርቃቂነቱ እና የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ኀልዮት አዋቃሪነቱ ነው፡፡ ግና፣ ይህ ‹‹ንድፈ-ሃሳብ›› ተብዬ ራሱ በርዕዮተ-ዓለምነት ለመጠራት የማይበቃ የተውሸለሸለ ጭብጥ ስለመሆኑ በርካታ ምሁራን በጥናቶቻቸው ከማስረገጣቸው ባሻገር፣ አገሪቷን ለከባድ ኢኮኖሚያዊ ድቀት፣ ሕዝቧን ደግሞ ለጥልቅ ድህነት መዳረጉን ብቻ ማስታወሱ በቂ ይሆናል፡፡ ስለልማታዊ መንግስት አዋጭነት በብቸኝነት እንደተከራከረ ተደርጎ የሚለፈፈውን እንኳን ንቆ መተው ሳይሻል አይቀርም፡፡ ከታንዲካ ማካንደዋሬና መሰል የፅንሰ-ሃሳቡ አበጂዎች የዘረፋቸውን መከራከሪያዎች ማን ዘርዝሮ ይዘልቀውና፡፡ ‹መለስን ቅበሩት› የምለውም፣ እንዲህ ያሉ አስነዋሪ ማንነቶቹን ማስታወስ ስለሚያም ነው፡፡

Wednesday, August 20, 2014

የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የአፍ ወለምታ (ኤፍሬም ማዴቦ)

ባለፈዉ ሰሞን ቻይና አፍሪካ ዉስጥ ሰላሳ አመት በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ያደረገችዉ የኤኮኖሚና የፖለቲካ መስፋፋት ያሳሰባቸዉ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ምነዉ ምን አድረግናችሁና ነዉ ፊታችሁን ያዞራችሁብን ብለዉ ለመጠየቅ በርከት ያሉ የአፍሪካ መሪዎችን ቤተ መንግስታቸዉ ድረስ ጋብዘዋቸዉ ነበር። በዚህ የሃሳብ ልዉዉጥ፤ ምክር፤ የእራት ግብዣና የዋሺንግተን ዲሲን ጉብኝት ባጠቃለለዉ የፕሬዚዳንት ኦባማ ድግስ ላይ በመልካም የዲሞክራሲ ጅምራቸዉ የሚወደሱት የጋናና የደቡብ አፍሪካን መሪዎች ጨምሮ እንመራሀለን የሚሉትን ህዝብ በየቀኑ የሚያስሩት፤ የሚደበድቡትና የሚገድሉት የወያኔ መሪዎችም ተገኝተዋል። በዚህ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ጠ/ሚ ደሳለኝ ኃ/ማሪያምን አጅበዉ ከመጡት የወያኔ ሹማምንት አንዱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ./ር ቴድሮስ አድሃኖም ነበሩ። ዶ/ር ቴድሮስ በዋሽንግተን ዲሲ ቆይታቸዉ ብዙዎቻችንን እየዋለ ሲያድር ደግሞ እራሳቸዉንም ግራ ያጋባ የሬድዮ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዉ ነበር።

“በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ” የአገራችን ባለቅኔዎች አፉ እንዳመጣለትና እንዳሻዉ የሚናገርን ሰዉ . . .  ዋ ተጠንቀቅ በአፍ የሚነገር ነገር ዋጋ ያስከፍላል ለማለት የተረቱት ተረት ነዉ።  አዎ! ባለቅኔዎቹ እዉነታቸዉን ነዉ።  የሚያዳምጡንን ሰዎች ለማስደሰት ስንል ብቻ አፋችን እንዳመጣ የባጥ የቆጡን የምንዘባርቅ ሰዎች የምንላቸዉ ነገሮች እኛዉ ዘንድ ዞረዉ መጥተዉ መጥፊያችን ሊሆኑ ይችላሉ። በቅርቡ ዋሺንግተን ዲሲ ብቅ ብለዉ የነበሩትን የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ያጋጠማቸዉ ይሄዉ በጋዛ አፍ ተናግሮ የመጥፋት ቅሌት ነበር። ዶ/ር ቴድሮስ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ መንግስታቸዉ የሰራተኛ ደሞዝና የአየር ላይ ወጪ እየከፈለ በሚያስተዳድረዉ ሬድዮ አፋቸዉን ሞልተዉ የተናገሩትን ነገር አዲስ አበባ ተመልሰዉ በፌስ ቡካቸዉ በለቀቁት መልዕክት ለማስተባበል ቢሞክሩም ነገሩ “ከአፍ ከወጣ አፋፍ” ሆኖባቸዉ በስህተት ላይ ስህተት እየፈጸሙ ይገኛሉ።

ሬድዮ አገር ፍቅር በመባል ከሚታወቀዉ ሳምንታዊ ሬድዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ መሪዎች የአሜሪካ መንግስት ጓንታናሞ ዉስጥ ካሰራቸዉ የአልቃይዳ አባላት ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ ማረጋገጫ አግኝተናል ካሉ በኋላ የአሜሪካ መንግስት ይህንን ግኑኝነት አስመልክቶ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን ኢትዮጵያ ድረስ ሄዶ ለማነጋገር ለመንግስታቸዉ ጥያቄ እንዳቀረበ ተናግረዋል። ያልነገሩን ነገር ቢኖር የአሜሪካ መንግስት ባቀረበዉ ጥያቄ መሰረት ቃሊቲ ድረስ ሄዶ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን ማነጋገሩንና አለማነጋገሩን ብቻ ነዉ።

Tuesday, August 19, 2014

የሕዳሴ አብዮት ለፖለቲካው ( አስራት አብርሃም)


ወዳጄ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የህዳሴው አብዮት አይቀሬ እርግጠኛ ሆኗል፤ እኔም ያለኝ ግምት ተመሳሳይ ነው። በመሆኑም የዛሬው ፅሁፌ የሚያተኩረው የህዳሴው አብዮት እንዴትና የት ይጀምር? በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ይሆናል። በእኔ እምነት የህዳሴው አብዮት መጀመር ያለበት ከራሱ ከተቃውሞ ጎራ ነው የሚል ነው። ምክንያቱም የለውጡን ሀይል የሚመራው ይሄ የተቃውሞ ጎራ ስለሚሆን በመጀመርያ ውስጡን ማጥራትና ማጠናከር ስላለበት ነው። ስለዚህ፣ ከሁሉም ነገር በፊት የተቃውሞ ጎራው በትክክልና በተገቢው ሁኔታ እንዲታደስና እንዲለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል ማለት ነው። ስለፖለቲካው መታደስና መለወጥ ሲታሰብ ደግሞ እንዴት ነው የሚታደሰው? እንዴት ነው የሚለወጠው? የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሳት ተገቢ ይሆናል። የመጀመርያው ነገር፣ እስካሁን ከተጓዝንበት ኋላቀርና ውጤት አልባ የትግል ስልት የሚያወጣን፣ የተለየ ያካሄድ ለውጥና የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ለማደረግ የሚያስችለን ብቁ የሆነ ፖለቲካዊ አመራር ወደፊት እንዲመጣ ማድረግ ነው። በተለይ ደግሞ ፖለቲካዊ ትግሉ በአስራር፣ በአደረጃጀት፣ በዴሞክራሲያዊ ባህልና በበሳል አመራር ማጠናከርና ማነፅ ቀዳሚው ተግባር ነው የሚሆነው።

