Saturday, November 9, 2013

ተሻሻለ የተባለዉ የመከላከያ አዋጅ የአንድ ብሄር የበላይነቱን ማረጋገጡ ታወቀ

የአገሪቱን የመከላከያ አዋጅ ተመልክቶ መሻሻያ ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ የወያኔ ፓርላማ ተቋሙ የሚታይበትን ዋናዉንና ትልቁን ችግር ሳይመለከት ወያኔን የሚጠቅሙ ህጎችንና ደንቦችን ብቻ በማሻሻል የይስሙላ ስራ ሰርቶ ተበትኗል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸዉ የመከላከያ፤ የደህንነት፣ የህግ፣ የፍትህና የአስተዳደር ጉዳዩች ቋሚ ኮሜቴዎች ሰሞኑን ተወያይተዉ በወሰዱት እርምጃ 98 መቶ የሚሆኑት የአገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ከአንድ ብሄር ብቻ እንዲሆኑ መንገድ በከፈተዉ መዋቅራዊ አሰራር ላይ ምንም አይነት መሻሻል ወይም ለዉጥ አለማድረጉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው መኮንኖች ተናግረዋል። አንዳንድ የመከላከያ ሚኒስቴር ሹሞች የተሻሻለዉ አዋጅ እስከ ዛሬ የነበሩትን ህጎች ሁሉ የሚለውጥና መከላከያን የሚያሳድግ ነው ቢሉም ይህ በቻይናና በእስራኤል ህጎች ላይ ተንተርስሶ የተደረገዉ መሻሻያ መሰረታዊ የሆነውንና ወያኔ ሆን ብሎ ያዋቀረዉን የመከላከያ አወቃቀር እንዳይነካ መደረጉ ታውቋል።

ወታደራዊ ማእረግ እድገትን፣ ለመኮንኖች የሚሰጠዉን መኖሪያ ቤትና የሞት ቅጣት አፈጸጻምን በተመለከተ ለየት ያለ ትኩረት እንዲደረግባቸዉ አጥብቀዉ ያሳሰቡት የፓርላማዉ አባላት መሰረታዊ የሆነውንና አገሪቱን በማበጣበጥ ላይ ያለዉን በህወሀት የበላይነትና በዘር ላይ የተመሰረተዉን የመከላከያ አደረጃጀት እንዲቀየር ምንም አይነት ሙከራ ሳያደርጉ ወይም ሳይጠይቁ አይናቸዉን ጨፍነዉ አልፈዉታል።

ረቂቅ አዋጁን የተመለከቱ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች አዋጁ መከላከያን ከአገር ይልቅ የአንድ ፓርቲ አገልጋይ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ በየበረሃዉና በሰው አገር የሚንከራተተውን ተራውን ወታደር የሚጠቅም ምንም ነገር የለውም ሲሉ ትችታቸዉን ሰንዝረዋል። ፓርላማዉ የተነጋገረበትንየመከላከያ ረቂቅ አዋጅ የታማዦር ሹሙ/ጀኔራል ሳሞራ የኑስ፤ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ብርጋዴል ጀኔራል ዘውዱ፤ የ44ኛ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሬጅመንት ዋና አዛዥ ሊተናንት ኮሎኔል አዘዘው መኮንን፤ በሱዳን የተመድ የሰላም አስካበሪ አዛዠ ሌተናልት ጀኔራል ዮሀንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም፣ የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሌተናልት ጀኔራል ሳእረ መኮንን፣ የማእከላዊ እዝ አዛዥ ሌተናት ጀነራል አበበው ታደሰ ፣ሜጀር ጀነራል ሞላ ገብረማርያም እና አቶ ፀጋየ በርሄ ውይይት አድርገውበት ረቂቅ አዋጁን መደገፋቸዉ ታዉቋል። ይቀጥላል።

No comments:

Post a Comment