Saturday, November 30, 2013

Ethiopia most restrictive Sub Saharan Country, Freedom House reports 2013

Ethiopia has one of the lowest rates of internet and mobile telephone penetration in the world, as meager infrastructure, a government monopoly over the telecom sector, and obstructive telecom policies have notably hindered the growth of information and communication technologies (ICTs) in the country. Despite low access, the government maintains a strict system of controls over digital media, making Ethiopia the only country in Sub-Saharan Africa to implement nationwide internet filtering. Such a system is made possible by the state’s monopoly over the country’s only telecom company, Ethio Telecom, which returned to government control after a two-year management contract with France Telecom expired in December 2012. In addition, the government’s implementation of deep-packet inspection technology for censorship was indicated when the Tor network, which helps people communicate anonymously online, was blocked in mid- 2012.

Thursday, November 28, 2013

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!

በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንምመከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።

ወያኔ ስላልቻለ ነው እንጂ ይህንን ከአለም አጽናፍ እስከ አለም አጽናፍ ያስተጋባ የወገን ደራሽ ድምጻችንን አዲስ አበባ ላይ እንደ አደረገው በሃይል ለማፈን ወደኋላ አይልም ነበር።

ሀፍረት የለሾቹ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ይህን የተጋለጠ ሀገርና ህዝብ አዋራጅ ተግባራቸውን እና በውሸት የተበከለ ገመናቸውን ለመሸፈን ከዚያም አልፈው የዋሆችን በማታለል የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የተለመደ ቲያትር መስራቱን ተያይዘውታል። ቴዎድሮስ አድሃኖም ችግሩ ባለበት በሳውዲ መሬት ላይ ሳይሆን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በራሱ ወጪ አሳፍሮ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ባፈሰሳቸው ኢትዮጵያውያን መሃል እየተጎማለለ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ቲያትሩን ሲሰራ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይታይበትም።

እነዚሁኑ ወደ ሀገር የተመለሱ አእምሯቸው በችግር የተመሰቃቀለ ዜጎች ወደ ካሜራ እየገፉ ስለ ሳውዲ ኤምባሲያቸውና ስለመንግስታቸው ‘ድንቅ” አገልግሎት እንዲናገሩ ያስጠኗቸውን ተመሳሳይ አረፍተ ነገር መስማት የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ ተወዳዳሪ የሌለው ኮሜዲ ይወጣው ነበር።

እውነቱ ዛሬ በሀገራችን የሰፈነው ስደትና አብሮት የሚመጣው መከራ ሁሉ ዋናው አምራች ፋብሪካ ወያኔ መሆኑ ነው። ወያኔ የገነባው ጥቂት ጀሌዎቹንና ሎሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደረገው ስርአት ነው። የስደታችንና የመከራችን ምንጭ ስደት የሚመጣው በሀገር ተስፋ መቁረጥ ነው። እንጀራ ፍለጋና ጭቆናና አፈና ሽሽት አምልጠን በየባዕድ ሀገሩ እንድንከራተት የሚያደርገን የወያኔ ስርአት ነው። በታሪካችን ውስጥ ተሰደን በባዕድ የተዋረድነው በወያኔ ምክንያት ነው።

በሀገር ውስጥ በአፈና ስር ሆናችሁ፣ በውጪው አለምም በየኢምባሲው የምታሰሙት ጩኸትና የምታፈሱት እምባ እብሪትና ትእቢት ያደነደነውን፣ ዝርፊያ ያደነዘዘውን የወያኔን ልብ እንደማያሸብረው ማወቅ አለብን።

የወያኔ ሹማምንቶች ይግረማችሁ ብለው ከአላንዳች ሀፍረት ያውም በሳውዲ አረቢያ ወጪ ተጓጉዘው ሀገር የገቡትን ግራ የተጋቡ ስደተኞች ለፖለቲካቸው ማሳመሪያ በቴሌቪዥን ስእልና ፎቶግራፍ መነሻ ሲያደርጉትና ለፖለቲካ ስራ መሳሪያ ሲያውሉት እያየን ነው። በነሱ ቤት ብልጥ ፖለቲከኞች መሆናቸው ይሆናል። በኛ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ መሆናቸውን ግን ፈጽሞ አይሰማቸውም።

ወያኔ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው ለፍተው የሚኖሩት ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ያውቃል። ቢያንስ በየኢምባሲው ያስቀመጣቸው ነጋዴዎች ይነግሩታል። ችግሩን እንዳላየና እንዳልሰማ የሚያየው ከዜጎች ይልቅ እነሱ አፈር ግጠው ለፍተው ለሚያመጧት የውጪ ምንዛሬ የበለጠ ፍቅር ስላለው ነው። በዚህ ተግባሩ ወያኔ ወገኑን የሸጠ ባሪያ ፈንጋይ ነጋዴ እንጂ የመንግስት መሪ መሆኑ ያጠራጥራል።

ግንቦት 7 የፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ይህ የዜግነትና የሀገር ውርደት፣ ይህ ሁሉ የወገን መከራ የሚቆመው የዚህ ሁሉ መሰረት የሆነው ወያኔና ስርአቱ ከመሰረቱ ሲነቀልና ሲወገድ መሆኑን ላፍታም አይዘነጋውም።

እንባችን የሚደርቀው ደማችን በየቦታው መፍሰሱ የሚቆመው መብታችን እንደዜጋ ተከብሮ ቀና ብለን የምንሄድበት ሀገር በትግላችን የተቀዳጀን ጊዜ ብቻ ነው።

ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ በያላችሁበት ግንቦት 7 ሁኑ!! እኛ ከዚህ ውርደት ሞቶ የሚገኘው ነጻነት ይሻላል ብለን የተነሳን ልጆቻችሁ ነን። እርሰዎስ?

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Tuesday, November 26, 2013

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ

የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/


የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋሕነን/ በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የወያኔው 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፈለ/ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራ  ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል።

በሕዳር 13/2006 ዓ.ም የኢሕአግና የጋህነን ሰራዊት በወሰዱት ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት 66 /ስልሳ ስድስት/ ገድለው 113 /አንድ መቶ አስራ ሶስት/ በማቁሰል እንዲሁም ቁጥራቸው የበዛ የጦር መሳሪያዎችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርከዋል።

ሁለቱ ድርጅቶች በጋራ በተለያየ የትግል መስክ ሲተጋገዙና ሲተባበሩ ቆይተዋል የግንኙነታቸውን እድገትና ለውጥ የሚያሳይ ወታደራዊ ጥቃትም ፈፅመዋል።

ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘውና የሚፈልገው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ስምምነትና አንድነት መገለጫ ሊሆን የሚችል አኩሪ ጥቃት መሆኑ ይታመንበታል ። በጥቃቱ የተካፈሉ የሁለቱ ድርጅቶች ታጋዮች እንዳብራሩት ዛሬ በጋራ የጀመርነው ወታደራዊ ጥቃት በዚሁ የሚያበቃ ሳይሆን የጋራ ዓላማና ራዕይ እስካለን ድረስ ወደኋላ የማይቀለበስ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህም አክለው የዚህ ወታደራዊ ዘመቻ ዓላማ አገር እንደሌለው ሁሉ በሰው አገር ፍዳውን እያየና እየተሰቃየ እንዲሁም ለሞት እየተዳረገ የሚገኙውን በሳውዲ አርቢያ ለተፈፀመው በደል ለመበቀልና ሕዝባዊ ወገንተኝነታችንን ለማሳየት ታስቦ የተወሰደ ወገናዊ እርምጃ ነው በማለት አብራርተዋል።

በውጊያው ከሞት ተርፎ ለከባድ ቁስልና የአካል ጉዳት የተዳረገው የወያኔው ቅጥረኛ የ24ኛ ክፈለ ጦር አባላትን ከሁመራ አንስቶ እስከ ትግራይ የሕክምና ማዕከሎች ማጋጋዝ ዋነኛ ተግባሩ ሆኗል።

ይህንን የጀግና ጥቃትና ድል የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ሰራዊቱን እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ በመቀበልና ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ አጋርነቱን ያስመሰከረ ሲሆን የተጀመረው ወታደራዊ ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እንዲደገም ያላቸውን ልባዊ ምኞት ገልፀው በንፁሃን ላይ ያለ አግባብ ሲወሰድ የነበረው የቅጥረኞች እርምጃ አንጀቱ ላረረው ሕዝብ እምባ ያበሰ እንደሆነም ተናግረዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ ኢሕአግ/ እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋህነን/ ወያኔ ለ22 ዓመት ያህል አገሪቷን ሲበዘብዝና ሕዝቡ የዲሞክራሲያዊ መብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን በሃይል የመግዛቱ ሂደት እንዲያከትም የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠው መነሳታቸውን አስታውቀዋል።

ምንጭ፡ ethsat.com/amharic/


ዶክተር ብርሃኑ ስለ ሚዲያ ጥቅም ይናገራል


በሽብርተኝነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!

በቅዱስ ዮሃንስ

ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ሁለት ጥቅም ያስገኝላቸዋል፡፡ አንደኛ በፀረ- ሽብርተኝነት ስም ከምዕራባውያን ኃያላን ጎን በአጋርነት በመቆማቸው በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት (ለምሳሌ በመሣሪያ፣ በፖለቲካ ድጋፍ) ዳጎስ ያለ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ ሁለተኛ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም የሚያወጡት ሕግ የውስጥ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቃት የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ሽፋን ይሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ነው ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ከሰማይ የወረደ የተቀናቃኝ ማጥቂያ መሣሪያ ነው የሚባለው፡፡ ይህንን ያልኩበት አብይ ጉዳይ ዛሬ ሃገራችንንና ህዝቧን እያስጨነቀ ያለው የወያኔ አገዛዝ የፀረ ሽብርተኝነት ህግን ከለላ በማድረግ በሰላማዊ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣ፤ እጅግ የከፋ ደረጃ በመድረሱ ነው።

በሰላማዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ የመንግስት ለዉጥ ለማምጣት የሚታገሉ ሰላማዊ ዜጎችን አግባብ ባልሆነና ባልተጨበጠ ክስና ዉንጀላ ማሰር፣ አፍኖ መሰወር፣ ንብረትን ማዉደምና መዉረስ እንዲሁም የአደባባይ ግድያ ባለፉት 22 የወያኔ  የአገዛዝ ዘመናት የተለመዱ ተግባሮች ሆነዉ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ ይህ አምባገነናዊና ኢፍትሀዊ ተግባር በህግ ሽፋን ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለገዥዉ ስርአት የአፈናና የጥርነፋ መዋቅር ተባባሪ ያልሆኑና ለመብታቸዉ መከበር የሚታገሉ ዜጎች በአሸባሪነት ስም በጅምላ እየታፈሱና እየታሰሩ ይገኛሉ። ታፍነዉ የተወሰዱና ያሉበት ቦታ የማይታወቀዉም ጥቂቶች አይደሉም። ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሽብርተኝነት ተወንጅለዉ ታስረዋል። ሰብአዊ መብታቸዉም በማንአለብኝነት እየተረገጠ ይገኛል። ከነዚህ ንፁሀን ዜጎች ዉስጥ ብዙዎቹ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላቶች፤ የእምነት መሪዎችና ለሞያቸዉ ታማኝ የሆኑ ጋዜጠኞች መሆናቸዉን ስናይ ደግሞ ዘመቻዉ በሀገራችን ተጠናክሮ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል ለመጨፍለቅና ህዝብን ከትክክለኛ መረጃ አርቆና አፍኖ ለመግዛት ታስቦበትና ሆነ ተብሎ የተያዘ ስልት መሆኑን ግልፅ ነው።

በሽብርትኝነት ያለመከሰስ መብቱን በጠመንጃ ያስከበረው ወያኔ ግን ሰላማዊውን ህዝቡ በተለያዩ መንገዶች  እያሸበረ የስልጣን ቆይታውን ለማርዘም ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ዜጐችን በማፈናቀል፤ በእምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባትና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በመከፋፈል እያፋጀ የሽብር ሴራውን እየፈፀመ ይገኛል። ሰላማዊ ዜጋውን ፣አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን በልማት ስም ተወልዶ ባደገበት እትብቱ ከተቀበረበት ሃገር እያፈናቀለ ለስደት እየዳረገው ይገኛል፡፡ ለዚህም የሽብር ሴራው ሰለባ የሆኑት፤ የሚበሉት፤ የሚጠጡት እና በመጠለያ እጦት በየአደባባዩ ሰፍረው የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ የሚገኙት የአማራ ብሔረሰብ ወገኖቻችን ናቸው፤ እነዚህ ወገኖቻችን በሃገሪቱ አራቱም ማዕዘናት እየተፈናቀሉና እየተዋከቡ ይገኛሉ። ማፈናቀለ አልበቃ ያለው የወያኔ የሽብር መረብ ወደ እምነት ቦታዎችም በመዛመት ዋልድባን እና የተለያዩ የሃይማኖት ቦታዎችን በማፈራረስ በአለም ደረጃ እውቅና እና አድናቆት የተሰጣቸውን የሃገሪቱን የሃይማኖት፤ የታሪክ ቅርሶች በማውደም፤ ኢትዮጵያውያን በቀደምትነት በምንታወቅበት እምነታችን ላይ አደጋ በመፍጠር፤ አዋራጅ ድርጊቶችን በንቀት እና በጥላቻ እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ ከእምነት ቦታዎች ባሻገር በአለም ደረጃ እውቅናን ካገኙት ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ ተጠቃሹ የታችኛው አዋሽ እና ኦሞ ሸለቆዎች አንዱ ነው፡፡ ይህ ታሪካዊ ቦታ ያራዊቶች እና የተለያዩ የደኖች ስብስብ ያለበት ሰፊ የሃገራችን ቅርስ

ከአቶ ኃይለማሪያም መጠበቃችን ስህተት ነበር - ግርማ ካሳ

በሕገ መንግስቱ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ናቸዉ። የጦር ኃይሎች ኤታ ማጆር ሹምን፣ ተቀዳሚ ጠቅላይ ሚኒስትርን፣ የሚኒስቴር ካቢኔዎችን፣ የፌደራል ፖሊስ አዛዦችን … የመሾምና የመሻር ሙሉ ስልጣን አላቸው። ፓርላማዉን በትነው አዲስ ምርጫ መጥራትም ይችላሉ። ፓርላማው በፈለገ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴሩን አዉርዶ፣ ሌላ መሾም ይችላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተጠሪነታቸው ለፓርላማዉ ብቻ ነዉ።

የፓርላማ አባላት፣ በፓርቲያቸው ለእጩነት ቢቀርቡም፣ በሕዝብ የተመረጡ፣ ተጠሪነታቸው ለፓርቲዉ አመራር አባላት ሳይሆን፣ ለመረጣቸው ሕዝብ ብቻ ነዉ። በፓርላማዉ ካሉ 547 መቀመጫዎች ደግሞ፣ የሕውሃት አባል የሆኑት 38ቱ ብቻ ናቸው (6.9 በመቶ ብቻ)።

የአቶ መለስን ሕልፈት ተከትሎ፣ በሕጉ መሰረት፣ ፓርላማዉ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስቴር እስኪመርጥ፣ በወቅቱ ምክትል ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ አክቲንግ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ወዲያዉኑ መቀጠል ነበረባቸው። ነገር ግን የሕውሃት ሰዎች (አንዳንዶቹ የፓርላማ አባል እንኳን ያልሆኑ) «ኢሕአዴግ እንደ ፓርቲ ሳይወስን፣ አቶ ኃይለማሪያምን አክቲንግ ጠ/ሚ ማድረግ አይችልም» ብለው አቶ ኃይለማሪያም በምክትል ጠ/ሚኒስትርነት እንዲቀጥሉ አደረጉ። በሕገ መንግስቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴርን የሚሾሙት፣ የፓርላማ አባላት እንጂ፣ የፓርቲዎች ፖሊት ቢሮ አለመሆኑ እየታወቀ፣ ሕውሃቶች በዚህ ሁኔታ፣ ለስድስት ወራት አቶ ኃይለማሪያም ጠ/ሚ እንዳይሆኑ፣ ማከላከላቸው የሚያሳየዉ፣ ሕገ መንግስቱን በአፍጢሙ እንደገለበጡት ነዉ።

ከስድስት ወራት በኋላ፣ ሕወሃት፣ አቶ ኃይለማሪያም ጠ/ሚ እንዲሆኑ እያቅማማ ለጊዜዉ ተስማማ። ነገር ግን በአቶ ኃይለማሪያም አንገት ላይ ማነቆ ታሰረላቸው። ሶስት ምክትል ጠ/ሚ እንዲሾሙ ተደረገ። አቶ ደመቀ መኮንን፣ አቶ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል እና አቶ ሙክታር ከድር።

አቶ ደብረጺዮን እንደ ቴሌ ያሉትን መስሪያ ቤቶች ከመቆጣጠራቸዉ በተጨማሪ፣ የኢኮኖሚክና የፋይናንስ ዘርፉም በርሳቸው ስር እንዲሆን ተደረገ። በስልክ ፣ በኢንተርኔት የምንነጋገረዉን ሁሉ አቶ ደብረጽዮን ያዳምጣሉ፡፡ ባንኮችን፣ ቀረጥን የአገር ዉስጥና የዉጭ ንግድን የመዓድን እና የመብራት አገልግሎትን በሙሉ የሚቆጣጠሩትና የሚመሩት እኝሁ ሕወሃቱ አቶ ደብረ ጽዮን ናቸዉ።

ከትምህርት፣ ከጤና ፣ ከቱሪዝም ከመሳሰሉ ጋር የሚገናኙ መስሪያ ቤቶች ብቻ፣ ለአቶ ሙክታርና ለአቶ ደመቀ ተሰጡ። መከላከያ፣ ዉጭ ጉዳይና ደህንነት መስሪያ ቤቶች በአቶ ኃይለማሪያም ስር እንዲቆዩ ቢደረግም፣ ከታች ይቆጣጠሯቸው ዘንድ፣ አቶ ቴዎድሮስ አዳኖም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆነው ተሾሙ። ጀነራል ሳሞራ የነሱ የጦር ኃይሎች የኢታ ማጆር ሹም ፣ አቶ ጌታቸው ደግሞ የደህንነት ቢሮ ሃላፊ ሆነው እንዲቀጥሉ ተደረገ። ሁሉም ሕውሃቶች !!!!

«ዝም ብላችሁ ነዉ የምትደክሙት» ተብለን ነበር። እኛ ግን « አይ ፣ አቶ ኃይለማሪያም በሂደት ነገሮችን ያስተካክላሉ። ጊዜ ይሰጣቸው። ኢሕአዴግ ዉስጥ ጥሩ ልብ ያላቸው ብዙ አሉ» እያልን ተከራከርን። በዚህ አቋማችንም በተቃዋሚ ወግን ባሉት ተተቸን። «ወያኔ ናቸው» እስከመባልም ደረስን። 94% በመቶ የሚሆኑት ሕውሃት ያልሆኑ የፓርላማ አባላትም፣ ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው፣ ጡንቻቸውን በማሳየት በሕውሃቶች፣ ዉስጥ ዉስጡን የሚሰራዉን ጸረ-ዴሞክራሲያዊ፣ ጸረ-እኩልነትና ጸረ-ሕዝብ ተግባራትን ሊያስቆሙ የሚችሉበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችልም አሰብን።

ነገር ግን እንዳሰብነዉና እንደገመትነው አልሆነም። ኦሕድድ፣ የደቡብ ህዝቦች ፣ የነአዲሱ ለገሰ የአማራዉ ድርጅት አባላትና መሪዎች፣ በሚያስገርምና በሚያሳፍር ሁኔታ ለሕዝብ ጥቅም ከመቆም፣ ዉሻ ለባላቤቱን እንደሚታዘዘው፣ የጥቂት ሕወሃት ባለስልጣናት ታዛዦችና ባርያዎች መሆናቸውን ቀጠሉ።

በሳዉዲ ወገኖቻችን ላይ በተከሰተዉ ግፍ ዙሪያ «ተማጽኖ ለጠ/ሚ ኃይለማሪያም» በሚል ርእስ፣ ጠ/ሚኒስትሩ፣ ሕዝቡን እንደ አንድ ሕዝብ እንዲያስተባብሩና ከተቃዋሚዎች ጋር በመሆን፣ ገለልተኛ የስደተኞች ኮሚሽን እንዲያቋቅሙ ጠይቀን ነበር። ነገር ግን ፣ ዶር ቴዎድሮስ አዳኖምን፣ ቁልፍ ሚና ሲጫወቱ በየሜዲያዉ ስንመለከት፣ አቶ ኃይለማሪያም ድራሻቸዉን አጠፉ። (በነገራችን ላይ ዶር ቴዎድሮስ የሕውሃት አመራር ሆነው በሕውሃት ድርጅታቸው የሚደረገዉን ግፍ እያዩ ዝም ማለታቸው፣ ወይንም የግፉ አካል መሆናቸው እንደተጠበቀና ወደፊት በስፋት የምንነጋገርበት ሆኖ፣ በስደተኖች ዙሪያ እየሰሩ ያሉት ግን ማለፊያ ነው)

«በዚህ ብሄራዊ ዉርደትና ቁስል ወቅት፣ ሕዝብ ከርሳቸው መስማት ሲፈልግ፣ አቶ ኃይለማሪያም መሰወራቸው ተገቢ አይደለም። ዛሬ ብቅ ብለው ይሆን?» ብዬ በስማቸው ጉግል ሳደርግና ድህረ ገጾችን ሳካልል ፣ ያላዳመጥኩት፣ ከአንድ ወር በፊት ገደማ፣ በጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ዙሪያ፣ በእንግሊዘኛ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አገኘሁ። ሊንኩን ነካ አድርጌ ቪዴዎዉን ማየትና ማዳመጥ ጀመርኩ። ዘገነነኝ። ሰዉዬዉ «የአገር መሪ ነኝ ፤ መጽሃፍ ቅዱስ አነባለሁ፤ እጸልያለሁ ..» ይላሉ። ግን በዚህ ቃለ ምልልስ የሰማሁት የአንድ ዱርዬና ጀብደኛ ቃለ መልስን ነዉ። አዘንኩ። አፈርኩ። አቶ ኃይለማርያም ሕሊናቸውን፣ ወይንም «አነባለሁ» የሚሉትን መጽሃፍ ቅዱስ የሚያዳምጡ ሳይሆን፣ ሙሉ ለሙሉ የሕውሃትን ጥቅም የሚያስጠብቁ፣ ትግሪኛ የማይናገሩ «ሕውሃት» መሆናቸው ገባኝ።