በቅርቡ ሊካሄድ ታስቦ የነበረውና በኋላ በምርጫ ቦርድ ምክንያት ለጊዜው የተቋረጠው የአንድነትና የመኢአድ ውህድ ፓርቲ ፕሬዝደንት የሚሆን ሰው ለመምረጥ በአንድነት ውስጥ የታየው እጅግ ማራኪና አስተማሪ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ውድድር፣ የሰለጠነ የእጩዎቹ ደጋፊዎች ቅስቃሳ የዚሁ የህዳሴው አብዮት ጅማሮ አድርጌ ነው የምወስደው። ይሄ ዴሞክራሲዊ የሆነ ውድድር በማህበራዊ ሚዲያዎች፣ በጋዜጦችና በመፅሔቶች በጉልህ ይታይ ስለነበር የተቃውሞ ጎራ አባላት፤ ህዝቡ፣ የገዥው ፓርቲ ሰዎችም ጭምር በአንክሮ እንዲከታተሉት ምክንያት ሆኗል። ይህ እንቅስቃሴ አንድነትን ወደ ተሻለ ከፍታ የሚወስደው ከሆኑም ባሻገር ልክ እንደ ዐረቡ አብዮት ወደ ሁሉም የተቃውሞ ጎራ የሚዛመት አዲስ መንፈስ ነው ብዬ ነው የማስበው። ምንም እንኳ በተወሰነ መልኩ በዴሞክራሲያዊ ውድድርና በውስጣዊ መከፋፋል መካከል ያለውን ልዩነቱ በትክክል ያልገባቸው ወይም እንዲገባቸው ያልፈለጉ አንዳንድ ሰዎች የሚፈጥሩት ችግር የነበረ ቢሆንም በአጠቃላዩ እንቅስቃሴ ሲታይ ግን በኢትዮጵያ የፓርቲዎች ታሪክ ውስጥ በአዲስነቱ፣ በፈር ቀዳጅነቱና በአንፀባራቂነቱ ሊታወስ የሚችል ነው። ከዚህ ልምድ በመውሰድ የአንድነት አባላት ዴሞክራሲያዊ በሆነና በሰለጠነ መንገድ መሪዎቻቸውን መምረጥ የሚችሉበት ሁኔታ ከፈጠሩ፤ የሌሎች ፓርቲ አመራር አባላትም በተመሳሳይ መንገድ መሄድ የማይችሉበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም። ስለዚህ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የተሳካ የተሀድሶ አብዮት ማካሄድ ከቻልን ቀጥሎ በመኢአድ፣ በመድረክ፣ በአረና፣ በኦፌኮ፣ በደቡብ ህብረት፣ በኢዴፓና በአጠቃላይ በተቃውሞ ጎራ ባሉ ኃይሎች ሁሉ ይሄ የለውጥ እንቅስቃሴ እንዲቀጣጠል እድል የሚፈጥር ነው የሚሆነው። በመሆኑም ውህደቱ ለጊዜው ቢጨናገፍም በአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ዘንድ የተጀመረውን የትግል መነሳሳት መቀዝቀዝ የለበትም። ይሄ መነሳሳት ፓርቲውን በአዲስ መንፈስና በአዲስ ፖለቲካዊ አካሄድ ለማስኬድ በሚያስችል መልኩ ልንጠቀምበት እንችላለን። ባለበንት እንድንረግጥ ከሚያደርገን ያረጀና ያፈጀ ፖለቲካዊ አሰራር ፖለቲካው ይላቀቅ ዘንድ የለውጥ ኃይሉ በአንድነት ውስጥ የፓርቲው ህግና ስርዓት በሚፈቅደው መሰረት የተሀድሶ እና የለውጥ እንቅስቃሴ ማካሄድ መቻል አለበት። ይሄ የለውጥ እንቅስቃሴ የፓርቲውን አንድነትና ጥንካሬ አስጠብቆ አሸናፊ ሆኖ የሚወጣ ከሆነ በሁሉም የተቃውሞ ጎራ ውስጥ የሚቀጣጠል፤ በእንቅልፍና በድንዛዜ ውስጥ ያሉት ፓርቲዎች ሁሉ የለውጥና የፀደይ አብዮት ውስጥ የሚገቡበት ሁኔታ እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆን ነው።

የፀጥታ ሃይሎች በጭፍን ታዛዥነት የሚጥሷቸው መሰረታዊ መርሆች

ድምፃችን ይሰማ!

በሃገራችን ኢትዮጵያ ህገ መንግስት መግቢያ ላይ በግልፅ እንደሰፈረው ሃገራችንን እንዲመራ የሚመሰረተው መንግስት በኢትዮጵያ ህዝቦች ነፃ ፍላጎት፣ በህግ የበላይነት እና በህዝቦች ፈቃድ የህዝቡን የጋራ ጥቅም፣ መብት እና ነፃነት እንዲያስከብር የሚመሰረት የፖለቲካ ተቋም ነው፡፡ ይህ የፖለቲካ ተቋምም ህዝባችንን በትጋት እና በህግ በታቀፈ አካሄድ እንዲያገለግል ተደርጎ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባው ህገ መንግስቱ በጥብቅ ያሳስባል፡፡ በመቀጠልም ህገ መንግስቱ በአንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ህዝቦች የሃገራችን ኢትዮጵያ ሉአላዊ ስልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ረጋግጣል፡፡ ከዚያም በመቀጠል በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 1 ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ማንኛውም የውስጥ ደንብም ይሁን መመሪያ ውድቅ መሆን ያለበት መሆኑን በማስገንዘብ ያሰፈረ ሲሆን በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 2 ደግሞ ማንኛውም የመንግስት አካልም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ለህገ መንግስቱ ተገዢ መሆን እንዳለበት በጥብቅ ያስገነዝባል፡፡

እንግዲህ በህገ መንግስቱ መግቢያና በአንቀፆቹ የተገለፁትን ሃሳቦች ጠቅለል ባለ መልኩ ከተመለከትናቸው በሃገራችን የሚመሰረተው መንግስት ህዝብን ለማገልገል የሚመሰረት ተቋም መሆኑን እና የመንግስት አካል ሆነው የሚፈጠሩ ማናቸውም ክፍሎች ለህገ መንግስቱ ተገዢዎች፣ እንዲሁም ህገ መንግስቱን በተግባር ለመተርጎም የሚፈጠሩ መሆን እንዳለባቸው እንረዳለን፡፡ በተቃራኒው ህገ መንግስቱን የማፋለስ እና የመርገጥ መብት የሌላቸው መሆኑንም እንገነዘባለን፡፡ በተጨማሪም በማንኛውም የመንግስት ተቋማት ተቀጥሮ የሚሰራ ግለሰብ ዋነኛ እና ከፍተኛ ኃላፊነቱ ህዝብን ማገልገል እና የህዝቡን ጥቅም እና ነፃነት መጠበቅ መሆኑን እንረዳለን፡፡

ከዚህ መሰረታዊ ሃሳብ ከተነሳን በመንግስት ተቋማት ውስጥ በመቀጠር የህዝብን መብት እና ነፃነት የሚጋፉ፣ ወይም የማህበረሰባቸውን መብት እና ነፃነት የሚገፍ ማንኛውንም ትዕዛዝ የሚቀበሉ፣ የሚፈፅሙ እና የሚያስፈፅሙ አካላት ቢያንስ የሚከተሉትን ሶስት መሰረታዊ የህገ መንግስት ጥሰቶች መፈፀማቸውን ልንገነዘብ እንችላለን፡-

የሕዝብን የነፃነት ትግል ማስቆም ፈጽሞ አይቻልም (ሸንጎ)

ነኅሴ 10 ቀን 2006 

የአንድነት ፓርቲና የመኢአድ አመራሮችና አባላት ድርጅቶቻቸውን ለማዋሃድና የሚያደርጉትን ሰላማዊ የነፃነት ትግል ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር እንቅስቃሴ ከጀመሩ በርካታ ወራት እንዳስቆጠሩ የሚታወቅ ነው። የሀገሪቱ አፋኝ ህግ በሚፈቅደው መሠረት በጥሞና ደረጃ በደረጃ ተንቀሳቅሰው የውህደቱን ሂደት ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን የጋራ ጉባኤ ለማካሄድ ጥቂት ቀናት ብቻ ሲቀር የህወሓት/ኢህአዴግ መሣሪያ የሆነው “የምርጫ ቦርድ” ሰበብ በመፍጠር የታቀደው የውህደት ጉባኤ እንዳይካሄድ አድርጓል። ይህን እጅግ አሳፋሪና ተራ አፍራሽ ተግባር ሸንጎ አጥብቆ ያወግዛል።

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]———

Monday, August 18, 2014

_______ ለአገረ-ኢትዮዽያ _______


በድቅድቅ ጽልመት ውስጥ..
እንደክዋክብቱ..የሚያንፀባርቁ
በሃይለ-ብርሐናቸው..
ገዝፈው የሚታዩ..ጐልተው የደመቁ
በፍርሐት በረሐ..
እንደምንጭ የነጡ..ጠርተው የፈለቁ
በዕውቀት የዘለቁ..
ከድንቁርና ጋር..ቀድመው የተራራቁ
የማይታረቁ..
ከአመጽ..ከብጥብጥ..
ከሁከት..ከነውጥ..
ከሽብር መንፈስም..የማይተዋወቁ
እነሐሳበ-ስንቁ..እነብዕር ትጥቁ
ተቃራኒ ሃይላትን..
በእኩይ ተግባራቸው..ክፉኛ ያስጨነቁ
በማይታሰረው..
በማይበገረው..
ሠርክ በሚኖረው..
ጽኑ መንፈሳቸው..የነጻ አዕምሯቸው
በብርቱ ኃይላቸው..በብሩህ ተስፋቸው

Sunday, August 17, 2014

እንደገና ይድረስ ለሠራቱ

“የትግሬ” ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ራሱን የሠየመው የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን አገሪቷን እያጎሳቆለ ያለው ከሠራዊቱ ጀርባ ተንጠላጥሎ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን የተሸከመውን ሠራዊት ሳይቀር በጉስቁልናና በድንቁርና እንዲኖር ፈርዶበታል። ህወሃት ሠራዊቱ እንዲማር፤ ዘመኑ ከሚፈቅደው የቴክኖሎጂ እውቀት ጋር ራሱን እንዲያዋህድ እና በራሱ የሚተማመን የዘመነ ሠራዊት እንዲሆን ፍላጎት የለውም።አሜሪካን በአገሯ በሚገኙ የጦር ትምህርት ተቋማት ውስጥ ወታዶሮችን ለማሰልጠን ፍላጎት ብታሳይም ሳሞራ የኑስና መለስ ዜናዊ እምቢ ማለታቸውን አብዛኛው የሠራዊቱ አባላት የሰሙት አይመስልም። አሜሪካን በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ 42 ወታደሮችን አገሯ ወስዳ ለማስለጠን በጠየቀች ግዜ ሳሞራ የፈቀደው 13 ወታደሮች ብቻ ሂደው እንዲማሩ ነው። እነዚህም ከህወሃቶች መካከል ፊደል የቆጠሩ ተፈልገው በመገኘታቸው መሆኑም ታውቋል። በሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች የትምህርት ዝግጅት ቢኖራቸውም የትምህርት እድሉን ተከልክለዋል።

ህወሃት ከራሱ ውጪ ያሉት ሌሎች ላይ ምንም ዕምነት እንደሌለው በተለያየ አጋጣሚ ተናግሮታል። የትምህርት ዕድሉን ለምን መጠቀም እንዳልፈለጉ ሲጠየቅ ሳሞራ የኑስ “ሌሎችን አናምናቸውም አሜሪካን ሂደው ይቀራሉ” ብሎ መልስ መስጠቱም ተመዝግቦ ይገኛል። 11ኛ ክፍልን ያልዘለለው የህወሃቱ ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ ሠራዊቱን ታማኝና የማይታመኑ በሚል ይከፍላቸዋል። የህወሃት አባል የሆነ ወታደር ታማኝ ፤ ሌሎች የሠራዊቱ አባላት የማይታመኑ።

አሁንም የሠራዊቱ አባላት ስሙ !

