በዮናታን ተስፋየ
አንዳንዴ ለምን ለኢህአዲግ የምንመች ሁነን እንደምንቀርብ አይገባኝም . . . እንትና ተሳደበ . . . እንትና እንዲህ አለ . . . ያተባለ እዲህ ተባለ . . . ዘራፍ አካኪዬዋ . . . ለምን ስቦ በሚሰጠን ካርድ እንደምንጫወት አይገባኝም??! ለምን ንቅናቄያችንን አጥበን እንድንቀሳቀስ መጫወቻ ሲጥልልን እንደህፃናት ተሻምተን አንደምንቦርቅ ግራ ነው . . .
እዚህ ሀገር ላይ እኮ ያልተሰደበ የለም . . . ያልተዋረደ የለም . . . ሀገራችን እኮ ከረከሰች ከራረመች . . . በተለይ አማራ ተብሎ የተፈረጀው 22 ዓመት ሙሉ እንዲሸማቀቅ አንገቱን እንዲደፋ ያልተባለው የለም . . . ሌላውም እንደዛው ደቡቡ በሉት ኦሮሞው በሉት ሌላ ሌላውም ቀና ብሎ እንዳይሄድ ለማድረግ ያልተባለው ነገር የለም . . . ባጠቃላይ ህወሓት ኢትዮጵያን ለማጥፋት የኢትዮጵያዊነት ኩራት በሆኑ መልካም ትምክህቶቻችን ላይ የዘመተው እኮ ገና ከጫካ ሳይወጣ ነው! . . . ህወሓት የዚህችን ሀገር ህዝብ አሸማቆ ክብሩን አሳጥቶ ተመቻምቾ መግዛት እንደሚፈልግ እኮ ገና በእንጭጭነቱ የተለማመደው ነገር ነው!!! ታዲያ አሁን ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ . . .?!
ሀገር ፈርሷል . . . አንድነት ሳስቷል . . . ህዝብ ተሰዷል . . . ህዝብ ተገድሏል . . . ህወሓት የሀገር ጭራ አድርጎናል . . . ኢትዮጵያችንን ከክብሯ አሳንሶ አዋርዶናል ዓለም ንቆናል እድሜ ለህወሓት . . . አዲስ ነገር የለም!
የሚገርመው ግን ዝም ብለን አሁንም ለመገዛት መመቸታችን ነው! የህወሓትን ፀባይ ገና አልተረዳነውም! ዋና ምንነቱን ሸሽጎን በእሾህ እየወጋ ነድፎ እያሳበጠ ደግሞ ያተነፍሰናል! እኛም እየተንጫጫን ተባዩን ከማጥፋት ቁስላችንን እየነካካን ተስማምተነዋል!!! ከሰደበኝ የነገረኝ ሆነ እኮ ነገሩ . . . መንገሩንስ ንገሩን ይሁን ግን የህወሓትን ቁማር አጫዋች መሆናችን ከስድቡ ይልቅ ያማል! ይንጫጩ ብሎ የሆነ ነገር ሲለጥፍ እሷን ይዞ ሰደዶ . . . ዘይገርም ነው! አንዳንዴ 23 ዓመት ሙሉ የት ነበርን ያስብላል! ተብሎ ተብሎ እኮ የህወሓት ስነምግባር የጎደለው መረን የለቀቀ ባህርይው እንደሆነ የታወቀ ነው!
የችግሩን መሰረት ትተን ቅርንጫፉ ላይ ስንረባረብ እንደሚገረዝ ተክል ህወሓት ወድቆ እንዳይበሰብስ - እንዲያቆጠቁጥ እድሜውን እያረዘምንለት ነው! እኛም ምሳራችን ዶልዱሞ ከስር ቆርጠን እንዳንጥለው እየደከምን ነው! እስቲ ሰዎች እንመከር! ለኢህአዲግ አንመቸው!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
No comments:
Post a Comment