አበራ ሽፈራዉ /Abera Shiferaw/
የህወሓት ምስረታና ግቡ ኢትዮጵያዊነት እንዳልሆነና አብዛኞቹ የህወሓት መስራቾችም ኢትዮጵያዊነት የማይሠማቸው እንደሆኑም በተደጋጋሚ ለማየት፣ ለመስማትና ለማንበብ ችለናል።ዛሬም ይህ ማንነታቸውን የሚያሳዩ እጅግ ዘግናኝ ድርጊቶቻቸውን ለእነዚህ እውነታዎች ምስክሮች ናቸው። ህወሓቶች ግቦቻቸውን ለመተግበር ማናቸውንም ድርጊት ከመፈጸም ወደኋላ የማይሉ በዚህ ዘመን ምንም ተወዳዳሪ የሌላቸው የጭቆና ቡድኖች መሆናችውን ማንም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ሀቅ ነው።
ባለፉት 22 ዓመታት ብቻ እንኳን ብንወስድ እነዚህ ዘረኛና የአገሪቷና የህዝቧ ጠላቶች በግለሰቦች ላይ፣ቡድኖች ላይ፣ በተማሩ ምሁራን ላይ፣ በሐይማኖት ተቋማትና አማኞቻቸዉ ላይ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎችና አባሎቻቸዉ ላይ፣ በተማሪዎች ላይ፣ በልዩ ልዩ መሥሪያ ቤቶች በሚሠሩ ሠራተኞች ላይ፣በገበረየዎች ላይ፣በወታደሩና በፖሊሶችም ላይ ፣በሲቪክ ማህበራትና አባሎቻቸዉ ላይ በአጠቃላይ በአገሪቷ ሰብዓዊ ፍጥረት ላይ እስራትን ፣ግርፋትን ፣ሞት፣ ማፈናቀልን፣ ማሳደድን፣ ፈጽመዋል አሁንም ተው የሚል ሀይል በመጥፋቱ በአገሪቷና በህዝቧ ላይ ግልጽ የመንግስት ሽብር ቀጥሏል ፤ማንም የህወሓት ጥቃት ያልደረሰበት የኢትዮጵያ ክልል የለም ለማለት ያስችላል።
የአገሪቷን ንብረትና ሀብት፣ መሬት፣ የንግድ ተቋማትንና ማናቸውንም የመንግስት መዋቅር ተቆጣጥረው የብዝበዛ ግዜያቸውን እያራዘሙ ይገኛል፤ ይህን ችግር ለመቀየርና ነጻነትን ለማስመለስ እየተደረገ ያለውን ሠላማዊ ትግል ለማሳካት የሚደርጉትን ትግሎች በተደጋጋሚ ለማደናቀፍ የሚፈጥሩት ችግር ስንመለከት በርግጥም እነዚህ ሰዎች ለህዝብና ለሀገር እንዲሁም ለዲሞክራሲና ለፍትህ ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላቸውና ይልቁንም ዛሬ ጥቅሞቻቸዉን ላለማጣት የሚያደረጉት ርብርብ መሆኑን ከድርጊታቸው ለማየት ይቻላል። በእርግጥም ለዓመታት የፈጸሟቸው ወንጀሎች እንደሚያስጠይቋቸው የገባቸው ህወሓቶች ስልጣናቸውን በዲሞክራሲያዊ ግብዓቶች ይለቃሉ ብሎ የሚያምን ካለ ተሣሥቷል ያለፈው ታሪካቸው የሚያሳየን ይህንኑ ሃቅ ነውና።
ህወሓትን ለመታገል የትግሉ መንገድ ምንም ይሁን ምን ካልቆረጥን ይኸው መከራችን ማብቂያ እንደሌለው ማስተዋል ያለብን ይመስለኛል። ህወሓቶች በታጠቁት ትጥቅ ተመክተዋል ፤አንዳንዶችም በዘረፉት ሀብትና በአከማቹት ሃብት ተማምነዋለ፤ ድርጅቱም ቢሆን ባለዉ የታጠቀ ሰራዊት ተመክቷል ፣ የትጥቅና የወታደር ብዛትም ምንም መመለስ እንደማይችል ከታሪክ መረዳት ያልቻሉት ለምን እንደሆነ ባይገባኝም ምን አለበትም ውድቀታቸውን እያቀረቡ ይመስለኛል።
ባለፉት ቀናት በሰላማዊ የትግል መሥመር የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካ ፓረቲዎች ማለትም የሰማያዊ ፓርቲ ፣የአንድነትና የመድረክ ፓርቲዎችን ሠላማዊ እንቅስቃሴ ለመገደብ በአባሎቻቸውና በመሪዎቻቸው ላይ የሚያደርጉትን እስራትና ማዋከብ እንዲሁም በእስላምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚወስዱትን ግድያ ስንመለከት እነዚህ ህወሓቶች ወደለየለት የሽብር እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተዋል ህዝቡም በመንግስት እየተሸበረ ይገኛል።
ዛሬ ኢትዮጵያ በተደራጀና የራሳቸውን ጥቅም ከግብ ለማደረስ በተዋቀሩ የህወሓት መሪዎችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ወደለየለት ችግር ውስጥ ገብታለች፤ ዛሬ የተደራጁ የመንግስት አሸባሪዎች ኢትየጰያንና ህዘቦቿን በሽብር እያተራመሷት ይገኛሉ፤ ይሁንና ይህንን ችግር ለመለወጥ መፍትሔ ያለው በእኛው በኢትዮጵያውያን እጅ ነውና ከአገር ውስጥ ጀምሮ ኢትዮጵያውያንን በአሉበት አገራትም የተቀናጀ የትግል ስልት በመደገፍ መታገል እንዳለብን አመክራለሁ። ካልሆነ ግን የኢትዮጵያ ህዘብ አሁንም መከራ እንደሚገፋ ሊገባን ይገባል አላለሁ። ህወሓትን መመከት የወቅቱ ጥያቄ ነውና እንነሳ።
ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርክ
No comments:
Post a Comment