Saturday, April 12, 2014

የወያኔ ፖሊሶች ከ20 በላይ የቦዲ ብሄረሰብ ተወላጆችን መግደላቸዉ ተሰማ

ነብሰ ገዳዮቹ የወያኔ ጸጥታ ኃይሎች በቅርቡ በቦዲና በኮንሶ ብሄረሰቦች መካከል የተከሰተዉን ግጭት እናበርዳለን በሚል ሰበብ በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ ከሃያ በላይ የቦዲ ብሄረሰብ ተወላጆችን ሳይገድሉ እንደልቀረ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኝ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ አስታወቀ። የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ምክትል ሊቀመንበርና የዞኑ ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ መኮንን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በቦዴዎችና በኮንሶች መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የፌደራል ልዩ ሃይል በወሰደው እርምጃ ወደ 29 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለድርጅታቸው ሪፖርት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የሟቾችን ስም ዝርዝር በማጠናቀር ላይ ሲሆኑ ሰሞኑን ይፋ እንደሚያደርጉም ምክትል ሊቀመንበሩ ተናግረዋል ሆስፒታል ሄደው የቆሰሉትን ሰዎች መጎብኘታቸውና ማነጋገራቸውን የሚናገሩት አቶ አለማየሁ ፣ ከሁለቱ በስተቀር ሌሎች ወደ 6 የሚጠጉ ሰዎች በፌደራል ፖሊስ ጥይት መቁሰላቸውን እንደገለጹላቸው ተናግረዋል።



ምንም እንኳ የግጭቱ መነሻ መንግስት ካሰፈራቸው የኮንሶ ተወላጆች ጋር የተያያዘ ቢመስልም፣ ቦዴዎች ለሸንኮራ ገዳ ተክል በሚል ከአካባቢያቸውን እንዲነሱ መደረጉ የፈጠረባቸው ስሜት የችግሩ ዋነኛ መነሻ መሆኑን ገልጸዋል። ቦዴዎች ዘላኖች በመሆናቸው ለዛፎች ልዩ እንክብካቤ እንደሚያደርጉ የገለጹት ባለስልጣኑ፣ በእርሻ ስራ የሚተዳደሩት ሰፋሪ ኮንሶዎች ወደ አካባቢያቸው በመግባት ዛፎችን እየቆረጡ የእርሻ ማሳ ሲያስፋፉ ሲመለከቱና ለሸንኮራ ልማት በሚል ቀያቸውን እንዲለቁ ሲገደዱ የፈጠረባቸው ቁጭት ደም አፋሳሽ ወደ ሆነ ግችት ተቀይሯል።ምንም እንኳ በሁለቱ ጎሳዎች መካከል የተነሳው ግጭት በፌደራል ፖሊስ የሃይል እርምጃ ቢቆምም፣ ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን አቶ አለማየሁ ገልጸዋል። እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ፖሊስ አሁንም ድረስ በአካባቢው ይገኛል።

No comments:

Post a Comment