Friday, February 28, 2014

USA FULL REPORT ON ETHIOPIA EPRDF`s HUMAN RIGHTS ABUSES

Ethiopia

EXECUTIVE SUMMARY

Ethiopia is a federal republic. The ruling Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF), a coalition of four ethnically based parties, controls the government. In September 2012, following the death of former Prime Minister Meles Zenawi, parliament elected Hailemariam Desalegn as prime minister. In national parliamentary elections in 2010, the EPRDF and affiliated parties won 545 of 547 seats to remain in power for a fourth consecutive five-year term. Although the relatively few international officials allowed to observe the elections concluded that technical aspects of the vote were handled competently, some also noted that an environment conducive to free and fair elections was not in place prior to the election. Authorities generally maintained control over the security forces, although Somali Region Special Police and local militias sometimes acted independently. Security forces committed human rights abuses.

The most significant human rights problems included: restrictions on freedom of expression and association, including through arrests; detention; politically motivated trials; harassment; and intimidation of opposition members and journalists, as well as continued restrictions on print media. On August 8, during Eid al-Fitr celebrations, security forces temporarily detained more than one thousand persons in Addis Ababa. The government continued restrictions on activities of civil society and nongovernmental organizations (NGOs) imposed by the Charities and Societies Proclamation (the CSO law).

Other human rights problems included arbitrary killings; allegations of torture, beating, abuse, and mistreatment of detainees by security forces; reports of harsh and, at times, life-threatening prison conditions; arbitrary arrest and detention; detention without charge and lengthy pretrial detention; a weak, overburdened judiciary subject to political influence; infringement on citizens’ privacy rights, including illegal searches; allegations of abuses in the implementation of the government’s “villagization” program; restrictions on academic freedom; restrictions on freedom of assembly, association, and movement; alleged interference in religious affairs; limits on citizens’ ability to change their government; police, administrative, and judicial corruption; violence and societal discrimination against women and abuse of children; female genital mutilation/cutting (FGM/C); trafficking in persons; societal discrimination against persons with disabilities; clashes between ethnic minorities; discrimination against persons based on their [deleted] orientation and against persons with HIV/AIDS; limits on worker rights; forced labor; and child labor, including forced child labor.

Thursday, February 27, 2014

ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል!!!

የባህርዳር እና አካባቢው ሕዝብ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ሺህ ጊዜ እንደሚሻል አካሉን ብቻ ሳይሆን ህሊናውንም ለትግራዩ ነፃ አውጪ ህወሓት ባርነት ላስገዛው “የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)” እያለ እራሱን ለሚጠራው ድርጅት መሪዎች ተናገረ።

ባርነት ክፉ ነው። በባርነት ላይ የጭንቅላት ባዶነት ሲታከልበት ደግሞ አለምነው መኮንንን የመሰሉ የብአዴን መሪዎችን ይፈጥራል። የብአዴን መሪዎች ለጌታቸው ህወሓት ያላቸውን ታማኝነት ለማሳየት ራሳቸውን ማዋረዳቸው ሳያንስ እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ በጅምላ መስደባቸው ብአዴን እንደ ድርጅት የሚገኝበት የተዋረደ ደረጃ ያሳያል።

ህሊና ያለው ባርያ ዛሬ ነፃ ባይሆንም ወደፊት ነፃ የመውጣት ህልም አለው። ዛሬ በጉልበተኛ የባርያ አሳዳሪ ነፃነቱን ቢያጣም የህሊና ነፃነቱን ያላስደፈረ ባርያ ለነፃነት መታገሉ የማይቀር ነው። እንደ ብአዴን መሪዎች በታማኝ ባርያነቱ እየፈነጠዘ ያለ ባርያ ግን ነፃ ሰው የመሆን ህልሙንም ጭምር አጥቷል። እንዲህ ዓይነቱ ባርያ በአካልም፤ በመንፈስም ባሪያ ነው። ነፃ ሰው የመሆን እድል የለውም።

የአማራ ሕዝብ ብአዴንን የመሰለ አሳፋሪ ድርጅት በታሪኩ ገጥሞት አያውቅም። በፋሽስት ጣልያን ወረራ ጊዜ ለጠላት ያደሩ ባንዶች እንኳን ከዛሬዎቹ ብአዴኖች የተሻለ ክብር ነበራቸው። እነሱም ከዛሬዎቹም በተሻለ በጌቶቻቸው ጣሊያኖች ይሰሙ ነበር። በገዢዎቹ ለመወደድ የራሱን ሕዝብ የሚዘልፍ፣ የሚሰድብና የሚያዋርድ እንደ ብአዴን ያለ አዋራጅ ድርጅት በአማራ ምድር አልታየም።

የለሃጭ ተዋስዖ

በማስረሻ ማሞ (አምስተርዳም)

የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሞራል መሠረት እና ብቃት በሌላቸው ፖለቲከኞች እጅ ከወደቀ ሰንብቷል። ይህ የሰነበተ እውነታ በአሁን ሰዓት ከዝቅጠትም በታች እየኾነ ነው። ለኢትዮጵያ የሚያዋጣት ብሔርን መሠረት ያደረገ ፖለቲካዊ ርዕዮት ነው የሚለው የፖሊቲካል ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ሁሉን አቀፍ ፍትህ የተንሰራፋበት ቢኾን ምናልባት አዋጪ ሊኾን ይችላል የሚል ግምት ማስቀመጥ ይቻል ነበር። ነገር ገን ስትራቴጂው ወረቀት ላይ ሌላ መልክ የያዘ፤ ምድር ላይ ደሞ ሌላ ትርክት የዋጠው ነው። ከጅምሩ ፍትሃዊነቱ አጠራጣሪ ስለኾነ ስትራቴጂው ለማፋጀት ያለመና እርስ በርስ በጥርጣሬ ከመተያየት የማያመልጡ የብሄር ፖለቲከኞችን እየፈለፈለ ይገኛል። ለዚህም ነው ከሁለት ዐሥርተ ዓመታት በፊት “በትምክህት” ፍረጃ የተጸነሰው ሕዝብን የማቃለል ጅምር ወደ ለሃጭ ተዋስዖ ያደገው።

የብአዴን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አለምነው መኮንን ይህን የለሃጭ ተዋስዖ ከየት አመጡት? የሚለው ጥያቄ በእኔ እምነት ወሳኝ ጥያቄ ነው። ብዙዎች እንደሚያምኑት ብአዴን እንደ ፓርቲ የራሱ የኾነ ነጻነት እና እምነት ያለው ፓርቲ አይደለም፤ አሻንጉሊት እና አስፈጻሚ፤ ከሕወሃት የሚወርድለትን ትዕዛዝ እና ፖለቲካዊ ትንተና ለማስተላለፍ የሚያገልግል “ትቦ/ቧንቧ ፓርቲ” ነው። ከአራቱ የኢሕአዴግ ፓርቲዎች ውስጥ ራሱን ሥልጣን እንደሚጋራና 22 ሚልዮን ሕዝብ እንደሚወክል ድርጅት ፖለቲካዊ ስሌት ውስጥ አስገብቶ የሚንቀሳቀስ ፓርቲም አይደለም። “የአማራውን” ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችል ምንም ዐይነት ተነሳሽነትም የለውም። ይህን እውነታ በግልጽ ለመረዳት የፓርቲውን ቁልፍ ሰዎች ማንነት ማየት ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። አንድ የብሔር ፓርቲ የአባልነት መመዘኛ መስፈርቱ ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ቀድመን እናንሳ። በደም እና በዘር ከዚያ ብሔር የተገኘ ሰው ብቻ ነው የፓርቲው አባል መኾን ያለበት? ወይስ በምርጫም የዚያ ብሔር አባል ነኝ ማለትን ያካትታል?

በባህር ዳር ከተማ የታየው ህዝባዊ ተቃውሞ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም ተጠናክሮ ይቀጥላል!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
================================
በባህር ዳር ከተማ የታየው ህዝባዊ ተቃውሞ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም ተጠናክሮ ይቀጥላል!
===========================
ከአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!!!
========================================================
ከጊዜ ወደ ጊዜ አምባገነናዊ የአፈና መዋቅሩን በማጠናከር ለመድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓት በር መዝጋቱን አጠናክሮ ለብቻው አውራ ፓርቲ ለመሆን እየታተረ ያለው የኢህአዴግ መንግሥት ደርግ በውድቀቱ ዋዜማ ወደ ተላበሰው ባህሪ እየተሸጋገረ እንደሆነ ተስተውሏል፡፡

የዚሁን ድርጅታዊ ባህሪ ውርስ በዋነኛነት ከሚያስፈጽሙት የግምባሩ አባል ድርጅቶች አንዱ የሆነው ብአዴን ኢህአዴግ በአማራው ህዝብ ላይ እየፈፀመው ያለው የንቀት እና የማጥላላት ዘመቻም አብይ ተደርገው ሊወሰዱ ከሚችሉ የግንባሩ አፍራሽ ተግባራት በዋነኝነት ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የክልሉን ህዝብ የናቀ እና ያዋረደ አስነዋሪ ንግግር ካደረጉ በኋላ ከጥፋታቸው ከመታረም ይልቅ በክልሉ ቴሌቭዥን ያንኑ አምባገነናዊ ባህሪያቸውን እንደያዙ የግሌ ብቻ ሳይሆን የድርጅቴ አቋም ነው ሲሉ መመለሳቸውም መላውን የሀገሪቷን ህዝብ ያስቆጣ ተግባር ነው፡፡

ይህንን አስነዋሪ ተግባር የፈጸመውን ብአዴንን ከ70 እስከ 80 ሺህ የሚደርሱ የባህር ዳር ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች ከፓርቲያችን ጎን በመሰለፍ እሁድ የካቲት 16 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም የባህር ዳርን ጎዳና እና አደባባዮች በህዝባዊ ማዕበል ሲያስጨንቁ መዋላቸውም ሰላማዊ ትግሉ የደረሰበትን ሁኔታ በግልፅ የሚያስገነዝብ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የኢህአዴግ መንግሥት በአንፃሩ ዛሬም ከስህተቱ ለመማር ያልተዘጋጀ በመሆኑ ይህን የሰፊ ህዝብ ቁጣ በማጣጣል አፋኝ እና ተሳደቢ መሪዎቹን ከጉያው ላለመነጠል እየሞከረ እንደሆነም አስተውለናል፡፡ ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ አንድነት የባህር ዳር እና አካባቢው ነዋሪዎች ላደረጉት ህዝባዊ ትገል ከፍተኛ ክብር እና አድናቆት አለው፡፡ ይህንን ህዝባዊ መሠረታችንን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር በሁሉም የሀገራችን ክልሎች ተቃውሞው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ልናረጋግጥ እንወዳለን፡፡

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ይህንን የህዝብ ጥያቄ አለመቀበሉን እየገፋበት በመሆኑም በባህርዳር የታየው ህዝባዊ ተቃውሞ ቤሎች የሀገራችን ክልሎች ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን አቶ አለምነው መኮንን በፍርድ አደባባይ ለማቆም በአጭር ጊዜ ውስጥ ክስ መስርተን ለህዝብ ይፋ እንደምናደርግ እናረጋግጣለን፡፡

በመጨረሻም በዚህ ፈታኝ የትግል ምዕራፍ ፡-
1ኛ. መላው የኢትዮጵያ ህዝብ
2ኛ. በውጭ ሀገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን፤ የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎች ከጎናችን በመሆን ትግላችንን እንድትደግፉ ጥሪ እናቀርባለን !!!!
----------------------------------
በባህርዳር የታየው ህዛባዊ መነቃቃትና የትግል ስሜት በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ይደገማል !!!
-----------------------------
ድል የህዝብ ነው !!!
የካቲት 20 ቀን 2006 ዓ.ም

Wednesday, February 26, 2014

ሰንደቅ ጋዜጣ በዛሬው እትም… (ሙሉውን ጋዜጣ ያንብቡ)

ሰንደቅ ጋዜጣ በዛሬው እትም ከዚህ በታች ያሉትን ዜናዎችና በርካታ ጉዳዮችን ለህትመት አብቅቷል።


  • የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አንድነት ፓርቲ ያቀረበውን ቅሬታ ሳይቀበለው ቀረ
  • የአረና ስራ አስፈፃሚ ታራሚዎችን ልጠይቅ በማለታቸው ታሰርኩኝ አሉ
  • “ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል”
  • “[አቶ አለምነው] በይፋ ለተናገረው ነገር ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ እንከሰዋለን”
  • ጀነራል አል ሲሲን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመቀየር የተመዘዙ የመጫወቻ ካርዶች
  • ኢትዮ ቴሌኮም የዲያል አፕ ኢንተርኔት አገልግሎትን አቆመ
  • ከደቡብ ሱዳን ድርድር ጀርባ ያሉ የኢትዮጵያ ጥቅሞች

እና ሌሎችም…

ሙሉውን ጋዜጣ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) Sendek442

ሰሞነኛ ጉዳዮችን በወፍ በረር አንቀጾች ስንቃኛቸው

ይሄይስ አእምሮ (ከአዲስ አበባ)
(yiheyisaemro@gmail.com)

መግቢያ

“እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም እርሱ የሚጸየፋቸው ሰባት ናቸው፤ እነርሱም፡- ‹በንቀት የሚመለከት ዐይን፤ ሐሰት የሚናገር ምላስ፤ ንጹሖች ሰዎችን የሚገድሉ እጆች፤ ክፉ አሳብ የሚያፈልቅ አእምሮ፤ ወደ ክፋት ለመሮጥ የሚቸኩሉ እግሮች፤ በውሸት ላይ ውሸት እየጨመረ የሚናገር ምሥክር፤ በወዳጆች መካከል ጠብ የሚያነሣሣ ሰው› ናቸው፡፡” ምሳሌ 6፣ 16 – 19

ከአፍ ከወጣ አፋፍ ነው

አለምነው መኮነን የተባለው የወያኔ እንደራሴ በአማሮቹ ሀገር እምብርት ዋና ከተማ ባሕር ዳር ላይ በዝግ ስብሰባ ተቀምጦ በወሻከተው ነገርና መዘዙ ሳቢያ ብዙ እየሰማን ነው፡፡ ሰውዬው ጅል መሆን አለበት – አለዚያም ወፈፌ፤ ከአፍ የወጣ ነገር የትም ሊደርስ እንደሚችል ካጣው እውነተኛ በሽተኛ ነው፤ ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ መባሉ ይህን ዓይነት ዕብሪት ለመግለጥ ነው፡፡ ወያኔዎች ሊታወሱም ሆነ ሊረሱ የማይፈልጉ ዕንቆቅልሾች መሆናቸውን በሰሞኑ ድርጊታቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአሁኑ ኢትዮጵያዊ መቼት አማራን መሳደብ ትርጉም የሌለውና የደረቀ ወንዝን እንደመሻገር የሞተ ፈረስን እንደመጋለብ ያለ ዶንኪሾታዊ የጀብደኝነት ፉከራና ሽለላ  ነው፤ ስንትና ስንት ወቅታዊ ጠላት እያለ አርፎ የተቀመጠን ምሥኪን ወገን በጠላትነት ፈርጆ በተደጋጋሚ ኅሊናን ለማቁሰል መጣደፍ የዕድሜ ማራዘሚያ ክኒንን በከንቱ ውጦ እንደመጨረስ ያለ ሞኝነት ይመስለኛል፤ ወያኔዎች ሆይ! ያደርሳችኋል ግዴላችሁም – በኔ ይሁንባችሁ – እስከዚህን ቅጥ አምባራችሁ አይጥፋ፤ ጥጋባችሁን እንደምንም ቻል ለማድረግ ሞክሩ – የዱባ ጥጋብ ካለስንቅ እንደሚያዘምት እናንተም ይህች በሸፍጠኝነትና በሁለገብ ዓለማቀፋዊ ሻጥር የያዛችኋት አዱኛና የመንግሥት ሥልጣን ናላችሁን አዙራችሁ የምትሆኑትን አጥታችኋልና ፈጣሪ የምትቋምጡለትን ዕብሪት አስተንፋሽ እስኪልክላችሁ ባልተቆጠበ ትግስት ተጠባበቁ፤ ፈጣሪ “የነገሩትን የማይረሳ፣ የለመኑትን የማይነሳ” ቸር አምላክ ነውና የምትፈልጉትን የጦር ድግስ ይነፍገናል ብላችሁ ሃሳብ አይግባችሁ፡፡ የዱሮ ጦር ሠራዊት እንደናንተ ጥጋብ ሲወጥረው  ጦር አምጪ እያለ መሬትን ይደበድብ ነበር አሉ፡፡ በምታምኑበት ይሁንባችሁና አማራውን ተውት – ብሶቱን በእህህኣዊ ዕንባው ወደላይና ወደሚመለከተው አካል ያስተላልፍ፡፡ ጓድ አለምነው መኮንን ስማኝ- ቴፕ ሪከርደር እንኳን  የሰጡትን ላለመቀበል አንዳንዴ ያንገራግራል – ችንጊያው ሲጎትት፣ አልማዙ ሲበላ ወይንም ባትሪው ሲያልቅ፡፡ አንተ ግን በአማራው መሀል ተቀምጠህ በጌታዋ እንደተማመነችዋ በግ ቀን በጣለው ሕዝብ ላይ እንዳንዳች የሚቀረና ቅርሻትህን ለቀቅኽው፡፡ ግዴለም፡፡ ግፍን ያላሳለፈ፣ ጡርን ያልሰማ ወደ ደህና ቀን አይወጣምና ይህም ለበጎ ነው፡፡ ለአንተ ግን “መጥኖ መደቆስ ቀድሞ ነበር” ማለትን እወዳለሁ፡፡ አሁን ማጣፊያው ሲያጥርብህና ንግግርህን በማሳመር ሰውን ለማስገልፈጥ እንደዋዛ በወረወርከው ስድብ ሕዝባዊ የተቃውሞ ውርጅብኝ ሲበራከትብህ “የአራት ቀናት ንግግር በኮምፒውተር ተቆርጦ ተቀጥሎ ነው እንጂ የወጣሁበትን ሕዝብ እንዴት ልሳደብ እችላለሁ?” ብለህ በዐይኔን ግምባር ያ’ርገው መሃላ ብትሸመጥጥ የእናቴ መቀነት አሰናከለኝ ዓይነት የተበላ ዕቁብ መሆኑን ልትዘነጋ አይገባም፡፡ አንተ አማራን የተሳደብከው የተማመንከውን ተማምነህ ምናልባትም በተማመከው ኃይል ታዝዘህ ነው ብንል አንሳሳትም፤ የወደፊቱን እንጃህ እንጂ ለአሁኑ ከሽልማት በስተቀር የሚገጥምህ ክፉ ነገር እንደሌለ በደኖንና ዐርባጉጉን በማስታወስ ብቻ በሚገባ እንረዳለን፡፡ ዱባ ካላበደ መቼም ቅል አይጥልም፡፡ አማራ ነኝ የምትለው አለምነውም ሆንክ የሌላ ብሔር አባል ወይም ነጭም ይሁን ጥቁር የማንኛውም የሌላ ሀገር ዜጋ  አንድን ሕዝብ ለመሳደብ ምንም ዓይነት አመክንዮ የለውም፡፡ ቅጽሎች የተፈጠሩት ይህን ዓይነት አወዛጋቢ ሁኔታ ለማስወገድ ነው፡፡ አንተ የትግራይን ብሔር በጅምላ ተሳድበህ ቢሆን ኖሮ በአሁኑ ወቅት ሥጋህ ለጅብ ነፍህን ለጀሃነብ ሰጥተው፤ህ በሣምንታት ውስጥ ተረስተህ ነበር – ምሳሌ ነው – የትግራይ ሕዝብ እንደሕዝብ ባለመሰደቡ የሚቆጨው ሰው ካለ የሸንጎ ፍርድ የሚገባው የመጨረሻ ወንጀለኛ ሰው መሆኑን አጥቼው አይደለም፤ ሕዝብ በደግ እንጂ በክፉ ሊነሣ የሚገባው ኑባሬ አይደለም፤ አልተለመደምም፡፡ ነገር ግን ዘረኛው የወያኔ መንግሥት አማራውን ራሱ ተሳድቦ ስላላረካው ራሱ በሾመውና በአማራነት በፈረጀው ‹ባለሥልጣን› አማራን ሊያሰድበው ወደደ፡፡ ይህ ደግሞ የግፍ ግፍ ነው፡፡ ፈረንጆቹ “adding an insult to injury” እንደሚሉት ነው፡፡ ስብሃት ነጋ፣ ሣሞራ(ሙሃመድ) የኑስና መለስ ዜናዊ አማራን በመሳደብ የሚወዳደራቸው የለም – እስኪሰለቻቸው እየሰደቡ አሰድበውታል፤ ግን ስድብ አይጣበቅ ሆኖ ተቸገሩ፡፡ እንግዲህ የነሱ ስድብና የነሱ የዘመናት ጭፍጨፋ ሊያረካቸው አልቻለም ማለት ነው፡፡ ያሳዝኑኛል፡፡ አንድን ጠላቴ ነው የምትለውን ሰው አንተው ራስህ በጥፍርህም፣ በጥርስህም፣ በጠበንጃህም፣ … በቻልከው ሁሉ ቦጫጭቀኸው እየተንጠራወዘ አልሞትልህ ሲል በከፊልም ይሁን በሙሉ በ“ደም” ይዛመደዋል የምትለውን ሰው ፈልገህ በእጅ አዙር ለማጥቃት መሞከር ከሰይጣናዊነት ሌላ ምንም ሊባል አይችልም፡፡

