Thursday, May 15, 2014

የሞት ጣር ድምፅ በግምቢ ወለጋ ተሰማ!

በቅዱስ ዮሃንስ

ወያኔ የቀበረው የዘር መርዝ በቅሎና አድጎ አፈራለት ማለት ነው? እኛም እንደ ሩዋንዳ ልንሆን ነው? አረ እግዚኦ በል ወገን፣ እኔ የምሰማውን ላምን አልቻልኩም፥ እንባየንም ማስቆም ቸገረኝ ፤ ከመቼውም በላይ ልቤ አዘነ፣ ቅስሜ ተሰበረ ፣ ወገኖች በሳኡዲ ሲታረዱ አለቀስኩ ፣ ተሰለፍኩ ፣ ድምጼን ከፍ አድርጌ ከወገኔ ጋር በእልህ ጮህኩ፦ አሁንስ ለማን እንጩህ ፣ ዕባካችሁ ምከሩ ጎበዝ፦ በአገራችን ኢትዮጵያ ክፉ ቀን እያንዣበበ ነው፦ ወንድሙ ወንድሙን እንደ ኣውሬ አሳዶ ሊበላው ነው፤ የጨለማ ሰዓት መጣ በአገራችን ፤ በወገን ላይ ስጋትና ሺብር እጅግ ነገሡ ፦ ኢትዮጵያዊው አባት ድረሱልኝ ይላል ፥ እናት ነብሴ ተጨነቀች ሞትና እኛ ፊት ለፊት ተፋጠናል ፥ ማድረግ የሚቻል ነገር ካለ በፍጥነት ድረሱልን ይላሉ።

ሰላም ወዳድ የኦሮሞ እና የአማራ ሕዝብ ሆይ አድምጠኝ ፣ አንድነታችን በእሳት እየተፈተነ ነው፤ የስንት ታላላቅ አገር ኢትዮጵያ በእኛ ዘመን እንደዚህ አትሆንም እምቢ ለዘረኝነት እንበል ። የጎጠኝነት በሽታ ሕዝባችንን ሲያሸብር እያየን በምንም መልኩ አንታገሰው ፣ እነማን እንደሚያቀነባብሩት እናውቃለን ፣ የጋራ ጠላታችን ወያኔ ነው።


ይህ የሚሰማው ክፉ ነገር ማስተዋል በጎደላቸው ጥቂት ደካማ የኦሮሞ ተወላጆች መሣሪያነት የሚፈፀም ይሁን እንጂ በወያኔ እኩይ አመራር ተከክቶ የተቦካ የጠላት አጀንዳ ነው ፤ በብዙ ፈተናዎች ያለፈ ዘማናትን የተሸጋገረው ጨዋ ኢትዮጵያዊ ማንነታችን በእነዚህ የተልካሻዎች ተንኮል እንዳይበላሽ ጥንቃቄ ይደረግ ፣ ከቁጥጥር ውጭ ሳይሆን በሰከነ መንፈስ ተው የሚል የጋራ ኮሚቴም ቢሆን ይቁዋቁዋም ፣ ቀሳውስት ፣ ሙሁራን ፣ የአገር ሺማግሌዎች ይጠሩ፥ እየሆነ ያለን ነገር በመካድና በመሸፋፈን ፈውስ አይገኝም፥ ይህ የአሕዝብ ዓድን ጥሪ የመጨረሻው ደወል ነው፥ ለአገርና ለሕዝብ አስባለሁ በሚሉ ወገኖች ዘንድ በፍፁም ቸል ሊባል የማይገባው አንገብጋቢ ጉዳይ መሆን አለበት፥ እስላም ክርስቲያን ወገኔ አምልኮና የፅድቅ መንገድም በአገር ነውና አምላክን ለምን ወገንህን ምከር፥ የወያኔን የጥፋት መመሪያ ተቀብለው ተግባራዊ የሚያደርጉና በዚህ ዓሳዛኝ ወንጀል ተባባሪ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆችም ሆኑ ነገሩን ከሚገባ በላይ በማራገብ የማፋጀቱ ሚና ተዋናዮች ሁሉ ፍርድን ሳይዘገይ እንደሚያገኙ ማወቅ ይኖርባቸዋል፥ ንቃ ወገኔ የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ እንዳትሳሳት ጠላትህ ወያኔ ነው እንጂ ድሃው የአማራ ወገንህ ዓይደለም፥ ጠላትህ ወያኔና ጎሳን መሰረት ያደረገው የፌደራሊዝም ስርዓቱ ናቸው፥ ከዓማራውና ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተባብረህ ታገል ሥርዓቱን ዓሽቀንጥረህ ጣለው፥  ዓማራ ሆይ ታገስ ዓስተውል ይህ ግርግር የወያኔ ደባ ነው፥ ሚስጥሩ ይግባህ ሰሞኑን በጎንደር የጀመሩትን ዓሁን በወለጋ እየቀጠሉ ነው፥ በማንነት እና በጎሰኝነት ጥያቄ ሰበብ እርስ በዕርስ ያጋጩና ጋላጋይ መስለው ወደ ሕብረተሰቡ መግባት፣ መሳሪያዎችን መፈተሽና መውረስ ጉልበታሙን ማሰር በዓካባቢው ያለውን የትጥቅ ትግል ስጋት ለመቀነስ የያዙት ዓዲሱ ስልት ነውና ዓትደናገሩ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

No comments:

Post a Comment