እናንተ ምንም ያክል ጥሩ ዜጋ ለመሆን ብትጥሩ በህወሃቶች ዘንድ የምትታመኑ አይደላችሁም። ህወሃቶች ከእነርሱ ውጪ ባሉ ሌሎች ላይ ጥርሳቸውን እንደነከሱ እስከ ዛሬ አሉ። በሌሎች ዜጎች ላይ የመዘዙት የበቀል ሰይፍም ወደ ሰገባው የሚመለስ አልሆነም። በሁለት ዓመት ውስጥ 42 ወታደሮችን አሜሪካን ወደ አገሯ ወስዳ ለማስልጠን ብትጠይቅም 13ቱን ብቻ ተቀብለው 29ኙን አንፈልግም ማለታቸው የተመዘዘው የበቀል ሰይፋቸው አንዱ አንጓ መሆኑን የትምህርት ዕድሉን የተነፈገው የሠራዊቱ አባል ልብ ሊለው ይገባል። እነ ሳሞራ የኑስ ከእነርሱ ውጪ ያሉ ሌሎች ዜጎች በድንቁርናና በችጋር እየተሰቃዩ ይኖሩ ዘንድ ፈርደውበታል። በእንዲህ ሁኔታ እንዲኖር የተፈረደበት ሠራዊት፤ ውጪ አገር ሂዶ እንዳይማር የተከለከለ ሠራዊት፤ ዘር ሃረጉ እና ድርጅታዊ ታማኝነቱ እየታየ ለሹመት የሚበቃው የሠራዊት አባል ይህን ውስኔ ለወሰነበት ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ከሚያገኛት ከወር ደመወዙ ላይ ቆርጦ እንዲከፍል ይደረጋል። እንዲህ ዓይነት በደል በየትኛውም አገር ታይቶ አይታወቅም።

“አሸባሪነት” በወያኔ አገዛዝ ሥር ባለችው ኢትዮጵያ

በአገራችን፣ በወያኔ አገዛዝ መደበኛ ትርጉማቸውን ከሳቱ በርካታ ቃላት መካከል “የሽብር ድርጊት“ እና ”አሸባሪ“ የሚሉት ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። ሰፊ ተቀባይነት ያለው የአሸባሪ ትርጉም “የሽብር ድርጊቶችን የሚፈጽም ሰው ወይም ድርጅት” ማለት ነው። “የሽብር ድርጊቶች” የሚባሉት ደግሞ የተለመዱ ጥቃቶችን ሳይሆን የሀይማኖት፣ የፓለቲካ ወይም የርዕዮተዓለም ግብ ለማሳካት ሲባል በሰዎች ላይ ፍርሀትን ለማንገስ፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሱ አስከፊ ጥቃቶችን ነው። የሽብር ድርጊቶችን ሰላማዊውን ሕዝብ ጭዳ የሚያደርጉ በመሆኑ በጥብቅ ሊወገዙ ይገባል። ዓላማን በሽብር ድርጊቶች ማስፈፀም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

በወያኔ መዝገበ ቃላት ግን “ሽብርተኛ” እና “የሽብር ድርጊቶች” በዘፈቀደ የሚነገሩ ተራ ቃላት ሆነዋል። ስለአገራቸው እና ስለትውልድ የሚጨነቁ፤ ሀሳባቸው በነፃነት የሚያራምዱ፤ የወያኔን ፕሮፖጋንዳ እንደ በቀቀን የማይደግሙ ዜጎች “አሸባሪዎች” እየተባሉ ወደ እስር ቤቶች እየተወረወሩ ነው። ጋዜጠኞች፣ ጦማርተኞች፣ ፍጹም ሰላምተኛ አማኞች እና ሰላማዊ ፓለቲከኞች በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዙ ናቸው።

በአንፃሩ ደግሞ እውነተኛው አሸባሪ ህወሓት፣ የመንግሥትን ሥልጣን ይዞ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማሸበሩን በስፋት ተያይዞታል። ህወሓት ዘረኛ ርዕዮተ ዓለሙን ለማስፈፀም ሲል ባለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ውስጥ የፈፀማቸው የሽብር ድርጊቶች ተዘርዝረው አያልቁም። የህወሓት የሽብር ድርጊቶች ዓላማ የኢትዮጵያን ሕዝብ በፍርሀት አደንዝዞ መግዛት ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ “አሸባሪ” የሚለውን ቃል ራሱ በማሸበሪያ መሣሪያነት እያዋለው ነው። ይህ የውስጥም የውጭም ታዛቢዎችን የሚያሳስት በመሆኑ ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ነው።

Monday, August 11, 2014

የአንዳርጋቸዉ ትዉስታዎች

“በእኛ እምነት ታሪክ ከነባራዊ ሁኔታ ዉጭ በምኞትና በዘፈቀደ አይሰራም። የሚሰራ ቢሆን ኖሮ ነገስታቱና አምባገነኖቹ ዘሬም በዙፋናቸዉ ላይ በተገኙ ነበር። ባለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ህዝቦች መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆመዉ ከዚህ ወዴት እንደሚሄዱ ግልጽ ኢየባልሆነበት ሰዐት ሥልጣን ላይ ያለዉም ሆነ የሌለዉም የግሉን የተስፋ ጎዳናን እዉነተኛዉ የወደፊት ጎዳና አድርጎ የሚያይ ከሆነ ዛሬም እንደ ትናንቱ ከታሪክ መማር አልቻልንም ማለት ነዉ”።

“ከዲሞክራሲ ጋር ሲወዳደር ፍትህ ለሚለዉ ጽንሰ ሀሳብ “ኢትዮጵያዊኛ” ቃላቶች ያሉን መሆኑ የሚያስረግጠዉ ነገር ቢኖር ፍትህ ከማንነታችን ጋር የተቆራኘ መሆኑን ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ፍትህ ሲጓደል “በህግ አምላክ” ብለዉ በዳያቸዉን ለማስቆም የሚያሰሙት ጩኸት ፍትህ ከፈጣሪያቸዉ የተሰጠ ከሰብዓዊነታቸዉ ተነጥሎ የማይታይ እሴት አድርገዉ እንደሚመለከቱት የሚያመለክት ነዉ። በምድር ላይም ፍትህ የሚሰጥ ዳኛ ጠፍቷል ብለዉ ሲያስቡ እጃቸዉን ወደ ፈጣሪያቸዉ ዘርግተዉ አንተዉ ፍርዱን ስጠና የሚሉት ከፈጣሪያቸዉ ፍጹምነት የሚመነጭ እዉነተኛ ዳኝነት አለ ብለዉ ስለሚያምኑ ነዉ። ከዚህ በላይ ባጭሩ የተባለዉ የሚጠቁመዉ በኢትዮጵያዉያን ባህልና ስነ ልቦና ዉስጥ የፍትህ ጽንሰ ሀሳብ ያለዉን ትልቅ ትርጉምና ቦታ ነዉ”።

