UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
-------------------------------------------------------
ቁጥር አንድነት /801/2ዐዐ6
ቀን 01/ዐ5/2ዐዐ6 ዓም
-------------------------------------------
ለኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌዥዥን ድርጅት
አዲስ አበባ
-------------------------------------------
ጉዳዩ፡- በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌ,ቭዥን ድርጅት የተላለፈ ዘገባን ይመለከታል
-------------------------------------------
የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት በአዋጅ የተቋቋመና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ አገልግሎት እንዲሰጥ ኃላፊነት ያለበት የመገናኛ ብዙሃን መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ድርጅታችሁ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጋር በመተባበር ‹‹ሽብርተኝነት በኢትዮጵያ የአሸባሪ ድርጅቶች አሰያየምና ማንነት›› በሚል ርዕስ ታህሣሥ 15፣18ና 25 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በተላለፈው ዘገባ ላይ፡-
1. ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር የሚሰራ ፓርቲ እንደሆነ የሚያስመስል ዘገባ መተላለፉ፡፡
2. በሕግ አውጭው አካል ባልተፈረጀ ወይም በሕግ ተጠያቂ ያልሆነን ተቀማጭነቱን በውጭ ያደረገውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ጣቢያን እያጣቀሱና የፓርቲያችን አመራሮች የሰጧቸውን መግለጫዎችና ቃለ-ምልልሶችን ጭምር በመጠቀም እንዲሁም ምስሎቻቸውን እያቀረቡ የተሳሳተ መረጃ ለሕብረተሰቡ ተሰራጭቷል፡፡
በመሆኑም ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በሕጋዊ መንገድ ተቋቁሞ በሠላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ያለ መሆኑ እየታወቀ አሁን እየተላለፈ ያለው ነገር ከፓርቲያችን ዓላማና ፕሮግራም ውጭ ብቻ ሳይሆን ሕገ ወጥ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ፓርቲያችን ይህ አይነቱ ድርጊት እንዲቆምና ለተላፈውም ፕሮግራም ሚዛናዊነት የኛም ሃሳብ ተደምጦ በፕሮግራማችሁ እንዲቀርብ እንዲደረገግ እየጠየቅን ለወደፊቱም ፓርቲያችንን የሚመለከቱ ዘገባዎች ሲሰራጩ የኛም ሃሳብ እንዲስተናገድና ሚዛናዊነትን በጠበቀ መልኩ እንዲተላለፍ እንጠይቃለን፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ሃሳባችንን የመግለጽ ሕገ-መንግሥታዊ መብታችንን ለመገደብ የሚደረጉ ማናቸውንም እንቀስቃሴ አስመልክቶ ጉዳዩን ወደ ፍ/ቤት የምንወስደው መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ከሠላምታ ጋር
ግዛቸው ሽፈራው (ኢ/ር)
ፕሬዚደንት
No comments:
Post a Comment