«አንዳንዶች ሕውሃቶች አጥረዋቸው እያስገደዷቸው ነዉ» ሊሉ ይችላሉ። እኔ ግን አልስማም። የሚናገሩትን ተገደው ሳይሆን፣ የሚናገሩት፣ በስሜት፣ ጠረቤዛ እየደበደቡና አምነዉበት ሲናገሩ ነው የምንሰማቸው። ይቅርታ ይደረግለኝና፤ ለእኝህ ሰው የነበረኝ ከበሬታ ፍጹም ተሟጣል። እኝህ ሰው የመጡበትን ብሄረሰብ ያሰደቡ፣ የእግዚብሄርን ስም ያሰደቡ፣ ስለርሳቸው ጥሩ ሲናገሩና ሲጽፉ የነበሩትን «ደጋፊዎቻቸውን» ያሳፋሩ የማይረቡ ሰው ናቸው።

በቃለ ምልልሱ ፣ አቶ ኃይለማሪያም ስለ ቦምብ ያወራሉ። እስክንድር ነጋ፣ አንዱዋለም አራጌ፣ ርዮት አለሙ፣ በቀለ ገርባ እንዲሁም በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ሽብርተኞች ተብለው የሚማቅቁ ወገኖቻችን፣ ጀግኖቻችን እንጂ ሽብርተኞች አይደሉም። በአንድ ሰዉ ላይ አንዲት ጠጠር አልወረወሩም። በቤታቸው የተገኘ ፈንጂ፣ የተገኘ የራዲዮ ኮሚኒኬሽን መሳሪያዎችና ሚስጥራዊ ሰነዶች የሉም። የቀረበባቸው የተጨበጠ ማስረጃ የለም። በዚህም ምክንያት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ፣ አቶ አማረ አሞኜም «ሽብርተኞች አይደሉም» ብለው ሊፈቷቸውም ነበር። ሕውሃቶች «መለስ አደገኛ ያላቸውን መፍታት የለብንም። እዚያዉ ቃሊቲ ይበስብሱ» በማለት አቶ አማረን፣ በሌላ ዳኛ ለዉጠው፣ ፍርደ ገምድል ዉሳኔ አስወሰኑ እንጂ። የእነ እስክንድር ወንጀል፣ ሕዝብና አገርን መዉደዳቸው፣ እዉነት፣ ፍትህና እኩልነትን መስበካቸው ነዉ።

አቶ ኃይለማሪያም፣ የ«ሕወሃት» መሪ ሆነው እቅጩኝ ነግረዉናል። ደንፍተዉብናል። «የሕሊና እስረኞች አይፈቱም። የሕግ ስርዓት፣ መልካም አስተዳደር አይኖርም። የትግራይ ሕዝብን ሳይቀር እያሰቃዩ ካሉ፣ ከጥቂት የሕውሃት አመራሮች ፣ ከነስብሀት ነጋ ፍቃድ ዉጭ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍቃድ የለዉም። እነርሱ የሚሉትን ተቀብሎ፣ ተሰለፍ ሲሉት በነቂስ እየተሰለፈ፣ ከቤትህ እንዳትወጣ ሲሉት ቤቱ እየተቀመጠ፣ ከወጣም ደግሞ እየተደበደበ፣ ተናገር የሚሉትን እየተናገረ ፣ ተናገር ያልተባለዉን ከተናገረ እየታሰረ፤ ምረጥ የተባለዉን እየመረጠ፣ ምረጥ ከተባለው ዉጭ ከመረጠ ደግሞ፣ ድምጹ እየተሻረ፣ የባርነት ኑሮ ይቀጥላል» ነዉ እያሉን ያሉት።

እንግዲህ አብዛኞቻችን በእርቅ በሰላም በንግግር እናምናለን። በገዢ ፓርቲ ዘንድ በማንኛዉም ጊዜ ለእርቅና ለሰላም ዝግጁነት ከታየ እሰየው ነዉ የምንለው። ነገር ግን ከአቶ ኃይለማያም ጸያፍ ንግግር እንደሰማነዉ፣ ሕወሃት ከሕዝብ ፍላጎት ተቃራኒ የሆነ መንገድ የመረጠ ይመስላል። በመሆኑም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የራሱን እድል በራሱ ለመወሰን መዘጋጀት ይጠበቅበታል። 90 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ፣ እፍኝ በሚያህሉ ጥቂቶች፣ ታስሮና መብቱ ተረግጦ መቀጠል የለበትም። የአለም አቀፍ ሕግ በሚፈቅደዉ መሰረት፣ ሰላማዊ የእምቢተኝነት ዘመቻ በተቀናበረ መንገድ መደረግ አለበት።በዉጭ፣ በአገር የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ሁሉ፣ በቤታችን ጸሎት ከማድረግ ጀምሮ፣ የድርሻችንን ለመወጣት መነሳት አለብን። ነጻነታችችን፣ መብታችንን፣ ክብራችንና ማስመለስ ይኖርብናል።

ስለሰላም፣ ስለእርቅ፣ ስለፍቅርና ስለ ብሄራዊ መግባባት ስናወራ፣ በዚያኛዉ ወገን እርቅን የሚፈልግ የሰለጠነ ቡድን አለ ብለን እንጂ፣ ፈርተን፣ ባርነትንና ዘረኝነት አሜን ብለን ተቀብለን አይደለም። የሰው ልጅ እግዚአብሄር ሲፈጥረው በነጻነት ነዉ። የሰው ልጅ ያለ ነጻነቱ ሰው አይደለም።

ቃለ መጠይቁ እነሆ:

Monday, November 25, 2013

ተዋርደን አንቀርም!!! ኢ/ር ይልቃል ጌትነት


ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡


ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡
አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው“ብለዋል፡፡መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡

ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡በቃለ-መጠይቁ ሰላማው ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

Saturday, November 23, 2013

የፌደራል ፖሊሶች ሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃዉሞ ስልፍ የወጡ ኢትዮጵያዉያንን ደበደበ

ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በወንድሞቻቸዉና በእህቶቻቸዉ ላይ እየደረሰ ያለዉ በደልና ሰቆቃ አንገብግቧቸዉ ቁጣቸዉን ለመግለጽና የሳዑዲን መንግስት ለመቃወም በሳውድ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ተቃውሞዋቸውን ለመግለጽ የወጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ህጻን’ ወጣትና ሽማግሌ ሳይባል በፌደራል ፖሊሶች እንደተደበደቡ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና አስረዳ። በዚህ የሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ከተደበደቡት ሰዎች ሌላ የሰማያዊ ፓርቲና የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት መታሰራቸዉ ታዉቋል። በዚህ ወያኔ እመራዋለሁ የሚለዉን ህዝብ እንደ ጠላት ቆጥሮ ባጠቃበት አጋጣሚ ከ100 በላይ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪና በየክልሉ የሚኖረዉ ህዝብ በወያኔና በሳዑዲ መንግስት ላይ ቁጣዉንና ተቃዉሞዉን እየገለጸ መሆኑ ታዉቋል።

የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች፤ አባላትና ደጋፊዎች ከፓርቲዉ ጽ/ቤት ተነስተው ወደ ሰላማዊ ሰልፉ ቦታ ሲሄዱ 4 ኪሎ የኦሮሚያ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጎን በሚገኘው ወታደራዊ ገራዥ መታሰራቸውን የታወቀ ሲሆን ከመታሰራው ቀደም ብሎ ከፖሊስ ጋር እንሂድ አትሄዱም በሚል ጭቅጭቅ ላይ እንደነበሩ ተሰምቷል። ሌሎች የፓርቲው አባላትና አመራሮች ተበታትነው ወደ ሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ በመሄድ ላይ እያሉ ፖሊሰ ከፈተኛ መጎሳቆል ያደረሰባቸዉ ሲሆን በተለይ አንዲት ሴት ክፉኛ በመመታቷ ለህይወቷ እንዲያሰጋ ለማወቅ ችለኛል። አንድ አስተያየት ሰጪ አንደተናገሩት “በሰው አገር ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ለመቃወም ወጥተን ተመሳሳይ ስቃይ አስተናገድን” ብለዋል። የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ እስር ቤት ውስጥ ሆኖ በድብቅ በስልክ እንደተናገረው የድርጅቱን ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትንና ምክትላቸው አቶ ስለሺ ፈይሳን ጨምሮ 15 አመራሮች ጃንሜዳ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ። ወጣት ጥላየ ታረቀኝ ታስሮና ድብደባ ተፈጽሞበት ከተለቀቁት መካከል አንዱ ሲሆን ፣ የወያኔን አገዛዝን ድርጊት ለመግለጽ እንደሚቸገር ገልጿል። ሰማያዊ ፓርቲ ከጥቃቱ በሁዋላ ባወጣው መግለጫ” የኢትዮጵያ መንግስት ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ጎን በመቆም ዋና ተባባሪ መሆኑን በዛሬው እለት አስመስክሯል ብሎአል።

የግንቦት ሰባት ድምጽ ዘጋቢዎች ያናገሯቸዉ ብዙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የወያኔ ፖሊሶች የራሳቸውን ዜጋ በመደብደብና በማሰቃየት ብሎም በማሰር በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖች ላይ የተፈጸመውን በደል ሀገር ውስጥ በሚገኙ ንጹሀን ወገኖቻቸው መድገማቸዉ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነዉ ካሉ በኋላ በውሸት ዲሞክራሲ ስም የተደበቀው አምባገን አገዛዝ ህዝብን ለማሸማቀቅ የወሰደውን እርምጃ በመቋቋም አያት ቅድመ አያቶቻችን የሰጡንን አደራ በመቀበል ክብአችንንና ማንነታችንን በትግላችን እንደገና እናስከብራለን ብለዋል። የወያኔዉ ቃል አቀባይ ሽመልስ ከማል ለአልጀዚራ ቴሌቪዥን በሰጠዉ ቃለመጠይቅ ሰልፈኞቹ የተከለከሉት ባልተፈቀደ ሰልፍ ላይ በመገኘታቸውና ኢትዮጵያን ህዝብ በጸረ-አረብ ስሜት በማነሳሳታቸው ነው በማለት የተለመደዉን የቅጥፈት ንግግር ለአለም ህዝብ በማሰማት ለዜጎች ሳይሆን ለሳዑዲ ቱጃሮች ያለዉን ታማኝነትበግልጽ አሳይቷል።

አዜብ ህወሀትን ለመልቀቅ ማመከቻ ማስገበቷ ተሰማ

የቀድሞዉ ጠ/ሚኒስቴር ባለቤት የሆነችዉና የሙስናዋ እመቤት በመባል የምትታወቀዉ አዜብ መስፍን ከወጣትነት እድሜዋ ጀምሮ የገለገለችዉን ህወሀት ፓርቲ በቃኝ ብላ ለመተዉ ለፓርቲዉ ማ/ኮሚቴ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባቷን ዉስጥ አዋቂ ምንጮች አስታወቁ። ከባለቤቷ ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በፓርቲው የነበራት ተሰሚነትና የበላይነት እየተሸረሸረ በመምጣቱ፤ ከኤፈርት ሃላፊነቷ ሳትወድ በግድ በመነሳቷና እንዲሁም ጓግታለት የነበረው የአዲስ አበባ ከንቲባነት ስልጣን በማጣቷ፣ የተበሳጨችዉ አዜብ ተስፋ መቁረጥ መጀመሯ ፓርቲውን ለመልቀቋ ዋና ምክንያት እንደሆነ ምንጮቹ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ አዜብ የምትተማመንባቸዉ አብዛኞቹ የህወሀት ባለስልጣኖች ከስልጣን ተባርረዉ መታሰራቸዉና እንዲሁም በስብሃት ነጋ ቡድን እየተወሰደባት ያለው ፖለቲካዊ የበላይነት መቋቋም ስለተሳናት ከፓርቲው በግዜ መሰናበቷ ሌላ አማራጭ የሌለዉ መሆኑን በቅርብ የሚያዉቋት ሰዎች በመናገር ላይ ናቸዉ። የህወሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ በቅርብ ቀን ዉስጥ ተሰብስቦ የአዜብ መስፍንን ጥያቄ እልባት እንደሚሰጠዉ የጠቆሙት ምንጮች ከዚሁ ጋር አያይዘው ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ አዜብ በሲውዲን ወይም አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ዉስጥ በገዛቸዉ መኖሪያ ቤት ለመኖር ጓዟን እንደምትጠቀልል አመልክተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘረኛዉና ለብዙ ሰላማዊ ዜጎች ሞት ተጠያቂ የሆነዉ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ከኢታማጆር ሹምነቱ ቦታ ተነስቶ በምትኩ በቅርቡ የሌፍቴናነት ጄኔራልነት ሹመት የተሰጠዉ ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀልን ሊተካ እንደሚችል አዲስ አበባ ዉስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ቃል አቀባዮቻችን ገለጹ።

የወያኔ የግድያ እቅድ መክሸፍ ለሁመራና ወለወቃይት ጸገዴ ወጣቶች ችግር ፈጠረ!

ፋሽስት ወያኔ ‘ወያኔ ኦ ሚሊኒየም’ ብሎ ሰይሞት የነበረውና በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌና የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል አመራሮች ላይ የተጠነሰሰ የግድያ እቅድ ከከሸፈ ወዲህ ህዝባዊ ሃይሉ ይገኝበታል ተብለው በተጠረጠሩት አጎራባች ወረዳዎች በሚገኙ ወጣቶች ላይ የተጠናከረ አሰሳ በማድረግ ወጣቶችን በማሰር ላይ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ፋሽስት ወያኔ ልክ እንደቆሰለ አንበሳ እዚህም እዚያም በፍርሃት በመንደርደር በሁመራና በወልቃይት ጸገዴ የሚገኙ ወጣቶችን እያሰረ ይገኛል። ድርጊቱ ብዙዎችን እንዳሳሰበ የተገለጸ ሲሆን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ባካባቢው የሚገኙ ወጣቶች ሕዝባዊ ሃይሉ እየገኘው ባለው ስምና ዝና ተስበው ሊቀላቀሉ ይችላሉ ብሎ የሰጋው ወያኔ ይህን የእስር ርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ይጠቁማሉ።

ባካባቢው እያየው ባለው ነባራዊ ሂዎት ያልተደሰተው ወጣት፣ የነገ ተስፋየ ምንድን ነው ብሎ መልስ ያጣው ወጣት፣ ከትላንት ዛሬ፣ ከዛሬ ነገ ቀስ በቀስ እየሞተ መሆኑን የተረዳው ወጣት እንኳን ከተጠናከረ ድርጅት ጋር መቀላቀል ይቅርና በራሱም ጠንካራ የተቃውሞ ድርጅት ሊያቃቁም ይችላል የሚሉ ሌሎች ወገኖች ደግሞ “የህ አይነቱ የፋሽስት ወያኔ ድርጊት ወጣቱን የበለጠ ተቃዋሚ ያደርገዋል እንጂ አያለዝበውም”። ለዚህም ነው ባሁኑ ሰአት ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታጋይ እየጎረፈለት መሆኑ የሚሰማው ይላሉ። ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ፋሽስት ወያኔን በማስወገድ ሕዝቦቿ በመከባበር የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚደረገውን ሂደት ለማገዝ በትጥቅ ትግል ወያኔን ለመፋለም ዝግጅት እያደረገ ያለ የተቃውሞ ድርጅት ነው።

ወቅታዊ ችግሮቻችን የራሳችን መንግሥት ባለቤቶች እንድንሆን ይበልጥ ሊያበረቱን ይገባል!

በወያኔ አረመኔያዊ አገዛዝ ሳቢያ ከሀገራቸውና ከትውልድ ቀያቸው ተፈናቅለው በዐረቡ ዓለም በተለይም በሳዑዲ ዐረቢያ በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ ሰሞኑን እየደረሰ የሚገኘውን ዘግናኝ ሰቆቃና ግድያ በመሪር ስሜትና በንቃት እየተከታልን ነው። አበው “ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳው አይቀበለውም” እንዲሉ እነዚህ ወገኖቻችን በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ‹የሀገራቸው መንግሥት ነው› የሚባልለት የወያኔው መንግሥት እንኳንስ በባዕድ ሀገር በሚገዛው ሀገርም ውስጥ የሚያካሂደውን የመብት ገፈፋና ሕዝቤ በሚለው ዜጋ ላይ በዘር እየከፋፈለ የሚያራምደውን የግፍ አገዛዝ ዐረቦቹም ሆኑ ቀሪው ዓለም ያውቁታል። በመሆኑም ለነዚህ ምሥኪን ዜጎች የሚጮኽላቸውም ሆነ ለመብታቸው መከበር የሚቆረቆርላቸው አንድም መንግሥታዊ አካል እንደሌለ ከበፊት የተገነዘቡት እውነታ ነው። በወገኖቻችን ላይ ይህን ሁሉ ሰማይና ምድር የማይችሉት የግፍ ቁልል እነዚህ የዐረብ መንግሥታት የፀጥታ ኃይሎች ሲከምሩባቸው ማንም ዝምባቸውን እሽ የሚል ወይም ጠንከር ባሉ ቃላት እንኳን ተቃውሞ የሚያቀርብ አካል እንደማይር ያውቃሉ። ለዚህም ነው ታላላቅ የሚዲያ አውታሮች ሳይቀሩ ሀገሪቷንና ሕዝን በመናቅ በዝምታቸው መግፋትን የወደዱት። ይህ ነገር ከሃይማኖትም ይሁን ከቀለም፣ ከዘርና ከፖለቲካዊ እሳቤዎች አኳያ የሰው ልጅ ተፈጥሮን ባሕርይና የሀገራትንና የመንግሥታትን ተጻራሪ ድርብ አቋሞችን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። “ሰው ለሰው የሚጨነቀው፣ ምን ዓይነት ሰው ሲጎዳ ወይም ምን ዓይነት ሕዝብና የትኛው ሀገር ችግር ላይ ሲወድቅ/ሲወድቁ ይሆን?” በሚል ከፍተኛ ፍልስፍና ውስጥ የሚያስባ ልዩ አጋጣሚ ፈጥሯል። በእውኑ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ በበለፀጉ ሀገሮች የአንድ ንጉሥ-ንግሥት ንብረት ከሆነች ውሻ ያንሳሉን? ንግሥት ኤልሣቤጥ የሚወዷት የቤት ድመት ወይም የንጉሥ አብደላ የቤተ መንግሥት ውሻ ቢሞቱ ሲኤንኤንንና ቢቢሲን የመሳሰሉ ላለው የሚያሽቃብጡ ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት የመክፈቻ ዜናቸው እንደሚያደርጓቸው አይጠረጠርም። ወትሮም ብሂሉ “ላለው ይጨመርለታል” ነውና። እንደዚህ ያለው አካሄድ በውነቱ ቅስምን የሚሰብርና ከ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሰለጠነ የሚባል ማኅበረሰብ የሚጠበቅ አልነበረም።

Friday, November 22, 2013

ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ!!!

የሳዑዲ ልዑል አንጋቾቻቸውን አወደሱ


በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡

ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው ዝርዝር ጉዳይ ግን ከሁኔታው ምስጢራዊነት አኳያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

“አልዘገዩም” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም “አኢጋን ችግር በተከሰተ ቁጥር የሚቋቋምና የሚፈርስ የዕቁብ ይዘት ያለው ድርጅት አይደለም፡፡ ወይም እሣት ሲነሳ ድምጽ እያሰማ እንደሚከንፍ የእሣት አደጋ መኪና የሚመሰል ድርጅት አይደለም” በማለት የጋራ ንቅናቄውን የተጠና አካሄድ በመጠቆም የመለሱት አቶ ኦባንግ ይህ ችግር እንደሚከሰት አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡

Thursday, November 21, 2013

በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ጥቃት እና የፈዘዘው ስርኣት የፖለቲካ ክስረት መፍትሄው ኢሕኣዴግ የማይደፍረው ስር ነቀል ለውጥ ነው!!!

በምንሊክ ሳልሳዊ

ኢትዮጵያውያን በመካከለኛው ምስራቅ በስፋት መሰደድ የጀመሩት ባለፈው 20 አመታት የወያኔው ጁንታ መንግስት ስልጣኑን ተቆጣጥሮ በህዝቦች ላይ በተለየ መልኩ የፈጠረውን አደገኛ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቀውስ ተከትሎ መሆኑ እሙን ነው::ይህ ቀውስ የደረሰባቸው ወገኖቻችን ከተሰደዱባት ሃገር አንዷ ሳኡዲ አረቢያ ተጠቃሽ ናት::ሳኡዲ አረቢያ ከሃብቷ ብዛት የመጣ የስራ ፍቅር ባሌለው ወጣት ዜጋ የተሞላች እና ፔትሮ ዶላር ባሰከራቸው ቱጃሮች የምትተዳደር አገር መሆኗ እና የዜጎቿ የስራ አለመስራት የስራ እድሎችን ስላሰፋ የወያኔ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተጠቂዎች ወደዚሁ መሰደድን መርጠዋል:: ይህንን ተከትሎም ይህን ሰሞን የአለም ዋና አጀንዳ የሆነው የኢትዮጵያውያን በሳኡዲ አረቢያ እየደረሰባቸው ያለ ስቃይ ነው::

ሰቆቃው ያደረሰው የሰብኣዊ መብት ጥያቄ ከሳኡዲ መንግስት ላይ ይልቅ ወደ ወያኔው ጁንታ ላይ እንዲተኮር ያደረገ ሲሆን የወያኔው ጁንታ ለከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ተዳርጓል::በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው አስደንጋጭ እና ሰብኣዊነትን ያለፈ ድርጊት በመንግስት ባለስልጣናት መሃከል የፈጠረው መረበሽ እስከአለመግባባት አድርሷቸዋል::ይህንን የወያኔን አቋም የተመለከተችው ሳኡድ አረቢያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ የበላይነት ተቀናጅታለች::በከፍተኛ ደረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ ባሉ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ አትኩሮት አግኝቶ የአለም ጎዳናዎች ሳኡዲን እና ወያኔን በሚቃወሙ በሰላማዊ ሰልፍ እየተጥለቀለቁ ነው::ህገመንግስታዊ መብቶችን አለመከበሩን እና ለዜጎች አለመቆርቆርን በማሳየቱ በአለማቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል::ሚዲያዎች ከዜጎች የሳኡዲ ሰቆቃ ይልቅ በኢትዮጵያውያኑ ሰልፎች ላይ አትኩሮት ሰተዋል::

ከወያኔው መንግስት የሚንጸባረቁ አጀንዳዎች ለዘብተኛ አቋሞች በስህተት እንደተፈጠሩ ወቅታዊ ሁኔታኦች እያሳዩ ሲሆን ስርኣቱ አጣብቂኝ ውስጥ እና የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ እንደገባ ተረጋግጧል:: የሌላ ሃገር እምባሲዎች ዜጎቻቸውን በመጠበቅ ላይ ሲያተኩሩ የወያኔው ዲፕሎማቶች የዜጎች ንብረት የሆነውን ኤምባሲ በመዝጋት አገልግሎት አቁመዋል::
የደረሰውን ሰቆቃ ተከትሎ ስርኣቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመተባበር ለሉአላዊ የዜግነት ክብር መነሳሳት ሲኖርበት እና ህዝብን ማቀፍ ሲኖርበት ለብሄራዊ ውርደት ዜጎችን ዳርጓል::የፖለቲካ ፓርቲዎች የጠሩትን ሰልፍ በሃይል እና በደብዳቤ በትኗል::የወያኔው ስርኣት የህዝቡን ቁጣ ባለማንበቡ በችኮላ ያልበሰለ ሃሳብ በማራመዱ የፖለቲካ ኪሳራውን አስፍቶታል::ህገመንግስታዊ መብቶችን አለመከበሩን እና ለዜጎች አለመቆርቆርን በማሳየቱ በአለማቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያውያንን ቁጣ ቀስቅሷል::ሚዲያዎች ከዜጎች የሳኡዲ ሰቆቃ ይልቅ የወያኔን ስርኣት ጋጥወጥነት አትኩሮት ሰተውታል::

ለዚህ ሁላ ችግር መንስኤው ስርኣቱ በልማት ሽፋን የሚከተለው የፖለቲካ እና እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ችግሮች እንደሆኑ አግጥጦ ገሃድ ከመውጣቱም በላይ የአደባባይ ሃቅ ሆኖ ለለውጥ እንትጋ የሚሉ ድምጾች በመላው ሃገሪቱ ተንጸባርቀዋል:; የወያኔ ስርኣት ህዝብን የሚያሳትፍ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ እስካልተከተለ ድረስ እና አሁን ባለው ሂደት ላይ ለውጥ እስካላደረገ ድረስ የስደት ችግሩ በስፋት እየቀጠል ይሄዳል:;ዛሬ ሳኡዲ ላይ የደረሰው ሰቆቃ ነገ በሌሎች ሃገራትም ይቀጥላል::ይህ ብሄራዊ ውርደት በታሪካችን አይተነው የማናውቅ ነው:;ኢትዮጵያውያን ከቀድሞው ጀምሮ በፖለቲካ ቢሰደዱም እንደዚህ አይነት ውርደትን አስተናግደው አያውቁም::የአሁኑ ውርደት ያለው ስርኣት ለዜጎቹ ደንታ ቢስ በመሆኑ የተወለደ ችግር ነው::በሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ተመዘገበ ከመባል ውጭ የተባለው እድገት ምንም አይነት ህዝባዊ ጠቀሜታ እንዳላሳየ በይፋ አስመስክሯል::የተማረው እና የሚሰራው ሃይል መሰደዱ ኢኮኖሚው እንደኮላሸ እንጂ እንዳደገ አያሳይም::የዚህ ሁላ መንስኤው ስርኣቱ የሚከተለው አፋኝ የፖለቲካ እና የእኮኖሚ ፖሊሲ ስለሆን ድጋሚ ሊከለስ እና ሊፈተሽ ይገባዋል::

Wednesday, November 20, 2013

ትግላችን መስጂዶቻችንን ለመንጠቅ ከሚሞክረው መንግስት የተሳሳተ ምልከታ ጋር ነው! ድምፃችን ይሰማ

ረቡእ ሕዳር 11/2006

መስጂዶች ለኢትዮጵያዊው ሙስሊም ልዩ የሚያደርጋቸው አያሌ ምክንያቶች አሉ፡፡ በዋነኝነት መስጂዶች የአምልኮ ስፍራ ከመሆናቸው በተጨማሪ ሌሎች አማራጮች በማይታሰብባት ሃገራችን የዳዕዋም ብቸኛ ማዕከላት ናቸው፡፡ ባሳለፍናቸው 20 እና 30 አመታት ‹‹አንፃራዊ የእምነት ነፃነት ነበር›› ተብሎ ቢነገርም ሙስሊሙ በነዚህ ግዜያት ከመስጂዶች ውጭ የገነባቸው ተቋማት የሉትም፡፡ ስለዚህም ነው ‹‹መስጂዶች የህዝበ ሙስሊሙ የአይን ብሌን ናቸው›› ቢባል ማጋነን የማይሆነው፡፡

በምናደርገው ሰላማዊ የመብት ትግል ደግሞ መስጂዶች የተቃውሞ ማዕከላት እና አለፍ ሲልም የእንቅስቃሴው መገለጫዎች ናቸው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ የመጅሊስን ህገ ወጥነት አውጆ እንቅስቃሴውን ሲጀምር በመጅሊስ የሚተገበረው መንግስታዊ ዘመቻ መስጂዶቻችንን እንዳይቆጣጠር ማድረግ ትልቁ ዓላማው ነበር፤ አወሊያን መጠበቅን ከአላማዎቹ አንዱ አድርጎ የተነሳ እንቅስቃሴ የሌሎቹን መስጂዶች ከህዝብ የመንጠቅ ዘመቻ ዝም ብሎ ያልፋል ተብሎ ሊጠበቅ አይችልምና!

በሃገራችን የሚገኙት አብዛኞቹ መስጂዶች ደሳሳ ቢሆኑም እድሜ ጠገብ ናቸው፡፡ ብዙዎቹ በገጠር የሚገኙት ወለላቸው አፈር፣ ክዳናቸው ሳር ነው፡፡ በከተማዎች ያሉትም ቢሆን ከጥቂቶች በስተቀር ይዞታቸው የተጎሳቆለና እድሳት የናፈቃቸው ናቸው፡፡ የውጫዊ ይዘታቸውን ጎስቋላነት የሚያካከሱበት ግርማ ሞገሳቸው ግን በቀን አምስት ግዜ ለሰላት የሚያስጠልሉት ህዝበ ሙስሊም ነው፡፡

መስጂዶቻችን በእድሜ ጠገብ ቆይታቸው ሁሉንም አማኞች በእኩልነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ መንግስታት ሲቀያየሩ እና የተለያዩ አመለካከቶች ሲነሱና ሲወድቁ መስጂዶች አማኞችን በአንድነት አቅፈው ይዘው ለዛሬ አብቅተዋል፡፡ መላው ሙስሊምም ያለልዩነት ‹‹መስጂድ የኔ ቤት ነው›› ብሎ ያምናል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ አሁን ላለበት ደረጃ የደረሰውም ቢሆን አልጋ በአልጋ በሆነ መንገድ አልፎ አይደለም፡፡ የመስጂዶች ይዞታ እና አስተዳደር ምቹ ባልሆነበት አጣብቂኝ ውስጥም እንኳን አሁን የምናየው የዲን ተቆርቋሪ ትውልድ ተፈጥሯል፡፡ ይህ ትውልድ ነው መስጂድ የሁሉም ሙስሊም ቤት መሆኑን፣ ብሎም የመስጂድ ግርማ ሞገስ አማኞቹ መሆናቸውን በተግባር ሊያረጋግጥ የሚፈተንበት ወቅት ላይ የሚገኘው፡፡

አሁን በመተግበር ላይ ያለው መስጂዶችን ከባለቤታቸው የመንጠቅ ዘመቻ በሰከነ መንፈስ መታየት የሚገባው በመሆኑ ለረጅም ግዚያት የህዝበ ሙስሊሙ የመወያያ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከጉዳዩ አሳሳቢነት እና ከአተገባበሩ ውስብስብነት የተነሳም ቀጥተኛ መፍትሄ ማስቀመጥ ሲያዳግት በርካታ ባለድርሻ አካላት በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ምልከታ እንዲጠቁሙ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡

Monday, November 18, 2013

አንድ አንዳርጋቸውን መግደል የነፃነቱን ትግል ማስቆም አይቻልም!!!

ህወሃቶች የንጹሃን ዜጎችን ደም በከንቱ ሲያፈሱ የኖሩ ነብሰ ገዳዮች እንደሆኑ የሚታወቅ ነው። አሁንም ክብሬንና ነፃነቴን የሚሉ ዜጎችን ይዘው ደብዛቸውን ለማጥፋት ብዙ ዓይንና ብዙ ጆሮዎችን በየቦታው አቁመናል እያሉ ያቅራራሉ። ይሄን ሁሉ ዓይንና ጆሮ ይዘንስ የሚያሸንፈን ማን ነው ? ሲሉም ይደመጣሉ። እነርሱ እንደሚሉት ዓይኖቻቸው ማየት፤ጆሮዎቻቸውም መስማት የሚችሉ አይደሉም። የህወሃት ዓይኖች ማየት የተሳናቸው እውራን፤ ጆሮዎቻቸውም ማድመጥ የማያውቁ ደናቁርት እንደሆኑ የታወቀ ነው። ህወሃቶች ይህን የማይሰማ ጆሮና ፤ማየት የተሳነውን ዓይን ይዘው እየተደናበሩ፤ ይህን ለመደበቅ ህይዎት ያላቸው መስለው ይታያሉ። አዎን ህወሃቶች ጭው ባለ በርሃ ላይ ብቻችሁን እንደቆማችሁ እወቁ። የሚነገረው እና የሚሆነው በሙሉ ስለተሰወረባችሁ በብዙ ሚሊየኖች መሃከል ብቻችሁን እርቃናችሁን ቀርታችኋል። ብዙ ሚሊዮን ዓይኖች እና ጆሮዎች በእናንተ ላይ መተከላቸውን ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።

ግንቦት ሰባት የፍትህ፤የነፃነት እና የእኩልነት ንቅናቄ እንደ ህወሃት-ኢህአዴግ ጆሮዉ የተደፈነና አይኑ የታወረ ድርጅት አይደለም። ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የሚያይ ዓይን፤ የሚሰማ ጆሮና የሚያስተዉል ልቦና ያለው ህያው ንቅናቄ ነው። የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጥያቄ ግልፅ ነው። ነፃነት ! ፍትህ ! እና ዲሞክራሲ ! ናቸው። እነዚህ ጥያቄዎች በአግባቡ መልስ እንዲያገኙ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ተነስተናል ጉዞ ጀምረናል፤ ሺ አንድአርጋቸውን ፈጥረናል። ልብ ይበሉ ነፃነት ፍትህ እና ዴሞክራሲ ለሰው ልጆች የተሰጡ ክቡር ስጦታዎች ናቸው። ህወሃት እነዚህን ክቡር ስጦታዎች ከዜጎች ላይ ነጥቆና ህዝብን ረግጦ መቀጠል የለበትም። ህወሃት የዜጎችን ነፃነት ነጥቆ ፤ ፍትህን አጓድሎና ህዝብን ረግጦ እንደከዚህ በፊቱ በሠላም እኖራለሁ ብሎ የሚያስብ ከሆነ ተሳስቷል። በህወሃት ቅዥት አገራችን ተጎድታለች። ህዝቧም ለማያባራ ጉስቁልናና ውርደት ተዳርጓል። ብዙዎችም አገር አልባ ሁነው በየሰው አገሩ መፃተኛ ሁነው እንዲኖሩ ተገደዋል። በእኛ እምነት በአገራችን ላይ እየደረሰ ላለው ውርደት በዋናነት ተጠያቂው ህወሃት ነው። ህወሃት የኢትዮጵያ ዋነኛው ጠላት ነው የምንለውም ዜጎቻችንን ለጉስቁልናና ለውርደት ስላደረገም ጭምር ነው። እኛ ይህን አገር በቀል ጠላት ከሥሩ ነቅለን ለመጣል ተነስተናል። ከዚህ ትግል የሚያቆመን ምንም ዓይነት ምዳራዊ ኃይል እንደሌለ ህወሃቶች እንዲያውቁት እንፈልጋለን። ህወሃቶች አንገታችንን አስደፍተው አይገዙንም። ጥቁር ደም ያፈራቻቸው የቁርጥ ቀን ውድ ልጆቿ የነጻነት ታሪክ በጥቁር ቀለም ይጻፍ ዘንድ የሚያደርጉትን ሀገርን የማዳን ጥሪ እንዲህ በቀላሉ መግታት ከቶ አይቻልም። ወያኔዎች አትደናበሩ! ጋሬጣውን መለየትን ለእኛ ተውሉን።

ታዲያ ይህን ንቅናቄ አንድ አንዳርጋቸውን በመግደል ማስቆም የሚቻል የሚመስለው ጅላ ጅል ቡድን አገሪቷን እየገዛ በመሆኑ ተቆጭተናል። አንዳርጋቸውን መግደል ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊ አንዳርጋቸውን መፍጠርና ትግሉንም የሚያጠናክር እና የሚያፋፍም መሆኑን አልተረዱም። የኢትዮጵያ ህዝብ የእምቢተኝነት፣ የአልገዛም፣ የነጻነት ታሪክን ለማስከበር መሰዋእትነትን ለመክፈል ዝግጁ መሆንን ከአንዳርጋቸው ከተማረ ቆይቷል። መቆጨታችን ግን እንዲሁ በቁጭት ብቻ የሚቀር የሚመስለው ካለም ድግሞ ተሳስቷል። ይሄ ቁጭት በየደረሱበት የንፁሃንን ደም በከንቱ ማፍሰስ አገር መምራት የሚመስላቸውን ህውሃቶች ከተንጠለጠሉበት ዙፋን አውርደን በልካቸውና በአቅማቸው እንዲኖሩ ለማድረግ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን እንድንቀጥል ያደርገናል። ህወሃት ውስጥ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ግለሰብ ካለ አሁን ቆም ብሎ እንዲያስብ እናሳስበዋለን። ጀንበር ሳትጠፋባችሁ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚደረገውን ትግል ተቀላቀሉ። እርግጥ ነው ለነፃነት የሚደረገው ትግል በየመስኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ህወሃትም የእጁን እንደሚያገኝ ምንም ዓይነት ብዥታ እንዳይኖራችሁ ልንነግራችሁ እንወዳለን።

ግንቦት ሰባት የቆመበት መሠረት ፅኑ፤ ዓላማውም ህዝባዊ ነው። በዚህ በፀና መሠረት ላይ ህዝባዊውን ዓላማ አንግበው የተነሱ ሚሊዮኖች አሉ። እነዚህ ሚሊየኖች የሌሉበት ሥፍራ የለም። ከቤተ-መንግስት እስከ እርሻ ማሳ፤ ከስለላ ተቋማት እስከ አገሪቷ መከላከያ ኃይል፤ ከሃይማኖት ተቋማት እስከ መንግስት መሥሪያ ቤቶች፤ ከዘመናዊ ትምህር ተቋማት እስከ ተከበሩ ገዳማት ድርስ ለክብራቸው ዘብ የቆሙ ሚሊየኖች አሉ። እነዚህ ሚሊኖች የቆሙት መረቅ የበዛበትን ወጥ ዓላማ አድርገው ሳይሆን በፀናው መሠረት ላይ ለተተከለው ክቡር ዓላማ ነው። ይህ ክቡር ዓላማ ነፃነት፤ ፍትህ ፤እኩልነት እና የህግ የበላይነት እንጂ ሌላ አይደለም። እነዚህ ሚሊየኖች አትኩረው ማየት የሚችሉ ድንቅ ዓይኖች ያሏቸው፤ አጥርተው ማድመጥ የሚችሉ ክቡራን ጆሮዎች ያሏቸው መሆናቸውን ህወሃቶች እንዲያውቁት እንወዳለን።

ግንቦት ሰባት ማንንም ፍርሃት እና ድንጋጤ ውስጥ መክተት አይፈልግም።እንዲያውም ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የሚታገለው ዜጎች ሁሉ ከፍርሃት ነፃ ሁነው በደስታ እንዲኖሩ ለማስቻል ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ካሁን ወዲያ ከግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዓይንና ጆሮ የሚያመልጥ አንዳችም ነገር እንደማይኖር የሚያሳድደን ቡድን እንዲያውቀው እንፈልጋለን። ዓይንና ጆሯችን በሁሉም ሥፍራ በንቃትና በጥንቃቄ ነገሮችን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ህወሃቶች ከትዕቢታችሁ ብዛት የተነሳ የህዝቡን ምክር መናቃችሁን እናውቃለን።የወገኖቻችንንም ድምፅ ጫጫታ እያላችሁ እንደምትሳለቁም እናውቃለን። ይሄ እንደማይጠቅማችሁ ብዙ ግዜ ነግረናችኋል። የህዝቡን ምክር ስሙ፤ የወገኖቻችሁንም ድምፅ አድምጡ ብንላችሁ በእምቢታችሁ ፀንታችኋል። ልቦናችሁ እንደ ፈርዖን ልብ ደንድኗል።ልብ ማደንደን እንኳን እናንተን ለመሠለ ደካማ ፍጡር ይቅርና በዘመኑ እኔ “እምላክ” ነኝ እሰከ ማለት ለደረሰው ለፈርዖንም አልበጀም። እንዲህ ዓይነት የልብ ድንዛዜ እናንተ በዚያ ጠባብ ዓላማችሁ ጣልነው ለምትሉት ለመንግስቱ ኃ/ማሪያምም አልረባውም። አሁንም የእኛ ምክር አጭርና ግልፅ ነው። የመዘዛችሁትን የበቀል ሰይፍ ወደ ሰገባው መልሱ። የዘጋችሁትን በር ክፈቱ። የነጠቃችሁትን የዜጎች ነፃነት መልሱ። በህዝቡ ላይ ያወረዳችሁትን የፍርሃት ድባብ አስወግዱ። የተከላችሁትን የዘረኝነት እሾህ ንቀሉ። ከእውነት ጋርም ታረቁ። እንዲህ ብታደርጉ የዚያችን አገር በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን የሚበላችሁን እሳት ማጥፋት አይቻላችሁም። መጥተናል!!

እኛም ከምን ግዜውም በላይ ተጠናክረናል። የትግል ዘርፋችን ሰፍቷል። በሁሉም አቅጣጫ መረባችን ተዘርግቷል። ከዚህ መረብ የትም አታመልጡም። ማምለጫ መንገዳችሁ አንድ ብቻ ነው። እርሱም የህዝቡን ድምፅ መስማት፤ እውነተኛ መልስ መስጠት እና ለህግ ተገዢ መሆን። አበቃን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

Wednesday, November 13, 2013

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)በሳውዲ አረቢያ በዜጎች ላይየሚፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት አውግዞ በቅርቡ በሚጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ሕዝቡ በነቂስ በመውጣት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል በመቃወም ድምፁን እንደዲያሰማና ወገናዊ አጋርነቱን እንዲያሳይ መድረክ ጥሪ ቀረበ

የሳውዲ መንግስት በኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ላይ እየፈፀመ ያለውን ኢሰብኣዊነት አጥብቀን እናወግዛለን!!!
--------------------------------------------------------------------
መድረኩ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ህዝቡ በነቂስ እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን!
-----------------------------------------------------------
ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) የተሰጠ መግለጫ

ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ድብደባ፣ ግድያና በጅምላ ማጎር ከኢሰብአዊነቱም በላይ የሳውዲ መንግስት ለዜጎች ያለው ክብር በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የሚያሳፍር ድርጊት ነው፡፡ በኢትዮጵያዊነት ክብር ላይ የተሰነዘረ ጥቃትም ነው፡፡ በኢትዮጵያውያን ሉአላዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል ሲሆን ዜጎቻችን በጭካኔ ሲገደሉ፣ ሲፈነከቱ ሲታጎሩና ሲገረፉ ማየት አንገት ያስደፋል፡፡ በአንድ አፋኝ ስርዓት ውስጥ የምንገኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በላይ ምን እንላለን?

ይህ በሳውዲ መንግስት ደፋርና ኋላ ቀር የሆነ ድርጊት የኢህአዴግን መንግስት የዲፕሎማሲ ተፅዕኖ መፍጠር ድክመት ከመግለፁም በላይ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ያለውን ደንታቢስነት ይመሰክራል፡፡ ድሮስ በመልካም አስተዳደር እጦት ፍትህን ከተነፈገ፣ በሙስና ከተጨማለቀና በፖለቲካ ስልጣን ለመቆየት ቆርጦ ከተነሳ የስልጣን ኃይል ምን ይጠበቃል? ዜጎችንና ሃገሪቱን ያስደፍደራል፣ የሉኣላዊነትን ክብር ያስነካል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ የኢህአዴግ መራሹ መንግስት የተሳሳተ ፖሊሲ እየፈጠሩ ካሉት ችግሮች አንዱ ማህበራዊ ቀውስ መሆኑን ገጠዋል፡፡ ዜጎች ተስፋቸው ጨልሞ እየታያቸው ነው፡፡ ተስፋ ያጣ ዜጋ ተስፋ ይቆርጣል፡፡ በተወለደበት ቀየና ሃገር የኑሮ እምነትና ዋስትና የሌለው ዜጋ ሞት እየሸተተውም ይሰደዳል፡፡ በአገራችን ስራ አጥተው ስራ ፍለጋ ሲንከራተቱ በሰው ሃገር በረሃ ሰብአዊ ክብራቸው ተዋርዶ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎችን ዜና መስማት በኢህአዴግ አገዛዝ የተለመደ ሆኖአል፡፡ በጣም የሚያሳፍረው ኢህአዴግ እነዚህን ዜጎች “ህገ ወጥ ስደተኞች “ በሚል ፍረጃ ለመብታቸው ለመቆም ቁርጠኝነት የሚጎድለው መሆኑም ጭምር ነው፡፡

መድረክ ዜጎቻችን የሚሰደዱበት የተሻለ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ፍትህ ፍለጋ እንዲሁም አሰቃቂ የሆነውን የአንድ ፈላጭ ቆራጭ አምባገነናዊ ፓርቲ የፖለቲካ አስተዳደር ሽሽት መሆኑን ይገነዘባል፡፡

Tuesday, November 12, 2013

ትግሉ መሯል፤ እኛም ዝግጁዎች ነን!!!