የታሪክን ነባራዊነት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ለፍትህ የሚሰጠዉን ከፍተኛ ቦታና ለነጻነት ያለዉን አመለካከት በተመለከተ ከዚህ በላይ ያሰማናችሁን ሁለት አዉዶች በሁለት የተለያዩ መጽሐፎቹ ዉስጥ የጻፈዉ ዛሬ ፍትህ አልባ በሆነዉ የወያኔ ስርዐት ዉስጥ ለፍትህ፤ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ሲል ለፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ያለዉ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ነዉ። አዎ የፍትህና የነጻነት አርበኛዉ አንዳርጋቸዉ በግልጽ አንዳስቀመጠዉ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍትህ እስከነ ስሙ ሙልጭ ብሎ በመጥፋቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለት እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ እባክህ አምላኬ “ወይ ዉረድ ወይ ፍረድ” እያለ ፈጠሪዉን እየተማጸነ ነዉ። በእርግጥም ፍትህ ፈጣሪያችን ያደለን ትልቅ ማህበራዊ እሴት ነዉ፤ ሆኖም ይህንን የፈጣሪ ስጦታ እኛን የመሰሉ ሌሎች ሰዎች መጥዉ ሲቀሙንና እንዳሰኛቸዉ ሰረግጡን አንረገጥም ብለን እራሳችንን ነጻ ማዉጣትና የተቀማነዉን ፍትህ ከወያኔ ዘረኞች ቀምተን መልሰን ማህበራዊ እሴት የማድረጉ ኃላፊነት የእኛ የራሳችን ነዉ እንጂ የፈጣሪ አይደለም። ፈጣሪያችን ፍትህና ነጻነትን አንዴ ሰጥቶናል እነዚህን የፈጣሪ ስጦታዎች እንዳንቀማ መጠበቅና ከተቀማን ደግሞ ታግለን ማስመለስ ያለብን እኛ ብቻ ነን።

‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በበፍቃዱ ሃይሉ (ከእስር ቤት የተላከ ማስታወሻ)

‹‹ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!››፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ፡፡ በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ‹‹አባሪዎቼ›› ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል፡፡ ይኼ ነው እንግዲህ የምርመራችንን ሒደት የሚገልፀው ጥያቄ፡፡ ‹‹ተጠርጥረን›› የተያዝንበትን ጉዳይ የሚያረጋግጥ ሥራ ሠርተን ባለመገኘታችን (ወይም ‹‹ባለመናገራችን››) ታዲያ ጥፋትህ ምንድን ነው? ተባልን፡፡ ምርመራው የኛን ነፃ መሆን አለመሆን ለማጣራት ሳይሆን ጥፋት ለማግኘት ነበር፡፡ ብዙዎች ‹መንግሥት ዞን ዘጠኝን ለምን ሁለት ዓመት እንደታገሠው› ግራ በመጋባት ይጠይቃሉ፤ ባሕሪው አይደለምና፡፡ የኢትዮጵያ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ምኅዳር በቀላሉ እንደገመቱት ተይዘን፣ ተመርምረንና ‹‹ተገኘባችሁ›› የተባልነው ‹‹ የግንቦት 7 [እና ኦነግም ጭምር] አባልነት [ብሎም ግብ አስፈጻሚነት] ›› በሽታ ለተከሳሽነት አብቅቶናል፡፡ ቀጣዩ የክርክር ሂደት ነው፡፡

ከዚያ በፊት ግን ዞን ዘጠኝን በሩቅም በቅርብም የሚያውቁ በግራ መጋባት መልስ እንደሚሹ በማሰብ ይቺን አጭር ማስታወሻ ለመጻፍ ተገድጃለሁ፡፡ የእስራችን ሂደት ምን ይመስላል? የምርመራችንስ? እውን የግንቦት ሰባት አባል ነን? [ታዲያ] ለምን ታሰርን? በቅርቡ እንፈታ ይሆን?

ደቂቃም ይሁን ሊቅ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እውነታ የሚጽፍ ማንኛውም ሰው [ኢትዮጵያ ውስጥ ሳለ] አንድ ቀን እታሰር ይሆን እያለ መስጋቱ አይቀርም ፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በአንድ መጽሐፋቸው ላይ ሰው ነገረኝ ብለው የኢትዮጵያ ሕዝብን በሦስት የመደቡት፡- የታሰረ፣ ታስሮ የተፈታ እና ወደፊት የሚታሰር በማለት፡፡ እርግጥ ዞን ዘጠኝ ‹‹ሐሳቡን መግለጽ ፈርቶ ዝም ያለ ሁሉ እስረኛ ነው›› ብሎ መደምደም ሦስቱም ምድብ አንደኛው ውስጥ ያጠቃልለዋል ‹‹የታሰረ›› በሚል፡፡ ዞን ዘጠኞች ጦማራችንን በከፈተን በሁለት ሳምንት ሲታገድብን እና ሌላ ስንከፍት ግና መጨረሻ ላይ ታጋቾቹ እኛ እንደምንሆን እናውቅ ነበር፡፡ ያንን የሚያረጋግጥ ተደጋጋሚ የደህንነቶች ክትትል እና ምልክቶች ስለደረሱን መታሰራችን ማስደንገጡ ባይቀርም ያልተጠበቀ ግን አልነበረም፡፡

እስሩ በክትትሉ የተገኘነውን ስድስት የዞን ዘጠኝ አባላት እና ሦስት ጋዜጠኛ ጓደኞቻችንን መሆኑን በተለይ የጋዜጠኞቹ [ቢያንስ ለእኛ] ያልተጠበቀ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የኋላ ኋላ ስንመለከተው ግን በእኛ አስታኮ እነሱንም ማሰሩ የታሰበበት ዘመቻ እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡ እኛን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሒደትም ቢሆን በቅጡ የታሰበበት ነበር ሁላችንም (ከአስማማው በቀር) ከቀኑ በ11፡00 ገደማ በያለንበት ስንያዝ አስማማው በማግሥቱ ታስሯል፡፡ ሌሎቻችን ቤታችን በሚፈተሸበት ሰዓት ሕጉ የሚፈቅድበት ሰዓት(12፡00) አልፎ ነበር፡፡ በቁጥጥር ስር ካዋሉን በኋላ የሕገ-ወጥ አያያዝ ሰለባ የመሆናችን ሂደት የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡
ማዕከላዊን በክፉ ስሙ ቀድሞ ለሚያውቀው ሰው ግቢውን መርገጥ በራሱ ልብን ያርዳል፡፡ ሆኖም በልቤ /ጓደኞቼም እንደእኔ ሳይሰማቸው አይቀርም/ አንደኛ እኛ ጸሐፊ እንጂ ወታደር ወይም ሰላይ ባለመሆናች፣ ሁለተኛ መቼም ከበፊቱ የተሻለ ሰብዓዊ አያያዝ ሳይኖርም አይቀርም የሚል የዋህ ተስፋ በማሳደሬ ብዙም አልተሸበርኩም ነበር፡፡ የገባሁ እለት ከታሳሪዎች በተሰጠኝ ማብራሪያ ‹‹ሳይቤሪያ›› መግባቴን አወቅኩ፡፡ ከዚያ የ HRW-They want confession የተሰኘ ሪፖርት ላይ የተፃፉ ነገሮች ሁሉ ትክክል መሆናቸውን ለመረዳት የፈጀብኝ ከአንድ ሳምንት ያነሰ ጊዜ ነበር፡፡

