ሁልጊዜም በያመቱ የአባላት ግምገማ (በሂሳብ ሰዎች አጠራር የሰዎች ኢንቬንተሪ) የሚያካሂደው ፋሽስት ወያኔ፤ የታመመ፣ የደከመ፣ ተነሳሽነት የጎደለው እንዲሁም ሌላል ሌላም በሚል ሰበብ፤ የፖለቲካ አቋም መስመራቸውን ያላስተካከሉ የሚላቸውን እንደሚቀጣ ይታወቃል። በዚህ መሰረትም ብአዴን የሚባለው የወያኔው አንዱ አንጃ ኪራይ ሰብሳቢነት በሚል አጀንዳ የጀመረው ግምገማ ከፍተኛ ውዝግብና መተረማመስ ከመፍጠሩም በላይ በስብሰባው የተገኙ አባላት በብአዴንና በወያኔው አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማት ላይ መሆናቸው ታውቋል።
“ባይናችን እያየነውና እየሰማነው ካለው በአገዛዙ ሹመኞች የሚከወን ንቅዘት አንጻር እኛን እስክርቢቶ ወሰዳችሁ እያሉ መገምገም ፌዝ ነው” ያሉት የግምገማው ተሳታፊዎች “በሚሊዮን ዶላር በሚቆጠር መጠን ወደ ውጭ ሀገራት ባንኮች የሚወጣውን ሃብት መቆጣጠር የተሻለ ነበር” ሲሉ በምሬት ተናግረዋል። አክለውም “ልጆቻችንን በቅጡ ለመመገብና ለማሳደግ ካቃተን አባላት ላይ የአባልነት ክፍያ እያለችሁ ትሰበስባላችሁ ሌላው ግን አገዛዙ የቸረውን የአገዛዝ ቦታ ተጠቅሞ ከሕዝብ በዘረፈው ሃብት ሶስትና አራት ሕንጻዎችን ሲገነባ የሚናገረው የለም፤ እኛም መረረን መኖር አቃተን በዚሁ ሳቢያም አባላት መልቀቂያ እያስገቡ ነው ብለዋል።”
No comments:
Post a Comment