Monday, December 16, 2013

የወያኔዉ ጋጠወጥ ፍርድ ቤት የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን ባልፈጸሙት ወንጀል ተከላከሉ ብሎ በየነ

የሰብዓዊ መብታቸዉ አንዱ አካል የሆነዉ የማምለክ መብታቸዉ እንዲከበር በመጠየቃቸዉ ብቻ በወያኔ የጸጥታ ኃይሎች ታድነዉ ከአንድ አመት በላይ በግፍ ታስረዉ የቆዩት የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ዜጎችን ለማጥቃት ሆን ተብሎ የተፈጠረዉ የወያኔ ፍርድ ቤት ተከላከሉ ብሎ እንደበየነባቸዉ ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ተናገሩ። የየስሙላ ፍርድ ቤቱ አስር ሁለት እስረኞችን በነጻ የለቀቀ ሲሆን እነ አቶ አቡበከር አህመድና ሌሎች ደግሞ የተመሰረተባቸዉን ሽብር አነሳስታችኋል የሚል ክስ እንዲካለከሉ ብይን ሰጥቷል። አንደ ተከሳሾቹ ጠበቃ እንደ አቶ ተማም አባ ቡልጎ አባባል ሙራድ ሹኩር ጀማል፣ ኑሩ ቱርኪ ኑሩ፣ ሼህ ባህሩ ኡመር ሸኩር እና ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ሽብርን በመርዳት በሚለው ሀግ አንቀጽ ሰባት ተጠቅሶባቸዉ ክሱን ተከላከሉ የተባሉ ሲሆን ተከሳሾች መከላከያቸውን ከጥር 22 እስከ 27 እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ አዟል።

ውሳኔውን በተመለከተ አስተያየታቸውን ለኢሳት ቴሌቪዥንና ሬድዮ ቃለ መጠይቅ የሰጡት የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ተማም አባ ቡሉጎ፣ ምንም እንኳ ተከላከሉ የተባሉት አንቀጽ የቅጣት መጠኑን ቢቀንሰውም፣ የእሳቸዉ አላማና ፍላጎት ግለሰቦቹ በነጻ ተለቅቀዉ ወደ ቤተሰቦቻቸዉ እንዲመለሱ ማድረግ ነዉ ብለዋል። የወያኔ አገዛዝ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን መጀመሪያ ላይ የከሰሳቸዉ የሽብር ጥቃት ፈጽማችኋላ በሚል ጠንከር ያለ ክስ ቢሆንም ይህንን መሰረተ ቢስ ክስ የሚደግፍ መረጃ እንዳልተገኘ ጠበቃ ተማም አባ ቡልጎ ተናግረዋል።ብይኑ ሲሰጥ በእስረኞች ቆጠሩ ንጽበኩል ምንም አይነት የመደናገጥ ወይም የመረበሽ ምልክት አለማየታቸውን የተናገሩት ጠበቃው፣ የእኛ ደንበኞች ለምን እንደታሰሩ የሚያውቁ የሀይማኖት መምህራን እና ለእኛ ጽናትን የሚያስተምሩ ናቸው ብለዋል

የወያኔዉ የይስሙል ፍርድ ቤት የተመሰረተባቸውን ክስ ተከላከሉ የበየነዉ አቡበከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል መሃመድ፣ ያሲን ኑሩ ኢሳአሊ፣ ከሚል ሸምሱ ሲራጅ ፣ በድሩ ሁሴን ኑር ሁሴን፣ ሼህ መከተ ሙሄ መኮንን፣ ሳቢር ይርጉ ማንደፍሮ፤ መሃመድ አባተ ተሰማ፣ አህመድ ሙስጠፋ ሃቢብ፣ አቡበከር አለሙ ሙሄ፣ ሙኒር ሁሴን ሃሰን ፣ ሼህ ስኢድ አሊ ጁሃር፣ ሙባረክ አደም ጌቱ አሊዬ እና ካሊድ ኢብራሂም ባልቻን ሲሆን በነጻ ያሰናበተዉ ደግሞ ሃሰን አሊ ሹራባ፣ ሼህ ሱልጣን ሃጂ አማን፣ ሼህ ጀማል ያሲን ራጁኡ፣ ሼህ ጣሂር አብዱልቃድር፣ ሃሰን አቢ ሰኢድ፣ አሊ መኪ በድሩ፣ ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱሃፊ፣ ሼህ አብዱራህማን ኡስማን ከሊል፣ ወይዘሮ ሃቢባ መሃመድንና ዶክተር ከማል ሃጂ ገለቱን ነዉ።

No comments:

Post a Comment