Saturday, May 3, 2014

የትግራይ ህዝብ ጠላትች የህወሓት-ኢህኣደግ መሪዎች ናቸው!!!!


ምክንያቱም:

የህወሓት-ኢህኣደግ መሪዎች እጃቸው በንጹሐን ደም የጨቀየ፣ አንደበታቸው በውሸት የረከሰ፣ ኪሳቸው በሙስና ገንዘብ የተሞላ፣ ጭንቅላታቸው ከሥልጣቸው ውጪ አርቆ ማሰብ የማይችል የደርግ ፎቶ ኮፒዎች።
እንዴት???

መጀመርያ "የህወሓት-ኢህአዴግ መሪዎች እጃቸው በንጹሐን ደም የጨቀየ" የሚለው በተለያየ መንገድ እስኪ እንየው። ኣንደኛው እነኚ መሪዎች በሽዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ገበሬዎች በነ ግርማይ መጎስና ብስራት ኣማረ ኣስፈፃሚነት ሂወታቸው እንዲጠፋ ያደረጉ ናቸውና እጃቸው በንጹሐን ደም የጨቀየ ቢባሉ ኣይበዛባቸውም። በሌላ እይታ ስንመጣ ደግሞ እላይ የተጠቀሱት ገበሬዎችም ሆኑ ከስልሳ ሽ በላይ ታጋዮች በመራራው ትግል ሂወታቸው የተከፈለው ጨቋኝ ስርኣት ተወግዶ ህዝቦች በእኩልነት ፍትህ፤ እድገትና ሰላም የሚያገኙበት ስርኣት ለመፍጠር ነበር። ይሁንን ያንን ኣላማ ረስቶ የህወሓት-ኢህአዴግ መሪዎች የድሆችን ቤት ህጋዊ ኣይደለም እያሉ እያፈረሱ ለራሳቸው ግን ህጋዊ ባልሆነ የተከለለ ደን ውስጥ ገብቶ ፎቆች ሲሰሩ፤ ህዝቡን በስራ እጦና የሚታረስ መሬት በማነሱ ኣገር ትቶ በሚሰደድበት ትራክተር ገዝቶ ኣደራጅቶ ከመስጠት ይልቅ ራሳቸው ከውጭ ኩባንያዎች ተደራጅቶ መዝረፋቸው፤ ብትግራይ ህዝብ ስም እየነገዱ የትእምት ሃብት ለራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው መጠቀምያ ማድረጋቸው ሁሉ የንፁሃኑ የተሰውት ደም ከንቱ የሚያስቀር በመሆኑ የህወሓት፡ኢህአዴግ መሪዎች በደም የጨቀዩ መባላቸው ኣያንስባቸውም ባይ ነኝ።

"አንደበታቸው በውሸት የረከሰ፣ ኪሳቸው በሙስና ገንዘብ የተሞላ" የሚሉት ኣጠቃልለን ስናያቸው ደግሞ ህዝቡ በሳምንት ኣንድ ግዜ ውሃ በሚያገኝበት ግዜ የውሃ ሽፋን 80%- 90% ደረሰ እያሉ የሚዎርጩ የውሸት ዶክትሬት ያላቸው እንደሆኑ ላንተም መገመት ኣያቅትህም። ኪሳቸው በሙስና የተሞላ የሚለው እንኳን መንግስት ራሱም የሚያውቀው ስለሆነ ኣያከራክረንም። ነገር ግን በጣም የሚያሳዝነኝ የቅዱሳን ነጋና ባለቤትዋ በተሰብ የሆኑት ዶክተር ጌታቸውና ኣቶ ኣማኑኤል የመቐሌ ከተማ የውሃ ሽግር ለመፍታት የተመደበ 100 ሚልዮን ብር በልቶ ቻይናና ጃፓን ተደብቆ እየኖሩ ነው። የመቐሌ ህዝብም የውሃ ችግሩ ሚፈታለት ኣጥቶ እየተሰቃየ ነው። እነዛ በሙስና የጨቀዩ ባለስልጣናትም በኢንተርፖል ኣድርጎ ሰዎቹ ባያስሩዋቸውም ብሩን እንዲመለስ ኣድርጎ የህዝቡን ችግር መፍታት እየቻሉ ቤተሰቦቻቻው ለለመጉዳት ዝምታን መረጡ። ታድያ የህወሓት፡ኢህአዴግ መሪዎች ኪሳቸው በሙስና ገንዘብ የተሞላ መባላቸው የቱ ላይ ነው ጥፋቱ?


በመጨረሻ የቀረበው "ጭንቅላታቸው ከሥልጣቸው ውጪ አርቆ ማሰብ የማይችል የደርግ ፎቶ ኮፒዎች" የሚለው ለማየት መጀመርያ የደርግ ስራዎች እናስታውስ። ደርግ ለተቃወመው ሁሉ ኣገር ለማፍረስ፤ መንግስት ለመገልበጥ ከሚንቀሳቀሱ ወንበዴዎች ግንኑኘት ኣላቸው እያለ ንፁሃን ያስር፤ ያሰቃይና ይገድል ነበር። ኣሁን ደግሞ ሁሉም የተቃወመ የተለያየ ስም እየሰጡ ሰዎችን እያሰሩ፤ እያሰቃዩ እየገደሉ ይገኛሉ። እንደውም ወደ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ስትመጣ በደርግ ግዜ ይሻል ነበር። በደርግም በሃይለስላሴ ግዜም ማንም ወታደር ይሁን ፖሊስ ወደ ዩኒቨርስቲ ግቢ ኣይገባም ነበር። የኣሁኑ የህወሓት-ኢህአዴግ መሪዎች ግን ወታደሮቹ በየዶርሙ እየገቡ ንፁሃን ተማሪዎች እንዲገድሉ ያዝዛሉ።

ስለዚህ ኣጠቃልለን ስናይ የሰፊህ ህዝብ ትግል ውጤት ወደ ጥቂት በቤተሰብነትና ኣሽከርነት የተሳሰሩ ስዎች ተጠቃሚነት የቀየረ ወሮ በላ የትግራይ ህዝብ ጠላት የህወሓት-ኢህአዴግ መሪዎች ናቸው። ውሃ ሳንጠጣ የተለየ ውሃ እንዳገኘን፤ ሳንበለ የተለየ እንደበላን፤ ከሰፍትኔት በወር 45 ኪሎ ግራም በምት ሰጥ ስንዴ እዮነርን ከሌሎች በተለየ ጤፍ ኣፍሰን እንደምንበላ፤ የራሳቸው ከትእምት ሰርቆና ከኣንዳንድ ኣጭበርባሪዎች ዘርፎ የሰሩትን ፎቆች የትግራይ ህዝብ በመቐለ የተሰሩ ህንፃዎች እያሉ ልክ እኛን በሌላው ቢሄረሰብ ትከሻ እየተራመድን እንደምንኖር ኣድርጎ በማቀረብ እንድንጥላና ስማች በመጥፎ እንዲነሳ ያደረጉና እያደረጉ ያሉ የትግራይ ህዝብ ጠላት ኣሁንም የህወሓት-ኢህአዴግ መሪዎች ናቸው።

No comments:

Post a Comment