Tuesday, February 25, 2014

‘‘ፋሽዝም’’ በኢትዮጵያ!


በቅዱስ ዬሃንስ

ኢትዮጵያ በወያኔ ፈላጭ ቆራጭ ቡድናዊ አገዛዝ ስር ከወደቀችበት እነሆ ሁለት አስርተ ዓመታት ነጐዱ። ወያኔ ስልጣን ላይ ሲወጣ ካለፈው የተሻለ የዲሞክራሲ ለውጥ ይመጣል የሚል በብዙ ሰዎች ዘንድ የተስፋ ጭላንጭል ተጥሎለት ቢኖርም “ጅብ እስኪነክስ ያነክስ” እንዲሉ ስልጣናቸውን ካደላደሉ በኋላ ግን ተስፋ የተጣለለትን ዲሞክራሲ ደብዛውን በማጥፋት “ከፋፍለህ፣ በሆዱ ይዘህ፣ አሸብረህ፣ አደናግረህ፣ አናቁረህና አደንዝዘህ ግዛ” የሚለውን ሌሎች አምባገነን መንግስታት የሚከተሉትን የጡንቻ አገዛዝ ዘይቤ የዲሞክራሲ ሽፋን በመስጠት ዘላለማዊ ስልጣናቸውን ለማጠናክር ሲሉ በበለጠ ሲጠቀሙበት መቆየታቸው የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ቆይቷል።

በአገራችን ኢትዮጵያ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ አገዛዝ በዓለም ዙሪያ በተለያየ ዘመን ወደ ሥልጣን ከመጡት መሰል ፀረ-ሕዝብ መንግሥታት ቢብስ እንጂ በምንም መልኩ የተሻለ አይደለም።  ፋሽዝምን እንቃወማለን፣ እናወግዛለን እያለ በጫካ ያናፋ የነበረው ወያኔ ዛሬ በዲሞክራሲ ድባብ ሥር እየተገበረው ያለ አገርና ሕዝብን ማዋረድና መዝረፍ፣ መቀጣጫ እያለ በግፍ ማሰርና መግደል ምን ተብሎ ሊጠራ ነው? በአዲስ አበባ ፣ በጋምቤላ ፣ በአዋሳ ፣ በወለጋ ፣ በሰሜን እና በአራቱም ማእዘን የኢትዮጵያ ክልሎች በየእለቱ በወያኔ ታጣቂዎች እየተካሄደ ያለውን የጅምላ ጭፍጨፋ ምን ብለው ይጠሩታል?

ወያኔ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር ተሸክሞት የመጣውን በቀል አማራው፣ ኦሮሞው፣ ጋምቤላው፣ አፋሩ፣ ኦጋዴኑ ወዘተ. ዘር የማጥፋት ተግባሩን ፈጽሞታል፤ አሁንም እያጠፋ፣ እየገደለ በየወህኒ ቤቶቹ እየማገደው ነው። ይዞት የመጣው ድህነትና በሽታን ብቻ ነው። ፖሊሲው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዓለም ሃገሮች በድህነት ከወለል በታች ያደረገ ስርዓት ነው። የኢትዮጵያ ገበሬ የመሬቱ ባለቤት በነበረበት ወቅት እራሱን እና ቤተሰቡን አብልቶ ቀሪውን ለገበያ በማቅረብ ሕዝቧ እንደ አቅሙ በልቶና ጠጥቶ ያድር ነበር። የወያኔ መንግስት መሬት የመንግሥት ነው ብሎ በማወጁ የኢትዮጵያ ሕዝብ በገጠሩም በከተማም መሬት አልባ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዛ ሃገሩ ሁለተኛ ዜጋ ከመሆኑ የተነሳ ሲሞት እንኳን የሚቀበርበት ቦታ ያጣ ሕዝብ ሆኗል። የዚህ ጽሁፌ ዋና አላማ የወያኔ መንግስት የፋሽስት አገዛዝ ስለመሆኑ ምሳሌዎችን አንድ ሁለት በማለት ነቅሸ በማሳየት ማስረገጥ ሲሆን ወያኔ ከምስረታው ጀምሮ ያካሂድ የነበረውን የንፁሃን ወገኖቻችንን ጭፍጨፋ ለማስረጃነት በማንሳት ለማሳየት እሞክራሉ።

Monday, February 24, 2014

Open letter to the President of Switzerland: Re: Ethiopian Co-Pilot…

The Swiss Confederation

C/O Embassy of Switzerland
2900 Cathedral Ave. NW
Washington, DC 20008

February 24, 2014

Dear President Didier Burkhalter,

Re: Ethiopian Co-Pilot Hailemedhin Aberra Tegegn

It is to be recalled that on Monday, February 17th 2014, a Boeing 767 Ethiopian Airlines commercial airliner, Flight ET702, which was en route to Rome, was diverted to Geneva, where it safely landed at 6:02 am (0502 GMT). As it has been widely reported, the airliner was diverted from its official route by the Ethiopian co-pilot, Hailemedhin Abera Tegegn, who made a request for political asylum in Switzerland while hovering over Geneva.

Those of us who have gathered here today at the Swiss Embassy in Washington D.C. as well us so many others who have been unable to come due to work and other commitments, are eager to humbly appeal on behalf of our compatriot Hailemedhin Aberra Tegegn, who appears to have great faith in the fairness, judiciousness and hospitality of the people and government of Switzerland. Having first-hand experience of facing persecution in Ethiopia, we have little doubt that Mr. Tegegn was desperate not only to seek political asylum but also feel that he was evidently eager to attract global attention to the predicament and suffering of his fellow citizens in Ethiopia who are routinely being killed, jailed and tortured by the TPLF-led regime.

Sunday, February 23, 2014

ፍርድ ቤቶች ፍርድ ቤት ይቅረቡ!

ሥራቸውን በአግባቡና በትክክል የሚያከናውኑ ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አለኝታዎች፣ የዜጐች ኩራትና መተማመኛ ናቸው፡፡ በአንፃሩ ፍርድ ቤቶች ሥራቸውን በሕግና በታማኝነት የማይሠሩ ከሆነ ደግሞ የሕዝብ ሞራል እንዲወድቅ ሐሞቱም  እንዲፈስ ያደርጋሉ፡፡ ተስፋ ያስቆርጣሉ፡፡ 

በኢትዮጵያ በትክክል ሥራውን የሚሠራ ዳኛ የለም አንልም፡፡ ተገቢ ፍርድና ውሳኔ የሚሰጥ ችሎት በጭራሽ የለምም አንልም፤ አሉ፡፡ ምሥጋናም ይገባቸዋል፡፡ አጠቃላዩ ሁኔታ ሲታይ ግን ፍርድ ቤቶች ሥራቸውን እየሠሩ አይደለም፡፡ ሕግን እያስከበሩ አይደለም፡፡

ፍርድ ቤቶች ራሳቸው ፍርድ ቤት ይቅረቡ የሚያሰኝ ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን፡፡ በየትኛው በፍርድ ቤትና በየትኛው ችሎት ትክክለኛ ውሳኔ ይሰጣል የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ እጅግ አስቸጋሪ እየሆነ ነው፡፡

በፍርድ ቤቶች ዙሪያ አራት ዓበይት ችግሮች ይታያሉ፡፡

ችግር አንድ - ሙስና

ፍርድ ቤቶች ከማንኛውም ተቋም በላይ ከሙስና የፀዱ እንዲሆኑ ይጠበቃሉ፡፡ ሕገ መንግሥቱንና ሕጐችን የመተርጐም ኃላፊነት የተሰጣቸው ናቸውና፡፡ እነሱ ራሳቸው በሙስና ሊዘፈቁ ሳይሆን፣ በሙሰኞች ላይ በቀጥታ በመወሰን ሙስና እንዲጠፋ ለማድረግ ትልቅ ሚና እንዲጫወቱ ይጠበቃል፡፡

ግን! ነገር ግን! ራሳቸው የሙስና ሰለባ እየሆኑ ናቸው፡፡ ጉቦ በመብዛቱ በጥቅማ ጥቅም ቀጠሮ ማራዘም፣ ፋይል መዝጋትና ፍርድ ማዛባት በከፍተኛ ደረጃ እየታየ ነው፡፡ አሳሳቢና አስጊም እየሆነ ነው፡፡

ወርሃ የካቲት

በአገራችን ታሪክ ውስጥ ወርሃ የካቲትን ልዩ የሚያደርጓት ቁም ነገራት አሏት። አስቀድመን ጀግኖቹ አብርሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስግዶም ግሪያዚያንን ያስበረገገውን ቦንብ ያፈነዱበት ወር የካቲት መሆኗን ማስታወስ እንወዳለን። በዚህ ምክንያትም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ30 ሺህ በላይ ህዝብ ተገድሎ የሰው ደም እንደ ክረምት ጎርፍ ከተማዋን ያጥለቀለቀው በዚህች በየካቲት ወር ነው። በሌላ በኩል ጠላቴ “የአማራ ህዝብ እና ተፈጥሮ “ነው ብሎ በፅኑ የሚያምነው ህወሃት የተወለደው በወርሃ የካቲት ነው። የየካቲት ታሪክ በዚህ ብቻ አያበቃም በወርሃ የካቲት ህወሃት “የመከላከያ ኃይል ቀን “ እያለ ከበሮውን እየደለቀ የሚድሪቷ ከርስ እሰከሚበረበር ድረስ ዳንኪራ ይረግጣል።

ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ግን የካቲት የደስታ ወር አይደለችም። የካቲት በግፍ የተገደሉብንን ዜጎቻችንን እያስታወስን ልቦናችን በሃዘን የሚታወክበት እንጂ ሃሴት የምናደርግበት ወር አይደለችም። በየካቲት ወር ግራዚያን “ያገኛችሁትን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ግደሉ” ብሎ አዋጅ በማስነገሩ በጭካኔው የምንቆጣበት እንጂ በደስታ የምንሰክርበት ወር አይደለችም። በወርሃ የካቲት የሌላውን ቦታ ሳይጨምር በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ30ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ሲጨፈጨፉ ከግራዚያን ጎን ቁመው ወገኖቻቸውን ያስጨፈጨፉ ባንዳዎችን እያሰብን አንገታችንን ደፍተን የምናዝንበት ወር እንጂ የደስታ ወር አይደለችም። ወርሃ የካቲት ለኢትዮጵያዊያን በደግ የምትታወስ ወር አይደለችም። በወርሃ የካቲት የተወለደው ህውሃት የተባለው ዘረኛና ዘራፊ ቡድን በአገራችን ላይ ያደረሰውን ግፍ እያሰብን ግፉ እንዲያበቃ አእምሯችን የምንሰበስብበት ወር ነች። ህወሃት በመወለዱ ኢትዮጵያችን የድሆች ሁሉ ድሃ፤የደካሞች ሁሉ ደካማ፤ ልትበታተን አደጋ አፋፍ ላይ ያለች አገር ተብላ ሥሟ በበጎ የማይነሳ አገር እንድትሆን ሆነች።

ህወሃት በወርሃ የካቲት ተወለድኩ ሲል አወጀ። ከዚያም ቀጥሎ እንዲህ አለ “አማራና ተፈጥሮ ጠላቶቼ ናቸው” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ። ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን ከተገኘም አሸባሪ እና ትምክህተኛ ነውና ይገደል ሲል ያልተፃፈ ህግ አፀደቀ። በየካቲት ወር ይህን የሞት ድምፅ ብዙ ዜጎች በአርምሞና በግርምት ሰሙት። ህወሃት አገሪቷን ክተቆጣጠር በኋላ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማራ የገባበት አልታወቀም ተብሎ ለፓርላማ መሰል አካሉ ሪፖርት ቀረበ። በግራዚያን አዋጅና በህወሃት አዋጅ መካከል ልዩነት የለም። በየካቲት ወር ግራዚያን “ያገኛችሁትን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ግደሉ” ብሎ የሞት አዋጅ አወጀ። በዚህ አዋጅ ምክንያት በአንዲት ጀንበር 30ሺህ ኢትዮጵያዊያን በአዲስ አበባ ተፈጁ። ግዲያውን ለማስፈፀም ከፊቱ የቀደሙ በስም ኢትዮጵያዊን በምግባር ግን ፋሽት የሆኑ ምናምንቴዎች ነበሩ። ከእነዚህ ውስጥ የመለስ ዜናዊ እና የስብሃት ነጋ ወላጆች በፍፁም የሚረሱ አይሆኑም። እነዚህ የባንዳ ውላጆች በወርሃ የካቲት “አማራና ተፈጥሮ ጠላቶቼ ናቸው” ብለው አውጀው ህወሃትን መሥርተው ለስልጣን ከበቁ በኋላ 2ሚሊዮን አማራ ጠፋ። በወርሃ የካቲት የተወለደው ህወሃትና ፋሽስቶችን ከሚያመሳስለው ድርጊት መካከል አንዱ ይሄው ነው። በየካቲት የተወደው ህወሃት ኢትዮጵያን በመከራ አረንቋ ውስጥ ደፍቆ እስከ ዛሬ ዘለቀ። በዚህ ምክንያት ወርሃ የካቲት ለኢትዮጵያዊያን ደገኛ ወር አይደለችም።

Saturday, February 22, 2014

የሸፍጥ ክርክር የሃሰት ክምር የታሪክን እውነታ አይቀይርም!

ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ/ም ( February 22, 2014 )

I. መግቢያ:

የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ/ም የወያኔ/ኢሕአዴግ ሊቀ-መንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአገር-ውስጥ ጋዘጤኞች በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በድፍረት የሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴን ብቻ አይደለም መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእጅጉ ያሳዘነና ያሳፈረ ሆኖ አግኝተነዋል። በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እግር የተተኩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተረከቡት የመንግሥት ሥልጣንን ብቻ ሣይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከበሬታ-አልባነትንም በሚመስል መልክ ነው ይህንን በጣም የተምታታ፤ በተቃርኖዎች የተሞላና በእጅጉ ኃላፊነት-የጎደለው ጋዜጣዊ-መግለጫ የሰጡት።

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ባደረገው ያላሰለሰ ክትትል የወያ/ኢሕአዴግ መንግሥት ከሱዳን መንግሥት ጋር የሕዝብን መሠረታዊ-ሉዓላዊነት በሚዳፈርና ዘለቄታዊ ጥቅሙን ለባዕድ አሣልፎ በሚሰጥ ሁኔታ እየሸረበ ያለውን ደባና እየፈጸመ ያለውን አሣፋሪ ድርጊት በተገቢ ጥናትና በጠራ-መረጃ ላይ ተመሥርቶ በተከታታይ ባወጣቸው መግለጫዎች እንዲሁም በልዩ-ልዩ መገናኛ-ብዙኃን አማካይነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ለወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎችና ልዩ-ልዩ ተቋማት፤ ለሱዳን መንግሥትና ለዓለም-አቀፉ ማኅበረሰብ ጭምር ሲያሳውቅ መቆየቱ ይታወቃል። የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ግን አሁንም በዚህ የአገር ድንበርን በሚያክል ከባድ ጉዳይ ላይ ከዋናው ባለ-ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ የጀመሩትን እኩይ ተግባር እየገፉበት አንደሆነ ከራሣችው አንደበት እየሰማን ነው።

መሉን እነሆ ያንብቡ፡ ebac_022214 

የመከላከያ ተቋም ተግባር አገርን መጠበቅ ነዉ ወይስ አገርን መዝረፍ?

