Tuesday, November 4, 2014

‹‹ጥቁሩ አብዮት›› እና ኢትዮጵያ

በጌታቸው ሺፈራው

ከሳምንታትበፊት ከጓደኞቼ ጋር እስክንድር ነጋን ልንጠይቀው ወደ ቃሊቲ አቅንተን ነበር፡፡ በወቅቱ ስለ ለውጥ አውርቶ የማይጠግበውን እስክንድርንስለ ኢትዮጵያ መጻኢ እድል ስንጠይቀው የመለሰልን ቀላል ግን ደግሞ የሚገርም መልስ ነበር፡፡ እስክንድር ተስፋ አስቆራጭ የሚመስለውትግል ፍሬያማ ሊሆን እንደሚችልና በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚነሳው ጥያቄን ልክ እንዲህ ነበር ያስረዳን፡፡

‹‹እነጋናን፣ ዛምቢያን፣ እና ሌሎቹንም የአፍሪካ አገራት ነጻ እንዲወጡ ኢትዮጵያ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጋለች፡፡ አብዛኛዎቹ የአፍሪካአገራት አሁን ነጻ ካወጣቻቸው ኢትዮጵያ የተሻለ ዴሞክራሲ ገንብተዋል፡፡ እኛ እየጠየቅን ያለነው እንደነዚህ አገራት አይነት ስርዓትእንዲሰፍን ነው፡፡ የቅንጦት ጥያቄ አልጠየቅንም፡፡ መጠየቅ ከነበረብን እጅግ ትንሹን ነው እየጠየቅን ያለነው፡፡››

ከሶስትቀናት በፊት እስክንድር እኛ ነጻ አውጥተናቸው ከእኛ ይሻላሉ ካላቸው አገራት መካከል ቡርኪናፋሶዎች ለስርዓቱ ሌላ ጥያቄ አንስተውራሳቸው ሲመልሱት ስመለከት ያስታወስኩት እስክንድርን ነው፡፡ እኛ ምንም ጥያቄዎች ሳይመለስልን እነሱ ሌላ ጥያቄዎችን እያነሱ እራሳቸውመመለሱን ተያይዘውታል፡፡

ቡርኪናፋሶምንም እንኳ እንደ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ድሃ ብትሆንም እንደ እኛ 6ና 7 ሚሊዮን ህዝብ አይራብባትም፡፡ ምንም እንኳእስከ ትናንትና ድረስ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ላይ የተቆናጠጠ መሪ ያስተዳድራት የነበር ቢሆንም ፓርቲዎችና ህዝቡ ሀሳቡንየሚያንጸባርቅባቸው ሚዲያዎችና ሌሎች ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ዘርግታለች፡፡ ገና እ.ኤ.አ በ1990 ጀምሮ ሬድዮና ቴሌቪዥንንበግል በመያዛቸው ህዝቡ ለአማራጭ ሚዲያ ቅርብ ነው፡፡ ኢንተርኔት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚደረገው በስርዓቱ አይታፈንም፡፡ቡርኪናፋሶ እንደ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በጅምላ እስር ቤት የሚታጎሩባት፣ በገዥው ፓርቲ ጫና የሚሰደዱባት፣ ሚዲያዎች የሚታፈኑባትናየሚዘጉባት አገር አይደለችም፡፡

ባለፉትአመታት ለአጭር ጊዜ ከሶስት የማይበልጡ ጋዜጠኞች ታስረዋል፡፡ ባለፉት 20 አመታት በሚዲያው ታሪክ አስከፊው የሚባለው የአንድጋዜጠኛ ባልታወቁ ሰዎች መገደል ብቻ ነው፡፡ በቡርኪናፋሶ ያለፉት 20 አመታት ታሪክ ውስጥ በሚዲያው ጠባሳ ነጥብ ተደርጎየሚወሰደውና የውጭ ተቋማት ጫና ለማሳደር የሚጥሩበት ጉዳይም የዚህ ጋዜጠኛ ሞት ነው፡፡ ከአምስት አመት በፊት አንድ ጋዜጠኛየ‹‹እንገድልሃለን›› ማስፈራሪያ ስለደረሰበት ዓለም አቀፍ የጋዜጠኛ ማህበራት አሁንም ድረስ ስርዓቱን በመውቀሻነትይጠቀሙበታል፡፡ በቡርኪና ፋሶ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብሰባ እንዳያደርጉ፣ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጡ አይከለከሉም፡፡ የአገሪቱ ሲቪክማህበራት ኢህአዴግ መራሹ ‹‹መንግስት›› ስር ካሉት የተለዩ ናቸው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በሽብር ስም ወህኒአይወረወሩም፡፡ በአጭሩ ቡርኪናፋሶ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚጠየቁትን አብዛኛዎቹን የፖለቲካ ጥያቄዎች መልሳለች፡፡


