
የስብሐት ነጋና የአጃቢዉ የታምራት ገ/መድህን ድፍረት ዲሲ፤ ቨርጂኒያና ሜሪላንድ ግዛቶች ዉስጥ የሚኖረዉን ኢትዮጵያዊ ያስቆጣ ሲሆን ኢትዮጵያዉዉያኑ ፖሊስና ፍርድ ቤት በሁለቱ ወንጀለኞች ላይ የሚወስዱትን እርምጃ ለማወቅ በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸዉ። የዚህ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ያናገራቸዉ አንድ በቅርቡ ከኢትዮጵያ የመጡ ታደለ ጉርሙ የተባሉ ግለሰብ “የእነሱን ድብደባና እርግጫ ላለማየት አገሬን ጥዬ መጣሁ እነዚህ አይነ ደረቆች እዚህም እያመጡ ሰዉ ይደበድባሉ እንዴ” ካሉ በኋላ ደግነቱ አገሩ አሜሪካ ነዉና ሌላ ቢቀር እኛን አገራችን ዉስጥ የነፈጉንን ፍትህ እነሱ እዚህ በአይናቸዉ ያያሉ ብለዋል።
ኢትዮጵያ ዉስጥ በመካሄድ ላይ ያለዉ ህዝባዊ እንቅስቃሴ መጎልበት፤ የተቃዋሚ ኃይሎች ጡንቻ መፈርጠምና የቱባ ቱባ የህወሃት ባለስልጣኖች አገር ጥሎ መፈርጠጥ ያሳሰባቸዉ የወያኔ ሹማምንት በትዕቢተኛዉ መሪያቸዉ በስብሐት ነጋ መሪነት እዚህ አሜሪካ መጥተዉ ከአሜሪካ መንግስት ባለስልኖች፤ እግሬ አዉጭኝ ብለዉ ከፈረጠጡ አባላቶቻቸዉና ከጥቂት ሆዳም ደጋፊዎቻቸዉ ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸዉ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች መዘገቡ የሚታወስ ነዉ። ትላልቅ የአገዛዙን የደህንነት ባለስልጣኖች ጨምሮ ከፍተኛ የህወሃት መሪዎችን ይዞ አሜሪካ የገባዉ የወያኔ ቡድን አሜሪካ ደርሶ እንቅስቃሴዉን እስኪጀምር ድረስ ትግርኛ ተናጋሪ ከሆኑት የኤምባሰዉ ሰራተኞች ዉጭ ግርማ ብሩን ጨምሮ ሌሎቹ ከፍተኛ የኤምባሲዉ ባለስልጣኖች በፍጹም አለመስማታቸዉን ከዉስጥ አዋቂ ምንጮች የተገኘዉ መረጃ ያለመክታል። ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት አሜሪካ ሲመጡ አሜሪካ ዉስጥ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማዉቁ የሚያሳየዉ አስፈላጊ በሆኑ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ወያኔ ከትግርኛ ተናጋሪዎች ዉጭ ማንንም የማያምን ዘረኛ ድርጅት መሆኑን ነዉ ሲሉ ብዙዎች ትችት ይሰነዝራሉ።
No comments:
Post a Comment