የአዉሮፓ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ሲቀራመቱ ባህር ተሻግረዉ በመጡ የነጭ ባዕዳን ኃይሎች መገዛትን መርጦ የአዉሮፓን ወራሪዎች በሰላም በሩን ከፍቶ ወደ አገሩ ያስገባ እንድም የአፍሪካ አገር አልነበረም፤ የኋላ ኋላ ተሸንፈዉ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ቢወድቁም ሁሉም የአፍሪካ አገሮች እንደ አቅማቸዉ ከወራሪ ኃይሎች ጋር ተፋልመዋል። በአንድ ወቅት የቅርብ ጎረቤቶቻችንን ጨምሮ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች በወራሪ ኃይሎች ተሸንፈዉ የቅኝ ገዢዎች ቀንበር ጀርባቸዉ ላይ ሲጫን አገራችን ኢትዮጵያ ብቻዋን የአለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ሆና የኖረችዉ ጣሊያኖች፤ እንንግሊዞችና ፈረንሳዮች ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለይተዉ ስለወደዷት ወይም ስላከበሯት አይደለም። ይልቁንም ነፃነታችንና የግዛት አንድነታችን ተከብሮ የኖረዉ ኢትዮጵያ እናት አገሩ በጠላት ስትደፈር ከሚያይ ምትክ የሌላት ህይወቱ ብታልፍ ደስ የሚለዉ የኩሩና የጀግና ህዝብ አገር በመሆኗ ነዉ። የሚገርመዉ ይህ ኩሩና ጀግና ህዝብ ጣሊያንን የመሰለ በዘመናዊ መሳሪያ የታጀበ ኃይል ዉርደቱን ተከናንቦ ወደመጣበት እንዲመለስ ሲያስገድድ እንደ ዛሬዉ የተደራጀ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት አልነበረዉም። ዛሬ አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ላይ የተተከሉት ሁለቱ ታሪካዊ ሀዉልቶቻችን የሚነግሩንም ይሀንኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ ሠራዊት ሳይኖረዉ የጎበዝ አለቃ እየመረጠ በጣሊያን ፋሺስቶች ላይ የተጎናጸፈዉን አኩሪ ድል ነዉ።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘመናዊና የተደራጀ መከላከያ ሠራዊት ጥንስስ የተጣለዉ በዳግማዊ ሚኒልክ ዘመነ መንግስት ሲሆን እሱም ቢሆን ከአድዋ ድል በኋላ ቆይቶ የመጣ ክስተት ነዉ። በአፄ ኃ/ሥላሤና በደርግ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያ ለአንድ ፓርቲና ይህ ፓርቲ እወክለዋለሁ ለሚለዉ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ብቃት የነበረዉ፤ሙያዉን የሚያከብርና ለአገሩና ለወገኑ ታማኝ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት ነበራት። የወያኔ ዘረኞች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ የመጀመሪያ ኢላማቸዉ አድርገዉ ካወደሟቸዉ ዋና ዋና የአገራቸን ተቋሞች ዉስጥ የመጀመሪያዉ ይሄዉ የአገርና የህዝብ ደጀን የነበረዉ ተቋም ነበር። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ የአገር መከላከያ ሠራዊት እየተባለ የሚጠራዉ ተቋም ለጎጠኞች ጥቅምና የስልጣን መራዘም የቆመ፤ በዘረኝነት የተካፋፈለ፤ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ ሙያዊ ብቃት የሌለዉና የወገንና የአገር ፍቅር እንዳይኖረዉ ተደርጎ የተደራጀ ሰራዊት ነዉ። ይህንን ሠራዊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሳይሆን የወያኔ ሠራዊት እያልን የምንጠራዉም በዚሁ ምክንያት ነዉ።

ወያኔ/ኢህአዴግ = ህገወጥ እና ፀረ-ዴሞክራሲያዊ የሽብር ፓርቲ - መታገል የግድ ነው::

የህግ የበላይነት ባልተከበረበት ሀገር ስለዴሞክራሲያዊ መብቶች ማንሳት ተገቢ አይደለም፡፡ የወያኔ መንግስት ሁሉም ዜጋ በህግ ፊት እኩል ነው እያለ ሲፅፍና ሲናገር እንሰማለን፡፡ ወያኔ/ኢህአዴግ ይህንን ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በአመለካከት ከኔ እስካልተለያየህ ድረስ ማለቱ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በአስተሳሰብ የተለየ እስካልሆንክ ሰው ብትገድል እንኳ በእርቅ ነፃ መውጣት ትችላለህ፡፡ ስልጣንህን ተገን በማድረግ የህዝብ ንብረትና ገንዘብ ብትዘርፍ ዘመነኛ ተብለህ ልትሸለማለህ ትችል እንደሆነ እንጂ ሙሰኛ አያሰኝህም፡፡

የወያኔ ጁንታ የፍትህና የጸጥታ አካላት ህግን ተመርኩዘው በህገወጥነት እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል፡፡ እነዚህ የፍትህ አካላት የተባሉት የሚወስዱት ህገ-ወጥ እርምጃ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሳይሆን የወያኔን መንግስት ለሚቃወሙ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች በአጠቃላይ የተለየ ሐሳብ የሚያራምዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመጫን የተመሰረቱ ይመስሉኛል፡፡ በማንኛውም ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ ፖሊስ መጀመርያ ግለሰቡን "ከወያኔ/ኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች" አንዱ መሆኑን እና አለመሆኑን ከወያኔ/ኢህአዴግ ባለስልጣናት ይሁንታ ካላገኘ የማሰር አቅም አይኖረውም፡፡ የፍትህ አካላትም ክስ የሚመሰረቱበትን የግለሰቡን ማንነት አስቀድመው ከወያኔ/ኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች ውጭ መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላቸዋል፡፡ ዳኞችም እንግዲህ በአንፃሩ ከወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በአመለካከት ያልተለዩ ከሆኑ ወንጀል ቢፈፅምም ተጠርጣሪ ጠያቂ አለበት ማለት ይከብዳል፡፡ የፖለቲካ ታማኝነቱ ሳይታወቅ የተከሰሰ አባል እንኳ በችሎት ላይ እያለም ክሱ እንዲሰረዝለት የሚደረግበት አጋጣሚ አለ፡፡

Friday, February 21, 2014

የብአዴኑ አቶ አለምነው ህዝብን ይቅርታ ጠይቆ ለፍርድ መቅረብ አለበት!


የብአዴን/ኢህአዴግ ዋና ፀሐፊ እና የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አለምነው መኮንን በግልፅ እመራዋለሁ የሚለውን ህዝብ በመሳደቡ ያለምንም ማንገራገርና ማምታታት ይቅርታ ጠይቆ እራሱን ለፍርድ ማቅረብ አለበት፣ ማስተዋሉ ካለው፡፡ በርግጥ የኢህአዴግ መሪዎች የህዝብና የሀገር ክብር እንደሌላቸው ግልፅ ነው፡፡ ያው በትዕቢትና በጠመንጃ እንጂ አንዳቸውም ህዝባዊ ፈቃድና ይሁንታ አግኝተው እንደማይመሩ እራሳቸውም ያውቁታል፡፡

ነገር ግን እንደ አቶ አለምነው መኮንን በቆሸሸ አስተሳሰብ ህዝብን ያህል ነገር ባለጌ ስድብ የሚሳደብ አይደለም ህዝብን ቤተሰቡን የመምራት ብቃት አለው ብሎ ማመን ይቸግራል፤ ይበልጥ ለቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቹ አዘንኩላቸው፡፡

ብአዴን/ኢህአዴግም ቢሆን ምንም እንኳ ለህዝብ ክብር ኖሮት ባያውቅም አቶ አለምነው መኮንንን በአደባባይ ፍርድ በማቅረብና ከስራ በማሰናበት ተገቢውን ፍርድ ሰጥቶ ተፈፃሚ ማድረግ አለበት እላለሁ፡፡ አለበለዚያ አቶ አለምነውን እከላከላለሁ ብሎ የሚል ከሆነ እራሱ ብአዴን ህዝብን የመምራት ሞራል እንደሌለው አምኖ ስልጣኑን ለህዝብ ማስረከብ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከዚህ በኋላ ህዝብን የመምራት፣ ከህዝብ ታክስ መሰብሰብ፣….የሞራል ብቃቱ የለውም፡፡ ሰውዬው የሰደበው የአማራውን ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላውን የሀገራችንን ህዝብ ነውና፡፡ ህዝብን የሚንቅና የሚሳደብ በህገመንግስቱም ቢሆን ቅጣቱ ከባድ ነው፣ ህግ የሚያከብርና የሚያስከብር ስርዓት ባይኖረንም፡፡

ሁላችንም ሰክረን ነበር፡፡

በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

ድርጊቱ የተፈፀመው በ1983 ዓ.ም መጋቢት ወር ላይ ነው፡፡ ያኔ ወያኔ ወያኔ እያለ፣ ጎንደርና ባህርዳርን እንጂ አዲስ አበባን ተቆጣጥሮ ህዝቡ በኢህአዴግነቱ እውቅና ሳይሰጠው፡፡ ያኔ ጎንደርና አካባቢው ከደርግ ሰራዊት ነፃ ወጥቶ በወያኔ እንደተያዘ፣ ያኔ እኔ ከማስተምርበት በጣና ሀይቅ ዳር ከምትገኘው የጎርጎራ መንደር ወደ አዲስ አበባ መጥቼ፣ ንፋስ ስልክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስተማር እንደጀመርኩ - በመጋቢት 1983 ዓ.ም፡፡ ያን ጊዜ አንድ ጓደኛዬን ለመጎብኘት አዋሳ አካባቢ ወደምትገኝ ለኩ የምትባል አነስተኛ ከተማ ሄድኩ፡፡ ጓደኛዬ ብዙ ጓደኞች ነበሩት፡፡ ወዲያው የእኔም ጓደኞች ሆኑ፡፡ የጓደኛዬ ጓደኞች አብዛኞቹ መምህራን ነበሩ፡፡ ከሁለቱ የግብርና ሰራተኞች በስተቀር ማለቴ ነው፡፡ ከሳምንት ቆይታ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ልመለስ ስል በዋዜማው ጓደኞቼ (አሁን ሁሉም የጓደኛዬ ጓደኞች የእኔም ጓደኞች ሆነዋል) ተሰብስበው ጋበዙኝ፡፡ ቀን ተቀምጠን፣ ማታ ባንኮኒ ተደግፈን ተጨዋወትን፡፡

ማታ ላይ አብረን ስላሳለፍነው እጅግ አጭር ሳምንት ዋንጫችንን ደጋግመን አነሳን፡፡ በፍቅራችን ቅናት ይሁን በመለያየታችን ሀዘን ተፈጥሮ ጭምር አዘነች፡፡ የለኩ አድባር ጣራ ሰማይዋን በነጎድጓድ ጥፋሯ እያረሰች፣ ዳመና አይኗን ጨምቃ ዝናብ እንባዋን አፈሰሰች፡፡ እኩለ ለሊት ሆኖ ድንገተኛው የመጋቢት ዝናብ እስኪያባራ ጠጣን፡፡ ዝናቡ አባርቶ ከመጠጥ ቤቱ ስንወጣ እኩለ ለሊት አልፎ ነበር፡፡ ከዝናቡ የተጠራቀመው ጎርፍ በመንገዱ ግራና ቀኝ ይወርዳል፡፡ በዚህ መሀል አንዱ የግብርና ሰራተኛ፣ ‹‹በጣም ስለምወድህ ለመጨረሻ ጊዜ ልጋብዝህ እፈልጋለሁ፡›› አለኝ፡፡ ሌላው ጓደኛችን ቀጠለ፤ በርግጥ እንዳለው በጣም የሚወድህ ከሆነ ግብዣውን ልቀበለው ይገባል፣ ነገር ግን እሱ ለአንተ ያለው መውደድ ከሌሎቻችን በተለየ ከፍ ያለ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፣ በማለት ሃሳብ ሰጠ፡፡ ቀጠለና ሌላው ለዚህ ማረጋገጫ ያለውን ሃሳብ እንዲህ በማለት አቀረበ፡፡ ‹‹እውነት ከእኛ የተለየ የምትወደው ከሆነ በመንገዱ ግራና ቀኝ በሚወርደው ጎርፍ ውስጥ ግባና በደረትህ ተኛለት፡፡ ይህን ካደረግክ በእርግጥም ለእንግዳው የተለየ መውደድ አለህና ትጋብዘዋለህ፡፡›› ጓደኛችን ንግግሩን ሲጨርስና ጋባዡ ጎርፍ ውስጥ ሲነጠፍ አንድ ሆነ፡፡ ሁላችንም የጋባዡን የተለየና የላቀ መውደድ አረጋገጥን፡፡ ተደነቅን፡፡ ተገረምን፡፡ እንደዚያ ያለ የመውደድ ምጥቀት ከዚህ ቀደም ከመሀከላችን ተመልክቻለሁ የሚል አልተገኘም፡፡ ጓደኛችንን ከጎርፍ ውሃ ውስጥ ጎትተን አወጣነው፡፡ ፈተናውን በማለፉ ግብዣው ተፈቀደለት፡፡ አንድ መጠጥ ቤት አስከፍተን ገባን፡፡ ጋባዥ በጎርፍ የተነከረ ልብሱን እየጨመቀ ጋበዘን፤ ከለሊቱ ስምንት ሰአት ሲሆን ደግሞ በጎርፍ የራሱ ብሮችን ጨምቆ ከፈለና ግብዣው አበቃ፡፡

ያን እለት ምሽት የነበርነው ስድስት ጓደኛሞች ነበርን፡፡ ባይገርምም ሁላችንም ሰክረን ነበር፡፡ የሰከረው ጋባዥ፣ ግብዣ ለማድረግ የተለየ የጓደኝነት ፍቅርን ምክንያት አድርጎ ሲያቀርብ አምስታችንም ተቀበልነው፡፡ ምክንያቱም ሁላችንም ሰክረን ነበር፡፡ ትልቁ ፈተና ግን ያን የላቀ ፍቅር ማረጋገጥ ሆነብን፡፡ ሌላው ጓደኛችን ለዚህ ማረጋገጫ የሚገርም ‹ምሁራዊ› መፍትሄ ያለውን የጎርፍ ውሃ ጥምቀት ሲያቀርብ በአድናቆት ተቀበልነው፡፡ እንዲያውም ይህች ሀገር መቼም ቢሆን፣ ከአዲስ አበባ ርቆ ጠረፍ ቢኬድም የሚታደጋት ጠቢብ ምሁር እንደማታጣ አረጋገጥን፡፡ ምክንያቱም ሁላችንም ሰክረን ነበር፡፡ በመጨረሻም ስለዚህ ጓደኛችን እንግዳ ተቀባይነትና ታላቅ የመውደድ ጥበብ ዋንጫችንን አነሳን፡፡ የሆነው ሁሉ በታላቅ መገረምና መደነቅ፣ ተጠየቃዊ ውይይት ተደርጎበት ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ምክንያቱም ሁላችንም ሰክረን ነበር፡፡ ግን ያቺ ስካራችን ከእንቅልፍዋ የቀሰቀሳት፣ ባንኮኒ ውስጥ ቆማ ዋንጫችንን አረቄ የምትሞላዋ አስተናጋጅ አልሰከረችም፡፡ በስካር ሚዛኑን ያጣው ህሊናችን በሚያፈልቀው ቧልት እየገፈፈች፣ አንዳንዴም እየተንከተከተች ስካራቸንን ለማሳበቅ፣ ለማጋለጥ ትሞክር ነበር፡፡ ግን ማንም ከቁምነገር የቆጠራት የለም፡፡ ምክንያቱም ሁላችንም ሰክረን ነበር፡፡

እነሆ ዛሬ ከሃያ ሶስት አመታት በኋላ ሀገሬ ኢትዮጵያ ተጠየቃዊ ተጨባጭነት ያልተከተሉ ድርጊቶች በጠራራ ፀሐይ የሚፈፀምባት ሆነች፡፡ ዜጎቿም የእነዚህን በህሊና ተጠየቃዊነት መዛባት የተውሸለሸሉ ተግባራት ፈፃሚና አጽዳቂ ሆኑ፡፡ እነሆ የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ሰከረ፡፡ ሀገሬ በሚዛናዊ ህሊና፣ ተጠየቃዊ ቅብብሎሽ ሊተነተኑ የማይችሉ ተግባራት በሚፈፅሙና ይህን ድርጊት በሚያጸድቁ ዜጎች ተሞላች፡፡

ያልሰከረ የለም! ጎዳና ተዳዳሪው፣ የቀን ሰራተኛው፣ ወያላው… ድሀው በጠኔ ሰከረ፡፡ የጠኔ ስካር ደግሞ አንጀት ገብቶ ወስፋት እያስጮኸ ስለሆድ ያሳስባል እንጂ፣ ከፍ ብሎ ራስ ላይ አይወጣም፡፡ የወስፋት ጩኽት ክፋቱ የህሊናን ጩኸት አለማሰማቱ ነው፡፡ በመሆኑም አብዛኛው ድሀ ‹‹እዬዬም ሲዳላ ነው›ን ተረቶ፣ የህሊናውን ጩኸት ችላ አለው፡፡ ስለሚጮህ ወስፋቱ ቢጮህ ባልከፋ፡፡ ስለሚጮህ ወስፋቱ ለጥ-ፀጥ አለ፡፡ ማን ከርሱ ውስጥ ስለሚጮህ፣ ስለሚፈራገጥ ወስፋቱ ለስላሳና ዝምተኛ ይሆናል! ሰክሮ የህሊናውን ሚዛን የሳተ ካልሆነ በቀር!

የቤት ኪራይ ከፋዩ፣ ለኮንዶሚኒየም ቆጣቢው፣ ከእጁ ላይ ለአፉ የማያጣው፣… በጠኔ ከሰከረው ሙልጭ ድሀ ትንሽ ከፍ ያለው… ከላይኛው እጅግ ወርዶ፣ ከታችኛው ስንዝር ርቆ ‹መሀል› ላይ ያለው ዜጋም በምናገባኝና በራስ ወዳድነት ሰክሯል፡፡ ለዚህኛው ዜጋ ቁም ነገሩ በልቶ ማደሩ ነው፡፡ ወር ባይደርስ፣ ደሞዙ ቢቀነስ አያገባውም፡፡ ሊያገባ ያጫል፤ የሚወልደው ልጅ የሚማርበት ት/ቤትና ስርዓተ ትምህርት አያስጨንቀውም፡፡ ምክንያቱም በምናገባኝ ሰክሯል፡፡ ስለሱና ስለጎጆው፣ ስለ ልጁ አስተዳደግና ትምህርት የሚያገባቸው ደሞዝ የሚከፍለውና ስርአተ ትምህርት የሚቀርጽለት፣ ጎዳና የሚዘረጋለት መንግስትና የግል ትምህርት ቤት የከፈቱለት ባለሀብቶች ናቸው፡፡ የነዚህኞቹ ስካር ህሊናቸው ከጉበናቸው አልፎ እንዳያስብ አድርጎታል፡፡ ከጉበናቸው ውጪ በሀገራቸው ስለሚደረገው ማድረግ የሚገባቸው ልማታዊ ዜና ማዳመጥ፣ የምርጫ ካርድ ማውጣትና በአምስት አመት አንዴ ለኢህአዴግ ድምጽ መስጠት፣ በፀረ-ልማት ሀይሎችና በአሸባሪዎች ላይ አዋጅ ሲነገር ሰልፍ መውጣት ነው፡፡ ይህም ሆኖ የዜናው፣ የአዋጁና የመመሪያው ይዘት አያገባቸውም፡፡ የሚያገባቸው ማዳመጡ፣ መምረጡና ሰልፍ መውጣቱ ነው፡፡ የእነዚህኞቹ ስካር ከድሀው ከፍ የሚለው ፍርሀትንም ስለሚጭንባቸው ነው፡፡

ሀብታሞች፣ ባለሀብት ዜጎቻችንም ሰክረዋል፡፡ እነዚህኞቹን አናታቸው ላይ ወጥቶ ያሰከራቸው በየእለቱ ከጮማ ጋር የሚቆርጡት፣ ከውስኪ ጋር የሚጠጡት ኢትዮጵያን በገንዘባቸው ገዝተው የግላቸው የማድረግ ፍላጎታቸው ነው፡፡ ከዚህ ስካር ባንነው ወደ ህሊናቸው ሚዛን መመለስ አይፈልጉም፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ መግዛት ሲያልሙ ከስራቸው ያለውን በጠኔና በምናገባኝ የሰከረ ድሀ የሚያደርሱበት ይቸገራሉ፡፡ እናም ስካራቸው በድሀ ወገናቸው ጥላቻና ኢትዮጵያን የግል ሀብት በማድረግ ፍላጎት ተቃርኖ ሲወዘውዛቸው ውሎ ያድራል፡፡

በየመስሪያ ቤቱ የተሾሙ ባለስልጣኖቻቸውም ሰክረዋል፡፡ እነዚህን ያስከራቸው ደግሞ የስልጣን ጥማትና ስግብግብነት ነው፡፡ ባለስልጣኖቻቸውም ኢህአዴግ ገና ሲሾማቸው ከስልጣን ጥማት ጥንስሱ ጉሹን ይግታቸዋል መሰል ስለስልጣናቸው ጽናት የሚያደርጉት ድርጊት እንኳን የታወቀ ወሰን፣ የአይን ማረፊያ አድማስ አይገኝለትም፡፡ በአንድ በኩል ለስልጣን ያበቃቸውን ኢህአዴግን ለማስደሰት አኩርፎታል ያሉትን ሰድበው፣ ተቀይሞታል ያሉትን አስረው፣ ጠልቶታል ያሉትን አፍርሰው፣ ወዶታል ያሉትን ሾመው የልብ አውቃነታቸውን ለማሳየት እንቅልፍ ያጣሉ፡፡ በሌላ በኩል ስግብግብነታቸውን ለማስታገስ ታደጉት የተባሉትን ዜጋ ያድጉበታል፡፡ ጉቦ ሲቀበሉ፣ ቀረጥና ግብር ሲያጭበረብሩ፣ የዜጎችን ሀብትና ንብረት ሲወርሱ ህሊናቸውን አይሸነቁጣቸውም፡፡ ምክንያቱም ሰክረዋል፡፡ የሰከረ ህሊና ትልቅ ተግባሩ የሚጋልበው ሰካራም ለሚያደርገው ሁሉ ማጨብጨብ ነው፡፡

በየመንግስት መዋቅሩ የተዋቀሩ ኮሚቴዎቻችንም ሰክረዋል፡፡ እዚህ ነጥብ ላይ ተግባራዊ ምሳሌ ልጠቅስ እወዳለሁ፡፡ የዛሬ ሶስት ሳምንት በኮንትነታል ሆቴል በተዘጋጀ በሚዲያና ልማታዊ መንግስት ላይ ሊመክር በተቀመጠ ጉባኤ፣ የፋና ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ ሃላፊ/ስራ አስኪያጅ ባቀረቡት ንግግር (ጥናት)፣ በ1983 ዓ.ም ለሚዲያው ነፃነትና ዲሞክራሲያዊነት ትልቁ ማነቆ የሰለጠነ ሙያተኛ (ጋዜጠኛ) አለመኖሩ ነው ካሉ በኋላ፣ ይህ ችግር ዛሬም አልተቀረፈም አሉ፡፡ ሁሉም አድማጭ በአዘኔታ ተዋጠ፡፡ ችግራቸው ታየው፡፡ ሃያ ሶስት አመት ልማታዊም ሆነ ዲሞክራሲያዊ ጋዜጠኛ ለማስተማር በቂ አይደለም ወይ ብለን አልጠየቅንም፡፡ ምክንያቱም የሰከሩት ተናጋሪው ብቻ ሳይሆን እኛ ታዳሚዎቹም ነን፡፡ አብዛኛው የጉባኤው ታዳሚ በስልጣን ጥሞና ተስፋ፣ ጥቂቱ በምናገባኝ የሰከርረ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ያህል ለቡድን ስካር ማሳያ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ አይገኝም፡፡ ፌዴሬሽኑ በማንአለብኝነትና ተአብዮት ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ፣ ቆሞ መራመድ አቅቶታል፡፡ በዚህም የተነሳ ወደ የሰላሳ አንድ አመት ዳዴው እየተመለሰ ነው፡፡ ዋልያዎቹ ያስቆጠሩት እያንዳንዱ ጎል የአሰልጣኙና የፌዴሬሽኑ አናት ላይ ወጥቷል፡፡ በዚህም የተነሳ እጃቸውን የሚሰነዝረውን ልሳናቸው የሚናገረውን አያውቁም፡፡ አስራ አራት ሚሊዮን ብር በሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አንድ ጎል ብቻ ላገባ ቡድን፣ በአንድ ውድድር ላይ እንኳን ለሩብ ፍፃሜ ቡድኑን ላላደረሰ አሰልጣኝ፣ እውነት በስካር ህሊናው የደነዘዘበት ካልሆነ በቀር ማን የሸልማል! በቻን የአፍሪካ ዋንጫ አፍረን ያሳፈርናችሁ በፌስቡክና በሚዲያ ስታብጠለጥሉን ሞራላችን ተነክቶ ነው ይሉናል፡፡ ይህ እውን በስካር ከደነዘ ስንኩል ተጠየቅ በቀር ከየት ይመነጫል! እኛስ እውን በጠኔ፣ በምናገባኝ፣ በስልጣን፣ በሀብት የሰከርን ዜጎች ባንሆን ይህን እንቀበላለን! እውን ያልሰከረ ፌዴሬሽን፣ ያልሰከረ ባለስልጣን፣ ያልሰከረ መንግስት፣ እኛም ያልሰከርን ዜጎች ብንሆን ቡድኑ ድሮም ከሚታወቅበት ኳስ ማማሰልና አብዝቶ መቀባበል እምብዛም የጎላ ለውጥ ያላመጡትን፣ በቻን ላይ በሶስት ውድድሮች የሚያደርጉት ጠፍቷቸው እንደተቆጡት ህፃን ከወንበራቸው ሳይነሱ ሽንፈትን ያላመጡትን (የዋጡት አይመስለኝም) አሰልጣኝ በአሰልጣኝነት እንዲቀጥሉ እንፈቅድ ነበር! ግን እሳቸው ማንያህሎኝነትና እራስን ካለመመርመር የመነጨ ተአብዮት አስክሯቸዋልና በፈቃዳቸው ስራቸውን አለቀቁም፡፡ እኛም ሰክረናልና ይበቃዎታል አላልንም፡፡ ሁላችንም ሰክረናል፡፡ ሀገሬ የሰካራም ሀገር ሆናለች፡፡

ችግሩ ያኔ ከሃያ ሶስት አመት በፊት ስድስት ሆነን የሰከርን እለት፣ ፊት ለፊታችን አንዲት ያልሰከረች ኮማሪት ነበረች፡፡ በትዝብቷም ይሁን በሳቋ ስካራችንን ታጋልጥ ነበር፤ ሰሚ ባይኖርም፡፡ ዛሬ ሀገሬ ያልሰከረ ዜጋ የላትም፡፡ እንደዚያች ኮማሪት በትዝብቱም ይሁን በምፀቱ ስካራችንን አጋልጦ ወደ ልቦናችን የሚመልሰን ወገን የለም፡፡ ሁላችንም ሰክረናል፡፡ ሀገሬ የሰካራም ሀገር ሆናለች፡፡ ፈጣሪ ብሎ ስካሩ ቢያልፍ አንጎበሩ እንዴት ያደርት ይሆን!? ምስኪን ኢትዮጵያ!

ፋክት መጽሄት

Thursday, February 20, 2014

የሌላቸው ባለቤቶች (ከበድሉ ዋቅጅራ ሳላስፈቅድ የተዋስሁት)

መስፍን ወልደ-ማርያም

ጥር 2006

በድሉ ዋቅጅራ ‹የሌላቸው ባለቤቶች› የሚል ቅራኔ ውስጥ የገባው ከተጨባጭ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁኔታ ተነሥቶ ነው፤ አንዳንዴ ሁኔታዎች እያስገደዱን ቅራኔዎችን እንቀበላለን፤ አንድ ጌታ አሽከራቸውን ይጠሩና ባላገር ወደሚኖሩ እናታቸው ዘንድ ይልኩታል፤ ነገር ግን ‹ሞተው ከሆነ እንዳትነግረኝ› ብለው አስጠንቅቀውት ይሄዳል፤ ሴትዮዋ ሞተው ይደርሳል፤ ምን እንደሚያደርግ ግራ ገባው፤ ሲያንሰላስል ብዙ ቀናት ከቆየ በኋላ ጎፈሬውን ለሁለት ከፍሎ ግማሹን ይላጭና ግማሹን ብን አድርጎ ያበጥርና ጌታው ዘንድ ይቀርባል፤ አንዴ ጎፈሬውን እየነካካ፣ አንዴ የተላጨውን እየዳበሰ ጥያቄዎቻቸውን ሲመልስ፣ ጌታው ተቆጡና ‹ምንድን ነው የምታድበሰብሰው አርፈው እንደሁ በወጉ አትነግረኝም!› ብለው ሲጮሁበት ‹አዬ ጌታዬ አርስዎ መቼ በወጉ ላኩኝና!› ብሎ መለሰላቸው።

የበድሉ ‹የሌላቸው› በግማሽ እንደተላጨው ጸጉር ነው፤ ‹ባለቤቶች› ደግሞ እንደግማሽ ጎፈሬው ነው፤ የሌላቸው አላቸው፤ የአላቸው የላቸውም፤ እንደዚህ ያለውን ጉደኛ ሁኔታ እዚያው ጉደኛ ሁኔታ ውስጥ ካለው በቀር ሌላ ሰው አይገባውም፤ መብት ከግዴታ ሲገነጠል መብትም ግዴታም ባሕርያቸውን ለውጠው ሌላ ነገር ይሆናሉ፤ መብትም መሸጦ፣ ግዴታም መሸጦ ሲሆን ከራሱ በቀር ማን ለማን፣ ማን ለምን ኃላፊነት አለበት? መሬቱ ለሙስና ለምለም የሚሆነው እንዲህ እየሆነ ነው፤ ትንሽ መንደር ለትልቅ አገር መመሪያ ሲያወጣና የማንነት ምንጭ ሲሆን ‹‹ኢትዮጵያዊ ዝበሃል መንነት የለን፤›› ብሎ በአደባባይ መናገር ይቻላል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ኢትዮጵያዊ በሚባል ጋዜጣ ላይ ሀሳቡን እየጻፈ፣ ኢትዮጵያዊ የሚባል ብር እየተቀበለ (በጎን ሊሬም፣ ዶላርም ሊኖር ይችላል፤) ኢትዮጵያዊ የሚባል ምግብ (ማካሮኒም ሊሆን ይችላል) እየበላ፣ ኢትዮጵያ ከምትባል አገር የሚያገኘውን ጥቅም ሁሉ እያግበሰበሰ ‹‹ኢትዮጵያዊ ዝበሃል መንነት የለን፤›› ማለት ይችላል፤ ሀሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው፤ ግን ‹ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት የለም› ብሎ የሚናገረው ለማን ነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፤ ለኤርትራውያን ነው? ለኢትዮጵያ ወጣቶች ነው? አንዱ የክህደት ትምህርቱ የገባው ወጣት ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ማንነት አይደለም ብሎ ጻፈልኝ፤ ፊደልን ተምረው ማንበብና መጻፍ ሲጀምሩ ድንቁርናን የሚያነግሡ ሰዎች በተፈጥሮ ያገኙትን ደመ-ነፍሳቸውን እውቀት ያደርጉታል፤ ፊደሉ የእውቀትን በር መክፈቻ መሆኑ ሳይገባቸው ይቀርና ፊደሉን የእውቀት መጨረሻ ያደርጉታል።

Wednesday, February 19, 2014

Ethiopian political refugee living in London alleges he was victim of 'unprecedented example of espionage on British soil'

The National Crime Agency has been asked to investigate the alleged use of computer software to spy on an Ethiopian political refugee living in London in an unprecedented example of espionage on British soil.

The charity Privacy International has made a criminal complaint to the agency’s National Cyber Crime Unit following the detection of the surveillance software FinSpy on a computer belonging to Tadesse Kersmo, who fled to Britain from Ethiopia in 2009.

FinSpy, a “Trojan” programme which was developed and produced by the British-German company Gamma International, allows a remote user to gain full access to a targeted computer and even to turn on functions such as microphones and cameras to record the computer’s owner without their knowledge.

Mr Kersmo, a university lecturer, claimed that he had been the victim of espionage by the Ethiopian Government because of his involvement with the political opposition group Ginbot 7. “I felt that the United Kingdom was a safe and free country but I was wrong and I feel very disappointed,” he said.

Monday, February 17, 2014

ተራ ኢትዮጵያዊ መሆናችንን አንናቀው ! ግርማ ካሳ

አገሬን ለቅቄ ስደት የጀመርኩት በ1984 ነዉ። ኢሕአዴግ ስልጣን በጨበጠ በአንድ አመቱ። ከአስራ አራት አመታት በኋላ ለአንድ ወር ጉብኘት ቦሌን ረገጥኩ። እሑድ ቀን ፣ ግንብት ሰባት 1997 ነበር።

ከዚያ በፊት ብዙም የፖለቲካን ነገር አልከታተለም ነበር። ምርጫ እንደሚደረግ፣ ቅንጅት ሕብረት እየተባለ የምርጫዉ ዘምቻ እንደተጧጧፈ ያወኩት ትኬት ከቆረጥኩ በኋላ፣ ከምርጫዉ 15 ቀናት በፊት ነበር። በአጭሩ አባባል፣ በአገሬ ዉስጥ እየተደረገ ከነበረዉ ሁኔታ የተለየዉ፣ ዲስኮንቴክትድ የሆነ ነበርኩ ማለት ይቻላል።

በወቅቱ የነበረዊ አንጻራዊ ዴሞክራሲ አስደሰተኝ። ቅንጅት አዲስ አበባን ሙሉ ለሙሉ አሸነፈ። ከሌሎች ቦታዎች የሚመጡም ዉጤቶች ቅንጅቶችን የሚያስደስት ነበሩ። በዚህ ጊዜ ችግሮች መፈጠር ጀመሩ። ኮሮጆ መቀየር የመሳሰሉት። አገሪቷ ወደ ቀውስ መግባት ጀመረች።በየቀኑ ጋዜጦችን እገዛለሁ። (አዲስ ዘመንን ግን ገዝቼ አላወቅም) የምወዳት ቡና ቤት ነበረች። ካፌ ማሩ ትባላለች። ቡናዬን ይዤ ጋዜጦችን አነባለሁ። አንድ ቀን እንደለመድኩት ገዝቼ ሳገላብጥ፣ ሁሉም የአንዲት ሴት ልጅን ፎቶ፣ በትልቁ አውጥተዋል። በቆምኩበት እንባ ይፈሰኝ ጀመር።

እየተዋረዱ መገዛት እስከመቼ!?

በቅዱስ ዮሃንስ

አለምነው መኮነን የተባለ የብአዴን ወኪልና የባንዳ አስፈፃሚ የአለቆቹን የዘወትር አባባል በማስረገጥ እመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ <<ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፤ ትምክህተኝነቱን ያልተው፤ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ>> ካለ በኋላ <<የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት>> በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ደከመኝ፡ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ህዝብ ዋጋ በማሳጣት የሌሎቹ ጠላት አድርጐ በማቅረብ፡ የዘረኞች ተባባሪነቱን አስመስክሯል።  

የአማራው ህዝብ የወያኔ ዘረኞች ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ መጋት ከጀመረ ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ። ፋሽስቱ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል። ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል።

ይህ የህወሀት የጸረ አማራ ፕሮፓጋንዳ ማሽን የሚመራው በዋና ዋናዎቹ የወያኔ  ሹሞች ቢሆንም ወያኔ የአማራን ህዝብ የሚገድለዉ፤ የሚያዋርደዉና የሚያሳደድዉ አማራ ነን በሚሉ ነገር ግን የአማራን ህዝብ በጅምላ በሚሰድቡና አማራዉ ሲገደል፤ ሲታሰርና ሲፈናቀል ይበልህ በሚሉ በእነ አለምነው መኮንን አይነት ወፍ ዘራሽ ካድሬዎች ነው። አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል እንዲሉ፡ የአማራው ህዝብ ዛሬ ቀን ጣለውና፣ በጠላቶቹ እጅ ወደቀ፣ የድፍን ስድና መረን ያደገ ዋልጌ ሁሉ የስድብና የዘለፋ አፍ ማሟሻ የመሆን ዕጣ ደረሰው። አለምነው መኮነን የተባለ የብአዴን ወኪልና የባንዳ አስፈፃሚ የአለቆቹን የዘወትር አባባል በማስረገጥ እመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ <<ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፤ ትምክህተኝነቱን ያልተው፤ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ>> ካለ በኋላ <<የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት>> በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ደከመኝ፡ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ህዝብ ዋጋ በማሳጣት የሌሎቹ ጠላት አድርጐ በማቅረብ፡ የዘረኞች ተባባሪነቱን አስመስክሯል።

Saturday, February 15, 2014

ወያኔን ካላጠፋነዉ ዘረኝነቱና ዉርደቱ ይቀጥላል!!!


ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች በራሳቸዉ እጅ የጻፉት ማኒፌስቶ በግልጽ እንደሚያሳየን እነዚህ ዘረኞች ጫካ ገብተዉ የትጥቅ ትግል እንዲጀምሩ ያነሳሳቸዉ በአማራ ህዝብ ላይ ያላቸዉ ጥላቻና መሰረተ ቢስ ቂም በቀል ነዉ። ይህ ጥላቻቸዉ ደግሞ አማራዉን በመግደልና ግዛቱን ሲያሻቸዉ ከራሳቸዉ ክልል ጋር በመቀላቀል አለዚያም ለጎረቤት አገሮች በመሸለም ብቻ ሊቆም ወይም ሊገታ አልቻለም። እነሆ የአማራው ህዝብ የወያኔ ዘረኞች ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ መጋት ከጀመረ ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ። ፋሽስቱ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል። ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል።


ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማዳከም፣ ለዘመናት ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያገለግለኛል ብሎ ዘመቻ ከከፈተባቸው ብሄረሰቦች አንዱና ዋንኛው የሆነው የአማራ ህዝብ በራሱ ማንነት እንዲያፍርና ብሄራዊ ኩራቱ እንዲሟሽሽ ላለፉት 23 አመታት በግብር ከፋዩ ህዝባችን ገንዘብ በሚተዳደሩ የመንግሥት መገናኛዎች ሳይቀር ከፍተኛ የስነ ልቦና ዘመቻ ተካሂዶበታል። በአማራ ሥም አማራውን የወያኔ አገር የማፍረስ አጀንዳ አስፈጻሚ ለማድረግ የተሾሙበት ተላላኪዎች በህወሃት አለቆቻቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም በተለያዩ አጋጣሚዎች አማራውን የሚያዋርድና የሚዘልፍ አስተያየት በአደባባይ ሲሰጡ ሰምተናል አይተናል። ይህ ተግባራቸው ለአማራ ህዝብ ቅንጣት ታህል ክብርና ፍቅር ያልነበረው ዘረኛው አለቃቸው መለስ ዜናዊ ከዚህች አለም በሞት ከተሰናበተ ቦኋላም ተጠናክሮ ቀጥሎአል።

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በኢትዮጵያ!


በቅዱስ ዬሃንስ

የወያኔ መንግስት በትልቁ ከሚታማባቸው ነገሮች አንዱ ደካማ የሰብዓዊ መብት አያያዙ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ የተስማማባቸውን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ለማክበር የተሰማማች ብትሆንም በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ የከፋ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ካለባቸው ሀገራት አንዷ ነች፡፡ ለዚህም ሂውማን ራይትስዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናልን የመሳሰሉ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሪፖርት ባወጡ ቁጥር በመልስ ምት የሚሰነብተውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን መመልከት በቂ ነው፡፡ ለነገሩ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማወቅ የነዚህን ተቋማት ሪፖርት መጠበቅ አያስፈልገንም፡ ፡ እኛው ራሳችን የነገሩ አካል ነንና፡፡ ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን የተንሻፈፉ የህግ አንቀፆች እየተጠቀሱብን ወህኒ እንወርዳለን፡፡ ለዚህ ደግሞ እስር ቤቶችን ሁሌም ቢሆን ከፖለቲካ እስረኞች ነፃ ሆነው አለማወቃቸው አንዱ ማሳያ ነው፡ ፡ እንደለየለት የሶሻሊስት ሀገር ዜጎችም የተዋጠ ጥሬ ሳይቀር ነገራችን ሁሉ ለቤተ-መንግስት ፍጆታ ይውላል፡፡ ዜጐች እኩልነት በሚሸረሸሩ ህጐች የተነሳ ንብረት የማፍራት መብታቸው እየተገደበ ይገኛል፡፡


በተለይ አሁን አሁን ፓርቲው ከያዘው ልማታዊ መንግስት መንገድ ጋር የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እየሰፋ መጥቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የልማታዊ መንግስት እሳቤ ከሰብዓዊ መብት በፊት ለፓርቲ መደላደልና ለኢኮኖሚ እድገት ቅድሚያ ስለሚሰጥ ነው፡፡ ፓርቲው እንደ አርአያ እየመዘዘው ያለው የምስራቁ አለም በሰብዓዊ መብት አያያዝ የተመሰገነ አይደለም፡ ፡ መቼም የኢህአዴግ የዘንድሮ ‹‹ሮልሞዴል›› ቻይናም እንደ ኢኮኖሚ እድገቷ በሰብዓዊ መብት አያያዟ ምሳሌ ልትሆን የምትችል አይደለችም፡፡

የቆሞ ቀርነት ፖለቲካ!

በመስከረም አበራ

ይህን ርዕስ ከዚህ በፊት አንስቸው ነበር፡፡ በወቅቱም “ቆሞ ቀርነት” የሚለውን ቃል አንድ ታሪካዊ ሁነት ላይ ብቻ በመመርኮዝ የፖለቲካ ትንታኔ የመስጠትን ስህተት ለማመላከት እንደሆነ ገልጨ ነበር፡፡ የቃሉ ትርጓሜ ለዚህ ፅሁፍም ተመሳሳይ እንደሆነ እየገለፅኩ ወደ ዋናው ሃሳቡ አልፋለሁ፡፡ ርዕሱን ደግሜ እንዳነሳው ያስገደደኝ አንድን ታሪካዊ ክስተትን ብቻ ተመርኩዞ፣ ያንኑም በቅጡ ሳያስተውሉ አደገኛ ማጠቃለያ የመስጠቱ ነገር እየበዛ በመምጣቱ ነው፡፡

የዘውዱ ዘመን ቆሞ ቀሮች!

በፊውዳሊዝም ፖለቲካዊ ዘይቤ የኖረው የሃገራችን ዘውዳዊ መንግስት የእድሜውን ርዝመት ያህል ሃገሪቱን ውጥንቅጥ ውስጥ ከቶ የኖረ ነው፡፡ ከዚህ ዘመን ውስጥ ደግሞ “ዘመነ መሳፍንት” ተብሎ የሚጠራው ከ 1769-1855 የቆየው ዘመን የሃገሪቱን ህልውና ፈተና ውስጥ ከቶ የነበረ የጦርነት እና የእልቂት ዘመን ነበር፡፡ የዘውዳዊ አገዛዙ ዘመን መደወሪያው ፊውዳሊዝም፣ ነገስታቱም ከቤተ-ክህነት ያልዘለለ ግንዛቤ የነበራቸው እንደመሆኑ በዘመኑ ስለጠፋው ጥፋት በዚህ ዘመን የንቃት ደረጃላይ ሆኖ መሪዎቹን ከመውቀስ ይልቅ በነበራቸው ውሱን ግንዛቤ ለሃገራቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና መስጠቱ ተሻይ ይመስለኛል፡፡ በተለይ የነገስታቱ የሃገር ፍቅር ከዙፋን አውርዶ እንደተራ ወታደር እስከመዋጋት የሚያደርስ ነበርና መወደስ አይበዛበትም፡፡

በአንፃሩ በዛሬ የንቃት ደረጃ ሲፈተሸ ጥፋት የሚባሉ በርካታ እንከኖች እንደነበሩባቸው የማይካድ ሃቅ ነው፡፡ ይህ የሚያግባባውም ትናንትን በዛሬ ሚዛን መመዘኑ ትክክል ነው ተብሎ ከታሰበ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ‘በሞተ ስርዓት ላይ ከዚህ በላይ ጊዜ ማጥፋት አይገባም’ እንዲሉ ፕሮፌሰር መስፍን ነገስታቱን እነሱ ካለፉ ከስንት አመት በኋላ ወደ ጠረጴዛ የመጣውን የሰብአዊ መብት አከባበር ፍልስፍና እያነሱ እሱን በመተላለፍ ማብጠልጠል እልፍ ማይል ወደ ኋላ ተጉዞ ቆሞ መቅረት ይመስለኛል፡፡ አሁን አሁን ብቅ የሚሉ ጦማሪያን ደግሞ እጃቸውን የሚያፍታቱት እነዚህን ነገስታት በማብጠልጠል ነው፡፡ ነገሩ በአመዛኙ ከኢህአዴግ ወደ ስልጣን መምጣት ጋር ሃገሪቱን ከወረሳት የዘረኝነት አባዜ የሚነሳ ነው፡፡ ለዚህ ማመሳከሪያው የእነዚህ ጦማሪን ትችት ፍላፃ የሚወረወረው ከነሱ ብሄር ባልሆኑ ነገስታት ላይ ሲሆን ’ከእኛወገን’ የሚሏቸውን ነገስታት ደግሞ በፊውዳላዊ ስርአት ውስጥ ዲሞክራት፣ ብፁዕ እና ነብር በጥፊ የሚገድሉ ጀግኖች ለማድረግ መፋተራቸው ነው፡፡ ነገሩ ባስ ሲል ደግሞ የእኛ ሰፈሩ ባላምባራስ እንትና ከእንትን ምንጭ ማዞሪያ መለስ የተመለመሉ ወታደሮችን ብቻ ይዘው ጣልያንን ስላርበደበዱ የተራራማውን እና ቆላማውን ምድር ህዝብ ይዘው ካሸነፉት አፄ እንትና አንሰው ምክትል ጀግና መደረግ የለባቸውም እየተባለ ቁም ነገር እንደያዘ ሰው በምሬት ክርክር ይገጠማል፡፡ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ባልተነሳበት፣ የሰው ልጅን ገበያ አውጥቶ መሸጥ ሽምብራ እንደመሸጥ ነውር በሌለው ዘመን አፄ እንትና ባሪያ እንዲሸጥ ፈቅዶ ነበርና የነፃነት አባት ሳይሆን ሃገር ከሃዲ ነው የሚል ክርክር በዚችው መፅሄት ላይ ያነበብነው “ትንታኔ” ነው:: ለሃገራቸው ክብር ሲሉ ከሃገር ዳርቻ በእግር በፈረስ ተጉዘው በጣምራ ክንዳቸው ጠላትን ድል የመቱ ወንድማማቾችን ለመነጣጠል “አንኮበራዊ” እና “አክሱማዊ” አርበኞች የሚል ስራ-ፈት ሽንሸናም እንደ ደህና ነገር እየተወሳ ይገኛል፡፡ ለአንባቢ ቁምነገር እንደሚያቀብል ሰው ብዕር አንስተው እንደ እየሩሳሌም ቆነጃጅት ‘አክሱማዊያን እልፍ ገደሉ አንኮበሮች ግን ሺ ብቻ’ እያሉ ለሰፈራቸው ሰዎች ለመዝፈንም ይሞክራቸዋል፡፡ ይህ ሲባል የተረሳው (እና ገዛኽኝ ፀጋው የተባለው ፀሃፊ በዚሁ መፅሄት በደንብ ያስቀመጠው)ጉዳይ ‘አንኮበራዊውም’ ሆነ ‘አክሱማዊው’ ገዥ ያደረገውን ያደረገው ግዛቱን አስፋፍቶ ከተገዥዎቹ የሚሰበስበውን አመታዊ ግብር መጠን ለማሳደግ እንጂ ‘ከአንኮበራዊ’ እና ‘ከአክሱማዊ’ ማን ይጀግናል ለሚለው መልስ የሚሆን ነጥብ አስመዝግበው አልፈው፣ እኛ የልጅ ልጆቻቸው ደግሞ እንድንተነትነው አልነበረም፡፡

Thursday, February 13, 2014

የመንግስት ጣልቃ ገብነት በሀይማኖት: የስብሃት ነጋ ምስክርነት


በሀይማኖት ጣልቃ ገብነት ጉዳይ በኢትዮጵያ ሙስሊም ማሕበረሰብና በኢህአዴግ መንግስት መካከል አለመግባባት መስፈኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መንግስት በሀይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱ እንዲያቆም ሲጠይቁ መንግስትም የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ማሳሰሩ ይታወሳል። (ኮሚቴዎችን በማሳሰር የህዝብን ጥያቄዎች ማዳፈን ይቻል እንደሆነ እንጂ መመለስ ግን አይቻልም)።

መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ የሚገባው በተለያዩ መንገዶች ሊሆን ይችላል። አንዱና ዋነኛው ግን የሀይማኖት መሪዎችን በመደለል የፖለቲካ መሳርያ እንዲሆኑ ማድረግና የፖለቲካ ካድሬዎች የሀይማኖት መሪዎች አድርጎ መሾም ነው።

የፖለቲካ ሹመት (ካድሬነትና አገልጋይነት) ሌላ የሀይማኖት መሪነት ሌላ። ፖለቲካና መንፈሳዊ ህይወት የተለያዩ ናቸው። የፖለቲካ ሹመት ከሆነ በገዢው ፓርቲ ሊመረጥ ይችላል። የሀይማኖት መሪ ግን በምእመናን ነው መመረጥ ያለበት። ስራውም ፖለቲካ ሳይሆን ሀይማኖታዊ ነው የሚሆነው። ሀይማኖታዊ መሪው በፖለቲካ ተፅዕኖ ስር መውደቅ የለበትም።

ተዋርዶ መገዛት ይብቃን!

የወያኔ ሹማምንትና አደርባይ ሎሌዎቻቸው አንገቱን አስደፍተው የሚገዙትንና የሚዘርፉትን ህዝብ ይበልጥ ስብእናውን አዋርደው ሊገዙት ለምን እንደሚፈልጉ የማይገባን ጥቂቶች አይደለንም። እነዚህን ግፈኞች ቀረብ ብሎ ላያቸው ግን ይህ ድርጊታቸው እንቆቅልሽ አይደለም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝብ አይሰማንም ብለው በር ዘግተው ከሚያካሂዷቸው ጉባኤዎች እያፈተለኩ የሚወጡ የቪዲዮና የድምጽ መረጃዎች የነዚህን ግፈኞች ስነ ህሊና ግልጽ አድርገው ያሳያሉ።

ከወራት በፊት የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት የሀገር ሽማግሌ ሰብስቦ የወያኔ አላማ ከእሱ ጎሳ ጋር ተባብሮ ሌላውን ብሄረሰብ የበታች አድርጎ መግዛት መሆኑን ሲናገር የሚያሳይ ቪዲዮ ተመልክተን ነበር። የክልሉን ህዝብ የሚጨፈጭፈው ለዚህ ሲባል መሆኑን ለማሳመን ነበር በሩን ዘግቶ የተናገረው።

ሰሞኑን ደግሞ አንድ የአማራ ክልል የወያኔ ሹምና ሎሌ ልከአንደ እንደሶማሌው ሹም ካድሬዎቹን ሰብስቦ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቀ፤ ለ እግራቸው ጫማ የላቸውም በሚላቸው የአማራው ተወላጅ ላይ ለሰሚ በሚሰቀጥጥ ቋንቋ ያወርደው የነበረ ስድብ የሚነግረን ተጨማሪ ነገር ተመሳሳይ የወያኔን ምንነትን ነው።

Wednesday, February 12, 2014

አንድነት እና መኢአድ ብአዴንን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ ጠሩ


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ብአዴንን በመቃወም በባህርዳር ከተማ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠሩ፡፡ ፓርቲዎቹ ነገ በ4 ሰዓት በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በጋራ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ ለተቃውሞ ሰልፉ አስፈላጊው የማሳወቅ ተግባር መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

አንድነትና መኢአድ እሁድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ መነሻ ምክንያት እንዲያስረዱ በፍኖተ ነፃነት የተጠየቁት የአንድነት ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስዩም “አማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብአዴን የጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብን ክብር የሚያዋርድና በለሌሎች ብሔረሰቦች በክፉ እንዲታይ የሚያደርግ የጥላቻ ንግግር በማድረጋቸውና ብአዴንም እንደ ፓርቲ ማስተባበያም ሆነ የማስተካከያ እርምጃ ባለመውሰዱ የግለሰቡን አቋም እንደሚጋራ ያመለክታል” ብለዋል፡፡

Tuesday, February 11, 2014

ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ!

በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት 

(ከኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ የተወሰደ)

‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡

ይሁንና በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1906 ከታተመው የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102 ላይ ነው፡፡ የዛሬ 108 ዓመት አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!... ይህ ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤ ለምን? ቢሉ ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ‹ጠበቅ ያለ እርምጃ፣ የማያዳግም እርምጃ፣ የማስወገድ እርምጃ፣…› ወዘተ የሞሉ ከሕግ መርሕዎች ሳይሆን ከጥላቻ ፖለቲካ የሚመነጩ ፀያፍ አነጋገሮችን በሕዝብ የመገናኛ ዘዴዎች ሲተላለፉ እየሰማን እየታዘብን ነው፡፡ ቃል በቃል ‹ቀይ ሽብር ይፋፋም› ብሎ ማወጅ የቀራቸው የሕግም የግብረገብም ሚዛን ያልወጣላቸው ቀረርቶች በተለይ በእስር ቤት የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን እየሰበሰቡን ይገኛሉ፡፡

በኢ.ቴ.ቪ. የአብዮታዊ እርምጃ ፕሮግራሞች በቀረቡ ማግስት አሁን በዝርዝር ብለው የብዙ ቤተሰቦችን ስሜት ሊያሸማቅቁ የሚችሉ ሰቆቃና እንግልቶች በአስደማሚ ስልት ተቀናብረው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ እስኪ የተወሰኑትን እንይ፡፡ ማንኛውም ታሳሪ ቤተሰብ በቅርብ ሊጎበኘው በሚችለው እስር ቤት ይታሰር የሚለው ሕግ የተሻረው በእኛ ላይ ነው፡፡ ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት› ማለት ናት፡፡ ቤተሰብ ያን ያህል የበርሃ ጉዞ አቋርጦ የእኛዋ ሳይቤሪያ ሲደርስ በአድካሚና ግብረ-ገብ በጎደለው ፍተሻ መከራውን ማየቱ አንሶ ጆሮ ግንዱ ላይ በቆሙ የቤተሰብ አገናኞች ቤተሰባዊ ገመናውን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ሕፃናት ልጆች ወላጆቻቸው አንድ ላይ ሆነው ናፍቆታቸውን መወጣት አይችሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖሊሶቹ ሲዘናጉልን ልጆቻችንን አቅፈን እንስማለን፡፡ ይህ ከሆነ ቁጣና ዘለፋው ምንም አይደለም፡፡ ግን በሁኔታው ሕፃናቱ ክፉኛ ይበረግጋሉ፣ የእኛ ስጋት ይጋባባቸዋል፤ በዚህም መንፈሳቸው እርብሽብሽ ብሎ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፡፡

Monday, February 10, 2014

የአቶ አሥራት ጣሴ እስር የኢህአዴግ የጉልበት ፖለቲካ ማሳያ ነው! አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ የተሠጠ መግለጫ

የካቲት 1 ቀን 2006 ዓ.ም

ፓርቲያችን አንድነት በተደጋጋሚ ከገዥው ፓርቲ ህግን ከለላ በማድረግ እና የመንግስትን ሥልጣን በመጠቀም የሚደርስበትን ከፍተኛ አፈና ተቋቁሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን የበላይነት ለማረጋገጥ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠሉ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡

በተለይም ፓርቲያችን በመላው የሀገራችን ክፍል የዘረጋውን መዋቅር በህዝባዊ አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ በማሸጋገር በአምስት ዓመት ስትራተጂክ ዕቅዱ መሰረት እያከናወነ ያለው ህዝባዊ ንቅናቄ እና በተሳካ ሁኔታ ጠቅላላ ጉባዔ አካሂዶ ዴሞክራሲያዊ የአመራር ሽግግር ማድረጉ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ተስፋ ያሳደረ ቢሆንም ገዥውን ፓርቲ በአንጻሩ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተው ይስተዋላል፡፡

ኢህአዴግ ቀደም ሲል የፓርቲያችንን እንቅስቃሴ በመከታተል ከከፍተኛ አመራሮች መካከል አቶ አንዱዓለም አራጌ፤ ናትናዔል መኮንን እና ሌሎች በርካታ አባላትን የተለያየ ምክንያት ፈጥሮ እየወነጀለ ለእስር መዳረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህም በድንገት የተደረገ ሳይሆን የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር እና የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ በግልጽ በፓርላማ ተገኝተው ‹‹አንድነት ፓርቲ እግር ሲያወጣ እግሩን እንቆርጣለን›› ባሉት መሰረት የፈጸሙት ነበር፡፡

ኢትዮጵያዊነት - ”የለህም ይሉኛል፤ እውነት የለሁም ወይ?”