ምንምእንኳ ቡርኪናፋሶ ከእኛ የተሻለ፣ እኛ የምጠይቀውን ጥያቄ የመለሰች ቢሆንም፣ ፖለቲካዊ ስርዓት ብትገነባም በሚፈለገው መንገድዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሰፍኖበታል ለማለት ግን አያስደፍርም፡፡ ቡርኪናፋሶን ለባለፉት 27 አመታት ያስተዳደሩት ፕሬዝደንት ብላይሴኮምፓሬ ወደ ስልጣን የመጡት ተወዳጁን የቀድሞ የአገሪቱን ፕሬዝደንት ቶማስ ሳንካራን አስገድለው ነው፡፡ የገዳዮቹ ቻርለስቴለርና ሙአመድ ጋዳፊ የቅርብ ጓደኛም እንደመሆናቸው ለህዝቡ ምቹ ናቸው ማለት አይቻልም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሶሻሊስት ከነበረውቶማስ ሳንካራ የተለየ ሆነው በመገኘታቸው የምዕራባውያን ተላላኪ ሆነው አገልግለዋል፡፡ በተለይ የምዕራብ አፍሪካን አለመረጋጋትለመቆጣጠር ፈረንሳይና አሜሪካ ቡርኪናፋሶን ተጠቅመውበታል፡፡

እ.ኤ.አበ1991፣ በ1998፣ በ2005ና 2010 በተደረገው ምርጫ አሸነፍኩ ቢሉም ያልተዋጠላቸው በርካቶች እንደነበሩ ይነገራል፡፡በፕሬዝዳንትነቱና በፓርቲያቸው ደስተኛ ያልሆኑት ቡርኪናፋሶውያን እ.ኤ.አ በ2011 በርካታ አመጾችን አስነስተው ስርዓቱንአስደንግጠዋል፡፡ ለአብነት ያህል በዚሁ አመት ሰራዊቱ ደሞዜ አልተከፈለኝም ብሎ የጀመረው አመጽ ፕሬዝደንቱ ወደ ተወለዱበትመንደር እንዲደበቁ አስገድዷቸው ነበር፡፡ የህገ መንግስቱ መሻሻል ሀሳብ የቀረበው ከአመት በፊት ሲሆን ተቃሞው ገጥሞት እንደገናተቋርጦ ቆይቷል፡፡

ከእኛአገር የተሻለ ግን ደግሞ መሻሻል በነበረበት የቡርኪናፋሶ ዴሞክራሲ ውስጥህዝቡ ጥያቄውን ሲያቀርብ ቆይቶ ሰሞኑን አቅሙን አሳይቷል፡፡ ቶማስ ሳንካራን ያህል ተወዳጅ መሪ አስገድለው ስልጣን ላይ የወጡትንፕሬዝዳንት በሰዓታት ውስጥ ማፍረክረክ ችሏል፡፡ የገዥውፓርቲ ዋና ጽ/ቤት፣ ቴሊቪዥን ጣቢያው፣ ፓርላማው፣ የባለስልጣናትን ቤትና ሌሎችም የመንግስት ቢሮዎች በመቆጣጠርና በእሳት በማጋየትየጀመረው የተቃውሞው ጎራ የአንድ ቀን ውሎ ህገ መንግስቱን በማሻሻል ስልጣናቸውን ለማራዘም ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩት ፕሬዝዳንት‹‹መንግስትን አፍርሸዋለሁ፡፡ መልዕክቶቻችሁን ሰምቻለሁ፡፡ የሽግግር መንግስት ይቋቋማል›› ብለው የተለየ አቋም እንዲይዙአስገድዷቸዋል፡፡ ከዛ በፊት ብዙም ቁብ ሰጥተዋቸው ያልነበሩትን ተቃዋሚዎች ‹‹አመጹን እንድታቆሙ እለምናለሁ፡፡ ከዛሬ ጀምሮከሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ጋር በመወያየት ችግሩን መፍታት አለብን›› ብለው እንዲማጸኑ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ በስተመጨረሻም በአንድቀን የህዝብ አመጽ ስልጣን መልቅቃቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

በቡርኪናፋሶውገዥ ፓርቲ ላይ የተነሳው አመጽ ሰራዊቱንም ጭምር ያሰባሰበ ሲሆን ቀድሞው የጦር ሚኒስትር ጀኔራል ኩአሜ ሎውጉን ጨምሮ በርካቶችሰላማዊ ታጋዮችን ተቀላቅለዋል፡፡ ፓርላማ፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶችንና የባለስልጣናቱን ቤት ባነደደው እንቅስቃሴ የሞቱት ሰዎችጥቂቶች እንደሆነ የታወቀ ሲሆን ይህም መከላከያና፣ ፖሊስና ደህንነቱ ከህዝብ ጎን እንደቆመ በግልጽ አሳይቷል፡፡

ከኡጋዱጉ ወደ አዲስ አበባ?

የአረቡየጸደይ አብዮት በተነሳበት ወቅት ጂቡቲ፣ ሱዳን፣ ዚምባብዌ፣ ማዕከላዊ አፍሪካና ሌሎችም አምባገነኖች ስልጣን ላይ የተቆናጠጡባቸውአገራት ውስጥ ጅምር እንቅስቃሴዎች ተስተውለው ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ባልታየበት ስለ ጸደይ አብዮትያወሩት እነ እስክንድር በሽብርተኝነት ስም 18 አመት ተፈርዶባቸውየእርስ ቤት በር ተቆልፎባቸዋል፡፡ ይህን አብዮት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከሰት ያደርጋሉ ተብለው የተፈሩ በርካታ የታዋሚ ፓርቲ መሪዎችናጋዜጠኞም በተመሳሳይ መልኩ ለዘመናዊ ግዞት ተዳርገዋል፡፡

የአረቡንአብዮት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከሰት ያደርጋሉ ብሎ በርካቶችን የሚያስረው ስርዓቱ በአንድ በኩል የዓረቡ አብዮት ኢትዮጵያ የማይደገምባቸውየሚላቸው ምክንያቶችን በማስቀመጥ፣ በሌላ በኩል ለኢትዮጵያ በእጣ ፈንታ እንደማያዋጣ በማስመሰል ህዝብን ለማሳመን ጥሯል፡፡ ይህሁሉ የስርዓቱ ተቃርኖ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ ካለመቻሉ የመጣ መደነባበርና ግራ መጋባት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በተለይ ስራ አጥነት፣ሙስና፣ አፈና፣ በአረቡ ዓለም በስፋት የታየና ለአብዮቱም ዋነኛ ምክንያት እንደነበር የሚያውቀው ህወሓት/ኢህአዴግ ኢትዮጵያውያንያሉበት ተመሳሳይ ሁኔታ እንቅልፍ ቢነሳው የሚገርም አይሆንም፡፡

የአረቡዓለም አብዮት ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት የለውም ሲባል ኢትዮጵያ ከሰሜን አፍሪካ ይልቅ ከሰሃራ በታች ለሚገኙት የአፍሪካ አገራትቅርበት እንዳላት የሚያመለክት ነው፡፡ ግን አሁን ደግሞ በቡርኪናፋሶ ያ ገዥዎቹን እንቅልፍ የሚነሳው ውሽንፍር ተነስቷል፡፡ እንዲያውምከእኛ በተሻለ ፖለቲካ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ የምትገኝ አገር ውስጥ፡፡

60 በመቶየሚሆኑት ቡርኪናፋሶውያን ወጣቶች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያም ከዚህ ያላነሰ ደግሞም ስራ አጥ፣ በሙስና፣ በአስተዳደራዊ በደል፣ በአፈናአሳሩን የሚያይ ወጣት አገር ነች፡፡ ቡርኪናፋሶውያን እ.ኤ.አ በ2011 አመጽ ወጥተውበት ከነበረው የኑሮ ውድነት በላይ ኢትዮጵያውያንላለፉት 10 አመታት በዚህ በገዥው ፓርቲ የበላይነት የሚመራው የፖለቲካ ኢኮኖሚያ ካመጣው ጣጣ ጋር ከርመዋል፡፡

የሙስሊሙ፣ኦርቶዶክሱ፣ ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ.... ተናጋሪው በአሸባሪነት ሆነ በሌላ ስም እስርና ስቃይ እጣ ፈንታው ሆኗል፡፡ ጋዜጠኞችስርዓቱ በሚያሳርፍባቸው በትር በጅምላ አገር ለቀው እየተሰደዱ ነው፡፡ መከላከያው ስርዓቱ ካመጣው በማንነት የመከፋፈል አባዜ ባሻገርበሌሎች ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች እንደተወጠረ በየጊዜው የሚወጡት መረጃዎች ዋቢዎች ናቸው፡፡ የኤርትራ ተቃዋዎች ሰፋፊ ቢሮዎችተሰጥቷቸው ሲፈልጉ ሰለማዊ ሰልፍ፣ ሲፈልጉ ስብሰባ በሚያደርጉበት አገር የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በገዛ አገራቸው ጽ/ቤት ከማግኘትጀምሮ፣ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፣ ወረቀት መበተን ቅንጦት ሆኖባቸዋል፡፡

በእርግጥኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ተርፎ የፈሰሰው ግፍ ቱኒስ ላይ የተነሳውን የአረቦችን አብዮት አዲስ አበባ ላይ ይደግማል ተብሎ በመፈራቱበርካቶች ታስረዋል፡፡ መስቀል አደባባይ ‹‹የኢትዮጵያውያን ታህሪር›› እንዳይሆን በመፈራቱ የኃይማኖት በዓላትና የኢህአዴግ የድጋፍሰልፎች ውጭ ተቃዋሚዎች ዝር የማይሉበት ክልክል ቦታ ሆኗል፡፡

የሰሜንአፍሪካ ጎዳናዎች በወጣቶች በተሞሉበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን ለዚህ አብዮት ሞተር ከሆነው የማህበራዊ ሚዲያ ጋር የነበራቸው ትውውቅከአሁን ካለው አንጻር አነስተኛ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ህዝቡ ውስጥ የነበረው የኢኮኖሚ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመባባስ ውጭ የተለየመፍትሄ አልተሰጠውም፡፡ የህዝብ አገልግሎት ከመቆራረጥ ወደ መጥፋት በመሸጋገሩ ህዝብ በራሱ ሰላማዊ ሰልፍ እስከመውጣት ደርሷል፡፡የሽሮ ሜዳ ነዋሪዎችን ያስታውሷል!

ቡርኪናፋሶውስጥ ስርዓቱን በሁለት ቀን ያስወገዱት ወጣቶች ከ1500 አይበልጡም፡፡ ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ በተቃውሞ ጎራ ያለው ሳይጨምርአርብ አርብ መስጊዶችን በተቃውሞ ሲሞሉት የታዩት ሙስሊሞች ብቻ ለውጥ ሊያመጡ እንደሚችሉ የሚያጠራጥር አይሆንም፡፡ ተቃዋሚዎች የተበታተኑናየፋይናንስ አቅም የሌላቸው በመሆናቸው ኢትዮጵያ ካለው የተቃዋሚ ሁኔታ የተለየ ነገር አይታይባቸውም፡፡ ሆኖም ሰላማዊ ሰልፍም ሆነስብሰባ የማድረግ፣ በሚዲያዎች ሀሳባቸውን በመግለጽ ከኢትዮጵያ የተሻለ አጋጣሚ ነበራቸው፡፡

