Wednesday, October 14, 2015

በባህርዳር፤ በጎንደር እና በአጎራባች ከተማ ወጣቶች ኮርተናል!

በቅዱስ ዮሃንስ

በባህርዳር፤ በጎንደር እና በአጎራባች ከተማ ወጣቶች ኮርተናል! የፍርሀት ግድግዳን ደረማምሰዋልና!

ይህ አኩሪ የነፃነት ትግል አድማሱን አስፍቶ በሌሎችም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል!

ሰሞኑን የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ በባህርዳር፤ በጎንደር እና በአጎራባች ከተሞች የትግል ጥሪ ወረቀቶችን ለህዝብ በመበተን ሰፊ ስራ ሰርቷል። ስራዎች የተሰሩት ደግሞ እዚያው በሚኖሩ ነፃነት ናፋቂ የንቅናቄው አባላትና ደጋፊ ወጣቶች ነው። ድንቅ ስራ! አዎ! ይህ በሕወሓት አገዛዝ የተንገፈገፉት የአካባቢው ወጣቶች የነፃነት ትግሉን በአደራ ለመቀበላቸው አብይ ማረጋገጫ ነው። ይህ አኩሪ የትግል ንቅናቄ በሌሎቹም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ዘንድ በምሳሌነት ተወስዶ፤ አድማሱን አስፍቶ መቀጠል ይኖርበታል። እኛ ወጣቶች ሀገራችን በሕወሓት አገዛዝ ከተጋረጠባት እልቂትና የመፈራረስ አደጋ የማዳን ታሪካዊ አደራ አለብን! ሀገራችንን ማንም የወጭ ሀይል ደርሶ ከመበታተን አያድንልንም። ነፃነታችንንም እንዲሁ ማንም ሌላ አካል ደርሶ ሊያጎናጽፈን ፈጽሞ አይችልም። የሁሉም ነገር መፍትሄው በእጃችን ነው! አዎ! የሕወሓት አገዛዝ ለኢትዮጵያ የማይበጅ አጥፊ ስርዓት መሆኑን አውቀን በፅናት ለመታገል መወሰን! ከዚያ በየ አካባቢያችን መደራጀት፤ ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ተጨባጭ ትግል ማድረግ መጀመር። አለቀ!! ለአብነትም ከሰሞኑ በባህርዳር፤ በጎንደር እና በአጎራባች ከተማ በሚኖሩ ወጣቶች እየተደረገ ያለውን ሰፊ ንቅናቄ መመልከት በቂ ነው። ይሄን ስናደርግ ብቻ ካሰብነው የነፃነት ዓለም በቶሎ እንደርሳለን። ሀገራችንንም ከተደቀነባት የመበታተን አደጋ እናድናታለን።

አዎ! ከሰሜን፤ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለን ወጣቶች በዘር በሀይማኖትና በጎሳ ሳንከፋፈል በአንድነት በመነቃነቅ በአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦ ከዳር ለማድረስ የሞት ሽረት ትግል ማድረግ አለብን። ሰዓቱ ደግሞ አሁን ነው!! ተነሱ!!! ሁላችንም እንነሳ!!!

በአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የተጀመረው የነፃነት ትግል በኢትዮጵያ ወጣቶች ፊታውራሪነት ከዳር ይደርሳል!!

ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ወደ ፊት!!

No comments:

Post a Comment