በመስፍን ነጋሽ

ከማንነት ጋራ የተያያዙ ጥያቄዎች፣ ሙግቶች፣ በተቃራኒውም አስቀያሚ ሐሳብ አልባ ስድድቦች ሰሞኑን በርከትከት ብለዋል። ጥያቄዎቹና ሙግቶቹ መኖራቸውን አጥብቄ እደግፈዋለሁ። በእኔ እይታ አብዛኞቹ ምልልሶች ወይም ሙግቶች በመሠረቱ አዲስ ጭብጥም ሆነ መከራከሪያ አላቀረቡም። ቢሆንም የነበረውንም ቢሆን በአግባቡ በተደጋጋሚ እያነሱ ሐሳብ መለዋወጡ ጠቃሚ ነው፤ ሙከራው ቢያንስ እርስ በርስ መተዋወቅን ይጨምራል፤ አልፎም አዲስ ሐሳቦችን ለማፍለቅ እድል ይሰጣል።

የማነ ናግሽ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት የለም፤ ያለው በብሔረሰብ ላይ የተመሰረተ ማንነት ብቻ ነው የሚለውን ሐሳብ በትግሪኛ ጽፎት ተመልክቼ ነበር። ኃላም ራሱ ወደ አማርኛ እንደመለሰው ይህን ጽሑፍ ወደማጠናቀቁ ስቃረብ ተመልክቻለሁ። በመሠረቱ ሐሳቡ አዲስ አይደለም። በየማነ አስተያየት መነሻነት ሌሎችም አመለካከታቸውን አካፍለዋል፤ ጥቂቶቹን በሚገባ አንብቤያለሁ። በሒደቱ የታየው ጉዳዩን ከመመርመር ይልቅ ተናጋሪውን የማጥቃት ስልት ጠቃሚ ስላልሆነ ወደዚያ አንመለሰም። በሐሳቡ ላይ ግን አስተያየቴን ላካፍል።

1.    ስለማንነት እንደመነሻ

ሁልጊዜም ከጥንቱና ከስሩ መጀመር ጠቃሚ ቢሆንም ጽሑፌን ወደ መጽሐፍ ምእራፍነት እንዳይቀይረው በመስጋት፣ ከዚያ በላይ ደግሞ አንባቢዎቼ ስለማንነት እና ስለፖለቲካው መሠረታዊ ጉዳዮች ያውቃሉ ከሚል እምነት ስለማንነት ወደመዘርዘር አልገባም። በምትኩ ለክርክሬ የሚሆኑኝን መነሻዎች ብቻ እጠቅሳለሁ። አምስት ጭብጦች ላስይዝ፤

1.1. አንድ ሰው ብዙ አይነት ማንነቶች ሊኖሩት ይችላሉ፤ ይኖሩታልም። አንድ ማንነት በጉልህ የሚታየው ከሌላው ጋራ ሲነጻጸር እንደመሆኑ መጠን፣ አንድ ሰው ማንነቱን የሚገልጽበት መንገድ እንደሁኔታው ይለያያል። ጥያቄው ሃይማኖትን ሲከተል፣ ሃይማኖታዊ ማንነቱን ያስቀድማል እንደማለት። እዚህ የምናነሰው ግን ቋንቋን ጨምሮ ከተመሳሳይ ባህል፣ ታሪክ እና ስነልቦና  ጋራ ስለተቆራኘው ማንነት ነው። የማንነት ፖለቲካ በአገራችን በዋናነት የሚወከለውም በዚሁ ነው። ለውይይታችን እንዲረዳ በብሔረሰባዊ እና በአገራዊ ማንነት ላይ ብቻ እናተኩር።

1.2.ማንነት (ብሔረሰባዊም ይሁን አገራዊ) ማኅበረሰብ ሠራሽ ነው፤ ተፈጥሯዊ አይደለም። ማንነት ከቤተሰብ፣ ከማኅበረሰብና ከትምህርት ቤት የምንማረው ነው። ስለዚህም ባለበት አይረጋም፤ መጠነኑና ፍጥነቱ ቢለያየም ይለወጣል።

መታወቂያዬ ላይ “ኢትዮጵያዊ" ተብሎ እንዲጻፍ እፈልጋለሁ

በበፍቃዱ ዘ ሃይሌ

ራስን "ኢትዮጵያዊ" ብሎ መጥራት ነውር እንዲመስል ጠንክረው የሚሠሩ አሉ። አልተሳካላቸውም ብዬ አልዋሽም። ምክንያታቸው እስከዛሬ የነበረው ኢትዮጵያዊነት አማራ ለበስ ነው፤ የዘውግ ብሔርተኝነት አንጂ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት (ማንነት) ብሎ ነገር የለም የሚለው ነው። መነሻ ነጥቡ እውነት ላይ ቆሞ፣ መድረሻው ግን ተራ ድምዳሜ ነው። በዘመን ጥፋት ዘንድሮን መቅጣት! እርግጥ ብዙኃን ኢትዮጵያውያን ዘውጋቸውን የሚያስቀድሙ ብሔረተኞች ሊሆኑ ይችላሉ። እኔንና መሰሎቼን ግን እነሱ ሸንጎ በሉት ጨፌ ውስጥ አስገድዶ የመክተት ወንጀል ነው። የራስን ማንነት በዘውግ ብሔር መግለጽ መብትም ምርጫም የሆነውን ያክል በኢትዮጵያዊነት መግለጽም ነውር ሊደረግ አይገባውም።

እኔን እንደ ምሳሌ

እኔ ባጋጣሚ ከተውጣጡ ብሔሮች ነው የተወለድኩት። ያደግኩትም ከዚያ በበለጠ አካባቢ በመጡ ቤተሰቦች መሐል ነው። የአብሮ አደግ ጎረቤቶቼ ቤተሰቦች ሙስሊም ጉራጌዎች፣ ወሎዬ ሙስሊሞች፣ ክርስቲያን የወለጋ ኦሮሞዎች፣ ትግሬዎች… ናቸው። ልጅ እያለን ማን "ምን" እንደሆነ ትዝ ብሎን አያውቅም። ስናድግ ግን ስለዘውግ ማንነቶቻችን እንድንማር ብቻ ሳይሆን አንዱን እንድንመርጥ ተገደድን። (መማሩን ወደን መገደዱን ግን ከመጥላት ሌላ አማራጭ የለንም።)

ሁሉንም በቅጡ አልችላቸውም እንጂ የአማርኛም፣ ኦሮምኛም፣ ሶማልኛም፣ ትግርኛም፣ ጉራግኛም… ዘፈኖች ስሰማ ባለሁበት በስሜት እወዘወዛለሁ፤ በፍቅር የምበላቸው ምግቦች (ኪሴ ሁሌም አይፈቅድልኝም እንጂ) ክትፎ፣ ጨጨብሳ፣ (እና በተውሶ ፒዛ እና በርገር ሳይቀሩ) ናቸው። አክሱም፣ ላሊበላ፣ ጅማ፣ ጎንደር፣ ሐረርን የጎበኘሁት እና ሌሎችንም ልጎበኝ ቀናት የምቆጥረው የራሴ የሚል ውስጣዊ ስሜት ስላለኝ ነው። ለጉዞ ስወጣ "የእነርሱን ልጎብኝ" አልልም፤ "የአገሬን ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች ልጎብኝ" ብዬ ነው። ከኢትዮጵያ መውጣት የማልፈልገው እንደኢትዮጵያ የሚመጥነኝ እና የምመጥነው (fit የማደርግበት) ስፍራ እንደሌለኝ ስለማምን ነው። ልዩነታችን ጌጤ ነው። እኔ የሁሉም፣ ሁሉም የኔ ናቸው ብዬ ከልቤ አምናለሁ።

ነገር ግን ለፖለቲካ ግብአት ሲባል ኢትዮጵያዊ ማንነት ብሎ ነገር የለም አንዱን ማንነት ምረጥ ስባል ያመኛል። እንዳጋጣሚ በቤተሰቦቼ ካገኘሁት የዘውግ ማንነቶች ውስጥ የቱን ነው የምመርጠው? ካሳደጉኝ ጎረቤቶቼ የወረስኩትን ማንነትስ ለምን እቀማለሁ? አማራው ማንነቴስ? ኦሮሞው ማንነቴስ? ጉራጌው፣ ትግሬው፣… ማንነቴስ? ከድምር እኔነቴ አንዱን ብቻ መርጬ እኔ እንትን ነኝ አልልም፤ ነጠላ ማንነቶቼን በተናጠል አልወዳቸውም። ከድምሩ አንዱ ሲጎድል ያመኛል። ድምሩ ማንነቴ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ነው።

ኢትዮጵያዊነት እንደገና ይጤን

በታሪክ ሒደት ተጠቃሚ የነበሩ የዘውግ ማንነቶች አሉ። በተለይ አማርኛ ተናጋሪዎች (አማራዎች) ግምባር ቀደሞቹ ናቸው። ይህን መነሻ ይዘው ኢትዮጵያዊነትን ከአማራነት ጋር ቀላቅለው የሚደመድሙ ግን የራሳቸውን ትርጉም ይገምግሙ። የኔ ኢትዮጵያዊነት ግን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ካርታ የታቀፉ ማንነቶችን ሁሉ ያቀፈ፣ የሚያስተናግድ እና የሚያከብር ኢትዮጵያዊነት ነው።

ይህ ማለት ግን፣ አንድ ሰው አንድ ቋንቋ ብቻ ተናጋሪ በመሆኑ፣ የሚያውቀው ባሕልም የዚያን ዘውግ ብሔር ብቻ መሆኑ ኢትዮጵያዊ አያደርገውም ማለት አይደለም። ሙሉ ኢትዮጵያዊ ነው። ኢትዮጵያዊነት የሁሉም ነው። ነገር ግን ራሱን በዚያ የዘውግ ብሔር ማንነት ለመግለፅ ከፈለገ መብቱ ነው። የዘውጉ ብሔር ኢትዮጵያዊነት በሕግም (እንበል ከየትኛውም የአፍሪካ አገራት በረዘመ) የታሪክ ዕድሜም የፀደቀ ነው። ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒ ላንዱ የዘውግ ብሔር የተለየ ውስጠኝነት (belonging) የማይሰማው ሰውም ኢትዮጵያዊ ማንነቱን መነፈግ የለበትም።

ባለኝ መረጃ፣ መታወቂያ ላይ ብሔር የሚጻፈው አዲስ አበባ ብቻ ነው። እንዳጋጣሚ ደግሞ ከዘውግ ብሔርተኝነት ይልቅ ኢትዮጵያዊነትን የሚመርጠው የአዲስ አበባ እና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪ የሆነው ሕዝብ ነው። አንድ ሰው ቀበሌ ሄዶ "እኔ ኦሮሞም፣ አማራም፣ ሶማሌም… አይደለሁ፤ ብሔር የሚለው ላይ ኢትዮጵያዊ ተብሎ ይጻፍልኝ" ብሎ ቢሟገት ፖለቲካዊ ወንጀል እንደሠራ ተቆጥሮ ስሙ በጥቁር መዝገብ ይሰፍራል። መታወቂያውን ሊከለከል ወይም ቤተሰብ ካለው የአንዱን በውርስ ተለጥፎ በግድ ሊሰጠው ይችላል። ይህ ጭቆና ነው።

ብዙዎች "ኢትዮጵያዊነት" በሚሉ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሁሉ የሚያቀርቡት በፌዴራሊዝሙ እንደተሰነዘረ ጥቃት አስመስለው ነው። እንደዚያ የምር ማመናቸውን ግን እጠራጠራለሁ። እኔ ፌዴራሊዝሙ ላይ ከጥቃቅን ማስተካከያዎች በቀር ችግር የለብኝም። በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር አስፈላጊ ነው ከሚሉትም ወገን ነኝ። ይህ ሁሉ "ኢትዮጵያዊነት" እንዲያብብ እንጂ አንዲጠወልግ አያደርገውም። ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠወልገው የዘውግ ብሔረተኞች የከረረ ጥላቻ እና የተዛባ፣ ያልታረመ የኢትዮጵያዊነት ፍቺ ነው።

ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ የየትኛውም የዘውግ ብሔር ሙሉ አድርጎ አይገልጸኝም። ስለዚህ መታወቂያዬ ላይ "ኢትዮጵያዊ" ተብሎ ይጻፍልኝ።

ለኢህአዲግ አንመቸው!

በዮናታን ተስፋየ

አንዳንዴ ለምን ለኢህአዲግ የምንመች ሁነን እንደምንቀርብ አይገባኝም . . . እንትና ተሳደበ . . . እንትና እንዲህ አለ . . . ያተባለ እዲህ ተባለ . . . ዘራፍ አካኪዬዋ . . . ለምን ስቦ በሚሰጠን ካርድ እንደምንጫወት አይገባኝም??! ለምን ንቅናቄያችንን አጥበን እንድንቀሳቀስ መጫወቻ ሲጥልልን እንደህፃናት ተሻምተን አንደምንቦርቅ ግራ ነው . . .

እዚህ ሀገር ላይ እኮ ያልተሰደበ የለም . . . ያልተዋረደ የለም . . . ሀገራችን እኮ ከረከሰች ከራረመች . . . በተለይ አማራ ተብሎ የተፈረጀው 22 ዓመት ሙሉ እንዲሸማቀቅ አንገቱን እንዲደፋ ያልተባለው የለም . . . ሌላውም እንደዛው ደቡቡ በሉት ኦሮሞው በሉት ሌላ ሌላውም ቀና ብሎ እንዳይሄድ ለማድረግ ያልተባለው ነገር የለም . . . ባጠቃላይ ህወሓት ኢትዮጵያን ለማጥፋት የኢትዮጵያዊነት ኩራት በሆኑ መልካም ትምክህቶቻችን ላይ የዘመተው እኮ ገና ከጫካ ሳይወጣ ነው! . . . ህወሓት የዚህችን ሀገር ህዝብ አሸማቆ ክብሩን አሳጥቶ ተመቻምቾ መግዛት እንደሚፈልግ እኮ ገና በእንጭጭነቱ የተለማመደው ነገር ነው!!! ታዲያ አሁን ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ . . .?!

ሀገር ፈርሷል . . . አንድነት ሳስቷል . . . ህዝብ ተሰዷል . . . ህዝብ ተገድሏል . . . ህወሓት የሀገር ጭራ አድርጎናል . . . ኢትዮጵያችንን ከክብሯ አሳንሶ አዋርዶናል ዓለም ንቆናል እድሜ ለህወሓት . . . አዲስ ነገር የለም!

Sunday, February 9, 2014

ግንቦት 7 በአለም ዙሪያ ከሚገኙ አባላቱ ጋር መከረ

ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በተዘጋጀ የድርጅቱ የስራ እቅድ ላይ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ዓባላቶቹ ጋር አመርቂ ውይይት አካሄደ። ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የተደረጉትን እነዚህን አሳታፊ ውይይቶች የንቅናቄው ከፍተኛ አመራሮች እንደመሯቸውም ተያይዞ ተጠቅሷል።

በሁሉም ቦታ ፍጹም አሳታፊ የነበረውንና ሰአታትን የወሰደውን ይህን ውይይት የመሩት እነኝህ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ከድርጅቱ ምስረታ እስካሁን ድረስ ያለውን የድርጅቱን ጉዞ ባጭሩ ማብራራታቸውን የጠቀሰው ዘጋቢያችን ለቀጣይ ሁለት አመታት ምን መደረግ አለበት የሚለውን የስራ እቅድ ለተሳታፊዎች በማቅረብ ከፍተኛ ውይይት ከተደረገበት በሗላ በሁሉም ቦታ በአባላት ሙሉ ድምጽ ተቀባይነት አግኝቶ መጽደቁን ዘጋቢያችን ጨምሮ ገልጿል።

በስብሰባው ወቅት ለፍትህ፡ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ የሚደረገው ጉዞ ከታሰበው እቅድ በላይ በፍጥነት እየተጓዘ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህም በአባላቱ ከፍተኛ ቁርጠኝነት የተገኘ መሆኑ በየውይይቱ በአጽንኦት ተገልጿል። እኛ ከተባበርን የምንፈልገውን ከማድረግ የሚያግደን ሃይል የለም፣ የወገኖቻችን ስቃይ የሚያበቃበት የድሉ ምዕራፍ ላይም እንገኛለን ስለሆነም ሁላችንም በከፍተኛ የትግል መንፈስ ለመጨረሻው የድል ጉዞ በከፍተኛ ወኔ እንነሳ በሚል የትግል ጥሪም ተላልፏል።

በየከተሞች ከነበሩ የውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን አባላቱ በአዲስ የስራ መንፈስና ወኔ ለእቅዱ ስኬት እንደሚሰሩ መናገራቸውን የጠቆመው ዘጋቢአችን በአካል በስልክና በመሳሰሉት የመገናኛ መንገዶች ያነጋገራቸው በተለያዩ ከተሞች ውይይቱን የተሳተፉ አንዳንድ የድርጅቱ አባላት በተለይም በቀረበው የሁለት አመቱ የስራ እቅድ ደስተኞች በመሆናቸው ለስኬቱም ከምን ግዜውም በላይ እንደሚሰሩና ትግሉ ለሚጠይቀው ሁሉ መስዋእትነትን ለመክፈል ራሳቸውን ማዘጋጀታቸውን ዘጋቢያችን ጨምሮ ገልጿል።

ምንጭ፡ http://www.ginbot7.org/

የመሬት ቅርምት በአስቸኳይ ይገታ!!!

“የግብርና ሚኒስትር” በሚል “የሆድ ሲያውቅ፤ ዶሮ ማታ” ስያሜ የወያኔ የመሬት ሽያጭ ጉዳይ አስፈፃሚው የሆነው የሥርዓቱ ቀንደኛ አገልጋይ “መሬት መቀራመት ኢትዮጵያን ጭራሽ አይመለከታትም” ብሎ ሲናገር የሰማነው እና ያነበብነው በከፍተኛ ትዝብት ነው።

ለመሆኑ የመሬት ቅርምት ከኢትዮጵያ በላይ ማንን ሊመለከት ነው? ሱዳንን፣ ኤርትራን፣ ሳውዲን፣ ቻይናን፣ ህንድን ወይስ አሜሪካን? ከራሱ ከወያኔ ሹማምንት የተራረፈው መሬት ለአረብ አገራትና ለእስያ ቱጃሮች በነፃ የሚታደለው ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለምን? ባዕዳን የሚረከቡት መሬት ስፋት በሄክታር መለካት ሲሰለቻቸው “ቤልጂየምን የሚያክል” እያሉ በስጦታ ያገኙትን መሬት በአገር ስፋት የሚለኩት ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለምን? የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያን ካልተመለከተ ከቶ ማንን ሊመለከት ነው?

