Saturday, April 12, 2014

ወ/ሮ አስቴር ማሞን ሹመት አገኙ

ወያኔ መልምሎ ያቀረበለትን የደካማ ግለሰቦች ሹመት ፓርላማ እየወሰደ አጽድቁልኝ ከማለት ሌላ ይህ ነዉ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ስልጣን የሌላዉ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በያዝነዉ ሳምንት ማብቂያ አካባቢ የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበርና የጽ/ቤት ኃላፊ የነበረችዉን ወ/ሮ አስቴር ማሞን በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር እንድትሆን ያቀረበዉን ሹመት ፓርላማው ተቀብሎ አጽድቋል።

የኦህዴድ ሊቀመንበርና የክልሉ ፕሬዚደንት ከነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ሞት በኃላ ኦህዴድ ባደረገው የሥልጣን ሽግሽግ አቶ ሙክታር ከድር ከምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ተነስቶ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት ሆኖ መሾሙ የሚታወስ ሲሆን ወ/ሮ አስቴር ማሞ ደግሞ በአቶ ሙክታር እግር ተተክታለች።

ወ/ሮ አስቴር ማሞ በጰጉሜ ወር 2002 ዓ.ም በተካሄደው የኦህዴድ ጉባዔ ከድርጅቱ ሥራ አስፈጻ ኮምቴ አባልነት አሰናብቷት የነበረ ሲሆን በመጋቢት ወር 2005 ዓ.ም የተካሄደው የኦህዴድ ጉባዔ አባዱላ ገመዳን፣ ኩማ ደመቅሳንና፣ግርማ ብሩን ከፓርቲው ሥራ አስፈጻሚነት ሲያሰናብት የወያኔ ታማኝ ሎሌ መሆኗ የሚነገርላት ወ/ሮ አስቴር እንደገና መመረጧ የሚዘነጋ አይደለም። የአቶ አለማየሁ አቶምሳን ሞት ተከትሎ በቅርቡ ፓርቲው ባደረገው ሽግሽግ አስቴር ማሞ ከኦህዴድ ጽ/ቤት ኃላፊነቷ በተጨማሪ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንት ሆና ተሹማለች።

No comments:

Post a Comment