Saturday, August 22, 2015

ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ማጠናከሪያ በቬጋስ ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ተዋጣ ፣የግንባሩ አመራር የወያኔን ሻዕቢያ ወረረን የማደናገሪያ ካርድ ቀደን መጣል አለብን ሲሉ ገለጹ

የአርበኞች ግንቦት 7 ትላንት ማምሻውን ረቡዕ ኦገስት 19 /2015 በላስ ቬጋስ ከተማ ባካሄደው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ጨረታን ጨምሮ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ብር ዌኢም ከ65 ሺህ ዶላር በማይ ገቢ ተሰበሰበ።ሕዝቡ ግንባሩ የጀመረውን ትግል በመደገፍ በስልጣን ላይ ያለውን የግፍ አገዛዝ ለመጣል እስከመጨረሻ ድጋፉ እንደማይለይ የተሌአዩ ተሰብሳቢዎች ገለጹ።

በስብሰባው ላይ ለጨረታ የቀረበው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፎቶና በኤርትራ በረሃ የሚገኙ ሴት ወጣት ታጋዮች ምስል በአንድነት ያለበትን ከ35 ሺህ ዶአለር በላይ በስፍራው የተገኙት ኢትዮጵያውአን ተጫርተው አቶ መላኩ አምባቸው የተባሉ አገር ወዳድ የጨረታው አሸናፊ ሆነዋል።

በዚህ ስብሰባ ላይ በአካል የተገኙት የድርጅቱ አመራሮች አቶ ሙሉነህ እዩኤልና አቶ ጋሳው ገብሬ በየበኩላቸው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ከኤርትራ በረሃም የግንባሩ ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፣ ድርጅቱ ከፍተኛ አመራር አቶ ነአምን ዘለቀና የግንባሩ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በተለያዩ ስፍራዎች ከሰራዊቱ ጋር ያደረጉት ውይይት ከሰራዊቱ አባላት ለመሪዎቹ የቀረቡ ጥያቄዎች በፊል ቀርቦ ታይቷል።

አቶ ሙሉነህ እዩኤል በስፍራው ባደረጉት ንግግር አርበኞች ግንቦት 7 በኢትዮጵያ ያለውን አገርና ሕዝብ አዋራጅ፣ዘረና ስርኣት ለመገርሰስ ሳይወድ ተገዶ በገባበት ጦርነት ከወያኔ በሚተኮሰው ጥይት ለሚሞተው ብቻ ሳይሆን አገሩን ነጻ ለማውጣት መስዋት የሚከፍለው በተኮሰውም ጥይት ለሚሞቱ እንደሚያዝን ገልጸዋል።

ግንባሩ ኤርትራን ለትግል የመረጠባቸውን እና በኢትዮጵያውያንም ሆነ በኤርትራውአን በኩል የሚነሱ ለምን መተባበር ያስፈልጋል የሚሉ ጥአቄዎችን አንስተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጃፓንና አሜሪካ በአንድ ወቅት የገቡበትን የጦርነት ሁኔታ በማንሳት ዛሬ አገራቱ ያላቸውን ግንኙነት በማስታወስ ጠላትነት ብቻ ቢያስቡና መተባበር የለብንም ቢሉ ኖሮ ዛሬ የጃፓን መኪና የአሜሪካን ገበያ ባላጥለቀለቀ በሌላ ዙር ጦርነት ውስጥ በነበሩ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።

በቅርቡ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ሻዕቢያ ወረረን የምትለዋን ካርድ መጠቀም ይጀምራል ያሉት አቶ ሙሉነህ እዩኤል ይህ ሆን ብሎ የሚደረግ የቅስቀሳ ካርድን የወቅቱን ተጨባጭ ሁኔታ በመረዳት፣ወያኔ በአገርና በሕዝብ ላይ ያለውን ግፍና የማያቋርጥ በደል በመመልከት ከዚህ አዳራሽ ስንወታ ቀደን መታል አለብን በማለት ለምን ከኤርትራ ጋር መስራት እንደሚያስፈልግ ሰፊ ትንታኔ ሰጥተዋል። በስፍራው የተገኘው ሕዝብ አርበኞች ግንቦት 7 ለነጻነት ትግል በኤርትራ በኩል ለሚያደርገውን ትግል ያላቸውን ድጋፍ በከፍተና ሞራል ጭምር ሲገልጹ ተስተውላል።


አቶ ጋሻው ገብሬ ሌላው የግንባሩ አመራር በበኩላቸው በኢትኦጵአበስላለው አስከፊ አገዛዝ የፈተራው ስደት፣በዜጎች ላኢ የሚፈጸሙ ግልጽ የግፍ እርምጃዎች ወደ ትግሉ እንዲገቡ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል:፡ በውጭ ያለውም ኢትዮጵያዊ የቻለ ትግሉን በአካል ሌላውም ባለበት በመደገፍ የነጻነት ትግሉን በጋራ መደገፍ ይገባል ብለዋል። በስብሰባው ላኢ አንድ አባት ትግሉን ለመደገፍ የጣት ቀለበታቸውን አውጥተው ለትግሉ ሰልመዋል። አቶ ሙሉነህ እዩኤል በቬጋስ ያደረጉትን ሙሉ ንግግር ዘግይተን ለማቅረብ እንሞክራለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአርበኞች ግንቦት 7 ባለፈው ዕሁድ በዋሽንግተንና በሲያትል ቅዳሜ በዳላስ ከፍተኛ ሕዝብ በየስብሰባው አዳራሽ ተገኝቶ ለትግሉ አለውን ድጋፍ ላቅ ባለ ደረጃ አሳየ ሲሆን በዚህም ከሶስቱ ከተሞች ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ($200 ሺህ ዶላር) መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል። በዳላስ በአንድ የውጭ አገር ዜጋ የተሰራው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ምስል በ38 ሺህ ዶላር ጨረታ ሲሸጥ በዲሲ በከፍተና ፉክክር ለሌላ የአቶ አንዳርጋቸው ምስል ከሰባ ሺህ ዶላር በላይ በጨረታ አውጥቶ ተሸጧል።

ከግንባሩ መሪዎች መካከል ሊቀመንበሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ኤፍሬም ማዴቦ እና ሌላው ከፍተና አመራር አቶ ነአምን ዘለቀ ለወሳኝ ትግል ኤርትራ መግባታቸው በአገር ውስጥና በውጭ በነጻነት ወዳዱ ወገን ከፍተና መነቃቃት የፈጠረ ሲሆን በተቃራኒው በአገዛዙ መሪዎች ዘንድ መደናገጥ መፍጠሩን አስቀድመን በህብር ሬዲዮ መዘገባችን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment