ከባለራዕይ ወጣቶች ማህበር የተሰጠ መግለጫ
ስፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገራቸው ሉአላዊነት እና በህዝቦች መፈቃቀድ መፈቃቀርና መኖር ዙሪያ ማንም ሰንካላ ምክንያት በማቅረብ እንዲበታትነው መፍቀድ የለበትም በተለይ ይመራናል ያስተዳድረናል በምንለው መንግስት ከህዝቦች ፍቃድና እውቅና ውጪ በማስተዳደርና በመግዛት ዙሪያ ያለው የተራራቀ ልዩነትና የመንግስታችን አተያየም የመግዛት በመሆኑ የግዛት ጊዜውን በማራዘም የጭቆና ቀንበሩን ለማፅናት ሲል ለ3 ሺ ዘመናት የነበራትን ታሪክ በማበላሸትና በዚያ አኩሪ ታሪኳም ለዜጎች ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌትና ኩራት የሆነች ባላት ታሪክና ትሩፋት በተለይ በህዝቧ ያኗኗር ዘይቤ በኢትዮጵያ እድገት ውስጥ ያበበና ጎልቶ የወጣ ልዕልናዋም ከአጉረ አፍሪካ ተሻግሮ ለአለም መደነቂያ የሆነች ሀገራችን ላይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አጥልቶ ያለው የተቃርኖ እዳ የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር እየተጠነሰሰ ያለና በተግባራዊነቱም ጎልቶ የታየበት ጊዜ አይታወስንም በመሆኑም ዜጎች በመንግስት ትንኮሳና ሸር እየተፈፀሙ ያሉት ዜጎችን ከቦታቸው የማፈናቀል ለጠየቁት ጥያቄ አወንታዊ እርምጃ መውሰድ በጋዜጠኞችና በጦማሪያን ላይ የእስር እንዲሁም በቶፎካካሪ ፓርቲ አባላትና መሪዎች ላይ የሚደርሰው እንግልትና ወከባ የዚህች ሀገር ጎዞ ወዴት እያመራ ነው የሚለው እጅግ አሳሳቢ ነው ከዚህም በተረፈ በሚፈጠረው ግርግር ሰፊው የሀገራችን ህዝብ ተጎጂ የሚሆን በመሆኑና በተለይም በግንባር ቀደምነት የሀገራችን አምራችና አንቀሳቃሽ ብሎም ሀገር ተረካቢና አንቀሳቃሽ በምንለው ወጣት እጅጉን እየከፋ በመሄዱና ለጥቃትም ተጋላጭ በመሆኑ ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገደናል፡፡
1. የሀገራችንን ህዝቦች ለመከፋፈልና ወደ ማያቋርጥ እልቂት ለመምራት በፈጠራ ታሪክ ላይ ተመስርቶ እየተሰራበት ያለው ሴራ ባስቸኳይ እንዲቆም እና የእልቂት መነሻ የሚሆን በተለይም አኖሌ የተገነባው ሀውልት ባስቸኳይ እንዲፈርስ በምትኩም ህዝቦች በጋራ ተቻችለው የሚኖሩበትና የጋራ አሴት ሊፈጥር የሚችል የመደጋገፍና የመረዳዳት ህልውናውን የሚያጠናክር መዘከር እንዲሰራ እንጠይቃለን፡፡
2. መንግስት በህዝቡ ዘንድ መግባባትና መፋቀር እንዲሰራና ሀገራችን ለዜጎችም ብሎም ለወጣቶች ምቹ ማድረግ ሲጠበቅበት ዜጎችን ኢ.ህገ መንግስታዊ እና ኢ-ፍታዊ በሆነ መልኩ በሀገራቸው በየትኛውም ክፍለ ሀገር የመኖርና ሀብት የማፍራት መብታቸውን በመጣል ከቄያቸው እና ተከባብረው እና ተፋቅረው ከኖሩት ህዝብ በሀይል የማፈናቀል እርምጃ ባስቸኳይ እንዲቆም ይህን ያደረጉም የመንግስት ባለስልጣናት ለህግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
