Tuesday, November 4, 2014

የእንግሊዝ መንግስት ለጉጅሌው ወያኔ አገዛዝ ይሰጥ የነበረውን የ 27 ሚሊዮን ፓውንድ እርዳታ መሰረዙ ታወቀ

የእንግሊዝ መንግስት ከግብር ከፋዮች የሚሰበሰብውን ገንዘብ በንጹሃን ኢትዮጵያውያን ላይ መጠነ ሰፊ ኢ ሰብአዊ ድርጊትን እየፈጸመ ላለው ለፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ መለገሱ ተገቢ አይደለም ሲሉ በአገሪቱ ያሉ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቶችና የህግ አካላት ከፍተኛ የተቃውሞ ዘመቻ መክፈታቸውን ተከትሎ አገሪቱ ለጉጅሌው አገዛዙ ትሰጥ የነበረውን እርዳታ ለማቆም እየተገደደች መሆኗዋን ለማወቅ ተችሏል። የተቃውሞ ዘመቻውን ተከትሎ የእንግሊዝ አለማቀፍ የትብብር ተቋም ለጉጅሌዎቹ ሹማምንትና ቅጥረኛ ካድሬዎች ከ 70 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ወጭ በማድረግ በደህንነት ዙሪያ የሚሰጠውን ልዮ የማስተርስ ዲግሪ ስልጠና ማቋረጡን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን በዚህ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ደግሞ እንግሊዝ ለጉጅሌው ወያኔ አገዛዝ የፖሊስ አባላት ማጠናከሪያ የምትለግሰውን ድጎማ ማቋረጧን ቴሌግራፍ የተባለው የአገሪቱ ታላቅ ጋዜጣ ዘግቧል። ጉጅሌዎቹ በአገሪቱ እያደረሱት ያለው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ለእርዳታው መቋረጥ አብይ ምክንያት መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን የእንግሊዝ መንግስት ለፖሊስ አባላት ማጠናከሪያ በሚል ሲሰጥ የነበረው እርዳታ 27 ሚሊዮን ፓውንድ እንደነበርም በጋዜጣው ተመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጉጅሌው ወያኔ አገዛዙ በግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ በሆኑት በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የፈጸመው የውንብድና ተግባርን ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችንና ማስቆጣቱ የሚታወቅ ሲሆን በተለይ መቀመጫቸውን በእንግሊዝ ያደረጉት የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፤ የህግ አካላትና የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የእንግሊዝ መንግስት ለፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ እየሰጠ ያለውን ድጋፍ በአስቸኳይ እንዲያጤን የሚጠይቅ የተጠናከረ ዘመቻ ለመክፈታቸው አብይ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል። ድርጅቶቹ በቅንጅት በእንግሊዝ መንግስት ላይ እሳደሩት ያለው የተቃውሞ ዘመቻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተመለከተ ሲሆን እንግሊዝ ከዜጎቿ የምትሰበሰበውን የግብር ገንዘብ ኢትዮጵያውያንን እየገደለ፤ እያሰረና እያሰደደ እንዲሁም በኢትዮጵያውያን ላይ ኢ ሰብአዊ ድርጊት እየፈጸመ ላለው ፋሽስታዊ አገዛዝ ፈጽሞ መስጠት እንደሌለባት አበክረው እየጠየቁ እንደሚገኙ በእንግሊዝ የሚታሙ የተለያዩ ጋዜጦች መዘገባቸውን ለማወቅ ተችሏል።


በጉዳዩን ዙሪያ አስተያየታቸውን እየሰነዘሩ የሚገኙት የተለያዩ የፖለቲካ አራማጆች እንደተናገሩት በእንግሊዝ አገር የሚገኙ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ የህግ አካላት እንዲሁም እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በጥምረት የጀመሩት ለፋሺስታዊው አገዛዝ የሚሰጡ እርዳታዎችን በመቃወም የማሰረዝ ዘመቻን በማወደሰ የእንግሊዝ መንግስት ከጭቁኑ የኢትዮጵያውያ ህዝብ ጎን በመሰለፍ እየወሰደ ያለውን የእርዳታ ስረዛ እርምጃ ጥሩ ጅማሮ መሆኑን አመልክተዋል። በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በእንግሊዝ መንግስት እየታየ ያለው አበረታች ለውጥ ከዚህም ከፍ ወዳለ ደረጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤ እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት በንቅናቄያችን ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እስኪገባና አመርቂ ውጤት እስኪገኝ ድረስ እንደ ከዚህ ቀደም ሁሉ እየተደረገ ያለውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ደረጃውን በማሳደግ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ተናግረዋል። የእንግሊዝ መንግስት ባለፉት 3 አመታት ብቻ ከ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ ለጉጅሌው ወያኔ አገዛዝ መስጠቱ ይታወቃል።

በተያያዘ ዜና መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው አምንስቲ ኢንተርናሽናል የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ጉዳዮ በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና መንግስታት እንዲሁም እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ጭምር ሰፊ መነጋገሪያ ሆኖ መቀጠሉን ዴሊ ሜል የተባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ አስነብቧል።

No comments:

Post a Comment