በንቅናቄዓችን ፀሐፊ እና በግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራር አባላት ላይ የተቃጣው ረዥም ጊዜ የወሰደ የግድያ ሴራ መክሸፉ አስደስቶናል። ይህ ሴራ የወያኔ የስለላና የግድያ ኃላፊዎች በሆኑት ጌታቸው አሰፋ እና ጸጋየ በርሄ የቅርብ ክትትል የተመራ፤ የአሻንጉሊቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እውቅናና ይሁንታ የተሰጠው፤ ወያኔ ከፍ ያለ ተስፋ የጣለበት ሴራ ነበር።


“ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም” የተሰኘው ይህ በወያኔ የመጨረሻ ከፍተኛው አመራር የተመራው ሴራ ስለወያኔ ውስጣዊ አደረጃጀት ጠቃሚ መረጃዎችን ሰጥቶናል። ከዚህም በተጨማሪ የወያኔ ሹማምንት ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን ንቀት፤ ከአመት በኋላ ስለሚደረገው ምርጫ ውጤት፤ ለሰላዮቻቸው ስለሚሰጡት ጉርሻ መጠን፤ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ተስፋ ከጣሉበት ቅጥረኛ ነብሰ ገዳያቸው ጋር ካደረጉት የስልክ ንግግሮች ማድመጥ ይቻላል። ይህ ለበርካታ ጥናቶች በግብዓትነት ሊውል የሚችለውን በድምሩ ከስምንት ሰዓታት በላይ የሚፈጀው የስልክ ንግግር ቅጂ በሕዝባዊ ኃይሉ የመረጃ ክፍል አማካይነት ለሕዝብ በኢንተርኔት በነፃ ተለቋል። በአጋጣሚውም የወያኔ ገበና ተጋልጧል።

በአንፃሩ ደግሞ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የተደራጀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቢሆንም ምን ያህል ወያኔን እንቅልፍ እንደነሳ ተጨባጭ ማስረጃ ሆኗል። ይህ ለነፃነት ታጋዮች ከፍተኛ የስነልቦና ብርታት የሚሰጥ ነገር ሆኖ ተገኝቷል።

በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የተቃጣበትን ጥቃት ከማክሸፍ በተጨማሪ የወያኔን ገበና ማጋለጥ በመቻሉ የመጀመሪያው ሁነኛ ድል ተቀዳጅቷል።

ግንቦት 7 : የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ወያኔ ኦ ሚሊኒየም” አፕሬሽንን ላከሸፉ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አመራርና አባላት ያለውን አድናቆት ይገልፃል። ለወደፊቱም ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊደርሱ የሚችሉ መሆኑን በመገንዘብ የመከላከል ብሎም የማጥቃት ኃይሉን እንዲያጠናክር ይመክራል።
የንቅናቀዓችን እና የሕዝባዊ ኃይሉ አመራርና አባላት ለመስዋዕትነት የተዘጋጁ ናቸው። “ወያኔ ኦ ሚሊኒየም” ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ ትግላችን ይገታ ነበር ማለት አይደለም። ትግላችን መስዋዕትነትን የሚጠይቅ መሆኑን እናውቃለን። ጓዶች ሲወድቁ ሌሎች ሺዎች አርማቸውን አንስተው ትግሉን ይቀጥላሉ።
ትግሉ የሚጠይቀንን መስዋትነት ከፍለን ወያኔን ከሥልጣን አስወግደን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት የሆነባት ኢትዮጵያ እንደምትኖረን እርግጠኞች ነኝ።

ትግሉ መሯል፤ እኛም ዝግጁዎች ነን።

ድል ለግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

በሳውዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ላለው ጥቃት ተጠያቂው ወያኔ ብቻ ነው!!!


ወያኔ በትረ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ዓም ጀምሮ በአገራችንና በወገኖቻችን ላይ ከፈጸማቸው በርካታ ወንጀሎች አንዱ በህጋዊ መንገድ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንን ለባርነት ወደ አረብ አገራት በመላክ የአገራችንን መልካም ዝናና የህዝባችንን ክብር ያዋረደበት ተግባር ነው::


በወያኔ ንግድ ድርጅቶች ዋና ተዋናይነት ተመልምለው ለባርነት ሥራ የሚላኩትን ዜጎች በገፍ ስትቀበል የኖረቺው ሳውድ አረቢያ የሥራ ፍቃድ ያለቀባቸውን ከአገሯ ለማባረር ሰሞኑን በወሰደቺው የማዋከብ እርምጃ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን እየተደበደቡና ጎዳና ላይ እየተጎተቱ እሥር ቤት ታጉረዋል፤ ገንዘባቸውን ተዘርፈዋል፤ ከፖሊስ የሚደርስባቸውን ድብደባና እንግልት ለመቋቋም የሞከሩት በግፍ ተገድለው አስከሬናቸው ጎዳና ላይ ተጥሎሏል:: በርካታ ወጣት እህቶቻችን ደግሞ በአምስትና ስድስት የአረብ ጎረምሳ ወሲብ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ለአካልና መንፈስ ጉዳት ተዳርገዋል::

ይህ ሁሉ ሲሆን በአባይ ግድብ ግንባታ ሥም ገንዘብ ለመሰብሰብ ቦንድ ግዙ እያለ የሳውዲ ነዋሪ ሲጨቀጭቅ የኖረው በሳውዲ የወያኔ ኤምባሲም ሆነ አዲስ አበባ የሚገኙ ቅምጥል አለቆቹ ጥቃቱን ለማስቆም ድምጻቸውን ለማሰማት አለመፈለጋቸው ብቻ ሳይሆን ጥቃቱን ያደረሰውን የሳውዲ መንግሥት እርምጃ እውቅና የሚሰጥ መግለጫ በውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲህ መሰጠቱ እጅግ የሚያሳዝንና ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው::

ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በመላው አረብ አገር በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው የባርነት ስቃይ በፋሺስት ጣሊያን ዘመን በወገኖቻችን ላይ ከተፈጸመው የከፋና በተለይ በሴት እህቶቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ እንደ አገርና እንደ ህዝብ የገባንበት ውድቀትና ውርደት ማሳያ ነው ብሎ ያምናል::

ስለዚህ ይህንን ውርደት ማስቆም የምንችለው ለዚህ ሁሉ መከራና ውርደት የዳረገንን የወያኔንሥርዓት ታግለን በማስወገድ በምትኩ ለአገሩና ለህዝቡ ፍቅር ያለው፤ በያንዳንዱ ዜጋ ላይ የሚደርሰው መከራና ስቃይ የሚቆረቁረው፤ አገር ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጥሮ ለባርነት ሥራ ወደ ውጪ የተላኩትን የሚሰበስብ መንግሥት ማቋቋም ስንችል መሆኑ ታውቆ ወያኔን ለማስወገድ የተጀመረውን ትግል በተለይ ወጣቱ የህብረተሰባችን ክፍል በነቂስ እንዲቀላቀል የተቀረውም ህዝባችን አቅም የፈቀደውን ሁሉ እንዲያደርግ ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያቀርባል::

በመጨረሻም ምንም እንኳ በተለያዩ አረብ አገሮች በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ላለው መከራና ስቃይ ዋና ተጠያቂው ዜጎችን በህጋዊ መንገድ ለባርነት ከላከ ቦኋላ ጥቃት ሲፈጸምባቸው መከላከል ሳይፈልግ ዝም ብሎ እየተመለከተ ያለው የወያኔ አገዛዝ መሆኑ ባያጠያይቅም፣ የሳውዲ አረቢያም ሆነ ሌሎች አገሮች ተቆርቋሪ በለላቸው ዜጎቻችን ላይ የሚፈጽሙትን ወንጀል በአሰቸኳይ እንዲያቆሙና ተጠያቂዎቹንም ለህግ እንዲያቀርቡ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄን አቅም የፈቀደውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሁሉ ወያኔን ከማስወገድ ትግል ጋር አጣምሮ እንደሚገፋ ይገልጻል::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

የግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄን የህዝብ ግንኙነት

ታላቅ ሀገራዊ የተቃውሞ ጥሪ! ከወገኖቻችን ጐን በመቆም ብሄራዊ ክብራችንን እናስመልሳለን!!!

ታላቅ ሀገራዊ የተቃውሞ ጥሪ!

ከወገኖቻችን ጐን በመቆም ብሄራዊ ክብራችንን እናስመልሳለን

ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግሥት በኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈፀመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በመሆኑም በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ለማስቆምና የዜጐችን ህይወት ለመታደግ እንዲሁም ዜጐቻችን በአፋጣኝ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ መንግሥት እንዲያመቻች እና በተጨማሪም በዜጐቻችን ላይ ለደረሰው የአካል መጉደል፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈርና የህይወት መጥፋት ኃላፊነቱን የሚወስዱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ፤ ለተጐዱ ወገኖቻችንና ቤተሰቦቻቸውም አስፈላጊው ካሳ እንዲደረግላቸው ፓርቲያችን አበክሮ እያሳሰበ፤ የብሄራዊ ክብርና የወገኖች ስቃይ የሚያሳስባቸው አካላት በሙሉ በዚህ ታላቅ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የተቃውሞ እንቅስቃሴ አፈፃፀም፡-

1. በዜጐቻችን ላይ የአካል መጉደል፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ አስገድዶ መድፈርና የህይወት መጥፋት ያደረሰው የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ኢምባሲ በሚገኝበት ቦታ አርብ ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ጀምሮ የሚደረግ የተቃውሞ ሰልፍ፣
2. ከአርብ ጠዋት ጀምሮ እስከ እሁድ ማታ ድረስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሀዘን ልብስ (ጥቁር ልብስ) በመልበስ በግፍ ለሞቱና ለተንገላቱ ወገኖቻችን ሀዘናችንን መግለፅ፣
3. የእምነት ተቋማት አርብ በመስጊድ በጁምአ ሥነ ሥርዓት ላይ እና ቅዳሜና እሁድ በአብያተ ክርስቲያናት የፀሎት ሥነ ሥርዓቶች ላይ ወገኖቻችንን በፀሎት እንዲታሰቡ፣
4. ቅዳሜ በሚደረገው የኢትዮጵያና የናይጄሪያ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ተጫዋቾቻችን ጥቁር ሪቫን በክንዶቻቸው ላይ አጥልቀው እንዲጫወቱ፣ እንዲሁም መላው ደጋፊ ጥቁር ጨርቆችን በመያዝ ወይም ልብስ በመልበስ ሀዘኑንና ቁጭቱን እንዲገልፅ፣

በፓርቲው የተወሰነ በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ሲቪክ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዓለም አቅፍ ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ መላው ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጠራነው የተቃውሞ ሰልፍና እንቅስቃሴዎች ላይ በመገኘት ከግፉአን ወገኖቻችን ጐን መቆሙን እንዲያረጋግጥ በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
የወገኖቻችን ሰቆቃ እስኪያበቃ በፅናት እንታገላለን!!!

Monday, November 11, 2013

የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል!

በኃይሉ አርአያ (ዶ/ር) - የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት አባል

ሰሞኑን የኢሕአዴግ መንግሥት ይፈራል አይፈራም የሚል ጉዳይ ከፓርላማ ተነስቶ ወደ መገናኛ ብዙኃንም ደርሷል። ጉዳዩ የተነሳው የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ አዲሱ ፕሬዚዳንታችን በፓርላማ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ ባቀረቧቸው የማማሻሻያ ሐሳቦችና ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሰጡት ምላሽ ዙሪያ ነው። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዝ ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓም በአወጣው ዕትሙ ‹‹'ፈሪ' መንግሥት?›› በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ የማነ ናግሽ ጥሩ ትንተና አቅርቧል። የፍርኃት ነገር ከተነሳ ጋዜጠኛው ያነሳውን ለማዳበር በእኔም በኩል የምለው አለኝ። የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል። የኢሕአዴግ መንግሥት አሳምሮ ይፈራል ስል ግን በደፈናው አይደለም። በርካታ የማይፈራቸው ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ጦርነትን አይፈራም። በተለይ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ጥርሱን ነቅሎ ያደገበት ጉዳይ ነው። ሕግ መጣስን አይፈራም። ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን መጣስን አይፈራም። መዋሸትን አይፈራም።

የኢሕአዴግ መንግሥት ይፈራል ስል በተለይ የማተኩረው በአንድ ጉዳይ ላይ ነው። እውነት ላይ። የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን ይፈራል። እውነትን ስለሚፈራ እሱ ራሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲታወቅ ከሚፈልገው ውጪ ሕዝቡ እውነቱን እንዲያውቅ አይፈልግም። ይህ ደግሞ የአምባገነን አውራ ፓርቲዎች መንግሥታት አንዱና ዋናው የደባቂነትና የሸማቂነት መገለጫ ባህሪ ነው። የኢሕአዴግ መንግሥት እውነትን ለመፍራቱ በርካታ ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል። ለጊዜው ግን አራቱን ብቻ በምሳሌነት እንደሚከተለው ልጥቀስ።

1. ከቅርቡ የሶማሊያ ጦርነት ጋር በተያያዘ የእውነት መረጃን ከሕዝብ መደበቁ

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጎረቤት ሶማሊያ ውስጥ ገብቶ ከአክራሪና ከሽብር ኃይሎች ጋር ተዋግቷል። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ አሁንም እየተዋጋ ነው። ከማን ጋር ነው የተዋጋውም ሆነ የሚዋጋው? ለምንድን ነው የተዋጋው/የሚዋጋው? ጣልቃ ገብነቱ ሕጋዊ ነው አይደለም? ወደሚሉት ውስብስብ ጥያቄዎች አልገባም። እኔ የምገባው ወደ እውነት መረጃ አስፈላጊነት ነው። ጦርነት ነውና ወታደሮች ሞተዋል፣ ቆስለዋል። ገንዘብ ወጪ ሆኗል። የሞቱት የሕዝብ ልጆች ናቸው። ወጪ የሆነው የሕዝብ ገንዘብ ነው። ጦርነቱ የተካሄደው በውጭ ዕርዳታ ገንዘብ ነው እንዳልል፣ ነፍሳቸውን ይማርና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትራችን አቶ መለስ ዜናዊ ጦርነቱን በተመለከተ ፓርላማ ፊት በመቅረብ የአውራ ጣታቸውንና የሌባ ጣታቸውን ጫፎች አነካክተው ዜሮን በማሳየት ‹‹ሳንቲም ዕርዳታ አላገኘንም›› ማለታቸውን አስታውሳለሁ።

የሞቱት የሕዝብ ልጆች ናቸውና የኢትዮጵያ ሕዝብ ስንት ልጆቹ እንደሞቱ እውነቱን ለማወቅ ይፈልጋል። እውነቱን የማወቅ መብትም አለው። የወጣው የሕዝብ ገንዘብ ነውና ሕዝቡ ያወጣውን ለማወቅ ይፈልጋል። እውነቱን የማወቅ መብትም አለው። እኔ እስከማውቀው ድረስ በተለይ በእነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ የኢሕአዴግ መንግሥት የጉዳዩ ባለቤት ለሆነው ሕዝብ በይፋ የሰጠው መረጃ የለም። ምናልባት ለአሜሪካ፣ ለአፍሪካ ኅብረትና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ‹‹እኔ እንደ መንግሥት እየከፈልኩ ያለሁትን መስዋዕትነት ዕወቁልኝ›› በሚልና የባለውለተኛ ወሮታ ለማግኘት በሚስጥር አሳውቆ ሊሆን ይችላል። ይህ መደረጉ አይከፋም። መጀመሪያ መስማት ያለበት ግን ባለጉዳዩ ሕዝብ ነው። ለምንድን ነው ባለፈው እውነታውን ለሕዝብ ያላሳወቀውና አሁንም ቢሆን የማያሳውቀው? እውነትን ስለሚፈራ ነው። መደበቅና መሸመቅ ዓይነተኛ ባህሪው ስለሆነ ነው። ለሕዝብ የማወቅ መብት አክብሮት ስለሌለው ነው።

ጦርነቱን በበጎ ጎኑ አይተነው፣ ሠራዊታችን ሶማሊያ የገባው ሉዓላዊነታችንን ላለማስደፈር፣ ድንበራችንን ለማስከበር፣ የአገራችንንና የአካባቢያችንን ሰላም ለመጠበቅና ከዚያም ባለፈ የዓለማችንን ሰላም ለማስከበር ለሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው እንበል። ታዲያ እንደዚህ ላለ ‹‹የተቀደሰ›› ዓላማ የተከፈለን መስዋዕትነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀርቶ ዓለም እንዲያውቀው ይደረጋል እንጂ ይደበቃል?

ይህን አጭር ጽሑፍ ለማዘጋጀት ሳስብ እስቲ አሜሪካ በቪየትናም ጦርነት የሞቱባትን ወታደሮች ለሕዝብ በይፋ አሳውቃ እንደሆነ ልይ ብዬ ኢንተርኔት ውስጥ ገባሁ። "Us Soldiers Killed in Vietnam" በሚል ‹‹ጉግል›› ሳደርግ ያገኘሁት መረጃ ብዛትና ዝርዝር የሚገርም ነው። በአጭሩ ግን 58,220 ወታደሮች እንደሞቱ፣ የሟቾቹ ቁጥርም በዘር፣ በፆታ፣ በሃይማኖት፣ በመጡበት ‹‹ስቴት››፣ በሠራዊት ምድባቸው (አየር ኃይል፣ ምድር ጦር፣ መርከበኛ፣ ወዘተ.)፣ በአሟሟታቸው ሁኔታ (በውጊያ፣ በድንገተኛ አደጋ፣ በሕመም፣ እርስ በርስ መገዳደል፣ ወዘተ.)፣ በጦርነቱ መጀመሪያ የሞተ ወታደር ስም፣ ጦርነቱ ሊፈጸም ሲል በመጨረሻ የሞተ ወታደር ስም፣ ወዘተ፣ ተዘርዝሮ ተቀምጧል። በተመሳሳይ ሁኔታ የኢራቅንና የአፍጋኒስታንንም አየሁ። መረጃው ከሞላ ጎደል በታመሳሳይ ሁኔታ ተቀምጧል። ወጪ የሆነው የገንዘብ መጠን ሁሉ ተቀምጧል። ከዚያ በኋላ እስቲ መንግሥታችንም ምናልባት ሳናውቀው መረጃ አስቀምጦ እንደሆን ብዬ ለማየት ሞከርኩ። የውጭ ጋዜጦችና ሌሎች የዜና ምንጮች በዜና መልክ ካስቀመጧቸው ጥቂት ተባራሪ መረጃዎች በስተቀር ምንም ነገር የለም።

ለምንድን ነው የአሜሪካ መንግሥት ከላይ የተጠቀሱትን ጦርነቶች በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለሕዝቡና ለተቀረው ዓለም ሲሰጥ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሊያ ያካሄደውን ጦርነት በተመለከተ መረጃ ትንፍሽ ያላለው? ይህን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ብዙ ማለት ይቻላል። በአጭሩ ግን የአሜሪካ መንግሥት መረጃ የሰጠው እውነትን ስለማይፈራ ነው። በራሱ ስለሚተማመንና ሕዝቡንም ስለሚያምን ነው። የሕዝቡን መረጃ የማግኘት መብት ስለሚያከብር ነው። የኢሕአዴግ መንግሥት መረጃ ያልሰጠው በእኔ እምነት እውነትን ስለሚፈራ፣ በራሱ ስለማይተማመንና ሕዝቡንም ስለማያምንና መረጃ የማግኘት መብቱንም ስለማያከብር ነው።

የሳውዲ መንግሥት በዜጎቻችን ላይ እየፈፀመ ያለውን ግፍ በጥብቅ እናወግዛለን!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
------------------------------------------------
የሳውዲ መንግሥት በዜጎቻችን ላይ እየፈፀመ ያለውን ግፍ በጥብቅ እናወግዛለን!!
----------------------------------------------------
ቀጣይ ርምጃችንንም ለህዝቡ ለቅርቡ ይፋ እናደርጋለን!
------------------------------------------------
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
------------------
በአባቶቻችን ደም ታፍራና ተከብራ የኖረችው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በገዢው ፓርቲ ቸልታ፣ የፖሊሲ ችግርና የሀገር ፍቅር ማጣት የተነሳ ዜጎቿ በውርደት እንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ዛሬም መገለጫችን ስደት፣ ጦርነት፣ በዜግነታችን ክብር ማጣትና ሞት ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ሀገራዊ ውርደትና ሞት ከተበላሸ ሥርዓት የሚወለድ፣ ካልተስተካከለ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚፈጠር ነው፡፡

ፓርቲያችን የተሻለ ኢኮኖሚ ፍለጋ፣ የተሻለ ማህበራዊ ፍትህ ለማግኘትና አሰቃቂ የሆነውን ፖለቲካ ሽሽት ኢትዮጵያውያን ዜጎች ሀገራቸውን ጥለው እንደሚሰደዱ ያምናል፡፡ የመልካም አስተዳደር እጦትና ሥራ ፍለጋ የሚያንከራትታቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር የትየለሌም ነው፡፡ ጋሎፕ የተባለ አለማቀፍ ጥናት እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ጎልማሶች መካከል 46% የሚሆኑት ከሀገራቸው በመሰደድ ወደ ሌላ ሀገር ሄደው ለመኖር ይፈልጋሉ፡፡ ይህ የሆነው የተስተካከለ ስርዓት ባለመፈጠሩ ነው፡፡

ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በተለይ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው እንግልት፣ ድብደባ፣ ግድያና ለህይወት አስጊ በሆነ ሥፍራ ማጎር ከኢሰብአዊነትም በላይ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነው፡፡ ዜጎቻችን ዋስትናና ከለላ አጥተው በሳውዲ ፖሊስ በየጎዳናው ሲፈነከቱና ሲገደሉ ከማየት በላይ አሰቃቂ ነገር የት አለ? በሳውዲ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመው ወንጀል የሀገር ሉዓላዊነትም ጉዳይ ነው፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያን መንግሥት የዲፕሎማሲ ደካማነትና በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ባህላዊ ግንኙነቶች ላይ ተጽእኖ መፍጠር ያልቻለ መሆኑን ያስረዳናል፡፡ ደካማ መንግሥት፣ ደካማ አስተዳደርና የራሱን ስልጣን ብቻ የሚያዳምጥ ፓርቲ ዜጎቹን ያስደፍራል፣ ሉዓላዊነትን ያስነካል፣ ኢትዮጵያዊ ክብርን ያዋርዳል፡፡

አንድነት ፓርቲ የሰቆቃ ዘመናችን የሚያጥረው ለሀገር የሚያስብ የተስተካከለ ሥርዓት ሲፈጠር ብቻ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያውያንን ሰብአዊ ክብር ማስጠበቅ የተሳነው መንግሥት ላይ ጫና ማድረግና በሠላማዊ ትግል መቀየር ወሳኝ ነው፡፡ አንድነት የሳውዲ አረብያ መንግስት በዜጎቻችን ላይ የፈፀመውን ድርጊት ተከትሎ ያለውን አቋም እንደሚከተለው ያቀርባል፡፡

1. የሳውዲ መንግሥት በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈፀመ ያለውን የሰብአዊ ክብር ገፈፋ፣ እስር፣ ግድያና ማዋከብ በአስቸኳይ        እንዲያቆም፡፡
2. ለፈፀመው ሰብአዊ ጥፋት ተጠያቂ እንዲሆንና ለተጎጂዎች ካሳ እንዲከፍል፡፡
3. የኢትዮጵያ መንግስት ለተጎጂዎች አስቸኳይ ርዳታና ለችግራቸው መፍትሔ እንዲሰጥ፡፡
4. የኢትዮጵያ መንግሥትም ይህንን በፈፀመው የሳውዲ መንግሥት ላይ ጠንካራ አቋም እንዲይዝና ለኢትዮጵያውያን በችግሩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጥ እንጠይቃል፡፡

በተጨማሪም በዜጎች ላይ የተፈፀመውና እየተፈፀመ ያለው ግፍ የገዢው ፓርቲ የዲፕሎማሲ ድክመት ያመጣው መሆኑንና እንዲሁም የአምባሳደርነት ሥልጣን የሚሰጠው በችሎታ ሳይሆን በፓርቲ ታማኝነት እንደሆነ ያሳየን ነው፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግሩን ከሥሩ ለማድረቅ የሚያስፈልገው የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማሻሻያ መሆኑ ታውቆ ህዝቡ የተስተካከለ ሥርዓት የመፍጠር ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እያቀረብን በተከታይ የምንውደውን ርምጃ ለህዝቡ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለኢትያጵያና ኢትዮጵያዊነት!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ህዳር 2 ቀን 2ዐዐ6 ዓም
አዲስ አበባ

Sunday, November 10, 2013

Assassinating popular leaders will only invigorate the people

On Thursday November 7, 2013; the Valiant Ginbot 7 Popular Force intelligence unit foiled the assassination plot that targeted the secretary of Ginbot 7: Movement for Justice, Freedom and democracy, and commanders and high ranked officers of Ginbot 7 Popular Force. This futile attempt by the coward TPLF regime that took place in Eritrea territory is yet another sign and proof that this blood-stained regime cannot and does not survive without spilling the blood of innocent Ethiopians. Ginbot 7 and the Ethiopian people at large are outraged by the TPLF regime’s recent assassination attempt, and they strongly denounce this shameful act that does not serve any purpose.

In the last twenty two years, the TPLF leaders assaulted or killed anyone who dare did anything to slightly oppose them, they hated one group of innocent people for no apparent reason, and they even managed to turn one of the most peaceful country in the world into a land of hate politics. All in all, genocide, hate, random killing, mass killing and now targeted killing – the TPLF regime has no shortage of reasons for guilt. Ginbot 7, Movement for Justice, Freedom and Democracy praises the heroic acts of the Ginbot 7 Popular Force in foiling the assassination attempt on its leaders and commanders, and uses this opportunity to pass a clear message to the arrogant TPLF leaders that Ginbot 7 Popular Force is part of the popular struggle that will never and can never be undermined by killing its leaders. In its attempt to perpetuate its power, the TPLF regime has gone to another inglorious dimension of targeted assassination of political leaders. Ginbot 7 wants to remind the TPLF regime and its killing squad that the shame and the sour defeat they were forced to swallow on Thursday November 7 is just the tip of the iceberg.

Once again, Ginbot 7 denounces the recent cowardly act of the Ethiopian regime in its strongest sense, and wants to remind the Ethiopian people that this is a wakeup call that must be answered with due diligence. Torturing and killing popular leaders has always been a worthless coward act that invigorates the people and creates more courageous leaders. We Ethiopians should cheerfully acknowledge that in its futile attempt to harm us, our enemy has wounded itself, now it’s up to us to hit the nail on the coffin.

We shall overcome!

Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy

Public Relation

Saturday, November 9, 2013

ተሻሻለ የተባለዉ የመከላከያ አዋጅ የአንድ ብሄር የበላይነቱን ማረጋገጡ ታወቀ

የአገሪቱን የመከላከያ አዋጅ ተመልክቶ መሻሻያ ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ የወያኔ ፓርላማ ተቋሙ የሚታይበትን ዋናዉንና ትልቁን ችግር ሳይመለከት ወያኔን የሚጠቅሙ ህጎችንና ደንቦችን ብቻ በማሻሻል የይስሙላ ስራ ሰርቶ ተበትኗል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸዉ የመከላከያ፤ የደህንነት፣ የህግ፣ የፍትህና የአስተዳደር ጉዳዩች ቋሚ ኮሜቴዎች ሰሞኑን ተወያይተዉ በወሰዱት እርምጃ 98 መቶ የሚሆኑት የአገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ከአንድ ብሄር ብቻ እንዲሆኑ መንገድ በከፈተዉ መዋቅራዊ አሰራር ላይ ምንም አይነት መሻሻል ወይም ለዉጥ አለማድረጉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው መኮንኖች ተናግረዋል። አንዳንድ የመከላከያ ሚኒስቴር ሹሞች የተሻሻለዉ አዋጅ እስከ ዛሬ የነበሩትን ህጎች ሁሉ የሚለውጥና መከላከያን የሚያሳድግ ነው ቢሉም ይህ በቻይናና በእስራኤል ህጎች ላይ ተንተርስሶ የተደረገዉ መሻሻያ መሰረታዊ የሆነውንና ወያኔ ሆን ብሎ ያዋቀረዉን የመከላከያ አወቃቀር እንዳይነካ መደረጉ ታውቋል።

ወታደራዊ ማእረግ እድገትን፣ ለመኮንኖች የሚሰጠዉን መኖሪያ ቤትና የሞት ቅጣት አፈጸጻምን በተመለከተ ለየት ያለ ትኩረት እንዲደረግባቸዉ አጥብቀዉ ያሳሰቡት የፓርላማዉ አባላት መሰረታዊ የሆነውንና አገሪቱን በማበጣበጥ ላይ ያለዉን በህወሀት የበላይነትና በዘር ላይ የተመሰረተዉን የመከላከያ አደረጃጀት እንዲቀየር ምንም አይነት ሙከራ ሳያደርጉ ወይም ሳይጠይቁ አይናቸዉን ጨፍነዉ አልፈዉታል።

ረቂቅ አዋጁን የተመለከቱ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች አዋጁ መከላከያን ከአገር ይልቅ የአንድ ፓርቲ አገልጋይ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ በየበረሃዉና በሰው አገር የሚንከራተተውን ተራውን ወታደር የሚጠቅም ምንም ነገር የለውም ሲሉ ትችታቸዉን ሰንዝረዋል። ፓርላማዉ የተነጋገረበትንየመከላከያ ረቂቅ አዋጅ የታማዦር ሹሙ/ጀኔራል ሳሞራ የኑስ፤ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ብርጋዴል ጀኔራል ዘውዱ፤ የ44ኛ ክፍለ ጦር ሁለተኛ ሬጅመንት ዋና አዛዥ ሊተናንት ኮሎኔል አዘዘው መኮንን፤ በሱዳን የተመድ የሰላም አስካበሪ አዛዠ ሌተናልት ጀኔራል ዮሀንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም፣ የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሌተናልት ጀኔራል ሳእረ መኮንን፣ የማእከላዊ እዝ አዛዥ ሌተናት ጀነራል አበበው ታደሰ ፣ሜጀር ጀነራል ሞላ ገብረማርያም እና አቶ ፀጋየ በርሄ ውይይት አድርገውበት ረቂቅ አዋጁን መደገፋቸዉ ታዉቋል። ይቀጥላል።

ወያኔ ዉስጥ “እርቅ አስፈላጊ ነው” ነዉ የሚሉ ድምጾች እያየሉ መምጣታቸዉ ተሰማ

ሀያ ሁለት አመት ሙሉ ልባቸዉ በትዕቢትና በጥላቻ ተሞልቶ የተቃወማቸዉን እያሰሩና ለሚቀርብላቸዉ የእንተባበር ጥያቄ ሁሉ ጆሮ ዳባ ልብስ ሲሉ የሰነበቱት የህወሀት ጀብደኞች ዛሬ ኢትዮጵያን ግራ የሚያጋባና በአፍ ሊነገር የማይችል የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መክተታቸዉን አምነዉ የእርቅ ሃሳብ ላይ ማተኮር መጀመራቸዉን ጎልጉል የተባላ ድረ ገጽ ላይ የሚታተም ጋዜጣ የወያኔንና የኢህአዴግን ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቅሶ ዘገበ።ህወሀትም ሆነ ኢህአዴግ ዉስጥ አፈና፤ ስለላና አለመተማመን እየተባባሱ መምጣታቸዉንና በእነዚህ ሁለት ድርጅቱ ውስጥ በተፈጠረ አለመተማመን ሳቢያ ስጋት የገባቸው የህወሀት ሰዎች በእርቁ ሃሳብ እየገፉበት መምጣታቸዉን ዉስጥ አዋቂ ምንጮቹ ተናግረዋል።

ቀድሞዉንም ቢሆን በዋና ዋናዎቹ የህወሀት መሪዎች ገመድ ታስሮ የቆየዉ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ዉስጥ ያለዉ መተባበርና መግባባት ዛሬ ያ ገመድ ተበጥሶ በመካከላቸዉ አለመተማመን መንገሱ በስፋት እየተነገረ ነዉ። ዛሬ በተለይ ከመለስ ሞት በኋላ በህወሃትና ህወሃት በሚያዛቸው በሦስቱ አቻ ፓርቲዎች መካከል ያለው የመከባበርና የመገዛት ስሜት ተበላሽቶ፣ በኢህአዴግም ሆነ በህወሃት ዉስጥ የተፈጠረዉ ከፍተኛ ልዩነትና በሙስና ስም የተጀመረውን ዘመቻ ፓርቲዎቹን መዉጣት የማይችሉበት አዘቅት ዉስጥ እየከተተ መሆኑን ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸዉ። አንደ ጎልጉል ጋዜጣ የመረጃ ምንጭች አባባል ህወሀትና ኢህአዴግ ዉስጥ በጣት ከሚቆጠሩ እጅግ በጣም ጥቂት ግለሰቦች ዉጭ የሁሉም ሰዉ እጅ በሙስና የተጨማለቀ በመሆኑ ዛሬ አንዱ ሌላዉ ላይ ጣቱን እየቀሰረ “ማን ንጹህ ሆኖ ማንን ይጠይቃል?” እየተባባሉ የእርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ መግባታቸዉ ታዉቋል።

ህወሀት ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት በተጓዘባቸዉ መንገዶች በተለይም በሁሉም ነገር ከሁሉም በላይ ሆኖ ሊቀጥል እንደማይችል በራሱ በህወሀት ዉስጥን በየድርጅቶቹ ዉስጥ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ በስፋት እየተነገረ ሲሆን፤ ይህ ከሰሞኑ ይፋ ባልሆነ መንገድ የቀረበው “ታርቀን አገራችንን እንምራ” የሚለዉ የእርቅ ጥያቄ የቀረበዉ በያዝነዉ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሲኖዶስ ጉባኤ ላይ የተሳመዉን ከፍተኛ የተቃዉሞና አገራችንን አበላሻችኋት የሚለዉን ድምጽ ተከትሎ እንደሆነ ከብዙ የፖለቲካ ተንታኞች አካባቢ እየተደመጠ ነዉ። ከዚህ ቀደም ተደርጎና ተሰምቶ በማይታው መልኩ የሃይማኖት አባቶች ወያኔን በግልጽ ማውገዛቸውና “አገሪቷን ገደላችኋት” ብለዉ መኮነናቸው በወያኔ/ኢህአዴግ ዉስጥ ከፍተኛ መደናገጥ እንደተፈጠረ ለማወቅ ተችሏል። ወያኔ እራሱ በሾማቸዉ በቀድሞው ፓትሪያርክ አማካኝነት የቤተክርሲቲያን ተቋማትን እንደተቆጣጠረ የሚታወቅ ሲሆን ፈቃድና አሁን ግን አንደለመደዉ ቤተክርስቲያኒቱን መቆጣጠርና አመራሮቹን አንደበታቸውን ማፈን የማይችልበት ደረጃ መድረሱን በቅርብ ግዜ ከተደረገዉ የሲኖዶሱ ጉባኤ የተገነዘበ ይመስላል። ከዚህ በጨማሪ ከእስልምና እምነት ተከታዮች አካባቢ ከሁለት አመት በላይ የተካሄደዉን መልስ ያላገኘዉ የድምጻችን ይሰማ ጉዳይ ወያኔን የማይወጣበት አዘቅት ዉስጥ ከትተዉታል።

ባለፉዉ የቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤ ላይ የተነሱት ሀሳቦች ወያኔ ነገሮች ቀስ በቀስ ከእጁ እንደወጡበት የሚያሳይ እንደሆነ ያመለከቱት አንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የኢህአዴግ አባላት እግራቸዉ አንጅ ልባቸዉ ከድርጅቱ ጋር እንዳልሆነ ተናግረዋል ። አብዛኛው የኢህአዴግ አባልና ደጋፊ ድርጅታቸዉ ዉስጥ ሰላማዊ ለውጥ ተካሂዶ ኢህአዴግን ወደ እርቅ ለመገፋፋት ከፍተኛ ፍላጎት አንዳላቸዉ እየተነገረ ነዉ።

እርቅ ከተፈለገ ለምን በግልጽ አይቀርብም በሚል ለቀረበላቸው ሃሳብ ባለስልጣኑ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆኑም “ከማን ጋር ነው የምንታረቀው? እነማንን ነው ለእርቅ የምንጋብዘው? እርቅ ጠያቂ መሆን ያለበትስ ማን ነው?” የሚሉት ጥያቄዎች ዉስጥ ለዉስጥ እንደሚንሸራሸሩ አልሸሸጉም። በቅንጅት ጊዜም በተመሳሳይ የዕርቅ ፍላጎትና “ሥልጣን እናስረክብ” የሚል አቋም ተነስቶ እንደነበር ያስታወሱት እኚሁ ባለስልጣን፤ በወቅቱ ሃሳቡ ተግባራዊ ያልሆነው “ወያኔዎችን ወደመጡበት ጠራርገን እንመልሳቸዋለን” በማለት አንድ የቅንጅት አመራር ለሕዝብ መፈክር ሲያወርዱ ከተሰማ በኋላ ነበር የሚልና ብዙም አመኔታ የሌለዉ አስተያየት ሰንዝረዋል።

ወያኔ በ2007ቱ ምርጫ እንዲያጅቡት ጠፍጥፎ ከሰራቸው ድርጅቶች ጋር በግምገማ መወጠሩ ተሰማ

በወያኔው ምርጫ ሊሳተፉ የሚችሉ ሰላማዊ ፓርቲዎች መሳሳብና ትብብር ከመጠን በላይ ያስደነገጠው ወያኔ በራሳቸው መቆም የተሳናቸውንና እህት የሚላቸውን የኦሮሞውን ኦህዴድ፣ የአማራውን በአዴን፣ እንዲሁም የደቡቡን ደህዴን ዳዴ ወፌ ቆመች እያለ መቆም እንዲችሉ እያለማመደ መሆኑ ከያቅጣጫው እየተሰማ ነው። ፋሽስት ወያኔ እነዚህን ዘርን መሰረት አድርገው የተቦደኑ ጉጅሌዎች መጀመሪያውኑ ሆን ብሎ ከሰባበራቸው በሗላ ለምን እንደገና ቀና ለማድረግ እንደሚደክም ለብዙዎች ግልጽ አይደለም። ሆኖም ግን ከሌላ አቅጣጫ የሚሰማው ደግሞ ወያኔ በነዚህ ቡድኖች ውስጥ እያደረገው ያለው ይህ ሁሉ ግምገማና ማስፈራራት መጪውን ምርጫ በዚያም በዚህ ብሎ እስከሚያሸንፍ ድረስ ብቻ ነው ከዚያ በሗላ እንደገና ሰባብሮ አጣጥፎ መደርደሪያ ላይ ይሰቅላቸዋል ይላሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለይ በኦህዴድ እየተከናወነ ያለው ግምገማ ከታችኛው እስከ ላይኛው የአመራር አካላቱ በሙስና የተጨማለቁ በመሆናቸው መፈራራት የሌለበትና ቀልድ ነው ተብሏል። ከዚህ በፊት ከነበረው የወያኔ ልምድ እንደሚታወቀው፤ የወያኔ ግምገማ ታዛዥነትን ለማረጋገጥ ስለሆነ እየነቁ ነው የተባሉትን በማስወገድ የበለጠ ታዛዦችን ቦታ በማስያዝ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

በፋሽስ ወያኔ ነብሰ ገዳዮች በግፍ የተጨፈጨፉ ሰማእታት 8ኛ ዓመት ተዘከረ

ግንቦት 7 ፋሽስት ወያኔ ፍትህንና ዴሞክራሲን ባደባባይ በጠራራ ፀሐይ በመጨፍለቅ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰላማዊ ወገኖቻችን የሞት በሽዎች ለሚቆጠሩት ደግም የመቁሰልና መጎሳቆል እንዲሁም ለአስር ሺዎች እስራት ምክንያት በመሆን ነጻነታችንን ገፍፎ የቀበረበትን፣ ወገኖቻችን በግፍ ያለቁበትን ስምንተኛ ዓመት በሀዘን እያስታወሰ ይገኛል። ”ሁሉም ነገር ድንገት ብልጭ ብሎ ድርግም እንደሚል ብልጭታ እንዳልነበረ ሆነ። እባክህ ፈጣሪ ህልም አድርገው ብለው የተመኙ እንደነበሩ ሁሉ በተወሰነ መልኩ ህልም ነው ብለው ያመኑም አይጠፉም” ይላሉ ከዚያች ጨለማ ቀንና ከወያኔው አጋዚ ጦር የጭካኔ ርምጃ የተረፉ ባለ ታሪክ። ”በእጃችን ምንም ነገር አልነበረም፤ የተሰረቀ ድምጻችን ይመለስ ስንል በድብቅ ሳይሆን በግልጽ ነበር የወጣነው፤ ወንድ ሴት፣ ትልቅ ትንሽ ሁላችንም አንድ ላይ ነበርን፤ ፍጹም የሆነው ሰላማዊ እንቅስቃሴያችን በሗላ ላይ ባየነው መልኩ ይጠናቀቃል ብሎ ያሰበ ማንም አልነበርም፤ ግን እንደዚያ ነው የሆነው። ይላሉ አይናቸው እንባ እንደሞላ የያኔውን በማስታወስ።

ሌላጫው የጊዜው ተጎጅ ደግሞ፤ ”የፋሽስት ወያኔ አጋዚ ጦር ባለ በሌለ ሃይሉ ሕዝቡን ጨፈጨፈው ራሱ ባመነው እንኳ ወደ ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰላማዊ ሰልፈኞች አለቁ። ዘለው ካልጠገቡት ህጻናት እርዳታ እስከሚያስፈልጋቸው አእሩጋን ሁሉንም አጨዳቸው። ይህም ሁሉ ከሆነ በሗላ እርምጃው ከመጠን ያለፈ አልነበረም ተባለና ታለፈ። ጊዜ ጉዞውን አላቆመም ስምንት ዓመት አስቆጠረ ወያኔም ግድያውን አላቆመም። የንጹሃን ወገኖቻችንን ደም በግፍ ያፈሰሱት ሳይጠየቁ ፋሽስት ወያኔ ግን ለሌላ እርድ ለሌላ ጭፍጨፋ ራሱን እያዘጋጀ፣ ቢላውን እያፋጨ ይገኛል” ካሉ በሗላ ”እኔ እምለው፣ በእርግጥ እኔ አቅም የለኝም ሽማግሌ ነኝ። ግን ግን ልጆቻችንን፣ ወንድም እህቶቻችንን ዐይናችን ስር ከጨፈጨፈ አረመኔ ቡድን ጋር አብሮ ተባብሮ መስራት መልካም ነው እንዴ? ይላሉ።

ምንም እንኳ በአካል የተጎዱትን ሳይጨምር እስከ ሁለት መቶ የሚሆኑ እንደተጨፈጨፉ ቢገለጽና ፋሽስት ወያኔ ቢያምንም እርምጃው ካቅም በላይ አልነበርም በሚል ሰበብ ብቻ እስካሁንም ከዚህ የግፍ ግድያ ጋር በተያያዘ ማንም እንዳልተጠየቀ የታወሳል። ይህ ሁሉ ግፍ ተደብቆ የሚቆየው ግን ኢትዮጵያ ለሕዝቦቿ የሚጨነቅ፣ በህግ የበላይነት የሚያምን እውነተኛ ኢትዮጵያዊ መሪ እስክታገኝ ድረስ ብቻ ነው የሚሉ ግን ጥቂቶች አይደሉም።

በሌላ በኩል ደግሞ ዛሬም መብታቸውን በሚጠይቁ ግለሰቦች ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ወይም አባላት ላይ፣ የፋሽስት ወያኔ አሽከር አንሆንም በሚሉ ጠንካራ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና መጎሳቆል ቀጥሏል። አሁን በቅርቡ እንኳ በአንድነት ፓርቲ የአመራር አባል ላይ የደረሰው ለመናገር የሚሰቀጥጥ፣ ከህግ ውጭ የሆነና ከባህል ያፈነገጠ በየትኛውም ሃይማኖት ተቀባይነት የሌለው የግፍ ድርጊት በወያኔ ባለጌ የደህንት ሰው ተብየዎች መፈጸሙ ሕዝባችንን በከፍተኛ ሁኔታ እያነጋገረ መሆኑ እየታየ ነው።

ኢሕአዴግ እና የሃይማኖት ነጻነት

(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፱ ጥቅምት ፳፻፮ ዓ.ም.)

ተመስገን ደሳለኝ

… ኢሠፓ መራሹ መንግሥት በኢሕአዴግ ከተተካ ጥቂት ወራት ቢያልፈውም፣ የተራዘመው የእርስ በርስ ጦርነት ያልደረሰባቸው በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችን ገና በቅጡ አልተቆጣጠራቸውም፤ በአናቱም በኢሠፓ መንግሥት ሽንፈት ሳቢያ እንዲበተን ከተገደደው የአገሪቱ መደበኛ ወታደር አብዛኛው ከእነትጥቁ የትውልድ መንደሩንና ቤተሰቡን መቀላቀሉ በአገሪቱ ላይ ከባድ ፍርሃት አንብሯል፡፡ በሰላም ወጥቶ ለመመለስ ርግጠኛ መኾን የማይቻልበት ከባቢያዊ አየርም አስፍኗል፡፡ በበርካታ ቦታዎች ተጠንተውና ታቅደው የሚፈጸሙ ወንጀሎችም ከአምስት እስከ ዐሥራ አምስት በሚደርሱ ወታደሮች የተደራጁ ልዩ ልዩ ሕገ ወጥ ቡድኖች በየማዕዘኑ እያቆጠቆጡ መኾኑን አመላክትዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የዐዲስ አበባ ቆዳ ስፋትና የነዋሮዎቿ የአኗኗር ዘይቤን በቀላሉ ለመልመድ የተቸገሩ ተጋዳላዮች ለትንሽ ለትልቁ ግርግር ጠመንጃን እንደ መፍትሔ መምረጣቸው ችግሩን አባብሶታል፡፡ ጉዳዩ እያሳሰባቸው የሄደው የኢሕአዴግ ዋነኛ መሪዎችም እንዲህ ዐይነቱን አለመረጋጋትና ሥርዐተ አልበኝነት ለመቆጣጠር የመንፈሳዊ መሪዎች አስተዋፅኦ ወሳኝ ስለ መኾኑ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል(እንደ ቀደሙት ሥርዐቶች ኹሉ ለቅቡልነት ከሚጠቀሙበት በተጨማሪ ማለት ነው)፡፡ ይኹንና በመንበሩ ላይ የነበሩት ፓትርያርኩ አቡነ መርቆሬዎስ አገር ለቀው እንዲወጡ በመደረጉ ክፍተት ተፈጥሯል፡፡

ይህ ጊዜ ነው ከ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. ጀምሮ [ከኢየሩሳሌም ተሰደው] መኖርያቸውን አሜሪካን አገር ያደረጉ አንድ መንፈሳዊ አባት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ የተወሰነው፤ በጥሪው መሠረትም ወደ አገራቸው ሲገቡ መንግሥት የክብር አቀባበል አደረገላቸው፡፡ እኚኽ አባት ዛሬ በመንበረ ፕትርክናው የተሠየሙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ነበሩ፡፡ ኾኖም ከሳምንት ሽር ጉድ በኋላ አቡነ ‹‹የኢዲዩ አባል ነበሩ›› የሚል ወሬ በአመራሩ አካባቢ በስፋት መሰራጨቱ ያልተጠበቀ ዱብ ዕዳ አስከተለ፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ኢሕአዴግ እና ኢዲዩ በ፲፱፻፸ዎቹ መጀመርያ ትግራይ እና ጎንደር ውስጥ በርካታ መሥዋዕትነት ያስከፈለ ውጊያ ማድረጋቸው ብቻ አልነበረም፡፡ የመጀመርያዎቹ ሊቀ መንበሮች ስሁል ገሰሰ እና መሐሪ ተኽሌ(ሙሴ) ‹‹የተገደሉት በኢዲዩ ነው›› የሚለው ወሬ በድርጅቱ ውስጥ ከጫፍ ጫፍ የተናኘና የታመነበት ጉዳይ መኾኑ ነበር፡፡ በዚህም ላይ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ግራ ዘመምነት ተደማምሮ አቡነ ማትያስ በወቅቱ ወደ ታሪክነት ከተቀየረ ዓመታትን ባስቆጠረው ኢዲዩ ተፈርጀው ከታጩበት የፕትርክና መንበር ተገፈተሩ፡፡

ከዚህ በኋላ ነበር አብላጫውን የትጥቅ ትግል ዘመን በአሜሪካ ያሳለፉት አሰፋ ማሞ እና ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ‹‹ዉድብ›› የሰጠቻቸውን ተልእኮ ተቀብለው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ያመሩት፤ እናም ቀድሞም ትውውቅ ወደነበራቸው ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ዘንድ ሄደው ለፕትርክና ወንበር መታጨታቸውን አበሠሯቸው፡፡ በእንዲህ ያለ መንገድ መንግሥት የቀባቸው አቡነ ጳውሎስም እስከ ኅልፈታቸው ድረስ አወዛጋቢ መሪ ኾነው ዘልቀዋል፡፡

(በነገራችን ላይ በአሜሪካ ለመጀመርያ ጊዜ ከሲኖዶሱ ተነጥሎ የቆመ ቤተ ክርስቲያን የመሠረቱት አቡነ ጳውሎስ እንደነበሩ ይነገራል፡፡ አቡኑ ደርግ ለጥቂት ዓመታት አስሮ ከለቀቃቸው በኋላ ወደ አሜሪካ ሄደው የፈጣሪያቸውን ሰማያዊ መንግሥት ሲሰብኩ ቆይተው የህወሓት ሠራዊት ክንዱ እየበረታ በቁጥጥሩ ሥር ያዋላቸው ከተሞችም እየበዙ ሲሄዱ እርሳቸውም ስብከታቸውን ወደ ትግርኛ ቋንቋ ከመቀየራቸውም በላይ ለ‹ነጻ አውጭ›ው ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ ያሰባስቡ ጀመር፡፡ የሥርዐት ለውጥ መደረጉን ተከትሎም በፖሊቲከኞች በተቀነባበረ ሤራ ከአቡነ ጳውሎስ ጋራ ቦታ የተለዋወጡት አቡነ መርቆሬዎስም፣ እዚያው አሜሪካ ‹ተተኪ›ያቸው የጀመሩትን ብሔር ተኮርና ከሲኖዶሱ የተገነጠለ ቤተ ክርስቲያን አስፋፍተው ዛሬ ለደረሰበት ‹የጎንደሬ ማርያም›፣ ‹የትግሬ ገብርኤል›. . .ለተሰኘ አሳፋሪ ክፍፍል ዳርገውታል፡፡ በርግጥ ለአቡኑ[አቡነ መርቆሬዎስ] ከአገር መውጣት የኢሕአዴግ እጅ እንዳለበት እንድናምን የሚያስገድደን በቅርቡ ታምራት ላይኔ ‹‹በእኔ ፊርማ ነው ያባረርናቸው›› ማለቱን ዊኪሊክስ ካደረሰን መረጃ በተጨማሪ በትጥቅ ትግሉ ዘመን ህወሓት በተቆጣጠራቸው በትግራይና ወሎ ነጻ መሬቶች በሚገኙ ከተሞች ያሉ ነዋሪዎችን ቀስቅሶና አደራጅቶ ፓትርያርኩ ላይ ‹‹ሽጉጥ ታጣቂ ጳጳስ››፣ ‹‹ቀይ ደብተር ያለው/ለኢሠፓ አባላት የሚሰጥ/ የሸንጎ ተወካይ››. . .የመሳሰሉትን መፈክሮች እያሰሙ በተቃውሞ ሰልፍ እንዲያወግዟቸው ማስተባበሩን ስናስታውስ ነው)፡፡

ዛሬስ የሃይማኖት ነጻነት የት ድረስ ነው?

ከላይ ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብዬ በደምሳሳው ለመጠቃቀስ እንደሞከርኹት፣ ኢሕአዴግ በሃይማኖት ጉዳይ እጁን ጣልቃ ማስገባት የጀመረው ክንዱ ሳይፈረጥም ገና በረሓ ላይ ሳለ ነበር፡፡ በዚህ ኹኔታ የተጀመረው ጣልቃ ገብነት ዛሬም ድረስ ተባብሶ ቀጥሏል፤ ምንም እንኳ በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ እንደማይገባ በደፈናው ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ን በመጥቀስ በተደጋጋሚ ለማስተባበል ቢሞክርም ያለፉት ዓመታት ተጨባጭ ተግባሮቹ የሚመሰክሩት ግልባጩን ነው፡፡ ድርጅቱ ራሱም ቢኾን ጥያቄው በተነሣ ቁጥር ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ን የሚጠቅሰው ለስሙ እንጂ ሕጉ ተግባራዊ አለመኾኑን ሳይረዳ ቀርቶ አይደለም፤ አቶ ተፈራ ዋልዋም በ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. ኅዳር/ታኅሣሥ ወር ከታተመችው ሐመር መጽሔት ጋራ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ጉዳዩን አስመልክቶ የሰጡት አስተያየት የኢሕአዴግን አጭበርባሪነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡-

‹‹ኢሕአዴግ እኮ የሚመራው መንግሥት በደርግም ጊዜ፣ በኃይለ ሥላሴም ጊዜ እንደሚታወቀው ‹የቤተ ክርስቲያን ሥራ አስኪያጅ ሹምልን› ተብሎ ተጠይቆ ‹የለም ራስዋ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትሾማለች እንጂ እንደ ቀድሞው መንግሥት አይሾምላችኁም› የሚል መልስ የሰጠ መንግሥት ነው፡፡››

በሕዝበ ሙስሊሙ ተመርጦ ለእስር የተዳረጉት የኮሚቴ አባላትም በአንድ ወቅት ለሚመለከተው የመንግሥት ባለሥልጣን የጻፉት ደብዳቤ ጣልቃ ገብነቱን በግልጽ ያሳያል፡-

‹‹መንግሥት እንደ መንግሥት ሕዝቡ ተበድዬአለኹ፤ ምርጫ ይካሔድ፤ የመጅሊሱን አመራር አላመንኹበትም፤ ውክልና የለውምና ሕገ ወጥ ነው ያለውን አካል ሕገ ወጥነቱ እንዲረዝም ምርጫውን እርሱው እንዲያካሒድ መወሰን ሕዝብን ግራ አጋቢ ነው፡፡››

ሥርዐቱ በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ እንደማይገባ ለማሳመን ይህን ያህል ቢዳክርም በቅርቡ ‹‹የፀረ አክራሪነት ትግል የወቅቱ ኹኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች›› በሚል ርእስ የተዘጋጀው ባለ 44 ገጽ ሰነድ፣ መንግሥት በዘወርዋራ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ሙሉ በሙሉ የሚያምን ኾኖ አግኝቸዋለኹ፤

‹‹የመንግሥት መዋቅራትን ሴኩላር መንግሥት መኾናችንን ዐውቆ የመንግሥትን መዋቅር ተጠቅሞ የራሱን ሃይማኖት መሠረት ያደረገ አገልግሎት ከመስጠት ሙሉ በሙሉ ያልጸዳ መኾኑን የተለያዩ ጥቂት የማይባሉ ገሃድ የወጡ መገለጫዎች አሉ፡፡ እንዲያውም የትኛውም አክራሪ ኃይል ከመዋቅር(ከመንግሥት) አካል በርታ ሳይባልና ሽፋን ሳይሰጠው የሚንቀሳቀስ እንደሌለ አማኞቹ በገሃድ ይገልጻሉ፡፡››

መቼም ይህን ያነበበ ዜጋ መረጃው የተገኘው በመንግሥት ከተዘጋጀ ሰነድ ሳይኾን በኒዮሊበራሊስት›ነት ከተፈረጁት እነ‹‹ሂዩማን ራይትስዎች›› እና ‹‹አምንስቲ ኢንተርናሽናል›› ቢመስለው አይደንቅም፡፡ ሐቁ ግን ይኸው ነው፡፡ አገዛዙ ላለፉት ኻያ ሁለት ዓመታት መንግሥት እና ሃይማኖት እንዲለያዩ ማድረጉን ሲለፍፍ ከመቆየቱም በላይ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን የዘገቡ ጋዜጠኞችን ከሥሦ ዛሬም ድረስ ፍርድ ቤት እያመላለሳቸው እንደኾነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ አንጻር ይመስለኛል ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ የሚገኙት የእነ አቡበበከር መሐመድ ክሥ፣ የሼኽ ኑር ሑሴን ግድያ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ እየተሰነዘሩ ያሉ ውንጀላዎችንና መሰል ፍረጃዎችን አምኖ ለመቀበል የተቸገሩት፡፡

ያም ኾነ ይህ ሃይማኖትን ብቻ ሳይኾን ዕድርና ዕቁብንም ሳይቀር ‹ካልተቆጣጠርኹ ሞቼ እገኛለኹ› በሚል የቁጥጥር ልክፍት የተያዘው ኢሕአዴግ፣ በተለይም 99.6 ድምፅ አግኝቼ አሸንፌአለኹ ብሎ ካወጀበት ከምርጫ ፳፻፪ ማግሥት ጀምሮ ‹‹አናት ላይ ከተቀመጡ መሪዎቻቸው በቀር ሙሉ በሙሉ አልተቆጣጠርናቸውም›› የሚላቸውን የኦርቶዶክስ ክርስትና እና የእስልምና እምነቶችን ዋነኛ አጀንዳ አድርጎ እየሠራ ለመኾኑ በርካታ መረጃዎች አሉ፡፡

በ፳፻፫ ዓ.ም. ኅዳር ወር ‹‹የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና የኢትዮጵያ ሕዳሴ›› በሚል ርእስ በአቶ መለስ ዜናዊ ተሰናድቶ የተሰራጨው ጥራዝ፣ የሥርዐቱን ቀጣይ አካሔድና ይህን ኹናቴ የሚያሳይ ከመኾኑም በተጨማሪ ዛሬም ድረስ በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ መንግሥት የሚያዘጋጃቸው ሥልጠናዎችም ኾኑ ጥናታዊ ጽሑፎች መነሻ ሐሳባቸው ይኸው ዳጎስ ያለ ጥራዝ እንደኾነ ይነገራል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የስደተኛ ዜጐች እንግልት እንዲቆም ጠየቀ

ሰማያዊ ፓርቲ አረብ አገር በሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው እንግልትና ስቃይ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ትላንትና ረፋድ ላይ በጽ/ቤቱ “በመንግስት ቸልተኝነት በስደት ላይ ባሉ ዜጐች እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ ይቁም” በሚል መርህ በሰጠው መግለጫ እንዳብራራው፤ ዜጐች በኢህአዴግ ዘመን በሚደርሱባቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጫናዎች በህጋዊና ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ከሀገራቸው መሰደዳቸውንና ለእንግልት፣ ለሞትና ለስቃይ መዳረጋቸውን ጠቁሟል፡፡

“ፓርቲያችን የዜጐች ስደትና እንግልት ያሳስበዋል፤ መንግስት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥም ድምፃችንን እናሰማለን” ብለዋል፤ የፓርቲው አመራሮች፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ የፓርቲው የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ ወጣት ዮናታን ተስፋዬ እና የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ ዜጐች የሚሰደዱት በአገሪቱ ላይ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍትህ ባለመኖሩ ነው ያሉ ሲሆን በነዚህ ጫናዎች ምክንያት ዜጐች በየበረሃው በኮንቴይነር ታሽገው እየሞቱ፣ በባዕዳን ኩላሊታቸው እየተሸጠ፣ በባህር ላይ ሲያቋርጡ በባህር አውሬዎች እየተበሉ መሆኑን አብራርተዋል።

በተለይም ሰሞኑን በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጐች እየደረሰባቸው ያለውን አስከፊ እንግልትና ስቃይ አጥብቀው እንደሚያወግዙ ተናግረዋል፡፡ “ዜጐች በባዕድ አገር በሚደርስባቸው በደል የኢህአዴግ መንግስት ከዜጐች ጐን በመቆም ስቃያቸውና በደላቸው እንዲቆም በመጠየቅ አጋር መሆን ሲገባው፣ በአገር ውስጥ ባሉ ሚዲያዎች “ሀገሪቱ በልማት እያደገች ባለችበትና ስራአጥነት እየተቀረፈ ባለበት ወቅት ዜጐች ሀገር ለቀው መሰደዳቸው ስህተት ነው” በሚል በዜጐች ላይ ማላገጡን ያቁም ሲል ፓርቲው አሳስቧል፡፡ “በተለይ በሳውዲ አረቢያ በዜጐች ላይ እየደረሰ ስላለው እንግልት፣ የአለም ትልልቅ ሚዲያዎች አጀንዳ አድርገው እየተነጋገሩበት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ቸልታ “ይህቺ አገር መንግስት የላትም ወይ’ ያስብላል” ያሉት ኢ/ር ይልቃል የኢትዮጵያ ሚዲያስ ይህን አጉልቶ ካላወጣና ከዜጐቹ ጐን ካልቆመ ፋይዳው ምንድን ነው ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የስዊድን ጋዜጠኞች በህገ ወጥ መንገድ አገር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ እና ሲታሰሩ የአገራቸው መንግስት ጥፋተኛ ናቸው ብሎ ችላ ሳይል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተደራድሮ በአጭር ጊዜ እንዲፈቱ ማድረጉንና አገራቸውም ሲገቡ የጀግና አቀባበል እንደተደረገላቸው የገለፁት ሊቀመንበሩ የኢትዮጵያ መንግስት ዜጐቹ በግልጽ እየተሰደዱ እየተንገላቱና እየሞቱ እጁን አጣጥፎ መቀመጡ የሚያስተቻቸው እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ብርሃኑ በበኩሉ፤ በእድሜና በእውቀት ያልበሰሉ ህፃናት በህጋዊና ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከአገር እየወጡ ለስቃይ ሲዳረጉ፣ በኤጀንሲዎች እና በህገወጥ ደላሎች ላይ ጥብቅ እርምጃ መውሰድና ዜጐቹን በተለያየ መንገድ ማስገንዘብ ሲገባው፣ ጭራሽ በየክልላቸው ፓስፖርት እንዲያገኙ እያደረገ ማበረታታቱ እንደሚያሳዝነው ተናግሯል፡፡ “ኤጀንሲዎችን ማገድና ፓስፖርትና ቪዛ መከልከል አሁንም ትክክለኛ መፍትሔ አይደለም” ያለው ብርሃኑ፤ መንግስት ፖሊሲዎቹን ማሻሻልና ማስተካከል እንዳለበት አሳስቧል፡፡

የፓርቲው የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ ወጣት ዮናታን በበኩሉ፤ “ኢህአዴግ ለወጣቶች ስራ የሚሰጠውና የሚያደራጀው አባል እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው” ካለ በኋላ፤ “አብረን ከዩኒቨርሲቲ የወጣን ሆነን አባል ስለሆኑ ብቻ ትልልቅ ስራና ሃላፊነት ላይ የተቀመጡ ወጣቶች አሉ፡፡ እነሱ በመኪና እኛ በእግር እንተላለፋለን” ሲል አማሯል፡፡ “ኢትዮጵያ ውስጥ ልማትና እድገት ካለ ዜጐች ለቅንጦት አይሰደዱም” ያሉት የፓርቲው አመራሮች፤ በመንግስት ቸልተኝነት በኢትዮጵያ የስራ አጥ ቁጥር 40 በመቶ መድረሱን ገልፀዋል - አለም አቀፍ መረጃ መሆኑን በመጥቀስ፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ አገር ብድር ከ12 ቢሊዮን ዶላር በላይ መሆኑን፣ የአገር ውስጥ የብድር መጠን 80 ቢሊዮን ብር መሆኑን፣ ባለፉት 10 ዓመታት ከኢትዮጵያ 11.7 ቢሊዮን ዶላር በህገወጥ መንገድ መውጣቱን እና መሰል መረጃዎችን የገለፁት አመራሮች፤ እነዚህ መረጃዎች የአለም ባንክና የአይኤምኤፍ መሆናቸውን ገልፀው፤ “ይህ ባለበት ስራ አጥነት ተቀርፏል፤ ልማት አለ የሚባለው በህዝብ ላይ ማሾፍ ነው” ብለዋል፡፡

ፓርቲው ባወጣው ባለአምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ፤ የዜጐችን ህይወት ለመታደግ መንግስት በአስቸኳይ ከሳኡዲ መንግስት ጋር እንዲነጋገር፣ የሳኡዲ አረቢያ መንግስት በዜጐች ላይ እያደረሰ ያለው በደል የሰብአዊ መብት ጥሰት በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲያቆም፣ ዜጐችን ለስደትና ለስቃይ የሚዳርጉ የችግሩ መንስኤዎች፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች ለፍርድ እንዲቀርቡ እና ዜጐች የሚሰደዱበትን ምክንያት በጥልቅ በመመርመር አስከፊውን ስደት ለማቆም መንግስት የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲያደርግ… የሚሉት ይገኙበታል፡፡ ፓርቲው በቀጣይነት ጥናቶችንና መረጃዎችን በማሰባሰብ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልፆ፤ ለዚህ ስኬት ህብረተሰቡ፣ የሲቪክ ተቋማት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከጐኑ እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፡ አዲስ አድማስ

Friday, November 8, 2013

የግንቦት 7 መሪዎችን ለመግደል የተጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ!!!

በኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃለፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብራዊ ደህንነት አማካሪ በአቶ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ ከሸፈ።

ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ለግድያ የተላከው ሙሉቀን መስፍን የተባለው ግለሰብ በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በእየደረጃው ከሚገኙ የደህንነት ሀላፊዎች ጋር በስልክ ሲያደርግ የነበረው የስልክ ለውውጥ በህዝባዊ ሀይሉ የመረጃ ክፍል ሲቀዳ ቆይቷል።

ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም በሚል የተመራው የግድያ ዘመቻ -በነገው እለት ጥቅምት 30/2006 ዓም ሊካሄድ ታቅዶ እንደነበር የድምጽ መረጃው ያመለክታል።

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይል ሰራዊት የምረቃ በአል በነገው እለት የሚካሄድ መሆኑን መነሻ በማድረግ በእለቱ በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎችንና የኤርትራ ባለስልጣናትን ለመግደል የታቀደው ዘመቻ ከመነሻው ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ፣ በፍጻሜው ዋዜማ ላይ ሲድርስ ሙሉቀን መስፍን የተባለውን ለግድያ የተላከውን ግለሰብ ህዝባዊ ሀይሉ በቁጥጥር ስር በማድረግ ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም የተባለው ኦፕሬሽን ከሽፏል።

የድምጽ መረጃውን ኢሳት ዌብሳይት ላይ ተከታተሉ

http://ethsat.com/video/esat-breaking-news-nov-08-2013/

የሚዲያ ነፃነት ይረጋገጥ፤ የታሰሩ ጋዜጠኞችም በአስቸኳይ ይፈቱ!!! ከአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
    =================================================================
የሚዲያ ነፃነት ይረጋገጥ፤ የታሰሩ ጋዜጠኞችም በአስቸኳይ ይፈቱ!!!
================================================
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
      =================================================================
ከጥቅምት 27 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ትቅምት 29 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስድስተኛው የአፍሪካ ሚዲያ መሪዎች ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡ ፓርቲያችንም ይህንን ጉባዔ በአንክሮ እየተከታተለው ሲሆን በርካታ የአፍሪካ ሚዲያ ባለሙያዎች የፕሬስ ነፃነት ባልተረጋገጠበት፣ የግል ጋዜጦችና መፅሄቶች ተልካሻ ሰበብ እየተፈለገ በሚዘጉበት፣ ጋዜጠኞች ሀገር ጥለው እንዲሰዱ በሚደረግበት፣ በሀገር ውስጥ አንድም የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ ባልተቋቋመበት፣ ስርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኞች ወደ እስር የሚወረወሩበትና የሚታሰሩበት ገዥ ስርዓት ወዳላት ሀገራችን መጥተዋልና አቋማችንን ማሳወቅ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
ጉባኤው በሀገራችን መካሄዱ ላይ ምንም ተቃውሞ ባይኖረንም በገዥዎች የሚጨቆነው የአፍሪካ ሚዲያ ላይ ለውጥ ያመጣል የሚል ተስፋ ግን የለንም፡፡ ምክንያቱም ለሚዲያዎች ነፃና ገለልተኛ አለመሆን አምባገነን ገዥዎችና ስርዓታቸው ቀን ከሌሊት ነፃ ሚዲያና ነፃ አስተሳሰብ እንዳይኖር ስለሚሰሩ ነው፡፡ ስለዚህ ሚዲያውን የሚጨቁኑትና የሀሳብ ልዕልና እንዳይኖረው የሚያደርጉት ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት አምባገነን መሪዎች መሆናቸውን በስብሰባው ላይ የታደሙ የአፍሪካ መሪዎች ልብ እንዲሉ እንፈልጋለን፡፡

ፓርቲያችን አንድነት አጥብቆ እንደሚያምነው የአፍሪካ የሚዲያ ባለሙያዎች የሚዲያ ነፃነት የሚረጋገጠው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሲረጋገጥ መሆኑን አምነው በቅድሚያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዳይገነባ አንቀው በመያዝ የህዝቡንና የሚዲያውን ነፃነት ጨፍላቂ የሆኑትን አምባገነን ስርዓቶች መታገል እንደሚገባ፤ ለዚህም ሚዲያው አበክሮ እንዲሰራ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በአምባገነናዊ ስርዓት ውስጥም ነፃ ሚዲያ መመስረት የማይታሰብ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡

ወደ ሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣም ስርዓቱ ለነፃ ሚዲያ ማበብ ቁርጠኝነት ያነሰው በመሆኑ ከማስመሰል ባለፈና ለስርዓቱ አጨብጫቢ የሆኑ ሚዲያዎችን ከመቀፍቀፍ በዘለለ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ መጎልበት አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ተች ሚዲያዎችን ሊፈጥር አልቻለም፡፡ ይልቁንም በተቃራኒው በግል ተነሳሽነት ለመንቀሳቀስ የሚሞክሩትን ከማጥፋትና ጋዜጠኞችን ከማሰር ቦዝኖ አያውቅም፡፡ በተለይም ነፃው ፕሬስ በመንግስት የተቀነባበረና ከፍተኛ ጥቃት ሰለባ ነው፡፡ ስለዚህ በሀገራችን የተገኙ የአፍሪካ የሚዲያ ባለቤቶች የኢትዮጵያ መንግስት ለሚዲያ ነፃነት መረጋገጥ እንዲሰራ ተጨባጩን የሀገራችንን የሚዲያ እድገት እንዲመረምሩ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

በመጨረሻም በኢትዮጵያችን ያለው አምባገነን ስርዓት በርካታ ጋዜጠኞችን እስር ቤት አጉሯል፡፡ ጠንካራ የግል ጋዜጦችንም ዘግቷል፡፡ ለክቡራን የአፍሪካ ሚዲያ ባለቤቶችና አዘጋጅ ለሆነው አካል ጥያቄ እናቀርባለን፡፡ በሀገራችን ሃሳባቸውን በነፃነት ስለገለፁ ብቻ ለእስር የተዳረጉት አንዲፈቱና የሚዲያ ባለሙዎችም ይህንን በአካል ቃሊቲ በመሄድ ከእስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ የሱፍ ጌታቸውና ዝዋይ የሚገኘውን ውብሸት ታየን በማነጋገር እንዲያረጋግጡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ እግረ መንገዳችሁንም በኢህአዴግ ስርዓት ውስጥ ነፃ ፕሬስ ምን ማለት እንደሆነ ትረዳላችሁ፤ ስንቶቹ ሀገራቸውን ጥለው እንደተሰደዱ ታውቃላችሁ፡፡ 

ክብርና ነፃነት ለነፃ ሚዲያና ጋዜጠኞች!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
ጥቅምት 29 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አባባ

Thursday, November 7, 2013

ሀገራዊ ውርደት እንዲያበቃ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ!!!

የወያኔ ገዢ ጉጅሌ በባህርዩ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት አጋጥሟት የማያውቅ ፍጹም ኢሰብዓዊና ነውረኛ ስብስብ እንደሆነ ለመረዳት ኢትዮጵያዊያንን ለማዋረድ የሚጠቀሟቸውን ተግባራትና ቃላትን ማጤን ይበቃል።

በሶማሌ ክልል የኦብነግን ታጣቂዎች ቅስም ለመስበር ልጃገረዶችንና እናቶችን ብቻ ሳይሆን ወንዶችንም ጭምር በቤተሰብ ፊት በደቦ የሚደፍሩ፤ ለዚህ ተግባር የሠለጠኑ የልዩ ጦር አባላት መኖራቸው በስፋት የሚታወቅና በተደጋጋሚም የተዘገበ ጉዳይ ነው። ወያኔ፣ የኦጋዴን ወገኖቻችን በዚህ ጥቃት ተሸማቀው ያነገቡትን መሣሪያ ጥለው ፀጥ-ለጥ ብለው ይገዛሉ ብሎ ተስፋ ያደረገ ቢሆንም እየሆነ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። ዛሬ የሶማሌ ክልል ወንዱም ሴቱም፤ ወጣቱም አዛውንቱም በፀረ-ወያኔ አቋም የጋራ መግባባት ላይ ደርሷል። በኦጋዴን የወያኔ አስነዋሪ ጥቃት የፈጠረው ምሬት በውጭ አገራትም በሚደረጉ የፀረ ወያኔ ትግሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች ተሳትፎ እንዲጎለብት አድርጎታል። በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።

በአፋር ክልልም ተመሳሳይ ጥቃት የዘወትር ትዕይንት እየሆነ መጥቷል። የአፋር የወል የግጦሽ መሬቶች ለሸኮራ አገዳ ልማት በሚል ሰበብ ሲነጠቁ የተቃወሙ የአገር ሽማግሌዎች ተደብድበዋል፤ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ተደፍረዋል። በአፋርም ውስጥ ለጾታዊ ጥቃት የሰለጠነ የወያኔ ልዩ ጦር ተሰማርቶ በሴቶች ብቻ ሳይሆን በወንዶችም ላይ አስነዋሪ ጥቃት አድርሷል። በአፋር ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በአፋር ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።

በጋምቤላ ውስጥ ወያኔ ወገኖቻችን ከፈጀ በኋላ በሕይወት የተረፉትም ቅስማቸውን ለመስበር ጾታዊ ጥቃት በመሣሪያነት ተጠቅሟል፤ አሁንም እየተጠቀመ ነው። በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት በሁላችንም ላይ የደረሰ ነውና ቁጭታቸውን እንጋራለን። በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ጥቃት ሀገራዊ ውርደት ነው።

Wednesday, November 6, 2013

Africans must speak up for journalist jailed in Ethiopia

Tuesday 5 November 2013


The award-winning Ethiopian journalist Eskinder Nega will turn 45 this month in Kaliti prison outside Addis Ababa whilst serving an 18-year sentence as a convicted terrorist. The government in Addis would have the world believe he is a reckless, even racist, agitator bent on violent revolution. Yet, a review of the evidence against him and his writings reveals a thoughtful and principled man whose only crime has been to urge, peacefully and publicly, Ethiopia's rulers to deliver on their long broken promise of peaceful, democratic reform.

"Democracy is so important to Ethiopia, because we need it to moderate the differences between civilization and civilization," Eskinder said in a 2010 interview. "I hope the EPRDF (the ruling party) will be pragmatic enough to realise reform would be the better option, even for itself," he added. "I believe in forgiving… that we shouldn't have any grudge against the EPRDF, despite what it has done. I believe that the best thing for the country is reconciliation. I believe in the South African experience, that model."

In February 2011, inspired by the Egyptian military's tolerance of pro-democracy protesters in Tahrir Square, Eskinder wrote an article urging Ethiopian soldiers to heed their example, should demonstrations break out in Addis Ababa. The column appeared on a US-based Ethiopian news website blocked inside his country. In response, the state security detained Eskinder, accusing him of inciting the public against the government. A senior police official threatened to kill him if he did not stop writing about the Arab Spring.

A few months later, after the government invoked a vague terrorist plot to imprison prominent journalists, lawyers, teachers, academics and other dissidents, Eskinder spoke out again: "None of the recent detainees under the terrorism charges remotely resemble the profile (of a terrorist). Debebe is probably the ultimate antithesis of the fanatic, his pragmatism, his easy nature, defines him," he wrote, referring to prominent actor Debebe Eshetu. "Neither do journalists Woubshet (Taye) and Reeyot (Alemu) and opposition politician Zerihun Gebre-Egzabher fit the profile. The same goes for the calm university professor, Bekele Gerba."

Just five days after writing those words, Eskinder was arrested again, and charged under the same terrorism charges. As evidence, the prosecution submitted a video of a town hall meeting of an opposition party where Eskinder expressed his opinion that if repression continued, the people's patience would run out and there could be Arab Spring protests in Ethiopia. The prosecution claimed that by making such statements he was using his constitutional right to freedom of expression as a cover to overthrow that very constitution.

የመከላከያ የሒሳብ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር እንዳይታዩ የሚያደርግ አዋጅ ተረቀቀ


 በ2004 በጀት ዓመት ባልተሟላ ሰነድ ከ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ባላይ ወጪ በማድረጉ በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጠንካራ ትችት የቀረበበት የመከላከያ ሚኒስቴር የሒሳብ መዛግብቱን ዋናው ኦዲተርን ጨምሮ ለማንኛውም አካል ሚስጢር ማድረግ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ።

በሚኒስትሮች ም/ቤት ፀድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰሞኑን የቀረበው የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅ ሰነድ በአንቀጽ 72 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት አገራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ለመከላከል ሲባል እጅግ ጥብቅ ሚስጢር ብሎ የሰየማቸውን የሰው ኃይል ፕሮፋይል፣ የሒሳብ መዝገቦችና ሰነዶች እና የክፍያ ማስረጃዎች ለማንም አካል እንዳይገለጹ ሊያደርግ ይችላል ሲል ደንግጓል።

በአንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ሚኒስቴሩ ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ የሚያስገባቸው ለአገር መከላከል ዓላማ የሚውሉ ዕቃዎችና መሳሪያዎች ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ በነጻ እንደሚያስገባ የደነገገ ሲሆን፤ ዕቃዎቹን እንዲያስፈትሽ ወይም ሰነዶቹን እንዲያስመረምር እንደማይገደድ አስቀምጧል።

ሆኖም አንቀጽ 70 ንዑስ አንቀጽ 2 ከላይ ሚኒስቴሩ ከሚከተሉት ምንጮች የሚያገኘውን ገቢ የሚኒስትሮች ምክር ቤትን እያስፈቀደ ለመከላከያ አቅም ግንባታ እንዲውል ያደርጋል። በዚህ መሰረት የመከላከያ ተቋማት በሠላም ጊዜ የሚኖራቸውን የማምረትና አገልግሎት የመስጠት አቅም ለገቢ ማስገኛ ተግባር እንዲውል በማድረግ የሚገኘውን ገቢ፣ ለመከላከያ ጠቀሜታ የማያስፈልጉ ንብረቶችን በማስወገድ የሚገኘው ገቢ፣ በተቆጣጣሪ ባለስልጣንነት ከሚመራቸው ድርጅቶች የሚገኘውን የትርፍ ድርሻ እና ከሠላም ማስከበር ስምሪቶች የሚገኘው ገቢ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ እንዲመረመር እንደሚያደርግ በረቂቅ አዋጁ ተደንግጓል።

የፌዴራል ዋናው ኦዲተር ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ማጠናቀቂያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው የ2004 ዓ.ም የኦዲት ሪፖርት መሰረት የመከላከያ ሚኒስቴር ባልተሟላ ሰነድ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ካደረጉ ዘጠኝ ያህል የመንግስት ተቋማት መካከል 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በማስመዝገብ የላቀ ድርሻ መያዙ ይፋ ከተደረገ በኋላ የመከላከያ ሚኒስትሩን አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ጨምሮ ሌሎች የመከላከያ ሹማምንት ሪፖርቱን ሳይቀበሉት ቀርተዋል። ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝም በዚያው ወቅት በፓርላማ መድረክ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በየትኛውም አገር የመከላከያ ሚስጢር የተጠበቀ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ የመከላከያን ሚስጢሮች በጠበቀ መልኩ ኦዲት ለማካሄድ የሚያስችል ሕግ እንደሚወጣ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

ምንጭ፡ ሪፖርተር ጋዜጣው 

የመኪና አደጋ የደረሰበት የኢትዮ ምህዳር ጋዜጠኛ ሕይወቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ ነው

*ሕዝብ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ ተማፅኖ ቀርቧል
*የጋዜጣው ዋና አዘጋጅና ስራ አስኪያጅ በእስር ላይ ናቸው

በዘሪሁን ሙሉጌታ

ባለፈው ዕረቡ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮምህዳር ጋዜጣ ላይ ያቀረበውን የ300ሺህ ብር የስም ማጥፋት ክስ ለመከታተል ወደ ሐዋሳ አቅንተው ጉዳያቸው ከተከታተሉ በኋላ ለስራ በከተማዋ በባጃጅ ሲንቀሳቀሱ በሞተር ሳይክል አደጋ ከደረሰባቸው የኢትዮ ምህዳር ጋዜጠኞች አንዱ ጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነ የሕክምና እርዳታ ቢደረግለትም ጤናው መሻሻል ባለማሳየቱ ሕይወቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ ነው።

ጋዜጠኛ ኤፍሬም አደጋው በደረሰበት ወቅት አንገቱ አካባቢ አከርካሪው ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት አጥንቱ በመሰበሩና ነርቩን በመነካቱ ሁለቱን እግሮቹን ማንቀሳቀስ ተስኖት ነበር። ነገር ግን በኮሪያ ሆስፒታል በተደረገለት ሰዓታትን የፈጀ ቀዶ ጥገና ጤናው መጠነኛ መሻሻል ቢያሳይም በገጠመው የአተነፋፈስ ችግር ባለፈው ቅዳሜ አመሻሽ ላይ በድጋሚ ቀዶ ጥገና ተደርጎለታል። ከዚህ ቀዶ ጥገና በኋላም በራሱ መተንፈስ ባለመቻሉ በመሳሪያ ኃይል በመተንፈስ ላይ ነው። ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮም ከፍተኛ ክትትል በሚደረግበት ሪከቨሪ ክፍል ውስጥ ይገኛል። የአተነፋፈስ ሁኔታው እስከሚሻሻል ድረስም በሪከቨሪው ውስጥ እንደሚቆይም ለማወቅ ተችሏል።

ጋዜጠኛ ኤፍሬም ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከተመረቀ በኋላ በነጋድራስ ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት በሌሎች ተቋም በሕዝብ ግንኙነት መስራት ከጀመረ ጥቂት አመታትን ያስቆጠረ ወጣት ጋዜጠኛ ነው። ቤተሰቦቹም ሆኑ የሚሰራበት ተቋም ገና አዲስ በመሆናቸው ለህክምና የሚሆን የገንዘብ እጥረት ገጥሞታል።

በጋዜጠኛ ኤፍሬም ላይ ጉዳቱ እንደደረሰ የሰሙት በተለያዩ ጋዜጦች የሚሰሩ ጋዜጠኞች ባለፈው ቅዳሜ በአዲስ አድማስ ቢሮ በመሰባሰብ ምን እናድርግ ሲሉ ከተወያዩ በኋላ አምስት አባላት ያሉበት ኮሚቴ አቋቁመው ልጁ በሕክምና ተረድቶ የሚድንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የእርዳታ ማሰባሰቢያ የሚሆን የባንክ ሂሳብ ከፍተዋል።

ሆኖም ከልጁ የሕክምና ውስብስብነትና ከደረሰው አደጋ ከፍተኛነት የተነሳ ለህክምና እየተጠየቀ ያለው ገንዘብ አሁን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 130ሺ ብር መድረሱን የኮሚቴው አባል የሆነው ጋዜጠኛ ብዙአየው ወንድሙ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልጿል።

Tuesday, November 5, 2013

አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ አንድ (በፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

ጥቅምት 2006

ወያኔና የነፖሊቲካ አጋሮቹ የሚያደርጉትን ለእነሱ የሚመች አከፋፈል ትተን አበሻን ለሁለት እንክፈለው፤ ሆድ ያለውና ሆድ የሌለው፤ ወይም የሚበላና የማይበላ፤ ዛሬ የምናገረው ሆድ ስላለው ወይም ስለሚበላው አበሻ ነው፤ አታውቁት እንደሆነ ተዋወቁት፤ በአጠቃላይ ስንመለከተው ግን የአበሻ ፍቅርም ሆነ ጠብ ለሆድ ነው፤ አበሻን የሚያጣላው፣ የሚያነታርከው፣ የሚያቧጭቀው የሆድ ነገር ነው፤ ለመብላት ነው፤ አንዳንዴም ሎሌውን ለማብላት ነው፤ ግብር ለማግባት ነው።

አዳም አበሻ ሳይሆን አይቀርም፤ ሁሉንም ነገር ብላ ከተከለከለው በቀር ብሎ ያስቀመጠው ይመስላል፤በላባችሁ ወዝ ብሉ ተብለው አዳምና ሔዋን መረገማቸውን አበሻ ገና አልሰማም፤ አበሻ የተፈጠረው ገነት ውስጥ ቁጭ ብለህ ያለውን ሁሉ ብላ በተባለበት ጊዜ ነው፤ እግዚአብሔር አበሻን ሁሉንም ብላ ሲለው ምናልባትም በጆሮው ጭራሽ አታስብ ብሎት ይሆናል፤ እስቲ በመጀመሪያ ስለምግብ እንነጋገር።

በሌላው ነገር ሁሉ ኋላ-ቀር ቢሆንም በምግብ ጉዳይ አበሻን የመበልጠው ያለ አይመስለኝም፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምግብ ውድድር ቢያደርጉ በምግብ ዓይነት፣ በጣዕም፣ በአሠራሩ ጥበብ አበሻ በቀላሉ እንደሚያሸንፍ በፍጹም አልጠራጠርም፤ የቱ አገር ነው ወዝ ያለውና ለስላሳ እንጀራ ያለው? በነጭ ጤፍ በሠርገኛው፣ በጥቁር ጤፍ፣ በስንዴውና በገብሱ፣ በማሽላውና በዘንጋዳው፣ በበቆሎው በእጅ ለመጠቅለል፣ በጉሮሮ ለማውረድ እንደአበሻ አመቻችቶ የሚሠራ የቱ ሕዝብ ነው? እንጀራው ሲፈለግ ቃተኛ፣ ሲፈለግ አነባበሮ እየሆነ በቅቤና በአዋዜ ርሶ ሆድ የሚያርስ ምግብ ማን ይሠራል፣ ከአበሻ በቀር?

የዳቦው ዓይነትስ ቢሆን ብዛቱና ጣዕሙ! ድፎው፣ የዶሮ ዳቦው፣ አምባሻው፣ ሙልሙሉ፣ ቂጣውስ ቢሆን ስንት ዓይነት ነው?

አበሻ ከጥንትም ጀምሮ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ ስለዚህም ይጾማል፤ ለእግዚአብሔር ሲል፣ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ሲል ከወዳጁ ከምግብ፣ በተለይም ከሥጋና ከቅቤ ይለያል፤ መጾም ዓላማው ለነፍስ ቢሆንም ለሥጋም ትልቅ ጠቀሜታ አለው፤ በአካል ውስጥ የተጠራቀመውን ጮማና ሞራ ለማራገፍ ይረዳል፤ አበሻ ግን ምኑ ሞኝ ነው፤ በሆድ ቀልድ የለም! የጾም ምግብ የሚባል ነገር ፈጥሮ ሆዱን ያስደስተዋል፤ ሥጋና ቅቤ ቀረብኝ ብሎ እንዳይጠወልግ ተቆጥሮ ብዛቱ የማይታወቅ ዓይነት የጾም ወጥ አለው፤ ስንት ዓይነት የአትክልት ምግብ፣ በዚያ ላይ ሹሮው፣ ክኩ፣ ስልጆው፣ ተልባው፣ ሱፉ፣ የሽምብራ ዓሣው፣ አዚፋው፣ ስንቱ ይቆጠራል!

ጾሙ ያልፍና ፍስኩ ሲመጣ አበሻ ፊቱን ከአትክልት ዓለም ወደእንስሳት ዓለም ያዞራል፤ ከዶሮ ጀምሮ እስከበሬው ኡኡ እያለ ለእርድ ይሰለፋል፤ የዶሮው ወጥ፣ የበጉ ወጥና አልጫው፣ ቅቅሉ፣ ምንቸት አብሹ፣ ክትፎው፣ ጥብሱ፣ ዱለቱ፣ ጥሬ ሥጋው፣ ምኑ ቅጡ!

የአበሻ ምግብ በዚህ ብቻ አይቆምም፤ አንዳንድ አበሻን የማያውቁ ሰዎች አበሻ ፍቅር አያውቅም ይላሉ፤ አበሻ ሌላ ቀርቶ በምግብም ፍቅሩን ይገልጻል፤ የመዝናኛና የፍቅር ምግብም አለ፤ እነቅንጬ፣ እነጨጨብሳ፣ እነግፍልፍል እዚህ ውስጥ የሚመደቡ ናቸው።

አበሻ የመንገድ ምግብም አለው፤ አገልግሉ፣ ቋንጣው፣ በሶው፣ ጭኮው፣ ጭኮው፣ የቡና ቁርስ እያለ ቆሎውን፣ ንፍሮውን፣ በቅቤና በአዋዜ የራሰ ቂጣውን፣ አነባበሮውን፣ አሹቁን ይከሰክሳል፤ አበሻ ከተመቸው መቼ ነው ከመብላት የሚያርፈው? የቱ አገር ነው በዚህ ሁሉ ምግብ ተወዳድሮ አበሻን ማሸነፍ የሚችለው?