ወያኔ ለም መሬት ለራሱ ማግበስበሱ ሳያንስ “ልማታዊ ባለሀብቶች” እያለ ለሚያሞካሻቸው ለቅርብም ለሩቅም አገራት ቱጃሮች ሰጥቶ ባለሀገሩን አርሶ አደር ሜዳ ላይ በተነ። መጤው ቱጃር ባለመሬት ሆኖ ባለሀገሩ ለስደት አሊያም ለቀን ሠራተኝነት ተዳረገ። ይህ ግፍ የሚፈጥረው ስቃይ የማይበቃ ይመስል “በእቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ መሬት ሻጩ “የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት የሆኑ ነፃ መሬቶችን ብቻ ነው ለሰፋፊ የግብርና ኢንቨስትመንት የምንሰጠው። ማንም ከቀዬው አልተፈናቀለም” እያለ ይዘባበትብናል። “የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት” የሚባለው መሬት የወያኔ የግል ሀብት ከሆነ ሃያ ሶስት ዓመታት መቆጠራቸው እኛ ብቻ ሳንሆን እሱም ያውቀዋል።

Friday, February 7, 2014

ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ – ግርማ ካሳ

ከበደ ካሳ የሚባሉ አፍቃሪ ኢሕአዴግ ግለሰብ  “አንዳንድ ሰዎች «ብሄር ..?» ተብለው ሲጠየቁ  «ኢትዮጵያዊ!!!…»  እያሉ የሚመልሱት፣ የራሳቸዉን ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አድርገው ያስቀመጡና በራሳቸው ማንነት የሌሎቹን ለመጨፍለቅ የሚያልሙ – የቅዠት ታንኳ ቀዛፊዎች ናቸው…. ተዛብታችሁ ሌላንም ለማዛባት ለምትፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ብሄር አይደልም። ኢትዮጵያ ሃገር እንጂ የአንድ ሕብረተሰብ ክፍል መለያ አይደለም።” የሚል አባባል ፌስቡክ ላይ ለጥፈው አነበብኩ።

በአንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ  5 ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ሕገ መንግስቱ እንዲህ ይላል ፡

“በዚህ ሕገ መንግስት ዉስጥ «ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸዉን ባህርይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነዉ። ሰፋ ያላ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልዉና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛዉ በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው።

Thursday, February 6, 2014

ያለቦታው እና ጊዜው የሚንቋረር ጩኸት ♦ውህደት♦

  By: Yonatan Tesfaye

ለምንድነው የምንዋሃደው! እንዴትስ ነው የምንዋሃደው! ከማን ጋር ነው የምንዋሃደው! ትግሉስ ገብቶናል!

የመጀመሪያው ስህተት አብዛኛዎቹ የእንዋሃድ ጥያቄ አንሺዎች ችግር መዋሃዳቸው ጉልበት እንደሚሰጣቸው እንጂ ለምን አላማ ጉልበት እደሚያስፈልጋቸው አጥርተው አያውቁትም፡፡ ልክ ከዚህ በፊት እንደነበረው ተዋህዶ ኢህአዲግን በባሌም በቦሌም ማስወገድ እንጂ እንዴት እና በምን መልኩ መውረድ እንዳለበት የሚያስቀምጡት አንዳችም የጠራ መንገድ የላቸውም! ምርጫውን እያሰቡ ነው የምትሉ ከሆነ እናንተም ተሞኝታችኋል ማለት ነው! ሰላማዊ ትግል የሚባለው ገና ያልተገለፀላቸው ብዙዎች አሉ ህዝቡን ጭምር ማወናበድ ላይ ናቸው! አሁን ባለንበት ሰዓት ኢህአዲግ በፍትሃዊ ምርጫ ስልጣን ሊለቅ የሚችልበት የሞራል ዝግጅትም ሆነ ፍላገት የለውም፡፡ በዚህ ደረጃ ደግሞ ምርጫ ከኢህአዲግ ጋር መሰለፍ አጨብጫቢ ሆኖ ከማለፍ የዘለለ የሚፈይደው አንዳች የለም! ውህደት ተፈጥሮ እና ተቀቃዋሚዎች ሀይላቸው ባንድ ሆኖ ምርጫ አካሂደው ስልጣኑን መረከብ የሚችሉበት አቋም ቢኖራቸው እኳን ላለመገልበጡና ለፍትሃዊነቱ ደጀን የሚቆም የሰው ሀይል ከሌለ እና በተለይ በስነ ልቦና ረገድ ጠንካራ የሰላማዊ ትግል አቀላጣፊዎች ካልፈሩ አደጋው ይብስ ይከፋል! ተስፋ ሊያስቆርጥም ይችላል!

ሌላው እንዴት መዋሃድ እንደሚገባ ብዙዎቹ ምሁራኑ ጭምር በደፈናው የሚያልፉትና ማይደፍሩት ጉዳይ ነው፡፡ እንቁላል ቀስ በቀስ በእግሩ ይሄዳል እንደሚባለው አንድ ሆኖ ለመስራት እኮ መጀመሪያ አንድ ሊያደርግ የሚችል አቋም ላይ መድረስ የግድ ይላል! ያን ለማድረግ ደግሞ ነገሮች ደረጃ በደረጃ መጓዝ አለባቸው፡፡ መረዳዳት . . .መተጋገዝ . . .አብሮ መስራት . . .የጋራ መድረኮችና ውይይቶች ማዘጋጀት . . .በአባላት ደረጃ መቀራረብ መፍጠር ሌላም ሌላም . . .ከዚህ አንፃር አሁን ባለው ነባራዊ እዉነታ እንኳን ለመዋሃድ አብሮ ለመስራት እንኳን ረጅም ርቀት መሄድ የግድ ነው፡፡ ድልድይ ሳይሰሩ ወንዝ መሻገር አይቻልም! ደራሽ የመጣ ለት አጥረግርጎት ይሄዳልና! እናም ይህን ከግምት የማያስገቡ የተዋሃዱ እና የእንዋሃድ አባዜ የተጠናወታቸው ሰዎች ባጠቃላይ ካየነው ብስለት የጎደለው እና አርቆ ማየት የማያስችል አስተያየቶቻቸውን ደግመው ቢገመግሙ መልካም ነው፡፡

ስልክ ጠላፊው ሰላይ “ጋዜጠኛ”

በማህሌት ነጋ (ሲያትል)

ከሁሉ የእኔን ቀልብ የሳበው የቀጂው ማንነት ነበር። ለማጣራት ያደረኩት ጥረት ብዙም ግዜ አልፈጀብኝም። አበበ ገላው በዚሁ “ሊክድ” በተባለው ቅጂ “እኔ ከሞትኩም እንደ ሃየሎም መጠጥ ቤት በከንቱ መሞት አልፈልግም። መሞት የምፈልገው ለአላማ ነው ይላል።” በዚህ ግዜ አንድ ሳቅ ይሰማል። የኢያጎ ሳቅ። ዳዊት ከበደ ስለመሆኑ ብዙም አልተጠራጠርኩም።

ሰሞኑን አንድ ሚስኪን ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ከአንድ የከሰረ ፖለቲካኛ ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርግ በቪዲዮ ለቆ ስለነበር ለሶስት ደቂቃ ያህል ተምልክቼ ጭንቅላቴን በሃዘን እየነቀነኩ ዘጋሁት። እኔን ጨምሮ በርካቶች ድረ ገጾችን የምናስሰው መረጃ ፍለጋ እንጂ የከሰሩ ግለሰቦችን ደረቅ ወግ ለማዳመጥ እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው። በአንድ ወቅት ያዙን ልቀቁን ይሉ የነበሩት ሁለት ግለሰቦች የዛሬን አያድርገውና ኢትዮጵያዊያን እንደ ማንዴላ የነጻነት ታጋዮች አድርገው ያከብሯቸው ስለነበር ድምጻቸው የጎላ በራስ መተማመናቸው ከውስጣቸው ሞልቶ በአፋቸው ይገነፍል ነበር። ዛሬ ግን ድምጽ አጥሯቸው ቀልብ እርቋቸው ሲንሾካሾኩ ያየ ሁሉ እንደ እኔ ከንፈር መጦ የሁለቱን ምስኪኖች ወግ በግዜ ዘግቶ ወደ ስራው እንደሚመለስ ብዙም አያጠራጥርም።

“ምስኪኖች እነማን ናቸው?” እንደማትሉኝ እርግጠኛ ነኝ:: የአውራምባው ዳዊት ከበደና የኢዴአፓው ልደቱ አያሌው ጉዳይ መቼም አንገት ያስደፋል። ሁለቱም ጠላታቸው ወያኔ እንዳልሆነ እነርሱ እንደሌሎች “ጽንፈኛ” እንዳልሆኑ ሌሎችን ከሰው እራሰቸውን ከፍ ለማድረግ ሲጥሩ ላስተዋለ ጠበል የሚወስዳቸው ያጡ በሽተኞች መሆናቸውን ድርጊታቸው ይመሰክራል። ዲያስፖራውና የግል ጋዜጦች በተለይ የጋራ ጠላቶቻቸው ይመስላሉ። እንደው ለመንደርደሪያ እንጂ የዚህ ጹሁፍ አላማ የሁለቱ ምስኪኖች ወግ ስላልሆነ ወደ ቁም ነገሩ ልመለስ::

‘‘ኢትዮጵያውያን እንዲራቡ ያደረገው የኢህአዴግ የፖሲሊ ችግር ነው’’

አቶ ግርማ ሰይፉ

በኢትዮጵያ ተከታታይ የምግብ እጥረት እንዲፈጠርና ዜጎችም እንዲራቡ ያደረገው የኢህአዴግ የተሳሳተ የፖሲሊ መሆኑን አቶ ግርማ ሰይፉ ገለፁ፡፡

የተለያዩ አለም አቀፍ ሚዲዎች የተባበሩት መንግስታትን በመጥቀስ ከ10 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ለምግብ እጥረት መዳረጋቸውን መዘገባቸውን ተከትሎ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ያነጋገረቻቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያና በፓርላማ ብቸኛ የህዝብ ተወካይ የሆኑት የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በኢትዮጵያ ለረሀብ ምክንያት የሆነው የኢህአዴግ የፖሊሲ ችግር እንደሆነ አመላክተዋል፡፡ “ድርቅ ሲኖር ረሀብ ሁል ጊዜ ይኖራል ማለት አይደለም” ያሉት አቶ ግርማ ሀገራት ትርፍ ምርትን በአግባቡ በማከማቸት በድርቅ ጊዜ ረሀብ እንዳያጋጥም እንደሚያደርጉ አስረድተዋል፡፡ አክለውም “በሀገራችን ረሀብ የሚደርሰው ገበሬው ለራሱ ፍጆታ የሚሆን አነስተኛ ምርት ብቻ ስለሚያመርትና ምርቱ በድርቅ ምክንያት ሲስተጓጎል የሚበሉትን ስለሚያጡ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ሰንደቅ ጋዜጣ ሙሉውን እትም እነሆ!!

- በከባድ ወንብድና የተከሰሱት እስከ 30 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ
- የዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት የፖለቲካ እንጂ የሕግ ተቋም እንዳልሆነ ተገለፀ
- ባለራዕይ ወጣቶች ማኅበር ለጄኔራል ጃገማ ኬሎ የክብር ሽልማት ሰጠ
- በሦስት የመንግስት ተቋማት ላይ አንድነት ፓርቲ ክስ መሰረተ
- የግብፅ እና የሱዳን ባለስልጣናት በአባይ ጉዳይ ላይ ሊወያዩ ነው
- ሚኒስትሩ ከኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ጋር በተያያዘ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሉብን አሉ
- እና ሌሎችም…

ሙሉውን ጋዜጣ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ::

Wednesday, February 5, 2014

በአዲስ አበባ የወንድ የጎዳና ሕጻናት ላይ የሚደርሰው የወሲብ ጥቃት (ጥናታዊ ጽሑፍ)

በ አሸናፊ ደምሴ ሰንደቅ ጋዜጣ

በተለያዩ የጥናት ውጤቶች እንደተገለጸው የሕጻናት የወሲብ ጥቃት “በየትኛውም ሁኔታ ሊከሰት የሚችል ድርጊት” በማሕበራዊ፤ በኢኮኖሚዊ እና በጂኦግራፊያዊ ሁኔታዎች ሳይወሰን በየትኛውም ስፍራና ሁኔታ ሊከሰት የሚችል ተደርጎ ይወሰዳል። ጥቂት ጥናቶች ደግሞ ወንዶች ከወንዶች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት በሚፈጽሙበት ሁኔታ እንዳለ ያሳያሉ። በአዲስ አበባ ሕጻናት ላይም የወሲብ ጥቃቱ እንዳለ ጥናቶች ይጠቁማሉ። በወንዶች ላይ የሚደርሰው የወሲብ ጥቃት አስመልክቶ በ2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተደረገ ጥናት በአጠቃላይ ተጠቂዎች 22 በመቶ (47 ያህሉ) ለፖሊስ ሪፖርት አድርገዋል። 44 ያህሉ በጎረቤቶቻቸው፤ 3 በመቶ ያህሉ ደግሞ በማይታወቁ ሰዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል። ከተጠቂዎች መካከል 26 በመቶ ያህሉ የጎዳና ሕጻናት ናቸው።

ይኽው ጥናት እንዳመለከተው የጥቃቱ ፈጻሚዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 84 በመቶ ያህሉ ደግሞ ትዳር የሌላቸው ናቸው ይላል።በጥናቱ ዙሪያ የተጠኑ ጥናቶች በጣም ጥቂት በመሆናቸው አጥኚዎች ስለ ችግሩ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን አጥኚው ይገልጻል። በመሆኑም በወንድ ሕጻናት ላይ የሚደርሰውን የወሲብ ጥቃት የችግሩን ስፋት መንስኤና ውጤት እንዲሁም በተጠቂዎች ላይ የሚደርሰው የስነልቦና ችግርና የህግ አግልግሎት ላይ ያላቸው እውቀት ውስን መሆኑን ይገልጻሉ።

ይህ ጥናት በወንድ በጎዳና ሕጻናት ላይ የሚደርሰውን የወሲብ ጥቃት፤ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ገጽታ በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑትንና ሃሳባቸው ተቀባይነት የሌለውን የጎዳና ሕጻናትን ይዳስሳል። እድሜያቸው ከ8 - 18 የሆኑ ሕጻናትን በተለያዩ መስፈርቶች በሶስት ቦታ ከፋፍሎ ጥናቱ ተካሂዷል። በጥናቱ ከ250 በላይ ሕጻናት ተሳትፈዋል፤ በ24 ወንድ የጎዳና ሕጻናት ላይ ጥልቅ የህይወት ታሪክ መጠይቅ ተካሂዷል። ሕጻናቶቹም ከተለየዩ እምነቶች፤ ከተለያዩ የቤተሰብ ሁኔታዎች እንደመጡ ጥናቱ ያረጋግጣል። ጥናቱ የተካሄደው በአውቶቡስ ተራ፤ በጎጃም በረንዳ፤ መሳለሚያ፤ ሰባተኛ እና አትክልት ተራ አካባቢ በሚገኙ የጎዳና ወንድ ሕጻናት ላይ መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል። በጥናቱ ላይ 35 መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተጨማሪ ቁልፍ የመረጃ ምንጮች ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸዋል።

ወያኔ: የነፃው ፕሬስ ፀር!

በቅዱስ ዮሃንስ

ነፃ- ፕሬስ ለነፃነት፤ ለፍትህና ለእኩልነት የሚኖረውን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡ ገዢዎች ፕሬሱ ለአንባገነንነት አገዛዛቸው የሚመች ስለማይሆን ይፈሩታል፤ ይጠሉታል፤ ያጠፉታል። ወያኔም እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው።

ነፃ ፕሬስ የሀሳብ ነፃነት መብት አልፋና ኦሜጋው ነው ብል ማጋነን አይሆንም። የነፃ ፕሬስ መኖር የሚያረጋግጠው ጋዜጠኞች ያለምንም ጭንቀትና ፍርሃት የሚያስቡትን፡ የሚሰማቸውን፡ የሚሰሙትን እንዲሁም ምርምር አድርገው የደረሱበትን ዜናዎች በነፃ ለመፃፍና ለማሰራጨት ብሎም ሕዝብ እንዲወያይበት ለማድረግ ያላቸው ያልተገደበ መብት ነው። ይህም ጤናማ ሕብረተሰብ ለመፍጠር ብቻ ሳይሆን ለእድገቶቹም ጉልህ ድርሻ አለው።  ነፃ ፕሬስ የኃሳብ ነፃነት ተግባራዊ ለመሆኑ ዋስትናም መፈተኛም ነው። ኃሳብን ያለምንም ጭንቀትና ፍርሃት በነፃ ለመግለፅ መቻልና መለዋወጥ እንደ ምግብና መጠጥ፤ ሁሉ ሰብአዊ ክቡርነትን የተላበሰ ሕይወት ለመጎናፀፍም አስፈላጊም ናቸው። ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት መኖርና ዋስታናው ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሕግ መረጋገጥ ማለት ዘላቂነት ላለው ዴሞክራሲያዊ እድገት ለማገኘትም ዋና መሰረት ነው።

የተሳካ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የነፃ ፕሬስ አስፈላጊነት ትልቅ ቦታ እንዳለው ከልብ ይታመናል፡፡ ያለነፃ ፕሬስ ዴሞክራሲ አለ ብሎ መናገር ማወናበድ እንጅ እውነት ሊሆንም አይችልም፡፡  የነፃ ፕሬስ መኖር በራሱ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መኖር መገለጫ ነውና፡፡ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሲኖርም ነፃ ፕሬስ ይኖራል፡፡ ወደ እኛ ሃገር ስመለስ ግን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ወያኔ መንግስት ሆኖ ላለፉት 23 ዓመታት ሃገሪቱን ሲያስተዳድር ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በወረቀትና በቃል እንጂ ከዚያ በዘለለ በተግባር ሲፈፅም አላሳየንም፡፡ ለመተግበር የሞከራቸውንም እንደ ቀንዳውጣ ቀንድ መልሶ ሸሽጎታል፡፡ ስለዚህ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት የማያምን አምባገነን ስርአት ስለሆነ ለነፃው ፕሬስ ፀር በመሆን ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ በመስጠት ፋንታ አጥፊና ደምጣጭ ሆኖ እየሰራ ይገኛል።

ኢትዮጵያን ከቅርጫ ለማትረፍ

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የአሁኑ አስገራሚ ጊዜ ሸክስፒር፣ ጁሊየስ ቄሳር በሚለው ፅሁፉ ላይ ለተናገረው  አነጋገር ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል፣ “ሰዎች የሰሩት ተንኮል ከመቃበራቸው በላይ ሀያው ሆኖ ይኖራል” ብሎ ነበር ሸክስፒር፡፡ በአሁኑ ጊዜ አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ከሰሩት ተንኮሎችና ጭራቃዊነት የሞላው አስቀያሚ ተግባር ውርስ ጋር ፊት ለፊት ተፋጥጠን እንገኛለን፡፡ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ የግዛት አካል ተቆርሶ እንደገና ለሽያጭ ለሱዳን ቀርቧል፡፡ ይህንንም ጭራቃዊነት ተንኮል የቀበሮ ባህታውያኑ “የድንበር ማካለል“ ብለው ይጠሩታል፡፡ እኔ ደግሞ ድንበር መቁረስ፣ መቆራረስ፣ መሽረፍ እና መሸራረፍ ብዬ እጠራዋለሁ፡፡ ባጭሩ ኢትዮጵያን  ለቅርጫ ማቅረብ እለዋለሁ… ደግሞ ለሰላሳ ቁርጥራጭ የመዳብ ዲናሮች!

እ.ኤ.አ በ2008 “የኢትዮጵያ ጋሻ“ ተብሎ በሚጠራው የሰሜን አሜሪካ የሲቪል ማህበረሰብ ስብስብ ጉባኤ ላይ በመገኘት የእናት አገር ኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መጠበቅ በሚል ርዕስ ስሜትን የሚቀሰቅስ ንግግር አድርጌ ነበር፡፡

በዛሬዋ ዕለት እዚህ የተሰባሰብንበት ዋናው ምክንያት አቶ መለስ ዜናዊ እናት አገራችንን መቅን አሳጥተው ለመበታተን እንዲመቻቸው በበረሃ ሳሉ ነድፈው ያመጡትን ጭራቃዊ ዕቅድ እና ዕኩይ ምግባር ለማውገዝ እና ለማስቆም ነው፡፡ አቶ መለስ የአሰብን ወደብ አሳልፈው በሰጡበት ወቅት ዝምታን በመምረጣችን ወደብ አልባ የመሆንን ዋጋ ከፍለናል፡፡ እ.ኤ.አ በ1998 ባድመ ተወረረች፣ እናም የ80,000 ኢትዮጵያውያን ህይወትን የበላ መስዋዕትነት ተከፍሎ ጠላቶቻችን ከግዛታችን እንዲወጡ ተደረገ፡፡ ሆኖም ግን አቶ መለስ በብርሃን ፍጥነት ተገልብጠው የኢትዮጵያን አንጸባራቂ የጦር ሜዳ ድል ቀልብሰው የዲፕሎማሲያዊ ሽንፈትን በመጋት በእርቅ ሰበብ ስም ባድመን ለወራሪው ኃይል አሳልፈው ለመስጠት ስምምነት አደረጉ… (ዛሬ) በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ወገኖቻችን በግልጽ እንደነገሩን የአያት ቅድመአያቶቻቸውን መሬት እና መኖሪያ ቤታቸውን ሳይቀር አቶ መለስ ለሱዳኑ አምባገነን [በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በወንጀል ለሚፈለጉት እና ከፍትህ ለማምለጥ እራሳቸውን በመደበቅ ተወሽቀው ላሉት] መሪ ኦማር አልባሽር አሳልፈው ለመስጠት በሚስጥር ስምምነት ፈጽመዋል… ያንን ንግግር ካደረግሁ ከስድስት ዓመታት በኋላ እንኳን በሚያሳዝን ሁኔታ እናት አገራችንን ለመበታተን አቶ መለስ ከበረሃ ውስጥ ነድፈው ያመጡትን ጭራቃዊ ዕቅድ እኩይ ምግባር ለመቀልበስ ባለመቻላችን አዝናለሁ፡፡ አቶ መለስ አሁን በህይወት የሉም፣ ሆኖም ግን እኛን እንዲያጠፋ ጥለውት ከሄዱት ተንኮላቸው ስራቸው ጋር ፊት ለፊት ተጋትረናል፡፡ “መልካም ሰዎች ዝም ስላሉና ምንም ባላማድረ ጋቸው ይሆን ተንኮል የሚበረታው” የሚለው አባባል እውነታነት አለውን? በመጨረሻም ተንኮልና ጭራቃዊነት ድል ተጎናጽፏልን?

ኢትዮጵያ በአቶ መለስ ዜናዊ ቅርጫ መግባት

እ.ኤ.አ ዴሴምበር 2013 የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ዓሊ ካርቲ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ገዥ አካላቶች “ፋሻጋ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የነበረውን የድንበር አለመግባባት እና በሌሎች አካቢዎችም ያሉትን የድንበር ማካለል ስራዎችንም በሰላማዊ መንገድ ለማጠናቀቅ ስምምነት አድርገናል“ በማለት በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ስለሁለቱ አገር መሪዎች አስመልክቶ ካርቲ እንዲህ ብለዋል፣ “የመጨረሻውን የማካለል ስራ ለመተግበር ታሪካዊ ስምምነት አድርገናል፡፡“ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያሉትን “የድንበር ውዝግቦች” በማስመልከት ለሚቀርቡ አስተያየቶች ሁሉ ምንም ዓይነት ሀሳብ እንደማይቀበል ጠቅሶ ሲናገር፣ “በጠረፉ በተወሰኑ የወሰን ድንበር ነጥብ ቦታዎች ላይ“ በጣም ቀላል የሆኑ አለመግባባቶች ከመኖር በስተቀር ሌላ ቸግር እንደሌለ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

Tuesday, February 4, 2014

የአማራውን ሕዝብ ክብር የደፈሩና ያዋረዱ አምባገነን ገዥዎች ለፍርድ ይቅረቡ!!! (ከአንድነት የተሰጠ መግለጫ)


ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

«ጉድ ሳይሰማ…» እንደሚባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በስርዓቱ እየተፈፀመበት ካለው ጭቆናና በደል፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋ፤ አፈናና ስደት፤ ሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት በተጨማሪም በአምባገነን ገዥዎች እየተዋረደ፣ በአደባባይ እየተሰደበና ሰብዓዊ ክብሩ እየተጣሰ ይገኛል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖም ሀገራችን ላይ ያለው ስርዓት ህዝቡን የሚያዋርድ፣ ከህዝብ ጥቅም ይልቅ ስልጣኑን የሚያስቀድም፣ ለህዝብ ጆሮ የሚሰጥ አስተዋይ መሪ የሌለው ነው፡፡

ለዘመናት ያልተፈቱ ችግሮችና በመሪዎቹ የሚፈጠሩ ችግሮች ትከሻውን ያጎበጡት የኢትዮጵያ ህዝብም ስርዓቱን ከነችግሩ መሸከሙ አልበቃ ብሎ መሪ ነን በሚሉት እየተበሻቀጠና ለውርደት እየተዳረገ ይገኛል፡፡

ፓርቲያችን በትኩረት እየተከታተለው ያለውና ሰሞኑን የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይና በኢሳት ይፋ የተደረገው የአማራ ክልል ም/ ፕሬዘዳንትና የብአዴን ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን፣ የአማራውን ህዝብ በአደባባይ መሳደባቸውንና ማዋረዳቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች መለቀቃቸውና የክልሉ መንግስት ለማስተባበል እንኳ ዝግጁ አለመሆኑ የሚያሳየው ንቀትንና ጥላቻን ብቻ ሳይሆን እንመራዋለን የሚሉት ህዝብ ትከሻ ላይ ተቀምጠው ፀረ ህዝብ አቋም እንደሚያራምዱ ነው፡፡ ፓርቲያችን የብአዴን/ኢህአዴግ ባለስልጣን በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀሙትን ክብር የሚነካ አሳፋሪ ድርጊት በቸልታ ሊመለከተው እንደማይችል አስረግጦ ለመናገር ይወዳል፡፡ ፀረ ህዝብ አቋም የሚያራምዱ አምባገነኖችንም ከህዝብ ትክሻ ለማውረድ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋግጣል፡፡ አንድነት በቅርቡ በጉራ ፈርዳና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በዜጎች ላይ የተወሰደው የማፈናቀል ተግባር ስርዓቱና የስርዓቱ መሪዎች የፈጠሩት ችግር እንጅ የአካባቢው ሕዝብ የፈጠረው እንዳልሆነ ያምናል፡፡

አቶ አለምነው መኮንን የተባሉት ባለስልጣን የአለቆቻቸውን የዘወትር አባባል በማስረገጥ እመራዋለሁ የሚሉትን የአማራ ህዝብ «ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፣ ትምክህተኝነቱን ያልተወ፣ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ» ካሉ በኋላ «የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት» በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ለዚች ሀገር ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ክልል ህዝብ ዋጋ በማሳጣትና የሌሎች ጠላት አድርጎ በማቅረብ የማጥላላት ዘመቻ ከፍተዋል፡፡

ፓርቲያችንም ይህንን አሳፋሪና የዜጎችን ክብር የደፈረ የባለስልጣኑ አባባል በቸልታ የሚታይ ሆኖ አላገኘውም፡፡
ስለዚህ፡-

1. ግለሰቡ በዚህ የተዛባ አመለካከቱ ለአማራ ክልል ህዝብ መሪ ሊሆን ስለማይችል በአስቸኳይ ከፓርቲና ከመንግስት ኃላፊነቱ እንዲነሳና ለህዝቡ ይፋ እንዲደረግ፤

2. ህዝቡን ያዋረደው ባለስልጣን ላይ እርምጃ የማይወሰድ ከሆነ ግን የግለሰቡ አመለካከት የብአዴንና የክልሉ መንግስት አቋም አድርገን የምንወስድ መሆኑ እንዲታወቅ፤

3. አንድነት ፓርቲ ፀረ-ህዝብ አቋም ያለው ግለሰብ ባደረገው የህዝብ ጥላቻ ንግግር (Hate speech) ተነስቶ ለሕግ የሚያቀርብ መሆኑ እንዲታወቅ፤

4. ፓርቲያችን ህዝቡን በማስተባበር በባህርዳር ከተማ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራና ድርጊቱን የማውገዝና እንዲቆም የማድረግ ርምጃ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ስለዚህ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የክልሉን ህዝብ እየመራው ያለው ብአዴን/ኢህአዴግ ለህዝብ ክብር የሌለው ድርጅት መሆኑን አውቆ ከፓቲያችን ጎን በመቆም እንዲታገለው ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ጥር 26 ቀን 2006 ዓ.ም

Monday, February 3, 2014

እቅድ - ትራንስፎርሜችን - ራእይ = ኢሕአዴጋዊ መንጠራራት

አቅዶ የሚያብድ ሥውር አደገኛ ሕሊና፣ ቁምነገር አልባ ነው!‪

የሰላም ትልቁ ጠላት ከአቅም በላይ መመኘት ነው፡፡ 

የሥራ መንፈስ ከብዙሃኑ የልብ ፍቅርና የአገር መውደድ ስሜት ጋር በፅኑ መቆራኘት አለበት፡፡ ላገር አሳቢ እየመሰለ ውስጥ ውስጡን እንደሚቦጠቡጥ ሹም ባለበት ቦታ ዕቅድ ሲታቀድ ቢውል ፍሬ-ቢስ ነው የሚሆነው። ነባር ነባር በላተኛ አባርረን ትኩስ ትኩስ፣ ልጅ-እግር በላተኛ ካመጣን፤ የበላተኞች መተካካት እንጂ የአዲስ ደም - ቅያሪ አይሆንልንም፡፡ እጃችንን ዘርግተን የማንደርስበትን ነገር ለመጨበጥ መሞከር፤ በር ከፍተን ለዘራፊ እንደመተው ነው፡፡ የሰላም ትልቁ ጠላት ከአቅም በላይ መመኘት ነው፡፡ አሊያም የክቡር እምክቡራን ዕብደት ነው። “ከአቅም በላይ መኖር የዕድገት ፀር ነው” ይሉ ነበር ያለፈው ሥርዓት ነገረ-ሠሪዎች! ኮከብ እነካለሁ ብሎ ሠምበሌጥ ላይ መወድቅ ይከተላል፡፡ ለራስ ጥቅም ሲሉ የአገር ዕቅድ አወጣሁ ማለት መዘዙ ብዙ ነው፡፡ ድህነት ባጠጠበት፣ ችጋር በተንሠራፋበት አገር እንደ ህንድ እጉልላቱ አናት ላይ ጥቂት ባለ ፀጋ ሰዎች ብቻ ተቀምጠው፣ የበለፀገች ኢትዮጵያን መመኘት ከንቱ መገበዝ ነው፡፡

ኦሞት ኦባንግ – የታዳኝ አዳኝ ድራማ


ኢህአዴግም በበኩሉ እያደናቸው ነው

“ሁሉም ከህግ አያመልጡምና ዜጎች መረጃ በመሰብሰብ የቤት ስራችሁን ስሩ” ኦባንግ ሜቶ

ኦሞት ኦባንግ በዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለፍርድ እንዲቀርቡ እየታደኑ ነው!

ሰሞኑን አገር ጥለው መኮብለላቸው የተደመጠው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦሞት ኦባንግ በተለያዩ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ ታወቀ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ፍትህ የተዛባባቸው ዜጎች ሁሉ መረጃ በማሰባሰብና ለድርጅታቸው በመላክ የዜግነት የቤት ስራቸውን እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ ኦሞትን ፍትህ ደጅ ለማቆም ከ19 ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በኅብረት እየሰሩ መሆናቸውም አመልክተዋል። በሌላም በኩል ኢህአዴግም “ነገር ሳይበላሽ” እያደናቸው እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

በ2003 በጅምላ ለተጨፈጨፉና በሺህ ለሚቆጠሩ የአኙዋክ ተወላጆች መሰደድ ከመለስ ቀጥሎ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚባሉት አቶ ኦሞት፤ ሳምንት በፈጀ ግምገማ ከክልሉ ሊቀመንበርነታቸው መነሳታቸውና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው መመደባቸው ይታወሳል። “እውነተኛው ወያኔ” እየተባሉ የሚጠሩት አቶ ኦሞት ምንም እንኳ በሚኒስትርነት ደረጃ ቢመደቡም በሙስና ተወንጅለው እንደሚታሰሩ ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ አይዘነጋም።

Sunday, February 2, 2014

“ነገረ ኢትዮጵያ” የተሰኘች የህዝብ ልሳን የሆነች የሰማያዊ ፓርቲ ጋዜጣ



ሰማያዊ ፓርቲ በቅርቡ “ነገረ ኢትዮጵያ” የተሰኘች የህዝብ ልሳን የሆነች ጋዜጣ ለማሳተም ዝግጂት እያደረገ የነበረ ሲሆን ዝግጂቱን አጠናቆ ወደ ማተሚያ ቤት ከገባ በኋላ ግን ከፍተኛ የሆነ ስልታዊ ማደናቀፍ እየደረሰበት በመሆኑና ለጊዜው ማሳተም ባለመቻሉ እነሆ በድረ-ገፃችን ለንባብ በቅታለች! እርሰዎም ይታደሟት! ለጓደኛ ወዳጇችዎም ያጋሯት! መልካም ንባብ!

በ PDF ለማንበብ ይሄንን ይጫኑ


የድንጋይ ዉርወራ ፖለቲካ በዓዲግራት

በኣብርሃ  ደስታ

ዓረና-መድረክ ለጥር 18, 2006 ዓም በዓዲግራት ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ መጥራቱ ይታወሳል። ዓዲግራት ከተማ ከመቐለ በስተሰሜን በኩል በ120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። የስብሰባው ዓላማ ከዚህ ቀደም በዉቅሮ፣ ማይጨው፣ ዓብይ ዓዲና ሽረ ከተሞች እንዳደረግነው ሁሉ የዓረና ፓርቲ ዓላማዎችና ፖሊሲዎች ከህዝብ ጋር ለማስተዋወቅ እንዲሁም ህዝብን ፖለቲካ ማስተማርና ማደራጀት ነበር።

ስብሰባ ለማካሄድ ተፈቀደልን። የማዘጋጃቤት አዳራሽም ተሰጠን። ስብሰባ ለማድረግ ማስፈቀድና አዳራሽ ማግኘት በቂ አልነበረም። ህዝብ በስብሰባው እንዲሳተፍ የጥሪ ወረቀት መበተን ነበረብን። በማይክሮፎንም ማወጅ ነበረብን። ዓረና በዓዲግራት ከተማ ስብሰባ መጥራቱ ለማብሰር የዓረና ፓርቲ ልኡክ ወደ ዓዲግራት ከተማ ሐሙስ ጥር 15, 2006 ዓም ተላከ።

ዓርብ ጥር 16, 2006 ዓም ጧት የልኡካን ቡድኑ ለሁለት ተከፍለው ዓዲግራት አቅራቢያ በሚገኙ የዕዳጋ ሐሙስና የፋፂ ከተሞች የስብሰባው ቅስቀሳ አደረጉ። ወደ ፋፂ የተላከው ቡድን የተሳካ ቅስቀሳ አድርጎ በሰላም ወደ ዓዲግራት ሲመለስ በዕዳጋ ሐሙስ የነበረ ቡድን ግን “ሕጋዊ አይደላችሁም” በሚል ሰበብ የዓረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙት ሐላፊ የሆነው አቶ ዓምዶም ገብረስላሴና መምህር ሃይለ ገብረፃዲቅ ታሰሩ። ከሰዓታት እስር በኋላ ተፈቱ። ወደ ዓዲግራትም ተመለሱ።

ዓርብ ከሰዓት በኋላ እኔና አቶ አስገደ ገብረስላሴ ዓዲግራት ከተማ ገባን። ሁላችን በዓዲግራት ተሰባሰብን። ለሁለት ተከፍለን ቅስቀሳ ለመጀመር አንድ ቡድን ከፒያሳ ወደ መነሃርያ አቅጣጫ ሲንቀሳቀስ ሌላው ደግሞ ወደ ስታዲዮም (እንዳ ምስዮን) አከባቢ ተንቀሳቀሰ። ወደ መነሃርያ አከባቢ የተንቀሳቀሰ ቡድን በዓዲግራት ህዝብ ብዙ ድጋፍ አገኘ። ህዝቡ የሚበላና የሚጠጣ ያቀርብልን ነበር። ወረቀት በመበተንም ይተባበረን ጀመር። ይህ ሁሉ ሲደረግ የከተማው ሰራተኞች፣ የደህንነት ሰዎች፣ የፖሊስ አባላት እየተከታተሉ ያዩ ነበረ።