Thursday, May 22, 2014

ፍትህ! ፍትህ! ፍትህ!

ሰዓቱ 10ጉዳይ … ለአስር ነው፡- ህብረት ግዜዋ ነች!!!

የኢትዮጵያ ህዝብ በፋሽስቱ የወያኔ አገዛዝ በጦር መሳሪያ ተረግጦ በድህነት አዘቅት መኖሩ እሙን ነው፡፡ የመሳሪያን ጉልበት ያላንበረከከ ህዝብ መቼም ቢሆን ኑሮው ለቅሶ ነው፡፡ የእኛ ህዝብም ኑሮ አረረ መረረ ከማለት ያለፈ ሆኖ የማያውቀው የዚህ የጦር መሳሪያ ተሸካሚዎች ቀንብር ውጤት ነው፡፡ ፋሽስቱ ወያኔ 23 ዓመት የመረጠው መንገድ ቢኖር ወጣቶቻችንን ማሰር፤ መንገደል፤ ማሰቃየትን ነው፡፡በዚህ አይነት ሁኔታ የሚቀጥልበት መንገድ ግን ፈጽሞ መኖር የለበትም፡፡ ፍርሀት በውስጡ ተስፋ ላለው ነገር እንጂ ነገ ደረሶ ያጠፋኛል እያሉ ሊሆን ፈጽሞ አይገባም፡፡

ወያኔ በደህንነት እና በወታደር ጉልበት ሲያስለቅሰን ሊኖር አይችልም፡፡ ከሰሞኑ የኦሮሞ ህዝብ ሁሉ አቀፍ ትግል፤ የነጻነት ትግሉ መሀል እንደተሻገረ የሚያሳይ ነው፡፡ ሁሉም በየፊናው የሚያደርገው ትግል ደግሞ ከዚህ ጋር ሲዳመር፤ ሰዓቱ አስር ጉዳይ ለአስር መሆኑ የሚያሳይ ነው፡፡የትግራይ የወጣቶቹ እና የዓረና ፓረቲ ትግል፤ በአዲስ አበባ የአንድነት እና የሰማያዊ ፓሪቲ ህዝባዊ ተቃውሞዎች፤ አሁን የኦሮሞ ህዝብ ትግል መጥቀስ ያለውን ሁኔታ ያስረዳናል፡፡ ከመቼው ግዜ በላይ የዲሞክራሲ ጥያቄ በትውልድ አዲስ ራእይ ላይ ተከንካበሎ የጋራ ትብብር እና ህብረት የሚፈልግበት ደረጃ መድረሱን የሚያለክት ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ በወያኔ ላለፉት ለ23 የመከራ ዓመታት ሲነሰነስ የኖረውን ያለመተማመን ደባን ገሸሽ አድርጎ የመተባበሪያ መንገዶችን መፈለግ ወሳኝ ያደርገዋል፡፡ የሰው ልጅ ሁላ በየትኛውም ግዜ፤ እና ቦታ ፍትህን ይፈልጋል፡፡ ፍትህ ማለት ደግሞ ከኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እስከ አካለዊ ህልውና ማለት ነው፡፡ ሀገራችን በዚህ ረገድ የታደለች አይደለችም፡፡ ስለዚህም የትኛውንም ብሄር የምትወክል ብትሆን ከዚህ የፍትህ ጥያቄ ውጪ ልትሆን አትችልም፡፡ በነገህ እጣ ላይ መሳሪያ የያዘ ተቀምጦ፤ አጠገብህ ያለው መሳሪያ ያልያዘው ጠላትህ ሊሆን አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃይሎች ሁላ ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር ህዝቡ የሚፈልገውን መወሰን የማችልበት ሁኔታ ላይ ተቀምጦ፤ ጎን ለጎን እርስ በእርስ ቢፋጩ ህዝቡን እየጎዱ እንደሆነ ነው፡፡ስለዚህ መሳሪያ ለያዘው ኃይል (ወያኔ) የማይመች የትግል ስልት መከተል የግድ ይላል፡፡ ለዚህ ደግሞ ራሱን ፍትህን የመታገያ መንገድ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡


የኦሮሞ ህዝብ መሬት መነጠቅ ስህተት የሆነው ኢ-ፍትሀዊ ስለሆነ ነው፤ ይህ ነገር ለአማራም ቢሆን ይሰራል፤ ለተጋሩም ይሰራል፡፡የአማራ ህዝብ በመኖሪያ ቀየው ት/ቤት፤ ጤና ጣቢያ፤ …መንገድ አጥቶ የሚማቅቀው፤ ፍትህ ስላጣ ነው፡፡ የትግራይ ልጅ በዳስ ትምህርት ቤት የሚኖረው፤ ዘልአለም በደህነት እዲዳክር የሚደረገው ፍትህ ስላጣ ነው፡፡የተለያዩ ጉዳዮችን ብናይ ከፍትህ ውጪ የሚወጣ የኢትዮጵያ ምድር ጥያቄ የለም፡፡ወደፊትም በሰላማዊ መንገድ እስከመጣ ድረስ መልሱ የፍትህ ነው፡፡ፍትህን ጨፍለቆ የቆመውን ፋሽስቱ ወያኔን ዞር ሳያደርጉ ምንም አይነት መልስ ማግኘት የዋህነት ነው፡፡ ስለዚህ ለሁሉም የፍትህ ጥያቄዎች መልስ መጀመሪያ የሚሆነውን የጦር መሳሪያን ማንበርከክ ከሁሉ የሚቀድም አጀንዳ ማድረግ የግድ ይላል፡፡ አለዚያ የህጻነት ጨዋታ መመላለስ ከመሆን አያልፍም፡፡

ኢህአዴግ አኖሌ ላይ ሓውልት ባቆመ ማግስት የኦሮሞ ህዝብን ሲፈጅ ማየት ይህ አጥፊ ዓላማው ምን እንደሆነ ይናገራል፤ የአማራ ህዝብን አንድም ቀን መሰረታዊ ጥያቄ ሳይመልስ ስታዲዮም እንደክራበት ሰራሁ ሲል፤ …ህዝቡን ምንያህል እንደናቀው ያሳያል፤ ጭንቅ ውስጥ ሲገባ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች እያለ የትግራይን ህዝብ ከወንደሙ ለማቃቀር የሚነሳ ድርጀት ምን ያህል ነውረኛ፤ ዘላቂ የትግራይን ህዝብ ጥቅም ለማጥፋት ተነሳ መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡

ስለዚህ በታሪክ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ መነታረኩ፤ ፋሽስቱ ወያኔን ከመጥቀም እና ህዝባችን ከማስጨረስ ያለፈ ጥቅም የለውም፡፡ እነዚህን ነገሮች አስተውሎ ፤ ትግሉን አንድ ምእራፍ ለመግፋት እንዲያስችል፤…አንድ ላይ የሚቆሙንን አጀንዳዎች እየመረጡ፤ የነጻነት ትግሉን አንድ እርምጃ ወደፊት ለማስኬደ መጣር ያስፈልጋል። ይህን ሁላችንም ፋሽስቱ ወያኔን ለመታገል በሚሆን መንገድ ብቻ በማወቅና በማስተዋል ልናስኬደው ይገባል፡፡

ፍትህ ለጭቁኑ ህዝብ!

No comments:

Post a Comment