ደጋፊዎችን የማሰባሰብ ጥረት

የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በህሊናና የፓለቲካ እስረኞች ሁሉ ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ መክበድ፤ በፀረ-ሽብርተኝነት ስም በሕዝብ ላይ የሚነዛው ወያኔያዊ ሽብር መብዛት፤ እስሩ፣ እንግልቱ፣ መሳደዱ፣ የሀብት ዘረፋው በየዕለቱ እየጨመረ መምጣት እና ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ኑሮ እየከበደ መምጣቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ጋር ወሳኝ የሆነ ትግል መግጠሚያ ወቅት ላይ መደረሱ አመላካች ሆኗል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግል መንፈስ መነሳሳት በተጨባጭ ከሚያረጋግጡ አመላካቾች አንዱ የግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አባል ለመሆኑ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መጨመር ነው። ይህንን ለውጥ ተከትሎም ግንቦት 7 የአባላት ቅበላን ሥራ ለማፋጠን የሚረዱ እርምጃዎች ወስዷል። ሆኖም ግን በአባላት ቅበላ ወቅት ሊታለፉ የማይችሉ ጥንቃቄዎች መኖር እንዳለባቸው ደጋፊዎችም እጩ አባላትም ይረዳሉ ተብሎ ይታመናል።

በዚህም ምክንያት አሁንም እየጨመረ የመጣን ንቅናቄውን የመቀላቀል ፍላጎትን ለማስተናገድ፤ ለተግባራዊ ሥራዎች የተነሳሱ፣ ዓላማችንና ንቅናቄዓችንን የሚደግፉ ሆኖም ግን በተለያዩ ምክንያቶች በድርጅት አባልነት መቀላቀል የማይችሉ ወይም የማይፈልጉ አባላትን ለማሳተፍ የሚረዳ መዋቅር ማዘጋጀት ተገቢ መሆኑ ታምኖበታል። ስለሆነም እነዚህን ወገኖቻችን የትግላችን አካል ብቻ ሳይሆን የንቅናቄዓችንም አካል ለማድረግ እንዲቻል በአባላት ጉዳይ ሥር የደጋፊዎች ማስተባበሪያ መዋቅር እንዲደራጅ ተደርጓል። ይህ አደራጀት ግንቦት 7ን ለማዘመን እና ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የተመቸ ድርጅት ለማድረግ የሚደረገው ጥረት አካል ነው። ይህ አደረጃጀት በአንድ በኩል የድርጅቱን ምስጢራዊት ለመጠበቅ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ ባሉ ፍላጎቶች መካከል ያለውን ቅራኔ ለመቅረፍ የቀረበ መፍትሔ ነው።

በዚህም መሠረት በአባልነት ለመመዝገብ ስለእናንተ ምስክርነት መስጠት የሚችል የግንቦት 7 አባል ማቅረብ ለጊዜው ያልቻላችሁ፤ ወይም በሌላ ማናቸውም ምክንያት የግንቦት 7 ደጋፊ እንጂ አባል መሆን የማትፈልጉ ወገኖቻችን ግንቦት 7 ፍላጎታችሁን የሚያሟላ መዋቅር ማዘጋጀቱን በይፋ ያበስራል።

Saturday, August 9, 2014

የወያኔን ሴራ በማጋለጥ የድርሻችንን እንውጣ!!!

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ፋሽስቱ የወያኔ ቡድን የሚያደርገው ነገር የአምባገነኖችን ልዩ በሀሪ የሆነውን ስራ በመስራት ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየሰራ ያለውን ሴራ እንደሚከተለው በእኔ አስተያየት መግለጽ እፈረልጋለሁ፡፡

ሴራ 1
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን፤ አባላትን እና ደጋፊዎችን በማዋከብ እና በማሰር ቀጣዩን “ምርጫ” ልክ እንደ አለፉት “ምርጫዎች” ብቻውን አሸንፎ እንደገና ሌላ የመደንቆሪያ ና ህዝብን የማሰቃያ 5 ዓመታትን በእጁ ለመጨበጥ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡ እስኪ ተመልከቱት እነዚህ የተቃዋሚ መሪዎች ላይ እንደዚህ አይነት ውንብድና የተሰራው (እንደዚህ አይን ያወጣ ባይሆንም)” በምርጫ” 2002 ጊዜ በዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ የተፈፀመውን አይነት ውንብድና ማለት ነው፡፡ ምርጫው ካለፈ በሁዋላ የተቃዋሚ መሪዎችን በመፍታት ከሀገር እንዲኮበልሉ በማድረግ ኢትዮጵያን ( በወያኔዎች አጠራር ሀገሪቱን) የግል ንብረታቸው ለማድረግ የተጠነሰሰ ሴራ ነው፡፡

ሴራ 2
ጋዜጠኞችን በማሰር፤ በማዋከብ፤ በመደብደብ፤ አልበቃቸው ብሎ ግማሽ ደርዘን የህትመት ውጤቶችን በመዝጋት የቻሉት ከሀገር ተማረው እንዲወጡ ያልቻሉት ደግሞ ወደ ቃሊቲ፤ ቂሊንጦ፤ ዝዋይ….እንዲሰደዱ በማድረግ ለህብረተሰቡ ትክክለኛ እና ሚዛናዊ የሆነ መረጃ እንዳይደርሰው በማድረግ የዜና ምንጮችን በማድረቅ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ጋዜጠኞችን በአሸባሪነት መፈረጅ ማለት ምን ማለት ነው? ማንኛውም ግለሰብ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ በአሸባሪነት ለመፈረጅ አለማቀፋዊ መመዘኛወችን ወደጎን በመተው ስለተቃወሙ ብቻ ወይንም የወያኔን ፖለቲካዊ አመለካከት ስላልተቀበሉ ብቻ በገዛ ወገኖቻቸው ለግርፋት እና ለስቃይ በቅተዋል፡፡ ስለዚህ ለእነዚህ ወገኖቻችን ከጎናቸው መሰለፋችንን እንዲያውቁት እና ተስፋ እንዳይቆርጡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለወያኔዎች ማሳየት ያለብን ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት ጊዜ በመገኜት እና ሞራል በመስጠት ልናበረታታቸው ይገባል፡፡ በየማህበራዊ ድሀረረ ገጾች ላይ ወያኔዎች እየፈጸሙት ያለውን ግፍ ለህብረተሰቡ ማጋለጥ ይሄ ሀገር ወዳድ የወያኔ አባላትንም ይመለከታል(እንደ ንስሃ ይቆጠርቸዋልም) መረጃ በመስጠት መተባበር፡፡