Monday, November 4, 2013

ግንቦት 7 አድባር ትከተልህ!

በይሄይስ አእምሮ

ምን ብዬ ከየት እንደምጀምር አላውቅም፡፡ ሁሉም ነገር ተምታትቶብኛል፡፡ መፈጠሬ ራሱም አስጠልቶኛል፡፡

ግንቦት ሰባት ሆይ! እንደሰውም እንደድርጅትም ልብ ብለህ ስማኝ! በቃ፤ በቃ ማለት በቃ ነው፡፡ ከሰሞነኛ አንድ ኢትዮጵያዊ ውርደት በኋላ አቋሜን ሙሉ በሙሉ ለውጫለሁ፡፡ እናም በስሜት ግንቦት ሰባት ሆኛለሁ፤ በተግባርም እሆናለሁ፡፡ ያበጠው ይፈንዳ፡፡ ማንም በኔ አያገባውም፡፡ ግንቦት ሰባት የማይሆንን ተቋምም ይሁን ግለሰብ አወግዛለሁ – የማወግዘው የኔም የቤተሰቤም ውርደት እንዲቀጥል ፈቃደኛ መሆኑን ከመገንዘብ አኳያ ነው፡፡ በወጡ ሳይወጠወጥ የሥልጣን ጥማቸውን የውይይት መድረክ ላይ ፊጥ የሚያደርጉ ዜጎች ከአሁን በኋላ አንደበት የላቸውም፡፡ መድረክ ላይ መደስኮር ሌላ ነው – እኛ ያለንበትን መከራና ስቃይ ማጠየን ደግሞ ሌላ ነው፡፡ ከአሁን በኋላ ግንቦት ሰባትን የሚቃወም የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት እንደሆነ አድርጌ እወስዳለሁ፡፡ አሁን የራሴ እንጂ የማንም አፈቀላጤ አይደለሁም፡፡  ብርሃኑ ነጋን በግል መጥላት ይቻላል፡፡ አንዳርጋቸው ጽጌን በግል መጥላት ይቻላል፡፡ ኤፍሬም ማዴቦን በግል ማጥላት ይቻላል፡፡ ሌሎቹንም የድርጅቱን ሰዎች መጥላትና ሲያጠፉም መገሰጽ ይቻላል፡፡ ግንቦት ሰባት አንግቦት የተነሣውን ዓላማ ማውገዝና መጥላት ግን የወያኔ አባል – ደጋፊ አላልኩም – የወያኔው ቀንደኛ አባል መሆንን በጉልህ የሚያመለክት ነው፡፡ እዬዬም ሲዳላ ነው፤ ዕንባም የሚመጣው ሲመች ነው፡፡ ምርጫም አማራጭ ሲኖር ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ቀልድ አብዝተናል፡፡ በተለይ በስደት ዓለም እየተንፈላሰስን የምንኖር ኢትዮጵያውያን በሕዝብ ቁስል እንጨት ብቻ ሣይሆን ጨውና ሚጥሚጣ እየጨመርን በሚመር ቀልድ መዝናናት ቀጥለናል፡፡ ከአሁን በኋላ ግን የቄሣርን ለቄሣ የእግዜርን ለእግዜር ብለን እንነሳለን፤ አላጋጮችንና አምቧታሪዎችን እናጋልጣለን፡፡ በሕዝብ ስቃይ ደስታን የሚገዙ ሀዘን አምላኪዎችን ዝም ማለት ለተጨማሪ ሰቆቃ ከመዳረግ በስቀር አይጠቅመንምና ዝም አንበላቸው፡፡ የተከፋፈለች መንግሥት አትጸናም፡፡ እውነት ነው፡፡ መከፋፈላችን ከየት ወደየት እንዳመጣን እያየን ነው፡፡ ስለዚህ በረት በጥባጭ ኮርማዎችንና ወይፈኖችን በተቻለ መጠን አውግዘን እንለያቸው፡፡ በሕዝብ ስም የዐዞ ዕንባ ማንባት ሊቀር ይገባዋል፡፡

ማን ነው ግንቦት ሰባትን ማጥላላት የሚቻለው? ግንቦት ሰባት ከሻቢያ ጋር በመሥራቱ አይደለም እንዲህ የተጠመደው? እሰይ! እንኳን ከሻቢያ ጋር የሠራ! እልልልልልልል…..! አሁንም ከሻቢያ ጋር አይደለም ከሰይጣን ከራሱ ጋርም ቢሆን ተደራድሮ ይሥራ! እኔም ባገኘሁት አጋጣሚ ከሰይጣን ጋርም ቢሆን ለመሥራት አሁን ቃል ገባሁ፡፡ እንደኔ በንዴት ሳትንተከተኩ በጥሞና የምለውን ስሙልኝ፡፡ ወያኔ ሁላችንንም ወደጨለማ እያወረደ ወንዱን በወንድ ሴቷን በሴት እስኪደፍር ጠበቅነው፤ የለመኑትን የማይነሣው ወያኔም ይሄውና በጥይት መግደሉን እንደኋላቀርነት ቆጥሮት በቁማችን በሚያሣፍር መሣሪያ ከኋላችን እየገለበ ሊጨርሰን ተያይዟል፡፡ እምናገረው ሃቅና ሃቅ ብቻ ነው፤ የተራ ጉዳይ እንጂ ሁላችንም ተደፍረናል፡፡ በቀደም ዕለት ይህን ዜና ስሰማ በኔ የደረሰ ያህል ነው የተሰማኝም ያለቀስኩትም፡፡ ደግነቱ መጽናናት አለና አሁን መለስ ብሎልኛል እንጂ ወደያውማ ማንም ሊያጽናናኝ አልቻለም ነበር፡፡ ለኔው ነው ያለቀስኩት፤ ለልጆቼ ነው ያለቀስኩት፤ ለሁሉም ምሥኪን ህዝብ ነው ያለቀስኩት፤ ለሀገሬ እዚህ የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረስ ነው ስቅስቅ ብዬ ያለቀስኩት፡፡ ሁላችንም ለፈጣ ከልብ እናልቅስ፡፡

ኢሳይያስ አፈወርቂ በሥልጣንና በኤርትራ ሲመጡበት ጭራቅ ሊሆን ይችላል – ግን ዜጎቹን በግብረሶዶም በቁማቸው የሚገድሉለት የደኅንነት አባላትን አሰልጥኖና ኦሬንቴሽን ሰጥቶ በሙሉ ስንቅና ድርጅት አያሰማራም – በጭራሽ፡፡ ኢሳይያስ አፈወርቂ በአስተዳደር ይትበሃሉ ጭራቅ ሊሆን ይችላል – ግን በዘረኝነት ልክፍት ታውሮ የሚገዛውን ሕዝብ እርስ በርስ አያባላም፤ ኤርትራንም እየሸነሸነ ለባዕድ ዓሣማና ጅቦች አይሸጥም፡፡ የኤርትራ መንግሥት ጨካኘ ሊሆን ይችላል ግን የሀገሪቱን ሕዝብ ባህልና ሃይማኖት ደምስሶ በመላዋ ሀገር ሶዶማዊነትንና ሌዝቢያኒዝምን ባቋቋማቸው የሴኪዩሪቲና የአፈና ተቋማቱ አማካይነት በኃይል ድርጊት አያስፋፋም፡፡ ኢሳይያስ የፈለገውን ያህል ጨካኝ ቢሆን ወያኔ እያደረገው እንዳለው ተቃዋሚዎችን እያፈነ መናገር እንኳን የሚዘገንን ድርጊት አይፈጽባቸውም ነበር፡፡ ስለዚህ አሁን ግንቦት ሰባት ያልሆንኩ መቼም አልሆንም፤ አሁን ኢሳይያስ አፈወርቂን ቢያንስ በሰውነቱና በሰብኣዊነቱ ያልወደደኩ መቼም ልወደው አልችልም፡፡ ፈጣሪን በዚህች ቅጽበት የምለምነው ኢሳይያስ ሳያውቀኝና ሳላውቀው እንዳንሞት ነው፡፡ ይህ ግርዶሽ ተገፍፎ ለአንዲት ቀን እንኳን አዋርቼው የልቤ ቢደርስ ምኞቴ ነው፡፡ የኤርትራ ሕዝብ ከሀገሩ እየወጣ እየተሰደደ ያለው እንደኔ ሻጥረኛ የውጪ መንግሥታትና ተባባሪዎቻቸው ኤርትራ ላይ በፈጠሩት ጫና ምክንያት በተፈጠረ የኢኮኖሚ ድህነት እንጂ የኛን የመሰለ በደልና ግፍ በገዛ መንግሥታቸው ተፈጽሞባቸዋል ብዬ አላምንም፡፡ የኛ ችግር የአምባገነንት ችግር አይደለም፡፡ አምባገነን መንግሥት እኮ አንዳንዴ ለሕዝብ ይጨነቃል፤ ያስባል፡፡ ግፋ ቢል ሥልጣኑን ላለመሻማት ነው መጠንቀቅ የሚኖርብህ፡፡ የወያኔዎች ነገር ከአምባገነንነት በላይ ነው – የምልህ ከገባህ፡፡

ለምለው ሁሉ ምክንያት አለኝ፡፡ ለምን እንዲህ እንደምልም ታውቃላችሁ፡፡ የደላው ሙቅ ያኝካልና ስሜቴ ያልገባው ወይም በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ዜጋ ወይም የወያኔ ደጋፊ የሆነ ሰው ምን ሊለኝ እንደሚችል አውቃለሁ – ለምለው ነገር ሁሉ  ሪስኩን ሁሉ እወስዳለሁ፤ ደግሞም የለመድኩት ነው፡፡

ቀደም በሚል አንድ ወቅት ስለወያኔ እሥረኞችንና ከእሥር ተፈቺዎችን አፍ መሸበብ በተመለከተ በጽሑፍ የተናገርኩት ነገር ነበር፡፡ ሰሞኑን ፈጥጦ የወጣው ያ ነው፡፡ የወያኔ እሥረኛ አያያዝ በየትም ሀገር የለም፡፡ የወያኔ ‹ብላክሜል› በየትም ሀገር ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ አሁን በገሃድ እንዲህ አይነገር እንጂ ወያኔዎች ተስፋ ከቆረጡበት በተለይ ከግንቦት ሰባት 97 ወዲህ ሰዎችን ከተቃውሞ ጎራ ለማስወጣትና እንዳይገቡም ለማድረግ የማያደርጉት ነገር የለም፡፡ በፊትና አሁንም በጥቅም ለመያዝ ይሞክራሉ፡፡ በብዙ መልኩ እሱ እየተሳካላቸው ይመስላል፡፡ የአሁነኛው ግን ከበድ ያለና ኅሊናችን ችሎ የሚሸከመው አይደለም፡፡

ይህ ተግባራቸው ከዕብድም አይጠበቅም፡፡ መግደል ያባት ነው፡፡ መግረፍ ያባት ነው፡፡ በወጉ ማሰቃየት ወግ ነው፡፡ ወፌላላና በዘይት መጠበስ፣ ጥፍር በጉጠት መገንጠል ከደርግ ጀምረውን የለመድነው ነው፡፡ የአሁኑ ግን የመጨረሻቸው ይመስላል የተለዬ ሆኗል፡፡ እባካችሁን ወደሰማይ እንጩህ፤ እባካችሁን ሁላችን ግንቦት ሰባትን በቻልነው ተቀላቅለን ወይም ሌላ መስከረም ሁለትም ይሁን  ሐምሌ 19 የትግል ህምባር መሥርተን ይህን የብዔል ዘቡል መንግሥት እንጣል፡፡ ከዚህ በላይ ምን ያድርጉን? እነሽመልስ ማዘንጊያ እጮኞቻችንን እየቀሙ ነበር የሚያገቡብን፤ እነመላኩ ተፈራ ሚስቶቻችንን እየቀሙ ነበር የሚያገቡብን፣ እነመንግሥቱ ኃይለ ማርያም በሣንጃ ነበር መቀመጫችንን እየወጉ የሚገድሉን፡፡ የአሁኑ እኮ በታሪካችን እጅግ የተለዬ ነው፡፡ እግዚኦ በሉ፤ ወዮ ለመጪው ጊዜ! ዕልቂት ከፊታችን ይታየኛል! ሰማይ ተከፍቶ የመርገምት እሳት በሀገራችን ሲዘንብ ይታየኛል፡፡ አቤት እንበል፡፡

ወያዎች የሚፈጽሙት ግፍ የተለዬ ነው፡፡ እነ እንትና ከእሥር ከተፈታ(ች) በኋላ በስማም እንደተባለበት ሰይጣን እንዲህ ጭጭ ያሉበትን ምክንያት ለመረዳት በግድ መታሠር አያስፈልግም፡፡ ሁሉን እናውቀዋለን፡፡ ይህን መንግሥት ለመጣልና ቢያንስ በሰውነትህ የሚያምን የራስህ የሆነ ጨቋኝ መንግሥት ለማምጣት ደግሞ ሁሉም መታገል ይኖርበታል፡፡ ዴሞክራሲ ለኔ የቧልታይ ድንቃይ ኤዞፓዊ ድራማ ነው፡፡ መሥሪያ ቤቴ ውዬ በደህንነት ጋንጎች ተጠልፌ አይሆኑ ሆኜ ራሴን ሆስፒታል የማገኝባት ሀገር ካለችኝ ጥንቅር ትበል ወይም ሀገር እንዲኖረኝ መታገል ነው የሚኖርብኝ፡፡ ዴሞክራሲው፣ ምርጫው፣ ቢሮክራሲው ፣ የኑሮ ውድነቱ፣ አስተዳደራዊ በደሉ፣ ቅጥ ያጣው ዘረኝነቱ፣  ፍትህ ማጣቱ… ይሄ ይሄ ቀልድ ነው አሁን፡፡ ስለነዚህ አንስቶ ለመወያየት መጀመሪያ ሰው መሆኔ መታወቅ አለበት፡፡ ሰው መሆኔ ብቻም አይደለም፡፡ እንስሳ መሆኔም መታወቅ አለበት፡፡ አሁን ከሰውም፣ ከእንስሳም፣ ከግዑዝም ነገሮች በታች ነኝ፡፡ እኔ በኢትዮጵያ ምድር ምንድነኝ? ሰው እንዳልሆንኩ እኔም አውቃለሁ – እናስ ምን ነኝ ልበል? የፋሲካው በግ በገናው በግ እንደሳቀ ጀምበር ትጥለቅብን ወገኖቼ? የት ሄደ ያ ኢትዮጵያዊ ወኔና ጀግንነት? ወይንስ የሚወራው ሁሉ የውሸት ነበር ማለት ነው? ምንድነው የምንሰማውና የምናየው ሁሉ?

“ኧረ እኔስ ጨነቀኝ”

ሰውየው ያገባት ሚስቱ ቤተሰቦቿ ሃብታሞች ነበሩ። እሱ ደግሞ መናጢ የሚባል ደሃ ነበር። አንድ ቀን የማይቀረው ሞት የሚስቱን አባት ነጠቀና ቀብር ወጡ። አስከሬን እየተከተሉ ሲያለቅሱ ባል ሚስቱ ጎን ሆኖ ልክ እንደሷ “አባቴ አባቴ” በማለት ያለቅስ ጀመር። ሚስትም ” የት የወለደህን ነው አባቴ የምትለው” በማለት አፍታ ወስዳ ባሏን ገሰጸችው።

ባል ለቅሶውን ቀየረና “አባቷ፣ አባቷ …” በማለት ያስነካው ጀመር። ይህን ጊዜ ሚስት አሁንም ለቅሶዋን ቆም አድርጋ “የበላኸው ጨማ፣ የጠጣኸው ጠጅ አያንቅህም? አባቷ አባቷ የምትለው” አለችው። ባልም ደንግጦ ላፍታ ዝም በማለት ካሰበ በኋላ “አረ እኔስ ጨነቀኝ፣ አረ እኔስ ጨነቀኝ … ” በማለት እያለቀሰ የባለቤቱን አባት ሸኘ። ይህ አጠር ተደርጎ የቀረበ የቀድሞ ምሳሌ ነው።

ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ይወዳሉ። አገራቸውን በልጅ፣ በሚስት፣ በእናት፣ በአባት፣ በቤተሰብ … እየሰየሙ አንጎራጉረዋል። ተቀኝተዋል። ተደርሰዋል። ፎክረዋል። አቅራርተዋል። በዚህች አገራቸው ጉዳይ ለሚመጣ ማናቸውም ችግር “ቀልድ የለም” በማለት ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ተፋልመዋል። ወድቀዋል። ባንዲራቸውን ከፍ አድርገው ዘምረዋል።

በአንድ ወቅት ተፈጥሯል ተብሎ ከተመሰከረልን “የባንዳነት ገድል” ውጪ፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን ጠላት ሲመጣብን፣ ወራሪ ሃይል ሲያድምብን፣ አገራችንን ሊደፍሩ የሚቃጣቸው ሲነሱብን መተባበርና አንድ መሆን ልዩ ባህላችን ነው። የምንኮራበት ስጦታችንም ነው። ጠላትን ለመመከት በተደረገ ጥሪ በገዢዎቹ አኩርፎ “ወዲያ በሉ” የሚል ትውልድ አገራችን አላበቀለችም። ጠላትን ደቁሶና አሳፍሮ የሚመልስ ትውልድ እንጂ!!

ህወሃት እመራዋለሁ የሚለውን ህዝብና አገር ወደ ጎን በማለት ከሻዕቢያ ጋር ፍቅር ተጣብቶ በቀልን በዘራበት ወቅት፣ ኢትዮጵያን የሚወዱ ዜጎችን በጠላትነት እየፈረጀ ሲወነጅል፣ የብሔር መርዝ እየዘራ አብሮ የኖረ ህዝብ ሲያጋጭ፣ አገርን ዘርፎ ለዘራፊ አሳልፎ ሲሰጥና የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የህዝብ ሃብት ላይ ለጠቅላይ ሲጫወት፣ “ያገባናል” በማለት ለአገራቸው የሚከራከሩትን በጠራራ ጸሐይ ሲገል፣ ሲያስርና ሲያንገላታ ቆይቶ ራሱ በፈጠረው ችግር ህጻናትን በጀት ሲያስቆላ “ዞር በል” ያለው አልነበረም። ይልቁኑም ከዳር እስከዳር በመነሳት በባድመ ጦርነት ፈንጂ ላይ በመሮጥ አገርንና ህዝብን የሚያኮራ ገድል ለመፈጸም ተችሏል።

Saturday, November 2, 2013

ደብረማርቆ ዩኒቨርስቲ ዉስጥ ለተነሳዉ አመጽ የዩኒቨርሲቲዉ አስተዳደር ኢሳትን መኮነኑ ተሰማ!

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ አዲስ ያወጣዉን ፀረ ህዝብ መመሪያ ተከትሎ የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የአለባበስ ፤ የአመጋገብና የአምልኮ ስርዓት ህግ ማውጣቱን በመቃወም የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች የረሃብ አድማ መጀመራቸዉን የዩኒቨርሲቲዉ አስተዳደር ገለጸ። ከዚህ በተጨማሪ አዲስ ከወጣዉ መመሪያ ዉጭ ዩኒቨርሲቲዉ ለተማሪዎች የመደበዉ የምግብ ፍጆታ መጠን እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነዉ በሚል የተማረሩት የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች አመጽ መጀመራቸዉን የዩኒቨርሲቲዉ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ መናገራቸዉ ታዉቋል። ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ ከዚሁ ጋር አያይዘዉ እንደተናገሩት ተማሪዎቹን ቁርስ፣ ምሳና እራት ለመመገብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተፈቀደው የቀን በጀት 12 ብር ብቻ ነዉ ካሉ በኋላ በደብረ ማርቆስ ከተማ 12 ብር ከአንድ ሻይና ዳቦ በላይ መግዛት እንደማይችል ተናግረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ኢሳት ቴሌቪዥን ያናገራቸዉ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች ደብረ ማርቆስ ዉስጥ ለአንድ ተማሪ በቀን 12 ብር ለምግብ መመደብ ተማሪዎችን በረሃብ ለመጨረስ ከመሞከር ተለይቶ አይታይም ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲዉን ተማሪዎች ጥያቄ ትክክለኛነት ያረጋገጡት የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ ከመንግስት ፈቃድ ውጭ በሚልየን የሚቆጠር የበጀት ድጎማ እያደረግን ተማሪዎችን ለመመገብ ጥረት አድረገናል ብለዋል። ይህንን ሀቅ ሳይደብቁ የተናገሩትና የተማሪዎቸን ችገር በሚገባ የተረዱት ዶ/ር ንጉሴ የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ዉስጥ የተነሳዉ የተማሪዎች አመጽ ምክንያቱ አሰገዳጅ ህጉና የምግብ ማነስ ሳይሆን ኢሳትና ሌሎች ሃይሎች ያደራጁት አመጽ ነዉ ብለዉ መናገራቸዉ ብዙዎችን አስገርሟል።ይሀንን የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ኢሳት ላይ የሰነዘሩትን ክስ የሰማ አንድ የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪ አመጽ፤ ተቃዉሞና ህዝባዊ እምቢተኝነት ኢትዮጵያ ዉስጥ በየቦታዉ የሚታይ ከስተት መሆኑ እየታወቀ ፕሬዚዳንታኢን የደብረማርቆሱን አመጽ በኢሳት ላይ ማሳበባቸዉ የሚያሳየን የአዋቂ አላዋቂነትን ነዉ ብሏል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ የተቀሰቀሰዉ አመጽ በስድስት ህንጻዎችና በሶስት የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ አምቡላንሶችን ላይ ከፍተኛ አጉዳት ማድረሱ የታወቀ ሲሆን አመጹን ለመቆጣጠር የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ በተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጽሟል፡፡ ዬዩኒቨርስቲው መሪዎች የአካባቢው ነዋሪዎች ለዩኒቨርሲቲዉ አመጽ ድጋፍ ሰጥተዋል የሚል ስሞታ ያሰሙ ሲሆን ነዋሪዎች በበኩላቸው ተማሪዎች እየራባቸው ሲወድቁ በዝምታ አለመመልከት የዜግነት ግዴታችን ነዉና እርደታ ለመስጠት ተገድደናል ብለዋል።