በቅዱስ ዮሃንስ
ወያኔ ሥልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በአሰቦት ገዳም መነኮሳትና በአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ የደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋና እንዲሁም በአርባምንጭ ከተማ የኦርቶዶክስና የፕሮቴስታንት አማኞችን በማጋጨት የፈሰሰው ደም ፣ በጂማና በኢሊባቦር በስልጤና በጋሙጎፋ ክርስቲያኖችና አብያተክርስቲያናት ላይ የደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋ በዓይን ላየው ሁሉ መፈጠሩን የሚጠላበት ክስተት ነው::
በዚሁ በጅማ ባለፈው ዓምት አካባቢ ከ40 በላይ የፕሮተስታንት ቤተክርስቲያኖች እና ንብረቶች ወድመዋል:: በአጠቃላይ ይህ መንግሥት ሙስሊሙ ከኦርቶዶክሱ ኦርቶዶክሱ ከፕሮቴስታንቱ ተፋቅሮና ተቻችሎ እንዳይኖር አንዱን በአንዱን ላይ እያነሳሳ የሃይማኖት አቋማት ሲቃጠሉ ዳር ቆሞ እሳት መሞቅ የሚፈልግ መንግሥት ነው::
የሃይማኖት ተቋማት አልጋጭ ሲሉትም እርስ በእርሳቸው ማለትም ኦርቶዶክሱን ከኦርቶዶክስ ፣ ፕሮቴስታንቱን ከፕሮቴስታንቱ ፣ ሙስሊሙን ከሙስሊሙ እያተራመሰ የሃይማኖት ተቋማት ሰላም እንዳያገኙ እያደረገ ይገኛል:: ከዚህም አልፎ ተርፎ ከ1500 ዘመን በላይ ተከብሮ የቆየውን የዋልድባን ገዳም እያፈረሰ በውስጡ የሚኖሩ መነኮሳትንም እያሳደደ ይገኛል:: በዚህ ገዳም ብዙ አባቶች ከዓለማዊ ፍላጎትና ከእህል ተቆጥበው ቅጠላቅጠልና ፍራፍሬ ብቻ እየተመገቡ ቤት ሳይኖራቸው በዋሻና በዛፍ ሥር ተጠልለው ሰለ አገር ብቻ ሳይሆን ስለ መላው ዓለም የሚጸልዩ አባቶች ያሉበት ገዳም ነው:: በከተማ የደሀ ጎጆ እያፈረሰ በገዳም የአባቶችን ዋሻ እያረሰ መነኮሳቱን እያሳደደ በእጁ የገቡትን አስሮ እያሰቃየና እየገደለ ይገኛል:: ገዳማትንም ያለ ቅርስ ትውልዱን ያለውርስ እያስቀረ ነው::
ስለዚህ ውድ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ሆይ! ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ በኢትዮጵያ ውስጥ ታሪክም ቅርስም ሕዝብም ሃይማኖትም ተሟጥተው ያልቃሉና የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ እንደ ሶቬት ይሆናልና ለሕዝብህ ፣ ለወገንህና ለሀገርህ ስትል ወገብህን አጥልቀህ ተነስ። የሃገራችንን ጥፋት በጋራ እንመክት። አሜን!
No comments:
Post a Comment