የቡርኪናፋሶውገዥ ፓርቲ 27 አመት ሲቆይ ህዝብ ደስተኛ ሆኖ አይደለም፡፡ ከዚህ ይልቅ ከኢትዮጵያው ጋር የማይነጻጸር ቢሆንም ከምዕራባውያን ጋርባለው ግንኙነትና በፈርጣማ ክንዱ ስልጣን ለማስጠበቅ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል፡፡ በእነዚህ ሁሉ አመታት ህዝብ ደስተኛ ባይሆንምበሁለት ቀን ይህን ያህል ለውጥ ያመጣል ብሎ የገመተው ግን አልነበረም፡፡ የቡርኪናፋሶ ሁኔታ አፈናም ሆነ በምዕራባውያን ተላላኪነትራሱን ለማቆየት የሚጥር ስርዓት በህዝብ ኃይል በአጭር ጊዜ ሊሸነፍ እንደሚችል የቅርብ ጊዜ ምስክር ሆኗል፡፡ በተቃውሞው ጎራ ድካም፣በአፈናው ብዛት እስካሁን ቡርኪናፋሶውያን ያገኙትን መብትና ጥቅም ማግኘት ያልቻለው የኢትዮጵያ ህዝብ በስርዓቱ ላይ ይህ ነው የሚባልጫና ሊያደርግ እንደማይችል የሚገምቱት ብዙዎቹ ናቸው፡፡

ነገርግን ሙስሊም፣ ክርስቲያን፣ መምህራን፣ መከላከያ ሰራዊት፣ የራሱ አባል ድርጅቶች ጋር መስማማት ያልቻለው የኢትዮጵያ ገዥው ፓርቲምበህዝብ የሚፈተን ለመሆኑ ትናንት እነ ጋዳፊ፣ እነ ሙባረክና ቤን አሊ ላይ ከታየው ባሻገር የዛሬው የቡርኪናፋሶው ህዝብ ድል ትልቅምስክርነት ይሰጣል፡፡ በቱኒስ የተነሳው ለውጥ ከቱኒዚያ ከተሞች አልፎ የግብጹን ታህሪር፣ ትሪፖሊና ሌሎች የሊቢያ ከተሞችን እንዳጥለቀለቀው፣ስርዓትም እንደለወጠ ሁሉ ኡጋዱጉ ከሚገኘው ፓርላማ የተነሳው እሳትም አገሪቱ ውስጥ የነበረውን የስርዓቱ ቆይታ አውድሞታል፡፡

ጽሁፉንበእስክርንድ እንደጀመርኩት በእሱው መደምደሚያ መጨረስ ወደድኩ! ‹‹በሰሜን አፍሪካው አብዮት እንቅስቃሴዎቹ የተቀጣጠሉት በዋና ዋናከተማዎቹ ነው፡፡ እኛ አገርም ቢሆን ተመሳሳይ ነው የሚሆነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ የሚፈጠር ለውጥ አጠቃላይ የአገሪቱን ፖለቲካዊሁኔታ ይቀይራል፡፡... ውሃ በ99ንኛው ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው የሚፈላው፡፡ እስከዛ ድረስ ምንም አይነት ለውጥ አይታይበትም፡፡ ውሃየሚያፈላ ሰው 99 እስኪደርስ ድረስ ማህል ላይ ተስፋ ቆርጦ ሊተውው ይችላል፡፡ ግን 99 ዲግሪ እስኪደርስ ድረስ የራሱ የሆነ የማይታይለውጥ ያደርጋል፡፡ ተስፋ ያልቆረጠ በአንድ ዲግሪ ለውጡን ያየዋል፡፡››

ኦጋዱጉላይ ተስፋ ያልቆረጡት 1500 ወጣቶች የለውጡን የመሞቂያ ነጥብ ቀይረውታል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ኡጋዱጉ ላይ ካለው የከፋ ችግርቢኖርም እስካሁን 99 ዲግሪ አልደረሰም! ይህ የመፍያ ነጥብ፣ የኡጋዱጉው ውሽንፍር፣ ከአረቡ ይልቅ ለኢትዮጵያ ይቀርባል የሚባለውየጥቁር አፍሪካ ‹‹ጥቁሩ አብዮት›› ወደ አዲስ አበባ መቼ ይደርሳል የሚለውን ለጊዜውም መገመት የሚቻል አልሆነም፡፡ ግን ጭቆናበተትረፈተፈበት አገር ለውጥ ተፈጥሯዊ ነውና ነገ፣ ሳምንት፣ የዛሬ ወር፣ አመት... መከሰቱ ግን የማይቀር ነው፡፡ ገዥዎቹ ለለውጥዝግጁ እስካልሆኑ ድረስ ቁጥሩ አንድ ሺህም ሆነ ሚሊዮን የለውጡን ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚቀይረው ሳይታሰብ አደባባይ ላይ የሚገኘውህዝብ ነው!

