Friday, October 11, 2013

ሳይወለድ ሞት የለም!!!

                                            
                          

                 ከሞረሽ ወገኔ ዓለም አቀፍ የሴቶች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የአገራችን ሕዝብ ታሪክ በአመዛኙ የጦርነት ታሪክ እንደሆነ ይታወቃል። ጦርነት ደግሞ አውዳሚ ነው። በመሆኑም በታሪካችን በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱት ጦርነቶች አያሌ ሕይዎት ጠፍቷል ፣ ከፍተኛ ቁሣዊ እና መንፈሳዊ ኃብት ወድሟል። የተካሄዱት ጦርነቶች ዋነኛ መንስኤ የ«ሥልጣን ለእኔ ይገባኛል» ግብግብ ስለነበር ያደረሱት ጥፋት በተለይ በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ አልነበረም። ስለዚህ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን የጥፋቱም ሆነ የሹመቱ ተጎጂ እና ተጠቃሚ ያደረጉ ነበሩ። ለጥፋቱ ግን ግንባር ቀደም ሠለባና ተጠቂ የሆኑት፥ ሕፃናት ፣ እናቶች እና አረጋውያን እንደሆኑ ይታወቃል።


በታሪካችን አንድ ዘር በብቸኛነት የፖለቲካ ሥልጣንን ጨብጦ ፣ የሌሎችንም ጎሣዎች ጭምር በዘር አደራጅቶ ፣ «ተቀናቃኜ ነው« የሚለውን የሌላውን ነገድ አባሎች ግን በአድማ እና በሤራ ከምድረ-ኢትዮጵያ ለማጥፋት የተንቀሳቀሰበት አጋጣሚ በተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም። በአፍሪቃ ፖለቲካ ፥ በተለይም በኢትዮጵያ ፥ መሆን ያለበት ሣይሆን መሆን የሌለበት ስለሚሆን ፣ አንዳንድ ጊዜ ሁኔታዎች የወለፌንድ ሆነው ይገኛሉ። በተለይም በእኛ ዘመን ከአገሪቱ ሕዝብ አምስት ከመቶ ከማይሞሉት የትግሬ ነገድ የፈለቁት ገዢዎች ፣ ዘጠና አምስት ከመቶ የሚሆነውን የአገሪቱን ዜጎች እጅ ከወርች ጠፍረው አሥረው ያሰቃዩታል። ከሁሉም በላይ የትግሬ-ወያኔ ቡድን የራሱን ነገድ ተወላጆች በጥብቅ የወታደራዊ አደረጃጀት አደራጅቶ ፣ ዐማራ የተሰኘውን ነገድ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት ሌት ተቀን ይባዝናል። ይህ ናዚያዊ ቡድን በዐማራው ሕዝብ ላይ በከፈተው መጠነ ሠፊ የሆነ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ፣ የሥነ-ልቦና ፣ የባህል ፣ የማኅበራዊ እና ወታደራዊ ዘመቻዎች አያሌ ዐማሮች ተገድለዋል ፣ ከሥራ ተባርረዋል ፣ በአሠቃቂ ሁኔታ ተገርፈዋል ፣ ከቀያቸው እና ከአገራቸው ተሰድደዋል ፣ በመረጡት አካባቢ የመኖር መብታቸውን ተገፍፈው ፣ ኃብት ንብረታቸውን ተነጥቀው ተባርረዋል ፣ አልያም በማንነታቸው ተዋራጅ ሆነው በበታችነት ሕይዎታቸውን እንዲገፉ ፈርዶባቸዋል። በሠቆቃው የችግሩ ቀዳሚ ገፈት ቀማሾች የዐማራ ሕፃናት እና እናቶች መሆናቸውን ስናይ ደግሞ ልባችን ይበልጥ ይደማል ፣ ኅሊናችን ይቆስላል። ይህ የታሪካችን እጅግ አሣፋሪው እና አሣዛኙ ምዕራፍ ነው። በመሆኑም የትግሬ-ወያኔዎችን ድርጊት በአንክሮ ላየው የጀርመን ናዚዎች በአይሁዶች ላይ ከፈጸሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚበልጥ እንጂ የሚያንስ አይደለም። ግፉ ያንሳል ከተባለ ግን የሚያንሰው እንደ አይሁዶቹ ዐማራው ተደራጅቶ በዘሩ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ለዓለም ኅብረተሰብ አለማሰማቱ ብቻ ነው።

No comments:

Post a Comment