ሃገራችን ኢትዮጵያን ነገስታት መርተዋታል፤ ወታደራዊ አምባገነኖች ጨፍረዉባታል፤ ዛሬ ደግሞ ዘረኛ አምባገነኖች ቁም ስቅሏን እያሳዩዋት ነዉ። እቺን ለአስተዋይ መሪዎች ያልታደለች የአስተዋዮች አገር ዛሬ አለም የሚያዉቃት በድህነት፤ በረሀብና በስደት ነዉ። ድህነት፤ ረሀብና ኋላ ቀርነት ኢትዮጵያ ላይ የተደቀኑ ታላላቅ አደጋዎች ቢሆኑም ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያን ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈራት ድህነትና ረሀብ ሳይሆን በግድ የተጫነባት የጋንግሪኑ የወያኔ አገዛዝ ነዉ። ይህ የጥፋት ቡድን በወሮበላዎች የተመሰረተ፡ ሃገራችንን እያቆረቆዘ ያለ አገዛዝ መሆኑ በግልፅ በሃያ ሶስት አመት የስልጣን ጉዞው አስመስክሯል። ህወሃት ወያኔን ከመሰረቱ ወሮበላ የጥፋት አምባሳደሮች አንዱና ዋነኛው ደግሞ ቆሪጡ በረከት ስምኦን ነው።
በረከት ስምኦን የኢትዮጵያን ትልቅነት የሚያቀልሉና የኢትዮጵያን ህዝብ ማንነት የሚያሳንሱ አያሌ አጥንት የሚሰብሩ ንግግሮች ያደረገ እብሪተኛ ቱልቱላ ነዉ። በረከት እዉነትን ከዉሸት፤ ቁምነገርን ከቧልት አገርን ያክል ትልቅ ነገርና የቤቱን ጓዳ ለይቶ ማየት የማይችል እንኳን ለአገር ስልጣን ለዕቁብ ዳኝነትም የማይመኙት ከሃዲ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም እሱና የደደቢት ጓደኞቹ አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ የስልጣን መያዣ መለኪያዉ ብስለትና አስተዋይነት ሳይሆን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መጥላትና ማጥላላት በመሆኑ በረከት ስምኦን ዛሬም ድረስ እንደጨበጠ የያዘዉን ስልጣን ለመያዝ ችሏል። ከሰሞኑ ስራ ፈቱ የዲያቢሎስ ቁራጭ በረከት ስምኦን ለአገዛዙን ወሮበላ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የወያኔ ቅጥረኛ አስፈፃሚዎች በተዘጋጀው የምርጫ ተብየ ውይይትና ግምገማ ላይ ባደረገዉ ንግግር የኢትዮጵያ አርሶ አደር እስካሁን በተደረገለት ስራ በሚገባ የረካ ስለሆነ ” መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ውጣ ቢለው ይወጣል፣ መንግስት ተኛ ቢለው ይተኛል፣ ግፍ ብንፈጽም አንኳን አርሶ አደሩ ይህንን መንግስት ይሸከመዋል እንጂ ምንም አይለውም፣ በማለት ሃያ አመት ሙሉ መሬቱን ተቀምቶ በተገፋዉ የኢትዮጵያ አርሶ አደር ላይ አላገጠ። ቃለመጠይቅ መስጠትና አለመስጠት የራሱ ጉዳይ ነዉ። ሆኖም ቃለመጠይቁ በከፍተኛ የችግር አረንቋ ተመትቶ እየማቀቀ የሚገኘውን የሃገሬን ገበሬ ወገኔ መወረፉ ህመም ስለሆነብኝ ማርከሻ ይሆነዋል በሚል የዚህን እብሪተኛ ሰዉ ቃለመጠይቅ በዚህ ጽሁፌ ለመዳሰስ እሞክራለሁ። ለነገሩ ጉጅሌ ወያኔዎች ከአለቃቸው ከሟቹ ቱልቱላ መለስ ጀምሮ መላ ግብርአበሮቻቸው ለአነጋገራቸው ደንታ የሌላቸው፤ የሚያስቡት እንደጤናማ ሰው በጭንቅላት ሣይሆን እንደ አውሬ በጡንቻ መሆኑን ነፃነትን ናፋቂው ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡
ዛሬ በወሮበላው የወያኔ አገዛዝ ምክንያት የገበሬው ኑሮም መዝቀጡ እጅግ ያስለቅሳል፡፡ ገበሬው በቀን አንድ ጊዜም የሚቀምሰው በሌለበት ሁኔታ፣ ገበሬው ከገጠር እየፈለሰ ወደከተሞች በመግባት የጐዳና ተዳዳሪ እየሆነ ባለበት ሁኔታ፣ ገበሬው በማዳበሪያ ዕዳ የስንግ ተይዞ ኤሎሄ እያለ በሚገኝበት ሁኔታ፣ ገበሬው በአድሎኣዊ የመሬት ሥሪት ምክንያት መድሎ እየተሠራበት ማለፊያው የውሃ መሬት ለካድሬዎችና ለወያኔዎች እየተሰጠ ጭንጫውና መናኛው መሬት ግን ለድሃ ገበሬ እየተሸነሸነ ባለበት ሁኔታ፣ ገበሬው ከማሳውና ከመኖሪያው እየተፈናቀለ መሬቱ በልማት ስም ለወያኔ ከበርቴዎች እየተቃረጠ ባለበት ሁኔታ፣ ጨርቁ በላዩ ላይ አልቆ በባዶ እግሩ እየሄደ በእሾህና በእንቅፋት አሣሩን እንዲበላ ተፈርዶበት ባለበት ሁኔታ፣ … ይህ የሰው ነቀርሳ በረከት ተብየ የተናገረውን መስማት ከህመም በላይ ትልቅ ህመም ነው። ይህ የሰይጣን አምላኪ ወፍዘራሽ የመርገምት ልጅ በህዝብ መሳለቅና ሃገርን ማውደም እንደሚያረካው በተደጋጋሚ አይተናል፡፡
ለነገሩ ብሶቱን ችሎ፣ የሚደርስበትን ግፍና መከራ ተቋቁሞ በሞትና በሕይወት መካከል በሚኖር ገበሬ ላይ ቡዋልት እየሠሩ መሣለቅ ሊያስከትል እንደሚችለው ጦስ ለበረከትም ሆነ ለባልጩት ራስ ግብረ አበሮቹ አልገባቸውም፡፡ ይህ መሪር ቀልድ ዛሬ ለሱ በትእቢት ስለተወጠረ ምንም ላይመስለ ይችላል፡፡ ይሁንና እያንዳንዷ የህዝብ ግፍና እምባ ትልቅ ዋጋ ሳታስከፍል እንዲሁ የምትቀር እንዳልሆነች ይህ የቀን ጅብ ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡

ለዛሬ በዚሁ ይብቃኝ!
ድል ለጭቁኑ የሃገሬ ገበሬ ይሁን!
No comments:
Post a Comment