የህወሀት መስራችና የረጂም ግዜ መሪ የነበረዉ ዘረኛዉ መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት በተለየ በስምንት ወሩ ባለፈዉ መጋቢት መጨረሻ ላይ ይፋ ሆኖ የተመሰረተዉ የመለስ ፋውንዴሽን ከህዝብ ያገኛል ተብሎ የተገመተዉን የገንዘብ መዋጮ የሩቡን ግማሽም አለማግኘቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በሰልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገለጹ፡፡ በመለስ ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 781/2005 መንግስታዊ ተቋም ሆኖ የተመሰረተው ይህው ፋውንዴሽን ቤተመጻህፍትና ሙዚየም ለማቋቋም በማሰብ ሕዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ በየቀኑ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ቅስቀሳ ከተጀመረ ከአምስት ወራት በላይ ቢቆጠርም እየተዋጣ ያለው ገንዘብ እጅግ አነስተኛ መሆኑ ታውቋል፡፡
ህዝብ በያለበት ለመለስ ፋዉንዴሺን የገንዘብ መዋጮ ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆነዉ ፋውንዴሽኑን በበላይነት የምትመራዉና የሙስናዋ እመቤት በመባል የምታወቀዉ አዜብ መስፍንና ሟቹ ባለቤቷ ከህዘብ ዘርፈዉ በውጪ አገር ባንኮች ከፍተኛ ገንዘብ ማከማቸታቸዉን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና በውጪ አገር የሚገኙ የኢትዮጽያ መገናኛ ብዙኋን በተደጋጋሚ በመዘገባቸዉ እንደሆን ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸዉ። ከዚህ በተጨማሪ አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛና የግሉ ዘርፍ ለህዳሴዉ ግድብ ገንዘብ እያዋጡ መሆናቸዉና ህዝቡ መለስ ዜናዊን ለመሰለ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ለረገጠዉ ጨቋኝና ከፋፋይ ሰዉ የገንዘብ መዋጮ ማድረግ ባለመፈለጉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። የአዲሰ አበባ ምንጫችን ጨምሮም እንደገለጸዉ መዋጮው በውዴታ በባንክ ገቢ የሚደረግና ለጋሹ ስሙን ከማስመዝገብ በላይ መስጠትና አለመስጠቱ የማይታወቅ በመሆኑ ከፍተኛ የግንባሩ ካድሬዎችና ራሳቸውን የኢህአዴግ ደጋፊ ባለሃብቶች ነን የሚሉት ሳይቀሩ ለመዋጮው እጃቸውን አለመዘርጋታቸው መረጃው ያሳያል።
No comments:
Post a Comment