Saturday, December 28, 2013

የሃገሪቷን ኢኮኖሚ ለሞት የዳረገው የወያኔ ባለስልጣናት የውጭ ምንዛሬ ዘረፋ

የሕወሓት ስውር እጆች የግል ባንኮችን እያዳከማቸው ነው!!!

በምንሊክ ሳልሳዊ 

የውጭ ምንዛሬ ማለት ለአንድ ታዳጊ ሃገር እጅግ እንቁ የሆነ እና ሊንከባከቡት ሊያሳድጉት የሚገባ ብቸኛ የኢኮኖሚ ዋልታ ሲሆን ይህንንም በቁጠባ እና ብልሃት በተሞላበት የኢኮኖሚ አስተዳደር ከያዙት ትልቅ የኢኮኖሚ ግብ ላይ የሚያደርስ ነው:: የሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ምርኩዞች በላኪዎች እና በውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሚልኩት መሆኑ እሙን ነው::በላኪነት ስራ ላይ በብዛት ተሰማርተው የሚገኙት የገዢው መደብ አባላት እና ዘመድ አዝማዶቻቸው እንዲሁም በጥቅም ትሥሥር ላይ የተለጠፉ አቆርቋዥ ነጋዴዎች ንግድን ሽፋን ሃገሪቷን በማራቆት ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ::የወያኔ ባለስልጣናት ደሞ ከውጪ አገር ዜጎች ጋር የውስጥ ሽርክና በመፍጠር በጥቅም ትሥሥር ከመሬት ጀምሮ እስከ ማንኛውም ማተሪያሎች ከቀረጥ ነጻ ወደ ሃገር ውስጥ ሲገቡ በኢንቨስትመንት ስም ከሚመሰረተው ድርጅት ጋር የማይገናኙ ውድ እቃዎች ሳይቀሩ ገብተው ሃገሪቷ ማግኘት የሚገባትን እንዳተገኝ ባለስልጣናት ጋሬጣ ሆነዋል::

የወያኔ ባለስልጣናት ቤተሰቦች እና ዘመድ አዝማዶች በላኪነት ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ በግልጽ የሚታወቅ...ገንዘብን ምንም አይነት ዋስትና ሳያሲዙ በአነስተኛ ወለድ እየወሰዱ የማይከፍሉ እና ሰነድ የሚያስጠፉ ሲሆን ያለምንም ቀረጥ እና ታክስ ወደ ውጭ ሃገር ምርቶችን በመላክ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ወደ ሃገር ቤት ከማምጣት ይልቅ በተለያዩ የአውሮፓ እና የኢሲያ ሃገራት ባንኮች ይዶሉታል::

ብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬን ለመሸጥ እና ለመግዛት ዋጋ ቢወስንም የወያኔ ቴሌቭዥን ይህንን ቢናገርም በተግባር ግን እየተምታታ ያለው የውጭ ምንዛሬ ሂደት የግል ባንኮች ግን የውጭ ምንዛሬ መግዣ ዋጋን ወደጎን በመተው ከወያኔ የላኪ ድርጅቶች የውጭ ምንዛሬ በመሸጫ ዋጋ ሲሸምቱ እየተገኙ በዝምታ ታልፈዋል:: ይህም በሃገሪቷ የኢኮኖሚ ሂደት ላይ እንቅፋት የሆነ ሲሆን አንዳንድ ላኪዎች ከመንግስት ባንኮች የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሬ በተዘዋዋሪ ለግል ባንኮች ሲቸበችቡ እየታየ በዝምታ እየታለፈ ነው::የሕወሓት ስውር እጆች የግል ባንኮችን እያዳከማቸው ነው::በመተማ በሞያሌ በመልካ ጀብዱ በኩምሩክ በሁመራ በሃርትሼክ ወዘተ በኢትዮጵያ ዙሪያ ገባ የድንበር ከተሞች ላይ በከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተሰማሩት በአብዛኛው የወያኔ አባላት እና የአከባቢ ባለስልጣናት ካድረዎች ከሚወጡ የሃገር ውስጥ ምርቶች የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለግል ጥቅማቸው እንደሚያውሉት ታውቋል::ይህም ጉዳይ በከፍተኛ ደረጃ ከብሄራዊ ባንክ ጀምሮ እስከ ድንበር ከተሞች የባንክ ቅርንጫፎች ድረስ በሙስና መረብ የተያያዘ የባለስልጣናት ስውር እጆች የተደባለቁበት ነው::

መሰረታዊ ለሆኑ የገቢ እቃዎች የጠፋው የውጭ ምንዛሬ ለሃገሪቱ የፖለቲካ ፍጆታ የመከላከያ እና የደህንነት መዋቅሮች ሲመደብ ማየት በህዝብ ጉሮሮ ላይ ቆሞ ስልጣንን በማስረዘም ሃገርን እየገደሉ መሆኑ በአደባባይ እያየነው ያለነው ሃቅ ነው:; የብሄራዊ ባንክ ከጊዜው የገዢ መደቦች ጋር በማበር የሃገርን ሀለቄታዊ የኢኮኖሚ ጥቅሞች አሳልፎ እየሰጠ ከባንክ አሰራር ውጭ ከፖለቲካው ጋር ግንኘነት ያሌላቸው አስመጪ ነጋዴዎች ማግኘት ያለባቸውን የውጭ ምንዛሬ ባለማግኘታቸው በ20 እና 30 % ጭማሪ ምንዛሬዎችን በመግዛት ጋሬጣ የተፈጠረባቸው ሲሆን ይህ ሁሉ የገዢው መደብ አባላት የፈጠሩት የውጭ ምንዛሬ ዘረፋ በሃገሪቷ ላይ የኑሮ ውድነት እንዲሰራፋ አድርጎታል::

No comments:

Post a Comment