Thursday, February 6, 2014

‘‘ኢትዮጵያውያን እንዲራቡ ያደረገው የኢህአዴግ የፖሲሊ ችግር ነው’’

አቶ ግርማ ሰይፉ

በኢትዮጵያ ተከታታይ የምግብ እጥረት እንዲፈጠርና ዜጎችም እንዲራቡ ያደረገው የኢህአዴግ የተሳሳተ የፖሲሊ መሆኑን አቶ ግርማ ሰይፉ ገለፁ፡፡

የተለያዩ አለም አቀፍ ሚዲዎች የተባበሩት መንግስታትን በመጥቀስ ከ10 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ለምግብ እጥረት መዳረጋቸውን መዘገባቸውን ተከትሎ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ያነጋገረቻቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያና በፓርላማ ብቸኛ የህዝብ ተወካይ የሆኑት የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በኢትዮጵያ ለረሀብ ምክንያት የሆነው የኢህአዴግ የፖሊሲ ችግር እንደሆነ አመላክተዋል፡፡ “ድርቅ ሲኖር ረሀብ ሁል ጊዜ ይኖራል ማለት አይደለም” ያሉት አቶ ግርማ ሀገራት ትርፍ ምርትን በአግባቡ በማከማቸት በድርቅ ጊዜ ረሀብ እንዳያጋጥም እንደሚያደርጉ አስረድተዋል፡፡ አክለውም “በሀገራችን ረሀብ የሚደርሰው ገበሬው ለራሱ ፍጆታ የሚሆን አነስተኛ ምርት ብቻ ስለሚያመርትና ምርቱ በድርቅ ምክንያት ሲስተጓጎል የሚበሉትን ስለሚያጡ ነው፡፡” ብለዋል፡፡



ኢህአዴግ የሚከተላቸው የተለያዩ ፖሊሲዎች የኢትዮጵያ ገበሬዎች ከረሀብና ከምግብ እጥረት ተላቀው የተሻለ ህይወት እንዳይመሩ እንቅፋት መሆኑን የሚገለፁት አቶ ግርማ ሰይፉ “ኢህአዴግ የሚከተለው የመሬት ፖሊሲ አቅም ኖሮት ወደ ግብርና ለመግባት የሚፈልገውን ኢትዮጵያዊ መሬት በቀላሉ እንዳያገኝ አደርጓል፤ ገዢው ፓርቲ በኢትዮጵያ ያሰፈነው የዘር ፖለቲካም ዜጎች ወደ ተለያዩ ክልሎች ተዘዋውረው እንዳያመርቱ እንቅፋት ሆኗል፡፡” ብለዋል፡፡

መንግስት በሚያስተዳድራቸው ብዙሃን መገናኛዎች ከፍተኛ የግብርና ምርት መገኘቱን በተደጋጋሚ በሚገልፅበት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የዕለት ደራሽ እርዳታ ጠባቂ መሆናቸው መነጋገሪያ እየሆነው፡፡ በፍኖተ ነፃነት በጉዳዩ ላይ የመንግስትን ምላሽ ለማካተት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳች ጽ/ቤት ዴኤታ ለሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢደረግግም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም፡፡ የግብርና ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ታረቀኝ ፅጌም ስብሰባላይ መሆናቸውን ገልፀው ስልጉን ዘግተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment