ኢትዮጵያ ከአንድ ሺህ አራት መቶ አመታት በፊት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ማህበረሰብ ካሰፈነው ፍትህ የላቀ ፍትህ ማስፈን ችላ ነበር። የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉስ በነቢዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) አንደበት ‹‹በሐበሻ አንድም ሰው የማይበደልበት ንጉስ አለ›› ተብሎለታል። እንዲህ አይነት ፍትህ በዚህ መልኩ ለማስፈን ምን ያህል ፍትሀዊ፣ እውነተኛ እና የሰለጠነ ማህበረሰብ መገንባት እንደሚጠይቅ ግልፅ ነው። በሀገራችን የነበረው ፍትህ በጊዜው ነፃነት እና ፍትህ ፍለጋ ይዋትቱ የነበሩትን ማስጠለል የቻለ እና ዘመናትን ተሻጋሪ ነበር። ግና የዛሬው አሳዛኝ እውነታ ‹‹ሰዎች ስለ ፍትህ ግንዛቤ ባልነበራቸው በዚያ ዘመን የፍትህ ጥግ የደረሰችው አገራችን ሰዎች ሁሉ ወደ ዲሞክራሲ እና ፍትህ ፊታቸውን ሲያዞሩ ለምን ጀርባዋን ሰጠች?›› ብለን እንድንጠይቅ አስገዳጅ ሆኗል።
Read full story in PDF: …የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የተሰጠ መግለጫ..
No comments:
Post a Comment