5 comments:

  1. መልካም ቀን ሁሉም,

      አስቸኳይ ብድር ይፈልጋሉ? አሁን የብድር ክፍያ አማካሪ አነጋግሩ, ብድር ከ 2.5% ጋር. ቀላል, ፈጣን እና የተረጋገጠ ብድር ግብይት ነው.

    የመገኛ አድራሻ:

    EMAIL: nortionloanconsultant@gmail.com

    ቴሌፎን: +17815611941

    WHATSAPP: +2347067093957

    ሊታመኑ የሚችሉ የብድር ልውውጥ

    ReplyDelete
  2. መልካም ቀን,

      አፋጣኝ ብድር ፈልገዋል? ለቀጣይ ሂሳብዎ UNICREDIT በጣም ፈጣን አሁኑኑ ይገናኙ. በጣም ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው.

    የመገኛ አድራሻ:

    EMAIL: unicreditfastloan@gmail.com

    ቴሌፎን: +17815611941

    WHATSAPP: +2347067093957

    ሊታመኑ የሚችሉ የብድር ልውውጥ.

    ReplyDelete
  3. ሰላም,

    የእርስዎን የፋይናንስ ፍላጎት ለመፍታት አስቸኳይ ብድር ይፈልጋሉ? ከ 2,000.00 እስከ 100,000,000.00 የሚደርስ ብድር እንሰጣለን, በዚህ የማስተላለፍ ጊዜ ውስጥ ምንም የብድር ማረጋገጫ እና ምንም የብድር ፍሰት ባለመኖሩ አረጋጋጭ, ፈጣን እና ተለዋዋጭ ነን.

        ሁሉንም ብድሮች እና ያለምንም ቅድመ-ክፍያ በ 3% የወለድ መጠን ሁሉንም የምንዛሬ ብድር ሰጥተነዋል ... በዚህ ኢሜይል አማካኝነት ወደኛ መመለስ የሚፈልጉት.


    እባክዎ ፍላጎት ካሳየን በ (Zekoceanfinance1@gmail.com) በኩል ይመለሱ
                                                                    zekoceanfinance@gmail.com



    ከሰላምታ ጋር,

    ሚስተር ላንላዛር ማርከስ

    zekoceanfinance@gmail.com
    zekoceanfinance1@gmail.com

    ReplyDelete
  4. Témoignage d'un prêt entre particulier que je viens d’acquise chez Mme Laurence ,vraiment j'ai risquer ma vie pour trouver mon bonheur. Si votre demande de crédit est acceptée, chez Mme Laurence Nathalie BERTIER vous recevrez un e-mail : laurancebertier@gmail.com pour vous en informer et vous demander de signer électroniquement votre contrat de prêt.
    Vous recevrez alors la somme d’argent directement sur votre compte bancaire dans les 48h ; le libellé du virement contiendra (en général) Voici mon parcours que j'ai fais avant de trouver mon prêt des 45.000 euro.
    Vraiment pour tout vos besoins financièrement je vous pris de la contactez afin qu'elle puisse vous aider à résoudre vos problèmes. Voici son Email: laurancebertier@gmail.com

    ReplyDelete
  5. Nouvelle rentrée scolaire, témoignage 2023


    Je vie avec des douleurs horribles mais tant que je suis en vie j'ai envie de me battre.
    Cette année j'ai décidée de chercher un moyen de travailler pour que mon fils commence bien la rentrée scolaire je ne sais pas encore comment faire mais je trouverais.
    Aujourd'hui mon soucie c'est que j'ai besoin d'une voiture pour handicapée
    Grâce a Dieu Madame THALIA CLAUDINE CATOR nous aidez, Nous tenons à vous remercier pour l’aide que vous apportez à mon enfant David. Lorsque le grand-père de David vous a contacté, vous avez été très à l’écoute.
    pour mon enfant nous avons obtenu un pret de 5,000€ pour sa rentrée scolaire et pour d'autre achat mon enfant et moi son très heureux je vous conseille de faire le bon choix afin de ne pas tomber sur les faux du net. veuillez donc le contacter pour eviter les arnaques.

    Merci à tous ceux qui témoignent d'elle; elle est une référence. vous pouvez sans crainte la contacter sur son

    e-mail: thalyacator@gmail.com



    Pour tout cela je vous remercie sincèrement.

    Meilleures salutations,

    ReplyDelete