Sunday, August 11, 2013

በሐሙሱ የመንግስት የጅምላ ጥቃት ሰበብ መንግስት ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት ነው! (ድምፃችን ይሰማ)

እሁድ ነሐሴ 5/2005

በፖሊስ ጥቃት የተፈጸመባቸው የመንግስት ኃላፊዎች አሉ!

‹‹ይህን ተቃውሞው ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው›› የመንግስት ኃላፊዎች ለፓርቲ አባላት ገለጻ ሲሰጡ 

በእለተ ዒድ ፖሊስ በሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ በፈጸመው ድርጊት መንግስት ኪሳራ ውስጥ እየገባ ነው፡፡ የኢድ በዓል በተከበረበት ቀን በጣም በርካታ ሙስሊሞች የድብደባ ሰላባ ሲሆኑ የዚያኑ ያህልም በርካታ የመንግስት ኃላፊዎች መደብደባቸው ታውቋል፡፡ መንግስት ተቃውሞውን ለማስቆም በወቅቱ ከሰራቸው ሰፋፊ የሚዲያ ፕሮፖጋንዳዎች በተጨማሪ በመሬት ላይ የፖርቲ አባላቱን ፣የጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጆችን፣ የፖርቲው የሴት እና የወጣት ሊግ አባላትን እንዲሁም መካከለኛ አመራሮቹን በሙሉ በመጠቀም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ለዒድ ሰላት እንዳይሄድ ከፍተኛ ቅስቀሳ አድርገጓል፡፡ ሆኖም ይህ ቅስቀሳ ሙሉ በሙሉ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ሙስሊሙ ህብረተሰብም ያለምንም ፍርሃት ሙሉ ቤተሰቡን ይዞ በሰላት አደባባዮች በመገኘት ለሃይማኖቱና አገሩ ያለውን መከታነት አሳይቷል፡፡ 

መንግስት የስታዲየሙን የሰላት ስነ ስርአት የሚሳተፉ ሙስሊሞችን በጥሪ ካርድ ብቻ እንዲገቡ ለማድረግ ከወሰነ እና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከጀመረ በኋላ መረጃው ሕዝብ ዘንድ መድረሱን በመረዳቱና ኅብረተሰቡም በራሱ ካርዶችን ማሳተም መጀመሩን በመረዳቱ በካርድ ማስገባት የሚለውን ውሳኔ በመጨረሻ ሰዓት ሰርዞታል፡፡ መንግስት ከኢድ ሰላት ማቀብ የሚለው ሙከራው ሙሉ በሙሉ መክሸፉን የተረዳው በኢድ እለት ዋዜማ ነበር፡፡ አዲስ አበባ በዚያ መልኩ በአስፈሪ የጦር ቀጠና ብትሸፈንም ሙስሊሙ በኢዱ ቀን ተቃውሞውን ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይል ለመንግስት ተገልጾለታል፡፡ ያለው አማራጭ ተቃውሞውን ማፈን፣ ማደብዘዝ እንዲሁምም ከተቻለ መሸበብ ነበር፡፡ አልሀምዱሊላህ በአላህ ቁድራ እነዚህ ሁሉ አልተሳኩም፡፡ 

መንግስት ይህን እቅዱን ለማሳካት በስታዲየሙ ከ116 የአዲስ አበባ ወረዳዎች ከእያንዳንዱ ወረዳ 30 ካድሬዎች በጥቅሉ ወደ 4ሺ አምስት መቶ የሚጠጉ ካድሬዎችን ከሌሊቱ 11 ሰዓት አዲስ አበባ ስታዲየም እንዲደርሱና በስታዲየሙ ውስጥ ጥሩ የሚባሉ ይዞታዎች ላይ ቦታ ይዘው እንዲቀመጡ አድርል፡፡ በተጨማሪም የዛኑ ያህል ቁጥር ያላቸውና ከ116 የአዲስ አበባ ወረዳዎች እና ፓርቲ፣ ወጣት፣ ሴት ሊግ የተወጣጡ የመንግስት ሰዎች በስታየሙ ዙሪያ የመጀመሪያዎቹን ረድፎች ቦታ እንዲይዙ ተደርጓል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ የሌላ እምነት ተከታይም ጭምር ነበሩ፡፡ የመንግስት ኃላፊዎች ለፓርቲ አባላት፣ ለወረዳ እና ክፍለ ከተማ አስፈጸሚዎች እንዲሁም ለሴቶችና ወጣት ሊግ አባላት ‹‹ይህን ተቃውሞው ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው›› ብለው ገለጻ ሲሰጧቸው እነደነበር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ‹‹ይህን ማሳካት ካልቻላችሁ መኖር አትችሉም፤ የእንጀራ ገመዳችሁ ይበጠሳል›› የሚል ማስፈራሪያ ሰጠዋቸውም እንደነበር ታውቋል፡፡ 

ይህን ተልእኮ ለማሳካት በሕዝቡ መሐል ተቀላቅለው የገቡ የፓርቲ እና ሊግ አባላት በስታዲየም ውስጥና በአካባቢው የሚገኙ ሙስሊሞችን የመጠቆም እና የማስያዝ ኃላፊነትም ጭምር ተሰጥቷቸው የነበሩ ሲሆን የተቃውሞውን ቅኝት የማስለወጥና ተቀናቃኝ ሆኖ የመቅረብም ፍላጎት እንደነበራቸው ታውቋል፡፡ ሆኖም በሙስሊሙ መሀል በባህር ላይ ጠብ እንዳለች አንዲት የውሃ ጠብታ አንሰው የተገኙት ካድሬዎች በሌላው ከመዋጠ ውጪ ምርጫ አልነበራቸውም፡፡ ተቃውሞው ሲካሄድም ሆነ ሌላው ስርአት ሲፈጸም ተስለምልሞ ከማየት የዘለለ እድልም አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም የተሳካው ተቃውሞና ተምሳሌታዊ የቀብር ስነ- ስርአት ከተካሄደ በኋላ እነዚሁ በመሀከል የተሰገሰጉ ግለሰቦች ሙስሊሙን ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊመሩት ቢጥሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ 

ፖሊስ አሰቃቂ ድብደባወን በጅምላ ሙስሊሙ ላይ መፈጸም በጀመረበት ወቅት ግን እነዚህ የፓርቲ አባላት ከፖሊስ ድበደባ ሊተርፉ እዳልቻሉ ማወቅ ተችሏል፡፡ ጾታና እድሜን ሰያገናዝብ በጅምላ በተሰነዘረው ጥቃት በመንግስት ተልእኮ ተሰጥቷቸው ሙስሊሙ መሀከል ተቀላቅለው የነበሩ የመንግስት ሀላፊዎችም ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡ ይህ ድብደባ ከደረሰባቸው መካከል የየካ ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ሐላፊ እንዲሁም የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሀላፊ የሆኑ ግለሰቦች የሚኙበት ሲሆን አካላቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው ማወቅ ተችሏል፡፡ የፓርቲው አባላት ከዒዱ ክስተት በኋላ ትናንት ሶስት ወረዳዎችን በማጣመር ባደረጉት ከተማ አቀፍ ግምገማ ቅራኔያቸውን ያቀረቡ ሲሆን ዒዱን ለማደናቀፍ ያደረጉት ጥረት ሁሉ እንዳልተሳካና በተቃራኒው መንግስት በፈጸመው የጅምላ ድብደባ እና ግድያ ኪሳራ መሸመቱን አረጋግጠዋል፡፡ 

አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment