Saturday, December 28, 2013

እኔ ኣላውቅም ፈራሁ ጃዋር

በሄኖክ የሺጥላ

የበደሌ ቢራ ፋብሪካ ከ ኣዲስ ኣበባ 483 ኪ.ሜ  ርቀት ላይ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ኢሉ-ኣባ-ቦራ ( Eloo The father of  Holstein  Friesian) ኢልባቡርከተማ በሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ስኩውር ሜትር ይዞታ ላይ ስራውን እንደ ኣውሮጳውያን ኣቆጣጠር በ 1993  ማከናወን የጀመረ ትልቅ የቢራ ማምረቻ ድርጅትነው።

ኢሊባቡር መልካም ምድራዊ ኣቀማመጡም ሆነ ምድራዊ ልምላሜው፥ እንደ በቆሎ ፤ ገብስ፤ ጤፍ፤ የቅባት እሎች፤ ማር፤ ከነ ቦራ ደሞ ወተት፤ ቅቤ እና ወዘተየሚዘራባት፤ የሚታጨድባት፤ የሚቆረጥባት፤ የሚታለብባት ሃገር እንድትሆን ኣድርጉዋታል።

ኢሊባቡርን የጽሁፌ መንደርደሪያ ኣደረኩ እንጂ ዋናው ነጥቤ እሱ ኣይደለም። ዛሬ መናገ ወይም መጻፍ የፈለኩት ቴዲ ኣፍሮ በቅርቡ በመላው ኢትዮጵያ የሙዚቃዝግጅቱን እንዲያሳይ ወኪል የሆነውን የበደሌ ቢራን ያለመጠጣት ኣድማ ( boycotting)  በመላው ኢትዮጵያ ይደረግ ዘንድ ኣንዳንድ ግለሰቦች የጀመሩትን ነገርሰምቼ፤ ለምን በደሌን፤ ለምን ቴድን የሚል ጥያቄ ለሚጠይቁ፤ መልስ የሚመስለኝን ለመተየብ፤ ከተቻለም ለማሳየት መመኮር በመሻቴ ነው ።

ቴዲ ኣፍሮ በቅርቡ በጋዜጣ ላይ ስለ ኣድዋ ድል በሰጠው ኣስተያየት የተቆጡ፤ የተቀየሙ ግለሰቦች፤ ቴዲ ኣፍሮ ጥቁር ሰው ብሎ ንጉስ ሚኒሊክን፤ ከዛም በላይየኣድዋ ድልን በመዘከሩ የተበሳጩ የህብረተሰብ ኣካሎች፤ ቴዲ ኣፍሮ ከዚህ ቀደም ጃ ያስተሰርያል ብሎ በመዝፈኑ ቂም የቁዋጠሩ ሰዎች፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በሊግ ኦፍ ኔሽን በ 1936  የኢጣልያንን የተለከለ  የኬሚካል መሳሪያ መጠቀምን በመቃወማቸው፤ ኢትዮጵያን የ ዩናትድ ኔሽን ኣባል በማድረጋቸው፤ ቅራኔዎችን ኣብርደው ያፍሪካን ህብረት በመመስረታቸው፤ ለነዚህ ጉልህ ኣስተዋጾዎቻቸው በመዝፈኑ፤ ለነዚህ ለተጠቀሱት መልካም ስራቸው መታሰቢያ የጭንቅላቱ ውጤትየሆነውን ምዚቃ በማበርከቱ፤ ቴዲ ኣፍሮ ፤ ኣቀንቃኝ ና ኣዝማሪ ፤ ገጣሚና ሰኣሊ፤ ሃያሲና ደራሲ፤ ጸሃፊ ተውኔቱና ብላታው፤ ኣፉን በለጎመበት ዘመን፤ በብእሩየታሪክ ጋሻ፤ በግጥሙ ለቆሰለ ታሪክ ማገገሚያ፤ በዘፈኖቹ ( ከ ማሊ ሱፊዎች ባልተናነሰ መልኩ) የነብስን ክር እየተጫነ ያላስለቀሰው፤ ያላስተከዘው፤ ሰው እንደሌለየገባቸው ሰዎች፤ በይበልጥም የኣድዋ ድል፤ የጥቁር ኣንበሳዎች ድል መሆኑን ያሳየበት በመሆኑ እና ይህም የሚያማቸው ሰዎች፤ ዛሬ በደሌ ቢራ ቴዲ ኣፍሮንስፖንሰር ስላደረገ፤ በደሌ ቢራን  ያለመጠጣት ኣድማ ጠርተዋል። ኣሁን ቴዲ ኣፍሮን ኣብዶ በረንዳ ( የጫት ማከፋፈያ በረንዳ ነው) ቢሆን ስፖንሰር ያረገው ምን ሊሉ ነበር።። ባረገው እና የተከታዮቻቸውን መልስ ባየን።  ኣንድ ጊዜ ቆይ ጠብቁኝ ሳቄ መጣብኝ ያለው ተናጋሪ ማን ነበር።


ኣዲሱ የቴዲ ኣፍሮ ኣልበም (ጥቁር ሰው) የብዙዎቹን እትዮጵያዊያኖች ድምጽ ያስገኘለትን ያህል፤ ንጉስ ሚኒሊክ በድሎናል፤ ጡታችንን ቆርጦዋል፤ ወዘተ ወዘተርፈለሚሉት ደሞ፤ ከሚኒሊክ መፈጠር፤ ከታሪክ ኣንቅጽነቱና ኣኩሪ ገድሉ ጋር የጀመሩትን  እጹብ ጸብ ውሃ የሚደፋበት በመሆኑ፤ ጠላት ሊያፈራበት እንደሚችልመገመት ብዙም ኣይዳግትም። እናም ‘ነዚህ ሰዎች ቀደም ብዬ እንደ ጠቀስኩት፤ በደሌ ቢራን ያለመጠጣት ኣድማ እናድርግ እያሉ ነው። ልክ ናቸው፤ ህዝብበጥላቻም በቢራም ሰክሮ እንዴት ይሆናል፤ ባንዱ ብቻ ይበቃልና።

በነገራችን ላይ ይህንን ኣድማ ለማስመታት ከሚራወጡት እና ከሚሯሯጡት ሰዎች መሃከል ኣንዱ ጃዋር መሀመድ መሆኑን ሰምቼ ኣፍሬ ጥፍሬ ውስጥ ልገባነበር። ባንድ ወቅት ይሄ ወጣት ፖለቲከኛ ስለ ራሱ ሲናገር  “እኔ እናቴ መንዜና የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነች ኣባቴ ደሞ ኦሮሞና ሙስሊም ነው ፤ ታዲያ ከኔበላይ ኢትፖጵያዊነትን የሚወክል ምንነት ኣለ ወይ” ብሎ ነበር። መልሱ ሊሆን ይሚችለው ጃዋርዬ በውነትም የለም፤ እንዳንተው ኣቶ መለስም እኮ የተላቀቀነገርን ማጣበቅ የሚችል (ኡሁ የሆነ) (UHU…glue) ደም ነበራቸው፤ ግን ደሙ ሳይሆን የደሙ ባህሪ ነው ወሳኙ ነገር። የተሸከምነው ደም  ሳይሆን  በውስጣችንያፋፋነው ስብዕና ነው ማንነት ፤  ማንነት ስራ ነው እንጂ ኣንተ እንዳልከው የ-ኢ-ተጎራባች ዘር ደም ውህደት (ኬሚስትሪ ውጤት ኣይደለም)፤ ክርስቶስ ( ኤሳው… ኣለይሁ ሰላም) በ-በረት ተወለደ ብለን እናምናለን፤  ግን እንደ ሰብኣዊ ፍጡር በ-በረት መወለዱ ሳይሆን ሰው ሆኖ ሲኖር ያደረገውን ነገር ነው የምናስበው፤ ስለ ነብዩ ሙሃመድ (ሰ.አ.ወ) ኣንድ ሙስሊም ሲያስብ ስለ ዘራቸው ሳይሆን ስለ ስራቸው ነው የሚያስበው ብዬ ኣስባለሁ ።  ባንድ ወቅት ይሄውሰው፤ ፹ ከ ፻ የሚሆነው የሃገሬ እስላም ኦሮሞ ነው፤ እናም የእሮሞ ህዝብን ኢምፓወር ማድረግ፤ እስልምናን ኢምፓወር እንደማረግ ነው ኣለን፤ለመስማት ኣይደል የተፈጠርነው እናም ሰማነው፤ ባሜጃ ኣለን ዝም ብለን  ሰማነው፤ ቀጥሎም ኢትዮጵያ ኣውቶ ኦፍ ኦሮሚያ  ኣለን  እሱንም ሰማነው። በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ኣውት ኣፍ ኦሮሚያን ወደ ፈርንጅኛ ስቀዳው ( the child give birth of her mother) ኣይመስላችሁም ? ለመተርጎም የተገደድኩት የመጀመሪያው ራሱ እንግሊዘኛ መሆኑን ስለ- ተጠራጠርኩ ነው። ለነገሩ ስታንፈርድና ኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ እኮ መፈክር ኣያስተምሩም።

እና ዛሬ  በደሌ መጣ እና ወንድሜ ጃዋር  ሰማኒያ ከመቶ ካለው ሃሳብ ጋ ግንባር ለግንባር ተጋጨ (head on collusion) እናም  ሁለት የሚጋጩ ነገሮችንእንግዲህ እናስተውላልን።

፩)  መቼም ፹ ከመቶው  እስላም ኦሮሞ ነው ብለኽን፤ ኣንተም በዘር ብቻ ሳይሆን በእምነትም ጭምር ጠበኽ፤ ኣልገባኝም ታዲያ እንዴት ነው፤ እነማን ቦይ ኮት እንዲያረጉልኽ ነው ጥሪውን ያቀረብከው፤ ፳ ፐርሰንቱ እስላም ያልሆነው ኦሮሞ ? ደሞ ከ ፹ ከመቶ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ውስጥም ቢሆን ኣዲስ የበደሌ ኣድመናኛ ማግኘት ይቸግራል ብዬ ኣስባለሁ፤ ምክኒያቱም እነሱ ላንተ ሲሉ ሳይሆኑ ለዲናቸው ሲሉ ድሮም እንዲህ ኣይነቱን ነገር ይነኩት ነበር ብዬ ኣላስብም፤ በፍጽም ኣያደርጉትም፤ ታዲያ የማይጠጡ ሰዎችን ነው ኣድማ የጠራነው፤  ወይስ ሙሉ የኢትዮጵያዊነት ማሳያ ምሳሌ እንድትሆን ያደረገችህ የመንዜዋ እናትህን ዘመዶች፤  እኔ ኣላውቅም ፈራሁ  ሄኖክ ነው ያለኝ የልጅነት ጉዋደኛዬ፤ ባንድ ትልቅ የውሃ ጉድጉዋድ ውስጥ እንሹለክ ስለው።  እኔ ኣላውቅም ፈራሁ ጃዋር።

ዛሬ ጀርመን ያላትን ቅርጽ እንድትጠብቅ ወይም እንዲኖራት ያደረገው ኦቶ ቮን ቢስ ማርክ፤ የደም ትግል ውጤት ነው። ታዲያ ጀርመኖች በ ቢስ ማርክ ተናደው ፒሊሲነርን ( የጀርመን ታዋቂ ቢራ ነው) ቦይ ኮት እናርግ ኣላሉሉም። በፈረንሳይ እንዲህ የሚባል ታሪክ ኣለ፤ በኣሜሪካም፤  ኣረ ሆመር በጥንታዊያኖቹ የግሪክ ዘመን ስለነበረው ጦርነትም ጽፎዋል፤ ስለ ስርኣቱ፤ ስለ ኣገማምኖን እና የወንድሙ መንግስት፤ ስለ ሄለናዊው ስርኣት፤ ከዚያም በሁዋላ እነ ዳንቴ ስለ ጻፉት ስለ ዲቫይን ኮሜዲ፤ ፍሬድሪክ ዊልሃልም ኒቺ ስለተራቀቀበት የማህበረሰብ ስነ ልቦና፤ እነ ኣልበርት ካሙ ስለጻፉለት የፈረንሳይ ማህበረስብ እና በየስራቶቹ ውስጥ ስለ ነበርው ፍዳ፤ እነ ልዮ ቶሎስቶይ በሰላ ብእራቸው ስለዘገቡት የሩሲያ የጭቆና ቦለቲካ፤ እነ ፓብሎ ፒካሶ ጉሬንሽያ ብለው ስለገለጹት የስፔን ከተማ ስለ ስንቱ ለዚህ ለወጣቱ ፖለቲከኛ እንንገረው  እስኪ ባክህ ጁሃርዬ ገረፍ ገረፍ ኣርጋቸው (በቃ እንደውም ለዚህ ክረምት  ለፐርሰናል ዲቨሎፕመንት…ትመለከታቸው ዘንድ እጠይቅ፤ሃለሁ (ማሳሰቢያ በኣብዛኛው በኣማራ ጻሀፊ ኣይደልም የተጻፉት ቢሆኑም ደሞ ኣነተ ኣምሳ ፐርሰንት ኣማራ ኣይደለህ እንዴ፤ የምሬን እኮ ነው)

በታሪክ ላይ ጥላሸት መቀባት በፍጹም ለማንም ኣይሳካም፤ ወደድንም ጠላንም፤ ጠቅልለን የምንጎርሰውን እንጀራ የፈጠሩት ኣባቶቻችን ናቸው፤ ለሆዳችን ያለን ቅርበት ለታሪካችንም ይኑረን። ቴዲ እንዳለው ክፉውን በክፉ ለመመለስ ማሰብ ሌላ ክፉነት ነው። ሁለቱ ደሞች እንደ ደም ይሰሩ፤ ያስቡ ዘንድ ሰው እንሁን።

No comments:

Post a Comment