Friday, August 8, 2014

በአምስት ነጻ ጋዜጦች ላይ ጥቁር ሽብር እየተፋፋመባቸው ነው!!

ከትላንት በስትያ የፍትህ ሚንስትር መስሪያ ቤት በህዝብ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና ሬድዮ አምስት ጋዜጦችና መጽሄቶች ህገ መንግስቱን ለመናድ መሞከራቸውን በመግለጽ መግለጫ አውጥቶ ነበር። የመግለጫው ጭብጥ እንደሚያስረዳው ከሆነ፤ አምስት የፕሬስ ውጤቶች መንግስትን ሰላም የነሱ መሆናቸውና ወደፊትም በእንደዚህ መሰል የፕሬስ ውጤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ዛቻ በተቀላቀለበት ሁኔታ የተገለጸው። በአሁኑ ወቅት የሰብ አዊ መብት ገፈፋዎችን ጨምሮ ከህግ ውጭ የሚደረጉ የመንግስት አሸባሪ እርምጃዎችን፣ “ጥቁር ሽብር” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ይህ በፕሬስ ውጤቶች ላይ የተካሄደው እርምጃም የ”ጥቁር ሽብር” ሌላኛው ማሳያ በመሆኑ በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው።

በስም የተጠቀሱት አምስት የፕሬስ ውጤቶች ክስ ሳይመሰረትባቸው፤ ለፖሊስ ቃላቸውን ሳይሰጡ፤ የፍርድ ቤት መጥሪያ ሳያገኙ ነው፤ የፍትህ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ “አሸባሪ” የሚል ስያሜ ሊሰጣቸው የሞከረው። የፍትህ ሚንስቴር መስሪያ ቤት በዚሁ መግለጫው ላይ “ፋክት፣ ጃኖ፣ ሎሚ፣ አዲስ ጉዳይ፣ እና እንቁ የሚባሉ መጽሄቶችን እንዲሁም አፍሮታይምስ የሚባለውን ጋዜጣ በሚያሳትሙ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መስርቻለሁ” ብሏል። ይህ ክስ ፕሬሶቹ በቀጣይ የህትመት ስራዎቻቸውን ለማገድ የታቀደ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎ ህትመት ያቆሙ መጽሄቶች እና ጋዜጦች ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር የለም።

ትላንት ረቡዕ ለህትመት ወጥቶ የነበረው ሰንደቅ ጋዜጣ ይህን ጥቁር ሽብር አስመልክቶ የፍትህ ሚንስቴርን መግለጫ በማስቀደም የፖለቲካ ፓርቲ ሃላፊዎችንእና ጋዜጠኞችን አነጋግሯል። ስለሁኔታው ተጨባጭ መረጃ ይኖራቹህ ዘንድ የሰንደቅ ጋዜጣን ዝግጅት በፒ.ዲ.ኤፍ አቀናብረን ከዚህ በታች አቅርበነዋል። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።

Monday, August 4, 2014

ሠራዊቱ የህዝብ ወገንተኛነቱን የሚያስመሰክርበት ግዜ እየመጣ ነው

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የቀደመው ትውልድ ከቱርክ ኤምፓየር፤ ከግብፅ እና ከደረቡሽ፤ ከጣሊያን ወራሪ፤ ከሶማሊያ ተስፋፊ ኃይል እና ከሌሎችም የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተዋግቶ አገሪቷን ለአሁኑ ትውልድ ለማቆየት ትልቅ መስዋዕትነት ከፍሏል። በተለይ ነፍጥ አንግቦ የተሠለፈው ኃይል የከፈለው የህይወት መሥዋዕትነት የሚረሳ አይደለም። አገራችን ኢትዮጵያ ለዛሬው ትውልድ የቆየችው ከራሱ ይልቅ ለአገርና ለወገን የሚያስብ ትውልድ በመኖሩ መሆኑ የሚያከራክረን ጉዳይ አይሆንም።

የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የአገር ደህንነት ኃይል የቆመው አገርን ከጥቃት ለመከላከል ነው። አገር በጠላት እጅ ወድቃ በወገን ላይ ስቃይ እንዳይደርስ፤ ህዝቡም አገር አልባ እንዳይሆን መጠበቅ የአገሪቷ የሠራዊትና የደህንነት ኃይል ዋና ተግባር ነበር። ህወሃት መራሹ መንግስት አገሪቷን ከተቆጣጠረ ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥም የቆመው ሠራዊት እና የደህንነት ኃይል ተግባሩ ሌላ ሁኗል።

በዚህ ዘመን ሠራዊቱና የደህንነት ኃይሉ የአገርን ብሄራዊ ደህንነት የሚጠብቅ ሳይሆን ህወሃት የተባለውን ዘረኛና ዘራፊውን ቡድን የሚጠብቅ ኃይል መሆንን እንዲመርጥ ሁኖ አገርን ከጠላት የመከላከል ተግባሩን ረስቷል። ይህን ኃይል የሚመሩትም ደማቸውንና አጥንታቸውን ቆጥረው ከአንድ መንደር/ጎሣ የተሰባሰቡ እና ካርታ ይዘው የቆሙበትን ሥፍራ እንኳን ለመለየት የማይችሉ መሃይማን መሆናቸው አገሪቷ ያለችበትን አደጋ ከሚያመላክቱ ምልክቶች መካከል አንዱ ነው። ህወሃቶች የደርግ ሠራዊት እያሉ ሊሳለቁበት የሚሞክሩት የቀድሞው የአገሪቷ መከላከያ ኃይል ሲመራ የነበረው አውሮፓና አሜሪካን ድረስ ተጉዘው በተማሩ፤ ማዕረጋቸውም የዓለም ዓቀፉን ደረጃ የጠበቀ፤ አገሪቷን ወክለው አደባባይ ቢወጡ የሚያኮሩ እንደነበረ የታወቀ ነው። የሹመታቸው መሠረትም ደምና አጥንት ሳይሆን እውቀታቸው፤ ችሎታቸውና ወታዳራዊ ብቃታቸው ነበረ።በህወሃት የሚመራውን ሠራዊትና የደህንነት ኃይል የሚመሩት ቡድኖች ከቀድሞዎቹ ሥርዓት የጦር መሪዎች ጋር ሲወዳደሩ የጫማቸውን ጠፍር እንኳ ለመፍታት የሚታጩ አይሆኑም።ግዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል እንደሚባለው ሆነና ጨካኞችና ነፍሰ ገዳዮች በወንበሩ ቁጭ ብለው የአገሪቷን ውድቀት እያፋጠኑት ይገኛሉ።