3. መንግስት በሀገሪቱ ህገ-መንግስት አንቀጽ 29 ላይ የአመለካከትና ሐሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብትን በመጣስ በጋዜጠኞች በጦማሪያንና በፅሑፎች ላይ በቅርቡ የጅምላ እስር አከናውኗል በመሆኑም በሀገሪቱ የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ህገ-መንግስት ለዜጎች ህልውና በሚል ያዘጋጀው መንግስት እራሱ ጥሰት በመፈፀም የወሰደው ኢ-ፍታዊ እርምጃ ዜጎች የመናገር ሀሳባቸውን በነፃነት በመግለፅና የመፃፍ መብትን በመተላለፍ የተወሰደ እርምጃ በመሆኑ ባስቸኳይ እንዲፈቱ እየጠየቅን ዜጎች የሚያከብሩትን ህገ-መንግስት ያዘጋጀው አካል መንግስትም ህገ-መንግስቱን እንዲያብብ አለበለዚያ ግን ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ መብቶችን ለማስከበር በሚያደርገው ትግል ከሚከተለው አላስፈላጊ እልቂትና ጉዳት በፊት ከወዲሁ እልባት እዲበጅለት እናሳስባለን፡፡
4. መንግስት የአዲስ አበባን ከተማ ማስተር ኘላን ተከትሎ ቤተሰቦቻችን ያፈና ቀላል እርስት አልባ እና ቀጣሪ እንዲሁም ስራ ፈት በማድረግ ለድህነት ይዳርጋል በሚል ዩንቨርስሪቲዎች ለተጠየቀው ስላማዊ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት ሲቻል ዜጎች ላይ ሊያውም የሀገሪቱ ኢፍታዊ እርምጃ አግባብነት የሌለውና ይህን ያደረጉ አካላትም ሆነ ትዛዝ ያስተላለፈ አካል፡፡
የተማረ ብሎም ወጣትና ትኩስ እንዲሁም ሀገር ተረካቢ በሆነው ትውልድ ላይ የተወሰደው ኢፍታዊ እርምጃ አግባብ አይደለም ስንል እያወገዝን ይህ ድርጊት በንፁዋን ዜጎች ላይ እርምጃው እንዲወሰድ ያዘዙና እርምጃውን የወሰደ ባለስልጣናትም ሆነ ፌደራል ፓሊስ አባላት ለህግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
5. በተለይ ከዚህ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ችግሩን የብሔር ችግር ለማስመሰልና ወደ አላስፈላጊ ቀውስ ለመምራትና የእርስ በርስ ግጭት እንዲሆን ለማድረግና የመብትና የህይወት ጥያቄን በሌላ መልኩ ጥላሸት በመቀባት ለማጥቆር መምከር እጅግ አሳስቦናል በአሰቃቂ ጭፍጨፋ በአለም ሆነ በውጭ የሚገኘው አንዳንድ ፅንፈኛና ጎጠኛ ሰዎች እየተካሄደ ያለው ደባ ባስቸኳይ እንዲቆም እየጠየቅን ለሀገራችን እድገትና ብልፅግና ከጥላቻ ፓለቲካ እና ዘር መሠረት ካደረገ አድሎ በመቆጠብ ፍታዊ አሰራር እንዲሰፍን ዜጎችም ለ3ሺ ዘመን ተፋቃቅረውና ተቻችለው በመኖር ለተቀረው አለም ምሳሌ መሆን እንደተጠበቀ ሆና ቢስራ የተሻለ ነው እንላለን፡፡
6. የዜጎች ሰብአዊና ህገ-መንግስታዊ መብታቸው ተጠብቆ በመፈቃቀደና በመፈቃቀር ላይ የተመሠረተችዋን ኢትዮጵያችንን ደግሞ ለማየት የተፍካከረ ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ የሚያደርጉት ትግል ክልከላና እንቅፋት መደርደር ኋላ ለሚመጣው ችግር ተጠያቂ የሚሆን መንግስት በመሆን በዋነኝነትም ተጎጂው እና የችግሩ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ ወጣቱ ትውልድ ነውና ይህ ችግር ከመከሰቱ በፊት የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፈር ክፍት እንዲያደርግ መንግስትን እየጠየቅን አማራጭ ያለውና እኔ እበልጥ እኔ ብሎ በሚፎካከሩ የፓለቲካ ፓርቲ መካከል ምርጫው ለህዝብ ትቶ በጠላትነት መታየትና መወነጃጀል ለሀገራችንም ሆነ ለህዝባችን ስለማይበጅ ከወዲሁ የመግባባት መድረክ እንዲኖር እንጠይቃለን፡፡
ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!! ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር፡፡
ግንቦት 02/08/2006 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment