በአገራችን ታሪክ ውስጥ ወርሃ የካቲትን ልዩ የሚያደርጓት ቁም ነገራት አሏት። አስቀድመን ጀግኖቹ አብርሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስግዶም ግሪያዚያንን ያስበረገገውን ቦንብ ያፈነዱበት ወር የካቲት መሆኗን ማስታወስ እንወዳለን። በዚህ ምክንያትም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ30 ሺህ በላይ ህዝብ ተገድሎ የሰው ደም እንደ ክረምት ጎርፍ ከተማዋን ያጥለቀለቀው በዚህች በየካቲት ወር ነው። በሌላ በኩል ጠላቴ “የአማራ ህዝብ እና ተፈጥሮ “ነው ብሎ በፅኑ የሚያምነው ህወሃት የተወለደው በወርሃ የካቲት ነው። የየካቲት ታሪክ በዚህ ብቻ አያበቃም በወርሃ የካቲት ህወሃት “የመከላከያ ኃይል ቀን “ እያለ ከበሮውን እየደለቀ የሚድሪቷ ከርስ እሰከሚበረበር ድረስ ዳንኪራ ይረግጣል።
ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ግን የካቲት የደስታ ወር አይደለችም። የካቲት በግፍ የተገደሉብንን ዜጎቻችንን እያስታወስን ልቦናችን በሃዘን የሚታወክበት እንጂ ሃሴት የምናደርግበት ወር አይደለችም። በየካቲት ወር ግራዚያን “ያገኛችሁትን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ግደሉ” ብሎ አዋጅ በማስነገሩ በጭካኔው የምንቆጣበት እንጂ በደስታ የምንሰክርበት ወር አይደለችም። በወርሃ የካቲት የሌላውን ቦታ ሳይጨምር በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ30ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ሲጨፈጨፉ ከግራዚያን ጎን ቁመው ወገኖቻቸውን ያስጨፈጨፉ ባንዳዎችን እያሰብን አንገታችንን ደፍተን የምናዝንበት ወር እንጂ የደስታ ወር አይደለችም። ወርሃ የካቲት ለኢትዮጵያዊያን በደግ የምትታወስ ወር አይደለችም። በወርሃ የካቲት የተወለደው ህውሃት የተባለው ዘረኛና ዘራፊ ቡድን በአገራችን ላይ ያደረሰውን ግፍ እያሰብን ግፉ እንዲያበቃ አእምሯችን የምንሰበስብበት ወር ነች። ህወሃት በመወለዱ ኢትዮጵያችን የድሆች ሁሉ ድሃ፤የደካሞች ሁሉ ደካማ፤ ልትበታተን አደጋ አፋፍ ላይ ያለች አገር ተብላ ሥሟ በበጎ የማይነሳ አገር እንድትሆን ሆነች።
ህወሃት በወርሃ የካቲት ተወለድኩ ሲል አወጀ። ከዚያም ቀጥሎ እንዲህ አለ “አማራና ተፈጥሮ ጠላቶቼ ናቸው” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ። ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን ከተገኘም አሸባሪ እና ትምክህተኛ ነውና ይገደል ሲል ያልተፃፈ ህግ አፀደቀ። በየካቲት ወር ይህን የሞት ድምፅ ብዙ ዜጎች በአርምሞና በግርምት ሰሙት። ህወሃት አገሪቷን ክተቆጣጠር በኋላ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማራ የገባበት አልታወቀም ተብሎ ለፓርላማ መሰል አካሉ ሪፖርት ቀረበ። በግራዚያን አዋጅና በህወሃት አዋጅ መካከል ልዩነት የለም። በየካቲት ወር ግራዚያን “ያገኛችሁትን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ግደሉ” ብሎ የሞት አዋጅ አወጀ። በዚህ አዋጅ ምክንያት በአንዲት ጀንበር 30ሺህ ኢትዮጵያዊያን በአዲስ አበባ ተፈጁ። ግዲያውን ለማስፈፀም ከፊቱ የቀደሙ በስም ኢትዮጵያዊን በምግባር ግን ፋሽት የሆኑ ምናምንቴዎች ነበሩ። ከእነዚህ ውስጥ የመለስ ዜናዊ እና የስብሃት ነጋ ወላጆች በፍፁም የሚረሱ አይሆኑም። እነዚህ የባንዳ ውላጆች በወርሃ የካቲት “አማራና ተፈጥሮ ጠላቶቼ ናቸው” ብለው አውጀው ህወሃትን መሥርተው ለስልጣን ከበቁ በኋላ 2ሚሊዮን አማራ ጠፋ። በወርሃ የካቲት የተወለደው ህወሃትና ፋሽስቶችን ከሚያመሳስለው ድርጊት መካከል አንዱ ይሄው ነው። በየካቲት የተወደው ህወሃት ኢትዮጵያን በመከራ አረንቋ ውስጥ ደፍቆ እስከ ዛሬ ዘለቀ። በዚህ ምክንያት ወርሃ የካቲት ለኢትዮጵያዊያን ደገኛ ወር አይደለችም።
በኢትዮጵያዊያን ታሪክ ውስጥ የካቲት የምትታወስበት ሌላ አብይ ነገር ደግሞ አለ። አብርሃም ደቦጭና፤ሞገስ አስግዶም የተባሉ ከኤርትራ የመጡ ወጣቶች የኢትዮጵያ ጠላት በሆነው በግራዚያን ላይ የፈፀሙት ጀግንነት ነው። እነዚህ ሁለት ወጣቶች በጨካኙ ግራዚያኒ ላይ በወረወሩት ቦንብ በፋሽስቶቹ መንደር ጉዳት አደረሱ። ይሄ ድርጊት በአርበኝነት ተሠማርተው ለነበሩት ጀግኖች አበረታች ድርጊት እንደነበረ በታሪክ ተመዝግቧል። ከዚህ ድርጊት በኋላ ግን በሦስት ቀን ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ ከ30ሺህ በላይ ህዝብ ተገደለ። በዚሁ በየካቲት ወር አብርሃምና ሞገስ አልፈውበታል በተባለው በደብረ ሊባኖስ ገዳም የተገኙ 297 መናኞች እና ሌሎች 23 ኢትዮጵያዊያን በአንዲት ጀንበር እንዲገደሉ ተደረገ። ይሄ ሁሉ ግዲያ ሲፈፀም ቀላል የማይባሉ ባንዳዎች አብረው ከግራዚያን ጎን ቁመው ነበር። እንዲህ ዓይነቱን አሰቃቂ ድርጊት እንዲፈፀም ትእዛዝ የሰጠው ግለሰብ ሃውልት በአደባባይ ይሠራለትና ሥሙም ለዘላለም ይታወስ የሚሉ የፋሽት አቀንቃኞች በተነሱ ግዜ ህወሃቶች ዝምታን መረጡ። እንዲያውም የፋሽቶች ሃውልት በአደባባይ እንዳይቆም ለመቃወም የተነሱ ኢትዮጵያዊያንን በቆመጥ እየደበደቡ የተቃውሞው ድምፅ እንዳይሰማ ሰልፉን በማፈን ለፈሽቶች ያላቸውን ክብር አስመስከሩ። ከወርሃ የካቲት ትዝታዎቻችን መካከል መታወስ ያለበት አንዱ የህወሃት መልክ ይሄው ከፋሽስቶች ጋር የመደጋገፍ ድርጊቱ ነው።
ወርሃ የካቲት ሌላም ገፅታ አላት። በዚህች በየካቲት ወር ህወሃቶች የመከላከያ ቀን እያሉ በስካርና በፈንጠዝያ ያከብራሉ። ኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ከገነባችም ሃያ አንድ ዓመት ሞላት እያሉም ይዘባትላሉ። እውነቱ ግን አገራችን ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊቷን ካጣች ሃያ አንድ ዓመት መቆጠሩ ነው። በዘመነ ህወሃት ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አላት ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ላይ የምትገኝ አገር አይደለችም። ብዙ መልክ እና ባህል ባላቸው ዜጎች በቆመች አገር ውስጥ አጠቃላይ የመከላከያ ሠራዊቱ አዛዦች ከአንድ ወንዝ የተቀዱ ፤ከአንድ መንደር የተሰባሰቡ ስለመሆናቸው ቀደም ብለን ያወጣነውን መረጃ ማየት ይረዳል። የእነዚህ ቡድኖች ከአንድ ወንዝ መቀዳታቸው፤ ከአንድ መንደር መሰባሰባቸው ችግር አይደለም፤ችግሩ የሚነሳው ግለሶቦቹ ፍፁም ኃላፊነት የማይሰማቸው፤በአፍቅሮተ ንዋይ የታወሩ፤የአገርና የወገን ፍቅር የሌላቸው ፍፁም ጨካኝና ክፉ ዘረኞች ሁነው የመገኘታችው ነገር ነው አገሪቷን ውሉ ከማይታወቅ ችግር ውስጥ የዘፈቃት። ዛሬ ካርታ ይዘው የቆሙበትን ሥፍራ ለማሳየት የሚደናበሩ ጄኔራሎች ባለሚሊየን ዶላር ሃብት ባለቤት የመሆናቸው ነገር አገሪቷ ከተጋረጡባት ችግሮች መካከል አንዱ ነው። የመከላከያ ቀን ሲከበር የጦሩ አለቆች ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ዘራፊዎች፤ነፍሰ ገዳዮችና፤ አለሰፋራቸው ሚሊየነር ነጋዴ ሁነው የመገኘታቸው ነገር አብሮ መታወስ
በየካቲት ወር የመከላከያ ቀን ሲከበር አብረን የምናስታውሳቸው ሌሎች አሳዛኝ እውነቶች ደግሞ አሉ። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለማስታወስ ያክል የአገሪቷ መከላከያ ሠራዊት በሠላም አስከባሪ ሥም ሶማሊያ ድረስ ዘልቆ ገብቶ የሚሞትበትንና የሚገድልበትን ምክንያት ዜጎች የማወቅ መብት የላቸውም መባሉን ከመከላከያ ኃይል ቀን አከባበር ጋር አብረን የምናስታውሰው ጉዳይ ይሆናል። ከዚህ ጋር ተያይዞ መታወስ ያለበት እውነት ደግሞ በሠላም አስከባሪ ሥም የህወሃት ጄኔራሎች እየተፈራረቁ በየቀኑ ከ160 ዶላር በላይ ዓበል የመሰብሰባቸው ጉዳይ ነው። ጄኔራል ተብየዎች በየቀኑ ከ160 ዶላር በላይ ሲያጋብሱ ድሃው ወታደር ግን ለምንና ለማን እንደሚሞት ሳያውቅ በወጣበት ይቀራል። አስከሬኑም ክብር አጥቶ በሶማሌ ጎዳናዎች ላይ እየተጎተተ መሳቂያ መሳለቂያ ይሆናል። የህወሃት ጄኔራሎች ግን በዚህ ሁኔታ ዜጎችን እያስፈጁ ለሦስት ወታደር በወር የሚከፈለውን ደሞዝ በየቀኑ ወደ ኪሳቸው እየክተቱ በደስታ ይሰክራሉ።
የመከላከያ ኃይል ቀን ሲዘከር አብረን የምናስታውሰው በአገሪቷ ሥም የተቋቋመው ሠራዊት የገዛ ዜጎቹን ያለ ርህራሄ የሚገድል፤ ኦጋዴን ወርዶ ዘር የሚያጠፋ፤ጋምቤላ ወጥቶ ያገኘውን ሁሉ የሚገድል፤አዲስ አበባ ላይ ከተማሪ ቤት የሚመለስ ህፃንን ሳይቀር ተኩሶ ለመገድል የማይራራ። የሚፈፅመውን የጭካኔ ድሪጊት ከትክክለኛ ኃላፊነቱ ጋር ደባልቆ የሚያይ ቡድን መሆኑንም አብረን ማስታወስ አለብን። ይሄ ሠራዊት ተብሎ የሚጠራው ቡድን ሊጠብቀው የሚገባውን ህዝብ እንዲያሸብርና እንዲገድል ሁኖ የተቀረፀው በህወሃቶች እኩይ አመራር መሆኑንም በየካቲት ወር ክሚከበረው የመከላከይ ቀን ጋር አብረን እናስታውሳለን።
ወርሃ የካቲት የህወሃት የውልደት ወር፤የግራዚያን የግፍ ግዲያ ወር፤የህወሃት መከላከያ ኃይል የሚከበርባት ወር በመሆን እየታወሰች ነው። የካቲት በአገራችን ላይ የሃዘን ድባባ ያጠላባት ወር እንጂ ከበሮ የሚመታባት፤ ዳንኪራ የሚረገጥባት ወር የምትሆን አይደለችም። ህወሃቶች ግን ይህችን ወር እየጠበቁ ከበሯቸውን እየደቁ፤ የምድሪቷ ከርስ እስከሚበረበር ድረስ ዳንኪራ እየረገጡ ይውረገረጉባታል። ለብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ግን የካቲት የትካዜ ወር እንጂ የደስታ ወር አይደለም።
በመጨረሻም ህወሃቶችን እንዲህ እንላችኋለን !
የካቲትን እየጠበቃችሁ ከበሮ የምትደልቁበት ዘመን እንደሚያበቃ አትጠራጠሩ። ህወሃቶች ሆይ! ስሙን ! አገር አልባ አድርጋችሁናል። የአገራችንን ግርማ አጥፍታችሁ፤ዝናዋን አዋርዳችሁ የደካሞች ደካማ፤የርሃብተኞች ርሃብተኛ እንድትሆን አድርጋችኋል። ዜጎች በማይገባቸው ጦርነት ውስጥ ገብተው አለ በቂ እና አሳማኝ ምክንያት እንዲሞቱ አድርጋችኋል። በዜጎች ደም እየነገዳችሁ ብዙ ሚሊየነር ጄኔራሎችን አፍርታችኋል። ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ከምንኖር ሂደን የበርሃ ሲሳይ እንሁን፤ የባህር አዞም ይብላን እያሉ እንዲሰደዱ ምክንያት ሁናችኋል። እናንተ በዚህ ሁኔታ ህዝቡን እያስለቀሳችሁ የካቲት በደረሰች ቁጥር ከበሯችሁን እየደቃችሁ በደስታ ትሰክራላችሁ። ይሄ ግን በዚሁ እንደማይቀጥል እኛ እንነግራችኋለን። ደግሞም አትጠራጠሩ፤ በዚሁ አትቀጥሉም። ከእናንተ ጋር ያሉት ሌሎች ግራዚያኒ ያገኛችሁትን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ግደሉ ብሎ ትዕዛዝ ሲሰጥ ከጣሊያን ወታደሮች ለሚወረወርላቸው ፍርፋሪ ብለው ወገኖቻቸውን አሳልፈው እንደሰጡ እንደዚያን ግዜ ባንዳዎች ከማየት የዘለለ የሚባልላቸው ሌላ ነገር የለም። ወገናቸውን ህዝባቸውንና አገራቸውን የካዱ መሆናቸውን እኛ ብቻ ስናሆን ራሳቸውም ጭምር ያውቁታል። ለማንኛውም እናንተም ሆናችሁ ለምናምን ሲሉ ወገኖቻቸውን አሳልፈው የሰጡ የአስቆሮታዊው ይሁዳ ምሳሌዎች ቀናችሁ እየጨለመ መሆኑን ዓይናችሁን ከፍታችሁ እንድታዩ እንመክራችኋለን።
አበቃን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
No comments:
Post a Comment