ዛሬ ህወሃቶች በወንበሩ ቁጭ ብለዋል። እነዚህ ከጭካኔ በቀር እንጥፍጣፊ የአገር ፍቅር የሌላቸው ቡድኖች አቋቋምን ያሉት ሠራዊትና የደህንነት ኃይልም አገሩንና ወገኑን ከመጠበቅ ይልቅ የገዛ ወገኑን የሚያሸበር ቡድን እንዲሆን ተደርጓል። ሠራዊቱ እና የደህንነት ኃይሉ ለአገርና ለትውልድ እንዲያስብ ሳይሆን የጥቂት ዘረኞችን ዕድሜ ለማራዘም ዘብ የቆመ ኃይል እንዲሆንም ሁኗል። ህወሃት እየፈጠረ ያለው ሠራዊትና የደህንነት ኃይል በጀግና ማዕረግ አገሩንና ህዝቡን ከጥቃት ተከላክሎ በህዝቡ ተከብሮና ተወዶ እንዲኖር ሳይሆን በጭካኔው ታውቆ እና የወገኑን ፍቅር አጥቶ በስነ ልቦና ቀውስ ውስጥ የሚኖርን ኃይል ነው። እንዲህም ሁኖ በመቀረፁ ግደል ሲባል ገስግሶ ሂዶ የገዛ ወገኑን ይገድላል። አፍርስ ሲባል ፈጥኖ በብዙ ድካምና ወጪ የተገነባውን የወገኑን መኖሪያ ቤት ያፈርሳል። እሠር ሲባል ህፃን ከአዛውንት ሳይለይ ያገኘውን ሁሉ ወደ ወይኒ ቤት ያግዛል። በእንዲህ ሁኔታ ከወገኑ ተለይቶ፤ በወገኑ ላይ ዘምቶ፤ ወገኑን ወግቶ፤ ወገኑን አሥሮና አሰቃይቶ ራሡም እንደገና በክፉ ድርጊቱ ታሥሮ እንዲኖር ሁኗል።

Friday, August 1, 2014

የህወሃት ሽብር መቆም አለበት!

ዛሬ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለ አሸባሪ ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው፣ መንግስት በመተቸታቸው በግልጽ በመጻፋቸውና በአደባባይ በመናገራቸው ከዚህም አልፎ በጥርጣሬ በተለይም በብሄረሰብ ማንነታቸው እያሳደደ የሚያፍን የሚያሰቃይና የሚገል የሽብር ተቋም ካለ ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ መሬት ላይ ሰላማዊ ዜጎችን ኢላማ ያደረገ የተቃውሞ ሃይል በተግባርም ሆነ በአስተሳሰብ ከወያኔ ውጪ አንዳች ሃይል የለም።

አፋኙ የወያኔ ስርአት በተለየም የህዝቡን ሀብትና ንብረት እየዘረፉ የሚቀማጠሉት የህወሃት መሪዎችና ሎሌዎቻቸው የተቃውሞ ድምጽ በሰሙ ቁጥር እንደሚሸበሩና እንቅልፍ አጥተው እንደሚያድሩ ይታወቃል። አፍነውና ዘርፈው ገለው የሚገዙት ህዝብ ግፍ በዛብኝ ብሎ በተናገረ ቁጥር የሚሸበሩት እነሱ ብቻ እንጂ ህዝቡ አይደለም።

በኢትዮጵያ ምድር ያለው አሸባሪ ወያኔ ብቻ መሆኑን ሺ ምሳሌዎችን ጠቅሶ ማስረዳት ይቻላል። ሶስት አመት ሙሉ የሰላም እጃቸውን እየዘረጉ ከልመና ባልተለየ ሁኔታ መብታቸውን የጠየቁና ድምጻችን ይሰማ ያሉት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማንንም ዜጋ አላሸበሩም። የተገላቢጦሽ እነሱ አሸባሪ ተብለው የግፍ ሰቆቃ ይፈጸምባቸዋል። ጋዜጠኞችና ጦማሪዎቹ መንግስት ያወጣውን ህግ እንዲያከብር ስለጠየቁ በአደባባይ ስለጻፉ ግፍ ይፈጸምባቸዋል። እነሱ ያሸበሩት ሀገርና ህዝብ የለም። ከመንገድ ላይ ጎትተው እንደ እባብ ቀጥቅጠውና ፈነካክተው በማግስቱ ፍርድ ቤት ያቀረቧት ወየንሸት ሞላ የተባለች ባለ ተስፋ ወጣት የወያኔ አረመኔዎች በሙስሊሙ ህዝብ ላይ የሚሰሩትን ጭፍጨፋ እግር ጥሏት ከማየትና ከመታዘብ ውጪ ያሸበረችው ሰው፣ ሀገር የለም። በየወህኒ ቤቱ እና አፈና ጣቢያው ታስረው የሚቀጠቀጡት የኦሮሞ ልጆች ለጥያቄያቸው መልስ ሲጠብቁ ከመጨፍጨፍ ያለፈ የፈጸሙት እብሪት የለም። በየክልሉ ቀና ብለህ ባለስልጣን ተናገርክ፣ ጥያቄ ጠየቅክ፣ ባለስልጣን ደፈርክ፣ ተሰብስበህ አየንህ ወዘተ እየተባለ የሚገረፈው እንደ እንስሳ እየተገደለ የሚጣለው ገበሬ የሰራው ወንጀል የለም። አሸባሪም አይደለም! በየቦታው ቦንብ እየቀበረ አፈንድቶ ንጹሃንን ገድሎ ሊያፈነዱ ሲሉ ፈንድቶባቸው ራሳቸውን ገደሉ ብሎ በአደባባይ የሚሳለቀው አሸባሪው ህወሃት እንጂ ንጹሃኑ አይደለም።