Saturday, November 9, 2013

ወያኔ በ2007ቱ ምርጫ እንዲያጅቡት ጠፍጥፎ ከሰራቸው ድርጅቶች ጋር በግምገማ መወጠሩ ተሰማ

በወያኔው ምርጫ ሊሳተፉ የሚችሉ ሰላማዊ ፓርቲዎች መሳሳብና ትብብር ከመጠን በላይ ያስደነገጠው ወያኔ በራሳቸው መቆም የተሳናቸውንና እህት የሚላቸውን የኦሮሞውን ኦህዴድ፣ የአማራውን በአዴን፣ እንዲሁም የደቡቡን ደህዴን ዳዴ ወፌ ቆመች እያለ መቆም እንዲችሉ እያለማመደ መሆኑ ከያቅጣጫው እየተሰማ ነው። ፋሽስት ወያኔ እነዚህን ዘርን መሰረት አድርገው የተቦደኑ ጉጅሌዎች መጀመሪያውኑ ሆን ብሎ ከሰባበራቸው በሗላ ለምን እንደገና ቀና ለማድረግ እንደሚደክም ለብዙዎች ግልጽ አይደለም። ሆኖም ግን ከሌላ አቅጣጫ የሚሰማው ደግሞ ወያኔ በነዚህ ቡድኖች ውስጥ እያደረገው ያለው ይህ ሁሉ ግምገማና ማስፈራራት መጪውን ምርጫ በዚያም በዚህ ብሎ እስከሚያሸንፍ ድረስ ብቻ ነው ከዚያ በሗላ እንደገና ሰባብሮ አጣጥፎ መደርደሪያ ላይ ይሰቅላቸዋል ይላሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለይ በኦህዴድ እየተከናወነ ያለው ግምገማ ከታችኛው እስከ ላይኛው የአመራር አካላቱ በሙስና የተጨማለቁ በመሆናቸው መፈራራት የሌለበትና ቀልድ ነው ተብሏል። ከዚህ በፊት ከነበረው የወያኔ ልምድ እንደሚታወቀው፤ የወያኔ ግምገማ ታዛዥነትን ለማረጋገጥ ስለሆነ እየነቁ ነው የተባሉትን በማስወገድ የበለጠ ታዛዦችን ቦታ በማስያዝ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment