Saturday, October 12, 2013

ወያኔ በእሳት የተቃጠሉ አብያተ ቤተክርስቲያናት ለፖለቲካ ፍጆታ አየተጠቀመ ነዉ

ምስራቅ ጎጃም ዉስጥ አዋበልና አነደድ በሚባሉ ወረዳዎች የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ ባለው የአምስት ወር ጊዜ ዉስጥ በእሳት ተቃጥለው መዉደማቸዉንና በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳትና መጽሐፍትም የእሳቱ ሰላባ መሆናቸዉን ምስራቅ ጎጃም ዉስጥ የሚገኙ የዜና ወኪሎቻችን በላኩልን ዜና ገለጹ። በቃጠሎዉ እጅግ ያዘኑት የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል የቃጠሎዉ ምክንያት ባስቸኳይ ተመርምሮ በወንጀለኞቹ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ሰሚ ጆሮ እንዳላገኙ ዘጋቢዎቻችን አክለዉ የላኩልን ዜና ያስረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጉዳዩን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው በክልሉ ቴሌቪዥን በዜና መልክ እንዲገለፅ ያደረጉት ጥረትም አለመሳካቱ ታዉቋል፡፡

በአንድ አካባቢ ብቻ በተለያየ ጊዜ አብያተ ክርስትያናት በተደጋጋሚ ሲቃጠሉና ንብረት ሲወድም በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኋን አንድም ቀን አለመዘገቡ ወንጀሉ የመንግስት እጅ እንዳለበት በግልጽ ያሳያል ሲሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ሰዎች በመናገር ላይ ናቸዉ። ይህንን ጉዳይ በሚመለከት ዘጋቢያችን ያናገራቸዉ አንድ የምስራቅ ጎጃም የባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት ሰራተኛ አብያተ ቤተክርስቲያናቱ መቃጠላቸውን አረጋግጠዉ በቃጠሎው የተነሳ በህዝብና በመንግስት በኩል እንዲሁም በህዝቡና በቱሪዝም ኮሚሽን በኩል ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱን ተናግረዋል። መንግስት ድርጊቱን የፈጸሙት የሙስሊም አክራሪዎች ወይም የማህበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው ሲል፣ ህዝቡ ደግሞ አክራሪዎች አይደሉም በማለት እየተከራከረ መሆኑን ሰራተኛው ጨምሮ ገልጿል። የባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤትም የችግሩ መነሻ በውል ባይታወቅም በአክራሪዎች ምክንያት እንዳልሆ በውል እንደሚያምን አክለው ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment