
ሌላጫው የጊዜው ተጎጅ ደግሞ፤ ”የፋሽስት ወያኔ አጋዚ ጦር ባለ በሌለ ሃይሉ ሕዝቡን ጨፈጨፈው ራሱ ባመነው እንኳ ወደ ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰላማዊ ሰልፈኞች አለቁ። ዘለው ካልጠገቡት ህጻናት እርዳታ እስከሚያስፈልጋቸው አእሩጋን ሁሉንም አጨዳቸው። ይህም ሁሉ ከሆነ በሗላ እርምጃው ከመጠን ያለፈ አልነበረም ተባለና ታለፈ። ጊዜ ጉዞውን አላቆመም ስምንት ዓመት አስቆጠረ ወያኔም ግድያውን አላቆመም። የንጹሃን ወገኖቻችንን ደም በግፍ ያፈሰሱት ሳይጠየቁ ፋሽስት ወያኔ ግን ለሌላ እርድ ለሌላ ጭፍጨፋ ራሱን እያዘጋጀ፣ ቢላውን እያፋጨ ይገኛል” ካሉ በሗላ ”እኔ እምለው፣ በእርግጥ እኔ አቅም የለኝም ሽማግሌ ነኝ። ግን ግን ልጆቻችንን፣ ወንድም እህቶቻችንን ዐይናችን ስር ከጨፈጨፈ አረመኔ ቡድን ጋር አብሮ ተባብሮ መስራት መልካም ነው እንዴ? ይላሉ።
ምንም እንኳ በአካል የተጎዱትን ሳይጨምር እስከ ሁለት መቶ የሚሆኑ እንደተጨፈጨፉ ቢገለጽና ፋሽስት ወያኔ ቢያምንም እርምጃው ካቅም በላይ አልነበርም በሚል ሰበብ ብቻ እስካሁንም ከዚህ የግፍ ግድያ ጋር በተያያዘ ማንም እንዳልተጠየቀ የታወሳል። ይህ ሁሉ ግፍ ተደብቆ የሚቆየው ግን ኢትዮጵያ ለሕዝቦቿ የሚጨነቅ፣ በህግ የበላይነት የሚያምን እውነተኛ ኢትዮጵያዊ መሪ እስክታገኝ ድረስ ብቻ ነው የሚሉ ግን ጥቂቶች አይደሉም።
በሌላ በኩል ደግሞ ዛሬም መብታቸውን በሚጠይቁ ግለሰቦች ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወይም አባላት ላይ፣ የፋሽስት ወያኔ አሽከር አንሆንም በሚሉ ጠንካራ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና መጎሳቆል ቀጥሏል። አሁን በቅርቡ እንኳ በአንድነት ፓርቲ የአመራር አባል ላይ የደረሰው ለመናገር የሚሰቀጥጥ፣ ከህግ ውጭ የሆነና ከባህል ያፈነገጠ በየትኛውም ሃይማኖት ተቀባይነት የሌለው የግፍ ድርጊት በወያኔ ባለጌ የደህንት ሰው ተብየዎች መፈጸሙ ሕዝባችንን በከፍተኛ ሁኔታ እያነጋገረ መሆኑ እየታየ ነው።
No comments:
Post a Comment